1 331
订阅者
无数据24 小时
+97 天
+8030 天
帖子存档
#ዜና | በድሬዳዋ ስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የተዘጋጀ፥ አሰሪ እና ሰራተኛ የሚያገናኝ ዓውደ ርዕይ ተካሄደ።
በአስተዳደሩ ያለውን ስራ አጥነትን መቅረፍ አላማው ያደረገው ይህ ዓውደ ርዕይ፥ በተለያዩ የትምህርት መስኮች የተመረቁ ስራ ፈላጊዎችን ከአሰሪዎች ጋር በማገናኘት እንዲቀጠሩ ማድረግ ዋነኛ ግቡ መሆኑ ተገልጿል።
በአውደ ርዕዩ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ስራ፥ ክህሎት እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፥ ለዜጎች ምቹና ዘላቂ የስራ እድል መፍጠር እንደ አስተዳደር ትኩረት ከሚሰጣቸው ዓበይት ተግባራት መካከል አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ሮቤል አክለዉም ሥራ ፈላጊዎችን በማደራጀት፥ አሰሪ እና ሰራተኞች የሚገናኙበትን መድረክ በማመቻቸት እንዲሁም በውጭ ሀገር ሥምሪት ለዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚቻልባቸው መንገዶች መሆናቸውን ጠቅሰው፥ እነዚህን አማራጮች በመጠቀም የስራ አጥነት ቁጥርን ለመቀነስ እየሰራን ነዉ ብለዋል።
የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በበኩላቸው በስራ ፈላጊነት የተመዘገቡ 15 ሺህ ወጣቶች እንደሚገኙ አስታውቀው፥ ቢሯቸው አብዛኛዎቹን ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን ገልጸዋል።
የድሬዳዋ ነፃ ንግድ ቀጠና እና ኢንደስትሪ መንደር ሰፊ የሰዉ ሀይል እንደሚፈልጉ ይታወቃል ያሉት ወ/ሮ ፈጡም በየጊዜው ግንዛቤን በማዳበር አሰሪዎችን እና ወጣቱን በማገናኘት፣ የድሬዳዋን ልማት የምናፋጥንበት ጊዜው አሁን ነዉ ብለዋል።
ስራ ፈላጊ ወጣቶች በበኩላቸው ከማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ ቀጣሪ ተቋማትን በመፈለግ ሳንደክም፥ ከአሰሪዎች ጋር ፊት ለፊት እንድናገኝ እና በተማርነው የትምህርት መስክ ስራ እንድናገኝ አውደ ርዕዩ ጥሩ እድል ፈጥሮልናል ብለዋል።
በአውደ ርዕዩ ላይ 13 ቀጣሪ ድርጅቶች እንዲሁም 2 ኮሌጆችን ጨምሮ ስራ እና ሰራተኛ አገናኝ ፌዴሬሽኖች ተሳትፈዋል።
©️ Dire Tv
በድሬዳዋ ከተማ አሸዋ የገበያ ስፍራ በተከሰተው የእሳት አደጋ ጉዳቱ የደረሰባቸውን የንግዱን ማህበረሰብ መልሶ ለመማቋቋም ሁሉም የበኩሉን አስተዋፆ እንዲያበረክት ከታች በተዘረዘሩት የባንክ የሒሳብ ቁጥር ሁሉም ማህበረሰብ የአቅሙን ድጋፍ በማድረግ እንረባረብ።
Via Robel Getachew
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ከፍተኛ የሥራ አጥነት ቁጥር መቀነስን መነሻ በማድረግ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በመቋቋሙ በሀገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
በበጀት ዓመቱ ለ3.8 ሚሊዮን ዜጎች ሥራ ዕድል ተፈጥሯል፡፡
ከዚህ ቁጥር ውስጥ 3.4 ሚሊዮን ያህሉ በአገር ውስጥ የተፈጠረ ሲሆን በውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት ደግሞ 332 ሺ የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል፡፡
ሰኔ 27/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
የ2017 የፌዴራል በጀት 971.2 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2017 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት በጀትን 971.2 ቢሊዮን ብር አድርጎ አፀደቀ።
©️ etv
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደው 35ተኛ መደበኛ ስብሰባው በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ አጸደቀ፡፡
የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር የተከበሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በሥራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በዚህም በኢትዮጵና በኩዌት መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በሌሎችም መስኮች ጠንካራ ትስስር ተፈጥሮ የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሁለቱ ሀገራት የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱ ዓላማ በሁለቱ ሀገራት መካከል በሥራ ስምሪት መስክ ያለውን ትብብር ለማጠናከርና ህጋዊ ማዕቀፍ ለማዘጋጀት እንዲሁም በኩዌት የሚገኙ ዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ረቂቅ አዋጁ ወደ ሁለተኛ ንባብ ተሸጋግሮ አዋጅ ቁጥር 1337/2016 ሆኖ በሙሉ ድምጽ መጽደቁን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሰኔ 26/2016 ዓ.ም
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
በድረገጽ፡- http://mols.gov.et/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/MolsFDRE
ቴሌግራም፦https://t.me/fdre_mols
ቲክቶክ:- tiktok.com/@mols_official
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት https://lmis.gov.et
ለኮሌጅና ዩኒቨርስቲ ምሩቃን በሙሉ
****
የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ "ሥራና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚቢሽን(Job Fair)" የፊታችን አርብ ሰኔ 28/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በድሬዳዋ ወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ሁለገብ ሜዳ የሚካሄድ ይሆናል።
በዚህም ስራ ፈላጊ ምሩቃን የተለያዩ ድርጅቶች በቅጥር ሥራ የምታገኙበትን ሁኔታ ሊያመቻቹ እናንተን ስለሚጠብቁ የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን በመያዝና በአካል በመገኘት የዕድሉ ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
የድሬዳዋ አስተዳደር
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
+6
“እራስን ለመቻል እና ከጠባቂነት ለመላቀቅ እዲቻል ክህሎት መር የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል፡፡”
አቶ ሰልሃዲን አብዱልሃሚድ
የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች "ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት አደረጉ።
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱትና ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ የሰጡት የኮሌጁ የውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን አቶ ሰልሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆን በንግግራቸውም እንደ አገርም እንደ ተቋም የተጀመሩ የልማት ስራዎች ወደፊት እንዲቀጥል ለማድረግ በተቋም ደረጃ በርካታ ማሽነሪዎች እንዲሁም በእውቀት እና በክህሎት የዳበረ የሰው ሃይል ያለበት ኮሌጅ ውስጥ እንደመሆናችን መጠን የአቅማችንን ሰርተን በላባችንና በደማችን አገራችን በልማት ወደፊት እንድትሄድ በጋራ መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ከሌላው ሳንጠብቀወ በተገቢው መንገድ እየሰራን አገራችን በልማት እና በብልጽግና ወደፊት እንድትሄድ ክህሎት መር የስራ እድል ፈጠራ ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን በእለቱ የቀረበውን የውይይት ሃሳብ እንደ ኮሌጅ እንዲሁም እንደ ከተማችን ተጨባጭ ሁኔታ በማስተሳሰር ሊተገበር እንደሚገባ ከተሳታፊዎች አስተያየት ተሰጥቷል፡፡
የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጁ ኮምኒኬሽን
ሰኔ 25/2016 ዓ.ም ድሬዳዋ
"ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች ውይይት አደረጉ።
