en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe 👈

አዲስ ምልከታ🌍

አዲስ ምልከታ🌍

Open in Telegram

+ አዲስ የሳይንስ እይታ + አዲስ አስተሳሰብ + አዲስ እውቀት + ሃይማኖት + ፖለቲካ + ኢኮኖሚ + ሙዚቃ # የኢትዮጵያ ትንሳኤ

Show more
2 886
Subscribers
No data24 hours
+87 days
+4430 days
Posts Archive
📝 🇪🇹 🇪🇷 What began as a civil war has become a regional conflict as Eritrean forces cross into Tigray. The implications
📝 🇪🇹 🇪🇷 What began as a civil war has become a regional conflict as Eritrean forces cross into Tigray. The implications for the Horn of Africa are significant and complex https://acleddata.com/country/ethiopia 📎 Martin Plaut

ታዲያ እነዚህ የራስ ቅላቸው ሾጠጥ ያሉ ሰዎች ወደኋላ ሾጠጥ ያለ ራሳቸውን ለመሸከም የሚያስችላቸው የአንገት አጥንታቸው ከኛ የአንገት አጥንት መለየቱ ነው። ይኽም የሆነበት መንገድ እኛ ካለን የአንገት አጥንቶች ተጨማሪ አጥንት ያላቸው መሆኑ ነው። ይህንንም ሲታይ ቁመታቸው ከሰዎች ቁመት የሚበልጥ መሆኑን ያሳያል። በተጨማሪም እነዚህ ሰዎች ቀያይ ጸጉር ያላቸው መሆኑ ሌላ ፍንጭ ነው። በዓለም ቀይ ጸጉር እጅግ በትንሽ ቁጥር የሚገኝ ሲሆን፣ ያንን ቀይ ጸጉር ያላቸው ሰዎች 1-2 በመቶ የሚሆነው የዓለም ህዝብ ነው። ይህ በዓለም በጣም በትንሹ የሚገኝ መገለጫም፣ በነዚህ የራስ ቅላቸው ሾጠጥ ያሉ ሰዎች ላይ መገኘቱ ጥያቄን የሚያጭር ነው።

በዚህ ጥቁር ባህር ስፍራ ዙርያ በቁፋሮ የተገኙ ብዙ ለየት ያሉ አጽሞች አሉ። እነዚህም አጽሞች ከሺዎች ዓመታት በፊት የተገኙ ሲሆኑ ለየት ያለው መገለጫቸው የራስ ቅላቸው ወደ ኋላ ረዘም (ሾጠጥ) ያለ
በዚህ ጥቁር ባህር ስፍራ ዙርያ በቁፋሮ የተገኙ ብዙ ለየት ያሉ አጽሞች አሉ። እነዚህም አጽሞች ከሺዎች ዓመታት በፊት የተገኙ ሲሆኑ ለየት ያለው መገለጫቸው የራስ ቅላቸው ወደ ኋላ ረዘም (ሾጠጥ) ያለ መሆኑ ነው። ሳይንቲስቶች ይህንን ሲያብራሩ፣ የአከባቢው ሰዎች ካላቸው ባህል የመጣ ነው ይላሉ። ይኸውም ህፃናት ሲወለዱ ራሳቸውን በመጭመቅ ወደ ኋላ ሾጠጥ እንዲል የማድረግ (head binding) በሳይንሳዊ አጠራሩም "Artificial Cranial Deformation" ነው ይላሉ። ሰዎቹም ይህንን የሚያደርጉት እንዲህ አይነት የራስ ቅል ቅርጽ ያላቸው ሰዎች መሪዎች የመሆን እድል ስላላቸው ነው ተብሎ ስለሚታሰብ እንደሆነ ያስረዳሉ። ነገር ግን ይህ መልስ ችግር አለበት። በርግጥ ራስ ቅልን በዚያ መንገድ የመጭመቅ ባህል ቢኖርም፣ ነገር ግን አንዳንዶቹ ራስ ቅሎቹ በተፈጥሮ እንደዚያ እንደሆኑ መረዳት ተችሏል። ለዚህም ሁለት ምክንያት ማንሳት ይቻላል። አንደኛው ምክንያት፣ የራስ ቅሎቹ ይዘት (volume) ከተለምዶው የሰው ልጅ የራስ ቅል ይዘት የሚበልጥ መሆኑ ነው። እናም የራስ ቅልን መጭመቅ ቅርጹም ብቻ ይቀይራል እንጂ ይዘቱን አይጨምርም። ራስ ቅሎቹም በተለያየ ምክንያት የመመታት እና ራስ ቅሉ ወደ ውስጥ የመሰንቆር ምልክትን ስለማያሳይ፣ የነዚህ ሰዎች የአንጎል መጠንም ከሰው ልጅ የአንጎል መጠን ከፍ ያለ መሆኑን ያሳያል። ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ የራስ ቅላቸው ከጀርባ ሁለት አጥንት መሆን የሚገባው አንድ ወጥ አጥንት ሆኖ መገኘቱ እና ያም የህፃኑን ራስ በመጭመቅ የማይፈጠር መሆኑ ነው። በነዚህ ምክንያቶችም፣ ከሰው ልጅ በተወሰነ ደረጃ የሚለዩ ሰዎች በዚያ አከባቢ ኖረዋል። በኖሩበትም ነገስታት ሆነው ኖረዋል። የአከባቢው ሰዎችም እነሱም በመመልከት ልጆቻቸውን እንደዚያ ለማስመሰል ሲሞክሩ ነበር።

በዚህ ተከታታይ ጽሁፋችን ክፍል 5 ለ የተመለከትነው፣ በመጽሃፈ ኩፋሌ መሰረት የኖህ ልጆች ምድርን የተከፋፈሉት በዚህ መልኩ ነው። የቦታዎቹ ስሞች ዛሬ በምናውቃቸው ቦታዎች መሰረት ይህ ካርታ ላይ ያለ
በዚህ ተከታታይ ጽሁፋችን ክፍል 5 ለ የተመለከትነው፣ በመጽሃፈ ኩፋሌ መሰረት የኖህ ልጆች ምድርን የተከፋፈሉት በዚህ መልኩ ነው። የቦታዎቹ ስሞች ዛሬ በምናውቃቸው ቦታዎች መሰረት ይህ ካርታ ላይ ያለውን ይመስላል። የሴም እና የያፌት ዕጣ የደረሳቸው መሬት የሚዋሰነው በሶስት ነገሮች ነው። ራፋ ተራራ፣ ኡራል ተራሮች የሚባሉት ማኡት ባህር፣ አዞቭ የሚባለው ጤና ወንዝ፣ ዶን ወንዝ የሚባለው ናቸው። ከነሱ በስተ ደቡብ የሴም ልጆች በሙሉ ነው የደረሳቸው፣ ከነሱ በስተ ሰሜን ደግሞ የያፌት ልጆች ናቸው የደረሳቸው። በዚህ ስፍራ በተለይ ደግሞ ጥቁር ባህር በሚባለው ዙርያ የያፌት ልጆች በብዛት ኖረዋል። እንዲሁም ከኡራል ተራሮች አለፍ ብሎ በዚያ አከባቢ ባለው ስቲፕ በተባለው ሳራማ ስፍራ ብዙ የያፌት ዘር ነገዶች ኖረዋል። ክነሱም ውስጥ አንድ ልዩ የሆነ ነገድ የኛን ትኩረት የሚወስድ ነው። በአክባቤው ካሉ ሰዎች የተለዩ ባህሪያትን የሚያሳዩ ነበሩ። ለምሳሌ ቁመታቸው እጅግ የረዘመ፣ በተዋጊነት የሚታወቁ ነበሩ። እነዚህም ህዝቦች በኋላ ላይ የተለያዩ ህዝቦችን ፈጥረዋል። ከነሱም ውስጥ ግን ባለ ቀያይ ጸጉሮቹ የተለዩ ህዝቦች ነበሩ።

