en
Feedback
የቅዱስ ጳውሎስ ሕክምና ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ

የቅዱስ ጳውሎስ ሕክምና ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ

Open in Telegram

‹‹የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ፤ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› 📚ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ

Show more
1 106
Subscribers
+124 hours
+167 days
+5430 days
Posts Archive
እንኳን ለፈታሔ ማህፀንና ፈዋሴ ድውያን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ መታሰቢያ፣ ለኢትዮጵያዊው ቅዱስ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!                         ሠናይ ዕለተ ሰሉስ St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/EttrHKuh8yhd89KYb 📌 ጷጒሜን 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ርኅወተ ሰማይ (የሰማይ መከፈት) 2.ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት 3.ቅዱስ መልከ ጼዴቅ ካህን 4.አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ንጉሥ (የእመቤታችን ወዳጅ) 5.ቅዱስ ሰራጵዮን ዘሰንዱን 6.ቅዱስ አኖሬዎስ 7.ቅዱስ ቴዎፍሎስ 8.አባ ዮሐንስ 9.ቅዱስ ጦቢት 10.ቅዱሳን ጦብያና ሣራ   📌 ወርኀዊ በዓላት 1. በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ 2. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3. ቅዱሳን ሊቃነ ካህናት አበው (ዘካርያስና ስምዖን) 4. አባ ሊባኖስ ዘመጣዕ 5. አቡነ ዜና ማርቆስ 6. አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ዘደብረ በንኮል 7. ቅዱስ ቄርሎስ ሊቅ (ዓምደ ሃይማኖት)           ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

በዛሬው የሰኞ ፀሎት መርሃግብራችን ላይ መምህራችን በቤተክርስትያናችን የመሐረነ አብ ፀሎት ያለውን ቦታ እንዲሁም በአምልኮ እና በምስጋና ሥርዓታችን ውስጥ ዜማ ለምን እንዳስፈለገ አካትተው ያስተማሩት ትምህርት እነሆ✨

መርሐግብሩ የሰኞ ጸሎት አዳራሽ ውስጥ ነው።

ሰኞ ጸሎት መርሐግብር የጋራ መዝሙር🔔
አማኑኤል ተመስገን✨ አማን በአማን/፬/ አማኑኤል ተመስገን /፪./ ለዚህ ፍቅርህ ምን ልክፈልህ /፪./ ❴አዝ❵        ድብቁን ኃጢአት አንተ ብትገልጸው ይቅር ብለኸኝ ባትሸፋፍነው እንደ ሰው በቀል ቢኖር ጌታ ለኔ ኃጢአትስ የለውም ቦታ በየደቂቃው ኃጢአት ስሰራ ስሰርቅ ስበድል አንተን ሳልፈራ አንተ ግን ፊትህ ምንም ቢቀየም በቁጣህ በትር አልገረፍከኝም ምህረትህን ልከህ አድነኝ ዛሬ ታክቶኛልና በኃጢአት መኖሬ አለም በኃጢአት እየሳበችኝ በጽድቅ ደስታ መኖር አቃተኝ የኃጢአት ጉዞ ጣፋጭ ቢመስልም ውጤቱ መሮ ፍጹም አይጥምም እንደ በደሌ ስላልከፈልከኝ ተመስገን እንጂ ሌላ ምን አለኝ ✨ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን

እንኳን ለታጋሹ ጻድቅ አባታችን ቅዱስ ኢዮብ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ከ72ቱ አርድእት መካከል ለሆነው የቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙር ሐዋርያው ቅዱስ ቲቶ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!                        ሠናይ ዕለተ ሰኑይ St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/Cps5mkU51HmAbDpgY 📌 ጷጕሜን 2 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ቲቶ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)   📌 ወርኀዊ በዓላት 1. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት 2. ቅዱስ ኢዮብ ጻድቅ ተአጋሲ 3. ቅዱስ አቤል ጻድቅ 4. ቅዱስ አባ ጳውሊ ገዳማዊ (ታላቁ) 5. ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንጾኪያ 6. አባ ሕርያቆስ ዘሃገረ ብሕንሳ 7. ቅዱስ ታዴዎስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)                    ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

✨ነገ✨ ትምህርት ከዲ/ን በረከት ንጉሴ ጋር በጊዜ እንገናኝ😊
✨ነገ✨ ትምህርት ከዲ/ን በረከት ንጉሴ ጋር በጊዜ እንገናኝ😊

እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለልደቷ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ረድ ለነበረው ለሐዋርያው ቅዱስ ዑቲኮስ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!              ሠናይ ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/v3CX6OXAe66Vv5cOO 📌 ዻጒሜን 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (የታሠረበት) 2.ቅዱስ ዑቲኮስ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት) 3.ቅዱስ ብሶይ ቀሲስ (ሰማዕት) 4.አባ ዻኩሚስ / ባኹም (የ3,000 ቅዱሳን አባት) 5.አባ ሰራብዮን / ሰራፕዮን (የ10,000 ቅዱሳን አባት)   📌 ወርኀዊ በዓላት 1. ልደታ ለማርያም ድንግል እግዝእትነ 2. ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና 3. ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላዕክት 4. ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 5. ቅዱስ ሚልኪ ትሩፈ ምግባር                 ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

