en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Open in Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
194
Subscribers
No data24 hours
-37 days
-730 days
Posts Archive
ወላጆችህ በህይወት ካሉ እድሉ አለህ ። ተከፍሎ የማይዘለቅ የወላጆች ሀቅ አጭር ምክር በሙሐመድ ሲራጅ ሙ. ኑር https://t.me/msirage4

ወላጆችህ ሲናገሩ፣ ወደ ስልክህ ሳይሆን ወደ እነሱ ተመልከት!! ሸይኽ ሱለይማን አርሩሀይሊ

ኢብኑል ቀዪም ረሂመሁላሁ እንዲህ ብለዋል፦ "በሎጂኩ መለኮታዊ ራዕይን(ቁርኣንና ሐዲስ) የተጣረሰ በሙሉ ጤናማ አይምሮ ያለው በሙሉ መሳቂያ እስኪሆን አላህ አይምሮውን (አስተሳሰቡ) ያበለሽበታል።" [አሰዋኢቅ አልሙርሰላ (3/1002)]

እውነታው ይሄ ሆኖ.... # የሰለፎች አቋም በአላህ ስም እና ባህሪያት ላይ ለመሆኑ ማን ነው ትክክል!? ሙሐመድ ሲራጅ ሙ ኑር https://t.me/msirage4

ከኢብኑ ተይሚያህ መልእክቶች መንገድ የሳቱት ጠማማዎቹ ሰዎች ሲጓዙ ሚዛናዊ አይደሉም። ኩራት ይታይባቸዋል።  ሲያወሩም ድምጻቸውን ዝቅ አያደርጉም። መጥፎ ስራዎችን ሲያሰራጩ ልክ እንደሚያገሳ ወይፈን እየጮሁ ነው። በባጢል ሲደንሱ ደግሞ ልክ እንደ ድብና መሰሎቹ እንስሳቶች ናቸው። የአላህን፣የመልእክተኛውንና የሶሀባዎችን ንግግር መስማት አይሹም። እንዳውም ላለመስማት ይሸሻሉ። የአዛኙንና የንጉሱን ቃል (ቁርአንን) ከሚሰሙ ይልቅ የሸይጧንን መዝሙር ማድመጡ ያስደስታቸዋል። ጃሚዑል መሳኢል 8/398

ፊዩሽ መርከዝ የመን ላይ

ሸይኽ ሁሴን ስለ ሽርክ_ ጫት.mp37.61 MB

ትልቅ ወንድማዊ ምክር 🧨 አበላሽ ሴቶችን ከማግባት ተጠንቀቁ!! 🚷 አንተ ራስህ ከመበላሸትህ በፊት አግብተን እናስተካክላቸዋለን በሚል ምክንያት የተበላሸ እምነት ያላቸውን ሴቶች ከማግባት ተቆጠብ‼
ትልቅ ወንድማዊ ምክር 🧨 አበላሽ ሴቶችን ከማግባት ተጠንቀቁ!! 🚷 አንተ ራስህ ከመበላሸትህ በፊት  አግብተን እናስተካክላቸዋለን በሚል ምክንያት የተበላሸ እምነት ያላቸውን ሴቶች ከማግባት ተቆጠብ‼ • ምክንያቱም: ዒምራን ኢብኑ ሀጧንም ውቢቷን ኻሪጂያህ ሴት አግብቼ ወደ ሱና መልሳታለሁ ብሎ ራሱ የኸዋሪጅ አቀንቃኝ ሆኖ ቀርቷል። سير أعلام النبلاء( 214)

