ch
Feedback
Ethiopian Entrance examination preparation 2018

Ethiopian Entrance examination preparation 2018

前往频道在 Telegram

◉ This channel serve as quiz and short tricks provider! ✨ It provides all the quizzes and tricks from grade 9 through grade 12. 🔭 ◉ Some useful videos are also included! ➊➋ Entrance ተፈታኝ ከሆኑ ፣ join this channel right now!! 📝 Join it right away! 💎

显示更多
1 184
订阅者
+324 小时
+227 天
+5230 天
帖子存档
Repost from Advanced Freshman
📚 2018 1st semester Given courses ​💻በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በ 2018 (1st Semester) የተሰጡትን የ Natural እና Social Science ትምህርቶች ዝርዝር አስቀምጠንላችኋል። ​📱በተሰበሰበው Data መሠረት፣ በማንኛውም ዩኒቨርሲቲ ብትመደቡ በመጀመሪያው ሴሜስተር በእርግጠኝነት የምትወስዷቸውን 6 ዋና ዋና ኮርሶች ለይተን አዘጋጅተን Pdf'ፍ ላይ አስቀምጠናል! ​👨‍💻የተመደባቹበትን ግቢ ካወቃቹ በኃላ እነዚህን ኮርሶች አስቀድማችሁ ብታጠናቁ ትርፋማ ትሆናላችሁ። ሌሎች ኮርሶች የሚሰጡት ከ 7 ወራት በኋላ በ 2nd Semester ስለሆነ፣ አሁን ላይ ጊዜያችሁን በነሱ ባታባክኑ ይመረጣል። JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN👍

በክልላቸው እንድማሩ ተወስኗል‼ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባ‼ የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አልፈው ለከፍተኛ ትምህርት ያለፉ ተማሪዎችን የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎ
+1
በክልላቸው እንድማሩ ተወስኗል‼ የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርሲቲ ምደባ‼ የትምህርት ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አልፈው ለከፍተኛ ትምህርት ያለፉ ተማሪዎችን የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ምደባ ይፉ አድርጓል። ዋና ጉዳዮቹ ከስር የተገለፁት ናው። 📌ምደባው የተማሪዎችን ውጤት፣ ምርጫ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ቅበላ አቅም እና ፆታ ታሳቢ ያደረገ ነው። 📌70% ተማሪዎች ከራሳቸው ክልል/ዞን ውጭ፣ 30% ደግሞ በራሳቸው ክልል/ዞን እንዲመደቡ ተደርጓል። 📌500 እና ከዚያ በላይ ያመጡ ተማሪዎች በተናገሩት የመጀመሪያ ምርጫ ተመድበዋል፤ ለዓይነ ስውራንና የመስማት ችግር ላለባቸው ተማሪዎችም ልዩ ድጋፍ በሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበዋል። ውጤት ለማየት፦ እስኪስተካከል ጠብቁ👇 https://student.ethernet.edu.et/view-placement ቅሬታ ለማቅረብ፦ በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ውጤቱ ይፋ ከተደረገበት ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ በኦንላይን ብቻ ማቅረብ ትችላላችሁ። 👇 https://student.ethernet.edu.et/complaints በአካል ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት በመምጣት ቅሬታ ማቅረብ አይቻልም። የሐሰት ማስረጃ ማቅረብ ምደባን ያሰርዛል በማለት ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።ሲስተም ካስተካከሉ በኋላ እንደሚለቁት ይጠበቃል። JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN👍

🇷🇺 የሩሲያ የነፃ ትምህርት ዕድል (Open Doors 2027) ያለ ምንም የትምህርት ክፍያ በሩሲያ ከፍ ያለ ትምህርትዎን መከታተል ይፈልጋሉ? የOpen Doors የነፃ ትምህርት ዕድል ለዓለም አቀ
🇷🇺 የሩሲያ የነፃ ትምህርት ዕድል (Open Doors 2027)  ያለ ምንም የትምህርት ክፍያ በሩሲያ ከፍ ያለ ትምህርትዎን መከታተል ይፈልጋሉ? የOpen Doors የነፃ ትምህርት ዕድል ለዓለም አቀፍ ተማሪዎች ክፍት ሆኗል። ይህ የትምህርት ዕድል ከዲግሪ (Bachelor's) ጀምሮ እስከ ማስተርስ፣ ፒኤችዲ (PhD) እና ፖስት-ዶክትሬት ድረስ ማመልከት የሚችሉበት ሰፊ በር ይከፍትልዎታል። ይህ ዕድል ምን ምን ይዟል? - ሙሉ የትምህርት ክፍያ ነፃ (Tuition-free) - ወርሃዊ አበል (Stipend) - በሩሲያ ከሚገኙ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የጥናትና ምርምር ዕድሎች የትምህርት መስኮች፡ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ ኮምፒዩተር እና ዳታ ሳይንስ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ቢዝነስ፣ ሕክምና፣ ኢኮኖሚክስ፣ ፖለቲካ፣ የሩሲያ ቋንቋ እና ባህል፣ እና ሌሎችም በርካታ መስኮች አሉ። ⏳ የመጨረሻ ማመልከቻ ቀን: ህዳር 21 ቀን 2019 (November 1, 2026) ማን ማመልከት እንደሚችል፣ የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች እንዳሉ፣ የሚጠየቁ ሰነዶች እና የአሰራር ሂደት ዝርዝር መረጃ ለማግኜት: https://www.edmap.et/open-doors-russian-scholarship-2027-study-in-russia-tuition-free/

