ʜᴀʟᴀʟ™
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 ʜᴀʟᴀʟ™ 的分析概览
频道 ʜᴀʟᴀʟ™ (@halal_post) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 056 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 8 277,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 3 018 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 056 名订阅者。
根据 04 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -196,过去 24 小时变化为 5,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 8.80%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.32% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 974 次浏览,首日通常累积 700 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 19。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“خُذ ماشئت ، لا تستأذن بنشر الخير🤍.
Cross @Ifendim”
凭借高频更新(最新数据采集于 05 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
11 056
订阅者
+524 小时
-407 天
-19630 天
帖子存档
11 060
Repost from N/a
🌙 የ 81 ቃሪኦች ሙሉ ሱራ በአንድ የምታገኙበት ቻናል ልጠቁማችሁ ወላሂ የውሸት ማስታወቂያ አይደለም 🙌
Link👇https://t.me/+VU3MNQ4CuMI4OWQ0 https://t.me/+VU3MNQ4CuMI4OWQ0 https://t.me/+VU3MNQ4CuMI4OWQ0
11 060
ውስጣዊ ውበት ! የሚባል ነገር የለም ። ቁንጅና ፤ ስለ ሰውየው ማንነት ወይም ባህሪ ሳናውቅ ወዲያውኑ ልንፈርደው የምንችለው ነገር ነው ። ውስጣዊ የምትሉት ውበት ግን ስለ ሰውየው ታሪክ ፥ ዓላማ እና መንፈስ ወዘተ ማወቅ ይጠይቃል ። የአንድን ሰው ቅንነት ማየት አንችልም ፤ ማየት የምንችለው የቅንነቱን ውጤት (ድርጊቱን) ነው ።
አንድን ሰው ውብ ነው ለማለት መጀመሪያ ስለ ማንነቱ ማወቅ ካለብህ ፥ ይኼ የሞራል ዳኝነት ነው ። ደግነት አስፈላጊ ነገር ቢሆንም ፥ ከውበት ጋር ማቀላቀል ግን የሁለቱንም ትርጉም ያደበዝዘዋል ። አንድን ሴት "ውስጣዊ ውበት"ሽ እኮ ማለት ፤ መልከጥፉ °°°🖤
11 060
አንዲት ሴት እንዲህ ትላለች፦
"እህቴ ከአክስታችን ልጅ ጋር ተስማማችና እንዲህ አለችው፦ 'እስኪ ናና #እጨኝ፤ እኔ ደግሞ እምቢ እልሃለሁ። ይህንን የማደርገው ፍቅረኛዬን ለማበሳጨት ፈልጌ ነው' ብላ አሳመነችው።
እሱም እውነት መሰለውና እንደተስማሙት ሊያጫት መጣ። እሷ ግን 'እምቢ እላለሁ' ያለችው ልጅ ገና ጥያቄውን ሲያቀርብ ወዲያው 'እሺ!' ብላ እሺታዋን ገለጸች። የአባቴና የእናቴ ቤተሰቦችም በደስታ ዳሯትና አሁን ባሏ ሆነ።
ጉዱ ምን መሰላችሁ? እህቴ ምንም አይነት ፍቅረኛ አልነበራትም፤ የፈለገችው እሱን ራሱን ነበር!
አይ ሴቶች🥲😅
11 060
- ደጋግመህ ዴት ለማድረግ ሞከርክ~ አልተሳካልህም..በተደጋጋሚ 'አፍ የሚያስከፍት ነው' በምትለው መልኩ ጅንጀናህን ለማርቀቅ ለፋህ አሁንም አልተሳካም።
በብርዝናህ በኩል የሆነችዋን ተሞዳሙደህ፣ ተቶካትከህ
ሰካክሰህ ፎክ ተክ ብለህ(ለማሰማመጥ?) ጣርክ..ይህኔም አልተሳካም... እናም ወደ ሶሻል ሚዲያ እና ወደ ሰፊው ህዝብ መጣህ እና ስለ ሐራም የፍቅር ግኑኝነት ሰበከን..በእሳት አስፈራራኸን..በቁጣ አስጠነቀቅኸን..አሁን ካንተ በላይ የአዘል ሙኸርበጥ አለ ወይ ?...የለም!
ምን ለማለት ነው...ኣዎዎ
በራሳችሁ ምክንያት የተፈጠረ ጉድለታችሁን ለማስታመም ሐይማኖታዊ ወይም ባህላዊ ምክንያት አትፈልጉለት። ለሁለት ነገር ሲባል..
