1 321
订阅者
+124 小时
+67 天
+14830 天
帖子存档
Repost from Dire Dawa Polytechnic College
#ምዝገባ ላይ ነን#mamedire_official1 #xhaka34 #diredawapolytechniccollege
ኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢንፍሌሽን እንዲቀንስ ማድረግ ችላለች!
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ አዲስ ምዕራፍ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ስልጠና ጥራትና አግባብነት፤ ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ለማሻሻል መሰረተ ሰፊ የሪፎርም አጀንዳዎችን ቀርፆ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
የዘርፉ የሪፎርም አዳዲስ እሳቤዎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና መስኩን ሳቢ ለማድረግ እና ሀገራዊ የሥራ ገበያውንና የልማት ፍላጎቱን መመለስ እንዲያስችል ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ሪፎርሙን ተከትሎ በዘርፉ ወደ ሥራ ከገቡ ስርዓቶችና አሰራሮች መካከል ዲጂታላይዝድ በሆነ መልኩ የሚተገበረው የሳይኮሜትሪክ ምዘና አንዱና ዋነኛው ነው፡፡
ምዘናው በዋናነት ዘርፉን በአዲስ መልክ ለሚቀላቀሉ አዲስ ሰልጣኞች የሚሰጥ ሲሆን ይህም ለሰልጣኞች፣ ለስልጠና ተቋማቱ እና ለሀገር ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ታሳቢ ተደርጎ የተቀረፀ ስርዓት ነው፡፡
ምዘናው የሰልጣኞቹን ፍላጎቶት ብቻ ሳይሆን ተሰጥኦና ዝንባሌን መሰረት በማድረግ ውጤታማ ሊሆኑባቸው የሚችሉ የሙያ መስኮች እንዲመርጡ ያግዛቸዋል። ይህም ውድ ጊዜያቸውን ውጤታማ በማይሆኑበት የትምህርትና ስልጠና ዓለም ውስጥ እየማሰኑ እንዳያባክኑ ያደርጋል፡፡
ከዚህ ባሻገር የማሰልጠኛ ተቋማት የሰልጣኞች ምደባ ሥራቸውን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመምራት፣ በኮሌጁ የአቋራጭ ምጣኔን ለመቀነስ እና መረጃ ላይ የተመሰረተ ውጤታማ የካውንስሊግ ሥራ እንዲሰሩ የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡
ከሁሉም በላይና ባሻገር ደግሞ የሥልጠና ጥራትና አግባብነት እንዲሁም ውጤታማነትን ከሥራ ገበያ ፍላጎቱ ጋር በማጣጣም ብቁ፣ በቂና ተወዳዳሪ ሰልጣኞችን በማፍራት እንደ ሀገር ለሥራ ገበያው ፍላጎት ምላሽ የሚሰጥ የቴክኒክና ሙያ ስርዓት ባለቤት እንድንሆን ያደርገናል፡፡
ይህም ምርትና ምርታማነትን በማሻሻልና ቅልጥፍና በመጨመር ሀገራዊ ተወዳዳሪነታችንን በሁሉም መስክ በማሳደግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ ያስችላል፡፡ ከዚህ ባሻገር የሥራ አጥነት ምጣኔን ትርጉም ባለው መልኩ ከመቀነስ አኳያም ሚናው የላቀ ነው፡፡
በዚህ አዲስ የሪፎርም እሳቤ መሰረት በፓይለት ደረጃ የተመረጡ የፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የ2018 የስልጠና ዘመን አዲስ የሰልጣኞች ቅበላቸውን በተቀመጠው አግባብ ተግባራዊ እያደረጉ ይገኛል፡፡
የሳይኮሜትሪክ ምዘናውን መስጠት ከጀመሩ መካከልም በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኘው አንጋፋው የወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አንዱ ነው፡፡ ኮሌጁ እንዳስታወቀው ከጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዘናውን እየሰጠ ይገኛል፡፡
የሞጣ ፓሊክኒክ ኮሌጅም እንደ ወ/ሮ ስኂን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ሁሉ ከጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ምዘናውን ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ክህሎት ለሁለንተናዊ እድገትና ውጤታማነት ነው!
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
Repost from Ministry of Labor and Skills - Ethiopia
🚨 ከመወሰንዎ በፊት፣ ደጋግመው ያስቡበት!