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 🌿በረመዷን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች ⛔️ ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣ ⛔️ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሰሑርን አስቀድሞ በመመገብ ሱብሕ ሳይሰግዱ መተኛት፣ ⛔️ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም (ሙሰልሰላት) ማሳለፍ፣ ⛔️ረመዷንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣ ⛔️ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣ ⛔️ተራዊሕ ላይ በየአራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐ እና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን ማስገባት፣ ⛔️ የተራዊሕ ኢማሞች በጣም ረጅም የቁኑት ዱዓእ ማድረግ፣ ⛔️መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ ስርአት በሌለው መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ (ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣… አለ) ⛔️ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ" እያሉ መዞር፣ (10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣ ⛔️ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣ ⛔️እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣ ⛔️ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ አያስፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት ማለማመድ፣ ⛔️ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣ ⛔️ሴቶች ሽቶ ተቀብተው ለተራዊሕ መውጣት፣ ⛔️በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች በየ ጎዳናውና በየካፌው አላስፈላጊ መዝረክረክ፣ ⛔️ሃሜት፣ ⛔️ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣ ⛔️ቀኑን በካርታ፣ በዳማ እና መሰል አጉል ነገሮች ማሳለፍ፣ ⛔️ሙዚቃ ማዳመጥ፣ ⛔️የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣ ⛔️በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን ያለበት ከተመቼ ቁርኣን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።) ⛔️ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ ተሰብስበው እያወሩ መጠበቅ (የሚታይ ነገር የለም)፣ ⛔️አንዳንድ አካባቢዎች የዒሻእ ሶላትን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣ ⛔️አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣ ⛔️አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማስገደድ፣ ወዘተ ⛔️ከመግሪብ ሰላት በፊት ባለችዋ ወቅት ከዱዐ መዘናጋት ⛔️ኣዛን እስከ ሚጨርስ ድረስ ሳያፈጥሩ መቆየት ⛔️ፉጡር ላይ ተጠምዶ የመግሪብ ኣዛን ከመመለስ መዘናጋት ⛔️የመግሪብ ቀብልያ ከመስገድ ይልቅ ለዚህም ለዚያም እያቀባበሉ ሱና ማስመለጥ ⛔️በፉጡር ተጥዶ የመግሪብ ሰላት ቤት መስገድ ⛔️የመግሪብ ቀብልያም ይሁን ባዕድያ ቸላ ማለት ⛔️በኢፍጣር ሰዓት ከልክ በላይ በልቶ ራስን ማስጨነቅ ⛔️ከመግሪብ እስከ ዒሻ ያለው ወቅት በትርኪ ምርኪ ማባከን ⛔️የተራዊሕ ሰላት ከኢማም ጋ ሙሉ ከመስገድ መዳከም ⛔️ሰሁርን መተው ⛔️የሰሁር ሰዓት ዱዐ ከማድረግ መዘናጋት ⛔️ለጥንቃቄ በሚል ስሁርን በጣም በጊዜ መብላት ⛔️ህፃናት ጾም ከማለማመድ መዘናጋት

የዛሬ መሻኺኮቻችን ትናንትና በዚህ ሁኔታ ነበር ድንን የተማሩት ብዙ ተመቻችቶላቸው አልነበረም ።ብዙ ችግሮች ነበሩ፣ በቀሪአ እንጀራ ከፊሉ ከውሻ ጋር ትግል ሲገጥም፣ውሃ ጥሙ ፣ረሐቡ፣ በዳስና በደሳሳ ጎጆ ውስጥ ሁነው ብረዱ እና ቅዝቃዜው እንዲሁም የተፍቀ ጣውላ መሣይ እንጨት(ሉህ ይባላል በተለምዶ) በትክሻቸው ይዘው እየዞሩ እንዲህ ሁነው ነው ይህን አማና ያስረከቡህ !!! እኔ እና አንተ ግን በዚህ ከሰላም ውጭ ሁሉ በተሟላበት ሁኔታ የት ነው ያለነው????? እራሳችንን እንፈትሽ!!!!

🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿 🍃ቢያንስ ከራሳችን እንማር "ብልጥ ከሌሎች ይማራል፤ ሞኝ ከራሱ ይማራል" ይባላል። የመጀመሪያውን ብስለት ባለማስተዋል፣ ራስን ባለመቆጣጠር አልፈነዋል። ቢያንስ ከራሳችን ድክመት ብንማር ጥሩ ነው። ከደረሱትና ከሚደርሱት እንማር። በምን መልኩ? 🔻1. ወደራሳችን በጥልቀት እንመልከት። ራስን ጥሎ ሁሌ ሌሎችን ማሳደድ ኣኺራን ይጎዳል፣ ቡድንተኝነትን ያወርሳል። የልብ ድርቀትን ያስከትላል። 🔻2. የዑለማኦችን አካሄድ የምንፈልገውን እየመረጥን ሳይሆን ወይም በሌሎች የተመረጠልንን ሳይሆን ከነፍሲያ ወጥተን ከሁሉም አቅጣጫ እንመልከት። ነጠላ ንግግሮቻቸውን ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ አፈፃፀማቸውንም እናጥና። የእውነት እኛ በምናደርገው መጠን ሰው ላይ በማክ * ፈርም ይሁን ተብዲዕ በማድረግ ላይ የተናጠል ፍርድ ለመስጠት ይቸኩላሉ ወይ? በጭራሽ! 🔻3. በምናራምዳቸው እርምጃዎች ላይ የደዕዋችንን መስለሐ በሚገባ እናጢን። ደዕዋችንን የሚያሳጣን፣ መስጂዶቻችንን የሚያስነጥቀን ከሆነ ጩኸታችን ምን ፋይዳ አለው? አካሄዳችን የሰለፊያን ደዕዋ የሚያጠለሽ ከሆነ ወደድንም ጠላንም የጠላትን አጀንዳ እየፈፀምን ነው። 🔻4. ከሱና ዑለማኦች ውስጥ አንድ ወይም ሁለት ላይ አንገደብ። ይሄ አካሄድ አንዳንዶችን ተ0ሱብና ጉሉው ላይ ሲጥላቸው እያየን ነው። እውነታውን የማያምኑት ችግሩ ስለሸፈናቸው ነው። 🔻5. ተዝኪየተ ነፍስ ላይ እናተኩር። ለችግሩ መስፋት አንዱ ትልቅ ሰበብ የተቅዋ፣ የወረዕ መሳሳት ነው። ሌሎች ላይ ዋሽቶ መክሰስ፣ ሳያረጋግጡ በግምት መወንጀል፣ በጥላቻ ድንበር ማለፍ፣ የራስን ነውር እየደበቁ ሌሎችን መናከስ፣ ... አላህን መፍራት እንደሌለ ወይም እንደሳሳ የሚያጋልጥ ነው። እና እራሳችንን አንርሳ። 🔻6. አቅማችንን እንወቅ። ከቁመታችን በላይ የሆኑ ርእሶችን አናቡካ። 🔻7. ወደ ኢስላም ጠቅልለን እንግባ። አኽላቅም፣ ዙህድም፣ ወረዕም፣ ሲራም፣ ተርጊብና ተርሂብም የኢስላም አካል መሆናቸውን ከምላስ ባለፈ በተግባር እናረጋግጥ። ሰለፎች ከነዚህ ነጥቦች አንፃር የነበሩበትን የላቀ ደረጃ እናጥና። 🔻8. ሰው ተከትለን ገደል እንዳንገባ እንጠንቀቅ። በየመንደሩ የወደድኩትን ውደዱ፣ የጠላሁትን ጥሉ የሚሉ የሹም ዶሮዎች ይኖራሉ። እናስተውል! እነዚህ አካላት አብረውን ቀብር አይገቡም። እጃችንን ይዘው ሲራጥ አያሻግሩንም። እርቃናችንን ብቻችንን ለሒሳብ እንደምንቆም እናስብ። ነገ ከመመርመራችን በፊት ዛሬ ራሳችንን፣ አካሄዳችንን እንመርምር። እናስተውል! ከአንዳንዶች መናከሶች ጀርባ በሱና ስም የሚቀርብ የተዳፈነ የግል ቅሬታ አለ። የአንዳንዶቹ ጉልበት ጭፍን ጭፍራቸው ስለሆነ ገለል በማለት ራሳችንንም እናድን፣ እነሱንም እናስተንፍስ። ይጠቅማቸዋል እንጂ አይጎዳቸውም። 🔻9. የታየ ሁሉ ባደባባይ አይወራም። ጥፋት የመሰለን ነገር ጊዜ ስንወስድ እንዳሰብነው ላይሆን ይችላል። ክፍተትም ቢሆን መናገሩ ችግር የሚያባብስ ከሆነ አያያዛችንን ማጤን ያስፈልጋል። 🔻10. ለሰፊው ህዝብ እንዘን። በመጯጯህ ከሱና፣ ከዒልም፣ ከመስጂድ የምናርቃቸው እንዳይኖሩ ጥንቃቄ እናድርግ። 🔻11. የመንሀጅ ጥንካሬ ብዙ በመጮህ፣ ብዙ በመዝለፍ፣ ሳያጣሩ በግምት በመወንጀል፣ ንግግር እየቆለመሙ በመፈረጅ አይደለም የሚለካው። ስንወድም፣ ስንጠላም፣ ስናወድስም ስንተችም በልክ በሚዛን ሊሆን ይገባል። ይሄ ቁርኣናዊ መርህ ነው። ማሳሰቢያ፦ የፅሁፌ አላማ ራሴን ከችግሩ ነፃ አድርጌ ሌሎችን መንካት አይደለም። ይልቁንም ሰከን ብሎ በማጤን ለራሳችንም፣ ለወገናችንም፣ ለደዕዋችንም እንዘን፣ ሁላችንም እናስተውል የሚል ነው። አላህ ያለለት ሰው፣ ጎድቶም ተጎድቶም የኋላ ኋላ ሊነቃ ይችላል። በጊዜ ብንነቃ ግን ጉዳት እንቀንሳለን። ደግሞም ሳይመለሱ መሄድም አለ። በሰው ሐቅ ላይ ድንበር መተላለፍ ደግሞ ለመመለስም እንቅፋት ሊሆን ይችላል። አላህ ማስተዋሉን ያድለን። ✍IbnuMunewor የተወሰደ

