ch
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

前往频道在 Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite

显示更多
3 614
订阅者
+224 小时
-17 天
+1130 天
帖子存档
ጥያቄ?? በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን
ጥያቄ?? በአንድ ተቋራጭ ሥር የሚሠሩ ምክትል ሥራ ተቋራጮች (Sub Contractors) የሠሩበትን የሥራ ክፍያ ዋናው ተቋራጭ አልከፍል ቢላቸው ክስ መስርተው በዋናው ተቋራጭ ውል ላይ የተመለከተውን የሥራ ዋጋ የማግኘት መብት አላቸው?
መልስ:-
በኢትዮጵያ የሕንጻ ነክ ሕጎች መሰረት በአንድ የሕንጻ ተቋራጭ ሥር የሚሰሩ ምክትል /ንዑስ/ ሥራ ተቋራጮች (Sub contractors) ወይም ሠራተኞች (labours) ዋናው ተቋራጭ ለሠሩበት ሥራ ሳይከፍላቸው ከቀረ እና ለሠሩበት ሥራ ዋጋ እንዲከፈላቸው ክስ ካቀረቡ ክሳቸውን ባቀረቡበት ጊዜ አሠሪው ለሥራ ተቋራጩ ሊከፍል በሚገባው ገንዘብ መጠን በቀጥታ ገንዘባቸውን የመጠየቅ መብት ስላላቸው ያንን ክፍያ የማግኘት መብት አላቸው። ለምሳሌ፦ አንድ ተቋራጭ በውል ሰነዱ ውስጥ የአንድ ካሬሜትር የፎርምወርክ ሥራን በ500 ብር ሂሳብ ተዋውሎ ለምክትል ሥራ ተቋራጮች  (Sub contractors) በ300 ብር ተነጋግሮ ካሠራቸው በኋላ ክፍያ ሳይከፍላቸው ቢቀር (ቢያዘገይባቸው) ክስ ማቅረብ ይችላሉ። ክስ ሲያቀርቡ ሥራውን ለመሥራታቸው ማረጋገጫ ካቀረቡ እና የሥራው ጥራት ታይቶ ተቀባይነት ካገኘ ዋናው ተቋራጭ የተዋዋለበትን 500ብር ሊከፈላቸው የሚችልበት አግባብ አለ ማለት ነው። Construction Solution-👷‍♀👷 Telegram | Facebook | Tiktok Social media- Networks @consite🏗

👉Invitation for National Competitive Bid 🚧Bid Ref. No. DBE/NCB/IT/017/2025/26 ⭐️Development Bank of Ethiopia invites intere
👉Invitation for National Competitive Bid 🚧Bid Ref. No. DBE/NCB/IT/017/2025/26 ⭐️Development Bank of Ethiopia invites interested bidders for the supply, installation and implementation of privileged access management (PAM) solutions. Interested bidders can get the full information on our website using the following👇 https://dbe.com.et/?page_id=7700

