cookie

We use cookies to improve your browsing experience. By clicking «Accept all», you agree to the use of cookies.

avatar

ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

በዚህ ቻናል የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርቶች እና የአበው ቀደምት የተናገሯቸው መንፈሳዊ ንግግሮች እንዲሁም ልዩ ልዩ ሐይማኖታዊ ትምህርቶችና መልዕክቶች ይተላለፉበታል፡፡

Show more
Advertising posts
29 309
Subscribers
+5524 hours
+4617 days
+84130 days
Posting time distributions

Data loading in progress...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Publication analysis
PostsViews
Shares
Views dynamics
01
#ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦ #ቀዳም_ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) #ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም) @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
10Loading...
02
#ቆዳ_ለሐመረ_ብርሃን በአዲስ አበባና አካባቢው የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በረከት አያምልጣችሁ። እንደዋዛ የምትጥሉትን የፍየሎችና የበጎች ቆዳ ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የታሪክ ባለቤት መሆን የምትችሉበት መንገድ ተመቻችቶላችኋል ስለዚህ በየሚቀርባችሁ ቦታ ወስዳችሁ በመስጠት ጥሩ ምንጭ ኢትዮጵያን በጥራት አስቀጥሉ። የእንስሳቱ ቆዳ ከዚህ በታች የምትመለከቱትን ብራና ሁነው ይጠብቋችኋል። የፍየል እና የበግ ቆዳ ለሐመረ ብርሃን የትንሣኤ ዕለት ሚያዝያ 27 📍 ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት 📍መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል 📍 አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት 📍 ሰአሊተ ምሕረት 📍 ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ለበለጠ መረጃ፦ 0966767676 | 0944240000 | 0909444400 ይደውሉ።
4378Loading...
03
"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
1 81045Loading...
04
#የማርያም_ሐዘን - ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት የሚነበብ ልመናዋ፡ ክብሯ፡ ለዘላለሙ፡ ከእኛ ጋር ይኑርና፡ አንድ፡ አምላክ፡ በሆነ በአብ በወልድ፡ በመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ስም አምኖ የብህንሳ፡ ኤጲስቆጶስ፡ አባ ሕርያቆስ ድንግል፡ ማርያም፡ እመቤታችን ስላለቀሰችው፡ ልቅሶ፡ በዛሬው፡ ቀን የደረሰው ይህ ነው፤ አሜን። ወደ ዮሐንስ ቤትም በደረሰች ጊዜ አልዘገየችም። ወደ ቀራንዮ፡ ተመልሳ፡ ልትሄድ፡ የተወዳጅ፡ ልጅዋን፡ የመከራውን፡ ፍጸሜ፡ ታይ፡ ዘንድ፡ ቸኰለች፡ እንጂ። በመስቀል፡ ላይ፡ ነፍሱን፡ በፈቃዱ፡ ሰጥቶ፡ ዝም፡ በአለ፡ ጊዜ፣ በምድር፡ ላይ፡ ስለሆነው፡ ንውጽውጽታና፡ በሰማይም፡ ስለተደረጉ፡ አስደናቂ፡ ተአምራቶች፡ ሀገሪቱ፡ ሁሉ፡ ተሸበረች። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ምድር፡ ስትናወጽ፡ ጨለማ፡ በምድር፡ ሁሉ፡ ስትሰለጥን፡ አይታ፡ እነሆ፡ እነዚህ፡ ተአምራቶች፡ የልጄ፡ የሞቱ፡ ምልክቶች፡ ናቸው፡ ብላ፡ ጮኸች። እንዲህ፡ ስትልም፡ ዳግመኛ፡ ዮሐንስ፡ ደርሶ፡ እያለቀሰ፡ ከእርሷ፡ ዘንድ፡ ቆመ። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ዮሐንስ፡ ሆይ፡ በመስቀል፡ ላይ፡ ልጄ፡ በእውነት፡ ሞተን፡ አለችው። እርሱም፡ ራሱን፡ ዝቅ፡ አድርጎ፡ እናቴ፡ ሆይ፡ አዎን፡ ሞተ፡ አላት። ፮፤ ከዚህም፡ በኋላ፡ ታላቅ፡ ልቅሶ፡ ሆነ። በዚያችም፡ ሰዓት፡ ድንግል እመቤታችንን፡ ፍጹም፡ ጩኸትና፡ ልቅሶ፡ ጸናባት፤ በመረረ፡ ልቅሶም፡ እየጮኸች፡ ልጄ፡ ሆይ ከዚህ፡ ካገኘህ፡ የሞት፡ ፃዕር፡ የተነሣ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ፡ ሹም፡ ወይም፡ በሐዘን፡ የተሰበረውን፡ ልቤን፡ አይቶ፡ በማስተዋል፡ የሚፈርድልኝ፡ ዳኛ፡ አላገኘሁም፡ አለች። መኰንን፡ ሆይ፡ እንደ፡ ሕጉ፡ የምትፈርድስ፡ ቢሆን፡ ኖሮ፡ ንጉሥ፡ ልጄን፡ እንደራበው፡ እንደጠማው፡ የአይሁድ፡ ወገኖች፡ ባልሰቀሉትም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ ፈራጅ፡ ብትሆን፡ ባርያ፡ በጌታው፡ ፈንታ፡ መሞት፡ በተገባው፡ ነበር። በበርባን፡ ፈንታ፤ ሹም፡ ሆይ፡ በቅን፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ልጄን፡ ባልሰቀልከውም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ከልጄ፡ ይልቅ፡ ይሁዳ፡ ለሞት፡ የተገባው፡ በሆነ፡ ነበር። ሹም፡ ሆይ፡ ፍርድን፡ የምታውቅ፡ ቢሆን፡ ልጄን፡ ሥጋውን፡ አራቁተህ፡ መስቀል፡ ባልተገባህም፡ ነበር። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ ወንበዴውን፡ አድነህ፡ ጻድቁን ባልገደልከውም፡ ነበር። ዳኛ፡ ሆይ፡ መልካም፡ ፍርድን፡ የምታውቅ ብትሆን፡ ኑሮ፡ ጦሮች፡ በላይህ ላይ ሲያንዣብቡ፡ ጽኑዕ፡ የሆነውን፡ ባልገደልከውም ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ የጌታህን፡ ፊት፡ ባፈርክ ነበር። እኔ፡ ስለጦርነት፡ ሰልፍ፡ ስሰማ፡ የንጉሥ፡ ልጅ፡ በጦርነቱ፡ ውስጥ፡ የተያዘ፡ እንደሆን፡ እንዳይሞት፡ ስለእርሱ፡ እጅግ፡ በርትተው፡ እየተዋጉ፡ ወደ፡ አባቱ፡ በፍጹም፡ ጌትነትና፡ ክብር፡ እስከ፡ አደረሱት፡ ድረስ፡ ይጠብቁታል ። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ፡ ለምን፡ እንዲህ፡ ሆነ፡ በጠየቅኸው፡ ጊዜ፡ ዕውነቱን፡ አስረዳህ፣ ግን፡ በአንተ፡ ዘንድ፡ የተጠላ፡ ሆነ፡ ሐሰትን፡ ወደድክ፤ እምነትህንም፡ በሐሰቱ፡ ላይ፡ አጸናህ፤ እንግዲህ፡ ከእውነተኛው፡ ከእርሱ፡ በቀር፡ ማንን፡ ትጠይቃለህ። በፊትህ፡ የቆመው፡ እርሱ፡ እውነተኛ፡ እንደሆነ፡ አታውቅምን፡ እርሱም፡ በዕውነት፡ ሕይወት፡ ነው። ንጽሕት፡ ድንግል፡ ሆይ፡ በኢየሩሳሌም፡ ከተማ፡ በዚች፡ ትውልድ፡ መካከል የሆነውን፡ ታላቅ፡ ግፍ፡ እዪ፣ እነሆ፡ ከእነርሱ በሚበልጠው፡ ላይ፡ ተሰብስበው፡ ስም ለሞት ፍርድ፡ ሰጥተውታልና። ከዚህ፡ ሁሉ፡ በኋላ፡ ክርስቶስ፡ በመስቀል ላይ፡ እንደሆነ፡ ነበር፣ የመቶ፡ አለቃውን በዕውነት፡ ይህ፡ ሰው፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡ ብሎ፡ አመነ፤ እሊህ፡ ተአምራቶቹ በሁሉ፡ ዘንድ፡ ታመኑ። ፳፣ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ሳለ ምዕመናን ሁሉ፡ በአንድነት፡ አለቀሱለት። ስለጌታ፡ ስቅለት፡ ከሄሮድስ፡ ዘንድ ወደ መጣው፡ የመቶ፡ አለቃ፡ ጲላጦስ ልኮ አስመጥቶ፡ ወደ፡ ቤቱ፡ አስገብቶ፡ ወንድሜ ሆይ፡ ይህን፡ ጸድቅ፡ ሰው፡ አይሁድና ሄሮድስ ያደረጉትን፡ አየህን? ይህ፡ ሁሉ ተአምራት በምድር፡ እስኪሆን፡ ድረስ፡ በግፍ ሰቀሉት። ወንድሜ፡ ሆይ፡ በእውነት፡ እነግርሃለሁ፤ እነዚህ፡ ከፋቶች፡ ሁሉ፡ የተፈጸሙት፡ በሄሮድስ፡ ምክር፡ እንጂ፡ በእኔ፡ ፈቃድ፡ አይደለም፤ እኔ፡ እንዳይሞት፡ ልተወው፡ ወደድኩ፤ ነገር፡ ግን፡ ሄሮድስ፡ በዚህ፡ ደስ፡ እንደማይለው፡ ባየሁ፡ ጊዜ፡ ይሰቅሉት፡ ዘንድ፡ ለአይሁድ፡ ሰጠኋቸው፡ እንጂ። ተመልከት፡ አሁን፡ ለእግዚአብሔር፡ ስለ፡ ሰቀልነው፡ ልጄ፡ ምን፡ ብድርን፡ እንከፍላዋለን፡ አለው፣ የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ፡ ከጲላጦስ፡ ጋር፡ ደሙ፡ በሄሮድስና፡ በካህናት፡ አለቆች፡ ላይ፡ ነው፣ እያሉ፡ መራራ፡ ልቅሶ፡ አለቀሱ። በዚያን፡ ጊዜ፡ ጲላጦስ፡ ልኮ፡ የካህናት፡ አለቆች፡ ቀያፋና፡ ሐናን፡ ወደ፡ ጉባዔው አስጠርቶ፡ እናንተ፡ በግፍ፡ ደምን፡ የምትጠጡ፡ ተኵላዎችና፡ ቀበሮዎች፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ወደ፡ ሞተው፡ የናዝሬት፡ ሰው፡ አሁን፡ ተመልከቱ፣ ደሙም፡ በእናንተና፡ በልጆቻችሁ፡ ላይ፡ ይሁን፡ አላቸው። እነርሱግን፡ ደስ፡ በመሰኘት፡ እያፌዙ፡ ደረታቸውን፡ እየደቁ ፊታቸውንም፡ እየነጩ፡ እስከ፡ ሽህ፡ ትውልድ፡ በእኛና፡ በልጆቻችን፡ ላይ፡ ይሁን፡ ኣሉ። እነርሱም፡ እንደ፡ ሕጋችን፡ ፈጽመናል፡ ስለምን፡ እንፈራለን? እንደነግጣለን፡ አሉት። ጲላጦስም፡ የሐሰት፡ ሕግ፡ ፈጸማችሁ፡ እንጂ፡ ይህ፡ ሕግ አይደለም፡ ኣለ፤ አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባልከው፡ እነሆ፡ ልብሶችሁ፡ ተቀደዋል። ሕጉም፡ ሊቀ፡ ካህናቱ፡ ልብሶቹን፡ በቀደደ፡ ጊዜ፡ ከክህነት፡ አገልግሎት፡ ይከልከል፡ ይላል። ቀያፋም፡ እኔ፡ ልብሴን፡ የቀደድኩት፡ እርሱ፡ በእግዚአብሔርና፡ በሕጋችን፡ ላይ፡ የስድብ፡ ቃል፡ ስለ፡ ተናገረ፡ ነው፡ ብሎ፡ መለሰለት። ጲላጦስ፡ እንግዲህ፡ በሊቀ፡ ካህናት፡ ሥርዓት፡ ወደ፡ መቅደስ፡ ኣንተ፡ እንድትገባ አልፈቅድልህም፡ እንደ፡ ሕግ፡ አፍራሽ፡ እንጂ ። አንተ፡ ወደ፡ መቅደስ፡ እንደገባህ ሌላው ቢነግረኝ፡ ቸብቸቦህን፡ ከአንተ ላይ እቆጣለሁ፡ አለው። ቀያፋም፡ ከአንተ፡ በፊት፡ ብዙ ጊዜ አልፎአል፤ ብዙዎችም፡ ሹማምንት የሚቀድሙህ፡ አሉ፤ እስከ፡ ዛሬ፡ የካህናት አለቆችን፡ ወደ፡ መቅደስ መግባትን፡ የከለከላቸው፡ አለን፡ ብሎ፡ መለሰለት። ይህንም፡ ያለ፡ የሄሮድስን፡ ሥልጣን በመተማመን፡ ነበር፤ ጲላጦስም፡ ይህን፡ ሁሉ ተአምር፡ ስታይ፡ ከሕዝቡ፡ ሁሉ፡ ጋር፡ አሁንም፡ ልብህ፡ አያምንምን፡ አለው። ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባለ፡ ቀያፋም፡ አንተስ፡ በዚች፡ አገር፡ አዲስ፡ ተክል፡ ነህ፣ ይህ፡ ምልክት፡ የሆነበትን፡ ነገርና፡ የተደረገውን፡ ኣታውቅም። ይህ፡ ይቅርታ፡ የሚደረግበት፡ የመጋቢት ወር፡ ፀሐይና፡ ጨረቃ፡ ዑደታቸውን፡ ፈጽመው፡ ተራክቦ፡ የሚያደርጉበት፡ ሲሆን፡ በዚሁ፡ ወር፡ መሠርያኖች፡ ጨረቃን፡ እንደ፡ ደም፡ የሚሆንበትን፡ ያደርጋሉ፤ የፀሐይንም፡ ብርሃን፡ በሥራይ፡ ኃይል፡ ይስባሉ። የአግዓዝያንን፡ ተግባር፡ ይመረምራሉ፤ የሥንዴውን፡ የወይንንና፡ የዘይትን፡ ፍሬዎች፡ በማዘጋጀት፡ ይህን፡ የመሰለውን፡ ቀያፋ፣ በሐሰት፡ ይናገር ነበር። ጲላጦስም፡ ከወንበሩ፡ ላይ፡ ተነሥቶ፡ አንተ እርሱን፡ ከመጥላትህ፡ የተነሣ፡ በዓለም ሁሉ፡ ላይ፡ መዐትን፡ ልታመጣ፡ ትወዳለህ ብሎ፡ ከቆዳ፡ በተሠራ፡ በደረቅ፡ በትር ደበደበው፤ ጽሕሙንም፡ ነጨው።
2 97246Loading...
05
የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ ከሕይወት ይልቅ፡ ሞት፡ ይገባሃል፤ እያሉ፡ ያንን ሊቀ ካህናት፡ ይዘልፉት፡ ነበር። በአንድነት፡ ከዘለፉትም፡ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ፡ ይዘውት፡ ሄዱ፤ ወደ ንጉሥም ይወስዱት፡ ዘንድ፡ ተስማሙ። የድንግል፡ ማርያም፡ በረከት የተወዳጅ ልጅዋም፡ ምሕረት፡ ከእኛ፡ ጋራ፡ ለዘላለም ይደርብን፤ አሜን። (#ግብረ_ሕማማት)
3 04731Loading...
06
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡ ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡ ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
2 48740Loading...