ድብቁ የኔፍሊም ታሪክ፣ ክፍል 5 ለ:- መጽሐፈ ኩፋሌ። ከታች "Instant View" የሚለውን በመንካት ገብተው ያንብቡ። https://telegra.ph/%E1%8B%B5%E1%89%A5%E1%89%81-%E1%8B%A8%E1%8A%94%E1%8D%8D%E1%88%8A%E1%88%9D-%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD-%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D-5-%E1%88%88-%E1%88%98%E1%8C%BD%E1%88%83%E1%8D%88-%E1%8A%A9%E1%8D%8B%E1%88%8C-10-04

ድብቁ የኔፍሊም ታሪክ፣ ክፍል 5 ለ:- መጽሐፈ ኩፋሌ። ከታች "Instant View" የሚለውን በመንካት ገብተው ያንብቡ። https://telegra.ph/%E1%8B%B5%E1%89%A5%E1%89%81-%E1%8B%A8%E1%8A%94%E1%8D%8D%E1%88%8A%E1%88%9D-%E1%89%B3%E1%88%AA%E1%8A%AD-%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D-5-%E1%88%88-%E1%88%98%E1%8C%BD%E1%88%83%E1%8D%88-%E1%8A%A9%E1%8D%8B%E1%88%8C-10-04

Excitation of noble gases with plasma... we will discus this topic in the near future.

መላእክት፣ የወደቁትም ሆኑ በሰማይ በቅድስና የሚኖሩት፣ ከሰው ልጅ የላቀ እውቀት፣ ጥበብ፣ መረዳት አላቸው። እናም ስጋዊ ነገር የመንፈሳዊው መገለጫ መንገደ በመሆኑ፣ ይህ የመላእክቱ እና የአጋንንት ከ
መላእክት፣ የወደቁትም ሆኑ በሰማይ በቅድስና የሚኖሩት፣ ከሰው ልጅ የላቀ እውቀት፣ ጥበብ፣ መረዳት አላቸው። እናም ስጋዊ ነገር የመንፈሳዊው መገለጫ መንገደ በመሆኑ፣ ይህ የመላእክቱ እና የአጋንንት ከፍ ያለ እውቀት እና መረዳት ስጋ ለብሶ ሲገለጥ በዚህ መልኩ ከሰው ልጅ ከፍ ያለ መጠን ያለው አእምሮ ይዞ ነው። ስለዚህም፣ የወደቁት መላእክት ከሰው ልጆች ጋር ሲዋለዱ እና ልጆችን ሲወልዱ፣ ልጆቻቸው ከኛ ከሰው ልጆች የላቀ ቁመት ብቻ ሳይሆን አእምሮ፣ እውቀት፣ ጥበብ እና መረዳት ይዘው ነው። በዚህም ምክንያት በዘመናቸው ከነበሩት ሰዎች በመብለጣቸው የተነሳ በጦርነት፣ በፖለቲካ፣ በቴክኖሎጂ ወዘተ እጅግ የላቁ ነበሩ። ከጥፋት ውሃው ዘመን በኋላም ከነሱ የተቀሩት ቅሪት ዘሮች በዚሁ መልኩ የነበሩ ናቸው። በነበሩበት የዓለም ክፍሎችም ነገስታት እና የህዝቡ መሪዎች፣ የፖለቲካ፣ የቢዝነስ እና የጦርነት መሪዎች ነበሩ።

ይህ ስፍራ እስራኤል ከስድስት ቀኑ ጦርነት በኋላ ከሶርያ የወሰደችው የጎላን ከፍታዎች የሚባለው ስፍራ ነው። በመጽሃፍ ቅዱስም እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ሲሄዱ በመንገዳቸው ያገኙት ባሳን የሚባለ
ይህ ስፍራ እስራኤል ከስድስት ቀኑ ጦርነት በኋላ ከሶርያ የወሰደችው የጎላን ከፍታዎች የሚባለው ስፍራ ነው። በመጽሃፍ ቅዱስም እስራኤላውያን ወደ ከነዓን ምድር ሲሄዱ በመንገዳቸው ያገኙት ባሳን የሚባለው ሃገር ነው። ንጉሳቸው ዓግም እጅግ ግዙፍ የሆነ ረፋይም ተብለው ከተጠቀሱት የኔፍሊም ዝርያዎች እንደሆነ በብሉይ ኪዳን ተተርኮ ይገኛል። ይህ ስፍራ በመካከሉ ስድስት ሜትር ከፍታ ያለው አስቀድመን የጠቀስነውን አይነት መቃብር አሰራር (mound) አለው። ይህም ወደ 37 ቶን የሚመዝን የአለቶች ክምችት የተሰራ እና የሰው ልጅም ሊገነባው የማይችል እጅግ ግዙፍ ግንባታ እንደሆነ ይታያል።

በዓለም ታሪክ የተለያዩ የመቃብር አሰራሮች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ዋሻ መሰል አሰራሮች፣ እና ከምድር በላይ ከፍ ተደርገው በተለያየ ገንባታ መልክ የመስራት ባህል ሁሉም ቦታ የሚታወቅ ነው። ይህም የመቃ
+2
በዓለም ታሪክ የተለያዩ የመቃብር አሰራሮች አሉ። ከነዚህም ውስጥ ዋሻ መሰል አሰራሮች፣ እና ከምድር በላይ ከፍ ተደርገው በተለያየ ገንባታ መልክ የመስራት ባህል ሁሉም ቦታ የሚታወቅ ነው። ይህም የመቃብር አሰራር ብዙ ጊዜ የባለሃበት ወይም የባለ ስልጣኖች መቃብር ሲሆን ዘመዶቻቸው፣ ወታደሮቻቸውም ከንብረታቸው ጋር አብረው መቅበር የተለመደ ነበር። ይህም የመቃብር አሰራር "mound" ተብሎ የሚታወቅ ነው። ከነዚህም ውስጥ በእስራኤል የጎላን ከፍታዎች ስፍራ ላይ ያለው የመቃብር አሰራር የተለየ ነው። በጥንቱ ዘመን የነበረው የዐግ ንጉስ ባሳን፣ በርሱ ስም የተሰየመ ነው። አሰራርም እጅግ ግዙፍ በክብ የተሰሩ ግንቦች ያሉትና ከሰው ቁመት እጅግ ከፍ ያለ ነው። ስፍራው ደግሞ ከሰማይ ሆኖ ሲታይ ካርታው የዘንዶ መሰል ቅርጽ አለው። ከዚህም የተነሳ የዘንዶ (serpent) ቅርጽ ከመምሰሉ የተነሳ "serpent mound" ተብሎ ተሰይሟል። ይህም የዘንዶ ቅርጽ የሚመስል የመቃብር አሰራር ብዙ የዓለም ክፍሎች ጋር ተያይዟል። እርሱም ከኔፍሊም መሰል ዝርያዎች ጋር ተያይዞ ተጠቅሷል።

.