የግንባታ ኮንትራት ዋና ዋና ቃላትና ትርጓሜዎቻቸው በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው:- 1. የስራ መጠን ለውጦች (Variations) - ኦሚሽን (Omission): የታቀደ ስራ ሲቀነስ ወይም ሲሰረዝ (ዋጋ ይ
የግንባታ ኮንትራት ዋና ዋና ቃላትና ትርጓሜዎቻቸው በአጭሩ የሚከተሉት ናቸው:- 1. የስራ መጠን ለውጦች (Variations) - ኦሚሽን (Omission): የታቀደ ስራ ሲቀነስ ወይም ሲሰረዝ (ዋጋ ይቀንሳል)። - አዲሽን (Addition): አዲስ ስራ ወይም ተጨማሪ መጠን ሲጨመር (ክፍያ ይጨምራል)። - ቫሪዬሽን ኦርደር (VO): በዲዛይን ወይም በስራ መጠን ላይ ለውጥ ለማድረግ የሚሰጥ መደበኛ ትዕዛዝ። 2. የጊዜና የክፍያ ማበረታቻዎች/ቅጣቶች - ቦነስ (Bonus): ስራው ከቀጠሮው በፊት ሲጠናቀቅ ለኮንትራክተሩ የሚሰጥ ሽልማት። - ፔናልቲ (Penalty/LD): ስራው በጊዜ ካልተጠናቀቀ ከኮንትራክተሩ የሚቀነስ ቅጣት። - የጊዜ ማራዘሚያ (EOT): ከኮንትራክተሩ ቁጥጥር ውጭ በሆኑ ምክንያቶች ለስራው የሚታከል ተጨማሪ ጊዜ። - የዋጋ ለውጥ (Escalation): የጥሬ ዕቃዎች ወይም የነዳጅ ዋጋ በገበያ ላይ ሲጨምር የሚደረግ የዋጋ ማስተካከያ። 3. የክፍያ ዓይነቶችና ዋስትናዎች - አድቫንስ (Advance): ስራ ለመጀመር ቅድሚያ የሚሰጥ ክፍያ (ከ10% - 20%)። - ኢንተሪም ክፍያ (IPC): በየወሩ ለተከናወነ ስራ የሚከፈል ጊዜያዊ ክፍያ። - ሪቴንሽን (Retention): ለጥራት ዋስትና ከእያንዳንዱ ክፍያ የሚቀነስ ገንዘብ (5% - 10%)። - ፐርፎርማንስ ቦንድ: ኮንትራክተሩ ስራውን በአግባቡ ለመጨረሱ የሚይዘው የባንክ ዋስትና። - የመጨረሻ ክፍያ (Final Payment): ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ርክክብ ሲደረግ የሚፈፀም ክፍያ። 4. ከርክክብ በኋላ ያለ ኃላፊነት - የጉድለት ኃላፊነት ጊዜ (DLP): ስራው ካለቀ በኋላ ባሉት 6 ወይም 12 ወራት ውስጥ የሚታዩ ብልሽቶች ኮንትራክተሩ በነፃ የሚያስተካክልበት ጊዜ። @consite🏗

የዲዛይን እና ግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት:- የጨረታ ማስታወቂያ 1. የሥራው ዓላማ አንድ ሚሊዮን ብርቱ (One Million Birtu (OMB) ሀገር በቀል ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ዋና ዓላማውም እስከ 2030 ዓ.ም የአንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ሕይወት ማሻሻል ነው:: ድርጅቱ ከዘላቂ የልማት ግብ 7 (SDG 7) ጋር በተጣጣመ መልኩ ንጹህ የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ሁሉን አቀፍ እና ሰፊ ተደራሽነት ያላቸውን መፍትሄዎች በማቅረብ ላይ ያተኩራል። ይህንንም ለማሳካት በጠምባሮ ልዩ ዞን፣ ሙዱላ ወረዳ ለሚገነባ ኮንፕሬሄንሲቭ ሄልዝ ፖስት (Comprehensive Health Post) ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ስራዎች መስፈርቱን ለሚያሟሉ ብቃት ያላቸውን አማካሪዎች (ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች) አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። ሙሉ የአርክቴክቸር እና የምህንድስና ዲዛይን አገልግሎቶች የዋጋ ዝርዝር (BoQs) እና የቴክኒክ ሰነዶች ዝግጅት ግንባታ ቁጥጥር እና የውል አስተዳደር ግንባታው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር መስፈርትን የጠበቀ እና Compressed Earth Block (CEB) ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ይሆናል። የስራው ቆይታ ጊዜ ለዲዛይን እና የቅድመ ግንባታ ምዕራፍ 5 ሳምንታት ፤ ለግንባታ ቁጥጥር 6 ወራት ነው። 2. ተወዳዳሪዎች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች:- ለ 2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት አማካሪ ወይም ድርጅት፡፡ ቢያንስ 3 ዓመት ተዛማጅ የሥራ ልምድ፡ ተመራጭ ሁኔታዎች፡ በCEB ቴክኖሎጂ፣ በጤና ተቋማት ግንባታ እና በገጠር አካባቢዎች የመሥራት ልምድ ያልው ያላት። 7. የማመልከቻ ዝርዝሮች መስፈርቱን ሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች የታሸጉ እና ማህተም የተደረገባቸው የዋጋ ማቅረቢያዎችን (Quotations) በግንባር በሚከተለው አድራሻ ማቅረብ ይችላሉ፡ ቦሌ መድኃኒዓለም፣ አቢሲኒያ ፕላዛ፣ 10ኛ ፎቅ የመጨረሻ ቀን፡ የጨረታው ማስታወቂያው በወጣ በ10ኛው የስራ ቀን 11:00 ሰዓት ላይ ዘግይተው የሚመጡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም። 8. ተጨማሪ መረጃ ሙሉውን የሥራ መግለጫ (Statement of Work)፣ የዲዛይን ማጣቀሻዎችን እና አጋዥ ሰነዶችን ለማግኘት በሚከተሉት አድራሻዎች ያግኙን፡ ኢሜል: mihret.tsegaye@preciseethiopia.com  ስልክ ቁጥር: +251 926 043 198 ወይም ሰነዶቹን ለመውሰድ በግንባር ቢሮ ድረስ መምጣት ይችላሉ። ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ ማንኛውንም ማመልከቻ በሙሉም ሆነ በከፊል የመቀበል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። እንዲሁም ማስታውቂያው ከሚያበቃበት ቀን ቀደም ብሎ በቂ አመልካች ከተገኘ ያለምንም ማብራሪያ ሂደቱን በማንኛውም ደረጃ የማቆም መብት አለው። Source: Addis Zemen Published Date Sat, Apr 25, 2026 Closing Date Fri, May 08, 2026 at 11:00 (LT)

