en
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Open in Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
4 290
Subscribers
-1224 hours
-267 days
-9530 days
Posts Archive
⚡️🇮🇱— 'በሰሜን፣ ሰዎች በዚህ ሁለት ቀን ለአንድ ደቂቃ እንኳን አልተኙም ወይም አላረፉም።' በእስራኤል ሚዲያ ዘገባ መሠረት፣ 'በእያንዳንዱ ቅጽበት የማንቂያ ድምጾች፣ ፍንዳታዎች፣ መከላከያዎች፣ ጥቃቶች እና ወደ መጠለያዎች መሮጥ ይከሰታል። ሂዝቦላ ከተጠበቀው በላይ ረብሿል።'

እንደ ሐሳብ፡ የኢትዮጵያ መሪዎች ትኩረት በጣም ይፈልጋሉ፣ ይሄን እናውቃለን። በአንድ ወቅት የኖቤል ተሸላሚው ዓለምን አስታርቃለሁ ሲል እንደነበር፣ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፣ መጀመሪያ ከራስህ ጋር ተታረቅና ና ተብሎ ከዓለም መድረክ ላይ ከመባረሩ በፊት። ዛሬ ደቡብ ሱዳንና ጅቡቲም የሚደውሉ አይመስለኝም። እናም፣ አሁን ላይ ትኩረትን ፍለጋ ከላይ ወርደው የዑጋንዳንና የአሜሪካ ባሪያዎችን ስፖንሰር በማድረግ ወደ ሀገር እያመጡና እየቀወጡት ከመፈጥፈጥ፣ ሌላ ዘዴ ቢቀይሱ፣ እንደ ሀገርም ብንቀይስ፣ እንደኔ ጥሩ ነው እላለሁ። ስለዚህ፣ ዛሬ ካዛኪስታን እንዳደረገችው፣ የኛዎቹም የመጣው ይምጣ ብለው፣ የኢራንን ዩራኒየም በቢሾፍቱ ግምጃ ቤት በአደራ ለማስቀመጥ ፈቃደኛነታቸው ይግለጡ ለዓለም። ከመቶ ሺ ቲክቶከራም ይሄ አንድ ንግግር በቂ፣ ከበቂም በላይ በቂ ትኩረት ይስባል። ሰሞኑን እያሉን እንዳሉት "ቅዠታሞች" አይበሉን እንጂ፣ እርሶም ይሞክሩት ነው ነገሩ።

🇰🇿🇮🇷🇺🇸 ካዛኪስታን የኢራንን የዩራኒየም ክምችት በአደራ ለማስቀመጥ ጥያቄ አቅርባለች የተባበሩት መንግስታት የኒውክሌር ተቆጣጣሪ ኃላፊ ራፋኤል ግሮሲ፣ ዛሬ ለፋይናንሺያል ታይምስ በሰጡት መግለጫ መሠረት፣ ዋሽንግተን እና ቴህራን በኢራን አወዛጋቢ የኒውክሌር ፕሮግራም ላይ ስምምነት ከደረሱ፣ ካዛክስታን የኢራንን የዩራኒየም ክምችት ለማስቀመጥ ሀሳብ አቅርባለች።

🇹🇷 ቱርክ KAAN (ካን) የተባለ ተዋጊ ጀት መሥራት ጀምራ ነበር፣ ነገር ግን ሥራው እክል ገጠመው። 🇺🇸 የጀቱ ሞተር የአሜሪካ F1110 ጀት ሞተር ነው፣ ያንን ደግሞ አሜሪካ ለመስጠት ሳትፈቅ
🇹🇷 ቱርክ KAAN (ካን) የተባለ ተዋጊ ጀት መሥራት ጀምራ ነበር፣ ነገር ግን ሥራው እክል ገጠመው። 🇺🇸 የጀቱ ሞተር የአሜሪካ F1110 ጀት ሞተር ነው፣ ያንን ደግሞ አሜሪካ ለመስጠት ሳትፈቅድ ቀረች። 🇹🇷🛠 "ሀገር-በቀል" ሞተር ለማምረት፣ የቱርክ ሂሳብ ጠበብቶች እና ሮኬት ሳይንቲስቶች 2035 ላይ ምናልባት ብለዋል። 🇬🇧🇪🇺 አዲስ ሞተር እንኳ ብትሠራ፣ UK እና EU፣ ቱርክ ወደ ውጭ ኤክስፖርት እንዳታደርግ እንደሚይዟት ተናግረዋል። *** ቱርክም፣ ሜቴክ አላት ማለት ነው እንደኛ። ሞተር ከቻይና፣ ላሜራ እና ብየዳ ከሀገር፣ ከዚያ Made In የራስህ። ሌላውን ስፔርፓርት ሁሉ ከውጭ አስገባ፣ ችግር የለውም። ሞተርን የሚያክል ዋናውን ግን ከውጭ እንዳለ አምጥተህ ከገጠምክ በኋላ፣ እኔ ነኝ የፈበረኩት?

