(የወጣቶች አለም)🌏 عَالَمُ الشَّبَاب
Open in Telegram
🌟 እንኳን ወደ "የወጣቶች አለም" በሰላም መጣችሁ! 🌟 በኢስላማዊ እሴቶች፣ በአኽላቅ፣ በቁርኣን እና በሐዲሥ ብርሃን የወጣቶችን የዱንያ እና የአኺራ ስኬት ለማጎልበት የተዘጋጀ ልዩ መድረክ። 💡 ኢስላማዊ እውቀት | 🚀 አነቃቂ ምክሮች | 📚 የመልካም ስነ-ምግባር መመሪያዎች💥1ታሪክ 💥2የትዳር ተሞክሮዎች 💥3ኢስላማዊ የእውቀት ፈተና ተቀላቀሉን፤ በእስልምና ብርሃን አብረን እንደግ! 🌙✨
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
330
Subscribers
+124 hours
+57 days
+4630 days
Posts Archive
ሙሳ (ዐ.ሰ) በመድየን ከተማ መግቢያ ላይ በሚገኘው የውሃ ምንጭ ዘንድ ሲደርስ ምን ተመለከተ?
ሸይኽ ኢብኑ ኡሰይሚን (አላህ ይዘንላቸው) እንዲህ ብለዋል፡-
👉ሶላትን ማቋቋም ኢማን ነው
👉ችላ ማለት ደግሞ ክህደት ነው።
ሶላቱን ጠብቆ የሚኖር ሰው በልቡ፣ በፊቱ፣ በመቃብሩ እና በቂያም ቀን ብርሃን ሆኖ ያበራለታል።
ማታ ጥያቄና መልስ ይኖራል 2:20 ላይ ኢንሻአላሕ ተሳተፋ💫
Repost from 🌱📖"بناء الذات بنور الوحي
🌍 አለም ስለ "ፈተና "
ችግር ወይም ውድቀት ሲያጋጥም እንደ "መጥፎ እድልና ፍትሃዊ ያለሆነ ህይወት" እንደሆነ አለም ታስባለች ።ችግር የሰው ልጆችን ለማድከም የሚላክ መልአክ እንደሆነ ተደርጎ ይታሰባል ። ችግር የሚለው ሀሳብ ሲነሳ"መከራ ፣ማጣት ፣መታመም ፣መጨነቅ ፣ ወድቀት "የሚመጡ ናቸው ግን ሀብትን ፣ስልጣንን ፣ልጆች እንደፈተና አይቆጠሩም ። plus ችግር ሲከሰት ሚታለፈው በማዘብ በመጨነቅ ነው ብላ ታስባለች ።
ቁርአን: –
﴿وَنَبْلُوكُم بِالشَّرِّ وَالْخَيْرِ فِتْنَةً ۖ وَإِلَيْنَا تُرْجَعُونَ﴾
📌ፈተና በመጥፎ ነገር ብቻ አይደለም! እኛ ጥሩ አድርገን የሳናለቸው የፈተና አንድ አካል ናቸው በዛ ፈተናም ሂሳብ ልንደረግ ወደ ጌታችን እንመለሳለን ።
﴿وَلَنَبْلُوَنَّكُم بِشَيْءٍ مِّنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِّنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنفُسِ وَالثَّمَرَاتِ ۗ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ﴾
📍ፈተና ሲመጣ የህይወት በደል አድርገን ምናስበው እኛ ላይ ብቻ ለሚመስለን ሁሉ አላህ በመሃለችን ይህን ችግር እንደሚቀያይረው ካለን ነገር ላይ "በመቀንስ ፣ፍርሃትን በማቅረብ እንፈትናቸዋልን" ይላል ።ከዛ በመቀጠል ይህን ፈተና ላለፋት ለጠነኩሩት አብስራቸው🥰 ብስራቱ ደሞ ጀነት መሆናን በሌላ ቦታ ይናገራል ።so ችግር እኛን ሊሰብር ሳይሆን «ጥንካሬያችን ፈትኖ ይጨምርና የብስራት ስጦታን ያቀርብልናል! »
DONT FORGET IT:
ህይወት ራሳ የፈተና መድረክ ናት!
