الْــــقَــــوْلُ الــــسَّــــدِيــــدُ
Open in Telegram
الَّذِينَ آمَنُوا وَتَطْمَئِنُّ قُلُوبُهُم بِذِكْرِ اللَّهِ ۗ أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ እነዚያ ያመኑ ልቦቻቸውም አላህን በማውሳት የሚረኩ ናቸው ንቁ አላህን በማውሳት ልቦች ይረካሉ
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
2 158
Subscribers
No data24 hours
+1817 days
+41530 days
Posts Archive
ይሄኛው ደግሞ ማን የሚባለው ሩዝ ነው ?! ዘድሮ አይታይ የለም 🙌 ኢላሂ ቺሎታውን ስጣቸው ...... አሚን💧
ዋ ! ያሻህን ስራ ትመነዳለህ የቂን የሆን ሚንዳን!
የውመል ቂያማህ ይመጣል እኮ
የቂያማ ቀን መምጣቱ ጥርጥር የሌለው እና የማይቀር መሆኑን በማስታወስ ለዚያ ቀን መዘጋጀት እንደሚያስፈልግ ስንቶቹ ነን ግን የተዘጋጀነው?!💦
የውመል ጀዛዕ
እያንዳንዱ ሰው በምድር ላይ የሰራው መልካምም ሆነ መጥፎ ስራ ሳይቀር, ያለምንም መጉደል ሙሉ ዋጋውን የሚቀበልበት ጊዜ መሆኑን ምንስ ነው ስራችን ?! ዋ የኛነገር
አድሎ የሌለበት ፍትህ በዕለቱ ማንም ሰው ሳይበደል (ያልሰራውን ታሪክ ሳይሸከም ወይም የሰራውን ሽልማት ሳይነፈግ ) ሳይጓደልበት ፍፁም የሆነ የአሏሁታዓላን ፍትህ እንደሚሰፍን እያወቅን ስቶቻቺን ነን የምናስተውለው ?!💦
ﻻ إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ
ያ አሏህ! በዚያ በውርደት ቀን ማንም ከማንም ሊደርስ በማይችልበት ሰዓት ከዕዝነትህ እና ከጥበቃህ አትለየን ከቀጣህም ውርደት ጠብቀን! آمين
ደህና አርፈን ነበረ ከስጋት እና ከስቆቃ ህዕ አሁን መቶባቸዋል
ሊንክ መልቀቅ ነው የቴሌ ካፓኒ ተደራጅቷል መሰል ሰሞኑን ጥንቃቄ እናድርግ
🎁የሰርግ ፕሮግራም💍🎁
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
🌸 የእህታችን አለም ታደሰ እና የወንድማችን ሙሀመድ መኮነን 🌺
🌸 የእህታችን ዘይነብ ሙሀመድ እና የወንድማችን አወል ክብረት 🌺
⏰"በዕለቱ ተጋባዥ እንግዶቻችን
➊ ኡስታዝ አቡ ሀኒፋ
🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
➋ ኡስታዝ አቡ ሙሃመድ
🔖ርዕስ "በሰአቱ
❸ ኡስታዝ አቡ ሻኪራ
🔖"ርዕስ በሰአቱ ይነገራል
❹ ወንድም አቡ ሂበቲሏህ
🔖ርዕስ "በሰአቱ
❺ ኡስታዝ ዩሱፍ
🔖ርዕስ "በሰአቱ
❻ ኡስታዝ አቡ አመቲ ረህማን
🔖"በሰአቱ ይነገራል
❼ ወድም አቡ ሹራ
🔖ርዕስ "በሰአቱ
📖ቲላዋ🌺
🎤አቡ አፍናን
🎤አቡ ኢምራን
🎤አቡ ሀይደር
🎙 የፕሮግራሙ መሪ ወንድም አቡ አፍናን
🗓ቀን እለት እሁድ ምሽት
⏰ ሰአት
🇪🇹በኢቶ 3:00
🇸🇦በሳዑዲ 9:00
🇵🇸በዱባይ 10:00
ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ሊንክ👇
👇👇👇👇👇
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
🔺〰〰〰#_እዉነተኛ_ታሪክ〰〰〰🔺
#የታሪኩ_ርዕስ
#በሰለፍያ_ጥላ_ስር_የነፍስ_ዋጋ_ያስከፈለኝ_የፍጡር_ፍቅር"
#ክፍል_☞ #አስራ_አንድ_⓫ ፣
✍ #ፀሀፊ_☞ #አቡ_ኹዘይማ
.................. #እራቢያ ................