🔔🔔ተንስኡ ለጸሎት🔔🔔 እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች? ነገ ጠዋት የምንችል ሁላችን ተሰብስበን በጠዋት 10:50 ቅዳሴ እንሂድ። መቀስቀስ የምትፈልጉ ልጆች @bes21a ፣ 0908950
🔔🔔ተንስኡ ለጸሎት🔔🔔 እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች? ነገ ጠዋት የምንችል ሁላችን ተሰብስበን በጠዋት 10:50 ቅዳሴ እንሂድ። መቀስቀስ የምትፈልጉ ልጆች @bes21a ፣ 0908950042 አናግሩን። የምንሄድ ተማሪዎች የዐውደ ምሕረት መርሐግብር ከ3:30 በፊት ካለቀ፤ በሰላም ግቡ እንደተባለ በላይኛው በር በኩል ወጥተን በጋራ እንመለሳለን። የዐውደ ምሕረት መርሐግብር ካልተጠናቀቀ ግን ካፌ መግባት የምትፈልጉ 3:30 ላይ በላይኛው በር በኩል ተሰብስበን ወደ ግቢ መጥተን በጋራ ወደ ካፌ እንገባለን። መልካም አዳር!

እንኳን ለመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለነቢዩ ቅዱስ ሚልክያስ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!                     ሠናይ ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/xpxqhP0DmXxbH9Vat 📌 ነሐሴ 30 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ እንድርያስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ ሚልክያስ ነቢይ 3.አባ ሙሴ ዘሃገረ ፈርማ   📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ ማርቆስ ዘአንበሳ (ሐዋርያ) 2.አባ ሣሉሲ ክቡር 3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ነባቤ መለኮት 4.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት 5.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቀ መለኮት                 ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለአቡነ አትናቴዎስ እና ለአገልጋዮቹ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!                       ሠናይ ዕለተ ዓርብ St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/1WXrAByb1JqqeVbLK 📌 ነሐሴ 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አባ ዮሐንስ ሐጺር (ፍልሠቱ) 2.ቅዱስ አትናቴዎስ ሰማዕት 3.ቅዱሳን ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ (ሰማዕታት) 4.አባ ባስልዮስ ጻድቅ (ዘትግራይ)   📌 ወርኀዊ በዓላት 1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት 2.ቅድስት አርሴማ ድንግል 3.ቅዱስ ጴጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት 4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ 5.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት 6.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት) 7. ቅዱስ ላሊበላ                ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን ጌቶች አሉ ብለን ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን እሜቴ አሉ ብለን እህቶች እህቶች ደረሰ ጊዜያችን አበባየሆሽ ልንል በተራችን ግቢ ጉባኤንም ልናግዝ በአቅማችን 🌼ከጷጉሜ 2
ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን ጌቶች አሉ ብለን ደስ ብሎን መጣን ደስ ብሎን እሜቴ አሉ ብለን
እህቶች እህቶች ደረሰ ጊዜያችን አበባየሆሽ ልንል በተራችን ግቢ ጉባኤንም ልናግዝ በአቅማችን 🌼ከጷጉሜ 2 - 4 ለግቢ ጉባዔያችን ልብሰ ስብሐት መግዣ እንዲሆን በታሰበ የአበባየሆሽ ዝማሬ ገቢ ማሰባሰብያ ላይ እንገናኝ🌼 ሁላችንም እህቶች ለ @nuamiii ስማችንን ልከን በጋራ ተሰብስበን እንዘምር😊

እንኳን ለቸሩ አምላካችን ለቅዱስ አማኑኤል ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለቅዱሳን አባቶቻችን አብርሃም፣ ይስሐቅ እና ያዕቆብ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!                    ሠናይ  ዕለተ ሐሙስ St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/m15Ca1UU7ouOMrQEC 📌 ነሐሴ 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ አብርሃም (የአባቶች አለቃ) 2.ቅዱስ ይስሐቅ (የአባቶች አለቃ) 3.ቅዱስ ያዕቆብ (የአባቶች አለቃ) 4. አባ በርሳቦ ሰማእት እና ማህበሩ 📌 ወርኀዊ በዓላት  1. አማኑኤል ቸር አምላካችን  2. ቅድስት ዓመተ ክርስቶስ  3. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ  4. ቅዱሳን እንድራኒቆስና አትናስያ                ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

ትላንት የነበረን የጋራ ጸሎት እና መዝሙር መርሐግብር በፎቶ እግዚአብሔር አምላክ ቀጣዩን ዓመት ይባርክልን፤ በፍቅርና በትሕትና የምናገለግልበት ዓመት ያድርግልን። በቸር አቆይቶ ለንሴብሖ መርሃግብራችን
+5
ትላንት የነበረን የጋራ ጸሎት እና መዝሙር መርሐግብር በፎቶ እግዚአብሔር አምላክ ቀጣዩን ዓመት ይባርክልን፤ በፍቅርና በትሕትና የምናገለግልበት ዓመት ያድርግልን። በቸር አቆይቶ ለንሴብሖ መርሃግብራችን በሰላም ያድርሰን! የዓመት ሰው ይበለን!

እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለታላቁ ኢትዮጵያዊ ቅዱስ አቡነ ዘርዐ ብሩክ የልደት በዓል፣ ከ7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ለሆነው ለቅዱስ ሱርያል ዓመታዊ ክብረ በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!                      ሠናይ ዕለተ ረቡዕ St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/bd40OR7XFrueOJVcS 📌 ነሐሴ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1."12ቱ" ደቂቀ ያዕቆብ (እሥራኤል) 2.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ (የተጠራበት) 3.ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላእክት 4.ቅዱስ ብንያሚንና እህቱ አውዶከስያ (ሰማዕታት) 5.ቅዱስ ፊቅጦርና እናቱ ሣራ 6.አባ ባስልዮስ ፓትርያርክ ዘኢትዮዽያ (የተሾሙበት)   📌 ወርሐዊ በዓላት 1.መድኃኔዓለም 2.አቡነ መብአጽዮን               ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

✨ሰላም የእግዚአብሔር ቤተሰቦች✨ በመጪው መስከረም የሙሉ አባላት ስልጠና ተዘጋጅቶልናል። ለዚህም ከታቀዱት ርዕሶች ውስጥ ስልጠናው እንዲሰጥበት የሚፈልጉትን ርዕስ ይምረጡ። ✍ማሳሰቢያ: ስልጠናው ተሳታፊዎችን ያማከለ እንዲሆን ስልጠናው ላይ መገኘት የምንችል አባላት ብቻ ምርጫው ላይ እንድንሳተፍ በአክብሮት እንጠይቃለን🙏

እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለቅዱሳን ሰማእታት አባ ሞይሰስ እና እህቱ ሳራ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!                     ሠናይ ዕለተ ሰሉስ St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://telegra.ph/St-Paul-Gbi-Gubae-09-01 📌 ነሐሴ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ብጽዕት ሣራ (የአብርሃም ሚስት) 2.ቅዱሳን አባ ሞይስስና እህቱ ሣራ (ሰማዕታት) 3.ቅዱሳን አጋቦስና ቴክላ (ሰማዕታት)  4.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ 5.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ 📌 ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 2.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን 3.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን                    ዝርዝሩን ለማንበብ 👇

ይህን መርሐግብር ታስታውሱታላችሁ😊? ✨ ይህ ባለፈው ዓመት በመዝሙርና ኪነ ጥበባት ክፍል ተዘጋጅቶ የነበረ ልዩ የጋራ ጸሎት ምሽት መርሐግብር ነበረ። እነሆ አሁንም ሦስተኛ ጊዜ ልክ እንደባለፈው ጊዜ
+4
ይህን መርሐግብር ታስታውሱታላችሁ😊? ✨ ይህ ባለፈው ዓመት በመዝሙርና ኪነ ጥበባት ክፍል  ተዘጋጅቶ የነበረ ልዩ የጋራ ጸሎት ምሽት መርሐግብር  ነበረ። እነሆ አሁንም ሦስተኛ ጊዜ ልክ እንደባለፈው ጊዜ በዓመቱ ለነበረን የአገልግሎት ጊዜ እግዚአብሔር ይመስገን፣ ቸር አምላካችን እንዲሁ እንዳለን ጠብቆን በሰላም ለቀጣዩ ዓመት ያድርሰን ብለን ልንጸልይና ልናመሰግን ይህን የጸሎት መርሃ ግብር አዘጋጀን። 🕛 ዛሬ ከ 12:00 ጀምሮ በመገኘት የዚህ የጸሎትና የዝማሬ ማዕድ ተካፋይ እንድትሆኑ በእግዚአብሔር ስም ጋበዝናችሁ።

እግዚአብሔርን ፈልጉት.m4a42.83 MB

የዛሬው የሰኞ ፀሎት መርሃግብራችን ይህን ይመስል ነበር✨ በመርሃግብሩም መምህራችን "ወጣትነት" በሚል ርዕስ ላይ በመነሳት ከክርስቶስ ጋር ስለመኖር እና ክርስቶስን በልባችን ስለመሻት፣ በሁሉም ነገር
+1
የዛሬው የሰኞ ፀሎት መርሃግብራችን ይህን ይመስል ነበር✨ በመርሃግብሩም መምህራችን "ወጣትነት" በሚል ርዕስ ላይ በመነሳት ከክርስቶስ ጋር ስለመኖር እና ክርስቶስን በልባችን ስለመሻት፣ በሁሉም ነገር ውስጥ እርሱን ስለመፈለግ አስተምረውናል✨ ትምህርቱን ከታች ያገኛሉ፤ እንዴት እና ለምን የሚሉት ጥያቄወችን ይመልሳል ብዙም ትጠቀሙበታላቹና ትንሽ ጊዜ ሰጥታችሁ አድምጡት👇✨ መልካም አዳር✨