ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

前往频道在 Telegram
1 321
订阅者
+124 小时
+67 天
+14830 天
帖子存档
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ለተቀበላቸው ሰልጣኞች የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና እየሰጠ ይገኛል:: የህይወት ክህሎት(Life skill )ስልጠናው ብቁ በሆኑ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህራን አማካኝነት ለቀጣይ 3ቀናት ለአዲስ ሰልጣኞች እየተሰጠ እንደሚቆይ የተገለፀ ሲሆን ይህ ስልጠናም ሰልጣኞች የቀጣይ ህይወታቸውን በእቅድ እዲመሩ እንዲሁም ራሳቸውን ፈልገው እንዲያገኙና ስልጠናቸውን በዓላማ እንዲሰልጥኑ የሚያስችላቸውን ክህሎት የሚያገኙበት ስልጠና እንደሆነም ተገልፇል:: ሰልጣኞቹ የህይወት ክህሎት ስልጠናቸውን አጠናቀው ሲጨርሱ በቀጣይ የEntrepreneurship ስልጠና የሚወስዱ መሆኑም ተገልፇል:: ኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም

የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሀገር ውስጥ አልፎ በአለም ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ ስልጣኛችን እያፈራ እንዳለ ገለጸ፡፡ #ዜና| የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ቅበላ መርሃ ግብር በዛሬው እለት አከናወነ፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊና የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ዳይሬክተር የሆኑት ክብርት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ በንግግራቸውም ድሬዳዋ ከተማችን የኢንዱስትሪ ከተማ እንደመሆኗ መጠን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ውስጥ ይህን ኢንዱስትሪ የሚያንቀሳቅስ ባለሙያ ማፍራት የሚጠበቅብን ዋና ስራ ነው ያሉ ሲሆን፤ ወ/ሮ ፈጡም አያይዘውም በዛሬው እለት በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስልጠና ለመውሰድ የተመዘገባችሁ የከተማችን ወጣቶች ይህንን መልካም እድል በመጠቀም እራሳችሁን በእውቀትና በክህሎት ልታጎለብቱ ይገባል ብለዋል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሀገር ውስጥ አልፎ በአለም ተወዳዳሪ መሆን የሚችሉ ስልጣኛችን እያፈራ ነው ያሉት ደግሞ የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ናቸው፡፡ አቶ ሰለሃዲን አያይዘውም ሙያ የማይነጥፍ ሀብት ነው፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ደግሞ ፍላጎትና ተሰጥዎን ወደ ወደማይነጥፍ ሀብትነት የሚቀይር ትልቅ መንገድ ነው ብለዋል፡፡በመጨረሻም ኮሌጁን በመምረጥ እውቀትና ክህሎትን ፍለጋ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስለተመዘገባችሁ እጅግ ደስተኛ ነኝ በእውቀትና ክህሎት ሰልጣኞችን እንዲዳብሩ ከማድረግ በዘለለ ኢኮኖሚው ላይ ትልቅ ተጠቃሚ እንድትሆኑ በርካታ ስራዎችን የምንሰራ ይሆናል ብለዋል፡፡ በዛሬው እለት በኮሌጁ ከተደረገው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በተጨማሪ በPsychometric Test ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ የተከናወነ ሲሆን ከግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሩ በማስቀጠል በኮሌጁ ትምህርትና ስልጠና ለመውሰድ ለተመዘገቡ ሰልጣኞች የመጀመሪያ ዙር የPsychometric Test መስጠት ተችሏል፡፡በቀጣይ ቀናትም አዲስ የሚመዘገቡ እዲሁም በምዝገባ ሂደት ላይ ላሉም ሰልጣኞች ሁለተኛ ዙር ፈተና የሚሰጥ ይሆናል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 26/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከ ከEntrepreneurship Development Inistitut(EDI) ጋር መተባበር በBusiness Incubation center ዙሪያ ለሚመለከታቸው ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች ስልጠና ሰጠ:: ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የቴክኒክና ሙያ ኤጀንሲ ሀላፊና የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ል ሀላፊና ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ በንግግራቸውም የቴክኒክና ሙያ ዘርፋችን ክህሎት መር የስራ እድልን የሚመራ በመሆኑ ወጣቶች