ፍኖተ መጻሕፍት 📚FinoteBooks1623 ➮አድራሻ አዲስ አበባ ፒያሳ ገነተ ፅጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ማኅበረ በኩር ሰንበቴ ፊት ለፊት ለበለጠ መረጃ ፦በ0913083816 ይደውሉ።
前往频道在 Telegram
📚ፍኖተ መጻሕፍት @finoteBooks1623 ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 t.me/FinoteBooks1623
显示更多3 477
订阅者
+124 小时
-47 天
+6730 天
帖子存档
📖#ሰፌልያ📖
.....#ቅዱስ ጳውሎስ የቤተ ክርስቲያን ብርሃን ፣ የክርስቶስ ምርጥ ዕቃ ፣ የመናንያን አርኣያ ፣ የሰባኪያን መምህር ፣ የአገልጋዮች ሁሉ አርማ ነው:: ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ መጻሕፍትን የጻፈውን ይህንን ሐዋርያ ማወቅ ሐዲስ ኪዳንን ለማወቅ እጅግ ወሳኝ የሆነ ቅድመ ሁኔታ ነው::
#መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅን ኆኅተ ሰማይና በመሳሰሉ መጻሕፍቶቻቸው የቤተ ክርስቲያኒቱ ዘመነኛ የአማርኛ ሥነ ጽሑፍ ታሪክ ላይ አሻራቸውን ከተዉ ቀደምት ጸሐፍት መካከል አንዱ ናቸው:: በትንታግ አንደበታቸው በሰበኳቸው ድንቅ ትምህርቶቻቸውና "ስምሽን ጠርቼ መቼ አፍራለሁ?"ን በመሳሰሉ ውብ የዝማሬ ግጥሞቻቸው ብዙ የተጠቀምንባቸው መልአከ ሰላም ያሬድ አሁን ደግሞ የቅዱስ ጳውሎስን ሕይወት የሚዳስስ እና ከመጠራቱ እስከ ዕረፍቱ ድረስ ያለውን ሐዋርያዊ ጉዞ የሚያስቃኝ በደንብ የተደከመበት ሥራ ይዘውልን ብቅ ብለዋል:: ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ ይናገር ዘንድ ምርጥ ዕቃ እንደነበረ ይህ ሰፌልያ የተሰኘ መጽሐፍም መጽሐፍ ቅዱስ ጥናታዊ ይዘት ያለው ስለ ጳውሎስ ይናገር ዘንድ የተዘጋጀ ምርጥ ዕቃ ነው::
#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks162
📚ወላዲተ አምላክ በነገረ ድኅነት
...#በእውነት ከመጻሕፍት ተዋውቆ፡ መምህራንን ጠይቆ ምሥጢርን ከምሥጢር አራቆ፣ በብዕር አግዝፎ፡ በትዕግሥት ጽፎ ለትውልድ ማቅረብ ልዩ ዕድል /ስጦታ/ ነው:: ይህ መጽሐፍ ለአእምሮ ረቆ፣ ለአንደበት ርቆ ዕፁብ ለተነግሮ የሆነውን ነገረ ድንግል ማርያምን ከነገረ ድኅነት ጋር በማገናዘብ ከብሉያት፣ ከሐዲሳት፣ ከሊቃውንትና ከሌሎችም መጻሕፍት ለቅሞ በምሥጢር አጣጥሞ፣ በጥሩ አቀራረብ ቀምሞ እንደ ቅብዐ ዘይት ጨምቆ ይዞ ቀርባል፡፡ ስለሆነም በጥርጥር የጠወለገ ባለማወቅ የደረቀና ከጠለ ምሥጢር የራቀ ልብን ያለሰልሳል፤
✍️መጋቤ ሐዲስ ደጉ ዓለም ካሣ
[በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርስቲ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ መምህር]
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
📚#የብርሃን_እናት
◎14ተኛ ኅትም

እናቴ ማን ናት?