#ባለቤቱ_የሌለው_ስደት"
.........
የራጎ "ሲኦል" እና የቁርኣን መድኃኒት
በራጎ ምድር የሰው ልጅ ክብር እንደ በልግ ቅጠል ረግፎ አየሁት። ቤተሰቦቼ ብሩን ለመላክ ቢቸገሩም፣ በዚያ ግቢ ውስጥ የሚሰማው የግርፋትና የጭካኔ ድምፅ አስፈርቷቸው እንደምንም ላኩ። እዚያ ግን "የምድር ሰላም" ተነፍጎናል። መኝታው አፈር፣ ድባቡ ጭቅቅት፣ ጠረኑም ቅማልና ግማት የነገሰበት የቁም መቃብር ነው።
አንባቢያን ሆይ! ልብ በሉ። በዚያ ስቃይ መሃል ሶላት መስገድ እንኳ እንደ ቅንጦት የሚታይበት፣ የሰው ልጅ አእምሮውን ስቶ በጭንቀት የሚጮኽበት ቦታ ነው። ታዲያ በዚያ የጨለማ ቤት ውስጥ አላህ እኔንና አንድ የሀርቡ ልጅን ለምስኪኖቹ ጋሻ አደረገን።
እኛ ቁርኣን የምናውቅ በመሆናችን፣ አእምሯቸውን ስተው ለሚጮኹት ወንድሞቻችን "ሩቃ" (የቁርኣን ሕክምና) እናደርግላቸው ጀመር። በዚያ የክርፋትና የደም ሽታ በነገሰበት ግቢ ውስጥ፣ የአላህ ቃላት ሲነበብ ሰላም ይወርዳል፤ የታመሙትም ይሻላቸዋል። ደላላዎቹ እንኳ ይህንን ተአምር ሲያዩ፣ ለኔ ልዩ ክብር መስጠት ጀመሩ። እንዲህ አልኩ፦
"በራጎ ጨለማ - ግማቱ በነገሰበት፣
የቁርኣን ጸዳል - ሆነልን ብርሃነት፤
ሰው አእምሮውን ስቶ - ሲጮኽ በመከራ፣
ጌታዬ አቆመኝ - ከፈውስ ጋር አብራ።"
አምስት ቀን በዚያ ሰቆቃ ውስጥ ቆየሁ። በስድስተኛው ቀን ግን... የታሪኬ የመጨረሻውና እጅግ አስፈሪው ምዕራፍ ተበሰረ። "ወደ ሳውዲ ድንበር!" የሚል ትእዛዝ መጣ።
የሳውዲ ድንበር! ያ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ደም የፈሰሰበት፣ ጥይት እንደ በረዶ የሚዘንብበት፣ ተራራውና ሸለቆው የሰው አጥንት የለበሰበት አስፈሪ ምድር። ይህንን ጉድ የሚገልጽ ቃላት ያለ አይመስለኝም። የሰው ልጅ የሕይወቱን ዋጋ ለድንበር ጠባቂዎች ጥይት አሳልፎ የሚሰጥበት፣ ሞትና ሕይወት በአንዲት ሰከንድ የሚለዩበት ያ አደገኛ ጉዞ ተጀመረ።
"ድንበሩ ተከፍቷል - የሞት ደጃፍ ሆኖ፣
የሰው ልጅ ይጋዛል - ተስፋውን አዝሎ፤
በራጎ መከራ - ያለፍኩት እኔዬ፣
ወደ ሳውዲ እሳት - አመራሁኝ ጌታዬ።"
፦ የሞት ሸለቆና የጠይባ አደራ
-
ከራጎ ሲኦል ወጥተን በሁለት "ሻስ" መኪናዎች ተጭነን የየመንን ገደል ለገደል ሦስት ሰዓት ተጓዝን። መኪናው ሊሄድበት የማይችልበት ጋራ ስር አወረደን። "ከዚህ በኋላ የእግር መንገድ ነው፤ ጠንከር በል የሙሐመድ ልጅ!" ብዬ ለነፍሴ አሾካሾክሁላት። በዚያ በረሃ ውስጥ ሆኜ እንደ ዋሻው ባለቤቶችና እንደ ነቢዩሏህ ዩኑስ (ዐለይሂ.ሰላም) ጌታዬን እየተማጸንኩ፣ አንዲት ፕላስቲክ ውኃ ይዤ ጉዞዬን ቀጠልኩ።
-
