ch
Feedback
Min Addis?

Min Addis?

前往频道在 Telegram

I blog about marketing and sales, and also provide Infotainment news. Want to place ads? Click here: https://telega.io/c/min_ddis ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ሚዛናዊ ፣ አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ወሬዎች የሚለቀቁበት የኢንፎቴይንመንት ቻናል ነው

显示更多

📈 Telegram 频道 Min Addis? 的分析概览

频道 Min Addis? (@min_ddis) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 10 176 名订阅者,在 新闻与媒体 类别中位列第 18 121,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 3 260 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 10 176 名订阅者。

根据 01 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -199,过去 24 小时变化为 -5,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.26%。内容发布后 24 小时内通常能获得 12.38% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 2 368 次浏览,首日通常累积 1 260 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 16。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“I blog about marketing and sales, and also provide Infotainment news. Want to place ads? Click here: https://telega.io/c/min_ddis ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ሚዛናዊ ፣ አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ወሬዎች የሚለቀቁበት የኢንፎቴይንመንት ቻናል ነው”

凭借高频更新(最新数据采集于 02 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 新闻与媒体 类别中的关键影响点。

10 176
订阅者
-524 小时
-427 天
-19930 天
帖子存档
በልጃቸው የተገደሉት የቀበሌ አስተዳዳሪ በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ የበደላ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ማሬ ካሳ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉ ተገለጠ። የአካባቢው አስተ
በልጃቸው የተገደሉት የቀበሌ አስተዳዳሪ በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ የበደላ ቀበሌ ዋና አስተዳዳሪ የነበሩት አቶ ማሬ ካሳ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ህይወታቸው ማለፉ ተገለጠ። የአካባቢው አስተዳደር ባወጣው የሃዘን መግለጫ፣ ግለሰቡ ህይወታቸው ያለፈው ከፖለቲካዊ ልዩነት ጋር በተያያዘ በራሳቸው ልጅ በተፈጸመባቸው ጥቃት መሆኑን አስታውቋል። ​አቶ ማሬ ካሳ በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ለረጅም ጊዜ በካቢኔ አባልነትና በልዩ ልዩ የአመራር ሃላፊነቶች ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን፣ የቀብር ስነ ስርዓታቸው በበደላ ቀበሌ ተፈጽሟል። ነፍሳቸው በሠላም ይረፍ 🙏 ፓለቲካ የተባለው ጉድ ቤተሠብ አይል ወገን ጎደኛ 😳 ያገኘውን እየበላ ይሄዳል 💔 ስሜት ከአእምሮ ማዘዝና ማገናዘብ ሲበልጥ እጅግ ከባድ ነው ምንጭ:-ቋራ ወረዳ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ @min_ddis

