en
Feedback
Mohammed Seid - Miftah

Mohammed Seid - Miftah

Open in Telegram

​🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
2 481
Subscribers
+224 hours
+237 days
+35530 days
Posts Archive
photo content

ለኤአይ እዚህ መድረስ አባት ናቸው ሊባሉ የሚችሉ ሰዎች በተመጨረሻ "I Changed my mind" የሚሉን እያሾፋብን ነው ወይስ የጉዳት መጠኑ አሳስቧቸው? 🤔 አሁን ደግሞ ቢል ጌትስ ስለ Al ፈርቻለሁ እያሉን ነው! ቃል በቃል "The turbulent AI era is here. The choices we make now are critical."

የደረቀ ሃይቅ ምናምን የሚለውን ቪዲዮ እና ምስል እኔ አላየሁትም ያው ብዙ ጊዜ እንደምለው ሶሻል ሚዲያ ላይ ብኖርም የሶሻል ሚዲያ አልጎሪዝም የሚሰጠኝን እያየሁ የምውልና የማመሽ አይደለሁም! አሁን አንዳንድ ፎቶዎችን ተመለከትኩኝ ነገር ግን በጣም አዝኛለሁ ዲጀታል ክህሎት የምለው በምክንያት ነው። ቀን ከቤቴ እንግዶች መጥተው ስለ ጉዳዩ ሲያወሩኝ ግዴላችሁም እውነት አይሆንም አሁን እውነት እነ ውሽትን መለየት ግራ ያጋባል ነበር ያልኳቸው ። አንድ ምስል ሲለቀቅ ቢያንስ ለምን በቀላሉ የ #GoogleLense እንኳን አንጠቀምም? ሌሎች Investigation መንገዶች እንዳሉ ሳልዘነጋ! ከመቼውም ጊዜ በላይ አይናችንን እና ጆሮአችንን የምንከፍትበት ወቅት አሁን ነው። Deepfake እና Fake news መለየት መቻል አለብን!

📊 65 JOBS WITH THE LOWEST RISK OF AUTOMATION By Artificial Intelligence and Robots It is impossible to say that any job is 100% AI-proof, but the table below showcases careers with a lower risk of automation. While AI continues to reshape the workforce, these fields depend heavily on uniquely human skills and real-world decision-making that technology cannot easily replace. Median Annual Wage | Projected Growth (2024–2034) 1. Nurse Practitioners — $129,210 — 40% 2. Physician Assistants — $133,260 — 20% 3. Nursing Instructors and Teachers, Postsecondary — $79,040 — 17% 4. Mental Health Counselors — $59,190 — 17% 5. Occupational Therapists — $98,340 — 14% 6. Orthotists and Prosthetists — $79,110 — 13% 7. Marriage and Family Therapists — $63,780 — 13% 8. Nurse Midwives — $128,790 — 11% 9. Physical Therapists — $101,020 — 11% 10. Art Therapists — $65,910 — 11% 11. Music Therapists — $65,910 — 11% 12. Athletic Trainers — $60,250 — 11% 13. Mental Health and Substance Abuse Social Workers — $60,680 — 10% 14. Healthcare Social Workers — $68,090 — 9% 15. Dermatologists — $239,200 or more — 8% 16. Psychiatrists — $239,200 or more — 8% 17. Fitness and Wellness Coordinators — $61,340 — 8% 18. Choreographers — $55,310 — 6% 19. Coaches and Scouts — $45,920 — 6% 20. Manufactured Building and Mobile Home Installers — $41,880 — 6% 21. Neurologists — $239,200 or more — 5% 22. Bioengineers and Biomedical Engineers — $106,950 — 5% 23. Civil Engineers — $99,590 — 5% 24. Transportation Engineers — $99,590 — 5% 25. Advanced Practice Psychiatric Nurses — $93,600 — 5% 26. Clinical Nurse Specialists — $93,600 — 5% 27. Critical Care Nurses — $93,600 — 5% 28. Soil and Plant Scientists — $71,410 — 5% 29. Paramedics — $38,480 — 5% 30. Emergency Medical Technicians — $41,340 — 5% 31. Oral and Maxillofacial Surgeons — $239,200 or more — 4% 32. Orthopedic Surgeons, Except Pediatric — $239,200 or more — 4% 33. Prosthodontists — $239,200 or more — 4% 34. Surgeons, All Other — $239,200 or more — 4% 35. Chief Executives — $206,420 — 4% 36. Dentists, General — $172,290 — 4% 37. Physicists — $166,290 — 4% 38. Clinical Neuropsychologists — $117,580 — 4% 39. Neuropsychologists — $117,580 — 4% 40. Security Managers — $104,690 — 4% 41. Architects, Except Landscape and Naval — $96,690 — 4% 42. Psychology Teachers, Postsecondary — $80,330 — 4% 43. Hospitalists — $239,200 or more — 3% 44. Physical Medicine and Rehabilitation Physicians — $239,200 or more — 3% 45. Preventive Medicine Physicians — $239,200 or more — 3% 46. Sports Medicine Physicians — $239,200 or more — 3% 47. First-Line Supervisors of Police and Detectives — $105,980 — 3% 48. Anthropology and Archeology Teachers, Postsecondary — $95,770 — 3% 49. First-Line Supervisors of Firefighting and Prevention Workers — $92,430 — 3% 50. Emergency Management Directors — $86,130 — 3% 51. Urban and Regional Planners — $83,720 — 3% 52. Landscape Architects — $79,600 — 3% 53. Interior Designers — $63,490 — 3% 54. Recreational Therapists — $60,280 — 3% 55. Firefighters — $59,500 — 2% 56. Pediatric Surgeons — $239,200 or more — 2% 57. Architecture Teachers, Postsecondary — $101,460 — 2% 58. Art, Drama, and Music Teachers, Postsecondary — $80,190 — 2% 59. Social Work Teachers, Postsecondary — $76,210 — 2% 60. Set and Exhibit Designers — $66,280 — 2% 61. Directors, Religious Activities and Education — $54,840 — 2% 62. Obstetricians and Gynecologists — $239,200 or more — 1% 63. Adapted Physical Education Specialists — $67,430 — 1% 64. Education Administrators, Kindergarten through Secondary — $104,070 — -1% 65. Fish and Game Wardens — $68,180 — -1% Source: U.S. Bureau of Labor Statistics (2024–2034 projections) Publisher: U.S. Career Institute — Dream • Learn • Succeed #AI #FutureOfWork #Careers #Automation #DigitalTransformation