❌መንገዶች ሁሉ ከአሰቡበት አያደርሱም!
🚫 ሕገ-ወጥ የሥራ ስምሪት ለከፋ የሰብዓዊ መብት ጥሰት፣ ለአካል ጉዳትና ሞት የሚያጋልጥ የጨለማ መንገድ ነው።
ሕጋዊ የሥራ ስምሪት አማራጮችን ብቻ በመጠቀም መበት፣ ደህንነትና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትዎን ያረጋግጡ!
✈️ለህጋዊና ደህንነቱ ለተረጋገጠ የሥራ ስምሪት:-
✅በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ ይመዝገቡ(lmis.gov.et)፣
✅የቅድመ ጉዞ ስልጠና ይውሰዱ፣
✅ስለሚሄዱበት ሀገር በቂ መረጃ ይኑርዎት፣
✅መበትና ግዴታዎን ጠንቅቀው ይወቁ፣
መነሻዎ ትክክል ካልሆነ መዳረሻዎ ፈፅሞ ትክክል ሊሆን አይችልምና በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን ሲያስቡ ህጋዊ አማራጮችን ብቻ ይከተሉ።
📞ለማንኛውም መረጃና ጥቆማ
👉9138 ነፃ የስልክ መስመርን ይጠቀሙ
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም ፤ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
ለወቅታዊ ትኩስ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር
Official Website: mols.gov.et
Facebook: https://web.facebook.com/MolsFDRE
Telegram: t.me/fdre_mols
TikTok: tiktok.com/@mols_official
Twitter / X: twitter.com/Jobs_ሚኒስቴር
WhatsApp: whatsapp.com/channel/0029VakCgcYIyPtTbPZtDW1y
ፔትኮ ኢትዮጵያ ማብቃት ፕሮጀክት ከሥራና ክህሎት ቢሮ ጋር በመተባበር ሶስት በፕላስቲክ መልሶ መጠቀም እና አንድ በወረቀት ቦርሳ ማምረት ዘርፍ የተደራጁ ማህበራት ድጋፍ ተደረገላቸው።
በዚህም ከአስተዳደሩ ወረዳ አንድ እና ሁለት የተደራጁ ስራ ፈላጊ ወጣቶችና ሴቶች በፔትኮ ኢትዮጵያ ማብቃት የተዘጋጀላቸውን ስልጠና በመውሰድ እና የስራ ማስጀመሪያ ዕቃዎች ድጋፍ እንዲሁም አልባሳት ርክክብ መደረጉ ታውቋል።
በመርሃግብሩ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ እና በቢሮው የኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉጌታ ሀ/ማርያም ተገኝተዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት በአጠቃላይ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ https://lmis.gov.et የሚከናወነው ምዝገባ እንቅስቃሴን አስመልክቶ ከወረዳ የአንድ ማዕከል ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ።
በዋናነት ምዝገባ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እሰከ አሁን የተመዝጋቢዎች ቁጥር የደረሰበት ደረጃ ተገምግሟል፤ በተለይም ስራ ፈላጊ፣ ስራ ያላቸው እና ኢንተርፕራይዞችን ምዝገባ በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የታየ ሲሆን በዚህም ሂደት የተመላከቱ ክፍተቶችን ለማስተካከልና በቀጣይ በሁሉም የወረዳ አንድ ማዕከላት ደረጃ ያለውን አፈጻጸም ለማሻሻል እንዲሁም ቁጥሩንም ከፍ ለማድረግ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የሥራ ዕድል ፈጠራውን የተሳለጠ ለማድረግ የሚረዳው ይህ የዲጂታል ስርአት ተዘርግቶ ወደ ሥራ መገባቱ የሚታወቅ ሲሆን በዚህም ባለሙያዎቹ E-LMIS በዘርፉ ያመጣውን ለውጥ በመረዳት የምዝገባውን ውጤታማነት ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መግባባት መፈጠሩን የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና አንድ ማዕከል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ ተናግረዋል።
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት በሁለቱ የመንግስት ኮሌጆች እና የግል ኮሌጆች ላይ ኢንስፔክሽን አካሄደ።
