cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

Central Ethiopia Regional Health Bureau

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ 🔵 https://m.facebook.com/centralethiopiarhb 📞 📩

Show more
Advertising posts
3 549
Subscribers
+524 hours
+387 days
+11630 days

Data loading in progress...

Subscriber growth rate

Data loading in progress...

“ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቀነስ የቅደመወሊድ ክትትሎችን መጨመር እና የጤና ተቋማትን ማዘመን ያስፈልጋል “ - የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ የእናቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጤና የእቅድ አፈፃፀም “ፈጠራዎችን መተግበር እና ማዝለቅ ለላቀ የእናቶች፣ የህጻናት እና ወጣቶች ጤና “ በሚል መሪ ቃል በአርባ ምንጭ ከተማ እየተገመገመ ይገኛል። የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ መድረኩን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመቀነስ የቅደመወልድ ክትትሎችን መጨመር እና የጤና ተቋማትን ማዘመን እንደሚያስፈልግ ገልፀዉ በየደረጃዉ ያለዉ አመራር፣ ጤና በለሙያና የሚመለከተዉ ባለድርሻ አካላት ሁሉ በቅንጅት መስራት አለበት ብለዋል። በጤና አገልግሎት ተደራሽነት እና ጥራት ላይ የሚስተዋሉ ልዩነቶችን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ የተናገሩት ዶ/ር መቅደስ መሻገር ያልተቻሉ ተግዳሮቶችን በምርምር እና በፈጠራ በመታገዝ ወደሚፈለገው ደረጃ ማድረስ መሰረታዊ ትኩረት መሆን እንዳለበት አስረድተዋል። በአፈጻፀም ግምገማ መድረኩም የተገኙ ዉጤቶችንና ቀሪ ተግባራትን በመለየት በቀጣይነት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ተጨማሪ ጥረት የሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በትብብር የመስራት ሁኔታን ወደ ላቀ ደረጃ እንዲያደርሱ ዶ/ር መቅደስ ጥሪ አቅርበዋል። የእናቶች፣ የህጻናትና ጤና እንድሻሻል ያለመታከት እየሰሩ ያሉትን የጤና ባለሙያዎች በየደረጃዉ ያሉ አመራሮች እንድሁም ድጋፍ እያደረጉ ያሉ አጋር ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አመስግነዋል። እናቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ከህዝባችን ቁጥር ከፍተኛውን ቦታ የሚይዙ በመሆኑ በእነዚህ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ መስራት እና አለመስራት በቤተሰብ ደረጃም ሆነ እንደ አገር የሚያስከትለው ተጽዕኖ ከፍተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ገልፀዋል። ያልተዳረሱ ክትባቶችን ለማዳረስ በዘመቻ መልክ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት ዶ/ር ደረጀ የጨቅላ ህጻናት ሞት ቁጥር መሻሻል ቢያሳይም በቀጣይ ተጨማሪ ጥረቶች መደረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል። የመረጃ ጥራት በሚፈለገው ደረጃ ላይ አለመድረሱን የተናገሩት ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ አንዳንድ አገልግሎቶች በተለይ የቤተሰብ እቅድ አገልግሎት አፈጻፀም በክልሎች መካከል የማይጠበቅ ልዩነት በመኖሩ ጉዳዩ በመድረኩ የውይይት ትኩረት መሆን አለበት ብለዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸዉ እንደተናገሩት በጤናው ዘርፍ እየተደረገ ያለው ዘርፈ ብዙ ርብርብ በርካታ ተጨባጭ ለውጦችን ያስገኘ ቢሆንም በክልሉ የጨቅላ ህጻናት ሞትን ለመቀነስ፣ የድህረ ወሊድ የእናቶች አገልግሎትን ለማሻሻል እና ክትባት ለማዳረስ ተጨማሪ የባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ እንቅስቃሴ ይጠይቃል ብለዋል። የአፍላ ወጣቶች እና ወጣቶች ጤና ካውንስል ኃላፊ ወጣት ቶፊቅ እስማኤል ሀኪም እና የበጎ ፈቃድ አምባሳደር አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ በመድረኩ ላይ መልዕክት አስተላልፈዋል። የህጻናትና ጨቅላ ሕፃናት ጤና ዙሪያ የተዘጋጁ አራት ሰነዶችም በመድረኩ ላይ ይፋ ተደርገዋል። በግምገማ መድረኩ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከሁሉም ክልል እና ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮዎች፣ ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች እና ከሙያ ማህበራት እየተሳተፉበት ይገኛሉ። ምንጭ የፌዴራል ጤና ሚኒስተር የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
Show all...
👍 3
የጽዱ ጤና ተቋም ኢኒሺዬቲቭ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ተጀመረ ___ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ይፋ ተደርጎ የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጵያ አካል የሆነው የጽዱ ጤና ተቋም፣ ጽዱ አከባቢ ኢኒሺዬቲቭ በሀገር አቀፍ ደረጃ በአዲስ አበባ የተጀመረ ሲሆን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባና የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጃ ዱጉማን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራል እና የክልል የጤና ዘርፍ ሀላፊዎች በተገኙበት በዛሬዉ እለት በይፋ ተጀምሯል፡፡ በፌዴራል ደረጃ የተጀመረው ኢኒሺዬቲቭ ወደ ሁሉም ክልሎች ፣ ዞኖችና ወረዳዎች መስፋት አለበት