ድርጅታችን አክላ እንጂነርንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጥራታቸውን የጠበቁ ለመጋዘን ፡ ለመኖሪያ ቤት እንድሁም ለአጥሪ የምሆኑ EGA SHEET METAL EGA TILES CIS O.4 ,0.3,0.25 & 0.
+9
ድርጅታችን አክላ እንጂነርንግ  ኃ/የተ/የግ/ማህበር ጥራታቸውን የጠበቁ   ለመጋዘን ፡ ለመኖሪያ ቤት  እንድሁም  ለአጥሪ  የምሆኑ EGA SHEET METAL EGA TILES CIS  O.4 ,0.3,0.25 & 0.2 mm ለ ቆርቆሮ  አምራች ድርጅት   ኮይል(coil) በብዛት እናቀርባለን  በ 1እና 1.2 ሜትር ስፋት   (width ) ክፍለሀገር በአጋርነት መስራት ለሚፈልጉ ነጋዴዎች ድርጅታችን ዝግጁ መሆኑን እናሳዉቃለን ለበለጠ መረጃ 📲  0906852424 .      0986047070 email aklaengineerigplc@gmail.com Telegram akla engineering plc https://t.me/aklaengineeringplc

🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱 Red brick:- This is the classic brick color that you see Quality with affordable price 🧱ጥራት ያላቸውን እና ለተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የቀይ ሸክላ (ጡቦችን) እናመርታለን። 🧱 ለሙሉ የቤት ግንባታ፣ 🧱ለባንክ ቤት ካዝና፣ 🧱 ለግቢ አጥር ማጠሪያ፣ 🧱 ለመንገድ ዳር ጠርዞች፣ 🧱  ለሆቴሎች፣ሬስቶራንት፣እና ካፌዎች ማሳመሪያ ፣ 🧱 ለx-ray ክፍሎች፣ 🧱 ለፍሳሽ ማንዋሎች፣ 🧱 ለኪችን ሲንክ ማስቀመጫ ፣ 🧱 ለሻወር ገንዳ ማሰቀመጫ፣ 🧱 የPBC ፍሳሽ ማስወገጃ ለመሸፈን፣ 🧱 ለአበባ መትከያ 🧱 ለብረት ማቅለጫ ፈርኒስ፣ 🧱 ለፒዛ ኦቭን፣ 🧱 ለምድጃ፣ 🧱 ለቆሻሻ ማቃጠያ፣ *We produced High quality clay bricks for various construction purposes. 🧱 For building construction, 🧱 For bank vaults, 🧱 Fence for the yard, 🧱 For road edges, 🧱 For Hotels,Restaurants,and Cafes decoration, 🧱 For x-ray rooms, 🧱 For manuals, 🧱 For kitchen, 🧱 For shower tray 🧱 To cover PBC drains, 🧱 For garden, 🧱 Furnace For steel factory, 🧱 For pizza oven, 🧱 For waste incinerator.... 🧱 For more information join our telegram channel https://t.me/+d8A-rQlF5p5lZThk & Ticktok account @newpointbricksfactory 🧱Order now 📲0912854327,0902378888 🧱"Quality is our first priority" Thank you 谢谢🧱