ጌታችን በወንጌል እናቴ ማን ናት? አለ። ለምን? እንድናውቃት ከፍ አድርጎ ሲገልጣት። ማቴ ፲፪:፵፰።
እናቱ ማን እንደኾነች ሲያጠይቅ አስከትሎ ይናገራል። “በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ ኹሉ፣ እርሱ ወንድሜ፣ እኅቴም እናቴም ነውና” ብሎ።
እናት ለመባል የአባቱን ፈቃድ ማድረግ እንዲገባ መስፈርቱን አስቀምጧል። እመቤታችን በዚህ መስፈርት መሠረት እናት ተብላ ለመጠራት አንደኛ እና ብቸኛ ናት። የሰማዩ አባቱን ፈቃድ በማድረግ የሚተካከላት ቀርቶ የሚመስላት የለምና። እግዚአብሔር አብ ልጁ ሰው እንዲኾን በፈቀደ ጊዜ እንበለ ዘርዐ ብእሲ ትወልጃለሽ መባልን ይኹንልኝ ይደረግልኝ ብላ የተቀበለች አይደለችምን?
ሊቁም እንጅ “እስመ በፈቃዱ ወበሥምረተ አቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ መጽአ ወአድኃነነ - በእርሱ ፈቃድ፣ በአባቱ ፈቃድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ መጥቶ አዳነን” ይላል። ቅዱስ ኤፍሬም በማክሰኞ ውዳሴ ማርያም።
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልንስ ያ ኹሉ ሙግት የገጠመው ፈቃዷን ለማግኘት አልነበረምን? ቁጡው መልአክ ገራም የኾነው ከመሽቆጥቆጥ በቀር ኃይለ ቃል ያላወጣው እንደ ቃልህ ይኹንልኝ የሚለውን ሥምረቷን እስኪሰማ አይደለምን?
ስለዚህ ለማንም የማይቻለውን ለእርሷ ብቻ የተሰጠውን እኔን ለመውለድ እሺ በጄ ብላ የአባቴን ፈቃድ የፈጸመች ናትና እናቴ መባል ይገባታል ብሎ በምስጢር ማክበሩን ልብ ይሏል።
ወልደ ዳዊት በሥጋ ወልደ ዮሴፍ በአሳዳጊነት ወልደ አብ በባሕርይ ይባላል። በእናት ወገን ግን ወልደ ማርያም ከሚባል በቀር ሌላ እናት የለውም።

#፭ተኛ እትም
📚#ምሥጢረ_ምሥጢራት-፩
#ምሥጢረ_ምሥጢራትን_እንደ ጎበኘኋት፡፡✍️ [በመምህር ኃይለ ማርያም ዘውዱ ዘቦሩ ሜዳ]
ዘመኑ በመጻሕፍት አቅርቦት በኩል ምቹ ነውና ብዙ መጻሕፍትን የማንበብ እድል ገጥሞኛል። ምሥጢረ ምሥጢራት ግን እንደ ሥያሜዋ ከሌሎች ለየት ብላ አግኝቻታለሁ፡ በምሥጢረ ሥላሴ ላይ ብቻ ትኩረት ማድረጓ አንድ ልዩ ነገር ሁኖ፣ ከዚያውም ዘንድ ወደ ባሕረ ምሥጢሩ ስባ ጎትታ የምታስገባና በጥሩ የሊቃውንት መቅዘፍያ እየቀዘፈች ብዙ ሰዎች ወደ አላዩት የምሥጢር ወደብ የምታደርስ፤ ከይዘት አንጻር ከተመዘነች በምጥቀትና በጥልቀት ለዘመናችን የመጀመሪያ የምትባል መጽሐፍ ናት፡፡ መጽሐፏን የምትመለከቱ ሁሉ፦ በትሐት ሰብእና፣ በንጹሕ ልቡና፤ በቅጥነተ ኅሊና ሁናችሁ እንድትመለከቷት ወንድማዊ ምክሬ ነው።
መልካም ንባብ!!
