en
Feedback
الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ

Open in Telegram

​الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ ​እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
2 159
Subscribers
No data24 hours
+1817 days
+41530 days
Posts Archive
🤔✍️ ሀቅ ሀቅ ሀቅ💯
🤔✍️ ሀቅ ሀቅ ሀቅ💯

​رَبِّ هَبْ لِي مِن لَّدُن ذُرِّيَّةً طَيِّبَةً ۖ إِنَّكَ سَمِيعُ الدُّعَاءِ ጌታዬ ሆይ  ከአንተ ዘንድ ሷሊህ ንፁህ ዝርያን ስጠኝ አንተ ዱዓን ሰሚ ነህና ያአሏህ ምን ያማሩ አባትና ልጅ ናቸው ማሻአሏህ ተባረከሏህ ያአሏህ ....💦💦 የልጅን አባት መምረጥ 👆✅

أستغفر الله العظيم وأتوب إليه.
أستغفر الله العظيم وأتوب إليه.

🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺   #የታሪኩ_ርዕስ #በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"       #ክፍል_☞ #ሀያ_አራት(⓶⓸)_ ፣ ✍ #ፀሀፊ_ #አቡ_ኹዘይማ ...............☞ #ተስኒም ................ #ባለቤት_የሌለው_ስደት" የሴራው መጋረጃና የክብር መርገፍ በዚያ የብሎክ ሰቀቀንና የዝምታ ውርጭ ውስጥ ሆኜ፣ ነፍሴ መላ ስታጣና ሕሊናዬ እረፍት አጥቶ ሲባዝን፣ የተስኒምን የቅርብ ጓደኛ ለማናገር ወሰንኩ። "ምክንያቱ ምን ይሆን? ምን አጥፍቼ ነው የብሎክ ጽዋ የተጋተው?" ብዬ በባዕድ ስልክ ስማጸን፣ ጆሮዬ የሰማው ምስጢር ግን ከአይከል ክህደት በላይ ነፍሴን በቁሟ ቀበራት። ወንድነት ከዳኝ፣ ጉልበቴም ተብረከረከ። ነገሩማ እጅግ ረቂቅና የከፋ የሴራ ድግስ ነበር። ተስኒም እኔን እንደ ወንድ ሳይሆን፣ እንደ ሴታሴትና አጭበርባሪ አድርጋ እንድትቆጥረኝ ተደርጋ ኖሯል። የብሎኩ ምስጢር መሠረቱ እንዲህ ነው... ያቺ ተስኒምን በሸሪዓዊ መንገድ እንድታናግርልኝና የልቤን የሐላል ጥያቄ እንድታደርስልኝ በአማና የላክኋት የቅርብ እህቴ፤ ስለ እኔ ለተስኒም ስትነግራት በማይገባና ከመጠን በላይ በሆነ አነጋገር ታሞጋግሰኝ ነበር። ታዲያ ያቺ ልጅ ይህንን ያደረገችው በቅንነት አልነበረም፤ ከጀርባዋ የሴራ መርዝ አርግዛ ነበር። እኔንም እንደምትወደኝና ተስኒም ከእኔ ጋር በመሆኗ እድለኛ እንደሆነች አድርጋ፣ ድምጯን እንኳ እንዳታሰማ በስልክ ጽሑፎች መካከል የቅናት ድራማዋን አቀናብራ ጥላን ጠፋች። ስለ እኔ ብዙ የማይረባ ነገር ፈለሰፈች። "በአማና የላክኋት - የቅርብ ወዳጄ፣ በቅናት ታውራ - ሆነችብኝ አራጅ፤ ክብሬን ልታጸና - በደጅ ያቆምኳት፣ ወንድነቴን ገፋችው - ወደ ውርደት ገደል ታች።" .... ተስኒም ይህንን ነገር ገና ከጅምሩ ዳግም ልታጠናውና ልታጣራው ወስና ነበር መሰለኝ። ከእህትየው ጋር በስልክ ሲጻጻፉና ሊያወሩ የሞከሩትን ማስረጃዎች ሁሉ በቁም ነገር ስታከማች ቆይታለች። ቀናቶች ካለፉ በኋላ፣ ተስኒም ጋር ስልኳ ላይ የነበረውን መረጃ ስታጣራ፣ ያቺ ልጅ  ጋር ስታወራ ነበረውን