ru
Feedback
የጥበብ እመቤት 📜

የጥበብ እመቤት 📜

Открыть в Telegram

╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️‍🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
270
Подписчики
+224 часа
+107 дней
+15330 день
Количество постов

Загрузка данных...

Реакции
Комментарии
Telegram Stars
ТОП постов по

Загрузка данных...

Анализ публикаций
Посты
Динамика просмотров
የልቤ ❤️👑❤️ ናፍቆት ነህ ለልቤ የ"ፍቅር"ረሃቤ ላፍታም አልዘነጋህ አጠፋም ከሀሳቤ ንግግሬ መሀል ስምህ አፌ ላይ ነው ሰከንድ አትባክንም ሳነሳህ ውላለው። ሱሴ ነህ ማልተውህ ዘወትር ሁልጊዜ የህይወቴ ድምቀት ፈገግታ ነህ ወዜ ከምታውቀው በላይ ከቃላት የሚልቅ ላንተ ፍቅር አለኝ ብነግርህ የማያልቅ። ቃላትህ ፈውስ ነው አዎን ይጠግናል በፍቅር ማከሙን ሁሉን ያውቅበታል ልቤ ምርኮኛህ ነው ባንተ የተሸነፈ ስላንተ በማሰብ ለአንዴም ያላረፈ። ❤️👑❤️ 🌹 🌹🌹 🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ❤️👑❤️ 🌹🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹🌹 🌹🌹🌹 🌹🌹 🌹
14010Loading...
🌹🩷የኔ ንግስት🩷🌹 አንቺ ማለት ለእኔ... የህይወቴ ፀዳል፣ የልቤ እርካታ... የነፍሴ ማረፊያ፤ ካንቺ ጋር ሲሆንማ... ቀኑም ይደምቃል፣ የፍቅርሽ መዓዛ... ከሁሉም ይልቃል። ውብ ስጦታዬ ነሽ... ከሰማይ የደረስሽ፣ ልቤን የገዛሽው... በንፁህ ስስትሽ፤ እስካለች ድረስማ... ይህች አጭር ህይወቴ፣ ሁሌም እወድሻለሁ... የኔ ውድ እመቤቴ። ❣❣❣❣❣❣❣
17000Loading...
//ወፍ በሆንኩኝ//      ❤️❤ ❤️❤   ምንአለ ለዛሬ በሆንኩኝ እና ወፋ፤   በክንፌ በርሬ ግቢአችሁ ለማረፍ፤   ስትገባ-ስትወጣ አንተን እያየሁኝ፤   ለsecondat እንኳን ምነዉ ወፍ በሆንኩኝ፤   ፍቅርህን ሰርቄ ይዠው በበረርኩኝ፤   ❤️❤️❤️❤️❤️❤️                         
18000Loading...
❣💕💞💕💞💕💞❣       💖አፈቅርሻለሁ💖 ውስጤ ያለውን ስሜት ባይገልፁትም ቃላት ልቤ ሲለው አፌን "አፈቅርሻለሁ በላት" የረታሽው ልቤ በናፍቆት ቢጠቃም ወደድኩሽ ያልኩሽም አውቃለሁ አይበቃም :: 💞እወጅሻለሁ💞
19000Loading...
💞🌺💞🌺💞🌺💞🌺💞🌺 . . . #ፀሎቴ . . . ምነው ባደረገኝ ያንገትህ ላይ መስቀል፣ ከደረትህ መሀል ሁሌ እንድንጠለጠል፣ ምነው ባደረገኝ የእግርህን አልቦ፣ ሲናፍቅ ከሚኖር ልቤ አንተን ተርቦ፣ እዘለኝ በጀርባህ ልረፍ ከወገብህ፣ ውሃ ተሸክሜ ገንቦውን ሆኜልኝ፣ መደብህስ ብሆን እንደው ምን አለበት፣ የዛለው አካልህ ምታሳርፍበት፣ ተጫማኝ ግዴለም ጫማ ልሁንና፣ አብሬህ ልኳትን በዱር በጎዳና፣ ልበሰኝ ልብስ ሆኜ እርቃንህን ልጋርድ፣ ከገዳዩ ገላህ አጥብቄ ልዋደድ፣ ልሁን ሽፋሽፍትህ ከአይንህ ስር ልኑር፣ ነቅቼ ልጠብቅ ልክ እንደ ወታደር፣ ሸብ አርገህ እሰረኝ አዳሜ ከወገብህ፣ አጥብቄ ልቀፍህ ሆኜ ቀቦተህ፣ ንጉሴ ሆንና ንግስት ሆንልሀለሁ፣ ያልከኝን በፍቅር እታዘዝልለሁ፣ ምንጣፍም ያድርገኝ ለእግርህ መረገጫ፣ ምቾት እንዲሰማህ እንዳይነካህ ጭንጫ፣ ምነው በሆንኩና አዝማሪ የቤትህ ማስቆዬን ይዤ እልፍ ባዜምልህ ልክ እንደ በውቀቱ ዕውቀትን ቢያድለኝ፣ ምን ነበር ስላንተ ገድል ቢያስከትበኝ፣ ውሃመም ያርገኝና ልፍሰስ ከበላይህ በጉንጭህ ወርጂ ልሙት ከደረትህ አንዴ ብሆን ምነው የመሶብ እንጀራ፣ ተዋድጄ በኖርኩ ከአንጀትህ ጋራ፣ ፀሎቴ . . . አንተን የኔ ብቻ የግሌ እንዳረግህ ፀሎቴ ይሄ ነው እንድያርገኝ ዘመድህ፡፡ ✍ሄዋን ያንተው ስደተኛ             ❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹❣🌹            
18010Loading...
አለሁልሽ ካንቺው ጋር የብቸኝነትሽን... የስጋትሽን ዜማ፣ ልቤ አዳምጦታል ካንቺው ጋር በፅኑማ። የከበበሽ ጭጋግ፥ የከበደሽ የብቻነት ስሜት፣ እንዲበን አደርገዋለሁ... በፍቅራችን እውነት። እኔ እያለሁልሽ... ከጎንሽ ቆሜ፣ ብቸኝነት አይገዛሽም... አይደርስም ዘመኔ። ክንዴን እዘረጋለሁ... ልብሽን ልደግፈው፣ የብቻነትሽን ዋይታ... በሳቅ ልለውጠው። አትፍሪ የኔ ውድ... እጅሽን አልለቅም፣ ከጎንሽ ነኝ ሁሌም... ፈፅሞ አልርቅም። የፍቅራችን መሰረት... እምነታችን ፀንቶ፣ ያለሽበት እደርሳለሁ... የብቻነትሽን ግንብ ንዶ። ————————
20020Loading...
ወጣቱ አዛውንቱን ለመፈተን ተንኮል አሰበ። አንድ ትንሽ ወፍ በእጁ ይዞ "በእጄ ያለችው ወፍ በህይወት አለች ወይስ ሞታለች?" ብሎ ጠየቀው። ... የወጣቱ እቅድ፤ አዛውንቱ "በህይወት አለች" ካለ እጁ
ወጣቱ አዛውንቱን ለመፈተን ተንኮል አሰበ። አንድ ትንሽ ወፍ በእጁ ይዞ "በእጄ ያለችው ወፍ በህይወት አለች ወይስ ሞታለች?" ብሎ ጠየቀው። ... የወጣቱ እቅድ፤ አዛውንቱ "በህይወት አለች" ካለ እጁን ጨምቆ ሊገድላት፣ "ሞታለች" ካለ ደግሞ እጁን ከፍቶ ሊያበራት ነበር። በየትኛውም መንገድ አዛውንቱን ስህተት አድርጎ ሊያስቆጥረው አድብቷል። ... አዛውንቱ የወጣቱን ተንኮል ወዲያውኑ ስላነበበበት፣ "ልጄ መልሱ ያለው በአንተ እጅ ላይ ነው።" አለው። ... አንዳንድ ሰው ወስኖ በጨረሰ ጉዳይ ላይ አስተያየትህን ለይስሙላ ይጠይቅሃል፤ አንድም በተንኮል ለማጥመድና ስህተትህን ለመፈለግ፤ በሌላ ደግሞ ለማስመሰል። አንተ ግን ለተንኮላቸው አትመች።
20000Loading...
የብቸኝነት ጥላ ሰፊው ዓለም ጠቦኝ ሰው በሞላበት ብርሀኑ ጠፍቶብኝ በጨላማ እውነት የብቸኝነት ጥላ በላዬ ላይ አጥልቶ የሳቅኩበት ዘመን እንደጉም በኖ ከሰው ማሀል ሁኜ ሰው ናፈቀው ልቤ ትዝታህ ብቻ ነ
የብቸኝነት ጥላ ሰፊው ዓለም ጠቦኝ ሰው በሞላበት ብርሀኑ ጠፍቶብኝ በጨላማ እውነት የብቸኝነት ጥላ በላዬ ላይ አጥልቶ የሳቅኩበት ዘመን እንደጉም በኖ ከሰው ማሀል ሁኜ ሰው ናፈቀው ልቤ ትዝታህ ብቻ ነው ሚዞረው ከብቦኝ ብቻዬ ስኳትን በሰው መሀል ቁሜ ባዶነት ገደለኝ ደማብኝ አካሌ ድምፅህ ለመስማት ጆሮዬ ቢጓጓም ያለፈው ትዝታ ዛሬ አይመልስልኚም ብቸኝነት ጥላ ተከብቤ ዛሬ በናፍቆት ተቀጣሁ ጠፍቶብኝ መኖሬ።
26000Loading...