07
#ዓርብ_ስድስት_ሰዓት_የሚነበብ (የስምዖን ዐምዳዊ ጸሎት) ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ በዕንጨት መስቀል፡ ላይ፡ ራቁትህን፡ የሆንክ፡ ጨለማን ከለበሰና፡ ስሕተትን፡ ከሚያመጣ፡ ሰይጣን መንፈስ፡ ለየኝ። በኃይልህ፡ እታደስ፡ ዘንድ፡ በጥበብህም፡ እመገብ፡ ዘንድ፡ የሕይወት፡ ሐር፡ ልብስን፡ አልብሰኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን፡ የብርሃን፡ መጐናጸፊያ፡ የምታጐናጽፋቸው ኃይልንም የምታስታጥቃቸው በመስቀል፣ ላይ፡ ራቁትህን፡ ቆምክ። ልቡናዬን፡ ከፍጹም፡ ድንቁርና፡ ጨለማ፡ አርቅ፣ (አንፃ)፣ በልቤና፡ በሕዋሳቴ፡ ውስጥም፡ የጌትነትህን፡ ብርሃን፡ አብራ፤ ከምድራዊ፡ ሀሳብና፡ ጠባይ፡ ተለውጠው፡ ከሰማያውያን መላእክት፡ ጋራ፡ ያመሰግኑህ፡ ዘንድ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ የከበሩ፡ እጆችህን፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ የዘረጋህ፡ ፍቅርህ፡ በውስጡ፡ ያድርበት ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ እንዲከፈት፡ አድርገው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን ከእሳት፡ የፈጠርካቸው፡ ሰማይንም፡ እንደ ድንኳን፡ የዘረጋህ፡ የምድርንም፡ ስፋቷን ያበዛህ። በበላይዋም፡ ዓለማተ፡ ሰማይን፡ እጅግ፡ ከፍ አድርገህ፡ የፈጠርክ፡ ከበታችዋም፡ እጅግ ጥልቅ ያደረግህ፡ ዙሪያዋንም፡ በባህር፡ የከበብህ ትእዛዝህም፡ ምድርን፡ በባሕር፡ ላይ፡ ጸንታ እንድትኖር፡ ያደረጋት፡ በውስጥዋ፡ ያለውንም ሁሉ። በመስቀል፡ ላይ፡ እንዴት፡ እጅህን ዘረጋህ? እንዴትስ፡ በቀኖት፡ ተቸነከርክ፡ ወዴትስ ወረድክ? ለሞት፡ እስክትደርስ፡ ድረስ፡ የአዳምን፡ ማዳን፡ እንደምን፡ ወደድክ። አፍና፡ አንደበት፡ ካላቸው፡ ለጌትነትህ፡ ምስጋና፡ ማቅረብ፡ የሚችል፡ ማን፡ ነው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ፍቅርህን፡፡ በልቤ፡ ውስጥ፡ ቅረጽ፤ ከክፉ፡ ማሰሪያ፡ ፍታኝ፤ ለዘላለም፡ ጸንቶ፡ በሚኖር፡ ፍቅርህም፡ እሰረኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ማሕየዊ፡ መስቀልህን፡ አቅፌ፡ ከእርሱ፡ የሕይወትና፡ የመድኃኒት፡ መዐዛ፣ አሸት፡ ዘንድ፡ ስጠኝ። በልቡናዬም፡ ውስጥ፡ ንጹሕ፡ ደምህ፡ ይውረድ፤ ንጹሕ፡ መሠዊያ፡ ይሆን፡ ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ ያክብረው፤ በውስጡም፡ የሕይወትን፡ መንፈስ፡ ያንቀሳቅስ፤ የሕይወት፡ መንፈስ፡ አንተን፡ ይቀበል። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ በመስቀል ላይ፡ መጻጻንና፡ ሐሞትን፡ የጠጣህ ከታላቁ፡ ንጹሕ፡ ፍቅርህ፡ አጠጣኝ፤ ከመራራው፡ ሞተ፡ ነፍስም፡ አድነኝ። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ)
2 40049Loading...
08
ጴጥሮስ ሆይ እስከ ፈራህና ፈጥነህ እስከ ካድክ ድረስ ለእኔ ነው ትል ዘንድ በድጋሚ ሌላ መስቀል አላየህ፣ እንደ ብረትም የተሳለ አንደበት ሰጥቶህ ነበር። ጴጥሮስ ሆይ አንተስ ያለ እሳትና ያለእንጥረኛም ፈጽመህ አቀለጥከው። ጴጥሮስ ሆይ ከሰው ሁሉ ለገጽህ ግርማ ሰጥቶህ ነበር፤ ብርሃናቸው የማይጠፋ ዓይኖችን የሰጠህ ሲሆን ስለጌታህ አንዲት ጥፊ ትቀበል ዘንድ ዛሬ አልታገሥክም። ጴጥሮስ ሆይ የመንግሥት ሰማያትን መክፈቻ የሰጠህን ልጄን በካድከው ጊዜ አልፈራህም፤ በሊቀ  ካህናቱም ግቢ አልታገሥክም፤ በእርሱ ፈንታም ለዓለሙ ሁሉ የታመነ ጠባቂ አድርጎ ሾመህ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ ጌታህ አንድ ጊዜ እንኳ ጥቂት መከራ አልተቀበልክም። ጴጥሮስ ሆይ ለዓለሙ ሁሉ አባት ትሆን ዘንድ ሾመህ፤ አንተ ግን ለልጄ የወንድማማችነት ፍቅርን አላደረግህም። ጴጥሮስ ሆይ አምላካዊ እጁን በራስህ ላይ ጫነ፤ አንተ ግን ከመካድህ በፊት ዛሬ በራስህ ላይ የእሾህ አክሊል ይጭኑብህ ዘንድ አልፈቀድክም። ጴጥሮስ ሆይ ልጄ ለአንተ ወዳጅህ እንጅ እንደ ጌታህ እንዳልሆነ አስብ። ልጄን እንደዚህ ትክደው ዘንድ ለአንተ አግባብ ኣይደለም። ጴጥሮስ ሆይ ከእኛ ጋራ ይህ ሁሉ ድካም እንዳገኘው እንደ አባቴ ዮሴፍ ብትሆን ኖሮ። ጴጥሮስ ሆይ እንደ እርሱ ወደ ኄሮድስ ቢጎትቱህ በግብጽ ምድርም ከእኛ ጋራ መከራ ተቀባይ ብትሆን እንደ እርሱ መታገሥ ባልቻልክም ነበር እንጃ። አባቴ ጸድቁ ዮሴፍ ሆይ በአጥንቶችህ ላይ የሰማይ ጠል ይውረድ። ነፍስህም ዕፀ ሕይወትን ትመገብ፤ ከእኛ ጋራ ታግሠህ መከራ፡ ስትቀበል እንደ ጴጥሮስ ልጄን አልካድከውምና። ጴጥሮስ ሆይ ወደ ፍርድ አደባባይ አልወሰዱህ በባለ ሥልጣኖችም ፊት አላቆሙህ ፈጥነህ ጌታህን ካድከው። ድንግል በዮሐንስ ቤት እንደዚህ ስታለቅስ ሳለ ዮሐንስ እያለቀሰ መጣ እርሷንም እያለቀሰች አገኛት። ድንግል እመቤታችንና ዮሐንስም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርስ በርሳቸው እየተላቀሱ ሁለቱም አብረው ነበሩ። ዮሐንስም ድንግልን እናቴ ሆይ ጌታችንን ጴጥሮስ ስለካደው አታልቅሺ አላት፣ አሳልፎ እንደ ሰጠው እንደ ይሁዳ ነውር የለበትምና። በእራት ጊዜ ጴጥሮስ ሆይ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ሲለው መምህሬን ሰምቻለሁና። ጴጥሮስም እንደዚህ በአንተ ላይ ይደረግ ዘንድ አይገባም፤ ጌታዬ ፈጣሪዬም እስከ ዘላለሙ ድረስ እልክድህም መሞት ይሻለኛል፤ እንደዚህም በእኔ ላይ አይሆንም፤ ስለ አንተ ነፍሴን አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ። ከዚህ ቀደምም መምህራችን ጌታ መምህሬ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ሲገሥፀው ሰምቻለሁ። ሰይጣን ባለጋራዬ ወግድ ከኋላዬ ዕንቅፋት ሁነህብኛልና ሰው ሰውኛውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና አለው። አሁንም እመቤቴ እናቴ ሆይ ስለ አባቴ ጴጥሮስ መካድ አታልቅሽ ለኃጢአተኞች ሁሉ ለንስሐ ምሳሌ ነውና። በቃሉ ያመነውን የጌታችንን ቃል አስተባብሎ ነበርና። በሐዘኗ የሚገኝ በረከት ከዐይንዋ የፈሰሰ የዕንባ ውኃ ጸጋ ለዘላለሙ ከእኛ ጋራ ይኑር አሜን። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ_ሦስት_ሰዓት)
2 34245Loading...
09
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: #የማርያም_ሐዘን (#ዓርብ_በሦስት_ስዓት_የሚነበብ አባ፡ ሕርያቆስ፡ የደረሰው፡ ድርሳን፡ ይህ፡ ነው።) ወዳጆቼ ሆይ የአባቶች አለቃ የያዕቆብ ልቅሶ፤ ዛሬ ታደሰ አለ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ለወለደችው ለተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። መከራ ስለተቀበለችበት ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። የድንግልና ጡቷን ለእጠባችው ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በቤተልሔም በበረት ስለወለደችው ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በማኅፀንዋ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ለተሸከመችው ተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ ወልዳ ላልሳመቻቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ፤ እንደ ሰው ሁሉ በብብቷ ለተሸከመችው ልጇ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቦታ ወደቦታ ይዛ ላልተሰደደችባቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። ከሀገር ወደ ሀገር አዝላ ለተሰደደችበት ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ መቃብራቸውን ላላአየች ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። በአንድ ልጅዋ መቃብር ደጃፍ ላይ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። የባለ መልካም ጽሕም ሽማግሌ የያዕቆብ ልቅሶ በብላቴናይቱ ድንግል ዘንድ ዛሬ ታደሰ። ወንድሞቹ ባሰሩት ጊዜ ያዕቆብ ወደ ዮሴፍ አልተመለከተም። ድንግል ግን ልጅዋን በዕንጨት መስቀል ላይ ተቸንክሮ አየችው። ዮሴፍ በሰፊ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ያዕቆብ በላዩ፡ ያለቅስ ዘንድ ወደ ዮሴፍ አላየም። ድንግል ግን በአይሁድ ጉባዔ መካከል ተሰቅሎ ልጅዋን አየችው። ዮሴፍን ወንድሞቹ ልብሱን ገፈው ሲያራቁቱት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን በጎ ምክር በሌላት በአይሁድ መካከል ልብሱን ተገፎ ራቁቱን ሁኖ አየችው። ወንድሞቹ ዮሴፍን በሃያ ብር ሲሸጡት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን ይሁዳ ልጅዋን በሠላሳ ብር ሲሸጠው አየች። አራዊት ባልቀደዱት ልብስና በሌላ ደም ላይ ያዕቆብ አለቀሰ። አምላካዊ ደም ግን ድንግል ማርያም ስለእርሱ በላዩ የምታለቅስበት በቀራንዮ አለት ላይ የፈሰሰው ነው። ድንግል ግን ዛሬ ያየችው ልጅዋን ያለበሱትን ሌላ ልብስ ነበረ፤ የራሱን ልብስ ግን እርስ በርሳቸው ተካፈሉት። የዮሴፍ ወንድሞች ወንድማቸው ዮሴፍን በሸጡት ጊዜ አለቀሱ ተጸጸቱ። የእስራኤል ልጆች ግን ጌታቸውን በሸጡት ጊዜ አላለቀሱም፤ አልተጸጸቱም። የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸው በነገሠ ጊዜ ተደሰቱ። አይሁድ ግን ጌታቸው ከሙታን ተለይቶ በተነሣ ጊዜ ደስ አላላቸውም። ድንግል ሆይ፤ በእውነት በልጅሽ መቃብር ላይ ልቅሶሽ ጣዕም ያለው አሳዛኝ ነበረ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምን ታደርጊያለሽ? ብለው የልጅሽን መሰቀሉን በነገሩሽ ጊዜ በመላእክት መካከልም ቃልሽ ያማረ ነበር። እነሆ ልጅሽን በመኰንኑ ፊት አቁመውታል፤ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትም ያሰቃዩታል፣ ያቃልሉታል፣ ማርያም ሆይ ምን ታደርጊያለሽ? እነሆ ልጅሽን በፍርድ አደባባይ መካከል ልብሱን ገፈው እያራቆቱት ነው። የኢያቄም ልጅ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምንስ ታደርጊያለሽ? እነሆ በኢየሩሳሌም ሜዳ የሚሰቀልበትን ግንድ ብቻውን ተሸክሞአል፤ አንድ እንኳ ወደ እርሱ የሚቀርብ የለም። የሐና ርግብ ሆይ ለምን ተቀመጥሽ? የምትሰሪውስ ምንድን ነው? እነሆ ልጅሽን ሰቅለውት በቀራንዮ ቦታ ቁሞአል። የዳዊት ዘር ሆይ ልጅሽን በመስቀል ላይ ለምን ከፍ ከፍ አደረጉት? እመቤት ድንግል ሆይ በዮሐንስ ቤት ዛሬ ልቅሶሽ በእውነት ጣዕም ያለው ነበረ እንዲህ ስትዪ። ወዮ ለዚህ መራራ ወሬ ነጋሪ ለኢዮብና እስራኤል ለተባለ ያዕቆብ ከአረዷቸው መርዶ የመረረ ነው። ዛሬ ወደእኔ ለሚመጣ ለዚህ ለክፉ ወሬ ወዮ። ልጄ ሆይ አገሩን በኢቃጠሉ ጊዜ ለሎጥ ከአረዱት መርዶ ያስጨንቃል። በእኔ ላይ ለደረሰው ለዚህ አስጨናቂ ስብከት ወዮ። ልጄ ሆይ ስለ ኃያላነ እስራኤል ሞት ከአረዱአቸው መርዶ ይበልጣል። በዚህ በክፉ ወሬ ወደእኔ ለመጣው ለዚህ ወሬ ነጋሪ ወዮ። ልጄ ሆይ እነሆ ስታረጋጋኝ ሠላሳ ዓመት ይሆናል፤ ልገሥጽህም አልተቻለኝም። ዛሬ ወደ እኔ ወሬህ እስከመጣ ድረስ ወጥተህ እስከምትገባ አንዲት ሰዓት እንኳ አላመንኩህም። ልጄ ሆይ ለሐዘኔ ሁሉ ጥንቱ ሰሎሜ ናት፤ እኔ ዳኛውን አየው ዘንድ ከቤቴ አልወጣም፤ በፈራጁም ፊት አልቆምም። ሌባውን ራሱን ሲቆርጡት ሽፍታውንም ይገድሉት ዘንድ ሲፈርዱበት አላየሁም። ከቶ ቀራንዮን አላየሁትም፤ የጎልጎታንም ቦታ አላውቅም፤ ሁል ጊዜም በሚጣሉበት ቦታ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ክፉ የሆነ ፍርድ አላየሁም፤ በፍርድ አደባባይም ከቶ ለዘላለሙ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ያደረኩብህን ግፍ አላውቅም እኔም በዮሐንስ ቤት ነበርኩ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በሊቀ ካህናቱ በሐና ግቢ የተቀበልከው ግፍ ወሬው መራራ ነው። ልጄ ወዳጄ ሆይ ዛሬ ከእኔ ላይ ነጻነቴን አስወገድክ፤ ስለልደትህ በናዝሬት መልካም የምስራች ነገሩኝ። ዛሬ ግን በኢየሩሳሌም ይህችን ክፉ መርዶ አረዱኝ። በዮሴፍ ቤት መልካም ዜና በዮሐንስ ቤት ግን የሞት ዜና መጣልኝ ። ልጄ ወዳጄ ሆይ እኔ በልቤ ደስ እያለኝ ተቀምጨ ነበር። በየዕለቱ ፋሲካ ደርሶአል በዓሉን እናከብር ዘንድ ወደሀገራችንም እንመለሳለን እያልኩ ነበር፤ የዚህ ዓይነት ፋሲካም ደረሰኝ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በእንባና በሐዘን በዓሌ ወደ ልቅሶ ተመለሰ፤ ፋሲካየም ወደልብ ሐዘን። በዮሐንስ ቤት ሳለች ስለ ልጅዋ የመከራ ወሬ በመጣበት ጊዜ ድንግል እመቤታችን ይኸንን ልቅሶ ታለቅስ ነበር። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ከንጹሐን ሐዋርያት አንድ ፈለገች አላገኘችም፤ አይሁድን ከመፍራት የተነሳ ሁሉም ትተውት ሸሽተዋልና። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ስለ ጴጥሮስ መረመረች፤ እርሱማ የካህናት አለቆችን ከመፍራቱ የተነሳ ልጅሽን ከቶ አላውቀውም አለ፤ ሒዶም ተሸሽጓል አልዋት። ዳግመኛም ስለ ጌታችን ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ ለያዙት ሰዎች በተራራ ላይ ልብሱን ትቶ እንደ ሸሸ ነገርዋት። እንድርያስንም ፈለገችው፤ እርሱስ ወደ ከተማ አብሮት አልመጣም አልዋት፤ እንደዚሁ ቶማስም ሽሽቶ ሔደ። ስለ በርተሎሜዎስም ጠየቀች፤ እርሱም ከወንድሞቹ አስቀድሞ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ፊልጶስም ጠየቀች፤ እርሱም የፋናዎችን ውጋገንና መብራቶችን ባየ ጊዜ ፈርቶ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ዮሐንስ ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ አንድ ጊዜ ስንኳ እንዳልቆመ ነገርዋት። ስለ ማቴዎስም መረመረች፤ እርሱም ግብር ስለሚቀበላቸው አይሁድንና የካህናት አለቆችን እጅግ ስለፈራ እነርሱም ስለሚጠሉት በሌሊት ጨለማ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ሁሉም መረመረች፤ አብሮ ወደ ቀራንዮና ወደጎልጎታ ከሔደው ዮሐንስ በቀር አንድም አላገኘችም። ድንግልም ከልጅዋ ደቀ መዛሙርቶች ከዮሐንስ በቀር አንድ እንኳ ባለማግኘቷ እንደገና ዳግም ወደ ጽኑ ልቅሶና ሐዘን ተመለሰች። እንዲህ እያለችም አለቀሰች፦ ልጄ ወዳጄ ሆይ ወዮልኝ ወንድሞችህ ሸሹ ትተውህም ተሸሸጉ። አባቴ ጴጥሮስ ሆይ ጌታህን እንዳትክድ ሁልቀን እጠራጠርህ ነበር፤ ስለ እርሱ ወርቅ ብር አልሰጠህ ለምን ጌታህን ፈጥነህ ካድከው? ስለርሱ መርከብ ወይም ቀዛፊ አልሰጠህም፤ መምህርህንና ጌታህን ዛሬ ለምን ካድከው? ስለርሱ ምንም አልሰጠህም ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ እርሱ ወንድምን ወይም ወዳጅን አልሰጠህም። ልጄን ለምን ካድከው? በዚህ ሁሉ ልብህ ለምን ቀላል ሆነ?