በነጭ አውሮፓውያን ታሪክ ሴት ጠንቋዮች (witches) በሰፊው ይታወቃሉ። የሚፈጽሙት የጥንቆላ ተግባርም "witchcraft" ተብሎ ይጠራል። እኚህ ሴቶች ለረጅም ዘመናት በተግባሩ ካሳለፉ በኋላም በመካከለኛው ዘመን ክርስትና በአውሮፓ ሲጠናከር እነዚህን ሴት ጠንቋዮች ማደን ተጀመረ። እጅግ ብዙ የሆኑትም ተይዘው በሞት ተቀጡ። የአገዳደላቸው ሁኔታም ከነ ነፍሳቸው ከብዙ እንጨቶች ጋር ታስረው ላያቸው ላይ እሳት በመለኮስ ነበር። ከዚያም በኋላ አብዛኛው ቅሪታቸው ከአውሮፓ ጠፋ። ዛሬ ላይ ያሉ ሰዎች ክርስትና እየቀዘቀዘ ሲመጣ አስተሳሰባቸውም ተለወጠና ያንን የጥንቆላ፣ የባእድ አምልኮ ዘመን መመኘት ጀመሩ። እነዚያን ሴቶችም "ከዘመናቸው የቀደመ የሳይንስ እውቀት ስለነበራቸው ኋላ ቀር የሆኑት ሰዎች ሰይጣናዊ ናቸው ብለው በድንቁርና ገደሏቸው" እያሉ እነዚያን ሴቶች ያሞካሻሉ። ድንቆሮ ኋላ ቀር የተባሉት ክርስቲያኖቹ መሆናቸው ነው። የጭለማ ዘመንንም በዚያ ስም እንድንጠራ ያደረጉን ክርስትና የጠነከረበትና ባእድ አምልኮ (paganism) የጠፋበት ዘመን ስለነበረ ነው። ያም አስተሳሰባቸው በዚህ ዘመን ግልጥ እየሆነ መጣ። የሆነ ሆኖ፣ ሴት ጠንቋዮች ብዙ ጊዜ በዓለም ህዝቦች አይታወቁም። በብዛት የሚገኙት በነጮች ዘንድ ነው። ከዚህ ተመሳሳይ ደግሞ ሴት ጠንቋዮችን የምናገኘው በመጽሐፈ ሄኖክ ነው። የወደቁት መላእክት መጀመሪያ ጥንቆላን ያስተማሩት ለሴቶቹ ነበር። ታዲያ ይህ "witch" የተሰኘው ቃልም ሴት ጠንቋይ ብቻ ማለት አይደለም። ሌላም ከዚህ የወደቁት መላእክት ታሪክ ጋር የሚያያይዘው ነገር አለ። ምን ይሆን? እንመለስበታለን።

በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 2019 ዓመተ ምህረት። እንኳን አደረሳችሁ።

ዶኮተር ሮዳስ የኔፍሊምን ጉዳይ ከመጻሕፍት ላይ ጠቅሶ ብዙ ማስረጃ ያቀርባል። - መጽሐፈ መቃብያን ላይ ያለ ክፍል በግልጽ ቋንቋ መላእክቶቹ የሰው ስጋ ለብሰው መምጣታቸውን - ክብረ ነገስትም ያንን አስፍቶ መላእክቱ የሰውን ስጋ የተበሱት ከእግዚአብሔር ጋር ስለተከራከሩ፣ የአዳምን ስጋ ብንለብስ ኖሮ እንደሱ አንስትም ነበር ብለው ስለታበዩ እንደሆነ - እንዲሁም ያገቧቸው ሴቶች በአሰቃቂ ሁኔታ እንደ ወለዱ፣ ልጆቹም ግዙፍ ሆኖ ሁሉንም ነገር እንደበሉ ይጠቅሳል - ሌላም መጽሐፍ መጽሐፈ ምስጢረ ሰማይ ወምድር የሚባል መኖሩን እና እሱም ስለዚሁ ጉዳይ የሚያትት መሆኑን ይነግረናል።