ቢዝነሳቸውን እዚሁ ኮሌጆቻችን ውስጥ እንዲያጎለብቱ ማድረግ ይጠበቅብናል ያሉ ሲሆን አክለውም ሰልጣኞች ተሰጥዕኦዋቸውን እያሳደጉ ከቢዝነሱም ተጠቃሚ የሚሆንበትን የኢንኩቤሽን ማዕከል እንዲፈጠር ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ስልጠና የተዘጋጀበት አላማም ይህኑ ታሳቢ እድርጎ እንደሆነም ገልፀዋል:: EDI ወደ እኛ ዘርፍ ከተቀላቀለ ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስራዎች በመስራት ዘርፉ ላይ መነቃቃት እየፈጠረ እንደሚገኝ የገለፁት ደግሞ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በ2018 ከኢንስቲትዩቱ ጋር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን በጋራ ለማከናወን ሰፊ እቅድ መያዙንም ገልፀዋል:: ስልጠናው ከሁለቱ ፖሊ ቴክኒኮች እና ከኤጀንሲ ለተወጣጡ ባለሙያዎች እንዲሁም አስተባባሪዎች የተሰጠ ሲሆን በዚህ ስልጠናም የBusiness Incubation center (BIC) ታሪካዊ አመጣጥ/አጀማመርና ፅንሰ-ኃሳብን ጨምሮ የቢዝነስ ኢንኩቤሽን ሴንተር ለማቋቋም እና ለማስተዳደር  መከተል የሚያስፈልገውን መሰረታዊ መርሆዎች ን ከEDI በመጡ አሰልጣኞች አማካኝነት በጥሩ አቀራረብ ለተሳታፊዎች ስልጠናውን መስጠት ተችሏል:: በዛሬው እለት ለባለሙያዎችና አስተባባሪዎች የተጀመረው ስልጠና ነገም ቀጥሎ የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይ ለኮሌጁ ፑል አመራር አባላትና ለተመረጡ ሰልጣኝ ተማሪዎች የEntrepreneurship ስልጠና በመስጠት እንደሚቀጥልም ማወቅ ተችሏል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

ዜጎችን በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ የሚፈጠሩ በርካታ እድሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ  በክህሎት ልማቱ አቅጣጫ በሚደረገው ርብርብ የወላጆች እና የአካባቢው ማህበረሰብ ሚና የላቀ መሆኑ ተገለፀ:: የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስለ አጠቃላይ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ እንዲሁም የ2018 ዓ.ም የአዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎችን ቅበላ አስመልክቶ ለአስተዳደሩ ወረዳዎች የብሎክ አደረጃጀት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጀ:: የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ባስተላለፉት መልዕክት ያደጉ ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት እድገት መነሻ የሆናቸው በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ያሳደሩት እምነትና ዘርፉ ላይ በሰሩት ጠንካራ ስራ መሆኑን ጠቅሰው የአስተዳደሩን ነዋሪ በዚህ ረገድ ግንዛቤ ተፈጥሮለት የክህሎት ስልጠናዎች ላይ እንዲሰማራ እንዲሁም እንዱስትሪውን እንዲያንቀሳቅስ የማድረጉ ተግባርና ኃላፊነት የሁላችንም ድርሻ ነውም ብለዋል:: በመድረኩ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዘርፍ ገጽታ ግንባታ የአካባቢ ማህበረሰብ ውይይት በሚል ሃሳብ ሰነድ የቀረበ ሲሆን በማጠቃለያውም ከመድረኩ የተነሱ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ በተሳታፊዎች በርካታ ሀሳቦች ላይ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ በቅንጅት በሚሰሩ ተግባራት ላይ ከመግባባት መድረስ መቻሉን በቢሮው የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደን ገልጸዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኮሌጁን የግዢ ስርአት ለማዘመን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ በመሆን ሊሰሩ ይገባል ተባለ፡፡ #ዜና|በድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአለም ባንክ የግዢና ውል አስተዳደር ላይ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና በዛሬው እለት ተጀመረ፡፡ በስልጠናው ማጀመሪያ ላይ በመገኘት መድረኩን የከፈቱት የኮሌጁ EASTRIP ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ አሽረፊያ አብዲ እንዳሉት ይህ በዛሬው እለት ለሁሉም የኮሌጁ ባለድርሻ አካላት እየተሰጠ የሚገኘው ስልጠና በአለም ባንክ የግዢ ስርአት እና ውል አስተዳደር ላይ ትኩረቱን ያደረገ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ነው ያሉ ሲሆን የኮሌጁን የግዢ ስርአት ለማዘመን ሁሉም ባለድርሻ አካለት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡ወ/ሮ አሽረፊያ አያይዘውም ይህ ስልጠና ሲጠናቀቅ በኮሌጁ ውስጥ የሚደረጉ የግዢ አሰራራችን ላይ የተሸለ ለውጥ ማምጣት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ በዛሬው እለት የተጀመረው ይህ ስልጠና በአለም ባንክ ከፍተኛ የግዢ ባለሙያ በመሆን እየሰሩ ባሉ ኢ/ር ቀጀላ ፉፋ አማካኝነት በ EASTRIP ፕሮጀክት አስተባባሪነት እየተሰጠ ሲሆን በስልጠናው ላይ ኮሌጁ ኃላፊዎች፣የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች፣የግዢና ፋይናንስ ባለሙያዎች፣የጨረታ አጽዳቂ ባለሙያዎች እንዲሁም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ ለወቅታዊ ትኩስ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መረጃ You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC) Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute Telegram: t.me/Dire Dawa Polytechnic College TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞቹ የPsychometric Test እየሰጠ ይገኛል:: ይህ የPsychometric Test በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠ አቅጣጭ መሰረት በኮሌጃችንም ተ
+9
የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞቹ የPsychometric Test እየሰጠ ይገኛል:: ይህ የPsychometric Test በሀገር አቀፍ ደረጃ በተሰጠ አቅጣጭ መሰረት በኮሌጃችንም ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኝ ሲሆን በኮሌጁ የICT ዲፓርትመንት በሚገኝ Lab በOnline አማራጭ አዲስ ኮሌጁን ለሚቀላቀሉ ሰልጣኞች እየተሰጠ ይገኛል:: ፈተናው አዲስ ሰልጣኞች ከራሳቸው፣ከቤተሰቦቻቸውና ከጓደኞቻቸው ጋር ተመካክረው ለመምረጥ ከሚመጡት የስልጠና ዘርፍ በተጨማሪ የሰልጣኞችን የግንዛቤ፣ የስብዕናና ያላቸውን ተሰጥኦ የሚያመላክታቸው በመሆኑ ለወደፊት ውጤታማ የሚሆኑበትን የስልጠና ዘርፍ ከወዲሁ አውቀው እንዲወስኑ የሚያግዛቸው መሆኑም ተገልፇል፡፡ በእለቱ የኮሌጁ ዲን የሆኑት አቶ ታደለ አሰፋ የPsychometric Test አሰጣጡን በአካል ተገኝተው ያስጀመሩ ሲሆን ፈተናውን ለሚወስዱት ሰልጣኞችም ግንዛቤ የመስጠት ስራ አከናውነዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅምት 25/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

የ2018 ዓ.ም የአዲስ ተማሪዎች ቅበላ ሂደት አፈጻጸም አተገባበር ምልከታ ተደረገ። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊና የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እና በቢሮው የሰልጣኝ ልማትና ተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደን በኮሌጆች በመገኘት የአዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች የምዝገባ ሂደትን ጎብኝተዋል። የምዝገባ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑን የተመለከቱ ሲሆን ዜጎች ግንዛቤ ተፈጥሮላቸው ወደ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች መምጣታቸው የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው ምዝገባ ሊጠናቀቅ የቀረው ጊዜ አጭር በመሆኑ ያልተመዘገቡ እንዲመዘገቡ ጥሪ አስተላልፈዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ

💡ተሰጥዎንና ፍላጎትዎን ወደማይነጥፍ ሀብት መቀየር ይፈልጋሉ? 🛠ሙያ የማይነጥፍ ሀብት ነው፡፡ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ደግሞ ፍላጎትና ተሰጥዎን ወደ ወደማይነጥፍ💰ሀብትነት ቀይረው ወደ ስኬት የሚወስድዎ አውራ ጎዳና ነው፡፡ #አድራሻችን ከድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ወደ ኤርፖርት በሚወስደው መንገድ 150 ሜትር ላይ እንገኛለን