2 77254Loading...
10
#የሰሙነ_ሕማማት_ዓርብ ዕለተ ዓርብ በቤተክርስቲያን ልዩ ቀን ነው፡፡ የማይታመመው ታሞ የዋለበት፣ የወደቁ ከተረሱበት ከትቢያ የሚያነሳ እሱ ሲወድቅ ሲነሳ የዋለበት፣ ሕመምተኞችን የሚፈውስ እሱ ሲያቃስት የዋለበት፣ ከሲኦል የዲያብሎስ ግብር ነፃ የሚያወጣ ሲገረፍ የዋለበት፣ ወልደ እግዚአብሔር ለወዳጆቹ ድኅነት በመስዋዕትነት ሙሽራ የሆነበት የደስታ ቀን፤ አሳዳጅ አሳሪያችን ዲያብሎስ ከነወጥመዱ ድል የተነሳበት ቀን ነው። ከዚህም የተነሳ በቤተክርስቲያን የተለያየ ምስጢራዊ ስያሜዎች ተሰጥቶታል፡፡ #የስቅለት_ዓርብ ይባላል የዓለም ሁሉ መድኀኒት የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ ለዓለ ድኅነት መስዋዕት ሆኖ የዋለበት ዕለት በመሆኑ የስቅለት ዓርብ ተብሏል።  (ማቴ 27፡35) #መልካሙ_ዓርብ ይባላል ይህም የሚያስገነዝበን ከስቅለተ ክርስቶስ በፊት ማንም ሰው ሲያጠፋ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት ይደረግ ነበር፡፡ በተለይ በሮማውያንና በፈሪሳውያን ሕግ መስቀል የወንጀለኞች መቅጫ ነበረ። በዚህ ዕለት ግን ታሪክን የሚቀይር ነገርን የሚገለብጠው አምላክ የወንጀለኞች መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል በደሙ ቀድሶ የምህረት ምልክት፣ የሕይወት አርአያ፣ የዲያብሎስ ድል መንሻ ፣ የቤተክርስቲያን ጌጥ፣ የገዳማት ዘውድ ስላደረገውና በዕለተ ዓርብ በሞቱ ሕይወትን ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ተብሏል፡፡ በዚህ ዕለትም ጌታ ሁሉ ተፈጸመ ብሎ ቅድስት ነፍሱን ከቅድስት ስጋው በራሱ ፈቃድ ከለየ በኋላ አምላክነቱን ለመግለፅ ተአምራት አሳይቷል፦ 1. ፀሐይ ጨልማለች 2. ጨረቃ ደም ሆናለች 3. ከዋክብት ረግፈዋል 4. የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዷል 5. ምድር ተናወጣለች (ተንቀጥቅጣለች) 6. መቃብሮች ተከፍተዋል 7. ሙታን ተነስተዋል በዓመት አንድ ጊዜ የምናገኘው ይህ ዕለት ቀራንዮን የምናስብበት ነገረ መስቀሉን የምናስተውልበት እንጂ ስለምድራዊ ኑሮአችን ስንባክን የምንውልበትና በዋዛ ፈዛዛ ልናሳልፈው አይገባም፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
4 45794Loading...
11
Media files
3 5913Loading...
12
#የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡  የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17) #ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡ #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡ #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
4 21127Loading...
13
#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ "ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡"  (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ) "በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው" (ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ) @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
6 200108Loading...
14
Media files
6 10219Loading...
15
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ #ምክረ_አይሁድ_ይባላል ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡ #የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡ #የእንባ_ቀንም_ይባላል ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
6 52387Loading...
16
ንጹሕ ሆነን የረከሰ ምራቅን አለመጠየፍ እንዴት ይቻለናል? ያለ በደል የሚደረግ ውንጀላ እና ግፍንስ "በቃ" አለማለት እንዴት ይሆናልናል? ያለ ጥፋት የሚመጣብንን ምን ያህል ጥፊዎች እንታገሳለን? ስንት ጅራፎችንስ እንቀበላለን? ስንት ውርደቶችንስ እንሸከማለን? መድኃኔዓለም ይህን ሁሉ ነገር የተቀበለው ስለ እኛ መዳን ነው። እኔ ግን ስለ ራሴ መዳን በጀርባህ ላይ ካረፉት ጅራፎች የአንዲቱን ሰንበር ያህል እንኳን መከራ ለመቀበል ትዕግስቱ የለኝም። "ተሰሃለኒ እግዚኦ በከመ ዕበየ ሳህልከ" - "አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ" መዝ 50፥1 ዲያቆን አቤል ካሳሁን
4 77646Loading...
17
ዐቢይ ጦም ሊጠናቀቅ ሲል የተሰጠ ምዕዳን እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግዚአብሔር ረድቶንም ወደ ወደቡ ልንደርስ ተጠግተናል፡፡ ነገር ግን እንዲህ በመኾኑ ልል ዘሊላን ልንኾን አይገባንም፤ ይህን ምክንያት አድርገን ከከዚህ በፊቱ ላይ ትጋታችንንና ንቃታችንን እጅጉን እንጨምር እንጂ፡፡ የመርከብ አለቆች ብዙ ባሕረኞችንና ዕቃ ጭነው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ወደ ወደቡ ሊደርሱ ሲሉ መርከባቸው ከዓለት ጋር እንዳትጋጭና ድካማቸውን ኹሉ ከንቱ ላለማድረግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ ሯጮችም እንደዚሁ ወደ መጨረሻው መስመር ሊቃረቡ ሲሉ ኃይላቸውን ኹሉ አሟጥጠው ተጠቅመው ሽልማቱን ለመውሰድ ይጥራሉ፡፡ ትግለኞችም ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌለው ቡጢ ቢደርስባቸውም፣ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ተመትተው ቢወድቁም ሽል ማቱን ይወስዱ ዘንድ የመጨረሻውን ዙር ትግል እጅግ ከፍ ባለ ጉልበ ት ይታገላሉ፡፡ ስለዚህ የመርከብ አለቆች፣ ሯጮችና ትግለኞች ድል ወደ ማድረግ ሲቃረቡ እጅግ ከፍ ያለ ትጋትና ጥንቃቄ ኃይልም እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ወደ ታላቁ ሳምንት ደርሰናልና እግዚአብሔር ስለረዳን እያመሰገንን ጸሎታችንን፣ ተአምኖ ኃጢአታችንን፣ በጎ ምግባራችንን፣ ምጽዋ ታችንን፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን መስተጋብራችንን፣ ራስን የመግዛት ጠባያችንን፣ እንደዚሁም ይህን የመሰለው ሌላው ምግባራችንን ከፍ ባለ ትጋትና ጥንቃቄ ልንፈጽም ይገባናል፡፡ እነዚህን በጎ በጎ ነገሮችን ወደ ጌታ ቀን (ወደ በዓለ ትንሣኤ) የምንደርስ ከኾነ ከጌታችን ዘንድ ባለሟልነትን እናገኛለን፤ ከማዕዱ ዘንድ መሳተፍ ይቻለናል፡፡  (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ ገጽ 148)     @beteafework  @beteafework 
6 91854Loading...
18
#የሰሙነ_ሕማማት_ማክሰኞ #የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡ ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተዓምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይ ነውን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡ #የትምህርት_ቀንም_ይባላል፡- በማቴ. 21፥28፣ ማቴ. 25፥46፣ ማር.12፥2፣ ማር.13፥37፣ ሉቃ. 20፥9፣ ሉቃ. 21፥38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱም መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡ @beteafework
7 496111Loading...
19
#በግብረ_ሕማማት_ውስጥ_የሚገኙ_እንግዳ_ቃላት_እና_ትርጉማቸው፦ በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡ #ኪርያላይሶን፦ ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነው፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ" ማለት ነው፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ "አቤቱ ማረን" ማለት ነው፡፡ "ኪርያላይሶን" የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው "ዬ" ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ" ን ፈጥረው ነው፡፡ #ናይናን፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፣ ማረን" ማለት ነው፡፡ #እብኖዲ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው፡፡ "እብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው። #ታኦስ፦ የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣ አምላክ" ማለት ነው፡፡ "ታኦስ ናይናን" ማለትም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነው፡፡ #ማስያስ፦ የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ "መሲሕ" ማለት ነው፡፡ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነው #ትስቡጣ፦ "ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው። #አምነስቲቲ_ሙኪርያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ" ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡ #አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ፦ የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
9 136223Loading...
20
#በሰሙነ_ሕማማት_የሚፈጸሙ_ሥርዓቶች 1, #ስግደት :- በሰሙነ ሕማማት 41 ጊዜ ኪርያላይሶን 12 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያት እየተዜመ እጅግ አብዝቶ ይሰገዳል። 2, #ጸሎት :- በሰሙነ ሕማማት ከ24 ሰዓት ውስጥ 10 የጸሎትና የንባብ ሰዓታት ይገኛሉ እነዚህም ከጠዋቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት እንዲሁም ከምሽቱ 1 ሰዓት; 3ሰዓት; 6ሰዓት; 9ሰዓት; 11ሰዓት ናቸው። በእነዚህም ሰዓታት የጌታን ስቃይ ለማዘከር መዝሙረ ዳዊትና ግብረ ሕማማት ድርሳነ ማኅያዊ አብዝተው ይጸለያሉ። 3, #ጾም :- በሰሙነ ሕማማት ብዙ አዝማደ መባልዕት / አዘውትረን የምንመገባቸው ምግቦች አይበሉም። በዚህም ሳምንት እስከ ምሽቱ #አንድ_ሰዓት እንድንጾም; ይኸውም ቆሎ;ዳቦ;ወኃና ጨው ብቻ እንደታዘዙ በግብረ ሕማማት ላይ ተጽፎ ይገኛል። 4, #አለመሳሳም :- አይሁድ ጌታችንን ለመስቀል እየተንሾካሾኩ ስለተመካከሩና ይሁዳ ጌታችንን በመሳም አሳልፎ ስለሰጠው መሳሳም አይፈቀድም። መስቀልም በዘመነ ኦሪት የወንጀለኛ መቅጫ የእርግማን ምልክት ስለ ነበር ጌታችን በክቡር ደሙ ቀድሶ የድል አርማ እስኪያደርግልን ድረስ አንሳለመውም ገላ.3:13 ማቴ.10:38 ማቴ. 26:29 5. #አክፍሎት :- እመቤታችን; ያዕቆብና ዮሐንስ የጌታችን ትንሳኤ ሳናይ እህልና ውኃ አንቀምስም ብለው እስከ ትንሳኤው መቆየታቸውን በማሰብ የሚጾም ነው። 6, #ጉልባን :- ከባቄላ ከስንዴ ከገብስ የሚዘጋጅ በጸሎተ ሐሙስ ዕለት የሚበላ ንፍሮ ሲሆን ትውፊቱም የስቅለቱ ሐዘን መግለጫ ነው። 7, #ጥብጠባ :- ይህ ምዕመናን በሰሙነ ሕማማት የፈጸሟቸውን ኃጢአቶች ለካህን እየተናዘዙ በወይራ ቅጠል ቸብቸብ እየተደረጉ ስግደት የሚቀበሉበት ነው። ይህም የጌታ ምሳሌ ነው። 8, #ቄጠማ :- ጌታችን ብርሃነ ትንሳኤዉን እንደገለጠልን የምናስብበት ሲሆን የእሾህ አክሊል በመድፋቱ ምሳሌም በራሳችን ላይ እናስረዋለን። እንበለ ደዌ ወሕማም እንበለ ጻም ወድካም ያብጽሐነ ያብጽሕክሙ ለብርሃነ ትንሳኤሁ እግዚአብሔር በፍስሐ ወበሰላም። @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
7 549230Loading...
21
#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ #መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡ በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡ በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡ #አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦ ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡ በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
7 255125Loading...
22
Media files
5 64728Loading...