ብዙ የሚስጥር ማህበራትን ክፉ ተግባር እና በዓለም ላይ የሚከናወነውን ሴራ በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች የክፋቱን ሁሉ ምንጭ በአይሁዶች ላይ ያላክኩታል። ያም በተወሰነ ደረጃ እውነት ይመስላል ምክንያቱም እጅግ ብዙ ነገሮችን ስናጠና አይሁዶችን በዚያ እናገኛለን። ነገር ግን ይህ አይሁዶችን ብቻ ጥፋተኛ የማድረግ ነገር ስህተት ነው። ይህም የተለያዩ ምክንያቶች አሉት። 1ኛ፣ አይሁዶች ዛሬ፣ የዓለምን ህዝብ ለመጉዳት አደረጉት የተባሉትን ነገሮች ሁሉ እነሱም ተጎድተውበታል። ግብረሰዶም፣ የህፃናት ውርጃ፣ ኢ-አማኒነት (atheism)፣ የቤተሰብ ስርአት መፍረስ በሙሉ አይሁዶች ራሳቸው በእጅጉን የተጎዱበት ነው። እነሱ የችግሩ ፈጣሪዎች ከሆኑ እንዴት እነሱ ራሳቸው ተጎጂ ይሆናሉ? መርዝን የሚሰራ ሰው መርዙ ራሱን እንዳይጎዳውጥንቃቄ ያደርጋል እንጂ እንዴት እርሱ ራሱ አብሮ በመርዙ ይጠቃል? 2ኛ፦ እነዚህ የሚስጥር ማህበሮች የአይሁድ እምነት ውስጥ የሌሉ ነገሮችን ያምናሉ። ግኖስጢሳዊነት፣ የተለያዩ ጣዖት አምልኮዎች፣ የመሳሰሉት ለእነዚህ ሰዎች የአስተምህሮአቸው መሠረት ናቸው። አይሁድ አዲሱን የዓለም ስርአት ለማምጣት ሰሩ ብንል፣ ያ የሚያመጡት የዓለም ስርአት የጣዖት አማልክት የሚመለኩበት ለምን ይሆናል? ምክንያቱም እቅዱ ያ ነው። በመላው ዓለም ያለ ባእድ አምልኮ እና ጣዖት አምልኮ የሚመለክበት ዓለም እንዲመጣ ነው የሚፈለገው። ለዚያ ነው መጀመሪያ ኤቲስት ሰዎች እንዲበዙ የተሰራው። ጣዖታትን ለማምለክ መጀመሪያ የምናመልከውን አንድ አምላክ መካድ አለብን። ወደዚያ እንድንሄድ እየገፋፉን ነውደ። ስለዚህ አይሁድ ለምን ያንን የጣዖት አምልኮ ስርአት ለማምጣት ይሞክራሉ? 3ኛ፦ በዚህ ሁሉ ውስጥ የህዝብ ቅነሳ ፖሊሲ ሲካሄድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዶች እንዲሞቱ የማድረግ እቅድ አለ። ታዲያ አይሁዶች ለምን ራሳቸውን በሚሊዮኖች ይገድላሉ? ማነው በራሱ ህዝብ ላይ ጨክኖ ሚሊዮኖችን ለሞት አሳልፎ የሚሰጠው? 4ኛ፦ በመላው ዓለም አይሁድ ያልሆኑ ኤሊቶች አሉ። የአውሮፓ ሚስጥራዊ ንጉሳን ቤተሰቦች፣ በመላው ዓለምም በተለያዩ ሀገራት ያሉ ቡድኖች የዚህ እቅድ ተሳታፊ ናቸው። ስለዚህ መልሳችን ምንድን ነው? አይሁድ አሉበት ወይስ የሉበትም? ከጀርባ ሆነው የሚዘውሩት እነሱ ናቸው ወይስ አይደሉም? የዚህ መልስ የሚሆነው፦ አይሁድ ያልሆኑ፣ ነገር ግን አይሁድን ከፊት አስቀምጠው እቅዳቸውን የሚፈጽሙ ሰዎች አሉ የሚለው ይሆናል። በርግጥ በከፊል የአይሁድ ዘርም ሊኖርባቸው ይችላል፣ ነገር ግን ያ ሙሉ መልሱን አይሰጠንም። ለምሳሌ ያህል በአውሮፓ "black nobility" የሚባሉ ቤተሰብ አሉ። እነዚህም አይሁድ መሆናቸው አጠራጣሪ ነው። ነገር ግን እኛ ኢሉሚናቲ እያልን በስህተት የምንጠራውን ማሳሳቻ ቡድን ከፊት አድርገው፣ ከጀርባ እጅግ የሚደንቅ ዓለምን የመቆጣጠር ሂደት ይታይባቸዋል። ኢሉሚናቲ ማለት አንዱ የነዚህ ሰዎች የሽፋን ድርጅት ነው። ህዝብ የሚያውቀው፣ የሚከሰው ነው። ከዚህ ከሚታወቀው ከሚከሰሰው ጀርባ ግን ከርሱ እጅግ የገዘፈ ስልጣንና ተጽዕኖ ያላቸው፣ ማንነታቸው እንኳ በቅጡ የማይታወቅ ግለሰቦችና ቤተሰቦች አሉ። እነዚህም ሰዎች ዓለም አቀፍ የባንክ ስርአትን፣ ከሁሉም መንግስታት በላይ የሆነ የፖለቲካ መዋቅርን፣ የተለያዩ የ "በጎ አድራጎት" ድርጅቶችና ፋውንዴሽኖችን በመጠቀም ተጽዕኖአቸውንና ቁጥጥራቸውን ያጸናሉ። የማፊያ ቡድኖች፣ የስለላ ተቋማትና አሸባሪ ቡድኖችም ከነዚህ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያሉና በነሱ አመራር direction ስር የሚንቀሳሱ ናቸው። ይህንን በቀላሉ መመልከት ከፈለግን፣ እንየው። የስለላ ተቋሞች ሁሉ መሠረት የሆነው የኢንግሊዝ የስለላ ድርጀት ነው። ይህም የነዚህ ግሎባሊስቶች ሀብት ምንጭ የሆነውን British East India ድርጅት ጥቅም ለማስጠበቅ ከክፍለ ዘመናት በፊት የተመሠረተ ነው። ከዚሁ ድርጅትም ነው በኋላ ላይ እንደ ጆርጅ ኦርዌል ያሉ ሰዎች የፈለቁት። ከዚህ ድርጅት የወጡ ሰዎችም ናቸው ሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድንም የመሠረቱት። የማፍያ ቡድኖችስ እንዴት የነዚህ ሰዎች አንድ አካል ሆኑ ካልን፣ ይህን የሚያስረዳን አንድ መጽሐፍ አለ። በዚህ ቻናል አስቀድመን ሼር ያደረግነው አንድ መጽሐፍ "The technetronic era" የተሰኘው፣ አንድ የሚነግረን ነገር አለ። ይኸውም፦ ከንጉሳዊ ስርአት መውደቅ በኋላ የተፈጠረው የዓለም ስርአት፣ እንደ ጥንቱ የጉልበት መጠቀምን (violence) ከዓለም ያጠፋ እንደሆነ፣ ነገር ግን violence ሙሉ በሙሉ መጥፋት ስለማይችልም በተወሰነ ደረጃ በማፊያ ድርጅቶች መልኩ መቀጠል እንደተፈቀደለት ነው። ይህንን የፃፈው ሰው ልክ እንደ ሄንሪ ኪሲንጀር ሁሉ ዲፕሎማት ሆኖ በአሜሪካና ሶቪየት ህብረት መካከል ሲመላለስ የነበረ ሰው... ማለትም የሰዎቹን ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ማሽነሪ ከሚያንቀሳቅሱ ኤጀንቶች አንዱ ነበር። አሸባሪ ቡድኖችም በነዚሁ ሰዎች የተመሠረቱ ናቸው። ለምሳሌ የአክራሪ እስልምና አሸባሪዎች ሁሉ መሠረት የሆነው የወሃቢ እምነት የተፈጠረው በኢንግሊዝ የስለላ ሰዎች ከክፍለ ዘመናት በፊት ነው። ይህም በአደባባይ የሚታወቅ እውነታ ሲሆን መሃመድ አብድ-አል ወሃብ የሚባል ወጣትን በሳኡዲ አረቢያ መልምለው የፈጠሩት እንደሆነ ይታወቃል። በኋላም የሱ ቀዝቀዝ ያለው version ሰለፊ ተብሎ መጣ፣ እርሱም እንደ አልቃይዳ እና አልሸባብ ላሉ ቡድኖች መነሻ አይዲዮሎጂ ሆነ። ከነሱ የከፋው የ ISIS ቡድን ግን ወሃቢን ይዞ ተነሳ። ትክክለኛ ስሙ ISIL ነበር፣ ግን Isis ሆኖ ቀረ...ይህም በግብጽ አይሲስ፣ በባቢሎን ኢሽታር፣ በመጽሐፍ ቅዱስ አስጣሮት የምትባል ጣዖትን ስም ይመስላል። ያ አጋጣሚ ነው? አናውቅም። የሆነ ሆኖ ይህ አይሲስ ቡድን ከአንድ 09A ከሚባል ቡድን ጋር ይገኛል። ሁለቱም ደግሞ ከኢንግሊዝ የስለላ ድርጅት ጋ ግንኙነት አላቸው። እነዚህ ቡድኖችም የደም መስዋእት በማድረግ የሚታወቁ ናቸው። ስለዚህ ይህ ሁሉ የተወሳሰበ ዓለም አቀፍ መዋቅር፣ እና የጣዖት አምልኮ፣ የደም መስዋእት ስርአት፣ ከኤሺያ እስከ መካከለኛው ምስራቅ፣ እስከ አውሮፓና አሜሪካ የተዘረጋ ስርአት፣ የአይሁዶች ብቻ ጥፋት ነው ማለት እጅግ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።