◉ በመ/ር ገብረ መድኅን እንየው እና በመ/ር መዝገበ ቃልገብረ ሕይወት ተዘጋጅቶ በሊቃውንት ተመርምሮ የቀረበ።
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
🌻 መስከረም 21 — እመ ብዙሃን 🌻▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬ 📖🕯️ ክርስቲያኖችን ሰብስባ የያዘች ሰፊ መጋረጃ ሐዋ 10፥11 ➜
እንኳን ለእመቤታችን ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ! 🌻 መስከረም 21 ስለ ሁለት ታላላቅ ምክንያቶች ይከበራል።
1ኛ፦ እመ ብዙሃን ማርያም
በ325 ዓ.ም. የነበሩ ሃይማኖትን ያቀኑ፣ ሃይማኖታቸውም የቀና 318ቱ ሊቃውንት አባቶቻችን አርዮስን ያወገዙበት፣ ክርስቶስን አምላክ፣ እመቤታችንንም Mother of God ብለው የመሰከሩበት ታላቅ በዓል ነው።
ከስሙ ትርጉም እንደምንረዳው፣ እመ ብዙሃን ማለት የብዙዎች እናት ማለት ነው። ይህም የሊቃውንቱን ብዛት ያመለክታል።
ታሪኩም እንዲህ ነው፦
አርዮስ ወልድ ፍጥረትን ለመፍጠር የተፈጠረ መሣሪያ እንጂ ፍጹም አምላክ አይደለም ብሎ ተነሳ። እንደውም አልበቃ ብሎት፣ ክርስቶስ ሰው ሲሆን ለሚዋሐደው ፍጡር ሥጋ የተነገረውን በማምታታት፣ ለመለኮት እንደተነገረ እየጠቀሰ ምእመናንን ግራ አጋባቸው።
የመናፍቃን አንዱ ችግራቸው የአንዱን ጥቅስ ለሌላው ያለ አውዱ ማምታታት ነው።
በዚህ ምክንያት በየሀገረ ስብከቱ የነበሩ ሊቃነ ጳጳሳት ተሰበሰቡ። ቁጥራቸውም በትውፊታችን 2448 መሆኑ ይነገራል። ከእነዚህ ውስጥ 318 አባቶች ክርስቶስ በመለኮቱ ከአብ ጋር አንድ ነው ሲሉ፣ ሌሎቹ ግን ያላፈሉት ክህደት የለም።
ይህን መጻፍ ያስፈለገው አባቶቻችንን በደንብ እንድናውቅ ነው። «አባቱን የማያውቅ ልጅ...» እንደተባለው እንዳንሆን ነው። አባቶቻችንን እንድናውቃቸው ይርዳን!
ከዚያ በኋላ ሊቃውንቱ አርዮስን በመጽሐፍ ቅዱስ ተከራክረው አውግዘው፣ «ሐዋርያት እንዲህ አላስተማሩም» ብለው፣ የክርስቶስ አምላክነት ከአብ ጋር አንድ ነው በሚል ታወጀ።
ይህ ማለት ግን ሙስሊም ወንድሞቻችን እንደሚሉት፣ ክርስቶስን ፈጣሪ ሳይሆን በኒቂያ ፈጣሪ አደረጉት ማለት አይደለም። ይልቁንም ራሱ ባለቤቱ፣ ቅዱሳን ሐዋርያት እና ሐዋርያውያን አበው ያስተማሩት ከአርዮስ ክህደት ተለይቶ ጸና፤ አባቶቻችንም አጸኑት ማለት ነው።
የንጹሐን አባቶቻችን በረከት ይደርብን! ✝️
ይህ ጉባኤ ኒቂያ በመባል የሚታወቅ ሲሆን፣ ቤተ ክርስቲያን ከምትቀበላቸው ሦስቱ ዓለም አቀፍ ጉባኤያት አንዱና የመጀመሪያው ነው።
