ግጥም
前往频道在 Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
显示更多4 819
订阅者
+324 小时
+557 天
+23030 天
帖子存档
4 821
#እግረ_መንገድ
አላዋቂ ተጓዥ
እግር አለኝ ብሎ
መንገዱን ሳያበጅ ለመሄድ ይነሳል
ወትሮስ መንገድ እንጅ እግር መች ያደርሳል
እግርማ ታዛዥ ነው ባዘዙት ይሄዳል
ምን እግር ቢኖረው
መንገድ የሌለው ሰው ወዴት ይራመዳል
በማያደርስ እግር ሲሄዱ ከማርጀት
አንዴ ቆም ብሎ መንገድ ነው ማበጀት
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 821
የሆዳም ሰው ግብሩ
ሲተፋ ማደሩ!!!
አልጠግብ ባይ ከርሱ
ሁሉን ማግበስበሱ!!!
የሁሉን ሰው ድርሻ አለመጠን ጎርሶ
ህይወቱን ይገፋል ሆዱን ተንተርሶ!!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 821
🛡⚔ KURULUS {ዑስማን} OSMAN ⚔🛡
🧨መስራቹ ዑስማን ክፍል 241 & 242 በትርጉም ሊለቀቅ 30 ደቂቃ ነው የቀረው አሁኑኑ join ይበሉት⤵️ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
4 821
🛡⚔ KURULUS {ዑስማን} OSMAN ⚔🛡
🧨መስራቹ ዑስማን ክፍል 241 & 242 በትርጉም ሊለቀቅ 30 ደቂቃ ነው የቀረው አሁኑኑ join ይበሉት⤵️ ⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
4 821
❤️ #አፈቅርሻለሁ ❤️
አንድ ነገር ቀረኝ ከጥፋት መታቀብ
ፈልጌው አይደለም አላበዛም ሰበብ
ቅንነትሽ ደስታ ስሜትን ይስባል
ርሃብ ያስታግሳል ጥምንም ያስቆማል
ሻማ ሁነሽኛል በጨለመው ጎኔ
ለማንም አልፈቅድም እንዲለዪሽ ከእኔ
ሁሌም ወድሻለሁ ትናፍቂኛለሽ እሰከማይሽ በዓይኔ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 821
Repost from Moksho.exe
Don't judge a book by its cover. Judge it by the type of person that recommended you read that book
4 821
#ቀኑ_ይለወጣል
የትላንቱ ችግር ነገ ላይ ተረት ነው
ያሳለፍነው ስቃይ ወደ ፊት ክብር ነው
በዛሬ ውስጥ ሆኖ ፈተናው ቢከብድም
ይለወጣል ቀኑ ዛሬ ነገ አይደለም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 821
Repost from ጥንቅሻ✍🏼🦋
የፈጣሪ እዝነት ግሩም ነው!!
.
ይህን ለመፃፍ እጄን ሳነሳ አይኔ በእንባ ተሞላ፣ግን ከተማርኩት እና ብርታት ካገኘሁት የህይወት ክፍል ትንሽ ላካፍላችሁ፣ባለማወቅ ውስጥ ሁነን ከምንጠፋ ትንሽም ቢሆን ድክመታችንን አውቀን ወደ ጥንካሬ እንቀይረው፥
.
.
የሰው ልግስና ሁኔታን አስልቶ ነውና ይቋረጣል።የፈጣሪ ግሩምነት ግን በሁኔታ፣ ጊዜ እና ጥቅም የተመረኮዘ አይደለም።"በጠየቅነው ልክ የማይመለስ፣ በመለስነው ልክ ያልተጠየቅነው ነገር ብዙ ነው" ስንቱን ሰርቼ፣ ስንቱን አጥፍቼ ይቅር ብሎኝ ይሆን፥
.