መረጃ ይዛለችና  የቀዳችው ፋይል ውስጥ የእኔ ድምፅ መግባቱን አረጋግጣለች። ያኔ... ተስኒም በድምጿ ግለት እንዲህ ብላ አሰበች፦ "ይኸው ራሱ ነው! ሴት መስሎ በሌላ ስልክ ሲያመቻቸኝና ሊያጠምደኝ የነበረው አጭበርባሪ!" ብላ ጉድ አገር ዘረገፈች። ሀቂቃ ተዋረድኩ! በጣም ከፋኝ፣ በጣም አዘንኩ፣ በእጅጉም አፈርኩ። ያ በበረሃው ጥይት መሃል በክብር የቆመው፣ በጅቡቲ ማዕበል ያልተንበረከከው ወንድነቴ፣ ዛሬ በሴቶች የቅናትና የሴራ ተንኮል መሃል ወድቆ "ሴት መስሎ የሚጀነጅን አጭበርባሪ" ተባልኩ። ?ይህ ብቻ አይደለም፤ ተስኒምን በጓደኛዋ በኩል ለማናገር መሞከሬ ይበልጥ አስቆጥቷታል። ምስጢር የማልጠብቅ፣ ክብረ-ቢስና አጸያፊ ወንድ አድርጋ ሳለችኝ። በሕይወቴ መቼም የማይጠፋውን፣ ልብን የሚያደማውን መራራ መልእክት በጓደኛዋ በኩል እንዲህ ስትል ላከችልኝ፦ "ጥቅም የሚያሳድድ፣ ምስጢር የማይጠብቅን አጭበርባሪ ወንድ እንዴት ብዬ አምኜ የቤቴ ምሰሶ፣ የልጆቼ አባት አደርገዋለሁ? የራስህን መንገድ ምረጥ!" ወያሳቲር! ምንም እንኳ ጥፋቱ በውስጡ የኔነት ሰበብ ቢኖረውም፣ ተስኒም ግን ለአእምሮ የሚከብዱ አላስፈላጊ ቃላትን ሰንዝራብኝ በሯን ጥርቅም አድርጋ ሄደች። መረረኝ! ሰው ሁሉ አስጠላኝ። ከሕይወቴ ፈተናዎች ሁሉ የከፋውና ነፍሴን ያሰቃያት ይኸው ክስተት ነበር። ሰው ትዳር ይሆንልኛል ብሎ፣ መከራን እየደራረበ፣ የየመንን ጅራፍና የራጎን ሰቆቃ እያለፈ ሲጎርስ፤ መጨረሻው ግን እንዲህ ባለ የውርደት ቅንብር መበላሸቱ የቁም ሞት ነበር። "እውነት መስሎኝ የሮጥኩት - ያ የሐላል መንገድ፣ በውሸት ተተብትቦ - ሆነብኝ ስደት፤ ተስኒም በሯን ዘጋች - በቁጣ ማዕበል፣ እኔም ቀረሁኝ - በጸጸት ስቃጠል። ".... በመጨረሻም... ይህች ብዕሬ መልእክቴ ለተስኒም ትድረስ። እመኚኝ ተስኒም፤ አንድ ቀን ፨ ይህ እውነተኛ የብዕሬ ትንፋሽ አንቺ ጋ መድረሱ አይቀርምና ። የአሏህ ፈቃድ ከሆነ በሒወት እያለሽ ከደረሰችሽ 🚨 እኔ ካለሁበት የዱባይ ግለትና የሕሊና ቁስል ሆኜ አፍው ብዬሻለሁ! አንቺ እኮ በማታውቂው የሴራ ድግስና በሐሰት ወሬ ነው ልብሽ ተሰብሮ የፈረድሽብኝ። !እኔ ደግሞ በገዛ እጄ፣ ሰው ትሆነኛለች ብዬ አማና ጥዬ ባመጣኋት ያቺው እህቴ ሰበብ ነው ክብሬ ረክሶ የተዋረድኩት። ደሞ አንድ እውነትን በልብሽ ማኅደር ላይ አውጪና አውርጂው፤ አላህ ስላልወሰነው እንጂ መጀመሪያ እኮ የይቅርታዬን ጽዋ ተቀብለሽኝ፣ ልንተያይ ቀጠሮ ይዘን ነበር። እኔና አንቺ በአንድ ሐላል ጎጆ እንድንጣመር አላህ ስላልፈቀደውና ስላልጻፈው ነው ይኸው የፈተና ተራራ በመካከላችን የተጋረጠው። እመኚኝ... አላህ ካለፈው ወንጀላችንና ስህተታችን ሁሉ ይቅር ይበለን። ውድ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! እኔ እዚህ የውርደትና የፈተና ጥግ ላይ ደርሻለሁ። የኔ ድርሰት እዚህ ጋር በጸጸት እሳት ተለብልቦ ማቆሚያውን ይፈልጋል። እናንተስ ከእኔ ስህተት ምን ትማራላችሁ? የማሳረጊያ ጥሪ፦ የነፍስ መስታወትና የተውሂድ ዋስትና  በአላህ ስም እጅግ በጣም ርኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው። በሚል ክፍል (❷❺)  ይቀጥላል፣፣