•📖Quran ✧ The way of the world🧭 ይቀጥላል…
Share & join: 🌱@Binaulzat
ው🌸
ዷ🌸
ጓ 🌸
ደ🌸
ኛ🌸
ዪ🧕
🌷ዉዷ ጓደኛዬ የአሏህ ስጦታ
🍂ሰላምሽን ያብዛዉ የአለማት ጌታ
🌷አልሀምዱሊላሒ አንችን የሰጠኝ
🍂የድን ዉድ እህቴን እርሱ ያደለኝ
🌷የኔ አጠናካሪ የምሳሳልሽ
🍂ባለሽበት ቦታ ይብዛ ሰላምሽ
🌷ጓደኛ ሚለዉ ቃል ልምዴ ሆኖ እንጅ
🍂የምሳሳልሽ ነኝ እንደ እማዬ ልጅ
🌷አሏህ አንችን ሰቶ ያሥደሰተኝን
🍂ደግሜ ላመሥግን ሀያል ጌታዬን
🌷የኔ ፅጌሬዳ አበባዬ ነሽ
🍂ከተዉሒድ መድረሳ ሁሌም አልጣሽ
🌷ይቅርብኝ አያልቅም ስላንች ማዉራቱ
🍂ሰላምሽ ይብዛልኝ ስስት የኔ ብርቱ
🌷በድኔ አበረታች ሳጠፋ መካሪ
🍂አረህማን አደለኝ የአለማት ፈጣሪ
🌷እወድሻለሁ ብዬ ነግሬሽ ባለዉቅም
🍂 ዛሬ ልግለፅልሽ ሁሌም አረሣሽም
🌷ከምገልፀዉ በላይ በጣም እወድሻለሁ
🍂መልካሙንም ሁሉ እመኝልሻለሁ
🌷በስደት ሰበብ አረህማን የሠጠኝ
🍂በድነል ኢሥላም ላይ እሱ ያገናኘኝ
🌷የእዉነት እልሻለሁ በጣም ደስ ብሎኛል
🍂አንችን በማግኘቴ እድል ይሠማኛል
🌷መጠንከራችንም ከዚህ በላይ ያፍራ
🍂ጠቃሚ የሆነ ከዱኒያ እስከ አኺራ
🌷መልካም ስራ ሠርተን ለአኺራ ካልሆነን
ዱኒያ ላይ ከቀረ እዚህ ተደስተን
🍂ምንም አይጠቅመንም ኋላ እንቆጫለን
🌷ስለዚህ እህቴ እንበረታ አሁኑ ለነገ ቤታችን
🍂ለሚጠቅመን ሀገር ለእዉነተኛችን
🌷ጀነትን ለመዉረሥ እንታገል ዛሬ
?ተትረፍርእንዳይሆን መኖር ከዱር አዉሬ
🌷ተትረፍርፎ ሳለ ፀጋዋ የጀነት
🍂ካሣማሚዉ ቅጣት እንዳንሆን ከእሳት
🌷ጀነት ሰፊ ሆና ከምድር በላይ
🍂ቀብር እንዳይጠበን ዉዴ በእኛ ላይ
እንበርታ እህቴ
🥀ለአንች ነዉ በአሏህ መንገድ ላይ ላገኘሁሽ ዉድ እህቴ
ሰዎች ገፍተው ገፍተው ምርር አድርገውት ወደ አላህ እንደሄደ ሰው የታደለ ማን አለ?