በዚህም ከተረጂነት ለመላቀቅና በምግብ እራስን ለመቻል አገራዊ መግባባትን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑና በተረጂነት ተጨባጭ ለውጥ ባለመመዝገቡ ዜጎች አመለካከት በመቀየር አቅምን በማቀናጀትና በመደጋገፍ በተለይም የዘርፉን ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ማጠናከር እንደሚገባ የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል።
በመድረኩ ተሳታፊ ለሆኑ አመራሮችና ሠራተኞች በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን አገራዊ ዕሳቤውና አቅጣጫውን እንደ አስተዳደሩ ተጨባጭ ሁኔታ በማዘጋጀት ወደ ስራ ለመግባት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንዲሰጠው አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን አክለውም ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
"ከተረጂነት አስተሳሰብ ለመላቀቅና በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ" በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችና ሠራተኞች ውይይት አደረጉ።
በዚህም ከተረጂነት ለመላቀቅና በምግብ እራስን ለመቻል አገራዊ መግባባትን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑና በተረጂነት ተጨባጭ ለውጥ ባለመመዝገቡ ዜጎች አመለካከት በመቀየር አቅምን በማቀናጀትና በመደጋገፍ በተለይም የዘርፉን ተጨባጭ ሁኔታ በመረዳት ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ማጠናከር እንደሚገባ የቢሮው ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል።
በመድረኩ ተሳታፊ ለሆኑ አመራሮችና ሠራተኞች በቀረበው ሰነድ ላይ ሰፊ ውይይት ያደረጉ ሲሆን አገራዊ ዕሳቤውና አቅጣጫውን እንደ አስተዳደሩ ተጨባጭ ሁኔታ በማዘጋጀት ወደ ስራ ለመግባት ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ የሚያስችሉ ስራዎች ትኩረት እንዲሰጠው አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን አክለውም ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 25/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የአስተዳደሩን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የስርዓተ-ስልጠና መሳሪያዎችን ስርጭት፣ አጠቃቀም፣ አተገባበር እና ተግዳሮቶች የሚዳስስ ጥናት ተደረገ፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ ከክልልና የከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በሁሉም የትኩረት መስኮች ከደረጃ አንድ እስከ አምስት የስርዓተ ትምህርትና የስልጠና መሳሪያዎች በአዲስ መልክ በማዕከል በማዘጋጀት እና በማስተቸት አሰራጭቶ ለትምህርትና ስልጠናውም ተደራሽ በማድረግ ለኢንዱስትሪዎች የሰው ሃይል ልማቱን በእውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት የዳበረ በየጊዜው አዲስ ከሚፈጠሩ ክህሎቶች እና እውቀቶች እራሱን በማላመድ ምርታማነት ለማሳደግ በሚያስችል ለስልጠና እንዲውል መደረጉ ይታወቃል፤
ይህንን መሠረት በማድረግ በአስተዳደሩ የሚገኙ አሰልጣኝ መምህራንን አቅም በመጠቀም እነዚህ በፌደራል ደረጃ በማዕከል ተዘጋጅተው የተሰራጩ የውጤት ተኮር መተግበሪያ መሳሪያዎች ውስጥ አንዱ የሆነውን የስርዓተ-ስልጠና መሳሪያዎችን ሰርጭት፣ አጠቃቀም፣ አተገባበር እና ተግዳሮቶችን ምን እንደሚመስል በጥናት በማረጋገጥ Assessment of outcome-based training tools in technical vocational institute in Dire Dawa Administration በሚል ርዕስ የተጠና ጥናት ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ እንዲፀድቅና የተመላከቱ የመፍትሔ ሃሳቦችን በመውሰድ ስራ ላይ እንዲውል አቅጣጫ መቀመጡን የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት የሆኑት አቶ ጀማል አደም ገልጸዋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 24/2016 ዓ.ም
ድሬዳዋ
Repost from E-LMIS - ብቁ
🌏ለውጭ ሃገር የሥራ ስምሪት ተመዝግባችሁ በመጠባበቅ ላይ ላላችሁ ዜጎች!