photo content

🇺🇦⚡️🇷🇺 ይህን የሚገርም ቪዲዮ ተመልከቱት፣ ምሽቱን የተፈጸመ ነው። ዩክሬን የሩሲያን አድሚራል ኤሰን የተባለን የክሩዝ ሚሳይል ተሸካሚ የጦር መርከብን፣ በኖቮሮሲይስክ የባሕር ኃይል ጣቢያ በFPV-ድሮኖች አጥቅታለች። ይህ ጥቃት በመርከቡ ላይ ለአራተኛ ጊዜ የተፈጸመ ጥቃት ነው። ምስሉ በአቅራቢያው ካለ መርከብ የተወሰደ ሲሆን፣ ድሮኑ መርከቡን ከመምታቱ በፊት ከባድ የፀረ-አውሮፕላን ተኩሶችን ሲያመልጥ ይታያል።

🇧🇬 🇺🇸 'የአሜሪካ ኃይሎች በቡልጋሪያ የሚገኘውን የሶፊያ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በኢራን ላይ ለሚደረጉ የወደፊት ጥቃቶች ድጋፍ ለማድረግ የአየር ላይ ነዳጅ ለመሙላት የሚያገለግሉ ታን
🇧🇬 🇺🇸  'የአሜሪካ ኃይሎች በቡልጋሪያ የሚገኘውን የሶፊያ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ፣ በኢራን ላይ ለሚደረጉ የወደፊት ጥቃቶች ድጋፍ ለማድረግ የአየር ላይ ነዳጅ ለመሙላት የሚያገለግሉ ታንከሮች ዋና ማቆሚያ ቦታ አድርገውታል። እዚህ የሚታየው፣ ትናንት ምሽት በማኮብኮቢያው ላይ የቆሙ ግማሽ ደርዘን የሚሆኑ KC-135ዎች ናቸው። በማንኛውም አዲስ ግጭት ውስጥ፣ ሁሉም የቡልጋሪያ አውሮፕላን ማረፊያዎች ለኢራን ህጋዊ ዒላማዎች ናቸው' IRGC.

⚡️🇪🇹 የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስቴር ንጉሠ ነገሥት ለመሆን ባለው ጥኑ ፍላጎት፣ ሀገሩንም ቀጠናውንም አደጋ ላይ እየጣለ ነው - The Economist. 'እናቴ ህፃን እያለው ንጉሥ ትሆናለህ ብላ
⚡️🇪🇹 የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስቴር ንጉሠ ነገሥት ለመሆን ባለው ጥኑ ፍላጎት፣ ሀገሩንም ቀጠናውንም አደጋ ላይ እየጣለ ነው - The Economist. 'እናቴ ህፃን እያለው ንጉሥ ትሆናለህ ብላ ተንብያልኛለች፣ እኔም ወደ ዚያው በጌታ ፈቃድ እየገሰገስኩኝ ነው' ይላል፣ ከሥሩ ላሉት ባለስልጣናት። 'እነሱም የእሱን ራዕይ በእልፍኝ ቤት አገልጋይነት ስሜት እየተገበሩ፣ ሀገሩም መላ ቀጠናውም አደጋ ውስጥ ወድቋል። *** የጠቅላዩ የንጉሥነት ቅዠት፣ እንደ እኔ፣ የመነጨው፣ ከእናቱ 'ትንቢት' ሳይሆን፣ ከኤሜሬት ወዳጁ ሼክ መሐመድ ቢን ዘይድ አል ናሕያን አጀንዳ (Vision) ነው። 'ይሄን ይሄን ወስደህ ተግብር፣ ከዚያ ትሆናለህ' ብሎታል። ችግሩ፣ መሐመድ ቢን ዘይድ የሰጠው አጀንዳ ካሁን በኋላ ለኤሜሬትም አይጠቅማትም።