በደላቸው ወደ አላህ እንድንጠጋ ባደረገን ሰዎች ላይ የአላህ እዝነት ይስፈን!አላህን ካገኙ ወዲህ የሚታጣ ምናለ? (ምንም)
copy ✍
#𝟑_ሶስቱ_ወርቃማ_መርሆች
በዚህ ርዕስ ላይ የአህሉሱና አቋም ሶስት አጠቃላይ መርሆዎችን መሰረት ያደረገ ነው። እነዚህ መርሆዎችም በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ዙሪያ የተስተካከለ አቋም እንዲኖር ይረዳሉ፡፡
- የመጀመርያው መርህ : ሁሉም የአላህ ባህሪዎች ከፍጡራን ባህሪዎች ጋር ፍጹም እንደማይመሳሰሉ በማመን አላህን ማጥራት “ተንዚህ” ፡፡
- ሁለተኛው መርህ ፡ አላህ እራሱን በሰየመባቸው ስሞችና በገለፁባቸው ባህሪዎች፤ እንዲሁም መልዕክተኛውه አላህን በሰየሙባቸው ስሞችና በገለፁባቸው ባህሪዎች፤ ከአላህ ታላቅነትና ልዕልና ጋር በሚሄድ መልኩ ማመን፡፡
- ሶስተኛው መርህ ፡ ፍጡራን የአላህን ባህሪዎች «ከይፊያ» ማወቅ ስለማይቻሉ፤ ይህንን ለማወቅ የሚኖርን ውስጣዊ ጉጉትና መቋመጥ መግታት፡፡
እነዚህን ሶስት መሠረቶች ያረጋገጠ በአላህ ስሞችና ባህሪዎች ትክክለኛ የሆነውንና ከጥንት ጀምሮ የኖሩ ታላላቅ የኢስላም ሊቃዉንት ያፀደቁትን እምነት አረጋግጧል ማለት ነው፡፡
#ፊርዐውን_እና_አህባሾች...
አላህ ከዓርሽ በላይ መሆንኑ በተመለከተ፤ አላህ እንዲህ ብሏል፦
الرحمن على العرش استوى - طه: ٥ “አረህማን ከዐርሽ በላይ ከፍ አለ (ሆነ)” (ጣሃ 5)ፊርዐውን ከፍ ያለ ሰገነት ስሩልኝ ያለው "..የሙሳን ጌታ ብቅ ብዬ እንዳየው" ብሎ ነው፤ ይህንንም ያለበትን ምክንያት ሲገልፅ "ሙሳን ሀሰተኛ እንደሆነ አስበዋለሁ" ብሏል፤ ይህም ማለት እርሱ ይህን ቃል ያለው አላህ ከፍጡራን በላይ መሆኑን አምኖ ስለተቀበለ ሳይሆን ሙሳ አላህ ከፍጡራን በላይ መሆኑን ነግረዉት ስላስተባበለና በኩራት ውጥረት ስለካደ ነው፤ ስለዚህ አህባሾችም ይሁኑ ሌሎች የጀህሚያ ርዝራዦች በዚህ ጉዳይ ላይ በተዘዋዋሪ የርሱን ድምዳሜ ይጋሩታልና !!
وَقَالَ فِرْعَوْنُ يَا أَيُّهَا الْمَلَأُ مَا عَلِمْتُ لَكُمْ مِنْ إِلَهٍ غَيْرِي فَأَوْقِدْ لِي يَا هَامَانُ عَلَى الطِّينِ فَاجْعَلْ لِي صَرْحًا لَعَلِّي أَطَّلِعُ إِلَى إِلَهِ مُوسَى وَإِنِّي لَأَظُنُّهُ مِنَ الْكَاذِبِينَ القصص 38 ፈርዖንም «እናንተ ጭፍሮች ሆይ! ከእኔ ሌላ ለእናንተ አምላክን ምንም አላወቅሁም፡፡ ሃማንም ሆይ! ጭቃን ለእኔ አቃጥልልኝ፤ (ጡብ ሥራልኝ)፡፡ ለእኔም ከፍተኛ ሕንጻን ሥራልኝ፡፡ ወደ ሙሳ አምላክ ልወጣ እከጅላለሁና፡፡ እኔም ከውሸታሞቹ መኾኑን እጠረጥረዋለሁ» አለ፡፡(28:38)ታዋቂው አል-ኢማም አል-ቡኻሪን ጨምሮ የብዙ ሊቃውንት መምህር የነበሩት ታላቁ የኢስላም ምሁር «ኑዐይም ኢብኑ ሀም-ማድ» ይህን ሚዛናዊ አቋም ሲጠቁሙ እንዲህ ብለዋል፦