ንጋት ሲቃረብ ወደ ሳውዲ "መርከዝ" (የድንበር ጠባቂ ጦር ሰፈር) ተቃረብን። ፀሐይ ብቅ ስትል ግን፣ ሰላማዊው ተራራ በቆሎ ጥይት ጩኸት ተናወጠ። ድንበሩ የሰቀቀን ማኅደር ነው፤ ቃላት የማይገልጹት የሞት አዝመራ! ጥይቱ ሲነጋ "ምነው ባልተፈጠርኩ!" የሚያሰኝ የፍርሃት ድባብ ነገሠ። መሬት ለመሬት እየተሳብን፣ ጥይቱ ሲጮህ ድንጋይ ተከል እየሆንን፣ ከሞት ጋር ድብብቆሽ መጫወት ጀመርን።
"ተራራው ሲጮኽ - በጥይት ነጎድጓድ፣
ነፍሴ ተሸበረች - ልትወጣ ካካል።
ድንበሩ መቃብር - ሸለቆው ሰቀቀን፣
ጌታዬ ሆይ አውጣኝ - ከዚህ የሞት ቀን።"
-
በዚህ ድንጋጤ መሃል የቀኑ ግማሽ አለፈ። ጥይቱ አላሳልፍ ብሎን ባለበት፣ ከሌላ ደላላ ጋር የመጡ ስደተኞችን አገኘን። አብዛኞቹ ሴቶች ነበሩ፤ ጥይቱ ሲጮህ በድንጋጤ ይተፋሉ፣ ያለቅሳሉ። በዚያ መሃል አንዲት ልጅ ከእኔ ጋር በአንድ ድንጋይ ስር ተጠለለች።
ተያይዘን መሬት ላይ ተለጥፈን ሳለ፣ ዓይን ዓይኔን እያየች እንዲህ አለችኝ፦ "ስማ... መልከ መልካም ሰው ትመስላለህ፤ ፊትህ ላይ ኑር (ብርሃን) አለ። አትዋሽም ብዬ አምናለሁ። እኔ የአልብኮ ልጅ ነኝ፣ ስሜም ጠይባ ይባላል። እኔ ከዚህ ተራራ በሕይወት እንደማልወጣ አውቃለሁ፤ ለአላህ ብለህ ለቤተሰቦቼ ንገርልኝ" ብላ ስልክና መልእክት የተጻፈበት ወረቀት ሰጠችኝ።
አቤት መርዶ! ገና ሳትሞት ሞቷን የተነበየች ምስኪን ነፍስ! በዚያ በጥይት እሩምታ መሃል፣ የጠይባን ወረቀት ስቀበል እጄ ይንቀጠቀጥ ነበር። በገዛ ዓይኖቿ ሞትን እያየች ለእኔ አደራ የሰጠችኝ ያቺ ልጅ፣ የታሪኬ ሌላዋ ጥቁር ጠባሳ ሆነች።
-
"ጠይባ በድንጋዩ ስር - ሞቷን ስትናዘዝ፣
አደራዋ ከበደኝ - ልቤ ሲቀመቅዝ።
'አልወጣም' ስትለኝ - በቁሟ ተረድታ፣
ተራራው ተከፈተ - ነፍሷን ሊያወጣ።"
ኢንሻ አሏህ በቀጣይው ክፍል⓬
የሞት ሽረት ሩጫና የሳዑዲ መሬት
በሚል
.ይ
ቀ
-------ጥ
-----------------ላ
-------------------------------ል ⤵️
ታሪኩ የምን እደሆነ ተረድታቹሁታል መጀመሪያ ?! የሰው ልጅ እና ከድኑ ርቆ የሀራም ግንኙነት እኮነው ወይስ ተራ ፀያፍ መስሏቹህ ነው
ተረጋጉሲ ፊልም የካፊር ፊልም እና የሙስሊም የሂወት ታሪክ ይገናኛል ወይ ?! ሲቀጥል ማንበብ ያልፈለገ መብቱ ነው እለፉት እኛ ግን እናብብ ተማም
ይሄምኮ ነፍስያን ከእሳት ማዳን ጥሪ ነው ሁሉም የራሱ የሆነ ወቅት አለው ብዙወቹ ራሳቸውን ያነበቡበት ርዕስ ነው ?! ባረከሏሁ ፊኪ
አላቹህ ግን እያነበባቹህ ነው ?! መጨረሻም ጥያቄ አለው ሀቂቃ ሁለተኛ ክፍል 24 ድረስ ነው ይቀጥል ወላ ይበቃል ?!✍👆👍
እውነተኛው ታሪክ ቀጣይ ክፍል 11: ✍ ይለቀቃል እስከዛው በዚህ ጣሳ እየጠጣቹህ ነቃ ብላቹህ እድታነቡት በጣምምም ያጓጓል የዛሬው💦
ሳምንታዊ ፕሮግራማችን ተጀመረ
🎙በኡስታዝ አቡ አብዲ ረህማን
የቀጥታ ስርጭት
⬇⬇⬇
https://t.me/Multeka_Selefiyin?videochat=a80e9903da5b10df9e
Repost from Zɪʏᴀᴅ Pʀᴏ™
➲➢ ኢስላማዊ
የቴሌግራም ቻነሎች መግዛት ይፈልጋሉ ?