🚨 ከሰው እጅ መኪና ገዝተዋል? ታዲያ በገዙት መኪና ላይ ቀደም ሲል የተገጠመ GPS እንዳለ ወይም እንደሌለ አረጋግጠዋል? 🤔 ⚠️ እርስዎ ሳያውቁ የመኪናዎ የት እንደሚገኝና የት እንደሚንቀሳቀስ በሌላ ሰው እየተከታተለ ቢሆንስ? 🚗 ከሰው እጅ የገዙትን መኪና በመፈተሽ፣ በውስጡ ወይም በሌላ ቦታ የተደበቀ GPS Tracker መኖሩን ወይም አለመኖሩን እናረጋግጥልዎታለን። 🌟በኢትዮጵያ ትልቁ ችግር Gps መግጠም ሳይሆን የተገጠመ Gpsን ክትትል አለማድረግና የGpsን ጥቅም አለመረዳት ነው። 📍 ባሉበት ቦታ እንመጣለን! 🔍 መኪናዎን እንፈትሻለን 🛰️ GPS Tracker መኖሩን እናረጋግጣለን 📞 አሁኑኑ ይደውሉልን! ☎️ 0912743180 ☎️ 0914544755 G6 Technology PLC 🔐 የእርስዎ ግላዊነትና ደህንነት፣ የእኛ ትኩረትና ብቃት!! 💫Global Positioning System (GPS) ዓለም ወደ አንድ መንደር በሚመጣበት ግዜ...የተሽከርካሪዎቻችን ደህንነት በእጅ ስልክ መቆጣጠር እንዴት ይከብደናል? 🌟Gps በጣም በትንሽ ብር የሚገጠም ሁኖ በብዙ ብር የተገዛ ውድ መኪናችንን በቀላሉ የሚቆጣጠርልን ቴክኖሎጂ ነው። የንብረትዎ ደህንነት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው! የተሽከርካሪዎችዎ ደህንነት እና የስራ ቅልጥፍና ያሳስብዎታል? ስራዎን በሰው እምነት ብቻ ሳይሆን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ በማድረግ ትርፋማነትዎን ያረጋግጡ! ​G6 TECHNOLOGY PLC ተሽከርካሪዎችዎ የት እንዳሉ፣ እንዴት እየተነዱ እንደሆነ እና ስራዎ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ በዝርዝር የሚያውቁበትን ዘመናዊ የጂፒኤስ (GPS) መቆጣጠሪያ ሲስተም ይዞላችሁ ቀርቧል። ​የአገልግሎታችን ዋነኛ ጥቅሞች፦ 📍 ትክክለኛ ቦታን ማወቅ፦ ተሽከርካሪዎ ያለበትን ትክክለኛ ቦታ በስልክዎ ወይም በታብሌትዎ በቀጥታ መከታተል ያስችልዎታል። ⛽ የነዳጅ ብክነትን መከላከል፦ አላስፈላጊ ሞተር ማስነሳትን፣ ያልተገባ የነዳጅ ቅነሳን እና ከስራ ውጪ የሚደረጉ የግል ጉዞዎችን በማስቀረት ወጪዎን ይቀንሳል። ​የንብረትዎ ደህንነት ምርጫ ሳይሆን ግዴታ ነው! ☎️አሁኑኑ ደውለው ያስገጥሙ። 🙏ስልኮቻችንን በተደጋጋሚ ተይዞዋል ካሎት እባኮን ደግመው ይደውሉ። 📲 0914544755 ☎️ 0912743180 TikTok tiktok.com/@ethiogpss #GPS #CarSecurity #G6TechnologyPLC #VehicleSecurity #AddisAbaba G6 Technology PLC

photo content
+6

አርቲስት ካሙዙ ካሣ በአዲስ አበባ ምክር ቤት ቃለ መሃላ ፈጸመ የሙዚቃ እና የኪነ ጥበብ ባለሙያው ካሙዙ ካሣ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከአዲስ አበባ ሕዝብ የተሰጠውን ውክልና በመቀበል፣ በዛሬው ዕለት በ
አርቲስት ካሙዙ ካሣ በአዲስ አበባ ምክር ቤት ቃለ መሃላ ፈጸመ የሙዚቃ እና የኪነ ጥበብ ባለሙያው ካሙዙ ካሣ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከአዲስ አበባ ሕዝብ የተሰጠውን ውክልና በመቀበል፣ በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ፊት ቀርቦ የቃለ መሃላ ስነ ሥርዓት ፈጽሟል። ​አርቲስቱ ከቃለ መሃላ ስነ ሥርዓቱ በኋላ ባስተላለፈው መልዕክት፤ መራጩ ሕዝብ የሌሊት ብርድና የቀን ሐሩር ሳይበግረው ውክልና እንደሰጠው ገልጾ፣ የተጣለበትን የሕዝብ አደራ በታማኝነት፣ በቅንነት እና ያለ አድልዎ ለማገልገል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። ​በቀጣይም ለሕዝቡ ባስገባው ቃል መሠረት ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ፣ በተለይም በሥራ ፈጠራና በኪነ ጥበብ ዘርፎች ከተማዋንና ኢትዮጵያውያንን በሚመጥን መልኩ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጿል። @min_ddis