«من شبّه اللهَ بخلقه فقد كَفر، ومن أنكر ما وَصف به نفسَه فقد كفر، وليس ما وصف اللهُ به نفسَه ولا رسولُه تشبيها» «አላህን ከፍጡራኑ ጋር ያመሳሰለ በእርግጥ ክህደትን ፈፅሟል፤ (አላህ) ራሱን የገለፀበትን ያስተባበለም በእርግጥ ክህደትን ፈፅሟል፤ አላህ ራሱን የገለፀበትም ሆነ መልዕክተኛው (እርሱን የገለፁበትን ማፅደቅ) ማመሳሰል አይደለም!»#ጣኦት_አምላኪ_እና_ሙዓጢል... ከማማሳሰል ለመራቅ በሚል ፈሊጥ የአላህን ባህሪዎች የካዱ ሙዓጢላዎችን እና አላህን ከፍጡራን ጋር ያመሳሰሉ ሙመሲላዎችን የተመለከተዉን እውነታ ታላላቅ የኢስላም ሊቃውንት በአጭር ቋንቋ ገልጸውታል፤
المٌمَــثِّلُ يَعْبــُدُ صَنَــمًا وَالمُعَطِّـلُ يَعْبـُـدُ عَـدَمـًا● ለአላህ ስሞችና ባህሪዎች ግምት የሰጠዉና አላህን ከፍጡራን ባህሪዎች ጋር ያመሳሰለው “ሙመሲል” የሚያመልከው በአዕምሮው ውስጥ የሳለውን ጣኦት ነው። የአላህን ስሞችና ባህሪዎች ትርጉም አልባ ያደረገው “ሙዓጢል” ደግሞ አላህ ምንም ባህሪዎች እንደሌሉት አምኗልና፤ የሚያመልከው አለመኖርን “ዐደም”ን ነው ኢብኑ ተይሚያህ - ደርዑ ተዓሩዲል ዓቅሊ ወነቅል ቅጽ 6 ገጽ 348
اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ سَبْعَ سَمَاوَاتٍ وَمِنَ الأَرْضِ مِثْلَهُنَّ يَتَنَزَّلُ الأَمْرُ بَيْنَهُنَّ لِتَعْلَمُوا أَنَّ اللَّهَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ وَأَنَّ اللَّهَ قَدْ أَحَاطَ بِكُلِّ شَيْءٍ عِلْمًا [الطلاق: ١٢] «አላህ ያ ሰባት ሰማያትን ከምድርም መሰላቸውን የፈጠረ ነው፣ በመካከላቸው ትዕዛዙ ይወርዳል፦ አላህ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ መሆኑንና ሁሉን ነገር በዕውቀቱ እንዳካበበ ታውቁ ዘንድ» [አጥ-ጦላቅ 12]#አዎን! የዚህን ግዙፍ ዓለም ረቂቅ ሂደትና ክንውን የሚቆጣጠረውና የሚያስተናብረው ፈጣሪያችን ችሎታው ያለ ልኬት የመጠቀ፣ ጥበቡ ያለ አምሳያ የረቀቀ፣ ዕውቀቱ ያለ ገደብ የጠለቀ ስለመሆኑ የፍጥረተ-ዓለሙ ትዕይንት ራሱ መስካሪ ነው። ይህን ማወቃችንም ፍጥረታት ከተገኙበት ክቡር ዓላማዎች አንዱ መሆኑን የላይኛው አንቀፅ በግልፅ ያስረዳል። 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄
ማታ ከዚ ከዚ ጥያቄ ይወጣል እያነበባቹ ያጀማ 2;00 ይጀመራል
ይነበብብብብ
〰〰🍃#ሙሳ_ዐለይሂ_ሰላም🍃〰〰
ግዜው ዩሱፍ ዐ ሰ ከሞተ 97 አመታትን አስቆጥሯል።በዩሱፍ አማካኝነት የግብፅን ምድር ገብተው በመንፊስ ከተማ መኖር የጀመሩት የያዕቁብ ልጆች ሁሉ ሞተው አልቀው የልጅ ልጆቹ ግን በመተካካት ግብፅን እጅጉን እየሞሏት ነው።
ምንም እንኳን ያኔ በዩሱፍ (ዐ ሰ) ዘመን እነዚህ በኒ ኢስራኢሎች (የያዕቁብ ልጆች) በግብፅ ምድር የተከበሩ ሰዎች ቢሆኑም አሁን ላይ ያለው ንጉስ ግን እጅጉን ይበድላቸው ጀምሯል።
ይሄን ግዜ ነበር እንግዲ አላህ በኒ ኢስራኢሎችን ነፃ እንዲያወጣ ሙሳን የላከው።
የሙሳ የዘር ሀረግ፦
ሙሳ ኢብን...ዒምራን ኢብን...የስሀር ኢብን...ቃሂስ ኢብን...ላዊ ኢብን...ያዕቁብ ኢብን...ኢስሀቅ ኢብን...ኢብራሂም ኢብን....አዛር......ምናምን እያለ ይቀጥላል።
ሙሳ ከመወለዱ በፊት ፊርዐውን አንድ ቀን በህልሙ የሆነች እሳት ከእየሩሳሌም ወደ ግብፅ መጥታ የግብፃውያንን ቤት እየዞረች ታቃጥል'ና የበኒ ኢስራኢሎችን ቤት ስትተው ተመለከተ።
እና ይህ ህልም እረፍት የነሳው ንጉስ በነጋታው ጠንቋዮችን እና ኮከብ ቆጣሪዎችን ሰብስቦ የህልሙን ፍች ሲጠይቃቸው፦"ከነዚህ የያዕቁብ ልጆች(ከበኒ ኢስራኢሎች) አንድ ንግስናህን የሚሽር ልጅ ሊወለድ ነው" አሉት።
ፊርዐውን ይህን ሲሰማ በጣም በመደንገጥ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆችን እንዳለ እንዲገደሉ አዘዘ...ምንም አይነት ወንድ ልጅም ቢረገዝ እንደሚገድልም ትዕዛዝ አስተላለፈ።
የፊርዐውን ትዕዛዝ መተግበር ተጀመረ...በጣም ለቁጥር የሚያዳግቱ የበኒ ኢስራኢል ወንድ ልጆች እንደ ገፍ ተገደሉ። በመጨረሻም ይህ ህግ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት የግብፅ ህዝብ አቤቱታ ሲያቀርብ ፊርዐውንም ዘወትር የሚተገበረውን የግድያ ተግባር አንድ አመት ግድያ እንዲቆም እና አንድ አመት እንዲገደል አደረገ.....
በዚህ ሁኔታ ነበር የማይገደልበት አመት ላይ ሀሩን የተባለው የሙሳ ወንድም ተወልዶ፤ በሚገደልበት አመት ደሞ ሙሳ የተወለደው።