🇺🇸🇮🇷⚡️ — የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስካት ቤሰንት፦ ወደ $1 ቢሊዮን የሚጠጋ የኢራን ክሪፕቶን ይዘናል — ዋለቶቹን በቀጥታ ወስደናል። አንዳንዶቹ አሁንም እየፃፉ እየተገበያዩ ሊሆን ይችላል፣ የእነሱ የኪስ ቦርሳ መያዙን ግን አላወቁም። ይህ ከኢራን ህዝብ የተሰረቀ ገንዘብ ነው።

🇺🇸🇮🇷⚡️— ትራምፕ፣ ስብሰባውን ያለ ምንም ውጤት አጠናቅቆ ወጥቷል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚደረገው አዲስ ስምምነት ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሳያደርግ የሁለት ሰዓት ያህል የሲቺዌሽን ሩ
🇺🇸🇮🇷⚡️— ትራምፕ፣ ስብሰባውን ያለ ምንም ውጤት አጠናቅቆ ወጥቷል። ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚደረገው አዲስ ስምምነት ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ሳያደርግ የሁለት ሰዓት ያህል የሲቺዌሽን ሩም ስብሰባ ለቅቆ ወጥቷል፣ ሲል NYT ዘግቧል። አንድ ከፍተኛ የአስተዳደር ባለሥልጣን እንደተናገሩት፣ የተያዙ የኢራን ንብረቶችን መልቀቅን ጨምሮ አለመግባባቶች ቢቀጥሉም፣ ነገር ግን ስምምነት ሊደረስበት እንደተቃረበ ዋይት ሃውስ ያምናል።

— 🇺🇸/🇮🇷 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፦ 'ከኢራን ጋር አስቀድሞ ሳይተባበር ማንኛውም መርከብ በሆርሙዝ መተላለፊያ መተላለፍ የተከለከለ ነው። የወሽመጡን የወደፊት አስተዳደራዊ ማዕቀፍ በተመለከተ፣ ጉዳዩ የውሃ መስመሩ ባለቤት ለሆኑት ሁለቱ ግዛቶች — ለኢራን እና ለኦማን ሱልጣኔት — የሚተው ነው።'

⚡🇷🇺 በጦር ሜዳ ላይ ያለው ሁኔታ ግጭቱ ወደ መጨረሻው እየተቃረበ ነው ለማለት ለሩሲያ መሰረት ይሰጣል - የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን። *** ፑቲን ጦርነቱን ለማቆም ፈልጓል፣ አውሮፓና ዘለንስኪ ግን የሩሲያን ድክመት አሽትተዋል። በግሌ ጦርነቱ እንዲቆም የሚፈቅዱለት አይመስለኝም። እስከዛሬዋ ቀን ድረስ፣ ምክኒያት እየፈለጉ ሲተገትጉት ከርመው፣ እንዳያቆም አደናቅፈውታል። አሁንም ያደናቅፉታል። ሩሲያ ታግሳ ይሁን ደክሟት አላውቅም፣ የያዛት ነገር አለ። በሩሲያ የፑቲን ቀኝ ዘመም ተቃዋሚዎች፣ ፑቲን ለምን የሩሲያን ኃይል እስከመጨረሻው ተጠቅሞ ኪየቭን እንደማያንበረክክ ግራ ገብቷቸዋል። ሶፍት ነህ ብለው ይከሱታል። በነዚህ ኃይሎች ግልበጣን በጥቂቱም ቢሆን ይፈራል፣ ነገሩ ከዚህ በላይ ሸርተት ካለ። ይሄን ሁሉ የውስጥ ገበና አውሮፓዎች አንብበዋል። ስለዚህ ስለ ሰላም ያላቸውን ጋሬጣነታቸውን ይቀጥሉበታል። በዚህም የተነሳ ፑቲን በጦር ሜዳ ያለውን የበላይነት እንደያዘ ማቆም ይፈልጋል።