23
#ሰሙነ_ሕማማት ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ሰሙነ ሕማማት የጾመ ሁዳዴ የመጨረሻው ሳምንት፤ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማም የሚታሰብበት፤ ካህናትና ምእመናን በአጸደ ቤተክርስቲያን ተሰብስበው የሕማሙን ነገር የሚያወሳውን ዜማ የሚያዜሙበት፤ ግብረ ሕማም በመባል የሚታወቀውን መጽፍ የሚያነቡበትና የሚሰሙበት፤ በነግህ፣ በሠልስት፣ በስድስት፣ በተሰዓት /ዘጠኝ /ሰዓት፣ በሰርክ /በዐስራ አንድ/ ሰዓት እየመላለሱ የሚሰግዱበትና የሚጸለዩበት ልዩ ሳምንት ነው ከሆሳዕና ማግስት እስከ ትንሳኤ። በዚህ ሳምንት በተለይ ካህናት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ ምክንያቱም ጌታችን የደረሰበትን መከራና ስቃይ እንዲሁም የሰው ልጅ ፭ ሺ ፭ መቶ ዘመን በጨለማ ግዞት ይኖር እንደነበር ለማዘከርም ጭምር ነው። የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መከራና ሕማም በጽኑ እንድናስበው ያስተማሩን ሐዋርያት ናቸው። ለእነርሱም የነገራቸው ደግሞ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሰሙነ ሕማማት የጌታችንን ሕማማት ከማሰብ ጋር በየዕለቱ በርካታ ድርጊቶች መፈጸማቸውን የምናስታውስበት ሳምንት ነው፦ #ሰኞ #መርገመ_በለስ_የተፈጸመበት_ሰኞ_ይባላል፦ በዚህ ዕለት ጌታችን ከቢታኒያ ሲወጣ ተራበ ቅጠል ያለባትን በለስ ተመልክቶ ወደ በለሲቱ ቢቀርብ ከቅጠል በቀር ምንም ነገር ባለማግኘቱ “ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም ምንም ካንቺ ፍሬ አይበላ” ማር ፲፩፥፲፬ በማለት ስለረገማት መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ ይባላል። #አንጽሖተ_ቤተ_መቅደስ_ይባላል፡- ጌታ ወደ ቤተመቅደስ ሄዶ በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እና የሚለውጡትን “ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች” ማቴ ፳፩፥፲፫ በማለት ከቤተመቅደስ ገርፎ አስወጥቷቸዋልና። #ማክሰኞ #የጥያቄ_ቀን_ይባላል፦ ሰኞ ዕለት በቤተመቅደስ ሲሸጡ እና ሲለውጡ የነበሩትን ሁሉ እየገረፈ በማባረሩ ምክንያት ለሰው ልጅ ሹመትንና ስልጣንን የሰጠ ጌታ “በምን ስልጣን ይህንን ታደርጋለህ?” ማቴ ፳፩፥ ፳፫ ተብሎ በፈሪሳውያን ተጠይቋልና የጥያቄ ቀን ይባላል። #የትምህርት_ቀን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት በቤተመቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረም የትምህርት ቀን ይባላል። ሉቃ ፳፩ ፥፳፰ ፣ ማር ፲፪፥፪። #ረቡዕ #ምክረ_አይሁድ_ይባላል፦ ረቡዕ እለት የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንዳለባቸው የመከሩበትና ውሳኔ ያሳለፉበት ቀን በመሆኑ ምክረ አይሁድ ይባላል። ወቅቱ የፋሲካን በዓል የሚያከብሩበት ቀን በመሆኑ እና ብዙ ህዝብም ጌታን ይከተለው ስለነበር ሁከት እንዳይነሳ ስጋት ነበራቸው ። ነገር ግን ከአስራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ አሳልፎ እንደሚሰጣቸው ስለነገራቸው ሉቃ ፳፪፥፩-፮ ጭንቀታቸው ተወግዶ በጌታ መያዝ ተስማምተዋል። #የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል፡- ጌታችን በዚህ ዕለት በለምጻሙ በሰምዖን ቤት ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት/ባለሽቶዋ ማርያም/ ዋጋው እጅግ ውድ የሆነ የአልባጥሮስ ሽቱ አምጥታ በራሱ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባቸው ማቴ ፳፮፥፮-፯ የመዓዛ ቀን ይባላል። #የእንባ_ቀን_ይባላል፡- ባለሽቱዋ ሴት (ማርያም እንተ እፍረት) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። #ሐሙስ #ጸሎተ_ሐሙስ_ይባላል፦ ጌታችን ለአይሁድ ተላልፎ ከመሰጠቱ በፊት በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ ሲጸልይ በማደሩ ማቴ ፳፮፥፴፮ ጸሎተ ሐሙስ ይባላል።ጌታችን የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትህትና ዝቅ ብሎ ያጠበበት ዕለት በመሆኑም ዮሐ ፲፫፥፫-፲፩ ሕጽበተ ሐሙስ ይባላል። #የምስጢር_ቀን_ይባላል፡- ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ የቅዱስ ቁርባን ምስጢር ማቴ፳፮፥፳፮-፳፱ በዚህ ዕለት ተፈጽሟልና የምስጢር ቀን ይባላል። #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል፡- መሥዋዕተ ኦሪት /በእንስሳት ደም የሚቀርብ መሥዋዕት/ቀርቶ ለአለም ድኅነት ራሱን ያቀረበበት ቀን በመሆኑ ሉቃ ፳፪፥፳ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ ይባላል። #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል፡- ለኃጢአትና ለዲያቢሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱን እንዲሁም የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነም ዮሐ ፲፭፥ ፲፭ የነጻነት ሐሙስ ይባላል። #ዓርብ #የስቅለት_ዓርብ_ይባላል፦ ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ቤዛ ሆኖ በመልዕልተ መስቀል ላይ ተሰቅሎ የዋለበት ዕለት ነውና ማቴ ፳፯፥፴፭ የስቅለት ዓርብ ይባላል። #መልካሙ_ዓርብ_ይባላል፡- ከጌታ ስቅለት በፊት በተለይም በሮማውያን ህግ የወንጀለኛ መቅጫ ምልክት የነበረውን መስቀል ጌታችን በደሙ ቀድሶ የምህረት፣ የሕይወት አርማ፣ የዲያቢሎስ ድል መንሻ ስላደረገው፤ በሞቱ መልካሙን ሕይወት ስላገኘን መልካሙ ዓርብ ይባላል። #ቅዳሜ #ቀዳም_ስዑር_ትባላለች ፦ ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል። #ለምለም_ቅዳሜ_ይባላል፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል። #ቅዱስ_ቅዳሜ_ይባላል፡- ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል። (ስምዐ ጽድቅ  መጋቢት ፳፻፪ ዓ.ም) @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
8 905277Loading...
24
#ንጉሥ_በአህያ_ላይ (ሽራፊ ሃሳብ ከሆሳዕና ምንባብ) "አህያ" ስምዋ ስድብ ከሆነ የቆየች እንስሳ ናት።  የዚህች  በዓለም ሁሉ የምትገኝ እንስሳ የሕይወት ታሪክዋ በአብዛኛው ተመሳሳይ ነው።  በሚበዙት ሀገራት አህያ ከባድ ሸክም ስትሸከም ትውላለች ፣  ደክሟት ለማረፍ ብትፈልግና ሸብረክ ብትል እንኳን በዱላ የሚመታት እንጂ "እስቲ አረፍ በይ" የሚላት የለም። ጀርባዋ በሸክም ብዛት የቆሰለ ፣ እግርዋ በጭነት ብዛት የተብረከረከ ፣ ዱላ ያስመረራት ፣ ዕረፍት የናፈቃት እንስሳ ናት። ይህችን የተዋረደች እንስሳ በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ሰማያዊው ንጉሥ ክርስቶስ በትሕትናው ዙፋኑ አደረጋት። ዱላ በለመደችው ፣ ዕረፍት በናፈቃት በዚህች ምስኪን ላይ "ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜ ቀሊል ነው" ያለው ንጉሥ ተቀመጠባት። ኃያላን ነገሥታት ባማረ ሠረገላ ላይ ሆነው ፣ በሠራዊት ታጅበው ፣ ነጋሪት እያስመቱ ፣ መለከት እያስነፉ ፣ ሰይፍ  በታጠቁ ጦረኞች እየተፎከረላቸው ወደሚገቡባት ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአህያ ላይ ተጭኖ ፣ በዓሣ አጥማጆች ተከብቦ ፣ በሕፃናት ዝማሬና በዘንባባ ዝንጣፊ ታጅቦ ገባ።  ፈርተውት ሳይሆን ወደውት የሚዘምሩለት ንጉሥ ፣ ልብስ ገፍፎ የሚረግጥ ሳይሆን ልብሳቸውን አውልቀው ረግጠህ እለፍ የሚሉት ንጉሥ ፣ በቅንጦት ሠረገላ የሚሣፈር ሳይሆን "በአህያ ላይ ከተቀመጥኩ ይበቃኛል" የሚል ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። "የጽዮን ልጅ ሆይ ደስ ይበልሽ ፣ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያና በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል" የተባለላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? "የዋህና ትሑት ንጉሥ" ያላት ሀገር ፣ ከተማይቱን  እያየ የሚያለቅስላት ንጉሥ ፣ መልካምነቱን ለመሸፈን የሚፈልጉ ሰዎች ስለ እሱ አትናገሩ ቢሉ እንኳን የቢታንያ ድንጋዮች አፍ አውጥተው የሚመሰከሩለት ንጉሥ ያላት ኢየሩሳሌም ምንኛ የታደለች ናት? የታሰሩትን አስታውሶ "ያስፈልጉኛል ፣ ፈትታችሁ አምጡልኝ" የሚል ንጉሥ የነገሠባት ፣ ዘንባባ ተይዞ ስለ ሰላም የተዘመረባት ፣ "ሰላምሽ ዛሬ ነው" የተባለላት  ያቺ ከተማ ምንኛ የታደለች ናት? ወደ አህያይቱ ነገር እንመለስ ያቺን "ሸክም ያቆሰላትን ፣ ዕረፍት የናፈቃትን አህያ ክርስቶስ ፈትታችሁ አምጡልኝ ብሎ ዙፋኑ አደረጋት" የሚለው ታሪክ ለአህያ ብቻ ክብር የተሠጠበት ቀን መሆኑን የሚያሳይ ከመሰለን የዋሆች ነን። አህዮች አንብበው የማይጽናኑበት ወንጌል ላይ ይህ ክስተት የተጻፈው ለእኛ እንጂ ለምንም አይደለም። እንደ አህያ ዕቃ ባንሸከምም ፣ ጀርባችን  ባይቆስልም የልባችን ጀርባ በኃጢአት ሸክም የጎበጠ ፣ በበደል ብዛት የቆሰለብን ብዙዎች ነን። "መቼ ነው ይህንን የኃጢአት ሸክም አራግፌ ዕርፍ የምለው?" እያልን የምንሠቃይ ሞልተናል።  መድኃኔ ዓለም ያኔ የላካቸውን ካህናት ዛሬም ወደ እኛ ልኮ "ፈትታችሁ አምጡልኝ" ብሎ እኛንም ቢያስፈታን ምናለ? ለነገሩ የእኛ የኃጢአት ማሠሪያ እጅግ ትብትብ ያለ ስለሆነ ካህናቱም ሥልጣኑ እያላቸው  በትሕትና "ከኃጢአት ማሠሪያ እግዚአብሔር ይፍታ" ሲሉ እንሰማቸዋለን። #ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
5 91961Loading...
25
#ሆሳዕና በዕለተ ሆሳዕና እስራኤላውያን ለምን የዘንባባ ዝንጣፊ፤ የቴምር ዛፍ ዝንጣፊ እና የወይራ ዛፍ ዝንጣፊ ይዘው  ዘመሩ? (ማቴ. 21÷1-17፣ ማር. 11÷ 1-10፣ ሉቃ. 19÷29-38፣ ዮሐ. 12÷12-15) #የዘንባባ_ዝንጣፊ፡- ☞ይስሃቅ በተወለደ ጊዜ አብርሃም ደስ ብሎት ዘንባባ ይዞ እግዚአብሄርን አመስግኖበታል የደስታ መግለጫ በመሆኑ አነተ ደሰታ የምታስገኝ ሃዘናችንንም የምታርቅ አምላክ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ ዘንባባ ደርቆ እንደገና ህይወት ይዘራል የደረቀ ሕይወታችንን የምታለመልም አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የሰላም ምልክት ነው የሰላም አምልክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሾሃማ ነው አንተ ህያው አሸናፊ አምላክ ነህ ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ እሳት አይበላውም ለብልቦ ይተወዋል እንጅ ጌታም አንተ ባህርይህ የማይመረመር ነው ሲሉ ነው ☞ ዘንባባ የነፃነት ምልክት ነው ከባርነት ነፃ የምታወጣን አንተነህ ሲሉ ነው አኛም ይህን በማሰብ ዘንባባ ይዘን ሆሳእና በአርያም እያልን እለቱን እናስባለን፡፡ #የቴምር_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ ጣፋጭ ነው፦ በሃጥያት የመረረውን ሂወታችን የምታጣፍጥልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ የሚገኘው ከዛፉ ከፍታ ላይ ነው አንተ አምላካችን ልዑለ ባህሪ ነህ ከፍ ከፍ ያልክ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ዛፍ ፍሬ በውስጡ ያለው ፍሬ አንድ ነው አንድ አካል አንድ ባህሪ ነህ ሲሉ ነው። ☞ የቴምር ፍሬ በእሾህ የተከበበ ነው ይህም የአንት ባህሪ የማይመረመር በእሳት የተከበበ ነው ሲሉ ነው። #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ፡- ☞ የወይራ ቅጠል የሰላም ማብሰሪያ ነው ሰላማችንን የምታበስርልን የምታስገኝልን አንተ ነህ ሲሉ ነው፡፡ ☞ የወይራ ቅጠል ከእንጨት ሁሉ ጽኑ ነው አንተም ጽኑ ሃያል አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ ወይራ ለመብራት ያገለግላል ፍሬው ዘይት ያወጣል ከወይራ የሚገኝ ዘይት ጨለማን አሸንፎ ብርሃን እንደሚሰጥ ሁሉ አንተም ጨለማ ህይወታችንን የምታስወግድልን አምላክ ነህ ሲሉ ነው። ☞ በኦሪት ግዜ የወይራ ዘይት ለመስዋአትነት ይቀርብ ነበር አንተም እንደ ዘይቱ ለመተላለፋችን መስዋዕት ሆነህ የምትቀርብ አምላክ ነህ ሲሉ ነው። በመስቀል ላይ መስዋዕት ሆኗልና። በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡ @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
6 16468Loading...
26
“ፍቅርህ ከዘባነ ኪሩብ አውርዶ በአህያ ጀርባ ላይ እንድትቀመጥ አስገደደህ፡፡ ብዙ ዐይንና ብዙ ገጽ ካላቸው ከሰራዊተ መላክእት ይልቅ በዲዳዋ አህያ ትመሰገን ዘንድ ወደድክ፡፡ በሰማይ ሰራዊት ሠረገላ ተቀምጠህ ክብርህን ማሳየት አልወደድክም፤ በውርንጭላይቱ ላይ ተቀምጠህ ወደ ሰማይ ሰራዊት መሄድን መረጥክ እንጂ፡፡ በአርያም እሳታውያን የሚሆኑ ኪሩቤል ያመሰግኑሃል፤ በምድርም ሕፃናት ይዘምሩልሃል፡፡ በአርያም ብርሃናውያን መላእክት በብርሃን ክንፋቸው መንገድህን ያነጥፉልሃል፤ በምድርም ደቀ መዛሙርትህ ልብሳቸውን አንጥፈው መንገድህን አስተካከሉ፡፡ ወዮ! አርያማዊ ሲሆን ምንም ሳይንቀን ይጐበኘን ዘንድ ከአባቱ መጣ፡፡ እርሱም በገዛ ፈቃዱ ሰው እስከመሆን ደርሶ መጣ፡፡ በአህያ ላይ ተጭኖም ይጐበኘን ዘንድ መጣ፡፡ ነቢዩ ዘካርያስ የመንፈስ ቅዱስን እንዚራ ይዞ በደስታ ትንቢትን ለመናገር ይቻኰላል፡፡ እየደረደረም የጽዮንን ልጅ ይጠራታል፡፡” #ሊቁ_ያዕቆብ_ዘሥሩግም
6 974109Loading...