የሚያጓጓው ሰላም ~ አሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ። ሰላም ሰላሙን ለተከተሉ ሁሉ ይሁን፡፡ እኛ ሙስሊሞች ሰላማዊ ነን፣ ከሰላሙ ጌታ ሰላምን የምንሻ፡፡ ስማችንም ሀይማኖታችንም ከሰላም ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ እርስ በርስ ስንገናኝ ከማንኛውም የቃላት ልውውጥ በፊት ከየትኛውም ህዝብ በተለየ በቋንቋ የማይግባቡ ህዝቦችን የሚያግባባ ውብ፣ ድንቅ፣ አጭር አለማቀፋዊ ቋንቋ አለን- “አሰላሙ ዐለይኩም” (ሰላም በናንተ ላይ ይሁን)፣ “ወዐለይኩም አሰላም” (ሰላም በናንተም ላይ ይሁን)፡፡ እኛ እንደነ ጀምስ “ሀይ” እንደነ እንትና “ታዲያስ” … ብለን በጥያቄ፣ በነገር፣ በፉገራ፣ በመአት … አንጀምርም፡፡ ይልቁንስ በዱዓ ነው የምንጀምረው፣ በመልካም ምኞት! ፊትን ፈታ አድርጎ፣ እዝነትና ትህትና በተላበሰ መልኩ “አሰላሙ ዐለይኩም!” ኢስላም፣ ኢስቲስላም፣ ሙስሊም፣ ሰላም፣ …!! ከጌታችን ስሞች አንዱ አሰላም ነው፡፡ ከአምስቱ እለታዊ ግዴታዎቻችን ከሶላቶቻችን በኋላ ከአሰላሙ ከጌታችን ሰላምን እንለምናለን፣ “አላሁመ አንተ ሰላም፣ ወሚንከ ሰላም፣ ተባረክተ ያዘልጀላሊ ወልኢክራም” በማለት። “ጌታችን ሆይ! አንተ ነህ ሰላሙ፤ ሰላምም ካንተ ነው፤ በስምህ የሚገኘው በረከት ሰፋ፤ አንተ የልቅናና የቸርነት ባለቤት ሆይ”፡፡ ብንገናኝ፣ ብንለያይ፣ ብንፀልይ፣ ብንወያይ፣… በሰላም ነው፣ ለሰላም፣ ስለሰላም! ጌታችን አሰላም፣ የምንመኘው አገር ዳሩ ሰላም– የሰላሙ ሀገር - (ጀናህ)! የሰላሙ አገር ሰላምታም ሰላም ነው፣ ( وَتَحِيَّتُهُمْ فِيهَا سَلَامٌ) "በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው።" ከአንድየው ከአሰላሙ የሚመጣውም ብስራትም ሰላም ነው፣ (سَلَامٌ قَوْلًا مِنْ رَبٍّ رَحِيمٍ) "(ለነርሱም) አዛኝ ከሆነው ጌታ በቃል ሰላምታ አላቸው።" [ያሲን: 58] በሰላሙ ሀገር በጀናህ የሚሰማውም ወሬ ረብ- የለሽና እንቶ ፈንቶ ሳይሆን ሰላም ነው፣ (إِلَّا قِيلًا سَلَامًا سَلَامًا) "ግን ሰላም መባባልን (ይሰማሉ)፡፡" [አልዋቂዐ: 26] ሱብሐነላህ! አሁን እንደ ኢስላም ለሰላም ትልቁም ዋጋ የሰጠ አለወይ?! ሙስሊም መሆን ምንኛ መታደል ነው? ውስጣዊ ሰላምን የሚያጎናፅፍ ልዩ ተድላ! ሙስሊም ነዎት?! አላሁ አክበር!! የታላቅ ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል! ያሸነፉት ሎተሪ አይደለም! በጭራሽ! ያሸነፉት ለሰው-በላ ጭራ ^ቆች፣ ለፀረ-ሰላም ሀይሎች፣ ለነ ሻሮን ወንድሞች ጭምር የሚሰጠውን የነ ጀምስን የኖቤል የሰላም ሽልማት አይደለም፡፡ ሽልማትዎ አይን ያላየው፣ ጆሮ ያልሰማው፣ በሰው ልቦና ውስጥ ፍፁም ውል ብሎ የማይውቅ እጅግ ውድና አጓጊ ነገር ነው! ሽልማትዎ ይሄውና! ከባለ ሰላሙ ጌታ ከአሰላሙ በኢማን ለታጀበው የሰላም ትጋትዎ ዳሩ ሰላም! ጀናህ! فَمَنْ زُحْزِحَ عَنِ النَّارِ وَأُدْخِلَ الْجَنَّةَ فَقَدْ فَازَ "ከእሳትም የተራቀና ጀነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡" [ኣሊ ዒምራን: 185] ከዚህ የሚበልጥ ምን ሽልማት አለ? አያሽቀዳድምም? (وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِنْ رَبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ) ከጌታችሁ ወደ ሆነች ምሕረትና ስፋቷ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ሆነች ጀነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትሆን ተቻኮሉ፡፡" [ኣሊ ዒምራን: 133] ሙስሊም ሙስሊማት ዒባዱ ሰላም! የአዛኙ የአሰላም ባሪያዎች በምድር ላይ ሲጓዙ በሰኪና ነው፣ በትህትና፣ በሰላማዊ ሁኔታ፡፡ ቂሎች፣ ከቂል የሚጠበቁ ቃላትን ቢወረውሩባቸው፣ በቂልኛ ቢያናግሯቸው፣ ፀረ-ሰላም ሚሳኢል ቢያስወነጭፉባቸው፤ ኢላማውን በማይስተው የሰላም ሚሳኢል ያከሽፉታል፣ አቅጣጫ ያስቀይሩታል፡፡ “ሰላም” በማለት፣ ሰላም በመመለስ፣ በሰላምኛ በማናገር፡፡ وَعِبَادُ الرَّحْمَٰنِ الَّذِينَ يَمْشُونَ عَلَى الْأَرْضِ هَوْنًا وَإِذَا خَاطَبَهُمُ الْجَاهِلُونَ قَالُوا سَلَامًا "የአረሕማንም ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚሄዱት፣ ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው፡፡"  [አልፉርቃን: 63] የኢማን፣ የኢስላም፣ የሰላም አርአያዎቻችን ከአሰላሙ ጌታችን ለተቀበሉት የሰላም አደራ - ለኢስላም ሲሉ የደሙት፣ የቆሰሉት፣ የተሰቃዩት፣ የሞቱት ነቢዮቻችን ናቸው፡፡ እነዚያ በአስፈሪው የቂያማ ጭንቅ ጊዜ እንኳን ስለ ሰላም ዱዓ የሚያደርጉት “አላሁመ ሰሊም ሰሊም” በማለት፡፡ ሰላም በነሱ ላይ ይሁን፡፡ ውድ የኢስላም አጋሮቼ! እንቁ የኢስላም ወገኖቼ! በኢስላም ከአሰላም ዳሩ ሰላምን እንፈልግ፡፡ በኢስላማዊ ሰላምታችን ደግሞ ሰላማዊ ህይወት ለመጎናፀፍ የሚያግዘንን “አጅር” እንሰብስብ፡፡ ሰላምታን እናብዛ፡፡ የሰላም ሀዋሪያው ሰላም ወዳዱ ዐብዱላህ ብኑ ሰላም ረዲየላሁ ዐንሁ ከሰላሙ አርበኛ ከውዱ ነቢያችን ሙሐመድ ብኑ ዐብዲላህ ዐለይሂ ሶላቱ ሰላም እንዲህ የሚል የሰላም መልእክት አስተላልፈዋል፡- يَا أيُّهَا النَّاسُ، أفْشُوا السَّلاَمَ، وَأطْعِمُوا الطَّعَامَ، وَصِلُوا الأرْحَامَ، وَصَلُّوا والنَّاسُ نِيَامٌ، تَدْخُلُوا الجَنَّةَ بِسَلاَم “እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አብዙ፣ የተራበን አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች ሲተኙ ስገዱ፣ ጀነትን በሰላም ትገባላችሁ፡፡” ሱብሓነላህ! እስኪ ይህንን ውብ አነጋገር እናጣጥመው! ቃላቱ፣ ስኬቱ፣ መልእክቱ፣ ሰአቱ፣ ሂደቱ፣ ውጤቱ፣ ሁሉ ሰላም!! የነኚህን ቃላት ዐረብኛ ወዝ ላጣጣመ ደግሞ ሌላ እርካታ፣ ሌላ ጣዕም፣ ሌላ ሰላም! ውድ ሙስሊሞች የሰላም ሀይሎች የዳሩ ሰላም ናፋቂዎች! ከአሰላም የተጣለብንን ሀላፊነት እንወጣ፣ ሰላማችንን እንዳናጣ፡፡ ስለ ሰላም ዱዓእ እናድርግ። “አሰላሙ ዐለይኩም” እንባባል፡፡ የተሻለውን ጥለን የወራረዱ አንለቃቅም፡፡ ሰላምታችን ኮተት የለውም አያሳፍርም፡፡ ሰላምታችን ቦምብ አይደለም አያስፈራም፡፡ ሰላም እንዴት ያስፈራል?! ያ ሰላሙ! ሰላማችንን መልስልን። ወሰላሙ ዐለይኩም ወረሕመቱላህ፡፡ (ኢብኑ ሙነወር፣ 2001 ላይ የተፃፈ) IbnuMunewor