ለይቭ ላይ ያልተገባ ቪዲዮ ሲያዩ የተያዘባቸው - ቀሲስ ዲበኩሉ በላይ 😶😎 @min_ddis

አዶናይ ቸኮልክ ! አዶናይ መጀመሪያ ካናዳ ሀገር ላይ እየኖረ የቤት ኪራይ ክፈሉልኝ አለ። ሕዝቡም ተረባርቦ ከፈለለት። ወደሀገር ቤት መጣ። በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች እየቀረበ ስለሴጋ ጠቃሚነት አወራ።
አዶናይ ቸኮልክ ! አዶናይ መጀመሪያ ካናዳ ሀገር ላይ እየኖረ የቤት ኪራይ ክፈሉልኝ አለ። ሕዝቡም ተረባርቦ ከፈለለት። ወደሀገር ቤት መጣ። በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች እየቀረበ ስለሴጋ ጠቃሚነት አወራ። ስለትምህርት አላስፈላጊነት ሰበከ። ሁላችንም በንግግሩ ተቃውመን በየግላችን ተቃውመነው ሀሳባችንን ገለፅን። አዶናይ ታዋቂዋን ቲክቶከር ጃኒን አጠመዳት። በሷ ላይ ተንጠልጥሎ ፣ ዲቻ ቦይሶችን ይዞ ገፅታውን ገነባ። ጭራሽ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ትከሻ ለትከሻ ተለካካ። አብዛኞቻችን ተቃወምነው። ለጥምቀት ጎንደር ሄዶ ቱሪስቶችን ስለባህላችን በደንብ አስረዳ። እኛም በድጋሚ አደነቅነው። አዶናይ ግን በዚህ 2 ዓመት በማይሞላ ጊዜ ምን ሰርቶ ነው " የአዶናይ መንገድ " ብሎ መፅሐፍ ያሳተመው? ማነው ልጁን ከጀርባ ሆኖ እያሽከረከረው ያለው? የአዶናይን መንገድ እኮ ከጋሴ ትምህርቱ ጀምሮ እናውቀዋለን። ምን የተለየ ነገር ፅፎ ነው? ለሀገራችን ስንት የሚጠቅም ስራ የሰሩ ጉምቱ የምንማርባቸው ባለሙያዎች አሉ። አዶናይ ኸረ ሰው ይታዘበኛል በል። መፅሐፉ ጭራሽ 850 ብር ነው የሚሸጠው? በነፃ አያዋጣም ! Via:-ዘራሁን ተዝናኑ @min_ddis

ትዕግሥት አሰፋ ለስድስት ወራት ከውድድር ትርቃለች 🩸 የኢትዮጵያ ኮከብ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በበርሊን ማራቶን መጨረሻ ላይ ባጋጠማት የተረከዝ ጅማት (Achilles tendon) ጉዳት ምክንያት ዛ
ትዕግሥት አሰፋ ለስድስት ወራት ከውድድር ትርቃለች 🩸 የኢትዮጵያ ኮከብ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በበርሊን ማራቶን መጨረሻ ላይ ባጋጠማት የተረከዝ ጅማት (Achilles tendon) ጉዳት ምክንያት ዛሬ በጀርመን ቀዶ ሕክምና ታደርጋለች። ትዕግሥት በ2026 የበርሊን ማራቶን አብዛኛውን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ለማሻሻል በሚያስችላት ፍጥነት ስትመራ ነበር ። ነገር ግን  አንድ ማይል ገደማ ሲቀራት የተረከዝ ጅማቷ ጉዳት ደርሶባታል። ከፍተኛ ሕመም ቢሰማትም ውድድሩን ሳታቋርጥ በጽናት በመቀጠል በ2፡11፡04 አጠናቃለች። በዚህም የበርሊን ማራቶንን ለሦስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ችላለች። 2፡11፡04 የተመዘገበው ሰዓትም በሴቶች ማራቶን ታሪክ ከተመዘገቡ ፈጣን የሩጫ ሰዓቶች መካከል አንዱ ሆኗል ። የተረከዝ ጅማት ጉዳቱ ከባድ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ትዕግሥት ከውድድር ቢያንስ ለስድስት ወራት ልትርቅ ትችላለች። ትዕግሥት ዛሬ በጀርመኗ ሙኒክ ከእግርና ከቁርጭምጭሚት ጉዳቶች ሕክምና ላይ ልዩ ባለሙያ በሆነ ከፍተኛ የእግርና የቁርጭምጭሚት የቀዶ ሐኪም  በዶክተር ዮሐንስ ጋቤል አማካኝነት ቀዶ ሕክምና ይደረግላታል። @min_ddis

