Green በጎ
Open in Telegram
Green Bego (Green በጎ) is a growing community and student-led initiative founded by Green New Generation School students. We focus on charity, youth empowerment, and promoting positive actions within society.
Show moreThe country is not specifiedThe category is not specified
207
Subscribers
No data24 hours
No data7 days
No data30 days
Data loading in progress...
Similar Channels
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Tags Cloud
No data
Any problems? Please refresh the page or contact our support manager.
Incoming and Outgoing Mentions
---
---
---
---
---
---
Attracting Subscribers
July '26
July '26
+24
in 0 channels
June '260
in 3 channels
Get PRO
May '26
+64
in 3 channels
Get PRO
April '260
in 2 channels
Get PRO
March '26
+119
in 3 channels
| Date | Subscriber Growth | Mentions | Channels | |
| 11 July | 0 | |||
| 10 July | 0 |
Channel Posts
ርዕስ፡ የመልካምነት ጉዞአችንን እናጠናቅቅ!
ውድ የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ፣
ለወገን እንድረስ እናግዝ በሚል መርህ ብዙ ወገኖቻችን የሚረዱበትንና የሚታከሙበትን ሆስፒታል በጋራ ለመገንባት ከመቄዶንያ በቀረበልን ጥሪ መሰረት የገንዘብ ማሰባሰቢያ ስናካሂድ ቆይተናል።
በዚህም በእናንተ ደግና ሩህሩህ ወላጆች፣ አስተማሪዎች፣ ተማሪዎች እና በመላው የትምህርት ቤታችን ማህበረሰብ ባደረጋችሁት ልዩ ትብብር ከዕቅዳችን 500,000 ብር ውስጥ 360,000 ብር ማሰባሰብ ችለናል። ይህም 72% የዕቅዳችንን ግብ ማሳካት እንደቻልን ያሳያል።
ለዚህ ታላቅ ድጋፍ እና ትብብር ከልብ እናመሰግናለን።
ይህን ውጤት ያስመዘገብነው በሁላችሁም ድጋፍ እና በግሪን በጎ ክለብ አባላት ያላሰለሰ ጥረት ነው። አሁንም የቀረውን 140,000 ብር በአንድነት፣ በትብብር እና በቅንነት እንደምናሟላው ሙሉ እምነት አለን።
ስለዚህ ሁላችሁም የግሪን ማህበረሰብ አባላት እና ነገ በኔ ብላችሁ የምታምኑ ወገኖች ከዚህ ታላቅ ዓላማ ጎን በመቆም አስተዋጽኦዎን እንድታበረክቱ በአክብሮት እንጠይቃለን።
ወላጆችም ለልጆቻችሁ አርአያ በመሆን ድጋፋችሁን በሚከተለው የባንክ ሂሳብ ቁጥር ማድረግ ትችላላችሁ።
💳 CBE Account
1000748130358
(Mulusewu Muniye – Mekodonia
Kaleb Demissaw – Green School (Green Bego))
“መስጠት አያጎድልም!”እናመሰግናለን።። Instagram | TikTok | Telegram
| 2 | 🟢 የግሪን በጎ ፌስቲቫል፡ ከልብ የመነጨ ምስጋና! 🟢
ውድ የግሪን ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ወላጆች፣ በጎ ፈቃደኞች፣ አስተዳደር እና በቦታው ተገኝታችሁ የነበራቹ በሙሉ፤
ባለፈው ቅዳሜ (ግንቦት 8) በታላቅ ድምቀት የተካሄደው የግሪን በጎ ፌስቲቫል (Green Bego Festival) በማይታመን ስኬት መጠናቀቁን በታላቅ ደስታና ትህትና እንገልጻለን! 🌟
የእናንተ ከፍተኛ ተሳትፎ፣ መነሳሳት እና እውነተኛ ደግነት ታክሎበት በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ ከ180,000 ብር ማሰባሰብ ችለናል! 💸🎉
ይህ ትልቅ ስኬት ወደ ዋናው የገቢ ማሰባሰብያ ግባችን አንድ ግዙፍ እርምጃ ያቀረበን ሲሆን፥ እንደተለመደው 100% የተገኘው ገቢ በሙሉ ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማህበር የግንባታ እና የእንክብካቤ ፕሮጀክቶች ድጋፍ በቀጥታ የሚውል ይሆናል።
ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ለ፡
