ch
Feedback
Assaye Derbie

Assaye Derbie

前往频道在 Telegram

📈 Telegram 频道 Assaye Derbie 的分析概览

频道 Assaye Derbie (@asayede) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 335 名订阅者,在 博客 类别中位列第 2 651,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 347

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 335 名订阅者。

根据 26 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -104,过去 24 小时变化为 -8,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 35.99%。内容发布后 24 小时内通常能获得 12.61% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 158 次浏览,首日通常累积 1 808 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 30

📝 描述与内容策略

尚未提供频道描述。

凭借高频更新(最新数据采集于 27 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 博客 类别中的关键影响点。

14 335
订阅者
-824 小时
-327
-10430
帖子存档
"ቀባሪ አታሳጣኝ" እያለች ስትለምን፥ ስትጸልይ ኑራ፥ ባልገባት ምክንያት ፥ ጧሪዎቿን ቀብራ አየኻት ኢትዮጵያን ፥ አየኻት እማማን መውደቂያ ታዛ አጥታ ፥ በእንባዋ ስትረግመን?! ለዚህች እናት ማረፊያ
"ቀባሪ አታሳጣኝ" እያለች ስትለምን፥ ስትጸልይ ኑራ፥ ባልገባት ምክንያት ፥ ጧሪዎቿን ቀብራ አየኻት ኢትዮጵያን ፥ አየኻት እማማን መውደቂያ ታዛ አጥታ ፥ በእንባዋ ስትረግመን?! ለዚህች እናት ማረፊያ የሚሆን አንድ ክፍል ቤት የላችሁም?? በእጃቸው የያዙት ወረቀት ላይ የተፃፈው የብሶት ማመልከቻ በግዕዝ ፊደላት ፈንታ በላቲን የተፃፈ ቢሆን ኖሮ ከአዲስ አበባ ያባረራቸው አካል ኮንዶሚንየም ይሰጣቸው ነበር።

አገር አልባው ባላገር ▬▬▬▬ ከጭፍጨፋ ተርፈው፣ ንብረታቸውን ተዘርፈውና ጎጇቸው ሲቃጠል አይተው ከወለጋ ምድር ከተፈናቀሉ በኋላ ለረዥም ጊዜያት ቢንከራተቱም ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር ቀርቶ ኬንዳ
አገር አልባው ባላገር ▬▬▬▬ ከጭፍጨፋ ተርፈው፣ ንብረታቸውን ተዘርፈውና ጎጇቸው ሲቃጠል አይተው ከወለጋ ምድር ከተፈናቀሉ በኋላ ለረዥም ጊዜያት ቢንከራተቱም ኢትዮጵያ የምትባለውን አገር ቀርቶ ኬንዳ ዘርግተው የሚሰፍሩበት ምድር ማግኘት አልቻሉም፡፡ ወለጋ ድረስ ይመጣል ብለው ሲጠብቁት የነበረውን መንግሥት አዲስ አበባ ድረስ መጥተው ቢፈልጉትም ‹‹ከተማዬን ታቆሽሻላችሁ›› ብሎ አባረራቸው እንጂ መጠጊያ ታዛ አልሰጣቸውም፡፡ ብአዴንና አብንም በእኒህ አማራዎች ላይ የሚፈጸመውን ታይቶ የማይታወቅ የግፍ ግፍ ተመልክተው የመፍትሔ አካል ለመሆን አልደፈሩም፡፡ በሄዱበት እየተከተሉ ‹‹አይዟችሁ›› ከሚሏቸው የባልደራስ አመራሮች ውጭ ‹‹ኑ ወደ እኛ›› ብሎ የሚጠራቸው ወገን አላገኙም፡፡ በአረብ አገር የሚሰቃዩ ወገኖቻቸውን ያህል የሚሰቃዩበት የማጎሪያ ካምፕ የሚያመቻችላቸው መንግሥት ማግኘት አልቻሉም፡፡ አስከሬን እንኳን የሚቀበርበት ሁለት ክንድ መሬት አያጣም፡፡ ቆሻሻ እንኳን የሚጣልበት ኮሲ አይቸግረውም፡፡ በሕይወት ያሉት እኒህ አማራዎች ግን የሚያርፉበት የብስ ማግኘት አልቻሉም፡፡ ምን ብናደርግ ይሻል ይሆን? መፍትሔ አምጡ እስቲ...! Share