ሀ..የመጀመሪያው እውነት እና ችግሩ ራሳችሁ ስለሆናችሁ..ጉዳዩን በመወረፍ ሁኔታችሁ ስለማይስተካከል..በዚያ ጎዶሎው ስለማይሞላ..ስለማያሽርም..ስለማይለወጥ..አፍ የደሰከኮረውን ውስጥ ስለማይደግመው..ተዉት
ለ..ማንም ግድ ስለማይሰጠው..ስለማያገባን..መነሻው ስለሚገባን..የቱጋ እንደሳታችሁ ስለምንረዳ..ከምንም በላይ ልክ ይህ ሁኔታችሁን ስናይ ፊደል 'ሀ' ላይ ያለውን በማብሰለሰል ስለምንረሳችሁ(ስለምንረሳው)..ባጠዓላይ ትዝም ስለማይለን..ይቅር
11 060
....ሁሌ ነገሮችን እንደ ቀሽም ልብወለድ 'አንዳንዴ' ብሎ መጀመር ይታክታል ...በ'አንዳንዳንዶች' ውስጥ ተድበስብሰው የሚያልፉ ብዙ አንዳንዶች መኖራቸው ያተክናል ...የብዙዎቻችን 'አንዳንድ' በጥቂት እድሚያችን የተካበተ ግና... በህይወት ዘመን ሙሉ የማይገለፅ ነው ... ይህን መራራ እውነት እያወቁ ግን ላለማስተባበል ሁሌ 'አንዳንዴ' እያሉ መጀመር ቀሽምነት ካልተባለ ምን ሊሰኝ ነው....ሆኖም ግን ...
¤
....አንዳንዴ የማንገፋቸው የህይወት መራራ ፅዋዎች አሉ ....እንጎነጫቸው ዘንድ ግድ የሆኑ ...በኛ ሳይሆን በአላህ ፍቃድ ስር ያደሩ....በዚህ ጊዜ አሏህ ካንተ ትዕግስትህን እየፈተሸ መሆኑን እወቅ....
¤
....አንዳንዴ ብትሸሸው እንኳ የማታመልጠው ...ባትፈልገው እንኳን የሚፈልግህ...ከአንተ ቁጥጥር እና
ችሎታ ውጪ የሆነ የአላህ ፀጋ ያካብብሃል ....ግራ እስኪገባህ ድረስ በመልካም ነገር ያበስርሃል...በዚህ ጊዜ ለምስጋና እየጠራህ መሆኑን እወቅ...
¤
....አንዳንዴ ያለህበት ስብዕና በከፋ ሁኔታ ላይ እያለ ድንገት እሱን ማምለክን ያገራልሃል ...የየ'ለት መገዛትህን በልብህ ላይ ያፀናልሃል ....ታዛዥነትን ያሰብትብሃል...ግልፅ ባለ ሁኔታ ወደራሱ ሲጠራህ ትመለከታለህ....ይህም ላንተ ገረሜታን የሚፈጥር እና ከቁጥጥርህ ውጭ የሆነ ነው .... በዚህ ጊዜ በነዚህ ተግባራት የዋለልህን ውለታ ሊያሳውቅህ መሆኑን እወቅ...
❴..قُل لَّن يُصِيبَنَآ إِلَّا مَا كَتَبَ ٱللَّهُ لَنَا..❵
«..አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም..»በላቸው
.....የቻይነትህ ጥበብ እና ልቅና ከአቅሎችም በላይ የሆነው ጌታዬ ሆይ !... ...የሚገባህን አምልኮ አላመለክንህም ...የሚገባህን ምስጋና አላመሰገንህም ....ጥራት ይገባህ.!... ሱብሐነከ ያ ረብ 🖤
11 060
አንዳንዶች ደግሞ አጠያየቃቸውን የሚያሳምሩ አሉ...... አንዲት እህት ትዳር መጣላት ከዚያም ስለ ሰውየው ስትጠይቅ መስጂድ ሚሄድበት መኪና አለው? የቲሞችንስ ሰብስቦ የሚመግብበት ቤት አለው።
አሉ ነው!😂
11 060
Repost from N/a
11 060
https://t.me/MuradTadesse/48345
ያንተም ዱዐ ሙስተጃብ ሲሆን እኛም በጬኸታቸው ምክንያት እንቅልፍ ስናጣ ኧረ የአርሰናል ነገር ከፋ😭
11 060
.
💍የትዳር ወጪና የባል መከራ😭:
- በህንድ ሴቷ መህር #ትከፍላለች፤
- በግብፅ ደግሞ የቤት እቃውን ሴቷ #ታሟላለች።
የኛዋ ሀገር ግን... ወንዱ መህር መክፈል አለበት፣ ወርቅ መግዛት አለበት፣ ቤት ማዘጋጀትና እቃ ማሟላት፣ የሰርጉን ድግስ፣ የሰርግ አዳራሹንና የሙሽራዋን ወጪ ሁሉ እርሱ ይሸፍናል።🥀
ሙሽራዋ ላይ ያለባት ግዴታ ግን... ኢስቲኻራ ሰግዳ 'እሺ' ማለት ብቻ ነው😭
ስለዚህ ወንድሜ! ያላገባ ወንድ ካየህ 'ለምን እስካሁን አልገባህም?' ብለህ አትጠይቀው። ዝም በለው... ያለበት መከራ ይበቃዋል!