እናም «እመ ብዙሃን ማርያም» የሚለው የሊቃውንቱን ብዛት ያመለክታል።
ሁለተኛ፦ በጸጋ የሁላችን እናት ስለሆነች «እመ ብዙሃን» የሚል ትርጉም ተሰጥቷታል።
«ሰው እናታችን ጽዮን» ይላል። መዝ. 86፥3።
2ኛ፦ የመስቀል በዓል ✝️
ሁለተኛው የመስቀል በዓል ነው። «መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ አኑር» በሚል መርህ፣ እንደ ትውፊታችን ንጉሣችን አጼ ዳዊት መስቀሉን ከእስክንድርያ አስመጥተው፣ በመንገድ ቢያርፉም፣ ልጃቸው በሀገራችን የነገሠው ሁለተኛው ቆስጠንጢኖስ፣ ማለትም አጼ ዘርዓ ያዕቆብ፣ መስቀሉን ወደ ግሸን ያገቡበት ነው።
ዛሬ ብዙ ሰው ወደዚያ የሚጎርፈው ምክንያትም ይህ ነው። መስቀሉም እንደገባ ሀገሪቱ የነበረባትን ቸነፈርና ረሃብ ያራቀበት ነው።
እኛም የቀድሞ በረከት እንዲደርሰን፣ እናታችንን፦
«በልጅሽ መስቀል አጥርነት ሀገራችንን፣ ሕይወታችንን፣ ሃይማኖታችንንና ኑሯችንን ጠብቂልን» እያልን እንለምናት። 🙏
🌻 መልካም በዓል! 🌻
++++++++++++
✍️መምህር ታምራት ሀብተማርያም
+ጸልዩ ለነ ከመ ይሩጽ ቃለ እግዚአብሔር+
©️ጉባኤ ደብረ ምጥማቅ
፳፩/፩/፪፻፲፱ - ዓ.ም🌻 መስከረም 21 — እመ ብዙሃን 🌻▬▬▬▬▬▬ † ▬▬▬▬▬▬ 📖🕯️ ክርስቲያኖችን ሰብስባ የያዘች ሰፊ መጋረጃ ሐዋ 10፥11 ➜

፳፩/፩/፪፻፲፱ - ዓ.ም📚ኦሪት ዘፍጥረት 📚
✍️ #በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
...ኦሪት ዘፍጥረት የኦርቶዶክሳዊ ክርስትና ዋና ትምህርቶች ማለትም የነገረ ድኅነት፣ የነገረ ሰብእ፣ የነገረ ሥነ-ፍጥረት፣ ... መሠረት ነው፡፡
ኦሪት ዘፍጥረት ብዙ መተርጉማን ትኩረት ሰጥተው በስፋትና በጥልቀት ካብራሯቸውና ከተረጎሟቸው ቅዱሳት መጻሕፍት አንዱ ነው፡፡
#እኔ_ያደረግሁት ከእነዚህ የተለያዩ አባቶች፣ ሊቃውንት እና መተርጉማን ሐሳቦች መካከል የተወሰኑትን አሰባስቦ ማቅረብ ነው፡፡ በማኅበረ ቅዱሳን የቴሌቪዥን መርሐ ግብር በተከታታይ ከቀረበው የኦሪት ዘፍጥረት ማብራሪያ ትምህርት የመጀመሪያዎቹ ዐሥር ምዕራፎች ትምህርት (ከምዕራፍ 1 -10) በዚህ መጽሐፍ ቀርቧል፡፡
በመጻሕፍት ትርጓሜ ውስጥ ልብ ሊባሉ የሚገባቸው ጉዳዮች አሉ። ከእነዚህ አንዱ ጉዳይ በቤተ ክርስቲያን መሠረታዊ አስተምህሮ (ዶክትሪን) እና በመተርጉማን ግላዊ አስተያየቶች መካከል ያለውን ልዩነት በሚገባ ለይቶ ማወቅ ነው፡፡
..... በዚህ #መጽሐፍ የቀረቡትን የመተርጉማን ትርጓሜዎችና ማብራሪያዎች በአግባቡ ተረድተን #ለሕይወት እንድንጠቀምበት #የቃሉ ባለቤት #እግዚአብሔር ይርዳን፡፡ አሜን!
