የቀጠናው ተመልካች
Open in Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
4 295
Subscribers
No data24 hours
-217 days
-9130 days
Posts Archive
4 295
—❗️🇺🇸/🇮🇷 ትኩስ፦ የመግባቢያ ስምምነቱ የአሜሪካ ባሕር ኃይል ከፋርስ ባሕር፣ ከኦማን ባሕር እና ከአረቢያ ባሕር መውጣትን እና ከ12 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ የኢራን ንብረቶችን መልቀቅን ያካትታል – Al Mayadeen
***
4 295
🇺🇸 አስቸኋይ ዜና፡ ከ 20 በላይ የተኩስ ድምፅ ዋይት ሃውስ ላይ ተሰምቷል። ከየት ወይም በማን እንደተተኮሰ አልታወቀም። የዋይት ሃውስ ልዩ ኃይሎች በተጠንቀቅ ላይ ናቸው። ተኩሱ ሲሰማ ፕሬዝዳንቱ በዋይት ሃውስ ነበር --- CNN
4 295
🇮🇱🇺🇸 እስራኤል ከ'ረዳት አብራሪ' ወደ ተራ 'ተሳፋሪ' ደረጃ ዝቅ ተደርጋለች — The New York Times
ትራምፕ ኔታንያሁን በኢራን ጦርነት ላይ ሙሉ በሙሉ 'ከጨዋታ አስወጥቶታል'
👉'መረጃ እጥረት ያለበት' እና 'ከኮክፒት የተባረረ' ሆኗል።
🇺🇸TRUMP፦ ኔታንያሁ እኔ የምፈልገውን ሁሉ ያደርጋል።
4 295
🇺🇸🇮🇷⚡️ — ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የመግባቢያ ስምምነቱ በአብዛኛው እንደተጠናቀቀ እና የመጨረሻ ዝርዝሮቹ በቅርቡ እንደሚገለጹ ተናግረዋል።
እኔ፣ ከሳውዲ ዓረቢያ፣ ከኳታር፣ ከዩናይትድ አረብ ኤሜሬት፣ ከባሕሬን፣ ከዮርዳኖስ፣ ከቱርክ፣ ከፓኪስታን እና ከግብፅ መሪዎች ጋር፣ በኢራን ጉዳይ በጣም ጥሩ ስብሰባ አድርጌአለሁ። በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ፣ በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ እና በተዘረዘሩት ሌሎች የተለያዩ ሀገራት መካከል ስምምነት ላይ በአብዛኛው ደርሰናል። የመጨረሻው ደረጃ ላይ ነን። በተለየ መልኩ፣ ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቢቢ ኔታንያሁ ጋር የስልክ ጥሪ አድርጌ ነበር፣ ይህም በተመሳሳይ በጣም ጥሩ ሆኖ ነበር። የስምምነቱ የመጨረሻ ገጽታዎች እና ዝርዝሮችን በአሁኑ ጊዜ እየተወያየንባቸው ሲሆን በቅርቡ ይፋ ይሆናሉ። ከስምምነቱ ሌሎች በርካታ አካላት በተጨማሪ፣ የሆርሙዝ መተላለፊያ ይከፈታል።
4 295
🇺🇸🇮🇷🇮🇱⚡- "በአሜሪካ-ኢራን ስምምነት ላይ ያለው ትልቁ ችግር፦ ኢራን ወደፊት ጥቃት እንዳይደርስባት የምትቀበለው ዋስትና ነው፣" - የእስራኤል ቻናል 12 አሚቻይ ስቴይን።
4 295
⚡️🇺🇸🇮🇷 Axios፦ የትራምፕ አስተዳደር እና ኢራን ጦርነቱን ለማቆም ስምምነት ሊያደርጉ ተቃርበዋል፣ የቀሩት ክፍተቶች ደግሞ በበርካታ ነጥቦች አጻጻፍ ላይ ያተኮሩ ናቸው ብሏል፣ በድርድሩ ላይ መረጃ የሰጠ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን።
ባለሥልጣኑ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ስምምነቱን በተመለከተ ምንም የመጨረሻ ውሳኔ እንዳልወሰነ አፅንዖት ሰጥቷል።
ይህ፣ ወደ ሦስት ወር የሚጠጋ ዕድሜ ያለው ጦርነት ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ሊሆን እንደሚችል እስካሁን ከተሰጡት ጠንካራ ምልክቶች፣ አንዱ ነው።
4 295
🇺🇸⚡️🇮🇷 ኢራን፣ Strait Of Hormuz የተባለ የባሕር ወሽመጥን አንቃ ይዛ፣ ዓለምን እያስለፈለፈች ነው።
ኃያላን የተባሉ ሀገሮች ባሕሩን ከኢራን ነቅለው ቢያዟውሩት ይመርጡ ነበር፣ ነገር ግን ተፈጥሮ ሆነና የሚቻል አይደለም። ወሽመጥ ሸለቆ ውስጥ እንደገቡ ያወቁት ከገቡበት በኋላ ነው።
በተለይ ፈጣሪ ኢራንን የሀብታም አረብ ሀገሮች መተላለፊያ ትቦ ጫፍ ላይ አስቀምጧት፣ ይኸው፣ ከፋችና ዘጊ ሆና፣ ቀረጥ እየሰበሰበች የባንቧ ተቆጣጣሪ ሆናለች። ከዚህ በፊት አልማው የማታውቀውን ገንዘብ ነው ባሕር ላይ ኬላ ዘርጋታ እያገኘች ያለችው።
የጨነቀ ነገር ነው። እናም የገልፍ አረቦች ሳይላቸው አሜሪካና እስራኤልን ሆይሆይ ብለው ያስጀመሩትን ጦርነት፣ ዛሬ እንዲያቆሙላቸው በእንብርክክ እየለመኗቸው ነው።
አሁን ትራምፕ ከኢራን ጋር ከምንግዜውም በላይ ስምምነት ልንፈራረም ጫፍ ደርሰናል ብሏል። ይሄ ለአረቦች እፎይታ የሚሰጥ ዜና ይመስለኛል፣ ለጊዜው።
ፕሬዝዳንቱ በዚህ ሰዓት በዋይት ሃውስ ከሙስሊም ሀገሮች ጋር በስልክ እየተነጋገረ ነው። ውጤቱን ከጥቂት ሰዓታት በኋላ እንሰማለን።
4 295
— 🇦🇪❌🇪🇹 የሱዳን መንግሥት የአየር ክልሌን ጥሶ ገባ ያለውን ባይራክታር የተባለ የኢትዮጵያን ቱርክ ሰራሽ ድሮን፣ መትቶ መጣሉን አስታወቀ።
የድሮኑ ዋጋ $4 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ እንደሆነ ይገመታል።
4 295
— 🇺🇸/🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከፓኪስታን፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ከሳውዲ አረቢያ፣ ከኳታር፣ ከዮርዳኖስ፣ ከቱርክ እና ከግብፅ መሪዎች ጋር ኢራንን በተመለከተ እንደ ኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ላይ የኮንፈረንስ ጥሪ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
ምክትል ፕሬዝዳንቱ በፍጥነት ወደ ዋይት ሃውስ ተጠርቷል።
**
ይሄን ሁሉ የሙስሊም ሀገር ምን ሊለው ነው?
4 295
🇺🇸🇻🇪⚡️መሪዋ ታፍኖ ያለ ምንም ተኩስ ቀበቶዋን የፈታችው ቬኔዝዌላ፣ ዛሬ፣ የአየር ክልሏን ለአሜሪካ የጦር አይሮፕላኖች በመፍቀድ እንዲለማመዱባት አድርጋለች። ከልምምዱ በኋላ የዛሬ ወር በተመለሰው የአሜሪካን ኤምባሲ አርፈዋል።
4 295
🇸🇦⚡️በሳዑዲ ዓረቢያ የኢራንን ጦርነትን ተከትሎ የጋዝ ምርት ሙሉ በሙሉ ቆሟል፣ ለኃይል ማመንጫዎቿ ነዳጅ እያቃጠለች ነው -- ሮይተርስ