27
#ሆሳዕና (የዐቢይ ጾም ስምንተኛ ሳምንት) ሆሣዕና ከስምንቱ የዐቢይ ጾም እሑዶች አንዱና የመጨረሻው ሳምንት ተብሎ የሚጠራ ከትንሣኤ ቀድሞ የሚገኝ የሕማማት መገቢያ ዋዜማ ነው። ሆሣዕና አስቀድሞ ካለው ረቡዕ ጀምሮ የሚታሰብ ታላቅ የቤተክርስቲያን የበዓል ቀን እንደሆነ ይታወቃል። ይህን ስም በዚሁ ሰንበትና በዋዜማዎቹ ዕለታት የሚዘመረው ጾመ ድጓ ‘ሆሣዕና በአርያም’’ ‘ሆሣዕና ለወልደ ዳዊት’’ ‘ዕለተ ሆሣዕናሁ አርዓየ… ‘ ወዘተ. በማለት ሆሣዕና የሚለውን ቃል ቅዱስ ያሬድና ሌሎችም አባቶች በየቦታው እየጠቀሱና እየተዘመረለት በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ ኢየሩሳሌም የገባበትን ሁኔታ እየተረከ ስለሚዘምር ይህ ሰንበት በጌትነትና በክብር በውዳሴና ቅዳሴ ሆሣዕና በአርአያም እየተባለ በሽማግሌዎችና በሕፃናት አንደበት በድንጋዮችም ልሳን ሳይቀር እየተመሰገነ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በከብር ሲገባ ለሰጣቸው ለተቀደሰ ሰላሙና ፍቅሩ መታሰቢያ ሆኖ የተሰጠ ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ሌላ ቀን እንደ ተራ ሰው ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም ይገባ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ግን የአይሁድ ንጉሥ ሆኖ በክብር ገባ፡፡ ከቢታንያ ተነሥቶ ደብረ ዘይት ሲደርስ ከሐዋርያቱ ሁለቱን በቤተፋጌ ሰው ተቀምጦባት የማያውቅ ውርንጭላ እንዲያመጡለት ላካቸው፡፡ “በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሒዱ በዚያን ጊዜም የታሰረችን አህያ ውርንጫም ከእርሷ ጋር ታገኛላችሁ፤ ፈትታችሁም አምጡልኝ፡፡ ማንም አንዳች ቢላችሁ ለጌታ ያስፈልጉታል በሉ" አላቸው፡፡ ማቴ.21፡1-17 ወደ ቤተፋጌም ሄደው አህያዪቱን አገኙአት፡፡ ሲፈቱአትም ሳለ ባለቤቶቹ መጡባቸውና አስቆሟቸው፡፡ እነርሱም ኢየሱስ እንደፈለጋት ነገሩአቸው፡፡ ባለቤቶቹ ይህንን ሲያውቁ ተዋቸው፡፡ ሐዋርያትም የአህያዪቱን ውርንጭላ ፈትተው ወደ ኢየሱስ ወሰዱ፡፡ አጠገቡም ሲደርሱ ልብሳቸውን በአህያዪቱ ውርንጭላ ላይ አንጥፈው ኢየሱስን አስቀመጡት፡፡ #ለምን_ዘንባባ_ያዙ_ቢባል፡- ዘንባባ እሾሃም ነው ፤አንተም የኃይል የድል ምልክት አለህ ሲሉ፤በሌላም በኩል ዘንባባ እሳት ለብልቦ ይተወዋል እንጂ አይበላውም አንተም ባህርይህ አይመረመርም ሲሉ፤አንድም ዘንባባ ረጅም /ልዑል/ ነው አንተም ባሕርይህ ልዑል ነው ሲሉ ዘንባባ ይዘው ተቀብለውታል፡፡ #የተምር_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡- ተምር ፍሬው አንድ ነው አንተም ባህርይህ አንድ ነው ሲሉ፡፡አንድም፤ተምር ልዑል/ረጅም/ ነው አነተም ልዑለ ባህርይ ነህ ሲሉ፡፡ አንድም፤የተምር ፍሬው በእሾህ የተከበበ ነው በቀላሉ መለቀም አይቻልም ፤ የአንተም ምስጢር አነተ ካልገለጠከው አይመረመርም ሲሉ ነው፡፡ #የወይራ_ዛፍ_ዝንጣፊ_ነው_ቢሉ፡- ወይራ ጽኑዕ/ ጠንካራ/ ነው አንተም ጽኑዓ ባህርይ ነህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ለመስዋዕት ይሆናል፤ አንተም መስዋዕት ትሆናለህ ሲሉ፤አንድም ወይራ ዘይቱ ለመብራት ይሆናል አንተም የዓለም ብርሃን ነህ ሲሉ ይህንን ይዘው አያመሰገኑ ተቀበሉት፡፡ #ልብሳቸውንም_ማንጠፋቸው፡- እንኳን አንተ የተቀመጥክባት አህያ እንኳን መሬት መርገጥ አይገባትም ሲሉ ልብሳቸውን አነጠፉለት፡፡ እነዚያ ያላመኑ አይሁድ ለተቀመጠባት አህያ ይህንን ያህል ክብር ከሰጡ፤ በድንግልና ጸንሳ ለወለደችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምን ያህል ክብር ልናድረግለት ይገባን ይሆን?፡፡ #የዕለተ_ሰንበት_መዝሙር (ከጾመ ድጓ) ወእንዘ ሰሙን በዓለ ፋሲካ ቀርቡ አርዳኢሁ ለአምላከ ጽድቅ ኀበ ደብረ ዘይት ሙራደ ዓቀብ ሀገረ እግዚአብሔር ወተቀበልዎ ሕዝብ ብዙኃን አዕሩግ ወሕፃናት ነሢኦሙ አዕፁቀ በቀልት እንዘ ይብሉ ሆሣዕና በአርያም ተፅዒኖ ዲበ ዕዋል ቦአ ሀገረ ኢየሩሳሌም በትፍሥሕት ወበሐሴት ይሁቦሙ ኃይለ ወሥልጣነ፡፡….. ትርጉም: “በፋሲካ በዓል ሰሞን የእውነት አምላክ ደቀ መዛሙርት ወደ ደብረ ዘይት ቀረቡ፤ በሀገረ እግዚአብሔር (ኢየሩሳሌም) አቀበቱ ላይ ብዙ አረጋውያንና ሕፃናት የዘንባባ ቅጠል ይዘው ሆሣዕና በአርያም እያሉ ተቀበሉት፣ በአህያ ውርንጫ ላይ ተጭኖ በፍጹም ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ገባ። ለእነዚህ ኃይልና ሥልጣንን ይሰጣቸዋል። #መልዕክታት ዕብ.8÷1-ፍጻ. ከተናገርነውም ዋናው ነገር ይህ ነው፤ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፡፡ እርሱም የመቅደስና የእውነተኛይቱ ድንኳን አገልጋይ ነው፤ እርስዋም በሰው ሳይሆን በእግዚአብሔር የተተከለች ናት፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) 1ኛ ጴጥ.1÷13 ስለዚህ የልቡናችሁን ወገብ ታጥቃችሁና ነቅታችሁ ኑሩ፤ ኢየሱስ ክርስቶስም ሲገለጥ የምታገኙትን ጸጋ ፈጽማችሁ ተስፋ አድርጉ፡፡  (ተጨማሪ ያንብቡ) #ግብረ_ሐዋርያት የሐዋ.8÷26-ፍጻ. የእግዚአብሔር መልአክም ፊልጶስን ተናገረው፤ እንዲህም አለው÷ “በቀትር ጊዜ ተነሣና በደቡብ በኩል ከኢየሩሳሌም ወደ ጋዛ በሚያወርደው በምድረ በዳው መንገድ ሂድ፡፡” ተነሥቶም ሄደ፡፡” እሆም÷   (ተጨማሪ ያንብቡ) #ምስባክ "ንፍሑ ቀርነ በዕለት ሠርቅ፡፡ በእምርት ዕለት በዓልነ፡፡ እስመ ሥርዓቱ ለእስራኤል ውእቱ" መዝ.80÷3 ትርጉም፦ በመባቻ ቀን በታወቀችው በዓላችን ቀን መለከትን ንፉ፤ ለእስራኤል ሥርዐቱ ነውና÷ የያዕቆብም አምላክ ፍርድ ነውና፡፡ ወይም "እምአፈ ደቂቅ ወሕፃናት አስተዳሎከ ስብሓተ፡፡ በእንተ ጸላዒ፡፡ ከመ ትንሥቶ ለጸላዒ ወለገፋዒ፡፡" መዝ.80÷2 ትርጉም፦ ከሕፃናትና ከሚጠቡ ልጆች አፍ ምስጋናን አዘጋጀህ፡፡ ስለ ጠላት÷ ጠላትንና ግፈኛን ታጠፋው ዘንድ፡፡ #ወንጌል ዮሐ.12÷1-11 ፋሲካ ከሚውልበት ከስድስተኛው ቀን አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከሙታን ያስነሣው አልዓዛር ወደ ነበረበት ወደ ቢታንያ መጣ፡፡ (ተጨማሪ ያንብቡ) ቅዳሴ ፡- ቅዳሴ ዘጎርጎርዮስ፡፡
8 131121Loading...
28
ኑ! ያለንን በማካፈል በዓለ ትንሳኤን ከነዳያንና የአብነት ተማሪዎች ጋር #በወልድያ_ደብረ_ሰላም_መድኃኔዓለም_ካቴድራል #ከፈለገ_ሰላም_ሰንበት_ትምህርት_ቤት አብረን እናክብር።             ለፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት                        ዳሽን ባንክ           የሂሳብ ቁጥር 5033012404001 ለበለጠ መረጃ፦ ➛ቀሲስ ሰሎሞን ተስፋሁን- 09 13 23 10 26 ➛ ዶክተር ሰሎሞን በላይ - 09 16 03 35 43 ➛ ሐብታሙ እንግዳው -  09 38 36 01 75 ➛ ደርቤ ካሳ - 09 42 50 75 95 ጥያቄ ካለዎት @natansolo በዚህ ያናግሩኝ
8 1156Loading...
29
"የቤት ዕቃዎችን መግዛት ስንፈልግ፥ በጣም እንጠነቀቃለን፡፡ የሻጮቹን ማንነት አይተን፣ የዕቃዉንም ጥንካሬ አገላብጠን ተመልክተን ነው የምንሸምተው፡፡ ሚስት ስናገባም ከዚህ የበለጠ ልንጠነቀቅ ይገባናል፡፡ የገዛነው ዕቃ ችግር ቢኖርበት ለሸጠልን ሰው መመለስ እንችላለን፡፡ ሚስት ስናገባ ግን ወደ ቤተሰቦቿ መመለስ አንችልም፤ እስከ ዕድሜአችን ፍጻሜ ድረስ ከእኛ ጋር ነው የምትኾነው፡፡ ክፉ ናት ብለን ብንመልሳት፥ በሕገ እግዚአብሔር መሠረት አመንዝራ እንኾናለን፡፡ ስለዚህ ሚስት ስትመርጡ የሀገራችሁን ሕገ መንግሥትን ብቻ አታንብቡ፤ ከኹሉም በፊት ሕገ ቤተ ክርስቲያንን አንብቡ እንጂ፡፡" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
110Loading...
30

8 62873Loading...
31
"#በተለመደው_አካሄድ_የትም_አንደርስም!" (ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ) https://youtu.be/qP9gSnueBhA https://youtu.be/qP9gSnueBhA https://youtu.be/qP9gSnueBhA
8 7355Loading...
32
የሰውን ልጅ በሩህሩህነት አሸንፈው። ቀናተኛውን በመልካምነትህ እንዲደነቅ አድርገው፤ ሁሉንም ሰው ውደድ ነገር ግን ከሁሉም ሰው ጋር ርቀትህን ጠብቀህ ኑር። አባ እንጦንስ
8 027158Loading...
33
ኑ! ያለንን በማካፈል በዓለ ትንሳኤን ከነዳያንና የአብነት ተማሪዎች ጋር #በወልድያ_ደብረ_ሰላም_መድኃኔዓለም_ካቴድራል #ከፈለገ_ሰላም_ሰንበት_ትምህርት_ቤት አብረን እናክብር።             ለፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት                        ዳሽን ባንክ           የሂሳብ ቁጥር 5033012404001 ለበለጠ መረጃ፦ ➛ቀሲስ ሰሎሞን ተስፋሁን- 09 13 23 10 26 ➛ ዶክተር ሰሎሞን በላይ - 09 16 03 35 43 ➛ ሐብታሙ እንግዳው -  09 38 36 01 75 ➛ ደርቤ ካሳ - 09 42 50 75 95 ጥያቄ ካለዎት @natansolo በዚህ ያናግሩኝ
9 7935Loading...