አንዳንዴ እጄን ዘርግቼ መጠየቅ አፍራለሁ፥ ብዙ የማይገቡኝ ነገሮችን በመስጠት ውስጥ ያኖረኝ ፈጣሪን፡ለድክመቴ ብቻ መሸሸጊያ ሳደርገው፣ ዳግም ቀና ብዬ መራመድ ስጀምር ፡መሸሼን ሳስብ ያመኛል፥
.
ምን ልላችሁ ፈልጌ ነው...ብዙ ሰው መሆን አይጠበቅባችሁም ፈጣሪ ዘንድ ዋጋ እንዲኖራችሁ፣ የፈለጋችሁትን ጠይቃችሁ ለማግኘት፣ ወድቃችሁ መሸሸጊያ ለመፈለግ፣ ከምንም በላይ ደግሞ አጥፍታችሁ ምህረት ለማግኘት፥
.
ለመልካም ነገር እንኳን በቂ ላልሆነ እድሜ ክፉ አንስራበት...እስከዛሬ ስንት ቀን ተጨምሮልን ይሆን? ቀን ዕድሜ ነውና ስንኖር የማይገፋን ፈጣሪን ላለማስቆጣት እንኑር!!!
4 821
Repost from Thoughts
እውነትም... ዝናብ ትዝታን ይጠራል!!! " ክፍ... ክፍ" የሚለው ሳይሆን በጭጋግ ተሸፋፍኖ የሚመጣው ክብድ የሚል ድባብ ያለው፤ ሆድ ባር ባር የሚያስብል በቃ ከመሬት አስነስቶ ሆድ የሚያስብስ ዝናብ....
ኡፍፍ... አሁን ምናለበት ባይዘንብ?! ሁልቀን ሁልጊዜ ነፋሻማ... ፀሀያማ ቀን ቢሆን፤ ንፋስ እየጠራረገ ትዝታህን ከየዱካህ ላይ ቢወስደው...
አያይ... ዛሬ ንፋስ የለም ያለው ጭጋግ ብቻ ነው፥ ጉም ብቻ ...
ብቻ አየሩም ያኮረፈ መሰለኝ... ተፈጥሮም አብራኝ የናፈቀችህ አትመስልም?! ሰማዩስ ምን ሆዱን አባባው ቆይ እሱም እያለቀሰልን ቢሆንስ?!...
ብቻ ግን ዝናቡ ሲዘንብ ሲዘንብ... እያንዳንዱ ጠብታ ሸፋፍኜ የቀበርኩትን ትዝታህን አቧራውን አጥቦ አነሳው መሰል... ንፋሱ ሽው ባለ ቁጥር ልቤ ወደ ሺህ ቦታዎች እየደቀቀችልህ ነው...
ወይ ጉድ! አይገርምም?! ክረምቱ መጣና ትዝታሽ ሰፈረብኝ ያለውን ገጣሚ በሙሉ ስታዘብ እንዳልነበረ እድሜ ላንተ ይሄንንም አየሁት ማለት ነው?!
4 821
#ሰው_ፈልጉ
ለዕምነቱ ያደረ ቃሉን የማይበላ
ፊትን ተመልክቶ ሰው የማያዳላ
እውነት ተናጋሪ የሚኖር ለነፍሱ
ለሰው የሚራራ አብልጦ ከራሱ
ፊት ለፊት አድንቆ ዞሮ የማያማ
በተንኮል በሀሜት ልብ የማያደማ
ጥሩ ወዳጅ መስሎ እየሸነገለ
ወንድሙን ለነዋይ ዋሽቶ ያልገደለ
አደራ ጠባቂ ምሎ የማይከዳ
እስኪ ሰው ፈልጉ ከሁሉ የፀዳ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 821
አሁን በዚህ ዘመን ቢመጣ አምላካችን
መልስ ይሆነን ይሆን የትኛው ስራችን?
የግፋችን ባህር ሞልቶ በደላችን
እንዲሁ እንደከፋን አትምጣ ጌታችን
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