አላቹህ ወይ ?🕶🕶 ቀጣይ ክፍል (24 ) እለቃለሁ አፍዋን መታረስቸው ነው ቀጣይይይይ የምትሉ መጣ ጠይብ
አላቹህ ወይ ?🕶🕶 ቀጣይ ክፍል (24 ) እለቃለሁ አፍዋን መታረስቸው ነው ቀጣይይይይ የምትሉ መጣ ጠይብ

👳‍♀️በኦንላይን ገንዘብ ስሩ🧕 🏆 የሚያስፈልገው👇🏽 ✅ስልክ እና ዳታ ብቻ ✅ join ማለት እንዳትረሱ 💢አስታውሱ❗️ምንም የምትከፍሉት ገንዘብ የለም❌ 🖥ወላሂ የእውነት ማስታወቂያ ነው ተቀ
👳‍♀️በኦንላይን ገንዘብ ስሩ🧕 🏆 የሚያስፈልገው👇🏽 ✅ስልክ እና ዳታ ብቻ ✅ join ማለት እንዳትረሱ 💢አስታውሱ❗️ምንም የምትከፍሉት ገንዘብ የለም❌ 🖥ወላሂ የእውነት ማስታወቂያ ነው ተቀላቀሉ🖥

ፈጥኖ የመለስ Add የሚለውን በመንካት ምርጥ ቻናል ይሸለም ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• የመግሪብ ሶላት ስንት ረከዓ አለው ??

⚠️ ሶስተኛ ዙር የምዝገባ ፕሮግራም ⚠️ 🔋✅ ​የዕውቀት ጉዞዎን በ«ዙል ቢጃደይን» ይጀምሩ! ​ንፁህ የሆነችውን የሰለፎች መንገድ በቅደም ተከተል (ሲልሲላ) ለመማር ለሚጓጉ በሙሉ፤ በቤታችሁ ሆናችሁ
⚠️ ሶስተኛ ዙር የምዝገባ ፕሮግራም ⚠️ 🔋✅ ​የዕውቀት ጉዞዎን በ«ዙል ቢጃደይን» ይጀምሩ! ​ንፁህ የሆነችውን የሰለፎች መንገድ በቅደም ተከተል (ሲልሲላ) ለመማር ለሚጓጉ በሙሉ፤ በቤታችሁ ሆናችሁ ተጠቃሚ የምትሆኑበትን የ ONLINE መድረሳችንን ይቀላቀሉ። ​በ«ዙል ቢጃደይን የ ONLINE መድረሳ» የሚቀሩ ኪታቦች ዝርዝር ~ኢን ሻ አላህ~ ​🕋 ▬ተውሒደል ኡሉህያ ▬ 🕋 🔴 ኹዝ ዐቂደተክ 🔴 ሠላሠቱል ኡሱል 🔴 ቀዋዒዱል አርበዕ 🔴 አል ዋጂባት 🔴 ኪታቡ ተውሒድ 🔴 ከሽፉ ሹብሀት 🔴 ማዕና ላኢላሀ ኢለላህ ​🌙 ▬ አስማእ ወሲፋት ▬🌙 🔵 ሉመዓቱል ኢዕቲቃድ 🔵 ዐቂደቱል ዋሲጥያ 🔵 መንዙመቱ ሱለሚል ኡሱል 🔵 ላምየቱ ኢብኒ ተይሚያህ 🔵 ሀኢየቱ ኢብኒ አቢ ዳውድ    ​🛤 ▬▬ መንሀጅ ▬▬ 🛤 🟢 ሚን ኡሱሊ ዐቂደቲ አህሊሱነቲ ወልጀመዓ 🟢 ሸርሑ ሱና 🟢 ኩን ሰለፍያ 🟢 ሚንሀጁ ፊርቀቲ ናጂየቲ   ​⚖️ ▬▬▬ ፊቅህ ▬▬▬⚖️ 🟣 መቶ ሀዲስ 🟣 አርበዑን አን-ነወዊያ 🟣 ሹሩጡ ሶላት 🟣 ኡምደቱል አሕካም 🟣 አዱሩሱል ሙሂማ 🟣 ሚንሀጁ ሳሊኪን    ​📖 ▬▬▬ ሲራ ▬▬▬ 📖 🔶 ኡርጁዘቱል ሚኢያ 🔶 ኹላሶቱ ኑሪል የቂን 🔶 ሲረቱል ሙስጠፋ ​ 🛡 ▬▬አዝካር ▬▬🛡 💎 አዝካሩ ሶባሕ ወል መሳዕ (ሊሸይኽ ረስላን - ከሒፍዝ ጋር) 💎 ሂስኑል ሙስሊም (ከሒፍዝ ጋር)    ​🚨 ማሳሰቢያ: ① ሁሉም ኪታቦች ሲቀሩ ተስሚዕ ማድረግ ግዴታ ነው።
ለሌሎች ሼር አድርግ
​👉 ለመመዝገብ: @Ansi8800 👉 የቴሌግራም ግሩፓችንን ለመቀላቀል: https://t.me/zul_bijadeyn_online_medresa ​አላህ የዒልም ጉዞን ያግራልን!