#MoE የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ወስደው በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲያስገቡ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ተማሪዎች ምርጫቸውን ትምህርት ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው በኦንላይን ማስገባት ይችላሉ። የምርጫ ማስገቢያ ድረ-ገጹ፦ student.ethernet.edu.et ነው። - በሕክምና ምክንያት ልዩ ሁኔታ ያላቸው፣ - የአካል ጉዳተኛ የሆኑ፣ - ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች - ከ6 ወር በታች ሕፃን የሚያጠቡ እናቶች ተገቢውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስቴሩ ገልጿል። #MoE ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

FREE Tertiary Education Preparation Program training opportunity Join our Iteme training program specifically tailored for tertiary education preparation. 📅 Duration: 3 months 📍 Focus Areas: 👉vital soft skills, 👉English language proficiency 👉problem-solving abilities 👉enhance your readiness for the university journey ahead. 👉Master essential skills that are key to success in applying for both local and international scholarship opportunities. Requirements for application 1. Age 18-35 2. Finished Grade 12 3. Registered urban Refugee #The Iteme program is structured to assist refugee and vulnerable students in transitioning from secondary education to college and career pathways. Don't miss this opportunity to equip yourself for a successful future. Register now through this link https://docs.google.com/forms/d/1G8PY3EP7iRmUUD-w9IKdnBmtf_cIBg3xOMJPlNbUNsY/edit

📢 CALL FOR REGISTRATION — 2019 E.C. UNIVERSITY ENTRANCE EXAMINATION ==================== Adama Science and Technology University (ASTU) and Addis Ababa Science and Technology University (AASTU) invite eligible 2018 E.C. Grade 12 Natural Science students who scored 50% or above in the Ethiopian Secondary  School Leaving Examination to register for an additional entrance Examination. 🎓 PROGRAMS OFFERED ADAMA SCIENCE AND TECHNOLOGY UNIVERSITY (ASTU) Engineering * Architecture * Civil Engineering * Water Resources Engineering * Chemical Engineering * Mechanical Engineering * Materials Science and    Engineering * Electrical Power and Control    Engineering * Electronics and Communication Engineering *Computer Science and Engineering * Software Engineering Applied Sciences * Applied Biology * Applied Chemistry * Industrial Chemistry * Pharmacy * Applied Physics * Applied Geology * Applied Mathematics ADDIS ABABA SCIENCE AND TECHNOLOGY UNIVERSITY (AASTU) Engineering * Architecture * Civil Engineering * Chemical Engineering * Mechanical Engineering * Electrical and Computer      Engineering * Electromechanical    Engineering * Software Engineering * Environmental Engineering * Mining Engineering Applied Sciences * Industrial Chemistry * Food Science and Applied    Nutrition * Geology * Biotechnology 📅 REGISTRATION PERIOD August 25, 2018 E.C. – Pagume 2, 2018 E.C., until 6:00 AM. 🌐 REGISTRATION Eligible applicants can register online from anywhere through: 🌐 Online Registration: Registration Portal
https://stu.astu.edu.et/
or with these websites www.astu.edu.et www.aastu.edu.et 📅 Registration Period: August 25 – Pagume 3, 2018 E.C., until 6:00 AM 📝 Entrance Examination: The examination date will be announced after registration closes. Applicants will take the exam in person at their selected examination center. 📚 Exam Subjects: Biology, Chemistry, Physics, Mathematics, and English (Grades 9–12). For more information, please visit the following websites: 🌐 www.astu.edu.et 🌐 www.aastu.edu.et Adama Science and Technology University (ASTU)                       & Addis Ababa Science and Technology University (AASTU)