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የነዳጅ እጥረት/ ዋጋ መናር በግንባታ ውሎች ላይ ላለው ተፅዕኖ ምን መፍትሄ አለ? - የዋጋ ማስተካከያ አንቀጽ በውሉ ውስጥ ካለ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው በውሉ ቀመር (Formula) መሠረት ተሰልቶ የሚ
የነዳጅ እጥረት/ ዋጋ መናር በግንባታ ውሎች ላይ ላለው ተፅዕኖ ምን መፍትሄ አለ? - የዋጋ ማስተካከያ አንቀጽ በውሉ ውስጥ ካለ፣ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪው በውሉ ቀመር (Formula) መሠረት ተሰልቶ የሚከፈል በመሆኑ ስጋቱ በተወሰነ መልኩ ይቀንሳል። ሆኖም ነዳጅ ካለመገኘቱ ጋር ተያይዞ ለሚመጣ የስራ መጓተት፣ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ (EOT) የሚያሰጠው ነው። - የዋጋ ማስተካከያ (Price Adjustment) ለሌላቸው ውሎች የነዳጅ ዋጋ መናር እና እጥረት ችግሩ አገራዊ በመሆኑ እና በርካታ ፕሮጀክቶችን ሊያስተጓጉል ስለሚችል፣ የሚመለከተው አካል (የገንዘብ ሚኒስቴር) ልዩ መመሪያ በማውጣት የዋጋ ማስተካከያ እንዲደረግ ሊፈቅድ ይችላል። አሰሪ መ/ቤቶች ይህንን ልዩ ፈቃድ ሊጠይቁ ይችላሉ። - የነዳጅ ዋጋ መናር እና እጥረት ለረጅም ጊዜ ቀጣይነት ያለው ከሆነ የሚከተሉት አማራጮችም ሊታዩ ይችላሉ👇 1) ሥራን ለጊዜው ማቆም (Suspension): ነዳጅ ጨርሶ ካልተገኘ  (በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ) ሥራን ለጊዜው ማቆም አማራጭ ነው። ሆኖም ተቋራጩ በራሱ ውሳኔ ሥራ ከማቆም ይልቅ፣ አሰሪው በጽሁፍ ሥራ እንዲያቆም (Suspension order) እንዲሰጠው መጠየቅ ይኖርበታል። 2) ውልን በስምምነት ማቋረጥ (Amicable Termination): የነዳጅ እጥረቱ እና የዋጋ ንረቱ ተቋራጩን ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ የሚያደርገውና ፕሮጀክቱንም ለከፋ መጓተት የሚዳርገው ከሆነ፤ ሁለቱ ወገኖች ተነጋግረው ያለምንም የቅጣት ክፍያ  ውልን በስምምነት ማቋረጥ ይችላሉ። ከላይ የተነሱት ሃሳቦች በየውሎች ነባራዊ ሁኔታ ማየት ተገቢ ነው። ተጨማሪ ሃሳብ ካለዎት ያጋሩን? @consite🏗

👉 Kebridehar-Gode (Denan-Gode) Periodic maintenance Procuring Entity  Ethiopian Roads Administration Invitation Date:  Apr 17, 2026, 12:00:00 AM Procurement Reference No  ERA-NCB-W-0140-2018-BID-Open Procurement Category  Works Market Type  National Procurement Method  Open Clarification Request Deadline  May 7, 2026, 5:00:00 PM Bid Submission Deadline  May 17, 2026, 2:00:00 PM Bid Opening Schedule  May 17, 2026, 2:30:00 PM Annual Turnover  Peak annual construction turnover of ETB 51 Million calculated as total certified payments received for contracts in progress or completed within the last Five (5) years. Grade of Contractors for Local Bidders  BC –3, RC – 4 or GC – 3 and above Bid Security Amount  2,000,000 ETB Bid Security Form For SME  Bank_Guarantee, CPO, Bid Security Form For Local Bidders  Bank_Guarantee, CPO, Bid Security Form For Foreign Bidders  Bank_Guarantee, CPO, Notice Terms and Conditions  The Public Body reserves the right to accept or reject any Bid Proposal, and to annul the bidding process and reject all Bid Proposals at any time prior to contract award, without thereby incurring any liability to Consultants Apply online on EGP https://production.egp.gov.et/egp/bids/all/tendering/f97e4736-6314-4c58-8c2c-a9e49a079b20/open

✅ የግንባታ ስራ ክፍያ (payment) ለመውሰድ ወደቢሮው የሚመጡ ስራ ተቋራጮች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች https://t.me/ethioconradio
✅ የግንባታ ስራ ክፍያ (payment) ለመውሰድ ወደቢሮው የሚመጡ ስራ ተቋራጮች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ቅድመ ሁኔታዎች https://t.me/ethioconradio

👉 ፐርሲሊን እና ሴራሚክ ያላቸው ልዩነት ምንድን ነው? https://t.me/ethioconradio
👉 ፐርሲሊን እና ሴራሚክ ያላቸው ልዩነት ምንድን ነው? https://t.me/ethioconradio

👉የግንባታ ዲዛይን ለተቋራጭ ይሰጣልን ? 💫አንድ ግንባታ ዲዛይን በአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ከተሰራ በኋላ ሙሉ የዲዛይን ሰነዱ በወረቀት ቅጅ (hard copy) እና በሶፍት ቅጅ (soft copy
👉የግንባታ ዲዛይን ለተቋራጭ ይሰጣልን ? 💫አንድ ግንባታ ዲዛይን በአማካሪ ድርጅት ባለሙያዎች ከተሰራ በኋላ ሙሉ የዲዛይን ሰነዱ በወረቀት ቅጅ (hard copy) እና በሶፍት ቅጅ (soft copy) ለአሰሪው ይሰጣል። ነገር ግን በ’ ከተማ ልማት እና ሥራዎች ሚኒስቴር አዋጅ አንቀጽ 6 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት፦ ➀ኛ. ‘Custody of Drawings’ መሰረት፣ የግንባታ ዲዛይኑ የግንባታ ክትትል ለሚያከናውነው ተቆጣጣሪ መሐንዲስ በሶፍት ቅጅ  ሊሰጥ የሚችል ይችላል። ⓶ኛ. ለግንባታ ተቋራጩ (contractor) መሰጠት ያለበት የወረቀት ቅጂዎችን ሲሆን  ያለምንም ክፍያ በባለቤቱ ወጪ መዘጋጀትና ለተቋራጩ መሰጠት አለበት። - የግንባታ ተቋራጩ የሚፈልገው ተጨማሪ ቅጂዎች ካሉ በራሱ ወጪ እንዲባዙለትና እንዲሰጡት ማድረግ ይችላል፣ ነገር ግን ያለባለቤቱ ፍቃድ ማባዛትና ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ተቋራጩን ያስጠይቀዋል። - ግንባታው ሲጠናቀቅ ተቋራጩ በውሉ መሠረት በቅጂ የቀረቡትንና የተረከባቸውን ሁሉንም ዲዛይኖች ለመሐንዲሱ እንዲመልስ በሕግ ግዴታ አለበት። @consite🏗

FDRE-Procurement-Manual-Final-2018-NBGMS-1221-3.pdf2.94 MB

I am sharing 'ሀገር አቀፍ የአቅራቢዎች ፍላጎት መግለጫ' with you

ከቀረጥ ነፃ የገቡ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ክትትል እንዳይደረግ ተወሰነ የኮንስትራክሽን እቃዎች እና ማሽነሪዎች በታሪፍ መጽሃፉ መሰረት ነጻ አንዲኾኑ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ወደ ሃገር የገቡ የኮንስትራክሽን- መሳሪያዎች እና ማሽነሪዎች ላይ ለገቡበት አላማ ‹ስለመዋላቸዉ የሚደረገዉ ቁጥጥር እና ክትትል' ተፈጻሚ አይደረግባቸዉም ሲል ገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ ሰጥቷል። ፅቃዎቹ በታሪፍ መጽሃፉ ከቀረጥ እና ታክስ ነጻ ከመደረጋቸዉ በፊት ወደ ሃገር የገቡ ከሆነ እና አሁን ላይ የብድር ማስያዣነት ጥያቄ ከቀረበባቸዉ ደግሞ የአዋጁ አንቀጽ 130(6) ገደብ ተግባራዊ አይደረግባቸዉም ብሏል።

የኮንስትራክሽን_አማካሪዎች_የአሰራር_መመሪያ_1_1.pdf10.06 MB

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗 - Telegram 频道 @consite 的统计与分析