ትዕግሥት አሰፋ ለስድስት ወራት ከውድድር ትርቃለች 🩸 የኢትዮጵያ ኮከብ አትሌት ትዕግሥት አሰፋ በበርሊን ማራቶን መጨረሻ ላይ ባጋጠማት የተረከዝ ጅማት (Achilles tendon) ጉዳት ምክንያት ዛሬ በጀርመን ቀዶ ሕክምና ታደርጋለች። ትዕግሥት በ2026 የበርሊን ማራቶን አብዛኛውን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰን ለማሻሻል በሚያስችላት ፍጥነት ስትመራ ነበር ። ነገር ግን አንድ ማይል ገደማ ሲቀራት የተረከዝ ጅማቷ ጉዳት ደርሶባታል። ከፍተኛ ሕመም ቢሰማትም ውድድሩን ሳታቋርጥ በጽናት በመቀጠል በ2፡11፡04 አጠናቃለች። በዚህም የበርሊን ማራቶንን ለሦስተኛ ጊዜ ማሸነፍ ችላለች። 2፡11፡04 የተመዘገበው ሰዓትም በሴቶች ማራቶን ታሪክ ከተመዘገቡ ፈጣን የሩጫ ሰዓቶች መካከል አንዱ ሆኗል ። የተረከዝ ጅማት ጉዳቱ ከባድ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፤ ትዕግሥት ከውድድር ቢያንስ ለስድስት ወራት ልትርቅ ትችላለች። ትዕግሥት ዛሬ በጀርመኗ ሙኒክ ከእግርና ከቁርጭምጭሚት ጉዳቶች ሕክምና ላይ ልዩ ባለሙያ በሆነ ከፍተኛ የእግርና የቁርጭምጭሚት የቀዶ ሐኪም በዶክተር ዮሐንስ ጋቤል አማካኝነት ቀዶ ሕክምና ይደረግላታል። @min_ddis

ተወዳጁን ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅን ካጣነው እነሆ ዛሬ አራት አመት ሞላው💔 ነፍስህ በሰላም ትረፍ🙏 @min_ddis
ተወዳጁን ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅን ካጣነው እነሆ ዛሬ አራት አመት ሞላው💔 ነፍስህ በሰላም ትረፍ🙏 @min_ddis

እንኳን አደረሳችሁ❤🙏 መስቀል አደባባይ ዛሬ እንዲህ ደምቆ አምሽቷል😍 የመስቀል ደመራ በዓል 🔥❤ የፎቶ ምንጭ:-EBC @min_ddis
+3
እንኳን አደረሳችሁ❤🙏 መስቀል አደባባይ ዛሬ እንዲህ ደምቆ አምሽቷል😍 የመስቀል ደመራ በዓል 🔥❤ የፎቶ ምንጭ:-EBC @min_ddis