ሙሳ ልክ እንደተወለደ የሙሳ እናት ህፃኗን አይኗ እያየ እንዳይገድሉባት በጣም ተጨነከች።ምታደርገው ጠፍቷት በመዋለል ላይ ሳለች አላህም እናትየውን ከእንጨት የሆነ ሳጥን ሰርታ፤በዚያ ሳጥን ውስጥ ህፃኑን እንድታስገባው'ና ሳጥኑንም ከነ ህፃኑ ወንዝ ላይ እንድትጥለው አዟት፤ ይህንንም ህፃን ነቢይ አድርጎ እንደሚመልስላት ቃል ገባላት።
በዚህ መሰረት የሙሳ እናት ህፃን ልጇን በጨርቅ ጠቅልላ በሳጥን አሽጋ ሆዷ እየባባ በናይል ወንዝ አሻግራ ሸኘችው።
ውሀውም ሳጥኑን ከነ ህፃኑ እያንሳፈፈ የልጆችን ግድያ ትዕዛዝ ወደሰጠው ፊርዐን ግቢ ይዞት ገባ።በሰዐቱ የፊርዐውን የሚስቱ አገልጋዮች እዚያ ወንዝ ዳር እየታጠቡ ነበር'ና ይህን ሳጥን ሲመለከቱ በውስጡ ወርቅ ያለ መስሏቸው ለእመቤታቸው ሳጥኑን ሳይከፍቱ በስጦታ መልክ ወስደው አስረከቧት።
የሙሳ እህት እዚያ ቤተ መንግስት ውስጥ ተቀጥራ ትሰራ ነበር'ና እናቷ የጣለችው ሳጥን በገዳዮች እጅ መግባቱን ስታረጋግጥ ወደ እናቷ ስትከንፍ ሄዳ ነገረቻት።እናትም ልጇን ተመልሳ ሄዳ ሁኔታውን እንድታጣራላት ላከቻት። ልጅቷም ሁኔታውን ለማጣራት ቤተመንግስት ተመልሳ መጣች።
ንግስቲቱም አገልጋዮቿ እና ባለቤቷ ባሉበት ቦታ ሳጥኑ እንዲከፈት አዘዘች፤ሳጥኑ ሲከፈትም ልብን የሚያማልል ውብ እና ማራኪ ልጅ በሳጥኑ አገኙ።የፊርዐውን ሚስት ልጅ መውለድ አትችልም ነበር'ና፦"ልጅ ስለሌለን እባክህ ይሄን ህፃን አትግደለው።ወደ ፊትም ልጃችን አድርገን እንይዘዋለን " አለችው።
እሱ ህፃኑን መግደል ቢፈልግም የሚስቱን ሀሳብ መቃረን አልፈለገም'ና በሀሳቧ ተስማማ።
አሁን አስቸጋሪው ነገር መጣ....ይህን ምግብ ያልጀመረ ህፃን ማን ያጥባው??????
የተለያዩ አጥቢ እናቶች ይህን ህፃን ሊያጠቡ ቢሞክሩም ህፃኑ ግን የማንንም ጡት ከአፉ ሊያስጠጋ ፍቃደኛ አልሆነም።ይልቁኑ አጥቢዎቹ ሲመጡ ይባስ ያለቅስ ነበር።
የፊርዐውንም ሚስት እጅጉን ተጨነቀች አላህ በልቧ የሙሳን ፍቅር ስለከተበባትም በህፃኑ ለቅሶ ጭንቀት ምትገባበት ጠፋት።
ይሁ ሁሉ ሲሆን ሁኔታዎችን ትከታተል የነበረችው የሙሳ እህት ምንም እንደማያውቅ ሆና፦"ይህን ህፃን ለናንተ የሚያሳድግላችሁን ቤተሰብ ለመላክታችሁ!! ታማኝም ናቸው" አለቻት።
የህን ስትሰማ የፊርዐውን ሚስት ደስታዋ ወደር አጣ።የፈለጉትን ክፍያም ለአጥቢዋ እንደሚከፍሉም ቃሉ ገቡላት'ና የሙሳ ትክክለኛዋ እናት እንድትመጣ አደረጉ።
የሙሳ እናት ቤተ መንግስት ገብታ ልክ ልጇን ስትመለከት ልቧ ተንሰፈሰፈ...፣እንባዋ ከአይኗ ሊሾልክ ተቃረበ።እንደምንም ራሷን ተቋቁማ ህፃኑን ልታጠባ ስታቅፈው ህፃኑ ለቅሶውን ትቶ ጡቷን ይሞጥሙጥ ጀመር።ፊርዐውን እና ኣሲያ(የፊርዐውን ሚስት) ይህን ሲመለከቱ በጣም ተደሰቱ።