ያሉት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ፅዱ አካባቢ እና ጤና ተቋም በዋናነት በጤናው ዘርፍ ሊተገበር የሚገባው ኢኒሺዬቲቭ መሆኑን ገልጸዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ እንዳሻው ሽብሩ በበኩላቸው ፅዱ ኢትዮጵያ_ፅዱ ጤና ተቋም ኢኒሺዬቲቭ ለጤና ዘርፍ መልካም አጋጣሚ መሆኑን ጠቁመው በአብዛኛው የህፃናትና ጨቅላ ሕፃናት ህመምና ሞት በንፅህና ችግር የሚመጣ በመሆኑ ትልቅ መፍትሔ ይዞ የተጀመረ ኢኒሺዬቲቭ መሆኑን አብራርተዋል። በተጨማሪም በአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል ያለው የተኝቶ ህክምና ፍላጎት ካለው መሠረተ ልማት ጋር የተመጣጠነ አለመሆኑን የገለፁት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ የህብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት የሚያስችል በ41 ሚሊዮን ብር በጀት በ8 ወራት ውስጥ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት የሚሆን የተኝቶ ህክምና መስጫ ማስፋፊያ ህንፃ ግንባታ የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በዶክተር መቅደስ የተመሩጡ የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ ሀላፊዎች የተለያዩ ዋርዶችንም ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። ጉብኝታቸውን ቀጥለውም በቅርቡ ተጠናቆ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀውን የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ኮምፕሪሄንሲቭ ሪፈራል ሆስፒታል እንዲሁም በታዋቂው የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር አመኑ አዳሙ ስም የተሰየመውን ዶክተር አመኑ መታሰቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግንበታ የደረሰበትን ደረጃ ጎብኝተዋል። በቀጣይ መሰራት ባለባቸው ስራዎች ዙሪያም ተወያይተዋል።
Show all...
1
የኢኖቬሸን መመሪያ ትግበራ፣ ውጤታማ የጤና አመራር፣ የጤና ስርዓት ማነቆ ላይ መሠረት ያደረገ የአክርድቴሽን ማስተዋወቂያ መድረክ በመካሄድ ላይ ነው። የማእከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ የህክምና አገ/ት ዳይሬክቶሬት የ9 ወራት አፈጻጸም ግምገማ እና የኢኖቬሸን መመሪያ ትግበራ፣ ውጤታማ የጤና አመራር፣ የጤና ስርዓት ማነቆ ላይ መሠረት ያደረገ የአክርድቴሽን ማስተዋወቂያ መድረክ በቡታጅራ ከተማ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል። የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል መንግስት ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሽመልስ ዋንጎሮ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ለማሻሻል ስታንደርዶች መመሪያዎችና ኢኒሼቲቮችን በየጊዜው የፌዴራል ጤና ሚኒስተር እያዘጋጀ ወደ ክልሎች ያወረደ መሆኑን በማመላከት የህብረተሰቡን የጤና ተጠቃሚነት ማሻሻል ያስችል ዘንድ የክልሉ ጤና ቢሮ የወረዱ መመሪያዎችንና ኢኒሼቲቮችን በቁርጠኝነት እየተገበረ መሆኑን ገልጸዋል። በክልሉ በጤና ተቋማት የሚሰጠውን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት ለማሳደግ ተግባራትን በኢኖቬሽን በማዘመን ከተለመደው አሰራር በመውጣት ወቅቱን የሚመጥን ስራ ማከናወን እንደሚገባ የጠቆሙት አቶ ሽመልስ የኢኖቬሽን መመሪያ ትግበራን በየደረጃው ያሉ ባለድርሻ አካላት በሀላፊነትና በቁርጠኝነት ሊፈጽሙ እና ክትትል ሊያደርጉ እንደሚገባ ተናግረዋል። የጤናውን ሴክተር ተግባር ውጤታማ ለማድረግ በየደረጃው ያሉ አመራሮች ሚና የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ፋይዳው የጎላ እንደሆነ የገለጹት ሀላፊው ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር የጤናው ሴክተር ተግባር በሚፈለገው ልክ ውጤት እንዳያመጣ ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት በዘላቂነት ለመፍታት የጤና ስርዓት ማነቆዎች ላይ መሠረት ያደረገ ሪፎርም በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ሁሉም መሪ ሆስፒታሎች ተግባራዊ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል። አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊና የህክምና አገ/ቶች ዘርፍ ሀላፊ በበኩላቸው የጤናው ሴክተር አገ/ት አሰጣጥ ስርዓት ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለመፍታት በክልላችን የሚገኙ ሆስፒታሎች ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና እንዲያገኙ የረዥም ጊዜ ዕቅድ ተዘጋጅቶ የሚተገበረውን የአክርድቴሽን ፍኖተ ካርታ ሰራ በማሳለጥ ክልሉን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ለሚሰራው ስራ መሠረት የሚጣል መሆኑን አስገንዝበዋል። እንደ ክልል አክርዴት የሆኑ ተቋማት እንዲኖሩ ለማድረግ ዝርዝር ዕቅድ በማዘጋጀት ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ወደ ትግበራ መግባት እንደሚገባ ያመላከቱት አቶ ሳሙኤል የጤና አገ/ት ሰጪ ተቋማትን አክርዴት ለማስደረግና ክልሉን የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የክልሉ መንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን በመጠቆም በየደረጃው ያሉ አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት እንዲሰጡ ጠይቀዋል። የማ/ኢት/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
Show all...
Go to the archive of posts