የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 303
Subscribers
+824 hours
-47 days
-7130 days
Posts Archive
4 308
🇮🇱 🇺🇸⚡️🇮🇷 በማንኛውም ሰዓት አሜሪካ ኢራንን ልታጠቃ ትችላለች በሚል፣ እስራኤል የጦርነት ጊዜ ዝግጅት እያደረገች ነው — N12 Israel
4 308
🇰🇼 ከኢራቅ አሜሪካ '91 ጦርነት በኋላ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ኩዌት በ April 2026 አንዲት በርሚል ነዳጅ ወደ ውጭ ኤክስፖርት አላደረገችም።
4 308
🇮🇶 — ያተለመደ የአየር ላይ እንቅስቃሴ በኢራቅ ሰማይ ላይ እየታየ ነው። የአሜሪካ የስለላ አውሮፕላኖች በተለምዶ ከሚበሩበት ርቀት ርቀው በኢራን ድንበሮች ዛሬ በረራ ሲያደርጉ ተስተውለዋል።
4 308
🇮🇷ተደመሰሰ የተባለው የኢራን ባሕር ኃይል የሆኑ 40 ፈጣን የጦር መርከቦች፣ ዛሬ እንደ ፈረንጆቹ May 2፣ የሆርሙዝን ወሽመጥ ከዞሩ እና ከአሰሱ በኋላ ወደ ማረፊያቸው ሲመለሱ የሚያሳይ የሳተላይት ምስል፣ IRGC ለቋል።
4 308
🇺🇸🇶🇦🇰🇼🇮🇱🇦🇪 - የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመካከለኛው ምስራቅ ላሉ አጋሮች ከ 17.6 ቢሊዮን ዶላር በላይ ወታደራዊ መሳሪያ ሽያጮችን ፈቅዷል
ሳዑዲ አረቢያ 9.1 ቢሊዮን ዶላር ለዘርፈ ብዙ መሳሪያ
- ኳታር 4.01 ቢሊዮን ዶላር ለ Patriot አየር መቃወሚያ
ኩዌት 2.5 ቢሊዮን ዶላር ለጦርነት ማዘዣና መቆጣጠሪያ ስርዓት።
የተባበሩት አረብ ኤሜሬት 2 ቢሊዮን ዶላር ለአየር መቃወሚያዎች
እስራኤል 992 ሚሊዮን ዶላር ለ APKWS።
4 308
🇸🇦 | አዲስ የሳተላይት ምስል እንደሚያሳየው በሳዑዲ ዓረቢያ የአሜሪካ የልዑል ሡልጣን ጦር ሠፈር በኢራን ላይ ለሚደረግ ጦርነት ዝግጅቱን አጧጡፎ ይታያል።
ከዚህ በፊት በተሳካ ሁኔታ በኢራን ጦር የተመታውና በርካታ አይሮፕላኖች የወደሙበት ይህ የጦር ሠፈር፣ አሁን ላይ በአዳዲስ ወታደራዊ አይሮፕላኖች ተጨናንቋል፣ ብለዋል የአካባቢው ባለሙያ ተንታኞች። አይሮፕላኖቹ ምናልባትም እንደ ባለፈው ጊዜ ጥቃት እንዳይደርስባቸው፣ ተራርቀው ቆመዋል ነው የሚሉት። በቦታው የተዋጊ ጀቶች ብዛትም ከዚህ በፊት አልታየም ይላሉ።
ጦር ሠፈሩ በሳዑዲ የአሜሪካ የመካከለኛው ምሥራቅ ወታደራዊ ማዘዣ እና መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሆኖ ከ '91 እ.ኤ.አ የኢራቅ ጦርነት ጀምሮ በማገልገል ላይ ነው።
4 308
🇮🇱❗️⛪️ "አሜሪካ ዝም ልትል አትችልም፣ የእስራኤልንም አረመኔአዊ ድርጊቶችን ልታስቆም ግድ ይላታል" - MTG እስራኤል በሊባኖስ ገዳም ማፍረሷን በተመለከተ።
"የአሜሪካ ክርስቲያኖች ድምፃችሁን አሰሙ!"
