የጥበብ እመቤት 📜
Open in Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
271
Subscribers
-124 hours
+77 days
+15230 days
Posts Archive
271
ሄዋኔ ላንቺ ስል
በልሳኔ እሾህ አንቺን ከምጎዳ ቃል በምጥ ልጣ ልመደብ ከዱዳ መቼስ ታውቂው የለ ቃልና አቅሙ ምድር እንዲ የረጋው ሰማይም መቆሙ ከቶ አይደለም ሌላ ቃል ነው ሚስጥሩ የመኖሩ ምክንያት የፍጡር ቀመሩ እናም ቃል ተፍቼ አንቺን ከማደማ ልሳኔ ተጣብቆ ያንቺን ቅኝት ልስማ፡፡
271
ከትናንት እና ከነገ የቱ ይቀርባል ? አልኩት
እሱም.... ❝እንደመንገዱ ነው።❞ አለኝ
እንዴት ? አልኩት
እሱም.......
❝በትዝታ መንገድ ከተጓዝክ ትናንት፤ በተስፋ መንገድ ከሄድክ ነገ❞ አለኝ።
271
እንባዬን የት ላርገው?
ቀና በይ ይሉኛል-- ወዴት ልበል ቀና
ከላይ ተደፍቶብኝ- አገር እንደቁና
ጣራው ባጡ ቀርቦኝ
በር አልባ ግድግዳ- እንደ ዝናር ከቦኝ
በጫጩት ጉልበቴ- እየተወራጨሁ
እንባየን ዘግኘ- ሽቅብ እየረጨሁ፤
ወደ አማልክት ብጮህ-ጠሎቴን አይሰሙት
በየት በኩል ኖሬ፤
በየት በኩል ልሙት::
በምን ይገለፃል- የትውልዴ አበሳ
ከመንበርከክ ብዛት- መራመድ የረሳ
ያልፋል ተለጉሞ
ያልፋል ተከርችሞ
የጉልበቱን ኮቴ- ምድር ላይ አትሞ::
ወፈፌ ቀን አልፎ- እብድ ቀን ሲመጣ
ማልቀስ አመፅ ሲሆን- በሸንጎ ሚያስቀጣ
እንባዬን የት ላርገው?
ወዴት ልሸሽገው?
271
አለ አይደል? ትግስቱን ልባችን እስከምን እደሚችለው እንጃ... ትንሽ ነገር ለራስ መተው ጥሩ ነው በደጉ ግዜ። ያለውን የሰጠ መጪውን አያውቅምና፣ የከፋ ግዜ ክፉ ሰው ላይ ሲጥል መሄጃ ይታጣል። ለመጠየቅም ቢሆን የምጠይቁበት ሁኔታ እና ሰው ያስፈልጋል፤ እና በደጉ ግዜ ትንሽ መውደድ፣ ትንሽ ገንዘብ፣ ትንሽ እውቀት... ብቻ ለራሳቹህ ከምትሰጡት ነገር ትንሽ አስቀሩ። ቀንና ዘመን ሲለወጥ ትፅናኑበታላችሁ።
271
❤️መውደቅ ማለት ❤️
ሲጥልህ አደለም ድንጋይ አጎላድፎ
ስትወድቅ አደለም የረገጥከው ጠልፎ
ስትቆስል አደለም በድንጋይ ተመተህ
ስትደማ አደለም ግንብ ጋር ተጋጭተህ
#መውደቅ ማለት የኔ ወንድም
ስትወድ ነው የሰው ገንዘብ
ስትቀና ነው በሰው ማግኘት
እንቅልፍ ስታጣ ነው የሰውን ሀቅ በመመኘት
ወውደቅ ማለት እንደዚህ ነው ከሰው በታች እሚያደርግህ
ለፍተው ጥረው ያገኙትን ያለምንም መሰዋትንት
ያንተ እንዲሆን ሲያስፈልግህ
#አየህ አደል መውደቅ ማለት
የራስህን መንገድ ትተህ ስትሄድ ነው በሰው መንገድ
ሲጎልህ ነው ስነ ምግባር ስታጣ ነው የሰው መውደድ