ነቃ በሉ ቤተሰብ በሳምት 3 ቀን ጠጡ ቡና የኛ ያበሻ ቡና ብዙ ጥቅሞች አሉት እቤታቹ ቆላ እያረጋቹህ ቀመስ አርጉ ✅ ኪሉ ራሱ ይቀንሳል ወፍሮች ተጠቀሙት 👌👌 አሉ ደግሞ አንዳዶች አፋቸው ላይ ድግ
ነቃ በሉ ቤተሰብ በሳምት 3 ቀን ጠጡ ቡና የኛ ያበሻ ቡና ብዙ ጥቅሞች አሉት እቤታቹ ቆላ እያረጋቹህ ቀመስ አርጉ ✅ ኪሉ ራሱ ይቀንሳል ወፍሮች ተጠቀሙት 👌👌 አሉ ደግሞ አንዳዶች አፋቸው ላይ ድግስ ቢደገስ የማይወፍሩ ሰወች 🕶🕶😂😂 ለማናቸውም ደማቹሁን አነቃቂ ለማለት ነው አይዞቹህ ሲጀመር ቡና የምታፈላላ ሴት ልባም ናት ሲሉ ሰምቻለሁ ?!!

ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ ውዳሴም አይሻም የማንንም ታርጋ አፉን የለጎመው የለተሞን መንጋ ያለ አግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ ድምፅ ባለው ፁሁፍ ቅጥፈት የተዋጋ
+2
ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ ውዳሴም አይሻም የማንንም ታርጋ አፉን የለጎመው የለተሞን መንጋ ያለ አግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ ድምፅ ባለው ፁሁፍ ቅጥፈት የተዋጋ የሙነወር ልጅ ነው የባጢል አለንጋ አሏህ ሆይ እነዚህን የኡማው ኩራዝ የሆኑ ኡስታዞችን በጥበቃህ ስር አርጋቸው አደብን  ስረአትን  እውቀትን  ስነምግባርን  ቁጭ በሉና ከታላላቆቻቹህ ቅሰሙ   ባረከሏሁ ፊኩም  አቂዳው ከተስተካከለ  ከሰለፍዬች  ጋራ ስትቀመጡ  ከአፋቹህ የሚወጡት  ቃላቶች እንደሺቶና ሚስክ የጣፈጡ ይሆናሉ   አደብን ትላበሳላቹህ  ሀታ ተውሂድን ሱናን በምን መልኩ ተደራሽ እደምታደርጉ  ፈሩን ሳትለቁ  ትማራላቹህ👏✅👆

Repost from N/a
ከግደታ ሶላት ቡኋላ ዱዓ ማድረግ እንደት ይታያል ? መልስ👆 በሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን https://t.me/abuhureyrahmedresa

አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ ያልተኛቹህ የለይል ሶላት እዳረሱ🔮 قم صلّ ركعتين في جوف الليل، واخلع هموم الدنيا من
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱሁ ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ያስታውስ ያልተኛቹህ የለይል ሶላት እዳረሱ🔮 قم صلّ ركعتين في جوف الليل، واخلع هموم الدنيا من قلبك، واقترب من ربك بالخضوع والدعاء؛ فإنه ينزل كل ليلة إلى السماء الدنيا يقول: "هل من داعٍ فأستجيب

እንደምን ነው ወሎ አፈሩ መሬቱ፡ በሰው ሀገር ሁኘ ገደለኝ ናፍቶቱ፡ እንደምን ነው ወሎ ደሴና ኮምቦልቻ ፡ የሚወለድበት ቆንጆ ቆንጆ ብቻ፡ እንደምን ነው ወሎ ከሚሴ እና ሀርቡ ብሉልኝ ጠጡልኝ የሚሉት
እንደምን ነው ወሎ አፈሩ መሬቱ፡ በሰው ሀገር ሁኘ ገደለኝ ናፍቶቱ፡ እንደምን ነው ወሎ ደሴና ኮምቦልቻ ፡ የሚወለድበት ቆንጆ ቆንጆ ብቻ፡ እንደምን ነው ወሎ ከሚሴ እና ሀርቡ ብሉልኝ ጠጡልኝ የሚሉት አህሪቡ ፡ እንደምን ነው ወሎ ሀይቅ የጁና ጊራና፡ የሚወለድበት ደፋር እና ጀግና ፡ እንደምን ነው ወሎ ባቲና ወረኢሉ በፍቅር በናፍቆት ሰዉን የሚገሉ፡ እንደምን ነው ወሎ ቦረና እና መርሳ ሀራም አይሆንም ወይ እናንተን ብረሳ፡ እንደምን ነው ወሎ ወረባቦ አርዲቦ እንግዳ የሚሸኘዉ አብልቶና አጥግቦ፡ እደዉ በጠቅላላው እደት ነዉ መሬቱ በሰው ሀገር ሁኘ ገደለኝ ናፍቶቱ

ይህ የምታዩት የሰርግ ድግስ እዳይመስላቹህ የተሰባሰቡት ቁርዓንን አኽትመው ነው ይሄ ሁሉ ማሻአሏህ አትሉም አሏሁመዚድ የወንዶች የሪጃሎች የመሻይኾች የጀግኖች አገር ከሚሴ ነው ጀግና ጀግና ነው የምታፈ
ይህ የምታዩት የሰርግ ድግስ እዳይመስላቹህ የተሰባሰቡት ቁርዓንን አኽትመው ነው ይሄ ሁሉ ማሻአሏህ አትሉም አሏሁመዚድ የወንዶች የሪጃሎች የመሻይኾች የጀግኖች አገር ከሚሴ ነው ጀግና ጀግና ነው የምታፈራው🥇🥇 አገሪቱ አስደናቂ ናት ሀፊዞችን በብዛት ታፈራለች🏆🏆 እህ እ እኔማ ኢንሻአሏህ ይቺን የሀፊዞች መፍለቂያ የሆነች አገር መጎብኘቴ አልቀረም ?! ✍️✍️ እድል ነው ማሻአሏህ አቦ ያስቀኑኛል ፕሮግራም ከተዘጋጀ እገሌ ከከሚሴ ከከሚሴ ከከሚሴ ከዚበላይ ?!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ማንኛውም ሰው ለአላህ ብሎ "ራሱን ዝቅ" አያደርግም (አይተናነስም)፣ አላህ ደረጃውን (ከፍ) ቢያደርገው እንጂ። ሶሂህ ሙስሊም (2588)
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ "ማንኛውም ሰው ለአላህ ብሎ "ራሱን ዝቅ" አያደርግም (አይተናነስም)፣ አላህ ደረጃውን (ከፍ) ቢያደርገው እንጂ።    ሶሂህ ሙስሊም  (2588)