#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
#ኦሪት ዘፍጥረትን ብትን አድርጎ የሚያብራራ ብሎም ገቢውን #ማኅበረ_ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት የተበረከተ ነው።
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
📚ዜና አበው
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንዲህ አለ፦ ወንድሜ ሆይ! ከማር ይልቅ የሚጣፍጥ አርምሞን ገንዘብ አድርግ፤ ከኀዘንና ከትካዜ ጋር ከሚሆን ከሚጣፈጥ መብል ይልቅ ከአርምሞና ከዕረፍት ጋር እንጀራ በጨው ይበልጣልና። ምዕ ፩፥፫ ከአበው አንዱም እንዲህ አለ፦ "የድንጋይ መወርወር እስከ ሰማይ አይደርስም፤የግብዝ ሰው ጸሎትም ወደ እግዚአብሔር አይወጣም።" ምዕ ፫፥፳፫
[ከውስጥ ገጽ]
በሚያስገርም የሕይወት ተሞክሮ የታጀቡ የሚያንጹ ሕይወታዊ ምክሮች የያዘ መጽሐፍ ነው!📚ፍኖተ መጻሕፍት [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623
📚ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
«ከቅዱስ ያሬድ ቀጥሎ ታላቅ ቦታ የያዘ ኢትዮጵያዊ ሊቅ፡፡ ዐፄ ዳዊት ደግሞ “ኢትዮጵያዊ ቄርሎስ”ብለውታል፡፡»📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን። [ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?] ይደውሉልን!📞፦0913083816 Join us ◉Telegram t.me/FinoteBooks1623 ◉Facebook facebook.com/FinoteBooks1623 ◉Tiiktok tiktok.com/@finotebooks1623
📚ቃልኪዳን በነገረ ድኅነት
✍️በዲ/ን ያረጋል አበጋዝ
...ቆየት ካሉ ነገር ግን እንደ መጽሐፉ ብስለት ብዙዎች እጅ ካልገቡ፣ በጥልቅ ትንታኔ ከተዘጋጁ መጻሕፍት አንዱ የዲ/ን ያረጋል አበጋዝ “ቃል ኪዳን በነገረ ድኅነት” በሚል ርእስ የተዘጋጀው መጽሐፍ ነው፡፡ ይህን መጽሐፍ ያነበቡ አንባቢያን ትልቅ መንፈሳዊ መረዳትን ስለሚጠይቀው ስለ ቃል ኪዳንና ነገረ ድኀነት በቂ ግንዛቤ አግኝተውበት እምነታቸውን በማጽናት ከክርስቶስና ከቅዱሳን ጋር ተጣብቀው በምድር ሰማያውያንን መላእክትን መስለው ተዋሕዶዊ አኗኗርን ገንዘብ አድርገው ተመላልሰውበታል፡፡
ይህ መጽሐፍ ቅዱሳን ከአምላካቸው ጋር ያደረጉትን ቃልኪዳንና በተሰጣቸው ቃል ኪዳን እኛ እንዴት መጠቀም እንዳለብን የሚተነትን ብቻ ሳይሆን፣ ነገረ ድኅነትን ተተርሰው ለሚነሡ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ፣ ተግባራዊ ምልልሳችን በክርስትና ሕይወታችን ውስጥ ያለውን ፋይዳ፣ ስለንስሐና ሒደቶቹም በቂ ግንዛቤ እንዲኖረን ያበቃናል፡፡
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
..« - በእውነት አምላክን መበደል ፥ ከቅጣት ይልቅ እጅግ ያማል። በአኹኑ ዘመን ግን እኛ ያለን አመለካከት ፥ በጣም መጥፎ ከመኾኑ የተነሣ ፥ ገሃነምን መፍራት ባይኖር ኖሮ መልካም ለማድረግ እንኳን ባልመረጥን ነበር። ለዚኽ አመለካከታችን እንኳ የገሃነም ፍርድ ይገባናል ፤ ምክንያቱም ከክርስቶስ ይልቅ ገሃነመ-እሳትን እንፈራለንና። ቅዱስ ጳውሎስ ግን እንዲኽ አልነበረም። እኛ ግን አመለካከታችን ከዚኽ የተለየ በመኾኑ ለገሃነም ፍርድ የተገባን ኾነናል። ክርስቶስን እንደሚገባ ብንወደው ኖሮ ፥ የምንወደውን አካል መበደላችን ፥ ከገሃነም በላይ የሚያመን መኾኑን እንረዳ ነበር። ነገር ግን እርሱን መውደድ በእኛ ውስጥ ስለሌለ የቅጣቱን ታላቅነት ማስተዋል አልቻልንም። እኔም ከኹሉ በላይ አጥብቄ የማዝነውና የምቆጨው በዚኽ ምክንያት ነው።
ለመኾኑ እግዚአብሔር እርሱን እንወደው ዘንድ ምን ያላደረገልን ነገር አለ!? ምንስ ያልሰጠን ተስፋ አለ!? ምንስ ያስቀረብን ነገር አለ!? እርሱ ምንም ሳይበድለን ቊጥር በሌለውና ሊነገር በማይችል በረከቱ እያጽናናን ፥ እኛ ግን በክፉ ሥራችን ስሙን አሰደብነው። በብዙ መንገድ እኛን ወደ ራሱ ሲጠራንና ሲስበን ፥ እኛ ግን ከእርሱ ዘወር አልን ፤ እንዲኽ በማድረጋችን እንኳን ፈጥኖ አልተቆጣብንም ፤ ይልቁኑ እኛ ስንርቀው እርሱ ፈጥኖ እጆቻችንን ይዞ ከጥፋት ያወጣናል ፤ እኛ ግን እጆቹን ከእኛ ላይ በማስለቀቅ ለዲያብሎስ ራሳችንን አሳልፈን ሰጠን።
ኾኖም እንዲኽም አድርገነው እንኳ ከእኛ አልራቀም ፤ ይልቁንም ወደ እርሱ እንድንመለስ ቊጥር የሌላቸው መልእክተኞቹን ነቢያትን ፣ መላእክትን እና ቅዱሳን አባቶችን ላከልን። -»..