Repost from Tena Net
🏥 THE HEALTHCARE TEAM YOU DON'T SEE When you hear “healthcare team,” you probably think: 👩‍⚕️ Doctor 👨‍⚕️ Nurse 💊 Pharmac
🏥 THE HEALTHCARE TEAM YOU DON'T SEE When you hear “healthcare team,” you probably think: 👩‍⚕️ Doctor 👨‍⚕️ Nurse 💊 Pharmacist But modern healthcare is MUCH bigger. Meet the: 🫀 Perfusionist Operates the heart-lung machine during major cardiac surgery. 🧬 Genetic Counselor Helps patients understand genetic conditions, testing and inherited disease risk. 💻 Clinical Informaticist Connects medicine + data + technology to improve how healthcare information is used. ☢️ Radiation Therapist Delivers carefully planned radiation treatments to cancer patients. 🧠 Neurodiagnostic Technologist Performs specialized tests that help investigate brain and nervous-system disorders. 🫁 Respiratory Therapist Helps patients with breathing problems and manages respiratory support. 💡 Healthcare ≠ Doctor. #TenaNetDaily | Health Insight ⭐

🌐በሀገራችን Medicine የሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር ✅Addis Ababa University ✅Adigrat University ✅Aksum University ✅Ambo University ✅Arba Minch University ✅Arsi University ✅Bahir Dar University ✅Debre Berhan University ✅Debre Markos University ✅Debre Tabor University ✅Dilla University ✅Dire Dawa University ✅University of Gondar ✅Haramaya University ✅Hawassa University ✅Jigjiga University ✅Jimma University ✅Madda Walabu University ✅Mekelle University ✅Mizan-Tepi University ✅Wachemo University ✅Wolaita Sodo University ✅Wolkite University ✅Wollega University ✅Wollo University ✅Werabe University

ለማየት የተቸገራችሁ ተማሪዎች ከታች ባለው ግሩፕ admission number & first name ላኩልን በማየት እንግዛችሁ። አሁን ይስራል

ለማየት የተቸገራችሁ ተማሪዎች ከታች ባለው ግሩፕ admission number & first name ላኩልን በማየት እንግዛችሁ።

You can see your results now 🎉🎉🎉
You can see your results now 🎉🎉🎉

" ተማሪዎች ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው ውጤታቸው ማየት ይችላሉ " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡- - በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et - ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram - አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms 📨 @keleme_2013

The 2018 E.C. national examination results will be available through the official result-checking system starting 19/09/2018
The 2018 E.C. national examination results will be available through the official result-checking system starting 19/09/2018 E.C. at 1:00 PM. Galagala sa'atii 1 kasee kan ilalamuu

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ ምረቃ መደበኛ (በመንግስት ስኮላ
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ2019 የትምህርት ዘመን የቅድመ ምረቃ ትምህርት አመልካቾች የምዝገባ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን በቅድመ ምረቃ መደበኛ (በመንግስት ስኮላርሺፕ እና በግል ክፍያ) እንዲሁም በማታና ተከታታይ መርሃ-ግብር አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች ከዚህ በታች በተጠቀሱት ቀናት እና መስፈርቶች መሠረት ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርስቲው ገልጿል፡፡ አስፈላጊ መስፈርቶች እና ቀናት * የምዝገባ ቀን፡ ከነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ። * መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡ * በ2015፣ 2016፣ 2017 እና 2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ወስደው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ያመጡ ወይም ደረጃ 4 አጠናቀው (COC) ያለፉ * የመግቢያ ፈተና (UAT) የሚሰጥበት ቀናት ከጳጉሜን 02 እስከ ጳጉሜን 4 ቀን 2018 ዓ.ም ለመመዝገብ የሚከተለውን ሊንክ ይጫኑ (አሁን አልተከፈተም ፤ ከትንሽ ቀን በኃላ ይከፈታል) https://admission.aau.edu.et/

ልክ እንደወጣ ዉጤታቹን የምታዩበት websites እነዚህ ናቸው :: 1. eaes.et 2. eaes.gov.et 3. eaes.edu.et 4. result.neaea.gov.et 4. t.me/EAESbot