4 308
🇮🇷📰 The Wall Street Journal ምንጮችን በመጥቀስ - የኢራን አዲሱ የድርድር ፕሮፓዛል ጥቃቶችን ማስቆም እና እገዳውን ማንሳት የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት እንደ ቅድመ-ሁኔታ ያስቀምጣል።
የኢራን ሓሳብ የአሜሪካን ማዕቀብ ለማቃለል እና በኢራን የኒውክሌር ጉዳይ ላይ በኋላ ለመወያየት ሀሳብ አቅርቧል። ዋሽንግተን ለአዲሱ ሀሳብ ክፍት እስከሆነች ድረስ ኢራን በሳምንቱ መጀመሪያ ላይ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣለች።
4 308
🇮🇱 - Israel Hayom የጦር ሰራዊት ባለስልጣናትን በመጥቀስ፡
- ኔታንያሁ በሊባኖስ ለተፈጠረው ተስፋ አስቆራጭ ውጤት እና በኢራን ለተገኘው ከፊል ውጤት፣ ተጠያቂ የሚሆን የጦስ ዶሮ እየፈለገ ነው።
- ኔታንያሁ የተፈለገውን ውጤት አላሳካም በማለት፣ ጥፋቱን ወደ ሠራዊቱ ለማዛወር እየሞከረ ነው።
4 308
🇮🇷⚡️🇺🇸 አሜሪካ መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ ለማለፍ ለኢራን ምንም ክፍያ እንዳይከፍሉ፣ ሲከፍሉ የተገኙ በማዕቀብ እንደሚቀጡ አስጠነቀቀች።
4 308
🇮🇷⚡️🇺🇸 ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ትራምፕ ከደህንነት እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር በፔንታገን ኢራንን በተመለከተ ዝግ ስብሰባ ይቀመጣል።
4 308
🇺🇸❌🇮🇷 - የ US ማዕከላዊ ኮማንድ አዛዥ አድሚረል Brad Cooper ለፕሬዚዳንት Trump በኢራን ላይ "የመጨረሻ መፍትሄ" ዘመቻ ያለውን ወታደራዊ እርምጃ በይፋ ማሳወቁን የ FOX NEWS ዘገባ ያሳያል።
➡️ በሌላ በኩል ኢታማዦር ሹሙ ጄኔራል Dan Caine ንን ያካተተ ቡድን የኢራን መሠረተ ልማት እና አመራር ላይ ያነጣጠረ የአጭር እና ኃይለኛ የጥቃት ማዕበል ዕቅድን ለ Trump በዝርዝር አቅርበዋል።
4 308
🇮🇷🇺🇸🇮🇱⚡️ - የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ -
ፔንታጎን እየዋሸ ነው። የኔታንያሁ ቁማር እስካሁን አሜሪካን በቀጥታ 100 ቢሊዮን ዶላር አስወጥቷል። ይህም ከተገለጸው በአራት እጥፍ ይበልጣል። ለአሜሪካ ግብር ከፋዮች ቀጥተኛ ያልሆኑ ወጪዎች በጣም አሻቅበዋል። በአባወራ በወር 500 ዶላር ወጪ እንዲጨምርበት ሆኗል እና በፍጥነት እያደገ ነው። 'እስራኤል ትቅደም' ማለት ሁል ጊዜ 'አሜሪካ መጨረሻ ትሁን' ማለት ነው።
4 308
⚡️🇮🇷🇹🇷🇪🇬🇸🇦🇶🇦 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ዛሬ ጠዋት ከቱርክ፣ ከግብፅ፣ ከኳታር፣ ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከኢራቅ እና ከአዘርባጃን አቻዎቻቸው ጋር የስልክ ንግግሮች አድርገዋል። የጦርነቱን ማብቂያ እና የአሜሪካ-እስራኤል ጥቃትን በተመለከተ የቴህራንን አቋም እና ተነሳሽነት ገልፀውላቸዋል።