ብዙ የሚስጥር ማህበራትን ክፉ ተግባር እና በዓለም ላይ የሚከናወነውን ሴራ በቅርበት የሚከታተሉ ሰዎች የክፋቱን ሁሉ ምንጭ በአይሁዶች ላይ ያላክኩታል። ያም በተወሰነ ደረጃ እውነት ይመስላል ምክንያቱም እጅግ ብዙ ነገሮችን ስናጠና አይሁዶችን በዚያ እናገኛለን። ነገር ግን ይህ አይሁዶችን ብቻ ጥፋተኛ የማድረግ ነገር ስህተት ነው። ይህም የተለያዩ ምክንያቶች አሉት። 1ኛ፣ አይሁዶች ዛሬ፣ የዓለምን ህዝብ ለመጉዳት አደረጉት የተባሉትን ነገሮች ሁሉ እነሱም ተጎድተውበታል። ግብረሰዶም፣ የህፃናት ውርጃ፣ ኢ-አማኒነት (atheism)፣ የቤተሰብ ስርአት መፍረስ በሙሉ አይሁዶች ራሳቸው በእጅጉን የተጎዱበት ነው። እነሱ የችግሩ ፈጣሪዎች ከሆኑ እንዴት እነሱ ራሳቸው ተጎጂ ይሆናሉ? መርዝን የሚሰራ ሰው መርዙ ራሱን እንዳይጎዳው አድርጎ ይሰራል እንጂ እንዴት እርሱ ራሱ አብሮ በመርዙ ይጠቃል? 2ኛ፦ እነዚህ የሚስጥር ማህበሮች የአይሁድ እምነት ውስጥ የሌሉ ነገሮችን ያምናሉ። ግኖስጢሳዊነት፣ የተለያዩ ጣዖት አምልኮዎች፣ የመሳሰሉት ለእነዚህ ሰዎች የአስተምህሮአቸው መሠረት ናቸው። አይሁድ አዲሱን የዓለም ስርአት ለማምጣት ሰሩ ብንል፣ ያ የሚያመጡት የዓለም ስርአት የጣዖት አማልክት የሚመለኩበት ለምን ይሆናል? ምክንያቱም እቅዱ ያ ነው። በመላው ዓለም ያለ ባእድ አምልኮ እና ጣዖት አምልኮ የሚመለክበት ዓለም እንዲመጣ ነው የሚፈለገው። ለዚያ ነው መጀመሪያ ኤቲስት ሰዎች እንዲበዙ የተሰራው። ጣዖታትን ለማምለክ መጀመሪያ የምናመልከውን አንድ አምላክ መካድ አለብን። ወደዚያ እንድንሄድ እየገፋፉን ነውደ። ስለዚህ አይሁድ ለምን ያንን የጣዖት አምልኮ ስርአት ለማምጣት ይሞክራሉ? 3ኛ፦ በዚህ ሁሉ ውስጥ የህዝብ ቅነሳ ፖሊሲ ሲካሄድ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አይሁዶች እንዲሞቱ የማድረግ እቅድ አለ። ታዲያ አይሁዶች ለምን ራሳቸውን በሚሊዮኖች ይገድላሉ? ማነው በራሱ ህዝብ ላይ ጨክኖ ሚሊዮኖችን ለሞት አሳልፎ የሚሰጠው? 4ኛ፦ በመላው ዓለም አይሁድ ያልሆኑ ኤሊቶች አሉ። የአውሮፓ ሚስጥራዊ ንጉሳን ቤተሰቦች፣ በመላው ዓለምም በተለያዩ ሀገራት ያሉ ቡድኖች የዚህ እቅድ ተሳታፊ ናቸው። ስለዚህ መልሳችን ምንድን ነው? አይሁድ አሉበት ወይስ የሉበትም? ከጀርባ ሆነው የሚዘውሩት እነሱ ናቸው ወይስ አይደሉም? የዚህ መልስ የሚሆነው፦ አይሁድ ያልሆኑ፣ ነገር ግን አይሁድን ከፊት አስቀምጠው እቅዳቸውን የሚፈጽሙ ሰዎች አሉ የሚለው ይሆናል። በርግጥ በከፊል የአይሁድ ዘርም ሊኖርባቸው ይችላል፣ ነገር ግን ያ ሙሉ መልሱን አይሰጠንም። ለምሳሌ ያህል በአውሮፓ "black nobility" የሚባሉ ቤተሰብ አሉ። እነዚህም አይሁድ መሆናቸው አጠራጣሪ ነው። ነገር ግን እኛ ኢሉሚናቲ እያልን በስህተት የምንጠራውን ማሳሳቻ ቡድን ከፊት አድርገው፣ ከጀርባ እጅግ የሚደንቅ ዓለምን የመቆጣጠር ሂደት ይታይባቸዋል። ኢሉሚናቲ ማለት አንዱ የነዚህ ሰዎች የሽፋን ድርጅት ነው። ህዝብ የሚያውቀው፣ የሚከሰው ነው። ከዚህ ከሚታወቀው ከሚከሰሰው ጀርባ ግን ከርሱ እጅግ የገዘፈ ስልጣንና ተጽዕኖ ያላቸው፣ ማንነታቸው እንኳ በቅጡ የማይታወቅ ግለሰቦችና ቤተሰቦች አሉ። እነዚህም ሰዎች ዓለም አቀፍ የባንክ ስርአትን፣ ከሁሉም መንግስታት በላይ የሆነ የፖለቲካ መዋቅርን፣ የተለያዩ የ "በጎ አድራጎት" ድርጅቶችና ፋውንዴሽኖችን በመጠቀም ተጽዕኖአቸውንና ቁጥጥራቸውን ያጸናሉ። የማፊያ ቡድኖች፣ የስለላ ተቋማትና አሸባሪ ቡድኖችም ከነዚህ ሰዎች ቁጥጥር ስር ያሉና በነሱ አመራር direction ስር የሚንቀሳሱ ናቸው። ይህንን በቀላሉ መመልከት ከፈለግን፣ እንየው። የስለላ ተቋሞች ሁሉ መሠረት የሆነው የኢንግሊዝ የስለላ ድርጀት ነው። ይህም የነዚህ ግሎባሊስቶች ሀብት ምንጭ የሆነውን British East India ድርጅት ጥቅም ለማስጠበቅ ከክፍለ ዘመናት በፊት የተመሠረተ ነው። ከዚሁ ድርጅትም ነው በኋላ ላይ እንደ ጆርጅ ኦርዌል ያሉ ሰዎች የፈለቁት። ከዚህ ድርጅት የወጡ ሰዎችም ናቸው ሲ.አይ.ኤ እና ሞሳድንም የመሠረቱት። የማፍያ ቡድኖችስ እንዴት የነዚህ ሰዎች አንድ አካል ሆኑ ካልን፣ ይህን የሚያስረዳን አንድ መጽሐፍ አለ። በዚህ ቻናል አስቀድመን ሼር ያደረግነው አንድ መጽሐፍ "The technetronic era" የተሰኘው፣ አንድ የሚነግረን ነገር አለ። ይኸውም፦ ከንጉሳዊ ስርአት መውደቅ በኋላ የተፈጠረው የዓለም ስርአት፣ እንደ ጥንቱ የጉልበት መጠቀምን (violence) ከዓለም ያጠፋ እንደሆነ፣ ነገር ግን violence ሙሉ በሙሉ መጥፋት ስለማይችልም በተወሰነ ደረጃ በማፊያ ድርጅቶች መልኩ መቀጠል እንደተፈቀደለት ነው። ይህንን የፃፈው ሰው ልክ እንደ ሄንሪ ኪሲንጀር ሁሉ ዲፕሎማት ሆኖ በአሜሪካና ሶቪየት ህብረት መካከል ሲመላለስ የነበረ ሰው... ማለትም የሰዎቹን ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ማሽነሪ ከሚያንቀሳቅሱ ኤጀንቶች አንዱ ነበር። አሸባሪ ቡድኖችም በነዚሁ ሰዎች የተመሠረቱ ናቸው። ለምሳሌ የአክራሪ እስልምና አሸባሪዎች ሁሉ መሠረት የሆነው የወሃቢ እምነት የተፈጠረው በኢንግሊዝ የስለላ ሰዎች ከክፍለ ዘመናት በፊት ነው። ይህም በአደባባይ የሚታወቅ እውነታ ሲሆን መሃመድ አብድ-አል ወሃብ የሚባል ወጣትን በሳኡዲ አረቢያ መልምለው የፈጠሩት እንደሆነ ይታወቃል። በኋላም የሱ ቀዝቀዝ ያለው version ሰለፊ ተብሎ መጣ፣ እርሱም እንደ አልቃይዳ እና አልሸባብ ላሉ ቡድኖች መነሻ አይዲዮሎጂ ሆነ። ከነሱ የከፋው የ ISIS ቡድን ግን ወሃቢን ይዞ ተነሳ። ትክክለኛ ስሙ ISIL ነበር፣ ግን Isis ሆኖ ቀረ...ይህም በግብጽ አይሲስ፣ በባቢሎን ኢሽታር፣ በመጽሐፍ ቅዱስ አስጣሮት የምትባል ጣዖትን ስም ይመስላል። ያ አጋጣሚ ነው? አናውቅም። የሆነ ሆኖ ይህ አይሲስ ቡድን ከአንድ 09A ከሚባል ቡድን ጋር ይገኛል። ሁለቱም ደግሞ ከኢንግሊዝ የስለላ ድርጅት ጋ ግንኙነት አላቸው። እነዚህ ቡድኖችም የደም መስዋእት በማድረግ የሚታወቁ ናቸው። ስለዚህ ይህ ሁሉ የተወሳሰበ ዓለም አቀፍ መዋቅር፣ እና የጣዖት አምልኮ፣ የደም መስዋእት ስርአት፣ ከኤሺያ እስከ መካከለኛው ምስራቅ፣ እስከ አውሮፓና አሜሪካ የተዘረጋ ስርአት፣ የአይሁዶች ብቻ ጥፋት ነው ማለት እጅግ ትልቅ ስህተት ነው የሚሆነው።