🇺🇦⚡️🇷🇺 ሩሲያ ኪየቭን ስታስጠነቅቅበት የከረመችውን ጥቃት፣ ዛሬ ማታ ትጀምራለች ተብሎ ይጠበቃል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 በኢራን ቴሌቪዥን ላይ ሰበር ዜና እየጠበቅኩኝ ነው፣ ስለ ትራምፕ ቢናገሩ። እነሱ ኢግኖር ገጭተውት አዛን ነው የሚያሰሙት። የTasinm መገናኛ ብዙሃን ምንጮች ግን፣ ኢራንም ጉዳዩን በጥንቃቄ እያጤነችው ነው፣ ይፋዊ መልስ ትሰጣለች ተብሎም ይጠበቃል፣ ይላሉ። ትራምፕ በዚህ ሰዓት ከባለሟሎቹ ጋር ዝግ ስብሰባ ተቀምጦ እየመከረ ይገኛል፣ ወደ በኋላ የደረሱበት ይፈነዳል።

🇺🇸🇵🇰⚡️— የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ከፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢስሃቅ ዳር ጋር ተገናኝተዋል። *** ዘንድሮ እንደ ፓኪስታን የተከበረ ሀገር የለም፣ ሕንድ ብቻ ናት ጥርሷን እያስፋጨች ተናዳ ያለችው። የምሥራቅ አፍሪካው የኖቤል ተሸላሚም፣ ይሄኔ እኮ እዚህ ቦታ ላይ ራሱን እየሳለ በሕልሙ ቅቤውን ሲጠጣ ኖሯል።

— 🇺🇸/🇮🇷 New York Post የውጭ ፖሊሲ ዋና ሪፖርተር፦ 'ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረገውን ስምምነት መቀበል አለመቀበልን ለመወሰን አሁን ወደ ሲቺውዌሽን ሩም እየሄዱ ነው።'
— 🇺🇸/🇮🇷 New York Post የውጭ ፖሊሲ ዋና ሪፖርተር፦ 'ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር የተደረገውን ስምምነት መቀበል አለመቀበልን ለመወሰን አሁን ወደ ሲቺውዌሽን ሩም እየሄዱ ነው።'

—❗️🇺🇸/🇮🇷 ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የተጣለውን የአሜሪካ የባሕር ኃይል እገታ ሊያቆም መሆኑን ፍንጭ ሰጥቷል። በምላሹ፣ ኢራን ብዙ ነገሮችን እንድታደርግ ይጠይቃል — ከእነ
—❗️🇺🇸/🇮🇷 ሰበር ዜና፦ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በኢራን ላይ የተጣለውን የአሜሪካ የባሕር ኃይል እገታ ሊያቆም መሆኑን ፍንጭ ሰጥቷል። በምላሹ፣ ኢራን ብዙ ነገሮችን እንድታደርግ ይጠይቃል — ከእነዚህም ውስጥ ብዙዎቹ የተስማሙባቸው አይደሉም፣ የበለጸገ የዩራኒየም ክምችት አሳልፎ መስጠትን ጨምሮ። ትራምፕ በአሁኑ ሰዓት በስችዌሽን ሩም የመጨረሻውን ውሳኔ ለመወሰን ተቀምጫለሁ፣ ብሏል። ምሽቱን የመጨረሻው ውሳኔ ይጠበቃል።