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም የስልጠና ዘመን አዲስ ለተቀበላቸው ሰልጣኝ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እና የኦረንቴሽን መድረክ አካሄደ:: ለሰልጣኝ ተማሪዎቹ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የስራና ክህሎት ቢሮ ም/ል ሀላፊና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ሀላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ሲሆኑ በመልዕክታቸውም ወጣቶች የቴክኒክና ሙያ ዘርፉን መርጣችሁ እዚህ በመገኘታቸው እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን ወቅቱ ሚጠይቀውን ምርጫ አውቃችሁ በቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለመሰልጠን ዘርፉን በመቀላቀላችሁ እጅግ እድለኞች ናችሁና እንኳን ደስ አላችሁም ብለዋል:: ለአዲስ ገቢ ሰልጣኝ ተማሪዎቹ ኦረንቴሽን የሰጡት የኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ሲሆኑ በቅድሚያ ሰልጣኞች የልዩ ክህሎት ባለቤት ወደሚያደርጋችሁ ኮሌጃችሁ እንኳን በደህና መጣችሁ ያሉ ሲሆን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ለመሰልጠን እዚህ የተገኛችሁ ወጣቶች አሁን የምትገኙበት እድሜ በራሳችሁ ውሳኔ ምትወስኑበት እድሜ በመሆኑ ትክክለኛውና ጠቃሚውን መንገድ ለይታችሁ በመምረጥ የወጣትነት ጊዜያችሁን ውጤታማ ነገር ላይ እያሳለፋችሁ መሆኑን ከወዲሁ እርግጠኛ መሆን ይገባችኃልም ብለዋል:: የኮሌጁ ዲን አክለውም በኮሌጁ የትኩረት ዘርፍ ተብለው የተያዙና በዓለም ባንክ ፕሮጀክት ጭምር የሚደገፉ ሶስት የትኩረት ማዕከል የሆኑ የሙያ ዘርፎች መኖራቸውን ለሰልጣኞች ገልፀው እነርሱም የማኑፋክቸሪንግ ፣ የኤክትሪካል/እሌክትሮኒክስ እና የአውቶሞቲቭ ዘርፎች መሆናቸውን በመጥቀስ በእነዚህ ሶስት የትኩረት ዘርፎችን ምርጫቸው አድርገው ለሚቀላቀሉ ሰልጣኞች ከየትኛውም ዘርፍ በተለየ ሁኔታ እድለኞችና የላቀ ተጠቃሚ መሆናቸውንም በመድረኩ አብስረዋል:: በተጨማሪም ለአዲስ ገቢ ሰልጣኞች ስለ Psychometric Test አወሳሰድ ግንዛቤ የተፈጠረላቸው ሲሆን ሰልጣኝ ተማሪዎቹ በቀጣዮቹ 3ቀናት በኮሌጁ በሚኖራቸው ቆይታ የህይወት ክህሎት(Life Skill) ስልጠና እንደሚወስዱ የተገፀ ሲሆን ጎን ለጎንም የPsychometric Test የሚውስዱ ይሆናል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር  የሚገኙ ሶስት ፖሊቴክኒክ ኮሌጆችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ  በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ባሳየው ከፍተኛ የስራ አፈፃፀምን ጨምሮ አጠቃላይ በኮሌጁ ባስመዘገባቸው ተጨባጭ ውጤቶች ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ የሚገኙ በርካታ ኮሌጆች ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማችን እየመጡ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው እለትም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ፣ አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ እና ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የኮሌጅ ዲኖች እና የፕሮጀክት አስፈፃሚዎችን ጨምሮ ከአዲስ አበባ አስተዳደር ስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ ማዕረግ የምክትል ቢሮ ሀላፊና በቢሮው የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ተገኝተው የፕሮጀክት አፈፃፀም እና የስራ ልምድ ልውውጥ አካሂደዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ ጉብኝት መርሃ-ግብር ወቅት የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ በEASE ፕሮጀክት ያሳየውን የላቀ የስራ አፈፃፀም ሂደትን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው ገለፃና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻነት በነበረው ውይይት ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው በሚገኘው ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች መደነቃቸውን ገልፀው በተለይም ኮሌጁ በEASE ፕሮጀክት አተገባበር ላይ በአጭር ጊዜ ያሳየው የላቀ የስራ አፈፃፀም በሌሎች አቻ ኮሌጆችም ጭምር ሞዴል ተደርጎ እንዲታይ ያስቻለው መሆኑንም ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ የፕሮጀክቱን ማስተባበርያ ቢሮ እና በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን እዚህ በኮሌጁ ያገኟቸውን በርካታ ልምዶችንም ወደራሳቸው ወስደው ተግባራዊ በማድረግ እንደሚጠቀሙባቸውም ገልፀዋል:: የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ጥቅምት 22/2018 ዓ.ም ድሬዳዋ