"ውቢት ኢትዮጵያ"- ውቢት አመንሲሳ!❤️🙏 የኢትዮጵያን ተፈጥሯዊ ውበት፣ ግርማ ሞገስ እና ማራኪ ገፅታ በአንድ ምስል ማሳየት ቢቻል፣ ያለምንም ጥርጥር ወደ አዕምሯችን የሚመጣው የዝነኛዋ "ውቢት ኢትዮጵያ" ፖስተር ነው። የኢትዮጵያ ቱሪዝም ኮሚሽን “የ13 ወር ፀጋ” በሚል መሪ ቃል ዓለምን ካስደመመባቸው ድንቅ ስራዎች መካከል፣ የዚህች እንቁ እናት ምስል ለዘመናት የማይደበዝዝ አሻራ ጥሎ አልፏል። ይህች የተፈጥሮ ውበት የተቸረች እንቁ፣ በኦሮሚያ ክልል ወለጋ ተወልዳ ያደገችው ወ/ሮ ውቢት አመንሲሳ ትባላለች። የ4 ልጆች እናት የነበረችው ውቢት፣ ካፒቴን ከሆነው ባለቤቷ ጋር ኑሮዋን በዋና ከተማችን ሸገር አድርጋ የኖረች አንጋፋ እናት ነበረች። ብዙዎች እንደሚያስቡት ወ/ሮ ውቢት በሙያዋ ሞዴል ወይም የፊልም ተዋናይት አልነበረችም። በ1970ዎቹ የብሄራዊ ቱሪዝም ኮሚሽን የሀገርን ገፅታ የሚገነቡ እና ለገቢ ማሰባሰቢያ የሚውሉ ማራኪ ምስሎችን በማፈላለግ ላይ በነበረበት ወቅት፣ ውቢት በተፈጥሮ የታደለችው ኢትዮጵያዊ ቁመና እና ገፅታዋ ለዚህ ታሪካዊ ፎቶ እንድትመረጥ አድርጓታል። ከውበቷ ባሻገር የልቧ ንፅህና እና ሀገር ወዳድነቷ ይበልጥ የሚያስደምም ነው። ኩባዊ-ኢትዮጵያዊው የታሪክ ምሁር ኤድዋርዶ ባይሮኖ እንዳስቀመጠው፤ ውቢት አመንሲሳ ለዚህ ታሪካዊ እና በመላው ዓለም ለተሰራጨ ፎቶ "አምስት ሳንቲም" እንኳን ክፍያ አልተቀበለችም። ፖስተሩ ያስገኘው  ገቢ ሙሉ በሙሉ ለኮሚሽኑ ገቢ ሆኖ የሀገሯን ቱሪዝም እንዲያገለግል በፅኑ ትፈልግ ነበር። ይህ ድርጊቷ ለሀገሯ ያላትን ጥልቅ ፍቅርና ንፁህ ዜግነት ያሳያል። በታሪክ ማህደር ውስጥ ደማቅ ስም ያላት "ውቢት ኢትዮጵያ"፣ በ2000 ዓ.ም የህክምና እርዳታ ለማግኘት ወደ አሜሪካ አምርታ፣ በህዳር ወር 2001 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች። መልከ መልካሟ የሀገር ባለውለታ ውቢት ኢትዮጵያ (ውቢት አመንሲሳ) ሀገሯን በቅንነት ስላገለገለች እና የኢትዮጵያን ብሩህ ገፅታ ለዓለም ስላስተዋወቀች ዘላለማዊ ክብር እና ምስጋና ይገባታል። ፈጣሪ ነፍሷን በገነት ያኑርልን! 🤍🙏 @min_ddis