.......
11 060
ግብፃዊው ፀሐፊ አሕመድ ኻሊድ✍️
"ያ አንቺ ትፈሪው የነበረውና #እንድገድልልሽ ትለምኚኝ የነበረው አይጥ እንኳ... እኛ ከተለያየን በኋላ ወደ እኔ መጣና።
አይኖቼን እያየ እንዲህ አለኝ፦ "ለመሆኑ ያኔ እኔን ልትገድል የፈለግከው ለዚች (ለማትረባ) ሴት ብለህ ነበር? ውርደት ለአንተ ይሁን!'" 😂
11 060
«...እንዴት ነሽልኝ ግን...?!»
«...አልሐምዱሊላህ...»
ይህ 'አልሐምዱሊላህ' ምስጋናን ማቅረብ ብቻ መስሎ አይሰማኝም። ቃሉ ምስጋናን እየገለፀ ሆኖ ብቻ አይነበበኝም።
- አንዳንዴ 'አልሐምዱሊላህ'
"የሆነውን ሁሉ አላህ እንዳረገው አውቂያለሁ፣ ተረድቻለሁ፣ ያረገው ሁሉ እኔ ካሰብኩት የተሻለ እንደሆነ አምኛለሁ፤ ከእኔ ምኞት የሱ ውሳኔ ቀድሟል፤ የሱን ውሳኔ፣ የሱን መሻት፣ የሱን ማድረግ በፍቅር ተቀብያለሁ" የሚሉትን ሐረጋትን አዝሎ ይታየኛል
¤
አንዳንዴ 'አልሐምዱሊላህ
" ጭንቅ ጥብብ ብሎኛል፤ ጥልቅ የሆነን ህመም ታምሚያለሁ፤ ከገባሁበት አረንቋ መውጣት ተስኖኛል፤ ባመንኳቸው ሰዎች ክህደት ልቤ ክፋኛ ተጎድቷል፤ ይሆናል ያልኩት ቀርቶ ያላሰብኩት ሆኗል፤ ቃል የማይገልፀውን ህመም በልቤ ሸሽጊያለሁ፤ ግን ከጌታዬ ውጪ ምን ምሸሽበት፣ ምን ምከለልበት፣ ምን የምሽርበት አለኝ?! ..የዚህ ሁሉ ፈጣሪ እሱ !..እሱ እንዳረገ ያርገኝ ..» ተብሎም ይነበበኛል
-¤አንዳንዴ 'አልሐምዱሊላህ'
"በጣም ደስተኛ ነኝ፤ ነገሮች እንዳሰብኳቸው እየሄዱልኝ ነው፤ ኧረ እንደውም ካሰብኩት በላይም ሆኖልኛል፤ ጭንቄ ሁሉ በአሏህ ፍቃድ ተወግዷል፤ ለደስታዬ ለከት አጥቼ..ደስታዬን ምገልፅበት ቃል አጥቻለሁ፤ የዚህ ሁሉ አድራጊ እና ከሳች አሏህ ነው፤ ታድያ ይህን ስሜት 'አልሐምዱሊላህ' ከሚለው ቃል ውጪ ምን ይገልፅልኛል" የሚል መስሎም ይሰማኛል።
- ∞እና አልሐምዱሊላህ
ሁሉን አድራጊውን አላህ ከማመስገንም ባሻገር፤ የታመቁ ስሜቶችን ምንም ተጨማሪ ቃላት ሳይናገሩ መተንፈሻም ነው !
∞- አዎ አልሐምዱሊላህ
በምስጋና ከመዋደቅም ተሻግሮ፤ የአላህን ሁሉን ቻይነት እና ብቸኛ መሸሽያነት የመመስከሪያ ጥቅል ነው !
[...شَاكِرًا لِّأَنْعُمِهِ ۚ اجْتَبَاهُ وَهَدَاهُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ....]
«..ለጸጋዎቹ አመስጋኝ ነበር፤ መረጠው፡፡ ወደ ቀጥተኛውም መንገድ መራው፡፡..»
¤
አልሐምዱሊላህ🖤
11 060
⚠️ የድንበር ላይ ሕይወት አደጋ!
በአላህ ታዛዥነት (ዒባዳ) እና በእርሱ ትእዛዝ መጣስ (ወንጀል) መካከል የመኖር አንዱ ትልቁ አደጋ፤ የሕይወትህ ማጠቃለያ (ኻቲማህ) በየትኛው በኩል እንደሚሆን አለማወቅህ ነው።!
@halal_post
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
