የቅዱስ ጳውሎስ ሕክምና ኮሌጅ ግቢ ጉባኤ
前往频道在 Telegram
‹‹የቤተክርስቲያን ሕይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ፤ ስለዚህ ከግል ሕይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ›› 📚ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
显示更多1 038
订阅者
+324 小时
+187 天
+5830 天
帖子存档
እንኳን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለሰማዕቱ ቅዱስ አሞን የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ሠናይ ዕለተ ሰኑይ
St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/Qk7wtA9F1IfSIE0bp
📌 ሐምሌ 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ ሴት ነቢይ (ወልደ አዳም)
2. ቅዱስ ሕዝቅኤል ነቢይ
3. ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ቅዳሴ ቤቱ)
4. ቅዱስ አሞን ሰማዕት
5. ቅድስ መስቀል ክብራ (የቅዱስ ላሊበላ ባለቤት)
📌 ወርኀዊ በዓላት
1. የጌታችንና አምላካችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በዓለ ስቅለት
2. አቡነ መብዐ ጽዮን ጻድቅ
3. ቅዱስ መቃርስ (የመነኮሳት ሁሉ አለቃ)
4. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
5. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
6. ቅዱስ ቢፋሞን ጻድቅና ሰማዕት
7. ማር ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
ዝርዝሩን ለማንበብ 👇
እንደምን አላችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች
እንደምታውቁት ግቢ ጉባዔአችን በአዲስ ዓመት እና በደብረ ታቦር በዓላት ላይ ለልብሰ ስብሐት ማሰፊያ የሚሆን የገቢ ማሰባሰቢያ ዝማሬ ያዘጋጃል። የደብረታቦር በዓልን ልናከብር ቀናት ቀርተውታል። እናም በቡሄ በሉ ዝማሬ መሳተፍ የምትፈልጉ ወንድሞች @caladrius_s አሳውቁን።
🔔 የሰኞ ጸሎት የመግቢያ መዝሙር🔔መድኃኔዓለም ክርስቶስ መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል(፪) በለኒ መሀርኩከ (ወንድሞኖች) በለኒ መሀርኩኪ (እህቶች) በእንተ ማርያም ድንግል እስመ ሔር አልቦ እንበሌከ ቃል ትርጉም፦ በቀራንዮ ላይ የተሰቀልክ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሆይ ስለ ድንግል ማርያም ብለህ ይቅር አልኩህ በለኝ ካለ አንተ ይቅር ባይ የለምና
ካጋጠመኝ ላካፍላችሁ
💛ጌታችን ስለሰጠን ልዩ ስጦታ ስለ ቅዱስ ቁርባን ለመናገር ቃላት ያንሰኛል። እግዚአብሔር ፈቅዶ መቀበል ከጀመርኩኝ ጀምሮም በብዙ ተለውጫለሁ።
💛የመጀመሪያ ጊዜ ልቀበል ሳስብ የንስሃ አባቴ “እነዚህን ነገሮች አስተካክይ ከዛ ትቀበያለሽ” ብለውኝ ነበር። ያዘዙኝንም ነገሮች ካስተካከልኩ በኋላ “በቃ ዝግጁ ነኝ፤ አሁን ከተዘጋጀሁ ከዚህ በኋላም ሁሌ ዝግጁ ነኝ” ብዬ አሰብኩ። ህይወቴም ሙሉ ለሙሉ የሚለወጥ ድጋሜም ወደ ቀድሞ ኃጢያቴ የማልመለስ መስሎኝ ነበር።
💛ከተቀበልኩ በኋላ ግን በጣም ደነገጥኩ፤ እራሴንም ስመለከት I was the same.. እንደውም አዲስ አይነት መውደቅንም እየወደቅኩ ነበር። “ቆርቤ የለም እንዴ?” እያልኩ አሰብኩ።
💛ለኔ መቁረብ ወደኋላ መመለስ የሌለው መስሎኝ ነበር።
💛ነገር ግን ከንስሃ አባቴ ምክር እንዲሁም ከጊዜ ሂደት የተረዳሁት የክርስትና ህይወት ሁሌም መውደቅ መነሳት ያለው ነው። ቅዱስ ቁርባንም አንድ ጊዜ ዝግጁ በመሆን ሳይሆን በመውደቅ እና በመነሳት የምንኖረው ነው። አንድ ሰው ስለቆረበ ብቻ ሁሉን ኃጢያት ይተዋል፤ ህይወቱ ሙሉ ለሙሉ ይለወጣል ማለት አይደለም።
💛እኔ ኃጢያተኛ ነኝ የሚል ሰው ሁሉ ይቁረብ። ለኃጢያቱ ስርየት ታዲያ ሌላ ከየት ይገኛል? ኃጢያቱንስ የሚያሸንፍበት ኃይል ከየት ያገኛል?