2️⃣ በስራ ገበያ ላይ የሚኖረው ከባድ ተጽዕኖ እንደ ህግ፣ ሶፍትዌር ምህንድስና፣ የደንበኞች አገልግሎት፣ ህክምና፣ ዳታ ትንተና እና ማኑፋክቸሪንግ ያሉት የሥራ ዘርፎች በአንድ አስርት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት በ AI ይጠቃሉ። ይህ ሁኔታ በተለይም ወደ ስራ ገበያው በሚገቡ ወጣቶች እና መካከለኛ ባለሙያዎች ላይ ትልቅ የስራ እጥረት ይፈጥራል። ስራ ማጣት በግለሰብ ገቢ ላይ ብቻ ሳይሆን በህብረተሰብ ጤና እና ማህበራዊ ትስስር ላይ ከባድ ቀውስ ሊያስከትል እንደሚችል ጠቁመዋል። 3️⃣ የደህንነት እና የወንጀል ስጋቶች AI ተገቢው ጥንቃቄ ካልተደረገለት ለከፍተኛ አደጋዎች ይጋለጣል። ወንጀለኞች የሳይበር ጥቃቶችን በራስ-ሰር ለመፈጸም፣ የሐሰት መረጃዎችን እና ዲፕፌኮችን (Deepfakes) ለማስፋፋት እንዲሁም ባዮ-ሽብርተኝነትን ጨምሮ አጥፊ ድርጊቶችን በቀላሉ ለመፈጸም ቴክኖሎጂውን ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ አመላክተዋል። 4️⃣ መፍትሄዎች እና ወሳኝ ውሳኔዎች ለዚህ ታሪካዊ ፈጣን ለውጥ መፍትሄ ሲጠቁሙ፣ ኩባንያዎች ሰዎችን በሮቦት እንዳይተኩ በ AI ቶክኖች እና ሮቦቶች ላይ ግብር እንዲጣል አሳስበዋል። እንዲሁም እንደ እንክብካቤ ያሉ ስራዎች ለሰዎች ብቻ እንዲጠበቁ፣ ዓለም አቀፍ ትኩረት ተሰጥቶበት አስቀድሞ መርሃ ግብር እንዲዘጋጅ እና ተስማሚ ፖሊሲዎች እንዲተገበሩ አጥብቀው ጠይቀዋል። AI ዓለምን ፍትሃዊ ከሚያደርጉት መሳሪያዎች አንዱ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ፣ በሀብታም እና በድሃ መካከል ያለውን ልዩነት እንዳያሰፋው አሁንኑ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል በማለት ሀሳባቸውን አጋርተዋል። ቴክኖሎጂው ዓለምን በፍጥነት እየቀየረ ነው። እናንተስ ስለዚህ አዲስ የ AI ዘመን እና ተያያዥ አደጋዎች ምን ታስባላችሁ? በጌትስ ሀሳብ ትስማማላችሁ?