በዋናነት ኮሌጆቹ ህጋዊ የስልጠና ፍቃድ ያገኙባቸዉ የስልጠና ፕሮግራሞች፤ የንድፈ ሀሳብ እና የተግባር ምዘና በአግባቡ ስለመከናወኑ፤ ዉጤቶች በመመርያዉ መሠረት ሪፖርት ስለመደረጋቸዉ እንዲሁም የ2018 ዓ.ም ቅድመ ዝግጅት ስራዎች በተለይም የእቅድ ዝግጅት፤ የሰዉ ሀይል እና ግብዓት ማሟላታቸው ትኩረት ተሰጥቶበታል፡፡
በዚህም ኢንስፔክሽን ኮሌጆች የሚሰጡትን ትምህርትና ስልጠና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ እየተሰጠ ስለመሆኑ በማረጋገጥ የሚታዩ ችግሮችን በቀጣይ በአጭር ጊዜ በማስተካከል እርማት እንዲወስዱ ታሳቢ ያደረገ ነው።
የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ ስለ ኢንስፔክሽኑ የቴክኒክና ሙያ ስልጠናን ጥራት ለማምጣት ይህም ለዘርፉ እድገት አስፈላጊ በመሆኑ ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት መካሄዱን ገልጸዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
አጫጭር ስልጠና ለሚሰጡ ተቋማት የ2018 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠናዉን ጥራት ስታንዳርድ ለማስጠበቅ ክትትልና ድጋፍ ተደረገ፡፡
በዚህም ድጋፍና ክትትል የአጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማት የስልጠና ፍቃድ በተመለከተ በተሰጠው ፈቃድ ልክ እየሰሩ ስለመሆናቸውና ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖር ስልጠና የሚሰጥበት የሥልጠና ዘርፍ ላይ ማስተካከያ ለማድረግ በሚቻልበት እንዲሁም በእቅድ በመመራት ማሰልጠኛ ማንዋሎችና መሳሪያዎች በሚገባ መኖራቸውን ጨምሮ የአጠቃላይ ሰልጣኞችን መረጃ በማደራጀት ሰርተፍኬት የሚያገኙበትን አግባብ ተመልክቷል፡፡
በድጋፍና ክትትሉ ወቅትም ከተቋማቱ ለኤጀንሲው የሚቀርቡ ቅሬታዎቸ፤ የሚሻሻሉ አሰራሮችና አሰተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ስር የሚገኘው ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ የአሰልጣኝ ልማትና ተቋማት ጥራት ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታሪኩ ለገሰ እንደተናገሩት ይህ የድጋፍና ክትትል ልክ መደበኛ ስልጠና እንደሚሰጡ ተቋማት ሁሉ አጫጭር ስልጠና የሚሰጡ ተቋማትም ዜጎችን በማሰልጠን የሚያበቁ በመሆናቸው ትምህርትና ስልጠናው ጥራት ስታንዳርድ ለማስጠበቅ በቅርበት በመከታተል መደገፍ አስፈላጊነቱ ቀላል የማይባል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
ለአስተዳደሩ የሚዲያ አርሚ አባላት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
በድሬዳዋ አስተዳደር ለሚገኙ ለሚዲያ አርሚዎች የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ላይ በተለይም የ2018 ዓ.ም አዲስ ሰልጣኝ ተማሪዎች ቅበላን ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ተዘጋጅቷል።
በአስተዳደሩ የሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን የስልጠናውን አላማ አስመልክተው እንደገለፀት የዘርፉን አውድ የተረዳ እና የማህበራዊ ሚዲያ ቴክኒካል እውቀት ካለው የሚዲያ አርሚ ጋር በቅንጅት መስራት ውጤታማ የሚያደርግ መሆኑን አመላክተዋል።
በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሰልጣኝ ልማትና የተቋማት አቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጀማል አደን በአስተዳደሩ የሚገኙ የሚዲያ አርሚዎች የአስተዳደሩን ነዋሪ ተጠቃሚ ለማድረግ ስለ ቴክኒክና ሙያ ዘርፍ መረጃዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽነቱን ለማስፋት ባገኙት ግንዛቤ እንደከዚህ ቀደሙ በንቃት እንዲሳተፉ አሳስበዋል፡፡
የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት
ጥቅምት 17/2018 ዓ.ም
ድሬዳዋ