• ለትምህርት ቤታችን አስተዳደር እና መምህራን — በራዕያችን አምነው ስላበረታቱንና ቦታውን ስለፈቀዱልን።
• ለግሪን በጎ የስራ ክፍሎች እና በጎ ፈቃደኞች — ከበስተጀርባ ሆነው የቪአር (VR) ጌሞችን፣ የመዝናኛ ቦታዎችን እና አጠቃላይ የፌስቲቫሉን እንቅስቃሴዎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ላስተባበሩ።
• ለእያንዳንዱ ታዳሚ — በቦታው ተገኝታችሁ፣ አቅማችሁ የፈቀደውን አስተዋጽኦ አድርጋችሁ ቀኑን ልዩ ስላደረጋችሁልን።
እናንተ ፌስቲቫል ላይ መገኘት ብቻ ሳይሆን እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖቻችን ተስፋ ሆናችኋል። የርህራሄን እና የአንድነትን እውነተኛ ኃይል ስላሳያችሁን እናመሰግናለን።
የፌስቲቫሉን ይፋዊ ፎቶዎች እና ቪዲዮዎች እንዲሁም ቀጣይ ስራዎቻችንን በቅርቡ በዚህ ቻናል የምናጋራ ይሆናል፤ ይጠብቁን!
ግሪን በጎ —
በጎ በጎውን 💚
2026
Instagram | TikTok | Telegram | 6 961 |
| 3 | 🚨 1 ቀን ብቻ ቀረው! 🚨
ነገ ማንም እንዳይቀር! በደስታ እና በፈገግታ የሚሞላ፣ ልዩ እና የማይረሳ ጊዜ አብረን እናሳልፋለን። ✨
🗓️ ዋና ዋና መረጃዎች፦
• 🕒 የመግቢያ ሰዓት፦ ነገ ጠዋት ከ2:00 ጀምሮ በሮች ክፍት ይሆናሉ።
• 🎫 የቲኬት ማረጋገጫ፦ የገዛችሁት ቲኬት በSMS (በፅሁፍ መልዕክት) መድረሱን ያረጋግጡ። ካልደረሶት እባክዎ በፍጥነት ያነጋግሩን።
• 🎟️ የዕለቱ ቲኬት፦ አስቀድመው መግዛት ካልቻሉ፣ በዕለቱ በሩ ላይ መግዛት ይቻላል።
• 📍 ቦታ:- ዋናው ግሪን ስኩል ግቢ (Green new generation school)
🎈 ልዩ ልዩ አገልግሎቶች እና ዋጋቸው፦
የሚከተሉት አገልግሎቶች ከተጨማሪ ክፍያ ጋር የቀረቡ ናቸው፦
• 🎨 ፌስ ፔይንት (Face Paint)፦ 100 ብር
• 🍦 አይስክሬም እና ኮተን ካንዲ፦100 ብር
• 📸 ፎቶ ቡዝ (Photo Booth)፦ 350 ብር
ቲኬት ለመቁረጥ፦ https://chapa.events/to/green-bego-festival
ነገ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል! እንዳትቀሩ! 🎉
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የማበራዊ ድረገፆቻችንን ይቀላቀሉ፦
Instagram | TikTok | Telegram
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን | 4 719 |
| 4 | ONLY 3 days left🔥
🎉 Don’t miss the Green Bego Festival
📍 ቅዳሜ May 16 @ Green new generation school
🎟️ Get your tickets now on:
👉 chapa.event
Your weekend plans are officially set 😎
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የማበራዊ ድረገፆቻችንን ይቀላቀሉ፦
Instagram | TikTok | Telegram
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን | 3 506 |
| 5 | 🎉 Green Bego kids Festival 🎉
📅 ቀን: ቅዳሜ ግንቦት 8, 2018 (May 16, 2026)
መረጃ ፦
• 📍 ቦታ:- ግሪን ስኩል (Green School)
• 💰 ዋጋ፦ 325 ብር (ለአንድ) | 899 ብር (ለ3) | (New)1200ብር(ለ4) | 1450 ብር (ለ5)
🎟 ቲኬቶች በኦንላይን በ Chapa Events ይገኛሉ👇
https://chapa.events/to/green-bego-festival
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
🔗 https://t.me/Greenbego
Our TikTok account: https://vt.tiktok.com/ZS9ned7nL
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን
@greennewgenerationschool #greenschool #greenbego #kidsfestival #kidsfestivale #kidsfestivaleaddisabeba | 8 431 |
| 6 | 📣 ሁለተኛ የጊዜ ማራዘሚያ ማሳሰቢያ፡ የፌስቲቫሉ ቀን ተቀይሯል!