_​🌙 ለአላህ ቤት ግንባታ የሚደረግ ጥሪ! 🌙_ *ለሙስሊሙ ኡማ በሙሉ* *​"የአላህ ቤቶችን የሚገነቡት በውስጣቸው አላህንና የመጨረሻውን ቀን ያመኑ፣ ሶላትንም በአግባቡ የሰገዱ፣ ዘካንም የሰጡ እንጂ ሌሎች አይደሉም፤..." (ሱረቱ አ-ተውባ፡ 18)* _​ለወረባቦ ምሽጋ ቀበሌ 0 18 ሙስሊም ማህበረሰብ እና መላው የኸይር ሰራተኞች በሙሉ!_ _​በአደጋ ምክንያት ተቃጥሎ የነበረው የቀበሌ 0 18 መስጂድችን ዛሬ ላይ በህዝበ ሙስሊሙና በለጋስ ልቦች ትብብር ተገንብቶ_ *ለአብዛኛው ፍጻሜ ደርሷል። አሁን ላይ የቀረው ትንሽና የመጨረሻው የዕድሳት ሥራ ብቻ ነው።* _​የጀመርነውን መልካም ሥራ በጋራ እንጨርስ ዘንድ አሁንም የእናንተ እጅና ትብብር እጅግ ያስፈልጋል።_ ✨ ለአላህ ብሎ አንድን መስጂድ የገነባ አላህ በጀነት ቤትን ይገነባለታል" _​ይህንን ታላቅ የዕድል በር በመጠቀም_ *​በገንዘብዎ* *​በዕቃዎ* *​በጉልበትዎ እና* _​ለሌሎች በማጋራት (ሸር በማድረግ) የበኩልዎን አሻራ ያኑሩ።_ _​ዛሬ አብረን የጀመርነውን የኑር ቤት ነገ በድል እንጨርሰዋለን!_ ​📍 ለርዳታ እና አብሮ ለመቆም 👇👇 https://chat.whatsapp.com/G7qNg2Wjsq9BztM3BqXm3I?s=cl&p=a&ilr=1

ወሰናችሁን እወቁ!    አስተምራለሁ ካልሽ ነይ ዋትሳብ ቴሌግራም በውስጥ መስመር አስተምሪ   ነይ የዛኔ ለድን ያለሽ ጉጉት  ፍላጎት ጎልቶ ይታያል✅👏
ወሰናችሁን እወቁ!    አስተምራለሁ ካልሽ ነይ ዋትሳብ ቴሌግራም በውስጥ መስመር አስተምሪ   ነይ የዛኔ ለድን ያለሽ ጉጉት  ፍላጎት ጎልቶ ይታያል✅👏 ምን ትሰሪለሽ በሚዲያ ላይ በቪዶ ) በድምፅ  ኦዶ እየቀዳሽ  የምትዝረከረኪው፣  < ሴቶች ከመጋረጃ ጀርባ > ይሁኑ  ይሰተሩ  የሚለውን እየዘለላቹህ መሰለኝ የቀራቹሁት}  ኧረግ ሰሞኑንማ  ለየት ብላቹሃል?!   መሻይኾቻቺን ወንድሞቻቺን   እያፈሩ  በቪዶ አይዘልቁም ወሏሂ አስተምሮታቸው  በፁሁፍና በድምፃቸው ነው ሂጃብ ማለት ፊት ላይ ከቨር አድርጎ ሚዲያ ላይ እየተዝረከረኩ ወንዶችን መፈተን አይደለም። ሂጃብ የሀያዕ (የዕፍረት) እና የክብር መገለጫ ነው። ​ዝርክርክነቱን አቁሙ! ዲን ማስተማርም ሆነ እውቀት መቀስቀስ የሚዲያ ላይ መፎካከሪያ አይደለም። ሴትነትን የሚቀንሰውን ትውልድን የሚበክለውን እና ፊትናን የሚያስፋፋውን ይህንን ርካሽ ተግባር  አቁሙ።