አራት ወረዳ ተቆጣጠረ የሚባለው የኦነግ ታጣቂ ከአራት ኪሎው መንግሥት ቁጥጥር ውጭ ከመሰለህ ተሳስተኻል። ይህ ሁሉ ቲያትር በእነ ገተት የሚቀናበር ነው‼️😆 ሕዝባዊ ተቀባይነት እያጡ የመጡት ንጉሥም
አራት ወረዳ ተቆጣጠረ የሚባለው የኦነግ ታጣቂ ከአራት ኪሎው መንግሥት ቁጥጥር ውጭ ከመሰለህ ተሳስተኻል። ይህ ሁሉ ቲያትር በእነ ገተት የሚቀናበር ነው‼️😆 ሕዝባዊ ተቀባይነት እያጡ የመጡት ንጉሥም በ"ትህ-ኦነግ" ድጋፍ ዙፋናቸውን ለማስቀጠል ሳያስቡ አልቀሩም።

ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ "ለፓርላማው ያቀረብኳቸው ጥያቄዎች ተቆርጠው ቀሩብኝ" የሚል ይዘት ያለው ጽሑፍ ለጥፎ አየሁ። እኔ ደግሞ ዶክተር ደሳለኝን "መላሽ በሌለበት መድረክ ላይ ጥያቄህን አታባክን" ብዬ
ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ "ለፓርላማው ያቀረብኳቸው ጥያቄዎች ተቆርጠው ቀሩብኝ" የሚል ይዘት ያለው ጽሑፍ ለጥፎ አየሁ። እኔ ደግሞ ዶክተር ደሳለኝን "መላሽ በሌለበት መድረክ ላይ ጥያቄህን አታባክን" ብዬ መምከር እፈልጋለሁ። በበኩሌ ከምክር ቤት ይልቅ እስር ቤት መግባት የምመርጥ ቢሆን እግዜር እረግሞኝ ፓርላማ ብገባ ግን ለጠሚው የማቀርባቸው ጥያቄዎች እንዲህ የሚሉ መሆናቸው አይቀርም። 1. የምግብ ምርጫዎ ምንድን ነው? 2. የቤተ መንግሥቱ አዝመራ ከምን ደረሰ? 3. ቀበሮዎቹ ደህና ናቸው ወይ? 4.ያች ፈረንሳዊት ትደውላለች ወይ? 5. በሙቀት ስንቃጠል እያዩ ደመና መጭመቁን የተውት ምን ሆነው ነው? . . ከዚህ ውጭ ከእሳቸው መልስ እና መፍትሔ ይገኛል ብዬ አገራዊ ጥያቄ ለማቅረብ አልደፍርም።

ሳምንታዊ ቸክሊስት (አሳዬ ደርቤ) ▬▬▬▬ ➔ፋኖን የማሰልጠን ተግባር እንዲስፋፋ መቀስቀስ እና የሥልጠና መርሐ ግብሮችን መደገፍ፤ ➔በኦነግ ከወለጋ ተፈናቅለው፤ በኦሮሚያ ብልጽግና ደግሞ ከአዲስ አበባ ለተሳደዱ አማራዎች ጥብቅና መቆም፤ ➔በድርድር ሒደቱ ላይ ከአብን ይልቅ የአቻምየለህን ሐሳብ በመውሰድ የአማራ ሕዝብ ውክልና እንዲኖረው ጥረት ማድረግ፤ ➔በወልቃይትና በራያ በኩል ዳግም ጥቃት ለመክፈት ያሰፈሰፈውን ወረራ ሊመክት የሚችል ሃይል እንዲዘጋጅ መቀስቀስ፤ ➔አሸባሪው ሃይል በአፋር ሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል ለአለም አቀፉ ማሕበረሰብ ማሳወቅና ለተፈናቃዮች ድጋፍ ማድረግ፤ ጨምሩበት Share

የነበራቸውን ጸጋ ተገፍፈው፣ በመረጡት አካል ተክደው፣ በከባድ የሕልውና አደጋ ውስጥ የሚኖሩ ወገኖች "ጸጋ ተልከሰከሰች" የሚል ጽሑፍ የያዘ ቲሸርት አሳትመው ሙድ ሲይዙ ጤነኝነታቸው ያጠራጥረኛል። . በሱስ ብዛትና በተስፋ ማጣት ግንባራቸው አሸብሽቦ ፣ ቆዳቸው እንደ ሽቦ አልጋ እረግቦ ያለ እድሜያቸው ያረጁ ወጣቶች "ጂጂ ጠቆረች" እያሉ በኀዘን ሲቆራመዱ ፊታቸውን የሚመለከቱበት መስታወት ገዝቶ መስጠት ያምረኛል።

ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ሸዋ ወሎዬ የሚባል Cultural Identity እንጂ ፣ ጎንደሬ ወይም ጎጃሜ፣ ሸዋ ወይም ወሎዬ የሚባል Political Identity የለም። የነገ እጣ ፈንታህ አንድ ነው። ሸኔም
ጎንደሬ፣ ጎጃሜ፣ ሸዋ ወሎዬ የሚባል Cultural Identity እንጂ ፣ ጎንደሬ ወይም ጎጃሜ፣ ሸዋ ወይም ወሎዬ የሚባል Political Identity የለም። የነገ እጣ ፈንታህ አንድ ነው። ሸኔም በለው ወ*ያኔ አሜሪካም በለው ብልጽግና "አማራ" ብሎ ነው የሚውያቅህ! ትንግርቱ ገ/ጻድቅ (ረ/ፕሮፌሰር)

ለመጽሐፋችን የሕትመት ድጋፍ በጠየቅነው መሠረት የመጽሐፉን አስፈላጊነቱን የተረዱ ሁለት ደግ ሰዎች 20+30=50% ወጪውን ሲሸፍኑ ሌሎች ደግሞ 20 % ድጋፍ አድርገው 70% ደርሰናል። እናምከመጽሐፉ የሚገኘው ገቢ ለተሰው የፋኖ ቤተሰቦች የሚውል መሆኑን በመረዳት በዚህ ታሪካዊ መጽሐፍ ሕትመት ላይ አሻራችሁን ማሳረፍ የምትሹ ወገኖች በኢንቦክስ መጥታችሁ "አለን" ትሉኝ ዘንድ እጋብዛለሁ።

ለእነዚህ አርሶ አደሮች ጥርና የካቲት ማለት አዝመራቸውን ሰብስበው፣ አዲስ ቦላሌና ቀሚስ አሰፍተው ልጆቻቸውን የሚድሩበት ነበረ። አሁን ግን ለረዥም ዘመን ጥረው የገነቡት ሰቀላ ቤት፣ ያፈሩት ጥሪት፣
+2
ለእነዚህ አርሶ አደሮች ጥርና የካቲት ማለት አዝመራቸውን ሰብስበው፣ አዲስ ቦላሌና ቀሚስ አሰፍተው ልጆቻቸውን የሚድሩበት ነበረ። አሁን ግን ለረዥም ዘመን ጥረው የገነቡት ሰቀላ ቤት፣ ያፈሩት ጥሪት፣ ወደ ጎተራ ያስገቡት ምርት በዘረኞች ጥቃት ተቃጥሎ ልጆቻቸውን ጎጆ በሚያወጡበት ወቅት ወደ ጎዳና ወጥተዋል። ለሚጋቡ ልጆቻቸው ዳስ ጥለው በሚደሰቱበት የጫጉላ ወራት፣ ማንነትን መሠረት ባደረገ ጥቃት ለሚገደሉ ልጆቻቸው የእዝን ድንኳን ተክለው ማንባት ቢሰለቻቸው.... ሕግ በሌለበት ምድር ላይ "በሕግ አምላክ" እያሉ መሞት፣ ከአገር አልባ ሰማይ ስር "የአገር ያለህ" እያሉ ኡኡ ማለት ቢቸካቸው....ይሄው ከጎዳና ላይ ወድቀው የአምላክን ፍርድ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።

ሰፊው ሕዝብ በታክሲ መሄድ ከብዶት ኤርገንዶውን ገርግዶ በእግሩ መጓዝ ጀምሯል። ጠባቡ አመራር ደግሞ በV-8 መኪና መንቀሳቀስ አሰልች ሆኖበት በኪራይ አውሮፕላን መንፈላሰስ ይዟል። በአጭር ጊዜ ውስጥ
ሰፊው ሕዝብ በታክሲ መሄድ ከብዶት ኤርገንዶውን ገርግዶ በእግሩ መጓዝ ጀምሯል። ጠባቡ አመራር ደግሞ በV-8 መኪና መንቀሳቀስ አሰልች ሆኖበት በኪራይ አውሮፕላን መንፈላሰስ ይዟል። በአጭር ጊዜ ውስጥ የሕዝቡን ኑሮ አራቁቶ በቅንጦት የሚሰቃዩ አመራሮችን የቀፈቀፈ ፓርቲ ይሄን ዐየሁ!!😆