34
እኔስ ኦርቶዶክሳዊ በመሆኔ እኮራለሁ፦ ኦርቶዶክሳዊያን ሁሉ ቅዱሳንን እንደፀጋቸው ያከብራሉ፡ ማክበራቸውንም በአፍ ብቻ ሳይሆን በግብር ያሳያሉ፤ ቅዱሳንንም ከሚንቁ ጋር በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው፡ በቅዱሳን ፍቅር እየነደዱ የቅዱሳንን ክብር ይመሰክራሉ፡፡ ስለቅዱሳንም ዘብ ይቆማሉ፡፡ ይሄውም ስለቅድስና ዘብ መቆም ነው፡ ይሄውም ቅዱስ ስለሆነው አንዱ አምላካችን እግዚአብሄር ዘብ መቆም ነው፡፡ ቅዱሳንን የሚያናንቁት ራሳቸውን ቅዱስ ሲይደርጉ ኦርቶዶክሳውያን ግን “እኔስ በኃጢአት የወደቅኹ ከንቱ ሰው ነኝ” በማለት በትህትና ራሳቸውን ዝቅ ያደርጋሉ፡፡ እኔንም ከኒህ ወገን መሆኔ ያኮራኛል፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ያከብራሉ፡ “ወላዲተ አምላክ” እያሉ “ የእግዚአብሔር እናት አንቺ ነሽ” እያሉ የአምላካችን የክርስቶስን እናት ያከብራሉ፡፡ እመቤታችንን ለሚያናንቋት፡ ክብሯንም ዝቅ ለማድረግ ከሚሮጡ መናፍቃን ጋርም ክብሯን እየገለፁ ስለእመቤታችን ዘብ ለመቆም የመጀመሪያወቹ ናቸው፡፡ “የድኅነት ምክንያታችን አንቺ ነሽ” እያሉ፤ አምላካችን ክርስቶስ የተዋሐደው ትስብእት ካንቺ የነሳውን ነው። ስለዚህም ካንቺ የተገኘውን ክርስቶስን በላነው ጠጣነው ህይወትም ሆነልን በማለት እመቤታችንን ያከብሯታል፡፡ ወዲያውም ይህ ምስጢር ላልገባቸውና ለሚጠራጠሩ ደግሞም ለሚንቁ እመቤታችንን መናቅ ክርስቶስን መናቅ ነው በማለት ዘብ ይቆማሉ፡፡ ስለክርስቶስ ሰው መሆን ዘብ ይቆማሉ፡፡ እኔንም ከእነኚህ ወገን መሆኔ ያኮራኛል፡፡ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ መድኅን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ አምላክ ወልደ አምላክ፣ የሁሉ ፈጣሪ፣ የሁሉ አስገኝ፣ ሁሉን የሚዳኝ እግዚአብሔር ነው በማለት ያምናሉ፡፡ ሙስሊሞች ነቢይ ነው ባሉ ጊዜ እንዴት ይሆናል? በማለት ስለአምላክነቱ ይከራከራሉ፤ አርዮስና ጆሆቫ ዊትነስ ክርስቶስን ፍጡር ነው በማለት ባውካኩ ጊዜ አይደለም ክርስቶስ ስጋን የተዋሐደ የስጋ ፈጣሪ አምላክ ነው። ክብሩ ከአብ ጋር የሚስተካከል፡ ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በስልጣን እኩሉ የሆነ አምላክ እንጂ ፍጡር አይደለም በማለት ሽንጣቸውን ገትረው ስለክርስቶስ ባላቸው ፍቅር ለመመስከር ችላ አይሉም፡፡ ዳግመኛም ክርስቶስን እንደሙሴ የሚቆጥሩ፡ ዳግመኛም ክርስቶስ የፈፀመውን ድኅነት እንዳልተፈፀመ የሚቆጥሩ፡ ዳግመኛም በሁሉ ላይ የሚፈርድ ንጉስ ሲሆን ይለምናል የሚሉ ፕሮቴስታንቶች በመጡ ጊዜ “አይ ክርስቶስማ አምላካችን ነው፤ አምላካችንም አንድ ነው፤ እንግዲህ ወደማን ይለምናል? እርሱ እግዚአብሔር ነው።” በማለት ክርስቶስን ከሁሉ በላይ በማድረግ አሁንም ስለክርስቶስ ይመሰክራሉ። አሁንም ስለክርስቶስ ዘብ ከቆሙ ከእኒህ ወገን መሆኔ ያኮራኛል፡፡ እኛ ቅዱሳንን አናመልክም! የምናመልከው አስቀድሞ የነበረ፣ ሁሉን አሳልፎ የሚኖር አልፋና ኦሜጋ የሆነውን ቅድሱን እግዚአብሔር ነው። ከሳሽ ቢከስም በግድ አምልኳቸው ከሆነ የምናመልከውን እናውቃለንና አናመልክም ነው መልሳችን። ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያምን የድህነት ምክንያት አንቺ ነሽ ስንላት በፍጹም እምነትና ኩራት ነው። ሄዋን ሞት ወደ ዓለም እንዲመጣ ምክንያት ስትሆን ድንግል ማርያም ግን የዓለሙ መድኅን ሕይወት የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ምድር እንዲመጣ ዙፋን ሆና ተገኝታለችና፣ በኖኅ ዘመን ምድር በውኃ ስትጠፋ ኖኅና ቤተሰቡ ይድኑ ዘንድ መርከቧ ምክንያት እንደሆነች የጠፋውን ዓለም ይፈልግ ዘንድ እግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ምድር ይመጣ ዘንድ ምክንያት ሆናለችና የድኅነት ምክንያታችን እንላታለን። ቅዱስ ጳውሎስ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ።" ማለቱ የክርስቶስን ክብር መቀናቀኑ ይሆን? እርሱ ክርስቶስን እንደመሰለ እኛ እርሱን ብንመስል ክርስቶስን መሰልን ማለት ነው። እርሱ በህይወቱ ክርስቶስን መስሎ የተመላለሰ እስከ ሶስተኛው ሰማይ ተነጥቆ ሚስጥራትን የተመለከተ ስለ ቀደሙ አባቶቹ ትጋት የጻፈ እነሱ በየትኛው ቅድስናቸው ነው ቅዱሳንን ይንቁ ዘንድ ድፍረት የሆናቸው? እኔስ የትህትና አባት ክርስቶስ ዝቅ ብሎ እግራቸውን እንዳጠበ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ "እኔ ጭንጋፍ ነኝ።" 2ኛ ቆሮ 15፥8 በማለት ትህትናን ከሰበኩት ቅዱሳን፣ ስለ ትህትና ስለ ፍቅር አብዝታ ከምትሰብከው ከተዋሕዶ ህብረት ነኝና እኮራለሁ!!! አዎ የኦረቶዶክስ ተዋሕዶ ልጅ በመሆኔ እኮራለው! (orthodox and bible page) @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
7 36539Loading...
35
"ጌታ ሆይ አንተን ምን ብሎ መጥራት እንዳለበት የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ጌታ ሆይ እናትህን ድንግል ብለን እንጥራትን? እንዲያ ብለን እንዳንጠራት የአንተ እናት መሆኑዋ ምስክር ይሆንብናል፤ ጌታ ሆይ እናት እንበላትን? እንዲህ እንዳንል ወንድ የማታውቅ ድንግል ናት፤ የእናትህ ነገር ለመረዳት የረቀቀ ከሆነ አንተን ሊረዳ የሚችል ሰው ማን ነው?" ቅዱስ ኤፍሬም
6 54066Loading...
36
"አንተ ግን ለድኾች ምጽዋትን ትሰጣለህ፤ እኔም እጄን ዘርግቼ ካንተ እቀበላለሁ፡፡  የታረዙትን በምታለብሳቸው ጊዜ እኔን ታለብሰኛለህ። የታሰሩትን በምታረጋጋቸው ጊዜ በመካከላቸው ኾኜ በዚያ ታገኘኛለህ፡፡ በሽተኛውንም በምትጎበኘው ጊዜ ከእርሱ ጋር በአልጋው ላይ ኾኜ ዳግመኛ ታገኘኛለህ፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) ኑ! ያለንን በማካፈል በዓለ ትንሳኤን ከነዳያንና የአብነት ተማሪዎች ጋር #በወልድያ_ደብረ_ሰላም_መድኃኔዓለም_ካቴድራል #ከፈለገ_ሰላም_ሰንበት_ትምህርት_ቤት አብረን እናክብር።             ለፈለገ ሰላም ሰንበት ትምህርት ቤት                        ዳሽን ባንክ           የሂሳብ ቁጥር 5033012404001 ለበለጠ መረጃ፦ ➛ቀሲስ ሰሎሞን ተስፋሁን- 09 13 23 10 26 ➛ ዶክተር ሰሎሞን በላይ - 09 16 03 35 43 ➛ ሐብታሙ እንግዳው -  09 38 36 01 75 ➛ ደርቤ ካሳ - 09 42 50 75 95 ጥያቄ ካለዎት @natansolo በዚህ ያናግሩኝ
9 28010Loading...
37
https://youtu.be/qP9gSnueBhA https://youtu.be/qP9gSnueBhA https://youtu.be/qP9gSnueBhA
8 5126Loading...
38
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቀሲስ በላይ ጉዳይ ከቤተክርስቲያኗ ጋር የሚያገናኘው ነገር እንደሌለ አስታወቀች‼️ ከሰሞኑ ቀሲስ በላይ መኮንን በሀተኛ ሰነድ 6 ሚሊዮን 50 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ ለማዘዋወር ሞክረዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርትያኗ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር እንደሌለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ማስታወቋን ዶቸቬለ ዘግቧል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ግለሰቡ በቤተክርስቲያኗ በከፍተኛ ኃላፊነት የሚያገለግሉ ቢሆንም፤ ተጭበርብሯል ከተባለው ሰነድ ጋር ግን ቤተክርስቲያኗን የሚያገናኛት ምንም ነገር እንደሌለ አስታውቃለች፡፡ መምህር ዶ/ር አካለወልድ ተሰማ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የመንበረ ፓትሪያርክ ህዝብ ግንኙነት የሚዲያ ክፍል ዋና ኃላፊ “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር በዋሉበት ጉዳይ ላይ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን የመከታተል ጥረት ላይ ትገኛለች ማለታቸውን  ሸገር ታይምስ ሚዲያ ከዜና ምንጩ ዘገባ ለመመልከት ችሏል። ኃላፊው “እስካሁን በተደረገው ክትትል “ሊቀ አዕላፍ በላይ መኮንን በህግ ጥላ ስር የዋሉበት ጉዳይ ከቤተክርስቲያናችን ጋር የሚያገናኘው ምንም ጉዳይ እንደሌለና በግል ህይወታቸው ውስጥ የገጠማቸው ነገር እንደሆነ ነው የተረዳነው” ብለዋል። መምህር ዶ/ር አካለወልድ አክለውም በቀጣይ ጉዳዩ ቤተክርስቲያንን የሚጎዳ ነገር አለው ወይ? የሚለው በህግ ክፍል በኩል ማጣራት እንዲደረግ ትዕዛዝ መተላለፉንም አመልክተዋል፡፡
8 65614Loading...
39
"እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ ሆይ! ወርሐ ጾሙ ሲያልቅ ባዶ እጃችንን እንዳንገኝ በኹሉም ረገድ እንበርታ ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ በጾም እየደከሙ ሳለ የጾምን ዋጋ ሳያገኙ መቅረት አለና፡፡ "ይህስ እንደምን ነው?" ያላችሁኝ እንደኾነም "ከምግበ ሥጋ እየጾምን ሳለ የኃጢአትን መብል ስንመገብ፣ ሥጋን ከመብላት ተከልክለን ሳለ የድኻውን ቤት ስንበረብር፣ ወይንን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፉ መሻቶች ስንሰክር፣ ቀን ሙሉ ምግብ ሳንበላ ውለን ሳለ ዓይናችን ግን ክፉ ነገሮችን ሲመለከት ነዋ" ብዬ እመልስላችኋለሁ፡፡" #ቅዱስ_ዮሃንስ_አፈወርቅ
8 35240Loading...
40
በቤትህ ያለው ዳቦ ለተራበው ሰው የሚውል(ንብረቱ) ነው፥ በልብስ ማስቀመጫህ ውስጥ ያለው የማትጠቀመው ኮት የችግረኛው ገንዘቡ ነው፥ በጫማ ማስቀመጫህ ውስጥ አልፈልገውም ብለህ ሊበላሽብህ የሆነው ጫማ የደሃው ጫማ (ጫማ ለሌለው ገንዘቡ) ነው ፥ ያከማቸኸው ገንዘብ ለድሃው የሚገባው ነው.... ዛፍ በፍሬው ይታወቃል፥ ሰውም በድርጊቱ፡፡ መልካም ስራ መቼም አይጠፋም፡፡ መልካም እርዳታን የሚዘራ፥ ወዳጅነትን ያጭዳል፡፡ ደግነትን የሚተክል ፍቅርን ይሰበስባል፡፡ "ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ብቻ የለብንም፥ ነገር ግን ካነበብነው ተምረን ማደግ አለብን፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ምንም የማይጠቅም ነገር እንዳልተጻፈ ተገንዘብ፡፡ አሁንም ለጥንካሬ፣ ለመታገስ፣ ለመዳን፣ ለመለወጥ ጊዜ አለህ! ተኝተሃልን? ንቃ! ኃጢአት ሰርተሃልን? እንግዲያውስ  መስራቱን አቁም፡፡ #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳርያ @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework @beteafework    @beteafework
7 13344Loading...
#ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ) የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦ #ቀዳም_ሥዑር፡- በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡ #ለምለም_ቅዳሜ፡- ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡ (የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡) #ቅዱስ_ቅዳሜ፡- ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡ (ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም) @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework @beteafework       @beteafework
Show all...
Photo unavailableShow in Telegram
#ቆዳ_ለሐመረ_ብርሃን በአዲስ አበባና አካባቢው የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በረከት አያምልጣችሁ። እንደዋዛ የምትጥሉትን የፍየሎችና የበጎች ቆዳ ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የታሪክ ባለቤት መሆን የምትችሉበት መንገድ ተመቻችቶላችኋል ስለዚህ በየሚቀርባችሁ ቦታ ወስዳችሁ በመስጠት ጥሩ ምንጭ ኢትዮጵያን በጥራት አስቀጥሉ። የእንስሳቱ ቆዳ ከዚህ በታች የምትመለከቱትን ብራና ሁነው ይጠብቋችኋል። የፍየል እና የበግ ቆዳ ለሐመረ ብርሃን የትንሣኤ ዕለት ሚያዝያ 27 📍 ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት 📍መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል 📍 አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት 📍 ሰአሊተ ምሕረት 📍 ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል ለበለጠ መረጃ፦ 0966767676 | 0944240000 | 0909444400 ይደውሉ።
Show all...
👍 6
"ጸሎትን የምንጸልየው እግዚአብሔር የማያውቀው ነገር ኖሮ አይደለም፤ ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ ቀርበን ወዳጆቹ እንድንሆን፣ ዘወትር እንዲረዳን፣ ራሳችንን ዝቅ ለማድረግ፣ ኃጢአታችንንም እንድናሰብ ነው እንጂ።" #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
Show all...