ውድ ወላጆች፣
ቀደም ብለን የፌስቲቫሉን ቀን አራዝመን የነበረ ቢሆንም፣ በርካታ ወላጆች ቀኑ ከግንቦት ልደታ በዓል ጋር በመገጣጠሙ ምክንያት እንዲቀየርልን ባቀረባችሁልን ጥያቄ መሰረት፣ የተሳታፊዎቻችንን ፍላጎት በማክበር ቀኑን በድጋሚ ለማራዘም ወስነናል።
ልጆቻችሁም ሆኑ እናንተ ወላጆች በበዓሉ ቀን ቤተሰባዊ ግዴታችሁን እንድትወጡና በፌስቲቫሉ ላይም ያለምንም ስጋት እንድትገኙ ስንል አዲሱን ቀን እንደሚከተለው አስተካክለናል፦
🗓 አዲስ የጊዜ ሰሌዳ
• የነበረው ቀን፦ ግንቦት 1 (May 9)
• አዲሱ ቀን፦ ቅዳሜ ግንቦት 8 (May 16, 2026)
ሁሉም ዝግጅቶች (VR፣ ስዊሚንግ ፑል...) እንዳሉ ናቸው። ገቢውም ለመቄዶንያ በጎ አድራጎት የሚውል ይሆናል።
መረጃ ፦
• 📍 ቦታ:- ግሪን ስኩል (Green School)
• 💰 ዋጋ፦ 325 ብር (ለአንድ) | 899 ብር (ለ3) | 1450 ብር (ለ5)
• 🎟️ ቲኬት፦ https://chapa.events/to/green-bego-festival
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
🔗 https://t.me/Greenbego
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
ግሪን በጎ
በጎ በጎውን
#greenbego #greenbegofestival #greennewgenerationschool #mekedonia | 5 015 |
| 7 | 📣 ጠቃሚ ማሳሰቢያ፡ የፌስቲቫሉ ቀን ተራዝሟል!
ውድ ወላጆች፣
ለልጆቻችሁ የተሻለ ዝግጅት ለማቅረብ ስንል የ Green Bego Festival የሚካሄድበትን ቀን የቀየርን መሆኑን በታላቅ አክብሮት እንገልጻለን።
እባካችሁ የቀን ለውጡን ልብ በሉ፡
• የነበረው ቀን፦ ሚያዝያ 24፣ 2018 (May 2)
• አዲሱ ቀን፦ ቅዳሜ ግንቦት 1፣ 2018 (May 9, 2026)
ከቀን ለውጡ ውጭ ሌሎች ዝግጅቶች (VR ጨዋታዎች፣ የመዋኛ ፑል፣ ባውንሲ ቤቶች እና ሌሎችም) እንዳሉ ናቸው። የፌስቲቫሉ ገቢም እንደተለመደው ለ መቄዶንያ በጎ አድራጎት ማህበር ድጋፍ የሚውል ይሆናል።
ቀድማችሁ ቲኬት የቆረጣችሁ ወላጆች፣ ቲኬታችሁ በአዲሱ ቀን (ግንቦት 1) የሚያገለግል መሆኑን እናሳውቃለን። ቲኬት ያልቆረጣችሁ ደግሞ በ Chapa Events ማግኘት ትችላላችሁ።
ስለ ትብብራችሁ እናመሰግናለን! በዕለቱ ተገናኝተን ለልጆቻችን የደስታ ቀን እንፍጠርላቸው።
አጭር መረጃ፦
• ቦታ፦ ግሪን ስኩል (Green School)
• የቲኬት ዋጋ፦ 325 ብር (ለአንድ ልጅ) | 899 ብር (ለቤተሰብ 3 ልጆች) | 1450 ብር (ለጓደኛሞች 5 ልጆች)
• መግቢያ፦ ለወላጆች በነፃ ነው!
ቲኬት ለመቁረጥ፦ https://chapa.events/to/green-bego-festival
ለተጨማሪ መረጃ እና አዳዲስ ኩነቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦
🔗 https://t.me/Greenbego
ማንኛውም አስተያየትም ሆነ ጥያቄ ካላችሁ በዚህ ሊንክ ያግኙን👇
📩 https://t.me/greenbegosupport
#greenbego #greenbegofestival #greennewgenerationschool #mekodonia | 3 107 |
| 8 | 🎉 Green Bego Festival 🎉
ውድ ወላጆች፣
Green Bego እና Green School በመተባበር ለህፃናት ደስታ እና የማይረሱ ትዝታ የሚፈጥር ፌስቲቫል አዘጋጅተናል!
📅 ቀን: ሚያዝያ 24, 2018 (May 2, 2026)
🎈 የሚካተቱ ነገሮች:
• VR ጨዋታዎች 🎮
• ትራምፖሊን 🤸♂️
• ባውንሲ ቤቶች 🏰
• የመዋኛ ፑል 🏊♂️
• የሜዳ ጨዋታዎች ⚽
• ከወላጆች ጋር ጨዋታዎች 👨👩👧👦
• ሙዚቃ እና ዳንስ 🎵
• ፌስ ፔይንት 🎨
• ምግብ እና መጠጥ 🍔🥤
💳 የቲኬት ዋጋ (ለጨዋታዎች ብቻ):
• Single child (ነጠላ ልጅ): 325 ብር (VR, ትራምፖሊን, ባውንሲ, ፑል እና የሜዳ ጨዋታዎች ያካትታል)
• Family bundle (የቤተሰብ ቅናሽ - 3 ልጆች): 899 ብር
• squad bundle (የጓደኞች ቡድን - 5 ልጆች): 1450 ብር
⚠️ ማስታወሻ:
• ቲኬቱ ለጨዋታዎች ብቻ ነው
• ምግብ እና ፌስ ፔይንት በተለየ ክፍያ ይሆናሉ
• ወላጆች መግቢያ በነፃ ነው
🎟 ቲኬቶች በኦንላይን በ Chapa Events ይገኛሉ👇
https://chapa.events/to/green-bego-festival
💚 አስፈላጊ ማሳሰቢያ:
የፌስቲቫሉ ገቢ ሁሉ ለ Mekodonia Humanitarian Association የድጋፍ ስራ ይውላል።
👉 ልጆቻችሁን አምጡ፣ ደስታን እና ርህራሄን በአንድ ላይ እንፍጠር!
#Greenbego
#StudentImpact #greennewgenerationschool #mekodonia | 242 |
| 9 | Today, we are grieving a deep and painful loss.
Lidiya was our symbol of hope, strength, and inspiration. We stood with her through every step—fighting together, believing together. We were so close, just one final chemotherapy away from victory, but her journey came to an end.
Though our hearts are heavy, we trust in God’s timing.
Lidiya will forever live in our hearts. Her courage, her strength, and her spirit will continue to inspire us every day.
We love you, Lidiya. You will never be forgotten.🕊️💚
— Green Bego | 411 |
| 10 | እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ🎁
“ለመቆዶኒያ | For Mekodonia” is now live on YouTube.
See the full documentary and be part of something meaningful.
👉 Watch now on YouTube
https://youtu.be/8xPFJy_udqY?si=kOl6ereVziQiRJH6
🎥 Production Credits:
Produced by: Green Bego
Film by: Rodas solomon and Kaleb demissaw
Color grading & Editing: Kaleb demissaw
Interviewer : Eliana solomon
Best boy: Biruk wondson
Subtitle by: Nestanet wondeson
#Mekodonia #ለመቆዶኒያ #GreenBego #Ethiopia #Documentary #GiveBack | 740 |