የሥራና ክህሎት ሚንስቴር የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይልን ባለፉት ሁለት ዓመታት ወደ 4 የመዳረሻ ሃገራት የሁለትዮሽ ስምምነት በመፈጸም ዜጎች መብታቸው፣ ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ እንዲሰማሩ ሲደረግ ቆይቷል።
አሁን ደግሞ ዜጎች ለሥራ የሚሄዱባቸውን የመዳረሻ ሃገራት በማስፋት ዜጎች በሰፊው የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ ከተጨማሪ ሁለት ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል።
በአሁኑ ሰዓት ሃገራችን ስምምነት በመፈጸም የሰለጠነ እና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል የምታሰማራባቸው የመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት፣ ሳውዲ አረቢያ፣ ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ፣ ኳታር፣ ጆርዳን፣ ሊባኖስ እና ኩዌት ሲሆኑ በአውሮፓ እና በኢሺያ ደግሞ ከተለያዩ የሰው ሃይል ፍላጎት ካላቸው ካምፓኒዎች ጋር ስምምነት በመፈጸም በሚያቀርቡት ጥያቄ እና መስፈርት መሰረት የሰለጠነ የሰው ሃይል እያሰማራ ይገኛል።
በመሆኑም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከቴክኒክና ሞያ ኮሌጆች ተመርቃችሁ ሲስተሙ ላይ ተመዝግባችሁ ለውጭ ሃገር የስራ ስምሪት በመጠባበቅ ላይ የምትገኙ ዜጎች በተለያየ ሃገር በሚገኙ ቀጣሪ ድርጅቶች ስትመዘግቡ ያስገባችሁትን የተለያዩ መረጃዎች ማየት እንዲችሉ የሲስተም አክሰስ የተሰጣቸው በመሆኑ ቀጣሪ ድርጅቶቹ መረጃዎቻችሁን በማየት ለስራ እስኪመርጧችሁ በትዕግስት እንድትጠባበቁ እንዲሁም ያልተሟላ መረጃ ያላችሁ ዜጎች መረጃዎቻችሁን እንድታሟሉ እናሳስባለን።
ለተመዘገባችሁ መልካም ዕድልን እንመኛለን። ላልተመዘገባችሁ ዜጎች በመመዝገብ ዕድላችሁን እንድትሞክሩ እናሳስባለን።
✨ብቁ ሰራተኛ • ብቁ ቀጣሪ • ብቁ ውሳኔ ሰጪ!
💼የሥራ ባለቤት እርስዎ ኖት!
የ2016 ዓ.ም የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም "ብቃት" የወጣቶች ስራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም የስራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ፡፡
በመድረኩም የቢሮውና በአስተዳደሩ የሚገኙ አንድ ማዕከላት አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡ በግምገማ መድረኩም አንድ ማዕከላት አመታዊ የሥራ አፈጻጸማቸውን አቅርበው ባቀረቡት አፈጻጸም ላይ በመነሳት ሀሳብ አስተያየት ተሰጥቶ ያለባቸውን ክፍተትም ለማሟት ያግዝ ዘንድ የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ለዜጎች የስራ እድልን በመፍጠር አሁን ያለውን የሥራ አጥ ቁጥር ለመቀነስና የስራ ባህልን በማጎልበት የሚያስፈልጓቸውን የሙያና የክህሎት ስልጠናዎች ወስደውና ወደ ስራ እንዲሰማሩ በማመቻቸትና ራሳቸውን ከስራ አጥነት እንዲያላቅቁ በማድረግና በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡
በመድረኩም ላይ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በቢሮ እና በአንድ ማዕከላቱ መናበብ የተሰሩ መልካም ስራዎችን አበረታተው በቀጣይ በተለይ ዋና ዋና የስራ እድል የመፍጠሪያ የስራ ዘርፎች ማለትም በግብርና በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ ስራ ፈላጊዎችን በቋሚነት ወደ ሥራ ከማሰማራት አንጻር ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የሥራ ክህሎትና ቴክሎጂ ልማት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ሰኔ 23/2016 ዓ.ም
ሐረር