ከቴምፕላሮች ታሪክ ጋር ተያይዞ አንድ ተጠቃሽ ቤተሰብ አለ። ይኸውም በእስኮትላንድ የነበረው የ ሲንክሌር ቤተሰብ ነው። Sinclair የሚለው ስማቸው የመጣው Saint Clair ከሚለው ሲሆን በሀሰት ክርስትናን የተቀበሉ መስለው ግን በሚስጥር የራሳቸውን አምልኮ የቀጠሉበት ነው። የነዚህ ቤተሰቦች ሁለት ሃይማኖቶች በሚስጥር ይወክሏቸዋል። እነዚህም የአይሁድ እምነት እና ድሩይዲዝም ናቸው። በአንድ በኩል የቤተሰባቸው የሚጀመሪያው ሰው ወይም አባታቸው "Rabbi Makhir" የሚባል አይሁዳዊ ነው። ይህ ሰው በመካከለኛው ምስራቅ በኢራቅ የአይሁዶች የእምነት መሪ ነበር። ከዚያም ወደ አውሮፓ በመምጣት ንጉስ ሆነ፣ በአከባቢው የነበሩ አይሁዳውያንም መሪያቸው ሆነ። ይህም የሚከናወነው ቴምፕላሮች ከመነሳታቸው 4 ክፍለ ዘመናትን አስቀድሞ በ8ኛው ክፍለ ዘመን ነው። ይህም አይሁዳዊ "Theodoric" በመባል ስሙ ይቀየርና በፈረንሳይ አከባቢ ንጉስ ይሆናል፣ የአንድ ታዋቂ ንጉስን አክስትም ያገባል። ይህ ንጉስም Charlemagne የሚባል ሲሆን በመላው የአውርፓ ታሪክ የነገስታትና መሳፍንት ዘር ሁሉ መነሻ የሆነ ታዋቂ ንጉስና የ "Carolingian Dynasty" ጀማሪ ሰው ነው። ታዲያ ያ አይሁዳዊ ሰውም የሱ አክስት የሆነች ሴትን አግብቶ ልጅ ይወልዳል። የርሱ ልጅም Guillaume de Gellone የሚባል እርሱም ለአውሮፓ አሪስቶክራት ዘሮች አባታቸው የሆነ ሰው ነው። የርሱ የልጅ ልጅ ልጅም Popa of Bavaria የምትባል ሴት የቫይኪንግ ወራሪ የሆነውን Rollo የተባለውን ታገባለች። የርሱ ዘመዶችም በፈረንሳይ በስተሰሜን ከኢንግሊዝ ጋ የሚያዋስናቸው ባሕር ባለበት ቦታ Normandy የሚባል ግዛት ይሰጠዋል። ይህንን የምናነሳበት ምክንያት፣ ይህ ስፍራ ከክፍለ ዘመኖች በኋላ ቴምፕላሮች ከፈረንሳይ ወደ እስኮትላድ የማምለጣቸው ጉዳይ ግንኙነቱን እዚህ ጋር ስለሚያስረዳን ነው። ከዚያም እነዚህ ሰዎች በእስኮትላንድ ምድር የራሳቸውን የመሳፍንት ዘር መስርተው ይኖራሉ። እስከዛሬም ድረስ የሲንክሌር ቤተሰብ ሳይጠፋ አለ። የሚስጥር ማህበራትን ከሚዘውሩ ቤተሰቦችም አንዱ ሆኖ ከሮዝቻይልድ ቤተሰብ እኩል ብዙ ተጽዕኖን በዓለም ላይ ይፈጥራል። ታዲያ በእስኮትላንድ ሲኖሩ አንድ የሚያካሂዱት አምልኮ ነበር። የአየርላንድ፣ እስኮትላንድ፣ ፈረንሳይ አከባቢ የሚኖሩ ተመሳሳይ ህዝቦች ነበሩ። እነሱም Celtic ይባላሉ። እነዚህ ህዝቦችም ወደ 6 ተቀራራቢ ቋንቋዎችን የሚናገሩ ሲሆኑ ከዚህ በፊት ያነሳናቸው የ scythian ህዝቦች ጋር ይዛመዳሉ። ታዲያ እነዚህ ሰዎች ከጥንት ጀምሮ የሚታወቁበት የባእድ አምልኮ ነበራቸው፦ Druidism የሚባል። ይህ የባእድ አምልኮ ከእስኮትላንድ አልፎ የኢንግሊዝ ነገስታት ቤተሰቦች በሙሉ የሚሳተፉበት ሲሆነ የተለያዩ መስዋእቶች፣ የሰው ልጅን ጨምሮ የሚሰዋበት የህፃናት ደምም እንደ ግብር የሚቀርብበት ነው። ለንግስናቸውና ለሚስጥር ማህበሮቻቸውም መሠረት የሆነ ነው። ታዲያ የነዚህ የእስኮትላንድ እና ፈረንሳይ ነገስታት ዘሮች ናቸው የመስቀል ጦርነት እንዲነሳ እና ከአረቦች ጋር እንዲዋጉ ያደረጉት። ሚስጥራዊ ግባቸውም አይሁዳዊ ዘራቸውን በማሰብ በኢየሩሳሌም ላይ ራሳቸውን ማንገስ ነበር። እናም ከነዚህ የመሳፍንት ቤተሰብ አንዱ የሆነውን Godfrei de Bullion የኢየሩሳሌም ንጉስ አድርገዋል። ከዚያ በፊት ግን ወደ ኢየሩሳሌም በመሄድ ቴምፕላሮች በዚያ እንዲሰፍሩ አስደረጉ። የነዚህ ቴምፕላሮች ስምም "ምስኪን የክርስቶስ ወታደሮች" ተብሎ እንዲጠራ ተደረገ። የነዚህ ቴምፕላሮች ግብ ግን የሰለሞን ቤተመቅደስን ስፍራ መቆፈርና የተለያዩ ቅርሶችን መፈለግ (ለምሳሌ ቅዱሱን ጽዋ) የመሳሰለው ነበር። ቴምፕላሮች ከነዚህ ነገስታትና መሳፍንት ቤተሰቦች ጋር መዛመዳቸው በፍጥነት ሀብታም የመሆናቸውን ሚስጥር ይፈታዋል። ታዲያ በኋላ ላይ ክርስቶስን መካድ፣ ግብረሰዶም፣ ጣዖት አምልኮ ወዘተ እንደሚያካሂዱ ሲታወቅ የፈረንሳይ ንጉስ ከካቶሊክ ፖፕ ጋር ሆኖ አጠፋቸው። በውድቅት ሌሊት ታድነው እንዲለቀሙ አስደረገ። መሪዎቻቸውንም ቶርቸር አድርጎ ብዙ መረጃ ለማወጣጣት ሞከረ። ከወራት በኋላም መሪያቸው Hugues de Paynes ከነ ነፍሱ በእሳት ተቃጥሎ ተገደለ። ያ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ግን የተወሰኑ ቴምፕላሮች አምልጠው ወደ እስኮትላንድ ገቡ። በዚያ ካሉ የመሳፍንት ቤተሰቦች ጋርም ኖረው የነሱ ጋርዶች ሆኑ። ሰዎቹ የተቀበሩበት ቦታም የሲንክሌር ቤተሰቦች ያሰሩት የ Rosslyn ቤተክርስቲያን ነበር። ጣዖት አምልኮ የፈጸሙ እና በመስቀሉ ላይ ሽንት እንዲሸና ያደረጉ ሰዎች "ምስኪን የክርስቶስ ወታደሮች" ተብለው፣ ባእድ አምልኮ የሚፈጽሙ ሰዎች በሰሩት ቤተክርስቲያን ጓሮ ተቀበሩ። አይገርምም? በኋላም ከክፍለ ዘመናት በኋላ ፍሪሜሰንሪ የሚባል የሚስጥር ማህበር በድንገት ተጀመረ። ፍሪሜሰንሪ ብዙ አይነት ቢኖሩትም በዓለም የመጀመሪያው ግን የእስኮትላንዱ እንደሆነ ይታወቃል። ታዲያ እስኮትላንድ እና ፍሪሜሰንሪ ሲነሳ ሁሌም አብሮ የሚነሳው ይህ የሲንክሌር ቤተሰብ ስም እና የነሱ የውሸት "ቤተክርስቲያን" የሆነው ቤተ ጣኦት ሮዝሊን ነው። ታዲያ እስኮትላንድን ስናነሳ ሌሎች የነገስታት እና መሳፍንት ቤተሰብን ማንሳት እንችላለን። በመጀመሪያ የ እስቱዋርት ቤተሰቦች ሲሆኑ በኢንግሊዝ ከተነሱ ዳይናስቲዎች አንዱ የሆነው የ Stuart Dynasty መስራቾች ናቸው። ሌላኛው ደግሞ Leslie የሚባሉት የመሳፍንት ቤተሰብ ናቸው። እነዚህ የሌዝሊ ቤተሰብ የሚባሉ ሰዎች፣ ቴምፕላሮች ከፈረንሳይ ካመለጡ በኋላ የተጠጓቸው ቤተሰብ ናቸው። በኋላም የሮዝቻይልድ ቤተሰብ መነሻ እንደሆኑ መመልከት እንችላለን። የሮዝቻይልድ ቤተሰብ እንዴት ከዚህ መጣ የሚለው የራሱ ሰፊ ሀተታ አለው። በአጭሩ ግን፣ Rothes-child የሚለው ትክክለኛው የቤተሰባቸው ስም እንደሆነና፣ በአንድ ወቅት ከእስኮትላንድ ወደ ጀርመን ሄደው ስማቸውን እንደቀየሩ መመልከት እንችላለን። ይህም ቤተሰቡ ከተራ ሰራተኛ ወደ ናጠጠ ሀብታም እንዴት በፍጥነት እንደተለወጡ እና ወዲያውም ወደ ኢንግሊዝ ሄደው የነገስታት ቤተሰቦችን እንደተጋቡ፣ ባንከር እንደሆኑ ማብራሪያ ይሰጠናል። ምክንያቱም በዚያ ዘመን ከመሬት ተነስቶ የነገስታት ዘርን ማግባት የለም፣ ሰውየው ራሱ የነገስታት ወይም የመሳፍንት ዘር ከሌለው በስተቀር። እነዚህም ቤተሰቦች እርስ በርሳቸው እየተዋለዱ፣ የዓለምን ወርቅ እየመዘበሩ እና ግዙፍ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ማሽነሪዎችን ገንብተው፣ በተራቀቀ የቁጥጥር ስርአት ከዓለም መንግስታት በላይ ሆነው ከመጋረጃ ጀርባ እየገዙ ይኖራሉ። አዲሱ የዓለም ስርአት መጥቶም፣ እንደ ጥንቷ አትላንቲስ ያለ ዓለምንን መመለስ ይሻሉ።