ቢል ጌትስ እና የ AI ፈጣን ዘመን በትናንትናው እለት የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራቹ ቢል ጌትስ በድረ-ገጻቸው ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ሰፊ ጽሁፍ አጋርተዋል። ቢል ጌትስ በአርቴፊሻል
ቢል ጌትስ እና የ AI ፈጣን ዘመን በትናንትናው እለት የማይክሮሶፍት ኩባንያ መስራቹ ቢል ጌትስ በድረ-ገጻቸው ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተመለከተ ሰፊ ጽሁፍ አጋርተዋል። ቢል ጌትስ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዙሪያ ባወጡት አዲስ ሰፊ ጽሁፍ ላይ፣ ዓለም ወደር የሌለው እና አሻሚ ወደሆነ የቴክኖሎጂ ዘመን እየገባች መሆኑን አጥብቀው አስጠንቅቀዋል፡፡ ቴክኖሎጂው ከቀደምቶቹ አብዮቶች ፈጣን በሆነ መልኩ በማደግ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፣ በህብረተሰባችን ላይ የሚያስከትላቸውን በጎ እና መጥፎ ተጽዕኖዎችን በአንድ ጊዜ ይዞ እየመጣ መሆኑን አንስተዋል። ጌትስ በዋናነት ያነሷቸው ቁልፍ ጉዳዮች በአራት መልኩ በመክፈል ከዚህ በታች አስቀምጫለሁ 👇 1️⃣ የለውጡ ፍጥነት እና ልዩነት ከዚህ ቀደም የነበሩ የቴክኖሎጂ ለውጦች (ለምሳሌ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የተደረገው ሽግግር) ለመስፋፋት ትውልዶችን ወስደው ነበር። ነገር ግን AI ቋንቋን በቀላሉ የሚረዳ፣ የምንጠቀማቸው መሳሪያዎች የሚጠቀም እና የሰውን አእምሮአዊ አስተሳሰብ (Cognition) ጭምር መተካት የሚችል በመሆኑ ለውጡ እጅግ ፈጣን ነው። ጂኦፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፉክክሩ ከፍተኛ ስለሆነ ይህንን ፍጥነት ማቀዝቀዝ ከቶውንም የማይታሰብ መሆኑን ጌትስ አመልክተዋል።

ምን ታስባላችሁ? ለረጅም አመታት የተጠቀምንባቸው የ ፍለጋ ሞተሮች በAI ቻትቦቶች መተካት ይችሉ ይሆን? በአሁኑ ሰአት እንደ ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ የሚወሰደውስ የቱ ነው? Al ቻትቦት ወይስ በ Se
ምን ታስባላችሁ? ለረጅም አመታት የተጠቀምንባቸው የ ፍለጋ ሞተሮች በAI ቻትቦቶች መተካት ይችሉ ይሆን? በአሁኑ ሰአት እንደ ትክክለኛ የመረጃ ምንጭ የሚወሰደውስ የቱ ነው? Al ቻትቦት ወይስ በ Search engines የምናገኘው መረጃ?

አር ተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ዛሬ የተጀመረ ነው? ኮምፒውተሮች ከሰዎች ጋር ውይይት የማድረግ እና የማሰብ ሀሳብ ከብዙ አሥርተ ዓመታት በፊት የጀመረ ነው። እጅግ ራቅ ባሉ ዓመታት ማለትም በ1950 እንግሊዛዊው የሒሳብ እና ኮምፒውተር ሳይንስ ሊቅ አላን ቱሪንግ (Alan Turing) ማሽኖች ሰውን የሚመስል ዕውቀት ማሳየት ይችሉ እንደሆነ ለመገምገም "የቱሪንግ ፈተና" (Turing Test) በመባል የሚታወቀውን ሐሳብ አቅርቧል። ይህ የቱሪንግ ሀሳብ የ AI ቴክኖሎጂ ውልደት እንደመነሻ ተደርጎ ይወሰዳል። ​ከዛሬ 7 አስርት ዓመታት በላይ የተጀመረው ይህ ጉዞ ዛሬ የደረሰበትን ደረጃ ስናየው በእውነት አስገራሚ ነው! ​#ArtificialIntelligence #TechHistory #AlanTuring #MiftahTech #Ethiopia

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በጋራ ባቋቋሙት የAI UniPod የ10 ቀናት የግብርና Collaborative AI Studi
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም በጋራ ባቋቋሙት የAI UniPod የ10 ቀናት የግብርና Collaborative AI Studio Challenge ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ ጥሪ የፈጠራ ባለሙያዎች፣ ተመራማሪዎች እና ስታርታፖች የኢትዮጵያን ግብርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት መፍትሄዎች እንዲያሻሽሉ የሚጋብዝ ነው። ተሳታፊዎች የ10 ቀን በአካል የሚሰጥ ስልጠና፣ የሽልማት ዕድል፣ የስታርታፕ ማዕከል መቀላቀል እና ከባለሙያዎች ጋር የመተዋወቅ ዕድል ያገኛሉ። የማመልከቻ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ አንድ ሳምንት !

