የጥበብ እመቤት 📜
Open in Telegram
╱◥██████◣ │∩│🪟▤│🪟│ ▓▆▇█▓🚪▓█▇ 🍹❤️🔥✨🍁𝐖𝐄𝐋𝐂𝐎𝐌𝐄🍁✨ 𝚜𝚞𝚌𝚌𝚎𝚜𝚜 እንኳን ደህና መጡ ወደ የጥበብ እመቤት "ሕይወት ትጠይቃለች፣ ጥበብ ትመልሳለች " https://Wisdomlady
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
272
Subscribers
-124 hours
+77 days
+15230 days
Posts Archive
272
ይድረስ ለአዳሜ ......
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ
ንገሪኝ ካልከኝ ግን ዛሬም እዛው ነኝ
የኔ ደህና መሆን ምን ያሳስብሀል
ፍቅር ነው እንዳልል ትተሀኝ ሂደሀል
ደሞ ድንገት መጥተህ አዛኝ ያደርገሀል
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ
እኔነቴ ትቼ ባንተ ውስጥ አለሁኝ
ቀናት አልፎው ወራት ቢመጣ
አንተን ከማሰብ ውጭ ለውጥም አላመጣ
ህመሜ ብነግርህ መጠህ ልታድነኝ
ድንገት እየመጣህ ምነው ባታደማኝ🥹
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
…
ስለጥረትሽ አለም ግድ የለውም
ሰዎች የሚያዩት የጥረትህን ሂደት ሳይሆን፣ የፍሬውን ጣፋጭነት ብቻ ነው።
የለፋሽባቸውን…
የሌሊት እንቅልፍ ያጣሽባቸውን…
ያፈሰስሽውን ላብ…
የዋጥከ ሽውን መራራ ስሜት
ማንም ሊረዳሽ አይችልም ፡፡
ስለዚ ማንም ሳትሰሚ ለስኬትሽ ብቻ ሩጪ
ምክንያቱም
ያን መከራ የተጋፈጥሽው አንች ብቻ ነሽ -: 😊✌
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
አለ አይደል? ትግስቱን ልባችን እስከምን እደሚችለው እንጃ... ትንሽ ነገር ለራስ መተው ጥሩ ነው በደጉ ግዜ። ያለውን የሰጠ መጪውን አያውቅምና፣ የከፋ ግዜ ክፉ ሰው ላይ ሲጥል መሄጃ ይታጣል። ለመጠየቅም ቢሆን የምጠይቁበት ሁኔታ እና ሰው ያስፈልጋል፤ እና በደጉ ግዜ ትንሽ መውደድ፣ ትንሽ ገንዘብ፣ ትንሽ እውቀት... ብቻ ለራሳቹህ ከምትሰጡት ነገር ትንሽ አስቀሩ። ቀንና ዘመን ሲለወጥ ትፅናኑበታላችሁ
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
𝚠𝚒𝚜𝚑𝚎 𝚢𝚘𝚞 𝚠𝚎𝚛𝚎 𝚑𝚎𝚛𝚎 𝚗𝚎𝚡𝚝 𝚝𝚘 𝚖𝚎, 𝚠𝚎 𝚌𝚘𝚞𝚕𝚍 𝚑𝚊𝚟𝚎 𝚑𝚊𝚍 𝚜𝚘 𝚖𝚞𝚌𝚑 𝚏𝚞𝚗 𝚊𝚗𝚍 𝚊𝚗𝚘𝚝𝚑𝚎𝚛 𝚛𝚞𝚖𝚋𝚕𝚒𝚗𝚐 𝚋𝚞𝚖𝚋𝚕𝚒𝚗𝚐 𝚜𝚘 𝚒𝚏 𝚒 𝚝𝚘𝚘𝚔 𝚢𝚘𝚞 𝚗𝚘 𝚊 𝚍𝚊𝚝𝚎 𝚠𝚑𝚒𝚌𝚑 𝚙𝚕𝚊𝚌𝚎𝚜 𝚠𝚘𝚞𝚕𝚍 𝚒𝚝 𝚋𝚎 ?😥
እና ምናገባን የምትሉ አትጠፉም አ 😳🫣😂
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ጊዜ ወደፊት አይገፈተርም፡፡ ጊዜ ለሰው ጭንቀትም ሆነ ደስታ ደንታ የለውም፡፡ የራሱን ሥርዓት ጠብቆ ነው የሚጓዘው፤ ያለፈ ጊዜ አይመለስም፤ የወደፊቱ ደግሞ እንደፈለጉት ፈጥኖ አይመጣም፡፡ ሰው በጊዜ ቁጥጥር ሥር ነው እንጂ ጊዜ በሰው ቁጥጥር ሥር አይደለም፡፡ ሰዓት ሰው ሰራሽ ነገር ነው፤ ሞላውን በማዞር ካለበት ሰዓት ወይም ደቂቃ ማስቀደም ይቻላል፡፡ ቀንን ገፍቶ ማስመሸት ወይም ምሽትን ገፍቶ ማንጋት ግን የማይቻል እውነታ ነው፡፡
ስለዚህ ጊዜን እንቅደመው ወይስ ጊዜ እኛን ይቅደመን. !!?