4 308
🇮🇷⚡️🇺🇸 ኢራን "ለሁሉም ብቀላ" በሚል ርዕስ አዲስ ቪዲዮ አውጥታለች። ቪዲዮው የዩክሬን የመረጃ ማዕከላት በጠቅላዩ መሪ አያቶላህ ኻሜኔይ ላይ ከደረሰው ጥቃት በፊት መረጃ ለመሰብሰብ ያገለግሉ እንደነበር ይናገራል።
በዚህም የተነሳ ቪዲዮው የኢራን ሚሳኤሎች በዩክሬን ግዛት ላይ እነዚህን የመረጃ ማዕከላት ሲመቱ ያሳያል። ይህ እየተባባሰ የመጣው ግጭት ከአካባቢያዊ አለመግባባት ባሻገር እየሰፋ እና ቀስ በቀስ ብዙ አገሮችን እየሳበ ይገኛል።
ግጭቱ የሰከነ የሚመስለው ይኖራል፣ አርቴፊሻል ስክነት ነው። በማንኛውም ደቂቃ ሀገሮች ወደ ለየለትና ወደ ባሰ የጦርነት አውድማ ውስጥ ገብተው ሊወቃቁ ይችላሉ። ቋፍ ላይ ናቸው።
ጦርነቱ ሚዛኑን እየቀየረ፣ የተደበቁ የግጭት መስመሮችን እየገለጠ፣ ሂደቶችንም እየከፋፈተ እየመጣ ነው። በአሁኑ ጊዜ እየተሰራጨ ስላለው የቪዲዮ መረጃ ምንም አይነት ኦፊሴላዊ ማረጋገጫ ከኢራን መንግሥት እንደሌለ አጽንኦት መስጠት ያስፈልጋል። ይህን መረጃ ወደፊት በመግፋት እያመጡ ያሉት፣ ከኢራንን ጦር ጋር ግንኙነት ያላቸው ትላልቅ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ናቸው። በመገናኛ ብዙኃናቸው ውስጥ በንቃት እየተወያዩበት ያለ ጉዳይ ነው። በጦርነቱ ወቅት ዘለንስኪ ዩክሬን ኢራን እንደ አረብ ሀገራት ሁሉ እኔንም ታጠቃኛለች የሚል ፍራቻ እንደነበረው ሲገልፅ ነበር።
ይህ የሚባለው ከተረጋገጠ ዩክሬን እራሷን ወደዚህ እየሰፋ የመጣው የግጭት ውቅር ውስጥ ከሳቡት ሀገራት መካከል እንደምትገኝ ጥርጥር የለውም።
4 308
🇺🇸🇮🇷⚡️ - የዋይት ሀውስ ባለስልጣን ለWashington Eximnar:
አስተዳደሩ ለኢራን ጦርነት ፈቃድ ስለመጠየቅ ከኮንግረስ ጋር "ንቁ ውይይቶች"ን እያደረገ ነው።ትራምፕ ከኮንግረስ ምንም ፈቃድ ሳይሰጠው ጦርነት መጀመሩ፣ በአሜሪካ ሲያስተቸው የቆየና አጠቃላይ ሁኔታው በዚህ ምክኒያት ፓርቲዎችን እያወዛገበ ያለ ጉዳይ ነው።
4 308
🇺🇸🇮🇷⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ -
ቀድሞውንም አሸንፈናል፣ ግን በትልቅ ልዩነት ማሸነፍ እፈልጋለሁ። አሁን ብንመለስ፣ እንደገና ለመገንባት 20 ዓመታት ይፈጅባቸዋል። አሁን ያለንበት ሁኔታ በቂ አይደለም። በፍፁም የኑውክሊየር ጦር መሳሪያ እንደማይኖራቸው ዋስትና ሊኖረን ይገባል።
4 308
🇸🇰🇺🇸⚡️— Slovak Prime Minister Robert Fico:
ያለንበት ወቅት ጥሩ ወቅት አይደለም - ትራምፕ በሚተኛበት መንገድ ላይ በተመሠረተ የነዳጅ ዋጋ ጫና ውስጥ ነን። ጥሩ እንቅልፍ ከተኛ፣ የነዳጅ ዋጋ ይቀንሳል። ደካማ እንቅልፍ ከተኛ እና መግለጫ ከሰጠ፣ የነዳጅ ዋጋ ይቀንሳል።
4 308
🇦🇪 — ሰበር፡ UAE ዜጎቿ ኢራንን፣ ሊባኖስን እና ኢራቅን በአስቸኳይ ለቅቀው እንዲወጡ እና ወደ እነዚህ ሀገሮች እንዳይጓዙ አሳስባለች።