photo content

ጠንቋይ ነኝ ባለ ሰው ምክር ተነሳስቶ የ5 ዓመት ህፃን ልጅን ወንዝ ውስጥ በመክተት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ እስራት ተቀጣ ድርጊቱን የፈጸመው የቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ኢልኩሌ ቀበሌ ነዋ
+1
ጠንቋይ ነኝ ባለ ሰው ምክር ተነሳስቶ የ5 ዓመት ህፃን ልጅን ወንዝ ውስጥ በመክተት ህይወቱ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ  እስራት ተቀጣ ድርጊቱን የፈጸመው የቦረና ዞን ተልተሌ ወረዳ ኢልኩሌ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ጉዮ ገልማ ገንዲ የተባለ የ30ዎቹ አጋማሽ ወጣት ሲሆን አዋቂ ወይም ጠንቋይ ነኝ ባለ ሰው ምክር ተነሳስቶ የ5 ዓመት ህፃንን በመግደሉ የ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንደተፈረደበት የቦረና ዞን ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ጉዮ ከልጅነቱ እስከ ጉልምስናው ጠንክሮ ቢሠራም የሚፈልገው ደረጃ ላይ ባለመድረሱና ከእርሱ በኋላ የተነሱት በሀብት በመቅደማቸው የተነሳ በተሰማው ከፍተኛ የመማረር ስሜት አቋራጭ መንገድ ፍለጋ ወደ አንድ አዋቂ ዘንድ ያቀናል፡፡ አዋቂ ነኝ ባዩም የሠራኸው ሁሉ የተባረከ እንዳይሆን መድኃኒት ተሠርቶብሃል፤ ይህንን ለማክሸፍ የ5 ዓመት ወንድ ልጆችን የምሰጥህን ውሃ ማጠጣት አለብህ የሚል አደገኛ ምክር ይሰጠዋል። ምክር የተሰጠው ጉዮም ሐምሌ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 5 ሰዓት ተኩል ላይ ጌመቹ ዲዳ የተባለው የ5 ዓመት ህፃን የተሰጠውን ውኃ እንዲጠጣ ቢያስገድደውም ህፃኑ በመቃወሙ በንዴት አንገቱን አንቆ ኤላ ወደሚባል ወራጅ ወንዝ ውስጥ በመወርወር ሕይወቱ እንዲያልፍ ያደርገዋል። የቦረና ዞን ፖሊስ ዋና መምሪያ የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዲባ ቦሩ እንደገለጹት፤ ከሁለተኛው ህፃን በተገኘ ጥቆማ መሰረት ፖሊስ ወዲያውኑ ተንቀሳቅሶ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር ያዋለው ሲሆን ምርመራውን አጠናቆ ድርጊቱ መፈጻሙን ያረጋግጣል። ጉዳዩን መርምሮ የተመለከተው የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ጳጉሜ 4 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ጉዮ ገልማ ገንዲ በአጉል እምነት ተነሳስቶ በህፃኑ ላይ የፈጸመው ድርጊት ከባድና ጨካኝ በመሆኑ በ16 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

ሰውን በአለባበሱ አትገምተው!» በቅርቡ በ Meta Connect ትልቅ መድረክ ላይ የተከሰተው ነገር የብዙዎችን ትኩረትስቧል። የሜታ (Meta) ዋና የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ኃላፊ አሌክሳንደር
ሰውን በአለባበሱ አትገምተው!» በቅርቡ በ Meta Connect ትልቅ መድረክ ላይ የተከሰተው ነገር የብዙዎችን ትኩረትስቧል። የሜታ (Meta) ዋና የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) ኃላፊ አሌክሳንደር ዋንግ መድረክ ላይ ሲወጣ የነበረው አቀራረብ እጅግ አስገራሚ ነበር። ልክ ከእንቅልፉ እንደነቃ፣ ልብስ ማጠቢያ ቅርጫት ውስጥ የነበረን ቲሸርት መዞ የለበሰ፣ የቆዩ አርጊንዶ ጫማዎቹን አሻምቶ «ለመሆኑ ዛሬ መድረክ መውጣት ነበረብኝ እንዴ?» ብሎ ያስታወሰ ነው የሚመስለው! ጫማው ደግሞ ብዙ ዘመናትን ያገለገለ እና የደከመ ይመስላል። ነገር ግን «መፅሐፍን በሽፋኑ አትመዝን» እንደሚባለው ሁሉ፣ የዚህን ሰው ውጫዊ ገጽታ አይተህ እንዳትሳሳት! ይህ በ29 ዓመቱ ተራ የሚመስል አልባሳት የለበሰ ወጣት የ3.2 ቢሊዮን ዶላር ሀብት ባለቤት ነው። ✍️በአብርሃም ጥላሁን @min_ddis