ከቫምፓየር አፈ ታሪክ ጋ ተያይዞ በተደጋጋሚ የሚነሳው ይህ በቅርቡ የጠቀስነው ንጉስ ነው። በሮሜኒያ እና ሃንጋሪ መካከል ይገኙ የነበሩ ሁለት ሀገራትን ማለትም "Transylvania" እና "Wallac
ከቫምፓየር አፈ ታሪክ ጋ ተያይዞ በተደጋጋሚ የሚነሳው ይህ በቅርቡ የጠቀስነው ንጉስ ነው። በሮሜኒያ እና ሃንጋሪ መካከል ይገኙ የነበሩ ሁለት ሀገራትን ማለትም "Transylvania" እና "Wallachia" ይገዛ የነበረ ሰወሰ ነው። በተለይ Transylvania ከቫምፓየሮች ጋር ተያይዞ በጣም በሰፊው የሚጠቀስ ግዛት ነው። የቫምፓየር ፊልሞች እና ልቦለዶች ላይም እጅግ በተደጋጋሚ ይነሳል። ለምሳሌ በቅርብ ጊዜያት የተለቀቀ የአኒሜሽን ፊልም "Hotel Transylvania" ተጠቃሽ ነው። ይኸውም በአንድ ቤተመንግሥት የሚኖር ቫምፓየር ሰው እና የሴት ልጁ ታሪክ ሲሆን ሰውየውም "Dracula" ነው። ይህ ስም በብዙ ልብ ወለዶችና ፊልሞች ላይ እጅግ በተደጋጋሚ የሚነሳ ነው፣ የዚህ ምክንያቱም በከፊልም ቢሆን በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ ነው። ታዲያ በምስሉ ላይ የምናየው ንጉስ ታሪኩ ብዙ የሚገራርሙ ነገሮች አሉት። ለምሳሌ ቅጽል ስሙ "Dracula" ነበር። የአባቱ ስም ደግሞ Dracul ነበር። Dracula ማለትም በሀገራቸው ቋንቋ የ Dracul ልጅ ማለት ነው። Dracul ማለት ደግሞ ድራጎን ማለት ነው። እነዚህ ሰዎች፣ ከነሱ በፊት በነበሩ አባቶቻቸው ነገስታት ጊዜ ጀምሮ አንድ ማህበር ነበራቸው። ይኸውም "Order of Dragon" የሚባል ሲሆን በኦቶማን ቱርክ የመጣብንን ወረራ ለመመከት የመሠረትነው ነው የሚሉት። ነገር ግን ስሙን በድራጎን መሰየም ለምን አስፈለገ? እናም የቫምፓየርና የድራጎን ታሪክ እዚህ ጋር ለምን ተያያዘ? በሁለቱ መካከል ያለው ቁርኝት ምንድን ነው? ሌላው የሚገርመው ነገር ደግሞ ይህ ንጉስ ከኢንግሊዝ ንጉሳውያን ቤተሰቦች ጋር ይዛመዳል። ማለትም የርሱ የልጅ ልጆች በጋብቻ ከጀርመን ንግስት ጋር፣ እሷም በተራዋ ከኢንግሊዝ ነገስታት ጋራ ተዛምደዋል። በዚህም ምክንያት የኢንግሊዝ ነገስታት የዘር ሀረጋቸውን ሲቆጥሩ በአንድ በኩል እዚህ ሰው ጋር ይደርሳሉ። ይህም ሀገር ያወቀው ፀሐይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። በዚህ ቻናል ከጊዜያት በፊት እንደተመለከትነውም የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በሙሉ ከኢንግሊዝ ነገስታት ዘር የተገኙ ናቸው። ታዲያ ያም ማለት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች የዚህ ሰው ዘር አለባቸው ማለት ነው። ደግመን ለማስታወስ ያህል፦ ይህ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ይህ ሁሉ ሚስጥሩ ምንድን ነው? እንቀጥላለን።

ይህ የኔፍሊም ታሪክ እና በኖህ ዘመን የነበረው የጥፋት ውሃ ብዙ ነገሮችን ያሳየናል። እጅግ ብዙ ነገሮችንም አንድ ላይ ያስተሳስራል። ለረጅም ጊዜ ሰዎች ሁሉ የተረዱት ነገር ቢኖር አሜሪካ በአንድ ወቅ
ይህ የኔፍሊም ታሪክ እና በኖህ ዘመን የነበረው የጥፋት ውሃ ብዙ ነገሮችን ያሳየናል። እጅግ ብዙ ነገሮችንም አንድ ላይ ያስተሳስራል። ለረጅም ጊዜ ሰዎች ሁሉ የተረዱት ነገር ቢኖር አሜሪካ በአንድ ወቅት የጠፋው የአትላንቲስ ስልጣኔ ላይ የተሰራች እንደሆነች ነው። ያም የአትላንቲስ ስልጣኔ በአንድ ወቅት እጅግ የገነነ እንደነበርና ከዚያም በውቂያኖስ ስር እንደሰመጠ ይነገራል። ታዲያ ሙሉ አሜሪካ፣ ላቲን አሜሪካን ጨምሮ፣ ከግሪኮች ዘመን ጀምሮ አይታወቅም ነበር። ከመካከለኛው ዘመን በኋላ ግን፣ ልክ የሚስጥር ማህበራት ከተስፋፉ በኋላ፣ ፓጋኒዝም የተንሰራራበት የአውሮፓ ህዳሴ "Renaissance" ተብዬው ከተጀመረ በኋላ፣ መርከብ ተሳፍረው ውቂያኖስን የማቋረጥ ሀሳብ በድንገት መጣላቸው። ይህ አጋጣሚ ቢመስልም ብዙዎችን የሚገርም በሚመስል መልኩ አሜረካን አገኙ። አዲሱ ዓለም (The new world) ብለውም ሰየሙት። ታዲያ ይህ አዲስ ዓለም በኔፍሊም መሰል ታሪኮች፣ እፆች፣ ግዙፋን ሰዎች የተሞላ ነበር። እጅግ በሚደንቅ ሁኔታ ደግሞ፣ ያን ያቋረጡትን ውቂያኖስ፣ የአትላንቲክ ውቂያኖስ ብለው ሰየሙት። ወደ አትላንቲስ ለመሄድ... የአትላንቲክ ውቂያኖስን መሻገር? ምን ሊሉን እየሞከሩ ነው? እውነታውን ከፊታችን አስቀምጠዋል። አናስተውልም ብለው አስበው ነው? ወይስ ማስተዋል አለማስተዋላችንን መፈተን ፈልገው ነው? በዚህ አህጉር ነው እንግዲህ ከምድር በታች ያሉ ከተማዎችም ተገኙ የሚባለው። ኢሎን መስክ አንዱ የሀብት ምንጩ የመንግስት ድጎማ ነው። ለምን? ከመሬት በታች በግዙፍ ማሽኖች ስለሚቆፍር። የህዋ ምርምር ድርጅቱ ምንም ትርፍ የለውም፣ በጀት ስለሚለቀቅለት እንጂ። ነገር ግን በአሜሪካ መንግስት በቢሊዮን ዶላሮች ተከፍሎት ይቆፍራል። ለምን ይቆፍራል? ምን ፍለጋ ነው የሚቆፍረው? ማንም አያውቅም። ከሱና ጓደኞቹ ውጪ። ከሚቆፍራቸው ቦታዎች አንዷ የሎስ አንጀለስ ከተማ ነች። ታዲያ የፓስፊቅ ውቂያኖስ ዳርቻ የሆነችው ይህች ከተማ ከበታቿ ከርሷ የሚበልጥ የምድር ውስጥ ከተማ መገኘቱ ምን ይነግረናል? (ለንጽጽር ያህል ከተማዋ በአሜሪካ ካሉት ግዙፍ ከተሞች አንዷ ነች።) በውሃው በኩል ወደ ከተማው መግቢያ አለ? ያ ከተማ ከኖህ ዘመን በኋላ በውሃ ተውጦ ይሆን? ውሃው አፈር አልብሶት ተቀብሮ ይሆን? በተደጋጋሚ በፊልሞቻቸው ላይ፣ ከውሃ በታች ሰምጦ የቀረ ስልጣኔ እንዳለ ያሳዩናል። እውነቱን መናገር የአስተምህሮአቸው አንዱ አካል እንደሆነ አሁን እናውቃለን። የሚሰሩትን ነገር መደበቅ እንደማይችሉ እና የኛን ነፃ ፈቃድ ማግኘት ስላለባቸው ግልጽ እንደሚያደርጉለን የተረዳነው ነገር ነው። ግን ምንድነው የደበቁንስ ነገር?