ሰማህ አደል መውደቅ ማለት እንደዚህ ነው ሰው ሲጠላህ
271
Repost from ⚜ከምጡቃን አንደበት⚜
"በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ካንተ ጋር ነውና ፅና ÷ በርታ ፤ አትፍራ ÷ አትደንግጥም። "መልካም ፈተና ይሁንላችሁ፤ይሁንልን 🙏🙏— ኢያሱ 1፡9
271
#pay_attation
ሰው ላይ እንድትፈርድ የሚያስቸኩልህ ባህሪ የሚያሳየው ሁሉንም ሰው ከአንተ በታች ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ነው።
አንድ ሰው ልእለ ሰብነት (ታላቅነት) ላይ ለመድረስ ታላቅ ንቃት ይጠይቃል። ከውስጣችሁ ካለው ተራራ ጫፍ ላይ መውጣት ይጠበቅባችኋል። ይህ ደግሞ አስቸጋሪ ይመስላል።
ስለዚህ ቀላሉና ርካሹ መንገዱ ራሳችሁን የበላይ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ ....ምንም ድካም እማያስፈልገው ሌሎችን የበታች አርጎ መቁጠር ነው።
ለዛ ነው ሰው ላይ ለመፍረድ የምትቸኩለው። ሌላው ላይ ለመፍረድ የምታደርገው ጥረት አንተ የተሻልክ እንደሆንክ ለማሳየት ያለህን ፍላጎት ያረጋግጣል። "ይህ ሰውየ እኮ ሌባ ነው፤ ይህ ሰውየ እኮ ሴት ተደፍሯል፤ ይህኮ የለየለት እብድ ነው.............."
ለሁሉም ሰው ልክ ታወጣና መጨረሻ አንተ ብቻ ንፁህ ሆነህ ትቀራለህ። ግን ሰው ላይ መፍረድ የዝቅተኛ ሰው መለያ ነው።
#Be carefull
271
➨#ወዳጄ_ሆይ_ታገስ
ያ ቀን ይመጣል!!!
በጅማሬህ የሚሳለቁብህ ፤ ዴንታ የማይኖራቸው ሰዎች ይኖራሉ ። ይህን የምልህ ከሩቅ ሰዎች ሳይሆን ቅርብ እና የእኔ የምትላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ከስራው ህመም ይልቅ የእነሱ ምላሽ ልብህን ይፍቀዋል። በዚህም የተነሳ ውስጥህ ከሚባለው በላይ ነው የሚጎዳው። ነገር ግን ወዳጄ ጀገን በልን፤ ይሄ ህይወት ነው፤ አንተ የተሰማህ እና የታያህ ነገር ሌላው ላይረዳ ይችላል። እናት ልትሆን ትችላለች፤ የልብ ጓደኛህ፤ የትዳር አጋርህ፤ ፍቅረኛህ። ሌላም ሌላም መጥቀስ ትችላለህ ግን ከሚረዳህ ይልቅ የሚያደክምህ የሚበዛበት ጎዞ ስለሆነ ጠንከር በል። ብታቆም እነሱ ያሉህን ሆነ ትገኛለህ።
ብቸኝነት ጓደኛ ሲሆንህ፤ ያልጠበቅከው ነገር ሲያገጥምህ አይዞህ ያልፈል። በህይወት የሚረዳህ ፍለጋ ስትኳትን መድረስ የምትፈልገው ጋር አትደረስም። እመነኛ የገጠሙህ ችግሮች ጠንካራ ማንነት እንደ ንጉስ ካባ ያላብሱሀል። ታገሰ ለአንተም ያቺ ከልብ የምትስቅበት ጊዜ ይመጣል። የምትባአንገትህን ደፍተህ ስራ፡ ያ ቀን ይመጣል!!