ቻትቦት (Chatbot) ምንድን ነው? በዛሬው ዲጂታል ዓለም ውስጥ ቻትቦት (Chatbot) ከእኛ ጋር መስተጋብር የሚፈጥር አንዱ ቁልፍ ቴክኖሎጂ ሆኗል። እስቲ ይህ ቴክኖሎጂ ምን እንደሆነ እና እንዴት እንደሚሰራ በዝርዝር እንመልከት። 1️⃣ ቻትቦት ማለት ምን ማለት ነው? ቻትቦት በጽሑፍ ወይም በድምፅ ከሰዎች ጋር የሚግባባ የሶፍትዌር መተግበሪያ ነው። ጥያቄዎችን ለመመለስ፣ መረጃ ለመስጠት እና ሰዎች ውስብስብ ምናሌዎችን (Menu) ሳይፈልጉ ወይም የድር ገጾችን ሳይቃኙ ሥራዎቻቸውን በፍጥነት እንዲያጠናቅቁ ይረዳል። እነዚህን ቴክኖሎጂዎች በሚከተሉት ቦታዎች ማግኘት እንችላለን፡ 🔹የድር-ገጾች (Websites) 🔹የመልዕክት መላላኪያ መተግበሪያዎች 🔹ኤስኤምኤስ (SMS) እና ዋትስአፕ (WhatsApp) እንዲሁም ቴሌግራም 🔹የደንበኛ አገልግሎት ፖርታሎች እና ሌሎች ዲጂታል ቻናሎች 2️⃣ የባህላዊ እና የAI ቻትቦቶች ልዩነት ሁሉም ቻትቦቶች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተደገፉ አይደሉም። በዋናነት በሁለት ይከፈላሉ፡ 🔹ባህላዊ ቻትቦቶች (Traditional Chatbots): አስቀድሞ የተዘጋጁ ጥብቅ ደንቦችን፣ የውሳኔ ዛፎችን (Decision tree) እና የተጻፉ የውይይት አካሄዶችን ብቻ ይከተላሉ። ለሚጠበቁ እና ቀጥተኛ ጥያቄዎች በጥሩ ሁኔታ ቢሠሩም፣ ከተቀመጡላቸው የፕሮግራም ምላሾች ውጭ ለሆኑ ጥያቄዎች ግን ይቸገራሉ። 🔹የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቻትቦቶች: እንደ የተፈጥሮ ቋንቋ ማቀነባበሪያ (NLP)፣ ጄኔሬቲቭ AI እና ትላልቅ የቋንቋ ሞዴሎች (LLMs) ያሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ይጠቀማሉ። የተጠቃሚውን እውነተኛ ፍላጎት በመረዳት፣ የበለጠ ተፈጥሯዊ ምላሾችን ይሰጣሉ፤ ከሰፊ የውይይት ዓይነቶች ጋርም በቀላሉ ይላመዳሉ። ለምሳሌ፦ ChatGPT, Gemini, Copilot የመሳሰሉት 3️⃣ የዘመናዊ AI ቻትቦቶች አቅም እና ጥቅሞች የዛሬዎቹ የAI ቻትቦቶች ቀላል መልስ ከመስጠት ባለፈ ብዙ ነገሮችን ማከናወን ይችላሉ። 🔷ከሲስተሞች ጋር መገናኘት፡ መረጃዎችን ፈልጎ ለማውጣት፣ ግብይቶችን ለማጠናቀቅ ወይም ተጠቃሚዎችን በሂደት ውስጥ ለመምራት ከንግድ መተግበሪያዎች፣ ዳታቤዞች እና የእውቀት ማዕከላት ጋር ይተሳሰራሉ። 🔷የሰዎችን ሥራ ማገዝ፡ ተራ እና ድግግሞሽ ያላቸውን ጥያቄዎች በራሳቸው በመፍታት፣ ተጨማሪ እርዳታ ሲያስፈልግ ደግሞ ውስብስብ ውይይቶችን ወደ ሰው ረዳቶች ያስተላልፋሉ። 🔷ሁለገብ አገልግሎት፡ ድርጅቶች በደንበኛ አገልግሎት፣ በሽያጭ፣ በቴክኒክ ድጋፍ፣ መረጃ ለማካፈል እና በቀጠሮ አያያዝ ሥራዎች ላይ በስፋት ይጠቀሟቸዋል። ትናንት ይህን ጥያቄ አቅርቤ በርካቶች ተሳትፋችኋል ምላሽም ሰጥታችሗል ከልብ እናመሰግናልን ! ክፍል ሁለት ይቀጥላል .....

