Mohammed Seid - Miftah
الذهاب إلى القناة على Telegram
🛠 Digital Skills | AI | Innovation 📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች። 👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡ https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
2 482
المشتركون
+224 ساعات
+677 أيام
+35330 أيام
أرشيف المشاركات
ማንኛውም ሊንክ ሲላክላችሁ ጠቅ ከማድረግ በፊት please አረጋግጡ መዘዙ ብዙ ነው። እናንተም አካውንታችሁ ሿሿ ተደርጎ ለእኛም ያልሆነ አስቀያሚ ነገር እንዲላክ ፈቅዳችሁ!
በተለይ ቴሌግራም አካውንት
ኧረ ጎበዝ ተው ንቁ እንሁን!
በሰበር ወደ ሌላ ሀሳብ
Attention economy ምን እንደሆነ Sedo Martial Art በደንብ የተረዳው ይመስለኛል።
ሰዎች እንደ ሞኝ ይመለከቱታል እሱ ግን በእኔ አይታ ሞኝ አይደለም ! የሰዎችን ትኩረት በመሳብ ቢዝነስ እንዴት መስራት እንዳለበት በደንብ የተረዳ ልጅ ነው።
እልወዳደርም እንቁላል ምናምን ያለበት ቪዲዮ እንኳን ከ 1M በላይ ታይቷል። ይህንን እንዲል የ #ETFC አዘጋጆችም ይፈልጋሉ ምክንያቱም በርካታ ሰዎች መድረስ የሚችሉት በሴዶ በኩል ነው ይህ በአዳራሽ.Com በርካቶች ጓጉተው 350 ብር ትኬት እንዲገዙ እድል ይፈጥርላቸዋል።
ሰኢዶም ለሕዝቡ ብዬ ተመልሻለሁ በማለት አሁን ቪዲዮ ሰርቷል በዚያውም አዳራሽ. com ን አስተዋውቋል።
እና ጉዳዩ የ Attention ጉዳይ ነው ስልህ ነዉ ፤ ዘመኑ የ Attention ዘመን አይደል!
የግል አሳቤ ነው! 😍
AI በብዙ መልኩ ከእኛ መተሳሰር ከጀመረ ሰንበትበት እያለ ነው። በዛሬው ጊዜ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የምንጠቀምባቸው ቻትቦቶች፣ የምስል ማመንጫዎች እና ድምፅ አስተርጓሚዎች በሙሉ በብቃታቸው ANI (Artificial Narrow Intelligence) በሚባለው ምድብ ውስጥ ይመደባሉ።
ትርጉሙም በአንድ የተወሰነ ሥራ ላይ ብቻ የሰለጠነ "ጠባብ አእምሮ" እንደ ማለት ነው። (ለምሳሌ፦ ጽሑፍ መጻፍ ወይም ቋንቋ መተርጎም ቢችሉም ፣ ከዚህ ውጪ በራሳቸው ማሰብ አይችሉም።)
ነገር ግን አሁን ያለው ዓለም አቀፍ ፉክክር ማሽኖች ከዚህ ውስን አቅም ወጥተው፣ ልክ እንደ ሰው ሰፊ የማሰብ፣ የማመዛዘን፣ የመረዳት እና በራሳቸው የመማር አቅም ወደሚኖራቸው AGI (Artificial General Intelligence) ለመሸጋገር የዘርፉ ሳይንቲስቶችና ተቋማቶች ከፍተኛ ርብርብ ላይ ይገኛሉ።
ቀለል ባለ መልኩ ስናያቸው :-
• ANI = Narrow AI (በአንድ የተወሰነ ተግባር ብቻ የተወሰነ አእምሮ)
• AGI = HI (Human Intelligence) (የሰው ልጅ አእምሮ ጋር እኩል የሆነ የማሰብ አቅም ያለው ማሽን) ማለት እንደሆነ የዘርፉ ተመራማሪዎች ያስቀምጣሉ።
ጥያቄው የሚመጣው እዚህ ጋር ነው በሰው ልጆች የማሰብ አቅም የተወለዱት ማሽኖች ከሰው ልጅ የማሰብ አቅም ጋር እኩል (AGI) የሚሆኑበት ደረጃ ላይ ይደርሱ ይሆን?
አሁን ካለው የቴክኖሎጂ ፍጥነት አንፃር ማሽኖች የሰው ልጅ አእምሮ ደረጃ ለመድረስ ገና አሥርተ ዓመታት ይቀረናል ወይስ በቅርብ ዓመታት ውስጥ እናየዋለን? ወይስ ይህ ፈጽሞ ሊመጣ የማይችል ቅዠት ነው ትላላችሁ?
ሀሳባችሁን እና እይታችሁን ኮሜንት ላይ ሼር አድርጉን👇
በቀጣይ ከዚህም በላይ በሰው ልጅ ላይ ስጋት ስለደቀነው ASI የምላችሁ ይኖራል።
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት እና የዳታ ሳይንስ ትንበያ፡ 50% ተማሪዎች የሚያልፉት መቼ ነው?
ከዛሬው የትምህርት ሚኒስቴር መግለጫ በመነሳት ያሰናዳሁት መረጃ ነው።
እንደ ትምህርት ሚኒስቴር የዛሬው መግለጫ ከሆነ በዚህ ዓመት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች ውስጥ 70,544 (12.8%) ተማሪዎች ብቻ 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ይህ ማለት 87.2% ተማሪዎች ማለፊያ ውጤት አላስመዘገቡም ማለት ነው።
እስኪ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ያለውን የ5 ዓመታት የማለፍ ምጣኔ (ከ50% በላይ) ቁጥር ተመልከቱልኝ👇
በ2018 ዓ.ም.፦ 12.8% (70,544 ተማሪዎች አልፈዋል)
በ2017 ዓ.ም.፦ 8.4% (48,929 ተማሪዎች አልፈዋል)
በ2016 ዓ.ም.፦ 5.4% (36,400 ተማሪዎች አልፈዋል)
በ2015 ዓ.ም.፦ 3.2% (27,267 ተማሪዎች አልፈዋል)
በ2014 ዓ.ም.፦ 3.3% (29,909 ተማሪዎች አልፈዋል)
በዚህ ሂደት ከቀጠለ 50% ተማሪዎች 50% እና ከዚያ በላይ የማለፊያ ውጤት ማምጣት የሚችሉበት ያ ተናፋቂ ጊዜ መቼ ነው? ስንት ዓመትስ ይፈጃል?
እንደ ዳታ ሳይንስ (Data Science) ባለሙያነቴ ግምቴን በሁለት አማራጮች እንደሚከተለው ላስቀምጥ፦
1️⃣ አማራጭ አንድ (የቅርብ ጊዜውን ዕድገት መሠረት ካደረግን) ባለፉት ሁለት ዓመታት ውጤቱ ከሌሎች ዓመታት ጋር ሲነፃፀር ሻል ያለ ዕድገት አሳይቷል (ከ5.4% ወደ 8.4%፣ ከዚያም ዘንድሮ ወደ 12.8%)። ይህ ማለት በየዓመቱ በአማካይ የ3.7% ማሻሻያ እየታየ ነው ማለት ነው። በየዓመቱ በዚህ በ3.7% ፍጥነት ማደጉን ከቀጠለ፣ ቀሪውን 37.2% ልዩነት አሟልቶ 50% ለመድረስ 10 ዓመታት ያህል ይፈጃል ፤ ወይም በግምት በ2028 ዓ.ም. አካባቢ 50% ተማሪዎች ማለፍ ይችላሉ።