በዚህ ሁኔታ የሙሳ እናት እየተከፈላት ልጇን ለ2 አመታት ያህል አጠባችው።
ግዜ ግዜን እየተካ ሙሳም ትልቅ ልጅ ሆነ።ምንም እንኳን ሙሳ የፊርዐውን ያብራኩ ክፋይ ባይሆንም በህዝቡ ዘንድ ግን የፊርዐውን ልጅ በመባል ነው ሚታወቀው።
ከእለታት አንድ ቀን ሙሳ በጠራራ ፀሀይ ከተማ ውስጥ እየተራመደ ሳለ አንድ ግብፃዊ እና አንድ በኒ ኢስራኢላዊ ሲደባደቡ ተመለከተ። በኒ ኢስራኢላዊውም ሙሳን አድነኝ በማለት ተጣራ።
ሙሳም ይህን ግዜ ግብፃዊው ላይ ገራሚ ቦክስ ሰነዘረበት'ና ሳያስበው የግብፃዊው ህይወት በሙሳ እጅ አለፈች።ይሁን እንጂ ማንም አላወቀበትም ነበር።
ይሄን ግዜ ሙሳ በጣም በመፀፀት አላህን ምህረት ለመነው። አላህም ተውበቱን ተቀብሎት፦"ሙሳ ሆይ! በልቅናዬ እምላለሁ ይህች የገደልካት ነፍስ ለቅፅበት እንኳን በኔ ጌትነት ያመነች ብትሆን ከባድ ቅጣትን አቀምስህ ነበር" አለው።
ሙሳም ከዚያ ቀን አንስቶ የግብፃዊው ሟች ወገን መጥተው እንዳይበቀሉት በጣም ስለሰጋ እንቅስቃሴውን በጥንቃቄ ማድረግ ጀመረ።
በማግስቱም ሙሳ ከተማ ላይ ሳለ ይህ ትናንት ሲደባደብ የነበረው (በኒ ኢስራኢላዊው) የሙሳ ዘመድ ዛሬም ከሌላ ግብፃዊ ጋር ሲደባደብ ተመለከተው።
የሙሳ ዘመድ ሙሳን ሲመለከት ዛሬም የእርዳታ ጥሪውን ለሙሳ አሰማ።
ሙሳም ወገኑን(በኒ ኢስራኢሉን) ሲመለከት፦"አንተ በእርግጥ ግልጽ ጠማማ ነህ" አለው።
ወገኑም፦"በትናንትናው ቀን ነፍስን እንደ ገደልክ ልትገድለኝ ትፈልጋለህን በምድር ለይ ጨካኝ መሆንን እንጅ ሌላ አትፈልግም፡፡ ከመልካም ሠሪዎችም መሆንን አትፈልግም" አለው።
በዚያ አካባቢ የነበሩ የግብፅ ነዋሪያንም ወገናቸውን የገደለው ሙሳ መሆኑን ሲያውቁ እሱን ሊገድሉት መመካከር ጀመሩ።
ይህን የሰማ ሂዝቂል የተባለ ግብፃዊ ሙእሚን ለሙሳ፦"ግብፃውያን አንተን ሊገድሉ እየተመካከሩ ስለሆነ የግብፅን ምድር ለቅቀህ እንድትወጣ እመክርሀለሁ" ብሎ መከረው።
ሙሳም የግብፅን ምድር ትቶ በረሀውን እያቆራረጠ እግሩ ወደ መራው ቦታ መጓዝ ጀመረ።ብዙ ተጉዞ ረሀብ፣ጥማት እና ድካም ድንበር አልፈው ካዳከሙት በኋላ መድየን የምትባል ሀገር ደረሰ።
ሙሳ በከተማዋ መግቢያ ላይም ሲደርስ የመድየን ከተማ ነዋሪያን በሙሉ እንስሳዎቻቸውን ውሀ የሚያጠጡበትን አንድ ምንጭ ቦታ ደረሰ።ልክ እዛ ሲደርስ......
እስከዚ ነው አንብቡቡቡቡ
ትልቁ ሙሲባ ብሎ ማለት ሶብርን ማጣት ነው ።
የሙሲባን አይነት የምናስተናግደው አንድ መከራ ሲገጥመን ካለመታገሳችን ቆም ብለን ካለ ማሰባችን ነው።
ሶብር ከማጣት ጀርባ ብዙ ችግር አሉ ሚፈጠሩ አላህ በሁሉም ነገር ላይ ታጋሾች ያድርገን !!