🙏 55 41👍 6
#የማርያም_ሐዘን - ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት የሚነበብ ልመናዋ፡ ክብሯ፡ ለዘላለሙ፡ ከእኛ ጋር ይኑርና፡ አንድ፡ አምላክ፡ በሆነ በአብ በወልድ፡ በመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ስም አምኖ የብህንሳ፡ ኤጲስቆጶስ፡ አባ ሕርያቆስ ድንግል፡ ማርያም፡ እመቤታችን ስላለቀሰችው፡ ልቅሶ፡ በዛሬው፡ ቀን የደረሰው ይህ ነው፤ አሜን። ወደ ዮሐንስ ቤትም በደረሰች ጊዜ አልዘገየችም። ወደ ቀራንዮ፡ ተመልሳ፡ ልትሄድ፡ የተወዳጅ፡ ልጅዋን፡ የመከራውን፡ ፍጸሜ፡ ታይ፡ ዘንድ፡ ቸኰለች፡ እንጂ። በመስቀል፡ ላይ፡ ነፍሱን፡ በፈቃዱ፡ ሰጥቶ፡ ዝም፡ በአለ፡ ጊዜ፣ በምድር፡ ላይ፡ ስለሆነው፡ ንውጽውጽታና፡ በሰማይም፡ ስለተደረጉ፡ አስደናቂ፡ ተአምራቶች፡ ሀገሪቱ፡ ሁሉ፡ ተሸበረች። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ምድር፡ ስትናወጽ፡ ጨለማ፡ በምድር፡ ሁሉ፡ ስትሰለጥን፡ አይታ፡ እነሆ፡ እነዚህ፡ ተአምራቶች፡ የልጄ፡ የሞቱ፡ ምልክቶች፡ ናቸው፡ ብላ፡ ጮኸች። እንዲህ፡ ስትልም፡ ዳግመኛ፡ ዮሐንስ፡ ደርሶ፡ እያለቀሰ፡ ከእርሷ፡ ዘንድ፡ ቆመ። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ዮሐንስ፡ ሆይ፡ በመስቀል፡ ላይ፡ ልጄ፡ በእውነት፡ ሞተን፡ አለችው። እርሱም፡ ራሱን፡ ዝቅ፡ አድርጎ፡ እናቴ፡ ሆይ፡ አዎን፡ ሞተ፡ አላት። ፮፤ ከዚህም፡ በኋላ፡ ታላቅ፡ ልቅሶ፡ ሆነ። በዚያችም፡ ሰዓት፡ ድንግል እመቤታችንን፡ ፍጹም፡ ጩኸትና፡ ልቅሶ፡ ጸናባት፤ በመረረ፡ ልቅሶም፡ እየጮኸች፡ ልጄ፡ ሆይ ከዚህ፡ ካገኘህ፡ የሞት፡ ፃዕር፡ የተነሣ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ፡ ሹም፡ ወይም፡ በሐዘን፡ የተሰበረውን፡ ልቤን፡ አይቶ፡ በማስተዋል፡ የሚፈርድልኝ፡ ዳኛ፡ አላገኘሁም፡ አለች። መኰንን፡ ሆይ፡ እንደ፡ ሕጉ፡ የምትፈርድስ፡ ቢሆን፡ ኖሮ፡ ንጉሥ፡ ልጄን፡ እንደራበው፡ እንደጠማው፡ የአይሁድ፡ ወገኖች፡ ባልሰቀሉትም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ ፈራጅ፡ ብትሆን፡ ባርያ፡ በጌታው፡ ፈንታ፡ መሞት፡ በተገባው፡ ነበር። በበርባን፡ ፈንታ፤ ሹም፡ ሆይ፡ በቅን፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ልጄን፡ ባልሰቀልከውም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ከልጄ፡ ይልቅ፡ ይሁዳ፡ ለሞት፡ የተገባው፡ በሆነ፡ ነበር። ሹም፡ ሆይ፡ ፍርድን፡ የምታውቅ፡ ቢሆን፡ ልጄን፡ ሥጋውን፡ አራቁተህ፡ መስቀል፡ ባልተገባህም፡ ነበር። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ ወንበዴውን፡ አድነህ፡ ጻድቁን ባልገደልከውም፡ ነበር። ዳኛ፡ ሆይ፡ መልካም፡ ፍርድን፡ የምታውቅ ብትሆን፡ ኑሮ፡ ጦሮች፡ በላይህ ላይ ሲያንዣብቡ፡ ጽኑዕ፡ የሆነውን፡ ባልገደልከውም ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ የጌታህን፡ ፊት፡ ባፈርክ ነበር። እኔ፡ ስለጦርነት፡ ሰልፍ፡ ስሰማ፡ የንጉሥ፡ ልጅ፡ በጦርነቱ፡ ውስጥ፡ የተያዘ፡ እንደሆን፡ እንዳይሞት፡ ስለእርሱ፡ እጅግ፡ በርትተው፡ እየተዋጉ፡ ወደ፡ አባቱ፡ በፍጹም፡ ጌትነትና፡ ክብር፡ እስከ፡ አደረሱት፡ ድረስ፡ ይጠብቁታል ። ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ፡ ለምን፡ እንዲህ፡ ሆነ፡ በጠየቅኸው፡ ጊዜ፡ ዕውነቱን፡ አስረዳህ፣ ግን፡ በአንተ፡ ዘንድ፡ የተጠላ፡ ሆነ፡ ሐሰትን፡ ወደድክ፤ እምነትህንም፡ በሐሰቱ፡ ላይ፡ አጸናህ፤ እንግዲህ፡ ከእውነተኛው፡ ከእርሱ፡ በቀር፡ ማንን፡ ትጠይቃለህ። በፊትህ፡ የቆመው፡ እርሱ፡ እውነተኛ፡ እንደሆነ፡ አታውቅምን፡ እርሱም፡ በዕውነት፡ ሕይወት፡ ነው። ንጽሕት፡ ድንግል፡ ሆይ፡ በኢየሩሳሌም፡ ከተማ፡ በዚች፡ ትውልድ፡ መካከል የሆነውን፡ ታላቅ፡ ግፍ፡ እዪ፣ እነሆ፡ ከእነርሱ በሚበልጠው፡ ላይ፡ ተሰብስበው፡ ስም ለሞት ፍርድ፡ ሰጥተውታልና። ከዚህ፡ ሁሉ፡ በኋላ፡ ክርስቶስ፡ በመስቀል ላይ፡ እንደሆነ፡ ነበር፣ የመቶ፡ አለቃውን በዕውነት፡ ይህ፡ ሰው፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡ ብሎ፡ አመነ፤ እሊህ፡ ተአምራቶቹ በሁሉ፡ ዘንድ፡ ታመኑ። ፳፣ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ሳለ ምዕመናን ሁሉ፡ በአንድነት፡ አለቀሱለት። ስለጌታ፡ ስቅለት፡ ከሄሮድስ፡ ዘንድ ወደ መጣው፡ የመቶ፡ አለቃ፡ ጲላጦስ ልኮ አስመጥቶ፡ ወደ፡ ቤቱ፡ አስገብቶ፡ ወንድሜ ሆይ፡ ይህን፡ ጸድቅ፡ ሰው፡ አይሁድና ሄሮድስ ያደረጉትን፡ አየህን? ይህ፡ ሁሉ ተአምራት በምድር፡ እስኪሆን፡ ድረስ፡ በግፍ ሰቀሉት። ወንድሜ፡ ሆይ፡ በእውነት፡ እነግርሃለሁ፤ እነዚህ፡ ከፋቶች፡ ሁሉ፡ የተፈጸሙት፡ በሄሮድስ፡ ምክር፡ እንጂ፡ በእኔ፡ ፈቃድ፡ አይደለም፤ እኔ፡ እንዳይሞት፡ ልተወው፡ ወደድኩ፤ ነገር፡ ግን፡ ሄሮድስ፡ በዚህ፡ ደስ፡ እንደማይለው፡ ባየሁ፡ ጊዜ፡ ይሰቅሉት፡ ዘንድ፡ ለአይሁድ፡ ሰጠኋቸው፡ እንጂ። ተመልከት፡ አሁን፡ ለእግዚአብሔር፡ ስለ፡ ሰቀልነው፡ ልጄ፡ ምን፡ ብድርን፡ እንከፍላዋለን፡ አለው፣ የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ፡ ከጲላጦስ፡ ጋር፡ ደሙ፡ በሄሮድስና፡ በካህናት፡ አለቆች፡ ላይ፡ ነው፣ እያሉ፡ መራራ፡ ልቅሶ፡ አለቀሱ። በዚያን፡ ጊዜ፡ ጲላጦስ፡ ልኮ፡ የካህናት፡ አለቆች፡ ቀያፋና፡ ሐናን፡ ወደ፡ ጉባዔው አስጠርቶ፡ እናንተ፡ በግፍ፡ ደምን፡ የምትጠጡ፡ ተኵላዎችና፡ ቀበሮዎች፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ወደ፡ ሞተው፡ የናዝሬት፡ ሰው፡ አሁን፡ ተመልከቱ፣ ደሙም፡ በእናንተና፡ በልጆቻችሁ፡ ላይ፡ ይሁን፡ አላቸው። እነርሱግን፡ ደስ፡ በመሰኘት፡ እያፌዙ፡ ደረታቸውን፡ እየደቁ ፊታቸውንም፡ እየነጩ፡ እስከ፡ ሽህ፡ ትውልድ፡ በእኛና፡ በልጆቻችን፡ ላይ፡ ይሁን፡ ኣሉ። እነርሱም፡ እንደ፡ ሕጋችን፡ ፈጽመናል፡ ስለምን፡ እንፈራለን? እንደነግጣለን፡ አሉት። ጲላጦስም፡ የሐሰት፡ ሕግ፡ ፈጸማችሁ፡ እንጂ፡ ይህ፡ ሕግ አይደለም፡ ኣለ፤ አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባልከው፡ እነሆ፡ ልብሶችሁ፡ ተቀደዋል። ሕጉም፡ ሊቀ፡ ካህናቱ፡ ልብሶቹን፡ በቀደደ፡ ጊዜ፡ ከክህነት፡ አገልግሎት፡ ይከልከል፡ ይላል። ቀያፋም፡ እኔ፡ ልብሴን፡ የቀደድኩት፡ እርሱ፡ በእግዚአብሔርና፡ በሕጋችን፡ ላይ፡ የስድብ፡ ቃል፡ ስለ፡ ተናገረ፡ ነው፡ ብሎ፡ መለሰለት። ጲላጦስ፡ እንግዲህ፡ በሊቀ፡ ካህናት፡ ሥርዓት፡ ወደ፡ መቅደስ፡ ኣንተ፡ እንድትገባ አልፈቅድልህም፡ እንደ፡ ሕግ፡ አፍራሽ፡ እንጂ ። አንተ፡ ወደ፡ መቅደስ፡ እንደገባህ ሌላው ቢነግረኝ፡ ቸብቸቦህን፡ ከአንተ ላይ እቆጣለሁ፡ አለው። ቀያፋም፡ ከአንተ፡ በፊት፡ ብዙ ጊዜ አልፎአል፤ ብዙዎችም፡ ሹማምንት የሚቀድሙህ፡ አሉ፤ እስከ፡ ዛሬ፡ የካህናት አለቆችን፡ ወደ፡ መቅደስ መግባትን፡ የከለከላቸው፡ አለን፡ ብሎ፡ መለሰለት። ይህንም፡ ያለ፡ የሄሮድስን፡ ሥልጣን በመተማመን፡ ነበር፤ ጲላጦስም፡ ይህን፡ ሁሉ ተአምር፡ ስታይ፡ ከሕዝቡ፡ ሁሉ፡ ጋር፡ አሁንም፡ ልብህ፡ አያምንምን፡ አለው። ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባለ፡ ቀያፋም፡ አንተስ፡ በዚች፡ አገር፡ አዲስ፡ ተክል፡ ነህ፣ ይህ፡ ምልክት፡ የሆነበትን፡ ነገርና፡ የተደረገውን፡ ኣታውቅም። ይህ፡ ይቅርታ፡ የሚደረግበት፡ የመጋቢት ወር፡ ፀሐይና፡ ጨረቃ፡ ዑደታቸውን፡ ፈጽመው፡ ተራክቦ፡ የሚያደርጉበት፡ ሲሆን፡ በዚሁ፡ ወር፡ መሠርያኖች፡ ጨረቃን፡ እንደ፡ ደም፡ የሚሆንበትን፡ ያደርጋሉ፤ የፀሐይንም፡ ብርሃን፡ በሥራይ፡ ኃይል፡ ይስባሉ። የአግዓዝያንን፡ ተግባር፡ ይመረምራሉ፤ የሥንዴውን፡ የወይንንና፡ የዘይትን፡ ፍሬዎች፡ በማዘጋጀት፡ ይህን፡ የመሰለውን፡ ቀያፋ፣ በሐሰት፡ ይናገር ነበር። ጲላጦስም፡ ከወንበሩ፡ ላይ፡ ተነሥቶ፡ አንተ እርሱን፡ ከመጥላትህ፡ የተነሣ፡ በዓለም ሁሉ፡ ላይ፡ መዐትን፡ ልታመጣ፡ ትወዳለህ ብሎ፡ ከቆዳ፡ በተሠራ፡ በደረቅ፡ በትር ደበደበው፤ ጽሕሙንም፡ ነጨው።
Show all...
👍 18 9🙏 5😍 1
የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ ከሕይወት ይልቅ፡ ሞት፡ ይገባሃል፤ እያሉ፡ ያንን ሊቀ ካህናት፡ ይዘልፉት፡ ነበር። በአንድነት፡ ከዘለፉትም፡ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ፡ ይዘውት፡ ሄዱ፤ ወደ ንጉሥም ይወስዱት፡ ዘንድ፡ ተስማሙ። የድንግል፡ ማርያም፡ በረከት የተወዳጅ ልጅዋም፡ ምሕረት፡ ከእኛ፡ ጋራ፡ ለዘላለም ይደርብን፤ አሜን። (#ግብረ_ሕማማት)
Show all...
👍 32 22🙏 17
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡ ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡ ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" /ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
Show all...
35🙏 8💔 6👍 4
#ዓርብ_ስድስት_ሰዓት_የሚነበብ (የስምዖን ዐምዳዊ ጸሎት) ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ በዕንጨት መስቀል፡ ላይ፡ ራቁትህን፡ የሆንክ፡ ጨለማን ከለበሰና፡ ስሕተትን፡ ከሚያመጣ፡ ሰይጣን መንፈስ፡ ለየኝ። በኃይልህ፡ እታደስ፡ ዘንድ፡ በጥበብህም፡ እመገብ፡ ዘንድ፡ የሕይወት፡ ሐር፡ ልብስን፡ አልብሰኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን፡ የብርሃን፡ መጐናጸፊያ፡ የምታጐናጽፋቸው ኃይልንም የምታስታጥቃቸው በመስቀል፣ ላይ፡ ራቁትህን፡ ቆምክ። ልቡናዬን፡ ከፍጹም፡ ድንቁርና፡ ጨለማ፡ አርቅ፣ (አንፃ)፣ በልቤና፡ በሕዋሳቴ፡ ውስጥም፡ የጌትነትህን፡ ብርሃን፡ አብራ፤ ከምድራዊ፡ ሀሳብና፡ ጠባይ፡ ተለውጠው፡ ከሰማያውያን መላእክት፡ ጋራ፡ ያመሰግኑህ፡ ዘንድ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ የከበሩ፡ እጆችህን፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ የዘረጋህ፡ ፍቅርህ፡ በውስጡ፡ ያድርበት ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ እንዲከፈት፡ አድርገው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ መላእክትን ከእሳት፡ የፈጠርካቸው፡ ሰማይንም፡ እንደ ድንኳን፡ የዘረጋህ፡ የምድርንም፡ ስፋቷን ያበዛህ። በበላይዋም፡ ዓለማተ፡ ሰማይን፡ እጅግ፡ ከፍ አድርገህ፡ የፈጠርክ፡ ከበታችዋም፡ እጅግ ጥልቅ ያደረግህ፡ ዙሪያዋንም፡ በባህር፡ የከበብህ ትእዛዝህም፡ ምድርን፡ በባሕር፡ ላይ፡ ጸንታ እንድትኖር፡ ያደረጋት፡ በውስጥዋ፡ ያለውንም ሁሉ። በመስቀል፡ ላይ፡ እንዴት፡ እጅህን ዘረጋህ? እንዴትስ፡ በቀኖት፡ ተቸነከርክ፡ ወዴትስ ወረድክ? ለሞት፡ እስክትደርስ፡ ድረስ፡ የአዳምን፡ ማዳን፡ እንደምን፡ ወደድክ። አፍና፡ አንደበት፡ ካላቸው፡ ለጌትነትህ፡ ምስጋና፡ ማቅረብ፡ የሚችል፡ ማን፡ ነው። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ፍቅርህን፡፡ በልቤ፡ ውስጥ፡ ቅረጽ፤ ከክፉ፡ ማሰሪያ፡ ፍታኝ፤ ለዘላለም፡ ጸንቶ፡ በሚኖር፡ ፍቅርህም፡ እሰረኝ። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ፡ ማሕየዊ፡ መስቀልህን፡ አቅፌ፡ ከእርሱ፡ የሕይወትና፡ የመድኃኒት፡ መዐዛ፣ አሸት፡ ዘንድ፡ ስጠኝ። በልቡናዬም፡ ውስጥ፡ ንጹሕ፡ ደምህ፡ ይውረድ፤ ንጹሕ፡ መሠዊያ፡ ይሆን፡ ዘንድ፡ ልቡናዬን፡ ያክብረው፤ በውስጡም፡ የሕይወትን፡ መንፈስ፡ ያንቀሳቅስ፤ የሕይወት፡ መንፈስ፡ አንተን፡ ይቀበል። ጌታዬ፡ ኢየሱስ፡ ክርስቶስ፡ ሆይ በመስቀል ላይ፡ መጻጻንና፡ ሐሞትን፡ የጠጣህ ከታላቁ፡ ንጹሕ፡ ፍቅርህ፡ አጠጣኝ፤ ከመራራው፡ ሞተ፡ ነፍስም፡ አድነኝ። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ)
Show all...