If you are depressed You art living in the past. If you are anxious.you are Living in the future . You are living in the present. ✍️ Lao.Tzu
33000Loading...
አስመሳይ .... ሁሌ ልወደድ ባይ ለሰው ጥሩ መሳይ ንግግሩ ካፉ ፍቅሩ ካንገት በላይ የቆመ ከሰው ጋር ሰው መስሎ የሚታይ። ስቆ ሚያታልል ልሙት ብሎ እሚምል ወዳጅ መሰሎ ቀርቦ የሚወጋ ከቦ ከዛ ሰው ተጠንቀቁ ስለሳቀ አትሳቁ ከላይ ወዳጅ መስሎ የእውነት አፍቃሪ አስመሳይ ክፉ ነወ ሳይሞቱ ቀባሪ
38000Loading...
ስለ ህይወት.... ወጣ ውረድ የህይወት መንገድ ነው ነገር ግን ማቆያ ቦታ አይደለም በትዕግስት መፅናት ማለት ወደ ስኬት መድረሻ ምዕራፍ መግባት ማለት ነው። ሀዘን በደስታ መከራ በስኬት የሚተካው የፅ
ስለ ህይወት.... ወጣ ውረድ የህይወት መንገድ ነው ነገር ግን ማቆያ ቦታ አይደለም በትዕግስት መፅናት ማለት ወደ ስኬት መድረሻ ምዕራፍ መግባት ማለት ነው። ሀዘን በደስታ መከራ በስኬት የሚተካው የፅናት ዋጋ ሲከፈል ነው።የትዕግስት ፍሬዋ ሲቀመስ ሁሉም መራራ ነገር ይረሳል።
39000Loading...
M✍️ለአዕምሮ ሠላም የሚሰጡ የጥበብ መንገዶች ✍️1.ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር። ✍️2.ከሚረብሹህ ሰዎች ራስህን አርቅ፡ ✍️3.ሁልጊዜ ለፈጣሪህ ምስጋና አቅርብ። ✍️4. የሁሉንም ሰው ደስታን መ
M✍️ለአዕምሮ ሠላም የሚሰጡ የጥበብ መንገዶች ✍️1.ራስህን ከማንም ጋር አታወዳድር። ✍️2.ከሚረብሹህ ሰዎች ራስህን አርቅ፡ ✍️3.ሁልጊዜ ለፈጣሪህ ምስጋና አቅርብ። ✍️4. የሁሉንም ሰው ደስታን መጠበቅ አቁም:: ✍️5. ቂም መያዝ የራስን ቤት እንደ ማቃጠል ነው። ✍️6. በዛሬው በረከትህ ላይ ትኩረት አድርግ። ✍️7.ስለማትቀይረው ነገር መጨነቅን ተው። ✍️8.ደስታህን በሰዎች እጅ ላይ አታድርግ። ✍️9.ትናንት ላለፈው ስህተት ራስህን አትቅጣ።
93100Loading...
*_<<ተወዳጆች>>_* *(ስለ ልብ መታወክና ስለ እምነት)* *"ልጄ ሆይ፣* በውስጥህ የጭንቀትና የፍርሃት ማዕበል ሲነሳብህ አትደንግጥ። የነፍስ ጠላት ሰይጣን አንተን ተስፋ ለማስቆ
*_<<ተወዳጆች>>_* *(ስለ ልብ መታወክና ስለ እምነት)* *"ልጄ ሆይ፣* በውስጥህ የጭንቀትና የፍርሃት ማዕበል ሲነሳብህ አትደንግጥ። የነፍስ ጠላት ሰይጣን አንተን ተስፋ ለማስቆረጥና ካለህበት መስመር ለማውጣት በትዝታዎች፣ በጥርጣሬዎችና በትልልቅ የጭንቀት ሐሳቦች ልብህን ይወጋዋል። በእነዚህ ሐሳቦች ላይ አትደገፍ፣ አትከራከራቸውም። ልብህ ግራ ሲጋባ ‘ *ጌታ ሆይ* ፣ እኔ ደካማ ነኝና አንተ እርዳኝ፣ አንተ ጠብቀኝ’ በማለት ራስህን ዝቅ አድርግ። ሰይጣን አንተን ሊያጠፋህ ሲመጣ፣ አንተ ወደ እግዚአብሔር ስትሸሽ ያኔ ኃይሉ ይደክማል። ጭንቀትህ የቱንም ያህል ታላቅ ቢሆን፣ የእግዚአብሔር ምሕረት ግን ከዚያ በላይ ሰፊ ነው። ዛሬ የምታየው ጨለማ ነገ ብርሃን ሆኖ ያልፋል። ጽኑ ሁን፣ በትዕግሥትም ጠብቀው።"
42000Loading...