ነገረ ሳይበር ደህንነት (#Phishing) ፊሺንግ (Phishing) ወይም የዲጂታል ማታለያ ወጥመድ፡ ምንነቱ፣ አደጋው እና እራሳችንን የምንጠብቅባቸው መንገዶች ፦ በአሁኑ ዲጂታል ዘመን የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ የሳይበር ወንጀለኞች ሰዎችን ለማጭበርበር የሚጠቀሙባቸው ስልቶችም እጅግ ረቂቅ እየሆኑ መጥተዋል። ከእነዚህ የሳይበር ጥቃቶች መካከል በስፋትና በተደጋጋሚ የሚከሰተው ፊሺንግ (Phishing) ወይም የማታለያ ወጥመድ ይባላል። ፊሺንግ ማለት ዲጂታል ሌቦች እንደ ባንክ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ታዋቂ የንግድ ተቋማት ወይም የቅርብ ጓደኛ በመምሰል የሐሰት መልዕክቶችን የሚያሰራጩበት መንገድ ነው። ዋና ዓላማቸውም የተጠቃሚዎችን የልብ ትኩረት በመሳብ ወይም በማስፈራራት የእጅ ስልክ ቁጥርን፣ የባንክ ሚስጥራዊ ቁጥርን (PIN)፣ የሶሻል ሚዲያ የይለፍ ቃላትን (Password) ወይም የገንዘብ ማስተላለፊያ ማረጋገጫ ኮዶችን (OTP) ሰርቆ መውሰድ ነው። ይህንን ወጥመድ ልክ አንድ ዓሣ አጥማጅ መንጠቆው ላይ ትል አድርጎ ዓሣ እንደሚያጠምደው ሁሉ፣ እነሱም የሐሰት አሸናፊነት ማስታወቂያዎችን ወይም አስፈሪ ማስጠንቀቂያዎችን እንደ ማጥመጃ በመጠቀም ሰዎችን ያጠምዳሉ። እነዚህ አጥማጆች መልዕክቶቻቸውን ለማድረስ የተለያዩ የዲጂታል መገናኛ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። በብዛት የሚታወቀውና ስልካችን ላይ የሚመጣው የኤስኤምኤስ (SMS) ማጭበርበር ሲሆን፣ "የባንክ አካውንትዎ ወይም የቴሌብር አካውንትዎ ተቆልፏል፤ አሁኑኑ በዚህ ሊንክ ገብተው ካላስተካከሉ አካውንትዎ ይዘጋል" የሚሉ መልዕክቶችን ይልካሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በዋትስአፕ ግሩፖች ላይ "ይህንን ሊንክ ተጭነው የነፃ ኢንተርኔት ወይም የነፃ የገንዘብ ስጦታ ያግኙ፣ ለሌሎች 50 ሰዎችም ያጋሩ" የሚሉ የሐሰት ማስታወቂያዎችን ያሰራጫሉ። ከዚህ በተጨማሪም በቀጥታ የስልክ ጥሪ በመደወል "ከባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም ቴክኒክ ክፍል ነው የምንደውለው፤ ሲስተም እየቀየርን ስለሆነ አሁን ስልክዎ ላይ የሚመጣውን 6 አሃዝ ኮድ ይንገሩን" በማለት ሰዎችን ግራ በማጋባት አካውንታቸውን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠሩታል። ይህንን የዲጂታል ሌቦች ወጥመድ በቀላሉ ለይተን የምናውቅባቸው ጥቂት የአደጋ ምልክቶች (Red Flags) አሉ። የመጀመሪያው ምልክት 'አስቸኳይነት' ነው፤ ወንጀለኞቹ ቆም ብለን እንድንጠረጥርና እንድንመራመር ጊዜ አይሰጡንም። "አሁኑኑ ካላደረጉት አካውንትዎ ይዘጋል" በማለት እንድንደናገጥ ያደርጉናል። ሁለተኛው ምልክት ደግሞ የተሳሳቱና የተለወጡ ሊንኮች (URLs) ናቸው። ለምሳሌ የባንኩን ትክክለኛ ድረ-ገጽ ስም በትንሹ በመለወጥ (ከመደበኛው cbe. com. et ፋንታ cbe-bonus. com ወይም cbe-lottery. net በማድረግ) የሐሰት ገጽ ያዘጋጃሉ። ሌላው ትልቁ ምልክት፣ ሳይወዳደሩ ወይም ሳይሳተፉ "እጅግ ከፍተኛ የገንዘብ ወይም የዕቃ ስጦታ አሸነፉ" የሚሉ ከመጠን ያለፉና እውነት የማይመስሉ ማባበያዎች ናቸው። እራሳችንን እና ንብረታችንን ከዚህ የፊሺንግ አደጋ ለመጠበቅ ሁልጊዜም ተግባራዊ ልናደርጋቸው የሚገቡ ወሳኝ መከላከያዎች አሉ። ከሁሉም በላይ በማንኛውም ሁኔታ ስልካችን ላይ የሚመጣን የባንክ ወይም የሶሻል ሚዲያ ማረጋገጫ ኮድ (OTP) ለባንክ ሠራተኛም ቢሆን በፍጹም አሳልፎ አለመስጠት ዋናው መከላከያ ነው። ባንኮችም ሆኑ ታዋቂ ድርጅቶች ደንበኞቻቸውን ሚስጥራዊ ቁጥር እንዲናገሩ በስልክ ወይም በቴክስት በፍጹም አይጠይቁም። በተጨማሪም የማናውቀው ሰው በቴሌግራም ወይም በኤስኤምኤስ የላከልንን ማንኛውንም ሊንክ (Link) ከመንካት መቆጠብ እና ጥርጣሬ ሲኖር ወደ ድርጅቶቹ ይፋዊ እና መደበኛ ስልክ ደውሎ ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ዲጂታል ደህንነት የሚጀምረው በንቃትና ባለመቸኮል በመሆኑ፣ ማንኛውንም መልዕክት ስናይ ቆም ብለን ማስተዋል ከሳይበር ሌቦች ይጠብቀናል።