35🙏 11👍 6
ጴጥሮስ ሆይ እስከ ፈራህና ፈጥነህ እስከ ካድክ ድረስ ለእኔ ነው ትል ዘንድ በድጋሚ ሌላ መስቀል አላየህ፣ እንደ ብረትም የተሳለ አንደበት ሰጥቶህ ነበር። ጴጥሮስ ሆይ አንተስ ያለ እሳትና ያለእንጥረኛም ፈጽመህ አቀለጥከው። ጴጥሮስ ሆይ ከሰው ሁሉ ለገጽህ ግርማ ሰጥቶህ ነበር፤ ብርሃናቸው የማይጠፋ ዓይኖችን የሰጠህ ሲሆን ስለጌታህ አንዲት ጥፊ ትቀበል ዘንድ ዛሬ አልታገሥክም። ጴጥሮስ ሆይ የመንግሥት ሰማያትን መክፈቻ የሰጠህን ልጄን በካድከው ጊዜ አልፈራህም፤ በሊቀ  ካህናቱም ግቢ አልታገሥክም፤ በእርሱ ፈንታም ለዓለሙ ሁሉ የታመነ ጠባቂ አድርጎ ሾመህ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ ጌታህ አንድ ጊዜ እንኳ ጥቂት መከራ አልተቀበልክም። ጴጥሮስ ሆይ ለዓለሙ ሁሉ አባት ትሆን ዘንድ ሾመህ፤ አንተ ግን ለልጄ የወንድማማችነት ፍቅርን አላደረግህም። ጴጥሮስ ሆይ አምላካዊ እጁን በራስህ ላይ ጫነ፤ አንተ ግን ከመካድህ በፊት ዛሬ በራስህ ላይ የእሾህ አክሊል ይጭኑብህ ዘንድ አልፈቀድክም። ጴጥሮስ ሆይ ልጄ ለአንተ ወዳጅህ እንጅ እንደ ጌታህ እንዳልሆነ አስብ። ልጄን እንደዚህ ትክደው ዘንድ ለአንተ አግባብ ኣይደለም። ጴጥሮስ ሆይ ከእኛ ጋራ ይህ ሁሉ ድካም እንዳገኘው እንደ አባቴ ዮሴፍ ብትሆን ኖሮ። ጴጥሮስ ሆይ እንደ እርሱ ወደ ኄሮድስ ቢጎትቱህ በግብጽ ምድርም ከእኛ ጋራ መከራ ተቀባይ ብትሆን እንደ እርሱ መታገሥ ባልቻልክም ነበር እንጃ። አባቴ ጸድቁ ዮሴፍ ሆይ በአጥንቶችህ ላይ የሰማይ ጠል ይውረድ። ነፍስህም ዕፀ ሕይወትን ትመገብ፤ ከእኛ ጋራ ታግሠህ መከራ፡ ስትቀበል እንደ ጴጥሮስ ልጄን አልካድከውምና። ጴጥሮስ ሆይ ወደ ፍርድ አደባባይ አልወሰዱህ በባለ ሥልጣኖችም ፊት አላቆሙህ ፈጥነህ ጌታህን ካድከው። ድንግል በዮሐንስ ቤት እንደዚህ ስታለቅስ ሳለ ዮሐንስ እያለቀሰ መጣ እርሷንም እያለቀሰች አገኛት። ድንግል እመቤታችንና ዮሐንስም ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርስ በርሳቸው እየተላቀሱ ሁለቱም አብረው ነበሩ። ዮሐንስም ድንግልን እናቴ ሆይ ጌታችንን ጴጥሮስ ስለካደው አታልቅሺ አላት፣ አሳልፎ እንደ ሰጠው እንደ ይሁዳ ነውር የለበትምና። በእራት ጊዜ ጴጥሮስ ሆይ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ሲለው መምህሬን ሰምቻለሁና። ጴጥሮስም እንደዚህ በአንተ ላይ ይደረግ ዘንድ አይገባም፤ ጌታዬ ፈጣሪዬም እስከ ዘላለሙ ድረስ እልክድህም መሞት ይሻለኛል፤ እንደዚህም በእኔ ላይ አይሆንም፤ ስለ አንተ ነፍሴን አሳልፌ እሰጣለሁ እንጂ። ከዚህ ቀደምም መምህራችን ጌታ መምህሬ ጴጥሮስን ሦስት ጊዜ ሲገሥፀው ሰምቻለሁ። ሰይጣን ባለጋራዬ ወግድ ከኋላዬ ዕንቅፋት ሁነህብኛልና ሰው ሰውኛውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና አለው። አሁንም እመቤቴ እናቴ ሆይ ስለ አባቴ ጴጥሮስ መካድ አታልቅሽ ለኃጢአተኞች ሁሉ ለንስሐ ምሳሌ ነውና። በቃሉ ያመነውን የጌታችንን ቃል አስተባብሎ ነበርና። በሐዘኗ የሚገኝ በረከት ከዐይንዋ የፈሰሰ የዕንባ ውኃ ጸጋ ለዘላለሙ ከእኛ ጋራ ይኑር አሜን። (#ግብረ_ሕማማት_ዘዓርብ_ሦስት_ሰዓት)
Show all...
27👍 4🙏 3
ቤተ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ: #የማርያም_ሐዘን (#ዓርብ_በሦስት_ስዓት_የሚነበብ አባ፡ ሕርያቆስ፡ የደረሰው፡ ድርሳን፡ ይህ፡ ነው።) ወዳጆቼ ሆይ የአባቶች አለቃ የያዕቆብ ልቅሶ፤ ዛሬ ታደሰ አለ። በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ለወለደችው ለተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። መከራ ስለተቀበለችበት ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስም። የድንግልና ጡቷን ለእጠባችው ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በቤተልሔም በበረት ስለወለደችው ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። በማኅፀንዋ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ለተሸከመችው ተወዳጅ ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ ወልዳ ላልሳመቻቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ፤ እንደ ሰው ሁሉ በብብቷ ለተሸከመችው ልጇ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቦታ ወደቦታ ይዛ ላልተሰደደችባቸው ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። ከሀገር ወደ ሀገር አዝላ ለተሰደደችበት ልጅዋ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። ከቶ መቃብራቸውን ላላአየች ልጆች ራሔል የምታለቅስ ከሆነ። በአንድ ልጅዋ መቃብር ደጃፍ ላይ ድንግል ማርያም ለምን አታለቅስ። የባለ መልካም ጽሕም ሽማግሌ የያዕቆብ ልቅሶ በብላቴናይቱ ድንግል ዘንድ ዛሬ ታደሰ። ወንድሞቹ ባሰሩት ጊዜ ያዕቆብ ወደ ዮሴፍ አልተመለከተም። ድንግል ግን ልጅዋን በዕንጨት መስቀል ላይ ተቸንክሮ አየችው። ዮሴፍ በሰፊ ጉድጓድ ውስጥ ሳለ ያዕቆብ በላዩ፡ ያለቅስ ዘንድ ወደ ዮሴፍ አላየም። ድንግል ግን በአይሁድ ጉባዔ መካከል ተሰቅሎ ልጅዋን አየችው። ዮሴፍን ወንድሞቹ ልብሱን ገፈው ሲያራቁቱት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን በጎ ምክር በሌላት በአይሁድ መካከል ልብሱን ተገፎ ራቁቱን ሁኖ አየችው። ወንድሞቹ ዮሴፍን በሃያ ብር ሲሸጡት ያዕቆብ አላየም። ድንግል ግን ይሁዳ ልጅዋን በሠላሳ ብር ሲሸጠው አየች። አራዊት ባልቀደዱት ልብስና በሌላ ደም ላይ ያዕቆብ አለቀሰ። አምላካዊ ደም ግን ድንግል ማርያም ስለእርሱ በላዩ የምታለቅስበት በቀራንዮ አለት ላይ የፈሰሰው ነው። ድንግል ግን ዛሬ ያየችው ልጅዋን ያለበሱትን ሌላ ልብስ ነበረ፤ የራሱን ልብስ ግን እርስ በርሳቸው ተካፈሉት። የዮሴፍ ወንድሞች ወንድማቸው ዮሴፍን በሸጡት ጊዜ አለቀሱ ተጸጸቱ። የእስራኤል ልጆች ግን ጌታቸውን በሸጡት ጊዜ አላለቀሱም፤ አልተጸጸቱም። የያዕቆብ ልጆች ወንድማቸው በነገሠ ጊዜ ተደሰቱ። አይሁድ ግን ጌታቸው ከሙታን ተለይቶ በተነሣ ጊዜ ደስ አላላቸውም። ድንግል ሆይ፤ በእውነት በልጅሽ መቃብር ላይ ልቅሶሽ ጣዕም ያለው አሳዛኝ ነበረ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምን ታደርጊያለሽ? ብለው የልጅሽን መሰቀሉን በነገሩሽ ጊዜ በመላእክት መካከልም ቃልሽ ያማረ ነበር። እነሆ ልጅሽን በመኰንኑ ፊት አቁመውታል፤ የአይሁድ ሊቃነ ካህናትም ያሰቃዩታል፣ ያቃልሉታል፣ ማርያም ሆይ ምን ታደርጊያለሽ? እነሆ ልጅሽን በፍርድ አደባባይ መካከል ልብሱን ገፈው እያራቆቱት ነው። የኢያቄም ልጅ ማርያም ሆይ ለምን ተቀምጠሻል? ምንስ ታደርጊያለሽ? እነሆ በኢየሩሳሌም ሜዳ የሚሰቀልበትን ግንድ ብቻውን ተሸክሞአል፤ አንድ እንኳ ወደ እርሱ የሚቀርብ የለም። የሐና ርግብ ሆይ ለምን ተቀመጥሽ? የምትሰሪውስ ምንድን ነው? እነሆ ልጅሽን ሰቅለውት በቀራንዮ ቦታ ቁሞአል። የዳዊት ዘር ሆይ ልጅሽን በመስቀል ላይ ለምን ከፍ ከፍ አደረጉት? እመቤት ድንግል ሆይ በዮሐንስ ቤት ዛሬ ልቅሶሽ በእውነት ጣዕም ያለው ነበረ እንዲህ ስትዪ። ወዮ ለዚህ መራራ ወሬ ነጋሪ ለኢዮብና እስራኤል ለተባለ ያዕቆብ ከአረዷቸው መርዶ የመረረ ነው። ዛሬ ወደእኔ ለሚመጣ ለዚህ ለክፉ ወሬ ወዮ። ልጄ ሆይ አገሩን በኢቃጠሉ ጊዜ ለሎጥ ከአረዱት መርዶ ያስጨንቃል። በእኔ ላይ ለደረሰው ለዚህ አስጨናቂ ስብከት ወዮ። ልጄ ሆይ ስለ ኃያላነ እስራኤል ሞት ከአረዱአቸው መርዶ ይበልጣል። በዚህ በክፉ ወሬ ወደእኔ ለመጣው ለዚህ ወሬ ነጋሪ ወዮ። ልጄ ሆይ እነሆ ስታረጋጋኝ ሠላሳ ዓመት ይሆናል፤ ልገሥጽህም አልተቻለኝም። ዛሬ ወደ እኔ ወሬህ እስከመጣ ድረስ ወጥተህ እስከምትገባ አንዲት ሰዓት እንኳ አላመንኩህም። ልጄ ሆይ ለሐዘኔ ሁሉ ጥንቱ ሰሎሜ ናት፤ እኔ ዳኛውን አየው ዘንድ ከቤቴ አልወጣም፤ በፈራጁም ፊት አልቆምም። ሌባውን ራሱን ሲቆርጡት ሽፍታውንም ይገድሉት ዘንድ ሲፈርዱበት አላየሁም። ከቶ ቀራንዮን አላየሁትም፤ የጎልጎታንም ቦታ አላውቅም፤ ሁል ጊዜም በሚጣሉበት ቦታ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ክፉ የሆነ ፍርድ አላየሁም፤ በፍርድ አደባባይም ከቶ ለዘላለሙ አልቆምኩም። ልጄ ሆይ ያደረኩብህን ግፍ አላውቅም እኔም በዮሐንስ ቤት ነበርኩ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በሊቀ ካህናቱ በሐና ግቢ የተቀበልከው ግፍ ወሬው መራራ ነው። ልጄ ወዳጄ ሆይ ዛሬ ከእኔ ላይ ነጻነቴን አስወገድክ፤ ስለልደትህ በናዝሬት መልካም የምስራች ነገሩኝ። ዛሬ ግን በኢየሩሳሌም ይህችን ክፉ መርዶ አረዱኝ። በዮሴፍ ቤት መልካም ዜና በዮሐንስ ቤት ግን የሞት ዜና መጣልኝ ። ልጄ ወዳጄ ሆይ እኔ በልቤ ደስ እያለኝ ተቀምጨ ነበር። በየዕለቱ ፋሲካ ደርሶአል በዓሉን እናከብር ዘንድ ወደሀገራችንም እንመለሳለን እያልኩ ነበር፤ የዚህ ዓይነት ፋሲካም ደረሰኝ። ልጄ ወዳጄ ሆይ በእንባና በሐዘን በዓሌ ወደ ልቅሶ ተመለሰ፤ ፋሲካየም ወደልብ ሐዘን። በዮሐንስ ቤት ሳለች ስለ ልጅዋ የመከራ ወሬ በመጣበት ጊዜ ድንግል እመቤታችን ይኸንን ልቅሶ ታለቅስ ነበር። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ከንጹሐን ሐዋርያት አንድ ፈለገች አላገኘችም፤ አይሁድን ከመፍራት የተነሳ ሁሉም ትተውት ሸሽተዋልና። ከእርስዋ ጋራ ይሔድ ዘንድ ስለ ጴጥሮስ መረመረች፤ እርሱማ የካህናት አለቆችን ከመፍራቱ የተነሳ ልጅሽን ከቶ አላውቀውም አለ፤ ሒዶም ተሸሽጓል አልዋት። ዳግመኛም ስለ ጌታችን ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ ለያዙት ሰዎች በተራራ ላይ ልብሱን ትቶ እንደ ሸሸ ነገርዋት። እንድርያስንም ፈለገችው፤ እርሱስ ወደ ከተማ አብሮት አልመጣም አልዋት፤ እንደዚሁ ቶማስም ሽሽቶ ሔደ። ስለ በርተሎሜዎስም ጠየቀች፤ እርሱም ከወንድሞቹ አስቀድሞ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ፊልጶስም ጠየቀች፤ እርሱም የፋናዎችን ውጋገንና መብራቶችን ባየ ጊዜ ፈርቶ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ዮሐንስ ወንድም ስለ ያዕቆብ መረመረች፤ አንድ ጊዜ ስንኳ እንዳልቆመ ነገርዋት። ስለ ማቴዎስም መረመረች፤ እርሱም ግብር ስለሚቀበላቸው አይሁድንና የካህናት አለቆችን እጅግ ስለፈራ እነርሱም ስለሚጠሉት በሌሊት ጨለማ እንደሸሸ ነገርዋት። ስለ ሁሉም መረመረች፤ አብሮ ወደ ቀራንዮና ወደጎልጎታ ከሔደው ዮሐንስ በቀር አንድም አላገኘችም። ድንግልም ከልጅዋ ደቀ መዛሙርቶች ከዮሐንስ በቀር አንድ እንኳ ባለማግኘቷ እንደገና ዳግም ወደ ጽኑ ልቅሶና ሐዘን ተመለሰች። እንዲህ እያለችም አለቀሰች፦ ልጄ ወዳጄ ሆይ ወዮልኝ ወንድሞችህ ሸሹ ትተውህም ተሸሸጉ። አባቴ ጴጥሮስ ሆይ ጌታህን እንዳትክድ ሁልቀን እጠራጠርህ ነበር፤ ስለ እርሱ ወርቅ ብር አልሰጠህ ለምን ጌታህን ፈጥነህ ካድከው? ስለርሱ መርከብ ወይም ቀዛፊ አልሰጠህም፤ መምህርህንና ጌታህን ዛሬ ለምን ካድከው? ስለርሱ ምንም አልሰጠህም ወንድ ልጅም ቢሆን ወይም ሴት ልጅ። ጴጥሮስ ሆይ ስለ እርሱ ወንድምን ወይም ወዳጅን አልሰጠህም። ልጄን ለምን ካድከው? በዚህ ሁሉ ልብህ ለምን ቀላል ሆነ?
Show all...
👍 11 10🙏 1💯 1

55👍 28🙏 9