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12
271
" ፈራሽ ነው ገላዋ "
ፈራሽ ነው ገላዋ፣የዚች ምስኪን ዓለም፣
አይዘልቅም ስቃዩ፣አይኖርም ዘላለም፤
ይመጣል ይሄዳል፣ሁሉም በየተራ፣
ፊት እና ኋላ ነው፣ደስታና መከራ።
ለጊዜው ችግርሽ፣ቢገዝፍ እንደ ጫካው፣
ቻል አድርጊው ውዴ...
ችግርን ያየ ነው፣በደስታ ሚረካው።
271
➨#ወዳጄ_ሆይ_ታገስ
ያ ቀን ይመጣል!!!
በጅማሬህ የሚሳለቁብህ ፤ ዴንታ የማይኖራቸው ሰዎች ይኖራሉ ። ይህን የምልህ ከሩቅ ሰዎች ሳይሆን ቅርብ እና የእኔ የምትላቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ከስራው ህመም ይልቅ የእነሱ ምላሽ ልብህን ይፍቀዋል። በዚህም የተነሳ ውስጥህ ከሚባለው በላይ ነው የሚጎዳው። ነገር ግን ወዳጄ ጀገን በልን፤ ይሄ ህይወት ነው፤ አንተ የተሰማህ እና የታያህ ነገር ሌላው ላይረዳ ይችላል። እናት ልትሆን ትችላለች፤ የልብ ጓደኛህ፤ የትዳር አጋርህ፤ ፍቅረኛህ። ሌላም ሌላም መጥቀስ ትችላለህ ግን ከሚረዳህ ይልቅ የሚያደክምህ የሚበዛበት ጎዞ ስለሆነ ጠንከር በል። ብታቆም እነሱ ያሉህን ሆነ ትገኛለህ።
ብቸኝነት ጓደኛ ሲሆንህ፤ ያልጠበቅከው ነገር ሲያገጥምህ አይዞህ ያልፈል። በህይወት የሚረዳህ ፍለጋ ስትኳትን መድረስ የምትፈልገው ጋር አትደረስም። እመነኛ የገጠሙህ ችግሮች ጠንካራ ማንነት እንደ ንጉስ ካባ ያላብሱሀል። እናማ ወንድሜ ፈጣሪ ከአንተ ጋር ይሁን እንጂ የማትደርስበት ከፍታ የለም። ታገሰው ለአንተም ያቺ ከልብ የምትስቅባት ጊዜ ይመጣል። እናትህ ከልብ የምትስቅበት ቀን ይመጣል፤ ያ ቀን ይመጣል። አባት ኮርቼብሀለው የሚልህ፤ እንኳን ወለድኩህ የምትባልበት ቀን ይመጣል። አንገትህን ደፍተህ ስራ፡ ያ ቀን ይመጣል!!
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12
271
Repost from Never Give up!!!

#ቻናሉን_ለወዳጆቻችሁ_ሼር_በማድረግ_እንዲቀላቀሉ_አድርጓቸው::
#Never_give_up
https://t.me/payattetion12
271
እኔ ወደሀለሁ...
እኔ ወደሀለሁ
ታስሮ እንደመፈታት
እንደወሆን ብርታት
ዳዊት ከጎለድያድ
ደርቦ እንደመመታት
እኔ ወደሀለሁ...
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሹ እንደመውረስ
እኔ ወደሀለሁ......
እንደመቅደስ እጣን
እንደፋለኛ ስልጣን
እኔ ያንተ ቡዳ
ያንተ ልዝብ ሴጣን ።
271
" ወፊቷን በሆንኩኝ "!!!
በራሴ ችሎታ ቤቴን በሳር ሰሪ፣
ሳልዘራ ሳላጭድ ቀለቤን ሰፋሪ፣
በፈጣሪ ቸርነት ሳልጨነቅ ነዋሪ፣
ወፊቷን በሆንኩኝ በሰማይ በራሪ!!!
ዶላር ሰማይ ነግቶ ብር መሬት ወድቆ፣
እያሉ ከመኖር በሁሉም ተጨንቆ ፣
ምነው ወፍ በሆንኩኝ ከዛፍ ዛፍ በራሪ፣
ቀለብ የማይጨንቀኝ ቤቴን ብቻ ሰሪ።
271
ልቡ ጥበበኛ የሆነ” ሰው “ብልህ” ወይም “አስተዋይ” መባሉ ምንም አያስደንቅም! አን አሜሪካን ትራንስሌሽን) አዎን፣ ጥልቅ ማስተዋል፣ ለሚያገኙት ሰዎች “የህይወት ምንጭ” ነው። ይሁንና ስለ ሞኞችስ ምን ለማለት ይቻላል? እነሱ “ጥበብንና ተግሳፁን ይንቃሉ።” ተግሳፁ ባለመቀበላቸው ምን ይደርስባቸዋል? ከላይ እንደተመለከትነው ሰሎሞን “የሞኞች ቅጣት ራሱ ሞኝነታቸው ነው” ብሏል። ሞኞች ተጨማሪ ተግሳፁ የሚቀበሉ ሲሆን ይህ ደግሞ ብዙውን ጊዜ ከበድ ያለ ቅጣት ያስከትልባቸዋል። ከዚህም በላይ ሞኞች በራሳቸው ላይ ችግር፣ ሃፍረትና በሽታ ሊያመጡ አልፎ ተርፎም ያለ ዕድሜያቸው በሞት ሊቀጩ ይችላሉ
271
ዛሬን እንዳታጣ !!!
በግዜ እያሳበብክ ስህተትክን አትደብቅ፣
ይልቅስ ታርመህ ሰው በመሆን ድመቅ፣
ግዜ ለሰው እንጂ ሰው ለግዜ አይደለም፣
ያመኑት ጥፋት ነው ድልን የሚሸልም፣
የሰራ መሳሳት ያለ ነው በላቸው፣
በድጋሚ ጥረት ቆመህ አሳያቸው፣
በአለፈው ስህተት ዛሬ ቢመዝኑህ፣
ለማሸማቀቅ ጉባኤ ቢጠሩህ፣
የትላንቱንማ ለትላንት ትቻለሁ፣
ላይመለስ ዛሬ ተምሬበታለሁ፣
ብለህ ንገራቸው ጥቂት ቃላት አውጣ፤
በአለፈው ማንነት ዛሬን እንዳታጣ!!!
271
መልካም ፍሬን አፍራ
ማፍራትህ ከአልቀረ ልክ እንደዚህ አፍራ
ያለህን አትደብቅ መልካም ዘርን ዝራ
አንተን ቢከብድህም ያፈራኸው ፍሬ
ጎንበስ ቢያደርግህ ብስል ሆኖ ጥሬ
ለሌሎች ተስፋ ነው የነገ ምግባቸው
ይጠቀሙበታል መልካም ዘር ስጣቸው!
271
ከራስ ጋር አዎንታዊ ንግግር
ስለራሳችን የምናስበው እያንዳንዱ ሀሳብ ለእራሳችን የምንሰጠው ግምት ላይ አዎንታዊ ወይም አሉታዊ ተጽእኖ አለው። ለእራሳችን የምንነግረው ሀሳብ አሉታዊ ከሆነ ቀስ በቀስ ለእራሳችን የምንሰጠው ግምት እየወረደ ይመጣል። ስለዚህ እነዚህን አሉታዊ ሀሳቦች በአዎንታዊ ሀሳቦች የምንተካበት መንገድ መፈለግ አለብን። አዎንታዊ ሀሳቦችን ማሰብ ስለእራሳችን ያለን ግምት በጣም ጥሩ እንዲሆን ያደርጋል። የእራስ መተማመናችንም እንዲያደግ ያግዘናል።
🍎 ሄዋን
271
አንዳድ ቀን እኮ ሚነጋም አይመስልም እሄው ነጋ ነገን አላወቀውም አምላኬ አንተግን አውቅሀለው ከነገሩ ግዝፈቱ ይልቅ አንተን አውቅሀለው የገዘፈ ነገር ሁሉ ትልቅ አይደለም እኔ ሁሌም አምላኬን ትልቅ አደርጋለው❤️
🍎ሄዋን