Phishing ምንድን ነው? በድጋሜ የተለጠፈ 👇 https://t.me/miftahcode/191
Phishing ምንድን ነው? በድጋሜ የተለጠፈ 👇 https://t.me/miftahcode/191

ማንኛውም ሊንክ ሲላክላችሁ ጠቅ ከማድረግ በፊት please አረጋግጡ መዘዙ ብዙ ነው። እናንተም አካውንታችሁ ሿሿ ተደርጎ ለእኛም ያልሆነ አስቀያሚ ነገር እንዲላክ ፈቅዳችሁ! በተለይ ቴሌግራም አካውንት ኧረ ጎበዝ ተው ንቁ እንሁን!

በሰበር ወደ ሌላ ሀሳብ Attention economy ምን እንደሆነ Sedo Martial Art በደንብ የተረዳው ይመስለኛል። ሰዎች እንደ ሞኝ ይመለከቱታል እሱ ግን በእኔ አይታ ሞኝ አይደለም ! የሰዎችን ትኩረት በመሳብ ቢዝነስ እንዴት መስራት እንዳለበት በደንብ የተረዳ ልጅ ነው። እልወዳደርም እንቁላል ምናምን ያለበት ቪዲዮ እንኳን ከ 1M በላይ ታይቷል። ይህንን እንዲል የ #ETFC አዘጋጆችም ይፈልጋሉ ምክንያቱም በርካታ ሰዎች መድረስ የሚችሉት በሴዶ በኩል ነው ይህ በአዳራሽ.Com በርካቶች ጓጉተው 350 ብር ትኬት እንዲገዙ እድል ይፈጥርላቸዋል። ሰኢዶም ለሕዝቡ ብዬ ተመልሻለሁ በማለት አሁን ቪዲዮ ሰርቷል በዚያውም አዳራሽ. com ን አስተዋውቋል። እና ጉዳዩ የ Attention ጉዳይ ነው ስልህ ነዉ ፤ ዘመኑ የ Attention ዘመን አይደል! የግል አሳቤ ነው! 😍