ፈርጣማዉ ዳኛ ለፍጥነታቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዋል በብራዚል ሊግ ዳኛ የሆኑት አንደርሰን ዳሮንኮ ከብራዚል ሊግ የዳኞች ኮሚቴ በቀረበላቸው ምክረ ሃሳብ ከሰዉነት ክብደታቸዉ ወደ 12 ኪሎግራም መቀነሳ
ፈርጣማዉ ዳኛ ለፍጥነታቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዋል በብራዚል ሊግ ዳኛ የሆኑት አንደርሰን ዳሮንኮ ከብራዚል ሊግ የዳኞች ኮሚቴ በቀረበላቸው ምክረ ሃሳብ ከሰዉነት ክብደታቸዉ ወደ 12 ኪሎግራም መቀነሳቸዉ ተዘግቧል። የአለማችን ፈርጣማዉ ዳኛ በመባል የሚታወቁት እኚህ የ 45 አመት አርቢትር ለፍጥነት እና ቅልጥፍና በሚል ነዉ ኪሎአቸዉን እንዲቀንሱ የታዘዙት። ዳኛዉም ለህልማቸዉ ሲሉ ኪሎአቸዉን ቀንሰዉ ጨዋታ መርተዋል። በርከት ያሉ የእግርኳስ ተመልካቾች በዳኛዉ የሰዉነት ቅርጽ መለወጥ ጥያቄ ፈጥሮባቸዉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ መነጋገሪያ አድረወገዉት ነበር። Via:-ዳጉ ስፖርት @min_ddis

በቅርቡ ለ'ተደ*በደበ$ችው' ኦብሴ ቤት ተሰጣት ! የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለኦብሴ እና ለእናቷ የመኖሪያ ቤት ስጦታ አበረከቱ።በቅርቡ በሶስት ሴቶች አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት የ
በቅርቡ ለ'ተደ*በደበ$ችው' ኦብሴ ቤት ተሰጣት ! የአዲስ አበባ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ለኦብሴ እና ለእናቷ የመኖሪያ ቤት ስጦታ አበረከቱ።በቅርቡ በሶስት ሴቶች አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ጉዳት የደረሰባት ተማሪ ኦብሴ ፤ ዛሬ ግን ያ የጨለማ ምዕራፍ በደስታና በተስፋ ብርሃን ተተክቷል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣ የዚህች እናትና ልጅ ህመም እና የጽናት ጉዞ የርህራሔ ስሜት ፈጥሮባቸዋል። የከተማዋ መሪ መሆናቸውን ብቻ ሳይሆን እናታዊ ርህራሔን በማስቀደም፣ ለኦብሴ እና ለእናቷ ለወይዘሮ ማሜ ባርሴሳ የመኖሪያ ቤት ስጦታ በዛሬው እለት አስረክበዋቸዋል። ዛሬ ወይዘሮ ማሜ እና ልጃቸው ኦብሴ የራሳቸውን ደጃፍ ዘግተው በሰላም የሚያድሩበት፣ ልጃቸውን ያለ ስጋት የሚያሳድጉበት የሞቀ አዲስ ጎጆ አግኝተዋል። እናትና ልጅ ለተደረገላቸው መልካም ነገር በሙሉ ከልባቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል @min_ddis

"መስቀልና ባህላዊ አከባበር!" እንኳን ለ2019 ዓ.ም.ለብርሃነ መስቀሉ  በዓል በሰላም አደረሣችሁ አደረሰን!! አብርሐም ግዛዉ  ኢንተርቴመንት ከአፍሪካ ሬኔሳንስ ቴሌቪዥን አርትስ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር የፊታችን እሁድ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም  ከቀኑ 10:00 እስከ 12:00 ሰዓት ድረስ ልዩ አዝናኝና አስተማሪ የበዓል የመዝናኛ ኘሮግራም "መስቀልና ባህላዊ አከባበር" የተሰኘ ልዩ የዓዉዳመት ዝግጅት ይዞላችሁ ይቀርባል።እርስዎም እንዲከታተሉ ተጋብዘዋል።" "መስቀልና ባህላዊ አከባበር" አዘጋጅ አብርሐም ግዛዉ ኢንተርቴይመንት ከአርትስ ቴሌቪዥን ጋር በመተባበር መቼ!? የፊታችን  እሁድ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 10:00-12:00 ሰዓት

