en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Sinksar tube(ስንክሳር)

Sinksar tube(ስንክሳር)

Open in Telegram

እኔ ቅዱስ ነኛና ቅዱሳን ሁኑ 1ጴጥ 1:15

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
3 015
Subscribers
+3324 hours
+1177 days
+28330 days
Posts Archive
5875080773906403103_120.jpg0.35 KB

††† እንኳን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የተድላና የደስታ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† በዚሕች ቀን ለ40 ዓመታት በመላው ዓለም የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናት የተከፈቱበት ቀን ይታሠባል:: ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቡና ታስባ : በዓለመ መላእክት ከታየች በኋላ:- ¤አበው ተስፋ ሲያደርጓት ¤ነቢያት ትንቢት ሲናገሩላት ¤ሱባኤ ሲቆጥሩላት ¤ምሳሌም ሲመስሉላት ኑረዋል:: ††† ዘመኑ በደረሰ ጊዜ በአምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ :- ¤በመጸነሱ ተጸንሳ ¤በመወለዱ ተወልዳ ¤በጥበብና በሞገስ አብራው አድጋ ¤በጥምቀቱ ተጠምቃ ¤በትምሕርቱ ጸንታ ¤በደሙ ተቀድሳ ¤በትንሣኤው ከብራ ¤በዕርገቱ ሰማያዊነቷን አጽንታ ¤በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ወርዶላት በይፋ ለልጆቿ ተሰጥታለች:: ††† አባቶቻችን ቅዱሳን ሐዋርያት በመላው ዓለም ዞረው በብዙ ድካም የሠሯት ቤተ ክርስቲያን ለ200 ዓመታት እጅግ የበዙ መከራዋችን አሳልፋለች:: በ265 ዓ/ም የመጣባት መከራ ግን በዓለም ታሪክ እስካሁን አልታየም:: የወቅቱ ኃያላን ነገሥታት (ዲዮቅልጢያኖስና መክስምያኖስ) ዓለምን ለ2 ተካፍለው ክርስቲያኖችን የማጥፋት ዘመቻ ጀመሩ:: በመጀመሪያም በዓለም ያሉ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት እንዲቃጠሉ ካልሆነም እንዲዘጉ : በፈንታቸው ደግሞ አዽሎን: አርዳሚስ የተባሉ ጣዖቶች እንዲተኩ ትዕዛዝ ተሰጠ:: ለ40 ዓመታት ክርስቲያን ስለሆኑ ብቻ ሚሊየኖች ተገደሉ: ታሰሩ: ተሰቃዩ: ተሰደዱ:: መጻሕፍት ተቃጠሉ: አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ወደሙ:: በአባቶቻችንና እናቶቻችን ላይ ልንናገረው ከምንችለው በላይ ጭንቅና መከራ ደረሰ:: ነገር ግን ቅዱሳኑ ያን ሁሉ ችለው ጸኑ:: 47 ሚሊየን የሚያሕሉትን ደግሞ ሰይፍና እሳት በላቸው:: በዛ ዘመን አንድ ቤተ ክርስቲያን ለማግኘት ከአሕጉር አሕጉር መሔድን ይጠይቅ ነበር:: ከዚሕ ሁሉ በኋላ ግን እግዚአብሔር "ግፍ ይበቃል" ሲል በ305 ዓ/ም ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ነገሠ:: መክስምያኖስን በጦርነት ሲማርከው አውሬው ዲዮቅልጢያኖስ ግን አብዶ ሞተ:: ይህ ከተደረገ ከዓመታት በኋላ (በ313 ዓ/ም) ታላቁ ቆስጠንጢኖስ የዓለም መሪዎችን በዚሕች ቀን ጠርቶ አዋጁን በአዋጅ ሻረው:: "ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት ይከፈቱ:: በፈንታው ደግሞ ሁሉም ጣዖት ቤቶች ይዘጉ" አለ:: በሺሕ የሚቆጠሩ አብያተ ክርስቲያናትን በወርቅ አስለበጠ:: በዚሕ ምክንያት ይህች ቀን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን "ዕለተ ትፍሥሕት (የደስታ ቀን)" ተብላ ትከበራለች:: ††† ቸሩ አምላክ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ከመከራ ይሠውርልን:: ከበረከቷም ያድለን:: ትውልዱ ደካሞች ነንና ከማንችለው ፈተናም ይጠብቀን:: ††† ሰኔ 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅድስት ቤተ ክርስቲያን 2.ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ 3.ቅድስት ሶፍያ ሰማዕት (ከታላላቆቹ ሶፍያዎች አንዷ ናት) 4.ቅዱሳት ሰማዕታት ደባሞንና ብስጣሞን (የቅድስት ሶፍያ ልጆች) 5.ቅዱስ አውሎጊስ ሰማዕት 6.ቅዱስ ዋርስኖፋ ሰማዕት ††† ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 5.ቅድስት ዕሌኒ ንግስት 6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል ††† "ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ:: ኢየሩሳሌም ሆይ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ:: ኢየሩሳሌምስ እርስ በርሷ እንደ ተገለጠች ከተማ ተሠርታለች . . . ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም በውስጥሽ ሰላም ይሁን አልሁ:: ስለ አምላካችን ስለ እግዚአብሔር ቤት ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ::" ††† (መዝ. 121:1-9) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

††† እንኳን ለታላቁ ነቢይ ቅዱስ ሳሙኤል ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። ††† ††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ††† ††† ነቢዩ ቅዱስ ሳሙኤል ††† ††† እሥራኤል ከግብጽ ባርነት ወጥተው ከነዓንን ከወረሱበት ዘመን ጀምረው መሳፍንትና ካህናት ያስተዳድሯቸው ነበር:: በወቅቱ ታዲያ ክህነት ከምስፍና ተስማምቶለት ኤሊ የተባለ ሊቀ ካህናትና ልጆቹ (አፍኒና ፊንሐስ) ያስተዳድሩ ጀመር:: በዘመኑ ደግሞ ማኅጸኗ ተዘግቶባት ዘወትር የምታለቅስ ሐና የሚሏት ደግ ሴት ነበረች:: እግዚአብሔር የእርሷን ጸሎትና የሊቀ ካህናቱን ምርቃት ሰምቷልና ቅዱስ ልጅን ሰጣት:: "ሳሙኤል" አለችው:: "ልመናየን አምላክ ሰማኝ" ማለት ነውና:: ሐና ስዕለቷን ትፈጽም ዘንድ ሳሙኤልን በሦስት ዓመቱ ለቤተ እግዚአብሔር ሰጠችው:: በዚያም ስብሐተ እግዚአብሔርን እየሰማ : ማዕጠንቱን እያሸተተ : ከደብተራ ኦሪቱ ሳይለይ በሞገስ አደገ:: የኤሊ ልጆች (አፍኒና ፊንሐስ) ግን በበደል ላይ በደልን አበዙ:: ወቅቱ የአሁኑን ዘመን ይመስል ነበር:: ሁሉም ሰው ክፋተኛ የሆነበት በመሆኑ : እግዚአብሔር ርቆ ስለ ነበር ትንቢትና ራዕይ ብርቅ ነበር:: አምላክ ተቆጥቷልና ሳሙኤልን በሌሊት ሦስት ጊዜ ጠራው:: ነቢዩም ታጥቆ የፈጣሪውን ቃል ሰማ:: በዚሕም የተነሳ ታቦተ ጽዮን ለመጀመሪያ ጊዜ በአሕዛብ ተማረከች:: ከሰላሳ አራት ሺ በላይ ሕዝብ በኢሎፍላውያን አለቀ:: አፍኒና ፊንሐስም ተገደሉ:: ኤሊም ወድቆ ሞተ:: ከዚህች ቀን በኋላ ቅዱስ ሳሙኤል በእሥራኤል ላይ ነቢይና መስፍን ሆኖ ተሾመ:: በዘመኑ ሁሉ እንደሚገባው እየኖረ : የእግዚአብሔርን ለእሥራኤል : የእሥራኤልን ለእግዚአብሔር ሲያደርስ ኑሯል:: ሕዝቡ ንጉሥ በፈለጉ ጊዜ ሳዖልን ቀብቶ አነገሠላቸው:: እርሱ (ሳዖል) እንደ ሕጉ አልሔደምና ፈጣሪ ናቀው:: ሳሙኤል ግን ደግ አባት ነውና ክፋተኛውን (ሳዖልን) ከጌታው ጋር ያስታርቅ ዘንድ ብዙ ደከመ:: አለቀሰም:: እግዚአብሔር ግን ሳሙኤልን:- "አትዘን! እንደ ልቤ የሆነ : ፈቃዴን የሚፈጽም ዳዊትን አግኝቸዋለሁና እርሱን በእሥራኤል ላይ አንግሠው" አለው:: ቅዱስ ሳሙኤልም ወደ ቤተ ልሔም ሔዶ : ከእሴይ ልጆችም መርጦ ልበ አምላክ ዳዊትን ቀባው : አነገሠውም:: ቅዱስ ሳሙኤል በተረፈው ዘመኑ ለፈጣሪው እየተገዛ ኑሯል:: ነቢዩ ዘወትር ከእጁ የሽቱ ሙዳይና የቅብዐት እቃ (ቀንድ) አይለይም ነበረ:: እነዚህም የድንግል ማርያም ምሳሌዎች ናቸውና አባ ሕርያቆስ :- "ሙዳየ ዕፍረት ወቀርነ ቅብዕ ዘሳሙኤል" ብሎ አመስግኗታል:: ነቢዩም በወገኖቹ መካከል በዚሕች ቀን አርፏል:: እሥራኤልም አልቅሰውለታል:: ††† ቅዱስ ሉክያኖስ ††† ††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሉክያኖስ ይታሠባል:: በቀደመ ሕይወቱ ጣዖት አምላኪና አጣኝ የነበረው ቅዱሱ ማንም ሳያስተምረው ክርስቲያኖቹን በመመልከት ብቻ አምኗል:: የወቅቱ ክርስቲያኖች አኗኗራቸው : ትጋታቸው : ጽናታቸውና ፍቅራቸው እንዲሁ ይስብ ነበር:: ከእነርሱ እምነት መውጣቱን የተመለከቱ ኢ-አማንያን አታልለው ሊመልሱት ሞከሩ:: እንቢ ቢላቸው በድንጋይ ጥርሱን አረገፉት:: ደሙን አፈሰሱ:: አሁንም በሃይማኖተ ክርስቶስ በመጽናቱ በዚሕ ቀን (ሰኔ 9) ከቀኑ ስድስት ሰዓት ላይ በመስቀል ላይ ሰቅለው ገድለውታል:: ††† የቅዱሳኑን በረከት አምላካቸው ያድለን:: ††† ሰኔ 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ሳሙኤል ነቢይ 2.ቅዱስ ሉክያኖስ ሰማዕት 3.ቅዱስ ዮሐንስ ††† ወርኀዊ በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ሁሉ አባት) 2.አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ኢትዮጵያዊ) 3. ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ቅዱሳን ሊቃውንት (ርቱዐነ ሃይማኖት ዘኒቅያ) 4.የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን 5.አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ (ኢትዮጵያዊ) 6.ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ (ዓለመ ብፁዐንን ያየ አባት) ††† "እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ . . . " ††† (ዕብ. ፲፩፥፴፪) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

✨️️ ✨️️️️️️️ልዩ ፍርድ ቤት✨️️️️️️️ ብዙዎቻችን ወንድሞቻችንን ለማማት የፈጠንን ነን፡፡ የራሳችንን ግንድ ትተን የሰውን ጉድፍ ለማውጣት የምንቻኮል ነን፡፡ በወንድሞቻችን ላይ ለመፍረድ፥ እኅቶቻችንን ለመኰነን የምንጣደፍ ነን፡፡
ወዳጄ ሆይ! መፍረድ የእግዚአብሔር እንጂ ያንተ ሥልጣን አይደለምና ተጠንቀቅ፡፡ እህቴ ሆይ! በአምላክ ዙፋን ላይ ለመቀመጥ አታስቢ፡፡
ወዳጄ ሆይ! መፍረድ አማረኽን? እንኪያስ ምንም ወቀሳ የሌለበት፣ ይልቁንም ብዙ ጥቅም የሚያስገኝ የፍርድ ችሎት አለልህ፡፡ በራስህ ላይ መፍረድ ትችላለህና ተቀመጥ፡፡ ከኹሉም አስቀድመህ የበደልህን መዝገብ በፊትህ አኑረው፡፡ ነፍስህ የሠራችውንም ወንጀል በሙሉ በጥንቃቄ መርምር፡፡ ከዚያም “ነፍሴ ሆይ! ይኽንና ያንን በደል የፈጸምሽው ስለምንድነው?” በላት፡፡ የበደለችበትን ምክንያት ትታ በሌሎች ላይ ለማሳበብና በሌሎች ላይ ለመፍረድ ከዠመረችም “የተከሰስሽው በራስሽ ወንጀል እንጂ በሌላ ሰው ወንጀል አይደለም፡፡ እዚኽ ፍርድ ቤት የመጣሽው ስለእነዚያ ሰዎች ለመመስከር አይደለም፡፡ ስለዚኸ ንገሪኝ! ይኽን ያኽል በደል የፈጸምሽው፣ ይኽን ያንን ኹሉ ጥፋት ያጠፋሽው ስለምንድነው?” በላት፡፡ ዘወትር ይኽን የመሰለ አስጨናቂ ጥያቄ ጠይቃት፡፡ አፍራ የምትመልሰው ከሌላትም አስፈላጊውን ፍርድ (ቀኖና) ወስንባት፡፡ ይኽን ልዩ ፍርድ ቤት ዘወትር የምትቀመጥ ከኾነ ያንን የእሳት ባሕር፣ ያ እሳቱ የማይጠፋው ትሉ የማያንቀላፋው ስቃይ በልቡናህ ይቀረጻል፡፡ ✨️️️️️️️🍂 “ወደ እኔ መጥቶ ነው፤ እርሱ አታልሎኝ ነው፤ እርሱ ፈትኖኝ ነው" እያለች በዲያብሎስ እንድታመካኝም አትፍቀድላት፡፡ ይልቁንም፡- "አንቺ ባትፈቅጂ ነው እንጂ እነዚኸ ኹሉ በአንቺ ላይ ሥልጣን የላቸውም" ብለህ ንገራት፡፡ "እኔ እኮ ሥጋ ለባሽ ነኝ፤ የምኖረውም በዚኽ ኃጢአት በሞላበት ዓለም ነው" ካለችህም "ይኽ ኹሉ ሰበብና ምክንያት ነው፡፡ ብዙዎች አንቺ የለበስሽውን ሥጋ ለብሰው በዚኽ ዓለም ኑረው ጻድቃንና ሰማዕታት ኾነዋል፡፡ አንቺ ራስሽ አንዳንድ ጊዜ መልካም ምግባራትን ስታደርጊ ይኸ አኹን የምታሳብቢበትን ሥጋ ለብሰሽ ነው" በላት፡፡ ይኽን ስትላት ቢያማትም እጅህን አታንሳባት፡፡ ምክንያቱም ቀኖናው ከሞት የሚታደጋት መንፈሳዊ ልምምድ እንጂ የሚገድላት ቅጣት አይደለምና፡፡ ስለዚኽ ምክንያት የምታበዛብህ ከኾነ “እባብ አሳተኝ" ብላ ከተጠያቂነት ያለመለጠችውን ሔዋንን አስታውሳት፡፡ ይኽን ኹሉ ስታደርግም ከአጠገብህ ማንም አይኑር፡፡ የሚረብሽህ ሰው ከአጠገብህ አይገኝ፡፡ ይልቁንም ዳኛ በፍርድ ወንበር ላይ እንደሚቀመጥ አንተም በፍርድ ወንበር ፈንታ በምቹ ጊዜና ቦታ በጽሞና ተቀመጥ፡፡ ነቢዩ “በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ የምታስቡት ይታወቃችሁ" እንዳለው /መዝ.4፥4/ ይኽ ቦታና ጊዜ ከኹሉም ይልቅ ተስማሚ ነውና እራትህን ከበላህ በኋላ ዘወትር ይኽን የፍርድ ወንበር ወደ መኝታ ክፍልህ ይዘኸው ሒድ፡፡ ዕለት ዕለት ይኸን የምታደርግ ከኾነ ሐዋርያው “እኛ በራሳችን ብንፈርድ ኖሮ ባልተፈረደብንም ነበር" እንዲል (1ኛ ቆሮ.1፥31) በዚያ አስፈሪው የፍርድ ወንበር ፊት ያለ ፍርሐት ትቆማለህ፡፡ 📝ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ 📚ሰማዕትነት አያምልጣችሁ እና ሌሎች ✨️️️️️️️ገጽ 42-42 📝በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ ✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍂✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍂✨️️️️️️️✨️️️️️️️✨️️️️️️️🍂

በፍቅር ተመላለሱ "እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ። ኤፌሶን 5:1

🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