አስቾካይ 1 ቻናል ብቻ ነዉ ያለን
🏷 3.6k subscribers
👆በርካሽ መግዛት የፈለግ ብቻ ያናግረኝ
Repost from N/a
📚 ተጅዊድ በነፃ መማር የሚፈልግ ብቻ 🎊
በዚሁ ቴሌግራም በኦንላይን ያለ ክፍያ ማስተማር ተጀመረ 🌛
ቶሎ በሉ እንዳያመልጣቺሁ
እየተግባባን አይደለም ግን እኔና እናንተ ?! 💧✍👆📢 ሞቋቹሀል መሰል ተፍለክለኩ ኧረገኝ 🕶🕶
ለራስሽ ጊዜ ስጪ🌸
ሁልጊዜ ለሌሎች ስትሊ ራስሽን አትርሺው
የምትወጃቸውን ን ነገሮች ማድረግ ለምሳሌ፡ የሚያምር ቡና ፈላ ቆሎሺን ቆላ ከዛ ቁጭ ብለሽ 📚 ትንሽ ደቂቃም ቢሆን አንብቢው👑
የሚማርክ 🧴 ሽቶ መቀባት ፅድት ማለት ከክላስሽ 🌸 ወይም የምወጂውን ጣፋጭ 🍰 ኬክ መቅመስ ሰራ አድርጊው ዋ ) ከዛ የራስሽን ደስታ ፍጠሪ ኦኽታዬ
የሰው አገር እኳን ችላ ብለነው ከባድ ነው እና አይዞን አድ ቀን የናፈቅነው አላማ ተሳክቶልን ከቤታችን እናርፍ ይሆናል ! 🌸☕✨
إن شا ءلله
ስደተኛዋ እህቴ አይዞሽ
በእሳት ያልተፈተጠ ወርቅ የለም ፈተናው ከባድ ቢሆንም ጥንካሬሽ ግን ከሱ በላይ ነው።
የሰው ሀገር ጨለማ ለምዶ የራሳቸውን ህይወት እና ደስታ አስረስተው ለወገን ሲሉ የሚንከባለሉ እህቶቻችን ክብር ለእናንተ
ከሰው ሀገር ድካም በተጨማሪ የቤተሰቧን ሐላፊነት ብቻዋን ተሸክማ የነገን ተስፋ ለመዝራት የምታደርገው ሩጫ እጅግ ከባድ ነው።
ልብ ሲሰበር የሚያለቅስለት አካል ሳይኖር፣ እንባዋን ጭር አድርጋ በፈገግታ ቀን የምታነጋግድ ናት።
አንቺን የሚረዳሽ ጠፍቶ የሚሰብርሽ በዝቷል አይዞሽ እህቴ
ለራስሽ ብርታት ሁኚ የሚጎዱሽንና ልብሽን የሚሰብሩትን ሰዎች በዝምታ አሸንፊቸው፤ ትኩረትሽ ሁሉ በዓላማሽና በድልሽ ላይ ብቻ ይሁን
ያጀባር አንተ በጥበቃህ ስር አርጋት አንተ አሳርፈን በቤታችን ኢላሂ💦💦