ዜና እረፍት ! አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ አረፉ‼️ አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ድምፃዊው በኢትዮጵያ የሙዚቃ ወርቃማ ዘመን ከ60 በላይ የማይረሱ የሙዚቃ ሥራዎችን በማ
+3
ዜና እረፍት ! አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ አረፉ‼️ አንጋፋው ድምፃዊ ግርማ ነጋሽ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ድምፃዊው በኢትዮጵያ የሙዚቃ ወርቃማ ዘመን ከ60 በላይ የማይረሱ የሙዚቃ ሥራዎችን በማበርከት የራሳቸውን አሻራ አሳርፈዋል። ከታወቁ ሥራዎቻቸው መካከል “የኔ ሐሳብ” እና “ምነው ተለየሽኝ — መስከረም ሳይጠባ” ይጠቀሳሉ። ግርማ ነጋሽ የሙዚቃ ሥራቸውን በፖሊስ ሰራዊት ኦርኬስትራ ባንድ የጀመሩ ሲሆን፣ በኋላም በብሔራዊ ቲያትር በመስራት በሙዚቃው ዓለም ስማቸውን አስጠርተዋል። እ.ኤ.አ. በ2011 ከታዋቂው Either/Orchestra የጃዝ ባንድ ጋር በመሆን “የኔ ሐሳብ”ን በድጋሚ በመድረክ ላይ አቅርበዋል። በሙዚቃው ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽዖም የሕይወት ዘመን የክብር ሽልማት መቀበላቸው ተገልጿል። የአንጋፋው ድምፃዊ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ነገ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በአዲስ አበባ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም ተገልጿል። ግርማ ነጋሽ የሦስት ወንዶችና የአንድ ሴት ልጅ አባት ነበሩ። ነፍስ ይማር🙏 ምንጭ  ሚኪ አጋፔ @min_ddis

"ከ10 ዓመታት በኋላ ወንድሜን ዶክተር ቴድሮስን በኒው ዮርክ ድንገት በማግኘቴ ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ።" - አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ያሰፈሩት @min_ddis
"ከ10 ዓመታት በኋላ ወንድሜን ዶክተር ቴድሮስን  በኒው ዮርክ ድንገት በማግኘቴ ትልቅ ደስታ ነው የተሰማኝ።" - አቶ ጌታቸው ረዳ በኤክስ ገጻቸው ያሰፈሩት @min_ddis

😭💔 ከ 30 አመታት በላይ ደክሞ እና ለፍቶ ያፈራውን ንብረት በአንድ ጀንበር መንግስት ሲያፈርስበት፣ ውጭ ሀገር ድረስ ሄዶ የተማረው የማስተርስ እና ዶክትሬት ዲግሪ ህይወቱን ማቆየት / መሰረታዊ
😭💔 ከ 30 አመታት በላይ ደክሞ እና ለፍቶ ያፈራውን ንብረት በአንድ ጀንበር መንግስት ሲያፈርስበት፣ ውጭ ሀገር ድረስ ሄዶ የተማረው የማስተርስ እና ዶክትሬት ዲግሪ ህይወቱን ማቆየት / መሰረታዊ ፍላጎቶቹን እንኳን ማሟላት ሳያስችለው ሲቀር፣ በረ'ሀብ እና በች'ግር ሲሰ'ቃይ ቆይቶ በስተመጨረሻ ይህንን መልእክት ፅፎ በሚያሳዝን ሁኔታ ሰኔ 6 / 2018 ዓ.ም - ራ ሱ ን አ ጠ ፋ 💔 በጣም ያሳዝናል..! እጅግ በጣም። ይህ ሰው ዘሪሁን ይባላል። በቅርብ ጊዜ እንኳን ያሳተማቸው 3 መፅሀፍቶች ነበሩት። ከልብ አዝኛለሁ። ለቤተሰቦቹና ወዳጅ ዘመዶች መፅናናትን ይስጥ..! ፍራኦል ✍️ፍራኦል ሐበሻ እንደፃፈው @min_ddis