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ፍቅር ነጎድጓድ እንደ ሌላው ዝናብ ነው ድንገት ይዘብና ውስጣችንን በሀሴት ያረጥበዋል አዘራሩን ላወቀበት ጠቃሚ ዝናብ ሆኖ ያልፋል ላላወቀበት ደግሞ ጎርፍ ሆኖ ያልፋል
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
"በህይወትህ ካደረገከው ነገር ምን ይፀፅትል" ሲሉት
👨🦱ባል:- "የሰርጌ ቀን የሚስቴ ቤተሰቦች #አናስገባም ሰርገኛ እያሉ ሲጨፍሩ እሺ ብዬ አለመመለሴ🥹😂
272
ስኬት......
የሚያነቃቃ የሚያነሳስ ግብ መቅረፅ።
የምንቀርፅው ግብ ትርጉም ያለው፣ ከልብ የምንፈልገው፣ ውጤቱን ስናስበው የሚያስደስተንና ወኔያችንን የሚያነሳሳን መሆን አለበት። የምንቀረፅው ግብ ለስራ የሚያነሳሳ መሆኑን በደንብ መፈተሽ ይኖርብናል። ምክንያቱም የሚያነቃቃና የሚያነሳሳ ግብ የተግባር ሰው ያደርጋል። ያለንን አቅም እንድንጠቀምና ለዓላማችን ትኩረት እንዲኖረን ያደርገናል። የሚያነቃቃ ግብ ወደ ስኬት የሚመራ ሀይል ነው።
ህልማችንን ማሳካት እንፈልጋለን? ግባችንን ለማሳካት ከፍተኛ መነቃቃት አለን? የእነዚህ ሁለት ጥያቄዎች መልስ እኛን ከሌሎች በዘፈቀደ ከሚጓዙ ሰዎች ይለዩናል። አልያም በማይጠቅሙ ነገሮች እራሳቸውን ከበው ጊዜያቸውን ከሚያጠፉ ዓላማ ቢስ ሰዎችጋር አንድ ያደርገናል። ምርጫው የእኛ የራሳችን ነው። ከመጀመሪያው የሚያነቃቃን የሚያነሳስን ግብ በመቅረጽ በሙሉ አቅማችን ተግተን መስራት አለብን። መሀል መንገድ ላይ አልያም ወደ መጨረሻው ላይ ድካም አልያም አስቸጋሪ ፈተና ሲያጋጥመን፣ የውጤቱን አስፈላጊነት እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደ ፊት መገስገስ አለብን።
🥀🍿☕️🫖
https://t.me/mekuytrrwxnc/903
272
ይቅናህ ብያለሁ..... 💔
እግርህ ከተነሳ ለመሄድ ወስነህ
ልብህ ከሸፈተ ካጠገቤ ሁነህ።💔
ከኔ ርቆ መሄድ ውሳኔህ ከሆነ
መለየት ናፍቆ ልብህ ከጨከነ።💔
አዳሜ ሸኛሀለሁ ናፍቆት ደረቤ
መሸኘት ልማድ ሁኖዋል ልቤ።💔
ፈጣሪ ካልፃፈው የእህለወሀ ነገር
ይቅናህ በሄድክበት ክፉም አልናገር።💔
ያመጣህ ጎዳና ይውሰድህ መልሶ
ወትሮም መንገደኛ ይመለሳል ደርሶ።💔
💔🥀
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ያሳካናቸውን ጉዳዮች ዝርዝር ማዘጋጀት
በህይወታችን የሚያጋጥሙን ውጣ ውረዳች፣ መውደቅ መነሳታችን በራስ መተማመናችን ሊሸረሽሩብን ይችላሉ። በተለይም ስኬት ማጣት፣ ኪሳራ፣ ዉድቀትና የመሳሰሉ ነገሮች ልንገነባው በምንጥረውን በራስ መተማመን ላይ መጥፎ ጥላ ያጠሉበታል። ይህን ለመቋቋም ያሳካናቸውን ጉዳዮች ዝርዝር ማዘጋጃት አይነተኛ መፍትሄ ሆኖ ያገለግላል። ባሰብናቸው ቁጥር ደስታ የሚሰጡንን የምንኮራባቸውን ስኬቶች ዝርዝር በወረቀት ላይ መጻፍ እና በቤታችን ልናየው በምንችለው ስፍራ መለጠፍ። እንዲህ ካደረግን በኋላ ተስፋ የመቁረጥ ሲሰማን በራስ መተማመናችን ዝቅ ሲል ያዘጋጀነውን ዝርዝር ማንበብ በእርግጠኝነት የስሜት ከፍታንና የራስ መተማመናችንን መልሰን እንድንቀዳጅ ያግዘናል እና እንጠቀምበት።
🥀☕️🫖🍿
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ተው ይቅርብህ #አዳሜ በከንቱ መማሉ
ምን ያደርግልሀል በአፍ መደለሉ።
አትዋሽ የኔ ዓለም
ደግሞም አትበለኝ ካላንቺ አልኖርም።
ምክንያቱ አውቃለሁ ስትለየኝ ከኔ
ሌላ እንደምታቅፍ ዞር ብለህ ከኔ።
እናም አትበለኝ በጣም ወድሻለው
ጌታውን ስሞ ነው ይሁዳን የሸጠው።
ስለዚ አትንገረኝ አትዋሽ ይቅር
ለምንም ላይበጀን የምላስ ላይ ፍቅር።
በአፍ እየደለለ በቃል ያልታመነ
በከንቱ ውዳሴ ከልብህ ያልሆነ።
በቅፅቢ ተስፋ ስንቱ እየታመመ
የውሸት መውደድ ለማንስ ጠቀመ።
☕️🫖
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ዞር ዞር ስል ያገኘሁት አንድ ጓደኛየ የሚሰራው ቅንነት ላጋራቹ
ድንገተኛ የልብ ማቆም (Sudden Cardiac Arrest)
ከደቂቃዎች በፊት ሲስቅ ሲጫወት አሊያም የእለት ተግባሩን ሲያከናውን ያየነው ሰው በሚቀጥለው ቅጽበት ግን በድንገት ራሱን ስቶ ሊወድቅ ይችላል። ይህ የድንገተኛ የልብ ማቆም (Sudden Cardiac Arrest) አስደንጋጭ እውነታ ነው።
ድንገተኛ የልብ ማቆም የሚከሰተው የልብ ኤሌክትሪካል ስርዓት ሲታወክ ሲሆን፣ ልብ ወደ ሰውነት ደም መላክ ያቆማል። ተጠቂው ፈጣን የህክምና እርዳታ ካልተደረገለት፣ የመትረፍ እድሉ በእያንዳንዱ ደቂቃ ከ 7–10% ይቀንሳል።
ጤና ባለሙያዎች፣ ሕይወት በሰከንዶች ውስጥ እንዴት ሊቀየር እንደሚችል ደጋግመን እናያለን።ግን ደግሞ ዝግጁነት እና ትክክለኛ ምላሽ ሞትን ወደ ሕይወት ሊቀይሩ እንደሚችሉም እናውቃለን።
ስለ ድንገተኛ የልብ ማቆም ማወቅ ያለብን እውነታዎች
• በማንኛውም ዕድሜ ክልል ላይ ባሉ ሰዎች ሊከሰት ይችላል፣ ጤናማ በሚመስሉ ሰዎችም ጭምር።
• ብዙ ጊዜ ያለ ቅድመ ምልክት ይከሰታል።
• ክስተቱን ቶሎ መለየት እና እርምጃ መውሰድ ወሳኝ ነው።
• በፍጥነት CPR መጀመር የመትረፍ እድልን ሁለት እስከ ሶስት እጥፍ ሊያሳድግ ይችላል።
• የAED (Automated External Defibrillator) አጠቃቀም የሕይወት ማዳን እድልን በእጅጉ ያሻሽላል።
ምን ማድረግ እንችላለን?
• CPR እንማር፣ ሌሎችንም እናስተምር።
• AED በትምህርት ቤቶች፣ በስራ ቦታዎች፣ በስፖርት ማዕከላት እና በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች እንዲገኝ ማድረግ።
• የልብና ሌሎች መደበኛ የጤና ምርመራን ማድረግ።
• ድንገተኛ የልብ ማቆም አስቸኳይ የህክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ክስተት መሆኑን ለማህበረሰቡ ማሳወቅ።
ሕይወት የማዳን ስራ ለጤና ባለሙያዎች ብቻ የተሰጠ ተግባር አይደለም፤ ሕይወትን ለማዳን ዝግጁ ለሆኑና እርምጃ ለሚወስዱ ሰዎች ጭምር እንጅ ።
ዛሬ የምናድነው ሕይወት የወድፊት የስራ ባልደረባችን፣ ወዳጃችን፣ የቤተሰባችን አባል ወይም ገና ያልተጠናቀቀ ታሪክ ያለው ሰው ሊሆን ይችላል።
Dr.Getaneh Kassie Gashu 🇪🇹
College of Medicine and Health Sciences, Bahir Dar University, Ethiopia
እውነት ክብረት ይሀበልና ዶክተር ጌታነህ ሁሌ በቀናነት ለምታካፍለን ትምርት
🥀🍿🫖☕️
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
በራስ መተማመን ምን ማለት ነው??
መተማመን ማለት ስለራሳችን ያለን ግምት፣ በችሎታችንን በብቃታችን ያለን እምነት፣ እንዲሁም በውሳኔያችን ላይ ያለን እምነትና ቁርጠኝነት ድምር ውጤት ማለት ነው። ያለንን አቅም እና ችሎታ በሚገባ በመገንዘብ የራሳችንን ውሳኔ እንወስናለን፤ በውሳኔያችን ላይ ያለን ፅናት እና ቁርጠኝነት ባለን በራስ መተማመን ላይ ይመረኮዛል።
በስኬት መንገድ ላይ በራስ መተማመን ወሳኙን ሚና ይጫወታል። አንድ ሰው የቱንም ያህል ቢማር፣ ብልህ እና ጎበዝ ቢሆን በራስ መተማመን ከሌለው በሙሉ አቅሙ አይኖርም። እንዲህ አይነቱ ሰው የሌሎች መጠቀሚያ አልያም የበይ ተመልካች ይሆናል። በተቃራኒው ትንሽ ዕውቀትያለው አንድ ሰው በራስ መተማመን ካለው ብዙ ነገር በቀላሉ ያሳካል። ይህ ሰው በፍፁም ድፍረትና የእርግጠኝነት ስሜት የራሱና የሌሎች ህይወት መሪ ይሆናል። ህይወቱ በእጁ ነው፣ ወደፈለገው አቅጣጫ ይዘውረዋል።
ከፍ ያለ በራስ መተማመን ካለን የስኬት ቁልፍ በእጃችን ያለን ያህል ሊሰማን ይገባል። ምክንያቱም የማንደመስሰው እንቅፋት ከፊታችን አይኖርም። ወደ ስኬታችን እንዳንሄድ ሊያቆመን የሚችል አንዳች ሀይል አይኖርም። እንቅፋቶች፣ ችግሮች ይገዳደሩን ይሆናል እንጂ አያሸንፍንም። ግባችንን እንዳንመታ ሊያቆመን የሚችል አንዳች ሀይል አይኖርም።
በቂ በራስ መተማመን ከሌለን ወይም ዝቅተኛ በራስ መተማመን ካለን ማሻሻል እንችላለን። ለዚህ የሚረዱንን ነጥቦች በዚህ ምዕራፍ እንመለከታለን።
🥀☕️🫖🍿
https://t.me/mekuytrrwxnc
272
ሰው ......
ሰው መምሰል ቀላል ነው እምብዛም አይከብድም
ከልብ ካለቀሱ እምባም አይገደድም።
ግን ዘንጅሮ መልተዋል ሰው እየመሰለ
የካንገት በላይ የውሸት ለቅሶ አለ።
ነጭ ወረቀት አለ ጥቁርም አይጠፋም
አንዳንድ ቁምነገር መጫሩ አይጠፋም።
ነጭ ላይ በጥቁር በጥቁርም ነጭ
በጨላማው ብርሀን ማብራት ማብለጭለጭ።
በሂደት በሂደት መቼ ያልቃል መንገድ
ቢስቡት በጎቱቱት ረዝም ነው ገመድ።
ስንመለከተው ቆም ብለን ከዳሩ
ህይወት ዘመቻ ነው ጉዞውን አዳሩ።
🥀☕️
https://t.me/mekuytrrwxnc