════════
[ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፥ የሮሜ መልእክት ማብራሪያ ትምህርቶች መካከል ፥ የተወሰደ]
@MARY_THE_MOTHER_OF_GOD
📚ፍኖተ መጻሕፍት
....« - በእውነት አምላክን መበደል ፥ ከቅጣት ይልቅ እጅግ ያማል። በአኹኑ ዘመን ግን እኛ ያለን አመለካከት ፥ በጣም መጥፎ ከመኾኑ የተነሣ ፥ ገሃነምን መፍራት ባይኖር ኖሮ መልካም ለማድረግ እንኳን ባልመረጥን ነበር። ለዚኽ አመለካከታችን እንኳ የገሃነም ፍርድ ይገባናል ፤ ምክንያቱም ከክርስቶስ ይልቅ ገሃነመ-እሳትን እንፈራለንና። ቅዱስ ጳውሎስ ግን እንዲኽ አልነበረም። እኛ ግን አመለካከታችን ከዚኽ የተለየ በመኾኑ ለገሃነም ፍርድ የተገባን ኾነናል። ክርስቶስን እንደሚገባ ብንወደው ኖሮ ፥ የምንወደውን አካል መበደላችን ፥ ከገሃነም በላይ የሚያመን መኾኑን እንረዳ ነበር። ነገር ግን እርሱን መውደድ በእኛ ውስጥ ስለሌለ የቅጣቱን ታላቅነት ማስተዋል አልቻልንም። እኔም ከኹሉ በላይ አጥብቄ የማዝነውና የምቆጨው በዚኽ ምክንያት ነው።
ለመኾኑ እግዚአብሔር እርሱን እንወደው ዘንድ ምን ያላደረገልን ነገር አለ!? ምንስ ያልሰጠን ተስፋ አለ!? ምንስ ያስቀረብን ነገር አለ!? እርሱ ምንም ሳይበድለን ቊጥር በሌለውና ሊነገር በማይችል በረከቱ እያጽናናን ፥ እኛ ግን በክፉ ሥራችን ስሙን አሰደብነው። በብዙ መንገድ እኛን ወደ ራሱ ሲጠራንና ሲስበን ፥ እኛ ግን ከእርሱ ዘወር አልን ፤ እንዲኽ በማድረጋችን እንኳን ፈጥኖ አልተቆጣብንም ፤ ይልቁኑ እኛ ስንርቀው እርሱ ፈጥኖ እጆቻችንን ይዞ ከጥፋት ያወጣናል ፤ እኛ ግን እጆቹን ከእኛ ላይ በማስለቀቅ ለዲያብሎስ ራሳችንን አሳልፈን ሰጠን።
ኾኖም እንዲኽም አድርገነው እንኳ ከእኛ አልራቀም ፤ ይልቁንም ወደ እርሱ እንድንመለስ ቊጥር የሌላቸው መልእክተኞቹን ነቢያትን ፣ መላእክትን እና ቅዱሳን አባቶችን ላከልን። -»....