✍ እንደዉ በቴሌግራም ቻናል ተጠቃሚወች በጥቅሉ በሚባል መልኩ በጣም አዘንኩኝ እኔምለዉ ኢትዮ ሰዉ ሲሞት እገሌ ሞተ ለቀብር ድረሱ እገሊት ሞተች የገሌ እህት አባት አጋት አክስት .... ሞቱ ለቀብር እያላችሁ ሸር የምታደርጉ ኡስታዞች ወንድሞች ግን ምን ነካችሁ ??? አገባ አገባች ወለደች የሚል ሙፋጃአ አደረጋችሁት እኮ ። ስደት ላይ ያሉ ቤተሰቦችን ታሳቢነት ማድረግ ተሳናችሁ ??? ወይስ የስደት እህቶች ጨካኝ አረመኔ የቤተሰብ ሞት ምንም የማይመስለን መሰልናችሁ ??? እንደ ኡስታዞች ጭራሽ እናንተኳን አትረዱንም ?? እስቲ እደዚህ ሞተ ብላችሁ ስትጥፉ ያንንፅሁፍ ከዛ ከሟች ቤተሰብ የሆነች የሆነ ድንገት አይታ አይቶ በድንጋጤ የሆነ አደጋ ቢደርስባቸዉ ተጠያቂዉ ማነዉ ??? አረ እየተዛዘን ወገን ታዉ ። አስተዉሉ አመናችሁም አላመናችሁም ስደት ላይ ያለን እህቶች ለቤተሰቦቻቺን ከናንተ በበለጠ እናስባለን ። እባካችሁ ከመፃፋችሁ በፊት አስተዉሉ ። በስልክ እየተደዋወላችሁ ተነጋገሩ ። እንደኖርማን እገሌ ሞተ የቀብሩ ስነስራአት እዚህ ቦታ ነዉ ። አረ በፈጠራችሁ አስተዉሉ ። ለቻናል ባለቤቶች ሁሉ ሸር አድርጉልኝ ። ደነገጥ ቢሉ https://t.me/Abu_Hanifa_Hussen_Ibnu_edris

🌸 በአላህ ፈቃድ ስራ ጀምሬያለሁ—የሱና እህት/ወንድሞቼ አበረታቱኝ! 🌸 አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱሁ ይድረስ በዲኔ ለምትደሰቱ፣ ስራ አጥቼ ስቸገር አብራችሁኝ ለተጨነቃችሁ የሱና ቻናሎች
🌸 በአላህ ፈቃድ ስራ ጀምሬያለሁ—የሱና እህት/ወንድሞቼ አበረታቱኝ! 🌸 አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱሁ ይድረስ በዲኔ ለምትደሰቱ፣ ስራ አጥቼ ስቸገር አብራችሁኝ ለተጨነቃችሁ የሱና ቻናሎች፣ ውድ ሰለፊዮች እህትና ወንድሞቼ በሙሉ፦ አልሃምዱሊላህ! አላህ በችሮታው በሩን ከፍቶልኝ፣ በሀላል መንገድ ራሴን የምደግፍበትን የኦንላይን ገበያ (Aylan Online Market) ስራ በይፋ ጀምሬያለሁ። ላደረጋችሁልኝ ትብብር እና ዱዓ ሁሉ አላህ ያጅራችሁን ይክፈላችሁ። ነገር ግን አሁንም ቢሆን የእናንተ ድጋፍና ማበረታታት ለእኔ ትልቅ ጥንካሬ ነውና ከራሳችሁ ላይ አልወረድኩም! ይህንን መልዕክት በየቻናሎቻችሁ ላይ ሼር (Share) በማድረግ እንድታግዙኝ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ። በተለይ ዱባይና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) የምትኖሩ እህት ወንድሞቼ አሁኑኑ ኮንታክት አድርጉኝ። ✨ በአሁኑ ሰዓት የምናቀርባቸው አቅርቦቶች፦ 1️⃣ ልዩ መዓዛ ያላቸው ንጹህ ሽቶዎች — ቀኑን ሙሉ አብረዋችሁ የሚቆዩ። 2️⃣ MERA-OIL የተፈጥሮ የፀጉር ቅባት — ለደረቀ፣ ለሚያሳክክ እና ለሚሰባበር ፀጉር ፍጹም ተፈጥሯዊ መፍትሄ። ⓷ 📚 የወደፊት እቅዳችን፦ አላህ ባገራልኝ እና ነገሮች በተሳኩልኝ መጠን፣ ወደፊት ጠቃሚ የሆኑ የስኬት መጽሐፍትን እና የተለያዩ ኪታቦችን በማካተት የምናሰፋ ይሆናል። የሀላል ስራዬን በመደገፍ የበረከት ተካፋይ ይሁኑ! ጀዛኩሙላሁ ኸይረን። 🔗 እኛን ለማግኘት እና ቤተሰብ ለመሆን፦ 📞 ስልክ ቁጥር፦ [+971508629084] ➘ የቴሌግራም አድራሻችን፦ https://t.me/Aylan_Market ➘ የቲክቶክ አካውንታችን፦ https://www.tiktok.com/@aylan0547?_r=1&_t=ZS-98if0yUhDUL 🛍️ አይላን ኦንላይን ገበያ ) — እምነት እና ጥራት በአንድ ላይ!