2️⃣ አማራጭ ሁለት (የ5 ዓመቱን አጠቃላይ የዕድገት መስመር ካሰላን) ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ያለውን አጠቃላይ የ5 ዓመታት የዕድገት መስመር (Linear Trend) ካሰላን፣ ዓመታዊው አማካይ ዕድገት 2.42% አካባቢ ነው። በዚህ መደበኛ የኤሊ ፍጥነት ከቀጠለ ግን 50% ለመድረስ 15 ዓመታት ያህል ይፈጃል ፤ ወይም በ2033 ዓ.ም. አካባቢ 50% መድረስ ይቻላል።
እዚህ ጋር ያስቀመጥኩት ግምታዊ ሀሳብ ሁሌ ልክ ላይሆን ይችላል መስመሩም Linear ሆኖ ይቀጥላል ማለት አይደለም ሂደቱን ሊቀይሩ የሚቻሉ ስራዎች ከተሰሩ ምናልባትም Exponential እድገት ሊኖረውም ይችል ይሆናል። አሁን ያለውን ሂደት ከግምት በማስገባት የተቀመጠ ሀሳብ ነው።
ታዲያ ቆም ብለን ማሰብ አይገባን ይሆን? በየዓመቱ የሚወድቀውና ከ87% በላይ የሆነው ይሄ ሁሉ ተማሪ እጣ ፈንታው ምንድን ነው? የሀገርስ ተስፋ የት ላይ ነው? መፍትሔውስ የትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠው የሪሜዲያል (የማሟያ) ፕሮግራም ብቻ ነው ወይስ ሥር ነቀል የፖሊሲ ለውጥ ያስፈልጋል?
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
1️⃣ PHLEARN — ምርጥ የፎቶሾፕ (Photoshop) ማስተካከያ እና የላቁ የዲዛይን ምስጢሮችን በነፃ ከነ ፕሮጀክት ፋይላቸው ለመማር የሚረዳ አስገራሚ ቻናል!
2️⃣ Envato Tuts+ — ከግራፊክስ ዲዛይን መሠረታዊ እውቀት (Design Basics) ጀምሮ እስከ ፕሮፌሽናል ደረጃ የሚያስተምር ሰፊ ቻናል!
3️⃣ Bring Your Own Laptop — አዶቤ ኢሉስትሬተር (Illustrator) ፣ ፎቶ ሾፕ እና ሌሎችንም የዲዛይን ሶፍትዌሮች በተግባራዊ ፕሮጀክቶች በቀላሉ ለመለማመድ!
ከእኛ የሚጠበቅ
➖➖➖➖➖
ትጋት ፣ ኢንተርኔት ፣ ኮምፒውተር
ዛሬ ቀን 4፡00 PM ከሀርቫርድ ዩኒቨርርሲቲ (CS50) በ YouTube የሚትላለፍ ኮርስ ነው።🔴
ፍላጎት ያላችሁ ሊንኩን በመጠቀም ተከታተሉት ⤵️
https://www.youtube.com/live/FtG7TWHf_ag
ውድ ተማሪዎች!
AI የእናንተን ሥራ እንዲሠራላችሁ አታድርጉ፤ የእናንተን የማሰብ ብቃት እንዲያሳድግላችሁ እንጂ። በፈተና ወቅት አብሯችሁ የሚቀመጠው የራሳችሁ አእምሮ እንጂ AI እንዳልሆነ አትዘንጉ!
🧠 አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በትምህርታችሁ ላይ ትልቅ እገዛ ሊያደርግላችሁ የሚችል ድንቅ መሣሪያ ነው። ነገር ግን ሁሉንም ነገር AI እንዲሠራው ከፈቀድን፣ አእምሮአችን የማሰብ፣ የመፍጠርና የማስታወስ ብቃቱን እያጣ ይሄዳል።
ይህ ህግ ለሁላችንም ይሰራል!✅
ተማሪ ሆይ!