የተወሰኑ ኮፒዎችን የሕትመት ወጪ በመሸፈን በዚህ ታሪካዊ መጽሐፍ የምስጋና ገጽ ላይ ሥምዎን ተጠቃሽ ያድርጉ!! https://www.facebook.com/100999818947578/posts/16452888
የተወሰኑ ኮፒዎችን የሕትመት ወጪ በመሸፈን በዚህ ታሪካዊ መጽሐፍ የምስጋና ገጽ ላይ ሥምዎን ተጠቃሽ ያድርጉ!! https://www.facebook.com/100999818947578/posts/164528885928004/

የተወሰኑ ኮፒዎችን በማሳተም ሥምዎን በዚህ ታሪካዊ መጽሐፍ የምስጋና ገጽ ላይ ተጠቃሽ ያድርጉ!

ከስድስት ወር በፊት የአማራ ሳይንት ፈርጥ ስለሆነው ስለ ኮሎኔል ጌታቸው ተፈራ ጀግንነት ስተርክ "ሙገሳህ የትውልድ መንደርን መሠረት ያደረገ ነው" ብለው የተከራከሩኝ ነበሩ። ከሰሞኑን ግን ያ አድናቆ
+1
ከስድስት ወር በፊት የአማራ ሳይንት ፈርጥ ስለሆነው ስለ ኮሎኔል ጌታቸው ተፈራ ጀግንነት ስተርክ "ሙገሳህ የትውልድ መንደርን መሠረት ያደረገ ነው" ብለው የተከራከሩኝ ነበሩ። ከሰሞኑን ግን ያ አድናቆቴ እውነት መሆኑን በሚገልጽ መልኩ፣ የበላይ ዘለቀን ብርጌድ የሚመራው ይህ ኮሎኔል "በሁሉም አውደ ውጊያዎች ላይ ያሳየኸው ጀግንነት እና ብቃት ገራሚ ነበር" ተብሎ ከአማራ ልዩ ሃይል በአንደኝነት ተመርጧል። እንኳን ደስ አለህ አንተ የአማራ ኩራት!‼️

በአፋርም ሆነ በአማራ፣በሶማሌም ሆነ በትግራይ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ እና በክልላዊ ፓርቲያቸው እቅድ የሚመራ ነው። ግቡ ደግሞ ልክ እንደ ሸገር የተሰለቀጠች አገር እውን ማድረግ ነው።

ሕግ ቢኖር ኑሮ ፥ ዳኛ ቢኖር ኑሮ፤ አሳሪው ነበረ ከታሜ ክፍል ውስጥ ፥ የሚገኝ ታጉሮ። ፍቱት...‼️ ንጹሕ አትወንጅሉ ፥ በእራሳችሁ ጥፋት።
ሕግ ቢኖር ኑሮ ፥ ዳኛ ቢኖር ኑሮ፤ አሳሪው ነበረ ከታሜ ክፍል ውስጥ ፥ የሚገኝ ታጉሮ። ፍቱት...‼️ ንጹሕ አትወንጅሉ ፥ በእራሳችሁ ጥፋት።

የአማራ ብልጽግና አመራሮች በብድር ሥም የዘረፉት 60 ሚሊዮን ብር በአስቸኳይ ወደ ካዝናው መመለስ ይኖርበታል! የክልሉን አለመረጋጋት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ዝርፊያ የፈጸሙ አመራሮችም በሕግ ሊጠየቁ ይገባል።

አንዳንድ መንግሥታት የሕዝብን የዳቦ ጥያቄ መመለስ ባለመቻላቸው ሲገረሰሱ አይተናል። ድግስ ወዳዱ ብልጽግና፣ ከሕዝብ ርሐብ ባለፈ የአመራሩን ጥጋብ ማስታገስ ተስኖት በውስኪ ስካር እየተንገዳገደ ነው።😆

የእለት ጉርሱን ተነጥቆ ፆም ያድር ዘንድ የተፈረደበትን ሕዝብ "ከርሳም" እና "ፈርሳም" ብሎ የሚዘልፍ ጥጋበኛ አመራር ለአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ቀርቶ ለአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት አይመጥንም።