💛እኔም በተቀበልኩ ቁጥር አንድ እርምጃ ኃጢያቴን ለመተው ወደ እግዚአብሔር እንደቀረብኩ ይሰማኛል።
ከእህታችን❤️
6⃣ ቀን ቀረው።
✨ነሐሴ 2 - የምስጢር ቀን በፍልሰታ✨
✨ከነሐሴ 1 እስከ 16✨
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ግሩፓችንን ይቀላቀሉ 👇
https://t.me/StPaulGGBibleStudy
እንኳን ለጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም ወርሃዊ መታሰቢያ፣ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጠባቂ ለመሆን ለተመረጠው ለአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ እና የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳሳት ለሆኑት ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ሠናይ ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያን ቅድስት
St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://telegra.ph/St-Paul-Gbi-Gubae-08-01-2
📌 ሐምሌ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
2. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ (የድንግል ማርያም ጠባቂ)
3. ቅዱስ አባ ጢሞቴዎስ (ዘአልቦ ጥሪት)
4. አባ ሮዲስ
📌 ወርሐዊ በዓላት
1. ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2. አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3. አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4. ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
ዝርዝሩን ለማንበብ 👇
🔔🔔ተንስኡ ለጸሎት🔔🔔
እንደምን ዋላችሁ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች?
ነገ ጠዋት የምንችል ሁላችን ተሰብስበን በጠዋት 10:50 ቅዳሴ እንሂድ። መቀስቀስ የምትፈልጉ ልጆች @bes21a ፣ 0908950042 አናግሩን።
የምንሄድ ተማሪዎች የዐውደ ምሕረት መርሐግብር ከ3:30 በፊት ካለቀ፤ በሰላም ግቡ እንደተባለ በላይኛው በር በኩል ወጥተን በጋራ እንመለሳለን። የዐውደ ምሕረት መርሐግብር ካልተጠናቀቀ ግን ካፌ መግባት የምትፈልጉ 3:30 ላይ በላይኛው በር በኩል ተሰብስበን ወደ ግቢ መጥተን በጋራ ወደ ካፌ እንገባለን።
መልካም አዳር!
እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ መርቆሬዎስ ቅዳሴ ቤት፣ ለኢትዮጵያዊው ቅዱስ አቡነ ሕፃን ሞዐ እና ለሰማዕቱ ቅዱስ አበከረዙን የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ሠናይ ዕለተ ቀዳሚት ሰንበት
St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/hI7aM4vcR2Q2cRPkz
📌 ሐምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1. ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2. ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3. ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4. ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5. ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6. ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7. ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8. ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9. አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10. አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11. "25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)
📌 ወርሐዊ በዓላት
1. ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2. አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3. ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
ዝርዝሩን ለማንበብ 👇
እንኳን ለጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና ለቅድስት ክርስቶስ ሰምራ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አባ ዘዮሐንስ እና ለሰማዕቱ ቅዱስ አባ ኖብ የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
ሠናይ ዕለተ ዓርብ
St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/s40b7zcNbpkgDARdd
📌 ሐምሌ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮዽያዊ)
2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት
3."190,000" ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማሕበር)
4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ
5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮዽያዊ)
6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ዻዻሳት
7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ
📌 ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮዽያዊ)
ዝርዝሩን ለማንበብ 👇
በዕብራውይን 13: 14 ላይ ባለው ሀይለቃል ላይ በመነሳት የተማርነው ትምህርተ ወንጌል እነሆ✨
በዚህ የምትኖር ከተማ የለችንምና ነገር ግን ትመጣ ዘንድ ያላትን እንፈልጋለን።
+3
ከትናንት በፊት የነበረው በPC2 ወንድም እህቶቻችን የተዘጋጀው የእመቤታችን ፅዋ ይህን ይመስል ነበር✨
ከእመቤታችን ረድኤት እና በረከት ሁላችንንም ያሳትፈን፣ ፅዋውን ያዘጋጁልንን እህት እና ወንድሞቻችንንም አንድነታቸውን ይባርክልን የነፍስ ዋጋ ያርግልን: በቤቱ ያቆያችሁ
✨✨✨
እንኳን ለሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለሰማዕቷ ቅድስት መሪና እና ለቅዱስ ለንጊኖስ ሐዋርያና ሰማዕት የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ሠናይ ዕለተ ሐሙስ
St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/YNdza2X7wnmKMqC84
📌 ሐምሌ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት መሪና እናታችን (ታላቁዋ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ለንጊኖስ ሐራ (ሐዋርያና ሰማዕት)
3.ቅዱስ አብጥልማዎስ
📌 ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል
ዝርዝሩን ለማንበብ 👇
እንኳን ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል ወርሃዊ መታሰቢያ፣ ለኢትዮጵያዊው ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ እና ለሰማዕቱ ቅዱስ መቃርስ (የፋሲለደስ ልጅ) የእረፍት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ሠናይ ዕለተ ረቡዕ
St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/40COQFGUZUgl4uWbH
📌 ሐምሌ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት (ኢትዮዽያዊ)
2.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት (የፋሲለደስ ልጅ)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ (ክቡር ሰማዕት)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት (ቅዳሴ ቤታቸው)
5.ቅዱስ መርካሎስ
📌 ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ ጳውሊ የዋህ
ዝርዝሩን ለማንበብ 👇
✨የምስጢር ቀን በፍልሰታ✨
እግዚአብሔር ፈቅዶ በጋራ ከምስጢራት የምንሳተፍበት በጉጉት የምንጠብቀው የምስጢር ቀን ከ2 ሳምንት ያነሰ ጊዜ ቀርቶታል። ንስሐ ያልገባን እየገባን የገባን ቀኖናችንን እየፈጸምን እንቆይ።
✨ነሐሴ 2 እንገናኝ!✨
በተለያየ ምክንያት በዛ ቀን ከምስጢረ ቁርባን መሳተፍ ለማትችሉ በሳምንቱ ነሐሴ 9 በድጋሚ ስለሚዘጋጅ @Femana ላይ አሳውቁን።
እግዚአብሔር የዛ ሰው ይበለን!🙏
እንኳን ለወላዲተ አምላክ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን።
ዛሬ በ PC2 ወንድም እኅቶቻችን የተዘጋጀ ጽዋ ስላለ ሁላችንም ከያለንበት ተሰባስበን በደ/መ/ቅ/ሚ/ቤ/ክ 12፡00 ላይ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንሁን።
የእመቤታችን ምልጃና ጸሎት አይለየን!
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለመልአኩ ቅዱስ ዑራኤል መታሰቢያ፣ ለኢትዮጵያዊው ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ የልደት በዓል እንዲሁም ለሌሎች ቅዱሳን መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!
ሠናይ ዕለተ ሰሉስ
St. Paul Gbi Gubae – Telegraph https://share.google/BC7WkI3KQ2XGjYXDb
📌 ሐምሌ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
3.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)
4.ቅዱስ ላዕከ ማርያም ሔር (ኢትዮዽያዊ)
5.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ኢትዮዽያዊ) ልደታቸው
6.ብጹዕ አወ ክርስቶስና ሚስቱ (ጻድቃን)
7.ቅዱስ ሱስንዮስ ጻድቅ8.ቅዱስ ዮራኖስ መኮንን (የ100 አለቃው)
📌 ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ
4.አባ አሮን ሶርያዊ
5.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
ዝርዝሩን ለማንበብ 👇