​AI በብዙ መልኩ ከእኛ መተሳሰር ከጀመረ ሰንበትበት እያለ ነው። በዛሬው ጊዜ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምንጠቀምባቸው ቻትቦቶች፣ የምስል ማመንጫዎች እና ድምፅ አስተርጓሚዎች በሙሉ በብቃታቸው AN
​AI በብዙ መልኩ ከእኛ መተሳሰር ከጀመረ ሰንበትበት እያለ ነው። በዛሬው ጊዜ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምንጠቀምባቸው ቻትቦቶች፣ የምስል ማመንጫዎች እና ድምፅ አስተርጓሚዎች በሙሉ በብቃታቸው ANI (Artificial Narrow Intelligence) በሚባለው ምድብ ውስጥ ይመደባሉ። ትርጉሙም በአንድ የተወሰነ ሥራ ላይ ብቻ የሰለጠነ "ጠባብ አእምሮ" እንደ ማለት ነው። (ለምሳሌ፦ ጽሑፍ መጻፍ ወይም ቋንቋ መተርጎም ቢችሉም ፣ ከዚህ ውጪ በራሳቸው ማሰብ አይችሉም።) ​ነገር ግን አሁን ያለው ዓለም አቀፍ ፉክክር ማሽኖች ከዚህ ውስን አቅም ወጥተው፣ ልክ እንደ ሰው ሰፊ የማሰብ፣ የማመዛዘን፣ የመረዳት እና በራሳቸው የመማር አቅም ወደሚኖራቸው AGI (Artificial General Intelligence) ለመሸጋገር የዘርፉ ሳይንቲስቶችና ተቋማቶች ከፍተኛ ርብርብ ላይ ይገኛሉ። ቀለል ባለ መልኩ ስናያቸው :- • ANI = Narrow AI (በአንድ የተወሰነ ተግባር ብቻ የተወሰነ አእምሮ) • AGI = HI (Human Intelligence) (የሰው ልጅ አእምሮ ጋር እኩል የሆነ የማሰብ አቅም ያለው ማሽን) ማለት እንደሆነ የዘርፉ ተመራማሪዎች ያስቀምጣሉ። ጥያቄው የሚመጣው እዚህ ጋር ነው በሰው ልጆች የማሰብ አቅም የተወለዱት ማሽኖች ከሰው ልጅ የማሰብ አቅም ጋር እኩል (AGI) የሚሆኑበት ደረጃ ላይ ይደርሱ ይሆን? አሁን ካለው የቴክኖሎጂ ፍጥነት አንፃር ማሽኖች የሰው ልጅ አእምሮ ደረጃ ለመድረስ ገና አሥርተ ዓመታት ይቀረናል ወይስ በቅርብ ዓመታት ውስጥ እናየዋለን? ወይስ ይህ ፈጽሞ ሊመጣ የማይችል ቅዠት ነው ትላላችሁ? ሀሳባችሁን እና እይታችሁን ኮሜንት ላይ ሼር አድርጉን👇 በቀጣይ ከዚህም በላይ በሰው ልጅ ላይ ስጋት ስለደቀነው ASI የምላችሁ ይኖራል።

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እና የዳታ ሳይንስ ትንበያ፡ 50% ተማሪዎች የሚያልፉት መቼ ነው? ከዛሬው የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ በመነሳት ያሰናዳሁት መረጃ ነው። እንደ ትምህርት ሚኒስቴር የዛሬው መግለጫ ከሆነ በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች ውስጥ 70,544 (12.8%) ተማሪዎች ብቻ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህ ማለት 87.2% ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አላስመዘገቡም ማለት ነው። እስኪ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ያለውን የ5 ዓመታት የማለፍ ምጣኔ (ከ50% በላይ) ቁጥር ተመልከቱልኝ👇 በ2018 ዓ.ም.፦ 12.8% (70,544 ተማሪዎች አልፈዋል) በ2017 ዓ.ም.፦ 8.4% (48,929 ተማሪዎች አልፈዋል) በ2016 ዓ.ም.፦ 5.4% (36,400 ተማሪዎች አልፈዋል) በ2015 ዓ.ም.፦ 3.2% (27,267 ተማሪዎች አልፈዋል) በ2014 ዓ.ም.፦ 3.3% (29,909 ተማሪዎች አልፈዋል) በዚህ ሂደት ከቀጠለ 50% ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ውጤት ማምጣት የሚችሉበት ያ ተናፋቂ ጊዜ መቼ ነው? ስንት ዓመትስ ይፈጃል? እንደ ዳታ ሳይንስ (Data Science) ባለሙያነቴ ግምቴን በሁለት አማራጮች እንደሚከተለው ላስቀምጥ፦ 1️⃣ አማራጭ አንድ (የቅርብ ጊዜውን ዕድገት መሠረት ካደረግን) ባለፉት ሁለት ዓመታት ውጤቱ ከሌሎች ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ሻል ያለ ዕድገት አሳይቷል (ከ5.4% ወደ 8.4%፣ ከዚያም ዘንድሮ ወደ 12.8%)። ይህ ማለት በየዓመቱ በአማካይ የ3.7% ማሻሻያ እየታየ ነው ማለት ነው። በየዓመቱ በዚህ በ3.7% ፍጥነት ማደጉን ከቀጠለ፣ ቀሪውን 37.2% ልዩነት አሟልቶ 50% ለመድረስ 10 ዓመታት ያህል ይፈጃል ፤ ወይም በግምት በ2028 ዓ.ም. አካባቢ 50% ተማሪዎች ማለፍ ይችላሉ። 2️⃣ አማራጭ ሁለት (የ5 ዓመቱን አጠቃላይ የዕድገት መስመር ካሰላን) ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ያለውን አጠቃላይ የ5 ዓመታት የዕድገት መስመር (Linear Trend) ካሰላን፣ ዓመታዊው አማካይ ዕድገት 2.42% አካባቢ ነው። በዚህ መደበኛ የኤሊ ፍጥነት ከቀጠለ ግን 50% ለመድረስ 15 ዓመታት ያህል ይፈጃል ፤ ወይም በ2033 ዓ.ም. አካባቢ 50% መድረስ ይቻላል። እዚህ ጋር ያስቀመጥኩት ግምታዊ ሀሳብ ሁሌ ልክ ላይሆን ይችላል መስመሩም Linear ሆኖ ይቀጥላል ማለት አይደለም ሂደቱን ሊቀይሩ የሚቻሉ ስራዎች ከተሰሩ ምናልባትም Exponential እድገት ሊኖረውም ይችል ይሆናል። አሁን ያለውን ሂደት ከግምት በማስገባት የተቀመጠ ሀሳብ ነው። ታዲያ ቆም ብለን ማሰብ አይገባን ይሆን? በየዓመቱ የሚወድቀውና ከ87% በላይ የሆነው ይሄ ሁሉ ተማሪ እጣ ፈንታው ምንድን ነው? የሀገርስ ተስፋ የት ላይ ነው? መፍትሔውስ የትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠው የሪሜዲያል (የማሟያ) ፕሮግራም ብቻ ነው ወይስ ሥር ነቀል የፖሊሲ ለውጥ ያስፈልጋል? እናንተስ ምን ትላላችሁ?