60% የሳዑዲ ኤሌክትሪክ ኃይል ከተፈጥሮ ጋዝ የሚመነጭ ነው።
አሁን ላይ ትልቁ የሳዑዲ ጋዝ አውጪ ካምፓኒ፣ ARMACO፣ በጦርነቱ መዘዝ ምክኒያት የተፈጥሮ ጋዝ ማውጣት በማቆሙ፣ ሳዑዲ ለኃይል ማመንጫነት ነዳጅ እየተጠቀመች ነው።
ለዚህ ፍጆታ የምታውለውን ነዳጅ እያስገባች ያለችው ደግሞ ከውጭ ነው፣ በተለይ ከሩሲያ።
በአሁኑ ሰዓትም በቀን ከ1 ሚሊዮን በርሚል በላይ የውጭ ነዳጅ ለኃይል ማመንጫዎቿ ታቃጥላለች። በዚህም ምክኒያት ወደ 'ታዳሽ ኃይል' ልታደርግ የነበረው ሽግግር እክል ገጥሞታል።
ከዚህም በተጨማሪ፣ በቀን ታመርት ከነበረው ከ 8-10 ሚሊዮን ነዳጅ በርሚል ውስጥ፣ በጦርነቱ ምክኒያት 3 ሚሊዮን በርሚል ነዳጅ ከምርቱ ቀንሷል።
4 295
⚡️🇪🇹 የግብፅ ግንባር ቀደም የቴሌግራም ሚዲያ፡ "የኢትዮጵያ ወታደራዊ አመራሮች የአእምሮ ህሙማን ይመስሉኛል፣ ለፌዴራል ፖርላማቸው፣ ግብፅ ኢትዮጵያን ለመውረር ጥምረት እያዘጋጀች እንደሆነና በሀገሩ ውስጥ ያሉ ሁሉም ተቃዋሚዎች 'የፈርዖን ቀንበር' መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራቸው ሆስፒታል የለም?!
4 295
🇺🇸🇮🇷⚡"ከኢራን ጋር በተደረጉ ውይይቶች የተወሰኑ መሻሻሎች ታይተዋል፣ በሚቀጥሉት ቀናት አሜሪካ ስለ ኢራን የምታስታውቀው ነገር ሊኖር ይችላል" - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ።
4 295
🇮🇷/🇵🇰/🇺🇸 የኢራን ዋና ተደራዳሪ ቃሊባፍ ከፓኪስታኑ ማርሻል አሲም ሙኒር ጋር ባደረገው ውይይት፣ 'ድርድሮችን ከአሜሪካ ጋር ስታደርግ በየዋህነት አታደርግም። አሜሪካ 'ምንም ሐቀኝነት የሌላት' እና፣ 'ሙሉ በሙሉ እምነት የማይጣልባት አካል እንደሆነች እናውቃለን። ከአንዴም ሁለት ጊዜ በድርድር መሃል ጦር መዘውብናል። ኢራን ሕጋዊ መብቶቿን በዲፕሎማሲ ወይም በጦር ሜዳ እንደምታስከብር መጠራጠር አያሻም – Reuters
4 295
🇺🇸🇮🇷🇵🇰⚡- "ከፓኪስታኑ አስታራቂ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ላይ ደርሰናል እናም የአሜሪካን ምላሽ እየጠበቅን ነው።
የመግባቢያ ስምምነቱ ጦርነቱን ማቆም፣ እገታውን ማንሳት፣ የሆርሙዝ ወሽመጥን መክፈት እና የአሜሪካ ኃይሎች ከጦርነት ቀጠና መውጣትን ያካትታል።
የመግባቢያ ስምምነቱ የኒውክሌር ጉዳዮችን አያካትትም፣ ምክንያቱም እነሱ ውስብስብ ስለሆኑ እና ለድርድር በቂ ጊዜ ስለሚያስፈልጋቸው።
የመግባቢያ ስምምነቱ ከተፈረመ ከ30 ቀናት በኋላ፣ ለኒውክሌር ድርድር በር ሊከፈት ይችላል።
የፓኪስታን የጦር ሠራዊት አዛዥ [አሲም ሙኒር] የደረሱበትን የመግባቢያ ስምምነት ለዋሽንግተን ለማቅረብ ቴህራንን ለቅቆ ወጥቷል።
የመግባቢያ ስምምነቱን በማርቀቅ ረገድ የኳታር መንግሥት ቁልፍ ሚና ተጫውቷል፣ እንዲሁም በአስታራቂዎቹ እና በዋሽንግተን መካከል ግንኙነት ነበር።
ኢራን በመግባቢያ ስምምነቱ ውስጥ ከተገለጹት በላይ ተጨማሪ ቅናሾችን ማድረግ አትችልም፣" - አንድ የኢራን ባለስልጣን ለአል-ጃዚራ እንደተናገረው።