*🌏موقع دار الحديث بالفيوش يقدم :* 🔊 خطبة بعنوان : *الظلمُ والقصاصُ فيهِ يومَ القيامة*  📚 والتي كانت بدار الحديث بالفيوش 18 شعبان 1447هـ الموافق 6 فبراير 2026م 💺 للشيخ الفاضل/ *أحـــمـــد الــبــركــانــــي* حفظه الله تعالى ⏱ مدة الخطبة 36:10 دقيقة 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 🔗 ولمتابعة جديد موقع دار الحديث بالفيوش تابعنا على: 🔹 الواتساب : https://chat.whatsapp.com/HdKpTz9X8ir8jbTuioCGGP 🔹 موقع دار الحديث بالفيوش: https://dar-fh.com 🔹التليجرام - Telegram https://t.me/daralfuyush 🔹اليوتيوب - YouTube https://youtube.com/@daralfuyush?si=A-c3dLgDdY9ZNeH0

ረመዷን ሊገባ ሲቀርብ ቤታችንን በቀለም በተለያዩ የመብራት አይነቶች ማስዋብ ከሸሪአ አንጻር እንዴት ይታያል??☝️

#ለትዝብት ባልና ሚስት መጣላታቸውን ስንሰማ ለማስታረቅ ብዙ ብዙ እንደክማለን፡፡ ቤተሰቦች እርስበርስ በሚጣሉበትም ጊዜ ለማስማማት ብዙ እንጥራለን፡፡ በጓደኛሞችም መካከል አለመግባባት መፈጠሩን ካወቅን ከውጭ ሆነን ከመታዘብ ይልቅ ጉዳዩ ውስጥ ገብተን ለማስተካከል እንታገላለን፡፡ በዲን ጉዳይ የሆኑ ሰዎች መጣላታቸውን ወይም መለያየታቸውን ስናውቅ ግን ከአንደኛው በኩል እንሆንና ሌላኛውን የበለጠ ለማባረር እንታገላለን፡፡ አብዘኞቻችን ለመውቀስ እንጅ ለማስታረቅ ፍፁም አናስብም፡፡ ማስታረቅ በሰዎች መካከል ያሉ ልዩነቶችን መቅረፍ  መልካም ስራ መሆኑን ከተረዳን  ለማስታረቅ መቻኮል የነበረብን በዲን ጉዳይ የተፈጠሩትን አለመግባባቶች ነበር፡፡

በአንድ ነገር ላይ ባንስማማም እንኳ ወንድማማቾች መሆን አንችልም? ኢማሙ ሻፊኢ

ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ "ሰለፎች እርሰበርሳቸው ቅርንጫፋዊ የዲን አጀንዳ ላይ ልዩነት ነበረባቸው፣ ይህ ከመሆኑ ጋር በመካከላቸው ውዴታ፣ጥንቁቅነት ከመኖሩ ጋር ቅሬታ በውስጣቸው አይዙም ነበር።" [አልፈታዋ ኩብራ: 6/92]

አላህ ሆይ! ለሴት እህቶቻችን ሂጃባቸውን ከዚህች አለም      ፈተናዎች መሸሸጊያ ከአኼራው የእሳት ቅጣትም መሰተሪያ አድርግላቸው!!

ሴት ልጅ ሃያዕ ውበቷ ነው!!! ሴት ልጅ ወንድሞቿን ላለመፈታተን የምታደርገው ጥረት ምስጉን ነው!!! ወንድ ልጅ በብዙ ነገርሽ ይፈተናል! ! በጥቂቱ 1, በተፈጥሮ አላህ በለገሰሽ ውበት ይፈተናል 2, አላህ በሰጠሽ ውበት ላይ መራርቀሽ (ጨማምረሽ) በምታመጪው ውበት ይፈተናል 3, በአለባበስሽ ይፈተናል 4, በድምፅሽ ይፈተናል እነዚህን የወጥመድ በሮች ከዘጋሽለት እድሜ ልኩን ቢተጋ ሊከፍልሽ የማይችለውን ውለታ ውለሽለታል!!! መልካምና ሷሊህ ሴት ማለት  ፍፁም ከስህተት የጠራች ናት ማለት አይደለም ነገር ግን እሷን ለየት የሚያደርጋት ደረቅና ግትር አይደለችም የዘነጋችውን ነገር ባስታወስካት ጊዜ ወይም ምክርን ስትመክራት ትቀበላለች ከስህተቷም ትመለሳለች ጌታዋንም ምህረትን ትጠይቃለች!