የሚያጽናናሽ ሁሉ ራሱ ቁስል የሌለበት አይደለም" የሚሰጥሽም ሁሉ ከአንቺ የበለጠ ያለው ሰው አይደለም መስጠት ገንዘብ ወይም ንብረት ብቻ መካፈል አይደለም፤ አንዳንድ ሰዎች የቀራቸውን ትዕግስት ያካፍሉ
የሚያጽናናሽ ሁሉ ራሱ ቁስል የሌለበት አይደለም" የሚሰጥሽም ሁሉ ከአንቺ የበለጠ ያለው ሰው አይደለም መስጠት ገንዘብ ወይም ንብረት ብቻ መካፈል አይደለም፤ አንዳንድ ሰዎች የቀራቸውን ትዕግስት ያካፍሉሻል በልባቸው የቀረውን ተስፋ ይሰጡሻል ከራሳቸው ረጅም ሀዘን በፊት የመጨረሻዋን ፈገግታ እንኳ ከአንቺ ጋር ይካፈላሉ " ስለዚህ ለሚያሳዩሽ ፍቅርና ደግነት አክብሮት ስጪ' #ያ በእውነት ውድ ነውና»
42000Loading...
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ሕይወት ብርሃንና ጥላ ድብልቅልቅ ያለባት መድረክ ናት። አስደሳች ጊዜያት እንደ ብርሃን ሆነው ሲታዩን፣ ፈተናዎች ደግሞ የጥላውን ክፍል ይወክላሉ። ብዙውን ጊዜ ብርሃኑን ብቻ እ
➨#ወዳጄ_ሆይ_አስተውል ሕይወት ብርሃንና ጥላ ድብልቅልቅ ያለባት መድረክ ናት። አስደሳች ጊዜያት እንደ ብርሃን ሆነው ሲታዩን፣ ፈተናዎች ደግሞ የጥላውን ክፍል ይወክላሉ። ብዙውን ጊዜ ብርሃኑን ብቻ እንፈልጋለን፣ ጥላውን እንሸሸዋለን። ነገር ግን፣ ብርሃን ያለ ጥላ ትርጉም አይኖረውም፤ ጥላም ያለ ብርሃን ሊኖር አይችልም። ጨለማ የብርሃንን ዋጋ ያስታውሰናል፣ ፈተናዎች ደግሞ ውስጣዊ ጥንካሬያችንን ያጎለብቱታል። እያንዳንዱ የሕይወት ምዕራፍ፣ መልካምም ይሁን አስቸጋሪ፣ የራሱ የሆነ ትምህርት ይዞ ይመጣል። እነዚህን ሁለቱን ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ስንቀበል፣ ሕይወትን በሙሉ ምሉዕነቷ የመኖር ጥበብ ይገለጥልናል። #Never_give_up https://t.me/payattetion12
33000Loading...
ትርጉም የለሽ ግቦች ካላቸው መሀከል አትሁን👌 ​አንድ ገበሬ ሁልጊዜ በመንገድ ዳር እየተቀመጠ መኪና እስኪያልፍ የሚጠብቅ ውሻ ነበረው። አንድ መኪና ብቅ ሲል ብቻ ውሻው እየጮኸና ለመቅደም እየሞከረ
ትርጉም የለሽ ግቦች ካላቸው መሀከል አትሁን👌 ​አንድ ገበሬ ሁልጊዜ በመንገድ ዳር እየተቀመጠ መኪና እስኪያልፍ የሚጠብቅ ውሻ ነበረው። አንድ መኪና ብቅ ሲል ብቻ ውሻው እየጮኸና ለመቅደም እየሞከረ በመንገዱ ላይ ይሮጥ ነበር። ​አንድ ቀን ጎረቤቱ ገበሬውን፣ "ለመሆኑ ውሻህ መኪና ደርሶ የሚይዝ ይመስልሃል?" ብሎ ጠየቀው። ​ገበሬውም፣ "የሚያስጨንቀኝ እሱ አይደለም። የሚያስጨንቀኝማ አንድ ቀን መኪናውን ቢይዘው ምን ሊያደርገው ነው?" ብሎ መለሰለት። ​በህይወት ውስጥ ብዙ ሰዎች ልክ እንደ ውሻው በትርጉም የለሽ ግቦችን ይኖራሉ።
43000Loading...