1️⃣ PHLEARN — ምርጥ የፎቶሾፕ (Photoshop) ማስተካከያ እና የላቁ የዲዛይን ምስጢሮችን በነፃ ከነ ፕሮጀክት ፋይላቸው ለመማር የሚረዳ አስገራሚ ቻናል! 2️⃣ Envato Tuts+ — ከግራ
1️⃣ PHLEARN — ምርጥ የፎቶሾፕ (Photoshop) ማስተካከያ እና የላቁ የዲዛይን ምስጢሮችን በነፃ ከነ ፕሮጀክት ፋይላቸው ለመማር የሚረዳ አስገራሚ ቻናል! 2️⃣ Envato Tuts+ — ከግራፊክስ ዲዛይን መሠረታዊ እውቀት (Design Basics) ጀምሮ እስከ ፕሮፌሽናል ደረጃ የሚያስተምር ሰፊ ቻናል! 3️⃣ Bring Your Own Laptop — አዶቤ ኢሉስትሬተር (Illustrator) ፣ ፎቶ ሾፕ እና ሌሎችንም የዲዛይን ሶፍትዌሮች በተግባራዊ ፕሮጀክቶች በቀላሉ ለመለማመድ! ከእኛ የሚጠበቅ ➖➖➖➖➖ ትጋት ፣ ኢንተርኔት ፣ ኮምፒውተር

ዛሬ ቀን 4፡00 PM ከሀርቫርድ ዩኒቨርርሲቲ (CS50) በ YouTube የሚትላለፍ ኮርስ ነው።🔴 ፍላጎት ያላችሁ ሊንኩን በመጠቀም ተከታተሉት ⤵️ https://www.youtube.com/live/Ft
ዛሬ ቀን 4፡00 PM ከሀርቫርድ ዩኒቨርርሲቲ (CS50) በ YouTube የሚትላለፍ ኮርስ ነው።🔴 ፍላጎት ያላችሁ ሊንኩን በመጠቀም ተከታተሉት ⤵️ https://www.youtube.com/live/FtG7TWHf_ag

ውድ ተማሪዎች! AI የእናንተን ሥራ እንዲሠራላችሁ አታድርጉ፤ የእናንተን የማሰብ ብቃት እንዲያሳድግላችሁ እንጂ። በፈተና ወቅት አብሯችሁ የሚቀመጠው የራሳችሁ አእምሮ እንጂ AI እንዳልሆነ አትዘንጉ! 🧠 አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በትምህርታችሁ ላይ ትልቅ እገዛ ሊያደርግላችሁ የሚችል ድንቅ መሣሪያ ነው። ነገር ግን ሁሉንም ነገር AI እንዲሠራው ከፈቀድን፣ አእምሮአችን የማሰብ፣ የመፍጠርና የማስታወስ ብቃቱን እያጣ ይሄዳል። ይህ ህግ ለሁላችንም ይሰራል!✅

ተማሪ ሆይ! AI ለአንድ ትምህርት ዘርፍ ወይም ጥናት ጥሩ መነሻ ሀሳቦችን ሊሰጥህ ይችላል ፤ ነገር ግን መቼም ቢሆን እንደ ታማኝ እና ሊጠቀስ የሚችል (Citable) ምንጭ ሊወሰድ አይገባም። ሁልጊዜ መረጃዎችን ከታመኑ አካዳሚክ መጻሕፍት ማረጋገጥ ያስፈልጋል። AIን ሙሉ በሙሉ ስራህን እንድትሰራበት ሳይሆን፣ ትምህርትህን እና የአስተሳሰብ ችሎታህን ለማዳበር (ለማስተማሪያነት) ተጠቀምበት።