═══════════════
[ከቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ፥ የሮሜ መልእክት ማብራሪያው ውስጥ ካሉ ትምህርቶች መካከል ፥ ከአምስተኛው ድርሳን ላይ የተወሰደ]
📚#ፍቅር
--
ወንድሞቼ ሆይ፡- ሃይማኖት ቀላል ቅድስና ወይም እርግማን አይደለም! ወይም ደግሞ ቀላል ትእዛዝ ወይም ክለከላ አሊያም ተራ ሕግ ወይም ጸጋ አይደለም በሚቻለው ሁሉ ለእግዚአብሔርና ለሰዎች የሚሆን ፍቅር እንጂ፡፡ ከዚህ ፍቅር የሚመነጨውም ሁሉ መልካም ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔርንና ሰዎችን የማትወዱ ከሆናችሁ የተፈለገውን ያህል ብትጸልዩ ወይም ብትጾሙ ወይም ብታነቡ ወይም በተመስጦ ብትቆዩ ወይም አሥራት ብታወጡ ወይም ብታገለግሉ ወይም ብትሰብኩ የሃይማኖት ሰዎች ልትሆኑ አትችሉም፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው ፍቅርን እንጂ ቀላል ተግባራትን አይደለም፡፡ ከእናንተ የሚፈልገው እርሱ እናንተን እንደ ወደዳችሁ እናንተም እርሱን እንድትወዱት ነው።
📚ፍኖተ መጻሕፍት ለውድ አንባብያን በDHL እና በEMS እንዲኹም የDelivery አገልግሎት በመስጠት መጻሕፍትን ተደራሽ እናደርጋለን።
[ እንደ መጻሕፍት ያለ መንገድ ከወዴት ይገኛል?]
ይደውሉልን!📞፦0913083816
Join us
◉Telegram
t.me/FinoteBooks1623
◉Facebook
facebook.com/FinoteBooks1623
◉Tiiktok
tiktok.com/@finotebooks1623
❝ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማኅየዌ። በጼዴንያ ወግብፅ ዘአውኀዘት በኢሕሳዌ። ለመጸብሐዊ ማቴዎስ ማርያም እንተ ረሰይኪዮ ወንጌላዌ። ይኩነነ ወትረ ጸሎትኪ እምዘመነ ኵሉ ምንሳዌ፡፡ ዓቃቤ ዘመዓልት ወዘሌሊት ሀላዌ ።
--
ትርጉም ፦ በጼዴንያና በግብፅ ያለ ሐሰት ፈዋሽ ወዝን ላፈሰሰ ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል:: ቀራጭ ማቴዎስን ወንጌላዊ ያደረግሽው #እመቤቴ_ማርያም_ሆይ ጸሎትሽ ከጥፋት ዘመን ሁሉ ዘወትር የመዓልትና የሌሊት ቋሚ ጠባቂ ይሁነን::❞
ለበለጠ ማብራሪያ እና ታሪክ መጽሐፉን ተመልከቱ።መልካም በዓል! 📚ፍኖተ መጻሕፍት

📚#ፍኖት_መንፈሳዊት
[The way of Pilgrim ]
በእግዚአብሔር ቸርነት ክርስቲያን ነኝ፤ በምግባሬ ግን ታላቅ ኀጢአተኛ፤ አጠራሬም ቤት አልባና የትሕትናን ምንጭ በመፈለግ ላይ ያለ ከርታታ፤ ከቦታ ቦታ የሚዘዋወር የሚል ነው። ንብረቶቼ በጀርባዬ ያዘልሁት ደረቅ ዳቦ ያለው የከረጢት ቦርሳና በእቅፌ የያዝሁት መጽሐፍ ቅዱስ ናቸው፤ ይኸው ነው ያለኝ።ከበዓለ ኀምሳ በኋላ በኻያ አራተኛው እሑድ ወደ ቤተክርስቲያን በቅዳሴ ላይ ለመሳተፍ ኼድሁና ልክ [የቅዱስ ጳውሎስ] መልእክት እየተነበበ ሳለ ገባሁ። ንባቡ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ከላከው የመጀመሪያ መልእክት የተወሰደ ሲሆን፥ ይህም «ሳታቋርጡ ጸልዩ» ይላል።እነዚህም ቃላት በእኔ ላይ ጥልቅ ስሜት ፈጠሩብኝና እንዲህ ስል ዐሰብሁ፤ “አንድ ሰው ለሕይወት የሚያስፈልጉትን ነገሮች በመፈለግ ብዙውን ትኩረቱን በሚይዝበት በዚህ ዓለም ሳያቋርጥ እንዴት መጸለይ ይቻለዋል?” መጽሐፍ ቅዱሴን ከፍቼ ...
[ከመጽሐፉ የተወሰደ]