AI ለአንድ ትምህርት ዘርፍ ወይም ጥናት ጥሩ መነሻ ሀሳቦችን ሊሰጥህ ይችላል ፤ ነገር ግን መቼም ቢሆን እንደ ታማኝ እና ሊጠቀስ የሚችል (Citable) ምንጭ ሊወሰድ አይገባም። ሁልጊዜ መረጃዎችን ከታመኑ አካዳሚክ መጻሕፍት ማረጋገጥ ያስፈልጋል።
AIን ሙሉ በሙሉ ስራህን እንድትሰራበት ሳይሆን፣ ትምህርትህን እና የአስተሳሰብ ችሎታህን ለማዳበር (ለማስተማሪያነት) ተጠቀምበት።
ChatGPT እ.ኤ.አ. ኖቬምበር 30 ቀን 2022 ሲለቀቅ መጀመሪያ የተጠቀመው GPT-3.5 የተባለውን የቋንቋ ሞዴል የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ በ5 ቀናት ውስጥ 1 ሚሊዮን እንዲሁም በሁለት ወራት ውስጥ 100 ሚሊዮን ወርሃዊ ተጠቃሚዎችን በማፍራት በታሪክ ፈጣኑ መተግበሪያ መሆን ችሏል። በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂው ዕድገት እጅግ የላቀ ደረጃ ላይ ደርሶ መድረኩ ከ1 ቢሊዮን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ በሰፊው የሚዘወተረው የChatGPT ኤአይ ሞዴልም ወደ GPT-5 የላቁ ስሪቶች ተሻግሯል።
ይህ የChatGPT አስገራሚ ዕድገት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በሰው ልጅ ታሪክ ከታዩት ማናቸውም የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በላይ በፍጥነት እያደገ እና በቀላሉ በሰዎች እጅ እየደረሰ ለመሆኑ ዋነኛ ማሳያ ነው። የዓለም ባንክ እና የቴክኖሎጂ ተንታኞች እንደሚያመለክቱት፣ የድሮዎቹ ታላላቅ ፈጠራዎች (እንደ የእንፋሎት ሞተር፣ ኤሌክትሪክ እና ኢንተርኔት) በዓለም ዙሪያ ተስፋፍተው መካከለኛና ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ህዝብ እጅ ለመድረስ ከ20 እስከ 80 ዓመታት ፈጅቶባቸዋል።
🤔ይገርማል!
ይህ የ AI ታላቅ እድገት እድል ወይስ ስጋት ምን ትላላችሁ ሀሳባችሁን ሼር አድርጉን?
ፈጣን ለውጥ ባለበት በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን፣ በየትኛውም የሙያ መስክ (ጤና፣ አስተዳደር፣ ትምህርት ፣ ግብርና ወይም ንግድ) ዲጂታል አስተሳሰብ (Digital Thinking) መሠረታዊ ለውጥ የሚያመጣ ቁልፍ ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ ዲጂታል አስተሳሰብ ምን ማለት ነው?
ዲጂታል አስተሳሰብ ማለት በቴክኖሎጂ ዘመን የሚመጡ ፈታኝ ችግሮችን ለመፍታት፣ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ለመስራት እና ከሁኔታዎች ጋር በፍጥነት ለመላመድ ቴክኖሎጂን፣ መረጃዎችን (Data) እና ሰብአዊ ፍላጎቶችን አቀናጅቶ የመጠቀም የላቀ የአእምሮ ብቃት ወይም እይታ ነው።
የዲጂታል አስተሳሰብ ዋና መገለጫዎች፡
✅ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ (Data-Driven Decisions)፦ በግምት ወይም በባህላዊ መንገድ ብቻ ከመወሰን ይልቅ፣ ትክክለኛ መረጃዎችን ሰብስቦ በመተንተን ይበልጥ አስተማማኝ ውሳኔ ላይ መድረስ።
✅ አውቶሜሽን እና ቅልጥፍና (Automation & Efficiency)፦ በእጅ የሚሠሩ እና ጊዜ የሚወስዱ ሂደቶችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ (ለምሳሌ፦ የተለያዩ ሲስተሞችን በመጠቀም) ስራዎችን ፈጣን፣ ቀላል እና ከስህተት የጸዱ ማድረግ።
✅ ችግር ፈቺ አእምሮ (Problem-Solving Mindset)፦ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና አሰራሮችን እንደ ፈተና ሳይሆን፣ ያሉትን ችግሮች በቀላሉ ለመፍታት እንደ መልካም አጋጣሚና መሣሪያ ማየት።
✅ ቀጣይነት ያለው ትምህርት (Continuous Learning)፦ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚለወጡ አዳዲስ የዲጂታል ዕውቀቶችንና መሳሪያዎችን በፍጥነት ለመለማመድ እና ስራ ላይ ለማዋል ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን።
ስለዚህ በተሰማራንበት ዘርፍ በዲጀታል ማሰብ መጀመር የሚያመጣልን ዋጋ ትልቅ ነው ፤ ያውም ነገሮች በፍጥነት ወደ ዲጀታል እየሄዱ ባለበት በዚህ ጊዜ!
ሀሳባችሁን አጋሩን?⤵️
የኢኮደርስ ኮርስ ምዝገባ ይሰራል ምንም ችግር የለበትም ፤ በዚህ ቪዲዮ ማየት ትችላላችሁ 👇
https://www.facebook.com/share/v/18Lx9p2viw/
አንዳንድ ጊዜ ሶሻል ሚዲያ ላይ ስንገባ የቲክቶከሮችን፣ የዩቲዩበሮችን ወይም የፌስቡክ ኢንፍሉኤንሰሮችን የተቀባ፣ አሳሳች እና የቅንጦት ህይወት ስንመለከት ፤ ውስጣችን "ትምህርት የት አባቱ! ለካ አቋራጭ መንገድ አለ" ብለን ልናስብ እንችላለን።
የሶሻል ሚዲያ ብልጭልጭ ለቀረፃ የሚቀርብ ነው። እውነተኛው የህይወት ቅንጦት ግን በዕውቀት መታጠቅ፣ በዲሲፕሊን መመራት እና በትምህርት መገንባት ነው።
ነገ የዕድገትህን መሰረት የሚጥለው ዛሬ የምትቀስመው ትምህርት እንጂ የማለፊያ ስክሪን ላይ የሚታየው ትርኢት አይደለም። አንብብ፣ ተማር፣ ብቁ ሁን!
እኔ የሚሰማኝ እንደዚህ ነው እንግዲህ! ከተሳሳትኩ አውፍ በሉኝ
ወሳኝ እና ወቅታዊ ጥያቄ 🤔
በዩቲዩብም ሆነ በፌስቡክ ሬልስ ላይ የምናያቸው ቪዲዮዎች እውነተኛ መሆናቸውን ወይም በ AI (በዲፕፌክ - Deepfake) የተሰሩ መሆናቸውን መለየት ትችላላችሁ?
አሁን ላይ ቴክኖሎጂው እጅግ እየተራቀቀ ስለመጣ እውነትን ከሐሰት መለየት ከባድ ፈተና እየሆነ ነው።
እስኪ እናንተ በምን መንገድ ነው ዲፕፌክ ቪዲዮዎችን የምትለዩት? ወይስ አታስተውሉም? ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን!
አንዳንዱ AIን አልጠቀምም ተጠቅሜ አላውቅም ፣ ጠላት ነን ወዘተ እያለ ይፖስታል!
እንዴት?
በዚህ ወቅት አለመጠቀም ይቻላል? ምናልባት የምለቀው ይዘት ከ AI ሀሳብ ነፃ ነው ሊሆን ይችላል።
አውቀንም ይሁን ሳናውቅ Alን በእለት ተእለት የዲጀታል እንቅስቃሴ እንጠቀማለን። የዚህ አይነት ሀሳብ የሚያነሱ ምናልባት Al ምንድን ነው የሚለውን ጠለቅ ብለው እንዲረዱ እንመክራለን።
እናንተስ ምን ትላላችሁ?
ከANI እስከ ASI — የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ጉዞ ወዴት ነው?
የዘርፉ ባለሙያዎች የ AIን የዕድገት ደረጃ በሦስት ይከፍሉታል፦
1️⃣ ANI (Artificial Narrow Intelligence)
2️⃣ AGI (Artificial General Intelligence)
3️⃣ ASI (Artificial Superintelligence)
አሁን በዓለም ላይ በብዛት እያየናቸው ያሉ የ AI ቴክኖሎጂዎች (ChatGPT, Gemini, Copilot, DeepSeek, Kimi K3) በየትኛው ደረጃ ላይ የሚመደቡ ይመስላችኋል?
የሦስቱስ መሠረታዊ ልዩነት ምንድን ነው?
በጉዳዩ ላይ ያላችሁን እውቀትና አስተያየት በኮሜንት አጋሩን⬇️
እውቀት ስነ-ምግባር እና ተግባር ጋር ሲሆን እንዴት ደስ ይል ነበር!?
ለመሆኑ... ይህንን ድንቅ ሦስትዮሽ በጋራ መመልከት ለምን እንዲህ ናፈቀን?
በዚህ ወቅት መሠረታዊ ዲጂታል ክህሎት (Basic Digital Skills) ማለት እንደ ማንበብ እና መፃፍ ሁሉ የግድ ሊኖረን የሚገባ መሠረታዊ እውቀት ሆኗል።
ነገሮች በፍጥነት ወደ ዲጂታል እያመሩ አይደል? 🚀
በዚህ ሰፊ የዲጂታል እንቅስቃሴ ውስጥ ስንገባ ደግሞ Safety and Security ሁልጊዜም ከምንም በላይ ቅድሚያ ልንሰጠው የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ ነው። መሣሪያዎችን መጠቀም ብቻ ሳይሆን፣ መረጃዎቻችንን እና ግላዊ ደህንነታችንን መጠበቅ መቻል የዚሁ ጉዞ ማዕከል ነው።
እስኪ እናንተም በዚህ ሀሳብ ላይ ያላችሁን ተሞክሮ ሼር አድርጉን! 👇
ዩቲዩብ የ Monitization ሕጉን አሻሻለ!
የዩቲዩብ አጋር ፕሮግራም (YouTube Partner Program) ማሻሻያዎች ከጥር 1 / 2027 ጀምሮ በይፋ ሥራ ላይ ይውላል።
በአዲሱ ህግ ሞኒታይዝ ለመሆን ወይም ገቢ ለማግኘት
✅ 1,000 ተመዝጋቢዎች (Subscribers)
✅ ከ8,000 የህዝብ እይታ ሰዓታት (Public watch hours) ባለፉት 12 ወራት ወይም 20 ሚሊዮን የሾርትስ እይታዎች (Shorts views) ባለፉት 90 ቀናት። ማሟላት ግዴታ ሲሆን ይህም ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት ከነበረው በእጥፍ የጨመረ ነው። በእርግጥ በአንድ ቪዲዮ ሁሉ ሊመጣ ይችላል ሀሪፍ ይዘት ከስራን ማለት ነው ፤ ለእኛ ሀገር ከባድ ቢሆንም !
ለማንኛውም እስካሁን መስፈርቱን ካላሟላችሁ ፣ አሁን የቀረውን ጊዜ በመጠቀም ወደ ግባችሁ ድረሱ። 6 ወር ጊዜ አላችሁ!
🚀 በዛሬው ዘመን ቴክኖሎጂን በመጠቀም፡
📚 Online መማር - ከየትኛውም የዓለም ማዕዘን ሆነው አዳዲስ ክህሎቶችን ማዳበር፣
💻 Online ስራ መፍጠር - የገቢ ምንጭ መፍጠር እና ዲጂታል ንግድ መጀመር፣
🌐 Online ግንኙነት መፍጠር - ሀገር አቀፍ እንዲሁም ዓለም አቀፍ አጋሮችን እና ጓደኞችን ማፍራት ይቻላል።
አልጋ በአልጋ ነው እያልኩ አይደለም ቻሌንጅ አለው ነገር ግን የሚገጥሙን ችግሮች መቋቋ እና ማለፍ ያስፈልጋል!
እናንተ የትኛው ላይ ትኩረት አድርጋችሁ እየሰራችሁ ነው?
💬 ሃሳባችሁን ኮሜንት ላይ አካፍሉን!⬇️