•━════✿🍃🌺🍃✿════━•
በርካታ የዱንያን ፈተናዎች እና ደስ የማይሉ የሚረብሹ ስሜቶችን በየቀኑ እንታገላለን በዚህ ሁሉ መሀል ደህና መስለን ለመታየት የምናደርገው ጥረትም ሌላው ከባድ ትግል ነው
ያለንበትን ሁኔታ ሳያውቁ
በርቱ ቀላል ነው ይላሉ።
ሁሉም ሲወራ እኮ ቀላል ነው
ሲኖር ግን....ከባድ ነው!!
ሁልጊዜ ለሰዎች ጥሩ ሰው ሁን፤ ነገር ግን ራስህን አትጣ። ሰዎችን አክብር፣ ነገር ግን ክብርህን አታስቀንስ። መልካም ሥራ አድርግ ምስጋና ለመጠበቅ ሳይሆን አላህን ለማስደሰት። በችግር ጊዜ ታጋሽ ሁን፣ በደስታ ጊዜ አመስጋኝ ሁን፣ በሁሉም ሁኔታ ወደ አላህ ተመለስ። ህይወት አጭር ናት፤ ስለዚህ ጥላቻን ተው፣ ፍቅርን አስፋፋ፣ መልካም ስምን ተው እንጂ ክፉ አሻራ አትተው።"🌷
"የሰው እውነተኛ ውበት በመልካም ስነ-ምግባሩ እንጂ በመልኩ አይደለም
📖 እውነተኛ የወጣትነት ጥንካሬ በወጣትነት አላህን ማወቅ ነው!
እንደ ጃሂሎች ወጣትነ የፈለከው ምታደርግበት ፣የሻህ ምትሄድበት ፣ብዙ ነገራቶች በድፍረት ምንገባበት አይደለም!
አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣን ውስጥ ስለ ካህፍ ባለቤቶች (ወጣቶች) ሲናገር እንዲህ ይላል፦
﴿إِنَّهُمْ فِتْيَةٌ آمَنُوا بِرَبِّهِمْ وَزِدْنَاهُمْ هُدًى﴾
(ሱረቱል ካህፍ፡ 13)
"እነርሱ በጌታቸው ያመኑ ወጣቶች ናቸው፤ ቅን መሪነትንም (ሂዳያን) ጨመርንላቸው።"
ወጣትነት በእምነት እና በመልካም ስነ-ምግባር ሲከበቡ ለዱንያም ለኣኺራም ስኬት መነሻ ይሆናል። አላህ ወጣትነታችንን በበጎ መንገድ የሚያሳልፉ ያድርገን! 🤲
Share & join: -https://t.me/yemuslimwetatochdimts
♡ ከተብቃቃህ ትንሹ ብዙ ነው
⇨ ከተስገበገብክ ብዙው ትንሽ ነው
⇨ ከወደድክ ሩቁ ቅርብ ነው
⇨ ከጠላህ ቅርቡ ሩቅ ነው
ዱዓን ሲያምህ ብቻ እንደምትጠቀመው መድሃኒት አድርገህ አትመልከት፤
ባይሆን ዱዓን እንደምትተነፍሰው አየር ነው መመልከት ያለብህ፡፡ በሰላሙም በደስታዉም፣ በችግሩም በሀሴቱም ጊዜ ተጠቀምበት💫
ኢላሂ… 🤲
ሰዎች ባወቁት ማንነቴ ወደዱኝ፣ አንተ ግን ሁሉንም እያወቅክ ማርከኝ። ሸፈንከኝ።አስከበርከኝ።ነውሬን ደበቅክልኝ።
ጌታዬ ሆይ! በሰማይና በምድር መካከል ካንተ የተሻለ መሸሸጊያ የለኝም፤ የዛለችውን ነፍሴን በእዝነትህ ፈውሳት።
✨በሙሉ ልብህ ወደ አላህ ዙር
ሁሉ ነገር ወዳንተ ይዞርልሃል
ጁመአ እንዴት ነበር አሕባብ
1 🤩
2 🥰
3 😴
4 😇
5 😔
💜 ንስሮች ዝም ሲሉ
በቀቀኖች መለፍለፍ ይጀምራሉ
ዛሬጁመአ ነው ሰለዋት አሕባብ🥰
اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّد