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ? (የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ) - የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል። - ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስ
+1
የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ? (የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ) - የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል። - ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ አስገብቶ ማስፈተን በተጀመረበት የመጀመሪያ አመት ያለፉ 3.2% ፣ በሁለተኛው 2.9% ፣ በሶስተኛው 5.2% ፣ በአምናው አራተኛው ዓመት 8.9% ደረሰ አሁን በአምስተኛው ዓመት 12.8% ነው ያለፉት። - ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን  550,210 ተማሪ ነው የተፈተነው። - ፈተናውን ያለፈው ተማሪ ብዛት 70,544 ነው። - ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6% አልፈዋል። ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3% አልፈዋል። #በፐርሰንት - ክልሎች ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ተማሪ አሳለፉ ? (ያሰፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር ይለያያል) 1. አዲስ አበባ 32.3% 2. ሀረሪ 22.67% 3. አፋር 15.6% 4. አማራ 15.56% 5. ድሬዳዋ 11.29% 6. ትግራይ 11.2% 7. ኦሮሚያ 10.53% 8. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 9.23% 9. ሶማሌ 9.2% 10. ሲዳማ 6.95% 11. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 6.12% 12. ደቡብ ኢትዮጵያ 5.82% 13. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 4.92% 14. ጋምቤላ 3.74% በቁጥር ምን ያህል ተማሪ ከየክልሉ አለፉ ? (ያስፈተኑት ቁጥር ይለያያል) 1. ኦሮሚያ ➡ 20,807 ተማሪዎች 2. አዲስ አበባ ➡ 18,646 ተማሪዎች 3. አማራ ➡ 15,225 ተማሪዎች 4. ትግራይ ➡ 3,146 ተማሪዎች 5. ደቡብ ኢትዮጵያ ➡ 3,011 ተማሪዎች 6. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ➡ 2,800 ተማሪዎች 7. ሲዳማ ➡ 1,827 ተማሪዎች 8. ሶማሌ ➡ 1,616 ተማሪዎች 9. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ➡ 835 ተማሪዎች 10. አፋር ➡ 705 ተማሪዎች 11. ሀረሪ ➡ 599 ተማሪዎች 12. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ➡ 457 ተማሪዎች 13. ድሬዳዋ ➡ 410 ተማሪዎች 14. ጋምቤላ ➡ 280 ተማሪዎች - ባለፈው ዓመት ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች 1,232 ነበሩ ዘንድሮ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 565 ናቸው። - ከዚህ ቀደም ምንም ተማሪ ካላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በኮፒዩተር ፈተና ወደ 4,500 ተማሪዎች አልፈዋል። ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች በክልል ምን ያህል ናቸው ? • ኦሮሚያ 156 • አማራ 98 • ደቡብ ኢትዮጵያ 86 • ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 69 • ትግራይ 48 • ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 29 • ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 22 • አፋር 21 • ሲዳማ 16 • ሶማሌ 9 • ድሬዳዋ  5 • ሀረሪ 3 • ጋምቤላ 2 • አዲስ አበባ 1 - ሁሉንም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ያሳለፉ 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 ነበሩ ዘንድሮ 88 ሆነዋል። በክልሎች ምንም ያህል ትምህርት ቤቶች 100% አሳለፉ ? • ኦሮሚያ 37 • አዲስ አበባ 24 • አማራ 8 • ደቡብ ኢትዮጵያ 4 • ትግራይ 4 • ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3 • ሲዳማ 2 • አፋር 1 • ድሬዳዋ 1 • ሀረሪ 1 • ሶማሌ 1 • ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 1 - በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው። ኦንላይ የተፈተኑ 18.3% አልፈዋል። በወረቀት የወሰዱ 4.2% ናቸው ያለፉት። አንዱ ቶሎ በወረቀት ከመፈተን መውጥቶ ኦላይን ለመስጠት እቅድ አለው 60% ነው ዘንድሮ ቀጣይ አመት 100% ኦንላይን ሁሉንም። - የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ስንት ነው ? • በተፈጥሮ ሳይንስ • 🥇 ከወንድ 👉 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ 🥇 ከሴት 👉 583/600 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት እንጅባራ • በማህበራዊ ሳንይንስ • 🥇 ከወንድ 👉  576/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት 🥇 ከሴት 👉 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት -  ስልክ ይዘው የገቡ 265 ተማሪዎች ከፈተናው ተሰርዘዋል። - ኮምፒዩተር ላይ ባለ " ኢሬጉላተሪ " ተብለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያለ አለ። - ከዚህ በፊት ከነበረው መሻሻል እየታየ ስለሆነ በጣም ደስተኞች ነን። - ዘንድሮም ወደ ሬሜዲያል የሚገቡ ተማሪዎች ይኖራሉ። - ሬሜዲያል ሁሌ የሚኖር አይደለም። በሚያልፈው ተማሪ ብዛት ነው የሚወሰነው። ዘንድሮ 70 ሺህ ተማሪ ስላለፈ ዘንድሮ ሬሜዲያል የሚገባው ይቀንሳል። 📌 ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት የሚመለከቱባቸውን አማራጮች ተከታትሎ ያቀርባል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

ውጤት መቼ ይታያል ? ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ። በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።
ውጤት መቼ ይታያል ? ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ። በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

ከፍተኛ ውጤት ! በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 576.2 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት ተመዝግቧል። በሴት 569.1 ከቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት ተመዝግቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም
ከፍተኛ ውጤት ! በማኅበራዊ ሳይንስ ወንድ 576.2 ከዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት ተመዝግቧል። በሴት 569.1 ከቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት ተመዝግቧል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለ
" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል። " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር) ቲክቫህ ኢትዮጵያ ነሐሴ 16 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia