ch
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

前往频道在 Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service

显示更多
3 590
订阅者
无数据24 小时
+37
+4830
帖子存档
Medcon Engineering & Construction Plc Job Vacancy Announcement Deadline: Sept 3, 2025 👈
Medcon Engineering & Construction Plc  Job Vacancy Announcement Deadline: Sept 3, 2025 👈

🏣🏚የዓመቱ ወቅቶችና የሪል እስቴት ገበያ 🏢እንደማንኛውም የምርት ገበያ የሪል እስቴት ግብይትም የወቅቶች መፈራረቅ ተጽዕኗቸው ቀላል አይደለም። ወቅቶች በገበያው ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ መረዳት ለሻጭም ለገዢም ውሳኔ ለመስጠት ለዝግጅትም ይረዳቸዋልና ይህንን በዘርፉ የላቀ ልምድ ያላቸው ሀገራት ላይ ያሉ የሪል እስቴት ማህበራትና የሽያጭ ድርጅቶችን ጥናት ተመልክቶ የተሰራ ጽሁፍን ከሀገራችን ወቅቶች ጋር አዛምጄ እንደሚከተለው በአጭሩ ለማቅረብ ሞክሬያለሁ።   🌨🌨#የክረምት_ወቅት ከሰኔ 26 እስከ መስከረም 25 ያለው ወቅት ሲሆን የአየሩ መቀዝቀዝና ዝናባማ መሆን የግንባታ ሳይቶችን ጭቃማ ማድረጉ ተደማምሮበት የቤት ገዢዎች ለግዢ ተነሳስተው ዞረው ጎብኝተው መርጠው ለመግዛትና ተደጋጋሚ መመላለስ የሚያስፈልገውን የግብይት ሂደት ለማካሄድ ተነሳሽነት ማጣትን ስለሚፈጥር የሀገራችን የክረምት ወቅት በተለይ በመገንባት ላይ ላሉ ሳይቶች ጎብኚና ገዢ ለማግኘት ይቸገራሉ። በተጨማሪም የሀገራችን ኢኮኖሚ ግብርና መር ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የቢዝነስ እንቅስቃሴው በክረምት ወቅት ስለሚቀዛቀዝና  የሀገራችን የክረምት ወቅት አብዛኛው የንግዱ ማህበረሰብ ዓመታዊ  ግብር የሚገብርበት ወቅትም በመሆኑ ቀልቡን ሰብስቦ ገንዘብ መድቦ ለቤት ግብይት የሚወጣ ነጋዴ ጥቂት ነውና የክረምት ወር ለሪል እስቴት ግብይት ቀዝቃዛ የሚባል ወቅት ነው። ይህ የክረምት ወቅት አልሚዎችና አገበያዮች ጎብኚና ገዢ የሚቀንስባቸውና በዚሁ ምክንያት ዋጋ የሚቀንሱበት ወቅት ሲሆን ነገር ግን ለቤት ገዢዎች ጥሩ ቅናሽ የሚያገኙበት ነቅተው ለሚገዙ ቤት ገዢዎች በቅናሽ ለመግዛት አመቺ ወቅት ነው። #የመጸው_ወቅት ከመስከረም መጨረሻ እስከ ታህሳስ መጨረሻ ያለው ሲሆን እንደ ሁሉም የንግድ እንቅስቃሴ የሪል እስቴት ግብይትም መነቃቃት የሚታይበት ወቅት ነው ። ይህ ወቅት ከክረምት ወቅት የተሻለ ለመጎብኘት የተመቸ ነገር ግን ለግዢ ለውሳኔ ቀጣይ ወቅቶችን የሚያማትር ዕጩ ገዢ የሚገኝበት ነው። # የበጋ_ወቅት ከታህሳስ መጨረሻ እስከ መጋቢት ወር መጨረሻ ጠቅላላ የሀገራችን የንግድ እንቅስቃሴ የሚሟሟቅበት አየሩም ሞቃታማ የሚሆንበት ሳይቶችን ተዟዙሮ ለመጎብኘትም ሆነ ጉዳይ ለማስፈጸም ለመንቀሳቀስ የሚያበረታታ በመሆኑ አልሚዎችና የሽያጭ ባለሙያዎች ከሌሎች ወቅቶች የተሻለ ጎብኚዎችና ገዢዎች የሚያገኙበት ወቅት ነው። #የጸደይ_ወቅት (የበልግ ወቅት) ይህ ወቅት በበጋና በክረምት መካከል የሆነ (ከመጋቢት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጨረሻ) የሌሎች ወቅቶችን መለያዎች አስተባብሮ የያዘ ነው። ጸሀይ፣የበልግ ዝናብ ፣ የበልግ ምርት፣ ለክረምት ዝግጅት እርሻ ...የንግዱም ስራ ያንኑ የሚከተል ነው ። በርካታ ተጀምረው የነበሩ የቤት ግዢ ውሳኔዎች የሚወሰኑበት ፣ በዚህ ወቅት የሚመጡ ገዢዎችም በፍጥነት ለግዢ የሚወስኑበት ...ለአልሚዎና ለቤት ግብይት ባለሙያዎች የተሻለ የሚባል ወቅት ነው። #የበዓላት_ወቅቶች ከዓመቱ ወቅቶች በተጨማሪ  የበዓላት ወቅቶችም ተጨማሪ ልዩ ግንዛቤ ሊወሰድባቸው የሚገባ የበዓላት ወቅቶች ነው። የበዓላት ወቅቶች ቤት ገዢዎችን የሚባሉትን ሳይቀር የበዓል ዝግጅትና ድባብ ውስጥ የሚከቱ በመሆናቸው እንደሚጠበቀው የበዓላት መዳረሻዎችና የበዓላት ወቅቶች ለቤት ግብይት የተነቃቁ አይደሉም። የበዓላት ወቅቶች ካለፉ በኋላ ያሉ ወቅቶች የተሻለ የግብይት መነቃቃትን የሚፈጥሩ ናቸው። ለዚህም የሪል እስቴት አልሚዎችና አገበያዮች የበዓላት መዳረሻና የበዓላት ወቅቶችን ቀጥተኛ ከሆኑ የግዢ ጥያቄና ሙከራ ራሳቸውን ገትተው በመዝናኛ ፕሮግራም መልክ የሚጋጁ የተለያዩ መረጃዎችን በመደበኛም ሆነ በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችን ቢያስተላልፉ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ምርታቸውን በተዘዋዋሪ መንገድ ቢያስተዋውቁ ይመከራሉ።  መልካም ቅዳሜ! 👨‍⚕ኢ/ር ደሳለኝ ከበደ የሪል አስቴት ቢዝነስ አማካሪ

👉2 ሺህ 400 ብር ሲሸጥ የነበረዉ የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ ወደ 1 ሺህ 100 ብር ዝቅ ማለቱ ተገለጸ 💫የሲሚንቶ ግብይትን ለማረጋጋት በተወሰዱ የአሰራር ማሻሻዎች አዲስ አባባ በሚገኙ አከፋፋ
👉2 ሺህ 400 ብር ሲሸጥ የነበረዉ የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ  ዋጋ ወደ 1 ሺህ 100 ብር ዝቅ ማለቱ ተገለጸ 💫የሲሚንቶ ግብይትን ለማረጋጋት በተወሰዱ የአሰራር ማሻሻዎች አዲስ አባባ በሚገኙ አከፋፋዮች ዘንድ  ቀደም ሲል በ 2 ሺህ 400 ብር ሲሸጥ የነበረዉ የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ  ዋጋ ወደ 1 ሺህ 100 ብር ዝቅ ማለቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
በሚኒስቴሩ የሀገር ውስጥ ግብይት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሊቁ በነበሩ እንደገለጹት፣ አሁን ላይ የሲሚንቶ ንግድ በተጨባጭ የተረጋጋው በሁለት ምክንያቶች እንደሆነ ጠቅሰዋል።
⏺የመጀመሪያው አዳዲስ ፋብሪካዎች ጭምር ወደ ምርት በመግባታቸው በቂ የምርት አቅርቦት እንዲኖር ማስቻሉ እንደሆነ እና በሲሚንቶ ግብይት ሥርዓት ላይ ማሻሻያዎች መደረጋቸው እንዲሁም ዋጋውም ገበያ መር እንዲሆን መወሰኑ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በኢስት አፍሪካ ናሽናል ዲስትሪቢዩሽን የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አሸናፊ መለሰ በበኩላቸው፣ ለሚ እና ድሬዳዋ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካዎች የገበያውን ከ42 በመቶ በላይ ፍላጎት መሸፈናቸውን አንስተዋል።
▶️ይህን ተከትሎም የአንድ ኩንታል ሲሚንቶ ዋጋ በአዲስ አባባ በሚገኙ አከፋፋዮች ዘንድ ቀደም ሲል ከነበረበት 2 ሺህ 400 ወደ 1 ሺህ 100 ብር ዝቅ ማለቱን እና የተረጋጋ ግብይት መዘርጋቱን አመላክተዋል። 🚧ለሚ ናሽናል ሲሚንቶ በቀን 150 ሺህ ኩንታል እያመረተ መሆኑን ጠቅሰው፣ በሐዋሳ፣ አዳማ እና ጅማ ምርቱን በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችሉ ዲፖዎች መኖራቸውንም ጠቁመዋል። ⏺በቂ ምርት ወደ ገበያ ማቅረብ በመቻሉ ግብይቱን ከማረጋጋት በተጨማሪ የግንባታው ዘርፍ እንዲነቃቃ ማስቻሉን  መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡ 👈👈

Elegant & Durable PVC Doors ✨ Upgrade your home with stylish PVC doors featuring modern glass designs. Strong, beautiful, and
Elegant & Durable PVC Doors ✨ Upgrade your home with stylish PVC doors featuring modern glass designs. Strong, beautiful, and long-lasting! 📍አድራሻ : ጋዜቦ አደባባይ፣ ከ ሙሌሙል ዳቦ ቤት አጠገብ ለበለጠ መረጃ በዚህ ሰልክ ይደውሉ 📞 0930099145 | 0930099146" ቤትዎን በዘመናዊ እና ቆንጆ የPVC በሮች ያዘምኑ። ጠንካራ፣ ውብ፣ እና የረጅም ጊዜ የሚቆዩ!

👉 INTERCON Construction Chemicals ● Concrete Admixtures ● Bonding Agents ● Waterproofings ● Wall Putty, Prime Coat ● Concret
👉 INTERCON Construction Chemicals  ● Concrete Admixtures ● Bonding Agents ● Waterproofings ● Wall Putty, Prime Coat ● Concrete Repair Mortar ● Floor hardener, Epoxy ● Grout, Self-level mortar ● Quartz paint, Contextra ● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers  ● Geotextiles and other construction chemicals and materials Tel: 0961955555 Address: Signal, around signal mall

62.6 ቢሊየን ብር ውል የተገባለት የሚኤሶ - ድሬዳዋ ፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የጨረታ ሂደቱ ምን ይመስላል? 🚨ከዓለም ባንክ ድህረገጽ ላይ ይፋ ከሆነው የአሸናፊ ድርጅት ማሳወቂያ ላይ መረ
62.6 ቢሊየን ብር ውል የተገባለት የሚኤሶ - ድሬዳዋ ፍጥነት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት የጨረታ ሂደቱ ምን ይመስላል? 🚨ከዓለም ባንክ ድህረገጽ ላይ ይፋ ከሆነው የአሸናፊ ድርጅት ማሳወቂያ ላይ መረዳት እንደሚቻለው ፕሮጀክቱ በሁለት ሎት ተከፍሎ የተከናወነ ነው። 🚨ሎት 1 ላይ 5 ተጫራቾች የተሳተፉ ሲሆን 4 የቻይና እና አንድ የህንድ ድርጅቶች ናቸው። 📍አሸናፊው ድርጅት ለዚህ ሎት 31.14  ቢሊየን ብር (172.9 ሚሊየን በዶላር እና 9.3 ቢሊየን በብር) ያቀረበ ሲሆን በሌሎች ተጫራቾች ከቀረቡት  ዋጋዎች መካከል ከፍተኛው 39.1 ቢሊየን  ብር መሆኑን ያሳያል። 🚨 ሎት 2 ላይ 4 የቻይና ድርጅት የተሳተፉ ሲሆን አሸናፊው ድርጅት ለዚህ ሎት 31.4 ቢሊየን ብር (174.3 ሚሊየን በዶላር እና 9.4 ቢሊየን በብር) አቅርቧል። ለዚህ ሎት በሌሎች ተጫራቾች ከቀረበው ዋጋ  ከፍተኛው 38.5 ቢሊየን  ብር መሆኑን ያሳያል። 🚨 የፕሮጀክቱ የውል ጊዜ አራት ዓመት ሆኖ ዲዛይንና ግንባታው (Design-Build) በስራ ተቋራጩ የሚከናወን  መሆኑም ተጠቅሷል። ኮንትራቱ የtolling መሰረተ ልማቶች እና Intelligent Transportation System (ITS) አካቷል። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👵 Discussion: @procinsightet2

💥 መልካም ዜና ከ Noon Building Material 💥 - ለውድ ደንበኞቻችን በአይነቱ ለየት ያለ channel ይዘን መጥተናል, የ ዕቃዎችን ውድነት በማስመልከት የተዘጋጀ :: - በጅምላ ዋጋ
💥 መልካም ዜና ከ Noon Building Material 💥 - ለውድ ደንበኞቻችን በአይነቱ ለየት ያለ channel ይዘን መጥተናል, የ ዕቃዎችን ውድነት በማስመልከት የተዘጋጀ :: - በጅምላ ዋጋ እንሸጣለን:- - በየቀኑ የዋጋ ዝርዝር - ኦርጅናል እቃዎችን - አዳዲስ ምርቶችን $$ ሁሉንም የህንፃ መሳሪያዎች $$ በየቀኑ የዋጋ ዝርዝር $$ ኦርጅናል አቃዎች ብቻ ነው የሚያገኙት አድራሻ :- መርካቶ አድማስ ህንፃ F136B 📌 Contact +251912347922 or 0911943313 @Hamdi_Ah 🛍ቻናላችን :- @nuunhardwarestore

በኮንትራክሽኑ ዘርፍ የተሰጡ ሰበር ውሳኔው ህግ ናቸው። ይጠቅማሉ።

🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱 Red brick:- This is the classic brick color that you see Quality with affordable price 🧱ጥራ
🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱 Red brick:- This is the classic brick color that you see Quality with affordable price 🧱ጥራት ያላቸውን እና ለተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የቀይ ሸክላ ጡቦችን እናመርታለን። 🧱 ለሙሉ የቤት ግንባታ፣ 🧱ለባንክ ቤት ካዝና፣ 🧱 ለግቢ አጥር ማጠሪያ፣ 🧱 ለመንገድ ዳር ጠርዞች፣ 🧱  ለሆቴሎች፣ሬስቶራንት፣እና ካፌዎች ማሳመሪያ ፣ 🧱 ለx-ray ክፍሎች፣ 🧱 ለፍሳሽ ማንዋሎች፣ 🧱 ለኪችን ሲንክ ማስቀመጫ ፣ 🧱 ለሻወር ገንዳ ማሰቀመጫ፣ 🧱 የPBC ፍሳሽ ማስወገጃ ለመሸፈን፣ 🧱 ለአበባ መትከያ 🧱 ለብረት ማቅለጫ ፈርኒስ፣ 🧱 ለፒዛ ኦቭን፣ 🧱 ለምድጃ፣ 🧱 ለቆሻሻ ማቃጠያ፣    NEW POINT BRICK FACTORY *We produced best quality clay bricks for various construction purposes. 🧱 For building construction, 🧱 For bank vaults, 🧱 Fence for the yard, 🧱 For road edges, 🧱 For Hotels,Restaurants,and Cafes decoration, 🧱 For x-ray rooms, 🧱 For manuals, 🧱 For kitchen, 🧱 For shower tray 🧱 To cover PBC drains, 🧱 For garden, 🧱 Furnace For steel factory, 🧱 For pizza oven, 🧱 For waste incinerator, 🧱 For more information join our telegram channel 🧱Order now 📲0912854327,0902378888 🧱"Quality is our first priority 🧱Thank you 谢谢

የግሩፑ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ የድምድማት ፕሮግራም ተካሄደ ♦️የኤርፖርቱን ከተማ ቻይናዎች ሳይገነቡት አይቀርም ▭▭▭▭▭▭▭▭▭ ላለፉት ሁለት አመታት በቻይናው China Civil Enginee
+2
የግሩፑ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንፃ ግንባታ የድምድማት ፕሮግራም ተካሄደ ♦️የኤርፖርቱን ከተማ ቻይናዎች ሳይገነቡት አይቀርም ▭▭▭▭▭▭▭▭▭ ላለፉት ሁለት አመታት በቻይናው China Civil Engineering Construction Corporation (CCECC) እየተገነባ ያለው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት ግንባታ የዋናው ሕንፃ የመጨረሻ ከፍታ 45 ሜትር ላይ መድረሱን የቻይና ሚዲያዎች እየዘገቡት ነው።
የግንባታው ፕሮጀክት ከ33,560 ካሬ ሜትር በላይ በሆነ የመሬት ስፋት ላይ ያረፈ ሲሆን፣ በጠቅላላው ስድስት የተለያዩ ሕንፃዎችን ያካተተ ነው። ግንባታው ሙሉ በሙሉ በነሐሴ 2026 ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።
ሰኞ ዕለት በተካሄደው የሕንፃው ድምድማት ፕሮግራም ላይ የግሩፑ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው China Civil Engineering Construction Corporation (CCECC) በቢሾፍቱ የሚገነባው ግዙፍ ኤርፖርት እንዲገነባ ግብዣ ማቅረባቸውን ዤኑዋ ዘግቧል። ▭▭▭ ኢንፍራኮን ሚዲያን ፎሎው እና ሼር ያድርጉ! የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ t.me/infraconmedia

+2
ERA Quality Manual Vol.3 በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (ERA) ድህረገጽ ከሚገኙ የጥራት ማንዋል (Quality Manual) መካከል የግዥ ሂደቶች የሚመሩባቸው ስታንዳርድ  ሰነዶች ክፍል አንዱ ሲሆን በጣም ጠቃሚ ናቸው። ለሌሎች የመንግስት ተቋማትና የግል ድርጅቶችም እንደ መነሻ የሚጠቅሙ ጠቃሚ ሰንዶች በመሆናቸው ☝️👇 አጋራናችሁ፤ በተለይ ለግንባታ እና የማማከር አገልግሎት ጨረታዎች Standard Forms, Reports, Checklists, Memos and Letters ተካተውበታል። 📢 Join: @procinsightet 📬 Contact: @Procinsight_bot 👵 Discussion: @procinsightet2

China porcelain ceramic 60x60cm 80x80cm 60x120cm 20x1m 30x60 30x30 available 0911798889
+9
China porcelain ceramic 60x60cm 80x80cm 60x120cm 20x1m 30x60 30x30 available 0911798889