"ጠንካራ ስዎች ግን እንዴት ደስ ይላሉ የማንም ሙገሳ የማንም ወቀሳ ከፍ ዝቅ የማያደርጋቸው እራሳቸዉን ሆነው የሚኖሩ ከመጣዉ መአበል ጋር የማይሽራተቱ ጀግኖች ያስድስቱኛል::🌸💜🦋
"ጠንካራ ስዎች ግን እንዴት ደስ ይላሉ የማንም ሙገሳ የማንም ወቀሳ ከፍ ዝቅ የማያደርጋቸው እራሳቸዉን ሆነው የሚኖሩ ከመጣዉ መአበል ጋር የማይሽራተቱ ጀግኖች ያስድስቱኛል::🌸💜🦋
39100Loading...
አንዳንዱ ጋር ቸኩዬ አንዳንዱ ጋ ዘግይቼ ዋጋ ከፍያለሁ ። አንዳንዱ ጋር ጥጋቤ አንዳንዱ ጋ ትህትናዬ አስገምቶኛል። አንዳንዱ ጋር መጠየቄ አንዳንዱ ጋ ዝምታዬ ጥያቄ አስነስቷል። አንዳንዱ ጋር ጥንቃቄ
አንዳንዱ ጋር ቸኩዬ አንዳንዱ ጋ ዘግይቼ ዋጋ ከፍያለሁ ። አንዳንዱ ጋር ጥጋቤ አንዳንዱ ጋ ትህትናዬ አስገምቶኛል። አንዳንዱ ጋር መጠየቄ አንዳንዱ ጋ ዝምታዬ ጥያቄ አስነስቷል። አንዳንዱ ጋር ጥንቃቄ አንዳንዱ ጋ ግዴለሽነቴ አስመርምሮኛል ። አንዳንዱ ጋር ጨዋነቴ አንዳንዱ ጋ ብልግናዬ ረብሿል። አንዳንዱ ጋር አማኝነቴ አንዳንዱ ጋ አህዛብነቴ አጠያይቋል። አንዳንዱ ጋር ቸርነቴ አንዳንዱ ጋ ስስቴ አስገርሟል !!
43100Loading...
እኛው ነን ጠላትሽ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 ሀገሬ ዘመንሽ በጠመንጃ ገዝፎ ሰክኖ በመነጋገር ሰላም ፍቅር ሰንፎ ሁሉም ለወንበሩ ሲሞተና ሲገደል በየቦታው ሲወድቅና ሲጣል ጠላቶችሽ ሁነን ልጆችሽ በጋራ ከሩቅ ሳይሆን ፍዳሽ የቅረቡ ጎመራ ዘመን እየሄደ ዘመን እየመጣ ቢለያይም ቅሉ ሁሌም ያንቺ ጣጣ ከእኛ ነው መነሻው የሰላምሽ ጥልመት ከጎራዴም አያልፍም የሩቅማ ጠላት ። እኛ ነን ጠላትሽ🇪🇹🇪🇹😢
48000Loading...
ናፍቀሺኛል ብየ ናፍቀሺኛል ብየ ለመጮህ አልወጣ ሰውም ቢያፌዝ እንጂ አንቺን ይዞ አይመጣ ናፍቀሺኛል ብየ እኔም ግጥም አልፅፍ ምን ቤቱን ቢመታ ህመም አያሳልፍ ብቻ ናፍቀሺኛ.....ናፍቀሺኛል በጣም
ናፍቀሺኛል ብየ ናፍቀሺኛል ብየ ለመጮህ አልወጣ ሰውም ቢያፌዝ እንጂ አንቺን ይዞ አይመጣ ናፍቀሺኛል ብየ እኔም ግጥም አልፅፍ ምን ቤቱን ቢመታ ህመም አያሳልፍ ብቻ ናፍቀሺኛ.....ናፍቀሺኛል በጣም
51100Loading...