⚡️🇮🇷🇺🇸🇮🇱 ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ አዛዥ ሙሕሲን ረዛይ ኢራን በድርድር ወይም በቀጥታ እርምጃ የባህር ኃይል እገታውን እንደምትሰብር ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና የእስ
⚡️🇮🇷🇺🇸🇮🇱 ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ አዛዥ ሙሕሲን ረዛይ ኢራን በድርድር ወይም በቀጥታ እርምጃ የባህር ኃይል እገታውን እንደምትሰብር ተናግረዋል። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ እና የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ ዶግማ፣ ኢራን ሳትወድቅ ሊሳካ የማይችል አዲስ የቀጠና ሥርዓት ማስቀመጥ እንደሆነ ተናግረዋል። “ዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል እገታውን እንድታቆም እናስገድዳታለን – ወይ በድርድር ወይም ከተቃወሙ፣ በቀጥታ እርምጃ በመውሰድ” ሲሉ ረዛይ ተናግረዋል። በተጨማሪም፣ በአስር ዓመታት ውስጥ የአሜሪካ ኢኮኖሚ በዓለም ላይ ወደ ሁለተኛ ወይም ሦስተኛነት እንደሚወርድ ተንብየው፣ የኢራን ኢኮኖሚያዊ የወደፊት ተስፋ ግን ብሩህ እና ተስፋ ሰጪ ብለዋል።

🇮🇱⚔️🇱🇧 ከሮይተርስ የተገኘ አዲስ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ እስራኤል 20% የሚሆነውን የሊባኖስን ክፍል የሚሸፍኑ የመልቀቂያ ትዕዛዞችን በነዚህ ቦታ ለሚኖረው ሕዝብ ሰጥታለች፣ ይህም ከዚህ ቀ
🇮🇱⚔️🇱🇧  ከሮይተርስ የተገኘ አዲስ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ እስራኤል 20% የሚሆነውን የሊባኖስን ክፍል የሚሸፍኑ የመልቀቂያ ትዕዛዞችን በነዚህ ቦታ ለሚኖረው ሕዝብ ሰጥታለች፣ ይህም ከዚህ ቀደም ከተናገረችው እስከ ሊታኒ ወንዝ ካለው "Buffer Zone"ም በላይ ተሻግሮ የሚሄድ ነው። የጋዛ ታክቲክ በሊባኖስ።

🇺🇸🇮🇷 — የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ሊደረግ የሚችለውን ስምምነት መፈረም አለመፈረምን ለመወሰን ጥቂት ቀናት እንደሚያስፈልገው ለአማካሪዎቹ አሳውቋ— CNN ** ትራምፕ ሰነዱን
🇺🇸🇮🇷 — የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ ከኢራን ጋር ሊደረግ የሚችለውን ስምምነት መፈረም አለመፈረምን ለመወሰን ጥቂት ቀናት እንደሚያስፈልገው ለአማካሪዎቹ አሳውቋ— CNN ** ትራምፕ ሰነዱን መፈረም ፈርቷል። በአሜሪካ ከሁሉም አቅጣጫ፣ ከሚዲያው፣ ከአማካሪዎቹ፣ ከሴኔቱ፣ ከኮንግረስ እና ከሌሎችም፣ ሰነዱ ኢራንን የሚጠቅም፣ አሜሪካን ደግሞ ተሸናፊ የሚያስመስል ነው የሚል ቅሬታ እየተወረወረበት ነው። ኦባማ በኢራን ድርድር ወቅት፣ የድርድሩ አካል የሆነን $1.7ቢሊዮን ዶላር በካሽ ሰጥቷቸዋል እያለ በየቀረበበት መድረክ ኦባማን ሲያብጠለጥለው የኖረው ትራምፕ፣ በዚህ በአሁኑ ድርድር፣ ለኢራን እስከ $300 ቢሊዮን ዶላር የካሳ ክፍያ ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ሊፈርም ነው እየተባለ ተቸግሯል። አለመፈረምም አይችልም፣ ምክኒያቱም ምርጫ እየመጣበት ነው፣ የግሮሰሪ ዋጋ ከፍ ብሏል፣ ጦርነቱም በሕዝቡ ተጠልቷል፣ ስለዚህ ለአሜሪካ መጥፎ ስምምነትም ቢሆን ከጦርነቱ እስካስወጣው ድረስ መፈረም ይኖርበታል። አጣብቂኝ ውስጥ ነው።