ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

MoR West Addis Ababa (ምዕራብ)

前往频道在 Telegram

This is official Telegram Channel of MoR-West Addis Ababa branch. Join the channel. Training Dep. 0115585348, E-Tax 0114700197

显示更多

📈 Telegram 频道 MoR West Addis Ababa (ምዕራብ) 的分析概览

频道 MoR West Addis Ababa (ምዕራብ) (@morwestaa) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 14 589 名订阅者,在 政治 类别中位列第 3 745,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 432 位。

📊 受众指标与增长动态

自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 14 589 名订阅者。

根据 16 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 201,过去 24 小时变化为 15,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 51.69%。内容发布后 24 小时内通常能获得 18.47% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 7 541 次浏览,首日通常累积 2 694 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 13。

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“This is official Telegram Channel of MoR-West Addis Ababa branch. Join the channel. Training Dep. 0115585348, E-Tax 0114700197”

凭借高频更新(最新数据采集于 17 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 政治 类别中的关键影响点。

14 589
订阅者
+1524 小时
+677 天
+20130 天
帖子存档
05-02-2019 ዓ.ም                                                 ታትመው የደረሱ ደረሰኞችን ይመለከታል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራችሁ ከዚህ በታች የተገለፀው ድርጅቶች በሙሉ ደረሰኞች ዝርዝር ከብርሃንና ሰላም የህትመት ትዕዛዝ ደርሶላችሁ ወደ ቅ/ጽ/ቤቱ የመጣ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በሶስት ተከታታይ የስራ ቀናት እንድትረከቡ እየገለጽን ከተገለፀው ቀን ውጪ የሚመጣ ድርጅት የመጋዘን ኪራይ የምናስከፍል መሆኑን አውቃችሁ በተገለጸው ቀን እንድትወስዱ እያሳሰብን ለመረከብ ስትመጡ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥራችሁ ያለበትን ተራ ቁጥር እና የሚከተሉትን ማለትም 1. የደረሰኝ ህትመት የተጠየቀበት ደብዳቤ ዋናና ኮፒ 2. ዊዝሆልድ የተደረገበትን ደረሰኝ ዋናውን እና ኮፒ (ዋናውን ለብርሃንና ሰላም ካስረከባችሁ ኮፒ) 3. ብርሃንና ሰላም ያስቆረጣችሁትን የክፍያ ደረሰኝ ዋና እና ከፒ 4. በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ ውክልና ይዛችሁ መምጣት የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- https://t.me/morwestaa https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322 https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto www.tiktok.com/@user1449328103985

አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶች የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በነሃሴና መስ
+3
አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶች የግማሽ ቀን ስልጠና ተሰጠ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በነሃሴና መስከረም ወር ላወጡ ድርጅቶች በመሠረታዊ የታክስ ህጎች ላይ የአንድ ጊዜ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ስለታክስ ግንዛቤ ኖሯቸው መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲረዱ ማድረግ፤ ሳያውቁ ወደቅጣት እንዳይገቡ ግንዛቤ መፍጠር የስልጠናው ዓላማ መሆኑን ስልጠናውን የሰጡት የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ ኃይለሩፋኤል ኑርጊ በመግለፅ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ቀጣይ ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባር አስረድተዋል፡፡ በስልጠናው ስለ ታክስ ምንነት፣ የደረሰኝ ህትመትና አጠቃቀም፣ ግብር ቀንሶ ስለማስቀረት (ዊዝሆልዲንግ) ታክስ፣ ስለተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝና ሌሎች አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ማወቅ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከታክስ ህጉ አንፃር ገለፃ አድርገዋል፡፡ ከግብር ከፋዮች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- https://t.me/morwestaa https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322 https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto www.tiktok.com/@morwestaa

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የነሃሴ ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የነሃሴ ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን የስራ ኃላፊዎች
+6
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የነሃሴ ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የነሃሴ ወር ዕቅድ አፈጻጸሙን የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በዛሬው ዕለት ገምግሟል፡፡ የ2019 በጀት ዓመት የነሃሴ ወር አፈጻጸማችን የሚበረታታ ነው ለዚህ ደግሞ የአመራሩ፤ የሰራተኛውና የታማኝ ግብር ከፋዮች ሚና የጎላ በመሆኑ ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት የስራ አስኪያጅ ተወካይና የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ቢሊሱማ ባይሳ በቀጣይ ወራት ትኩረት ተሰጥቷቸው መከናወን ስለሚኖርባቻው ስራዎች በዝርዘር አንስተዋል፡፡ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በነሃሴ ወር 301,770,997.15 (ሦስት መቶ አንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰባ ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ሰባት ከ15/100) ብር ለመሰብሰብ አቅዶ 435,401,862.39 (አራት መቶ ሰላሳ አምስት ሚሊዮን አራት መቶ አንድ ሺህ ስምንት መቶ ስድሳ ሁለት ከ39/100) ብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 144.28 በመቶ ማሳካት መቻሉን የዕቅድና በጀት ክትትል ቡድን አስተባባሪ አቶ ጎሶምሳ ተሰማ ገልፀዋል፡፡ በወሩ የተናወኑ ዝርዝር ተግባራት፤ የጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎችና ቀጣይ ተግባራትን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ በቀረበው ሪፖርትና ቀጣይ አቅጫዎች ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን የታክስ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሺሻይት አባዲ እና የተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሂካ ባርባ በተነሱ ጉዳዮችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ከዘርፋቸው አንጻር ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- https://t.me/morwestaa https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322 https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto

+8
4 የተጨማሪ ዕሴት ታክስ vat New.pptx1.61 MB

+2
1_New_ከመቀጠር_የሚገኝ_ገቢ_እና_የወጪ_መጋራት_With_Intro.pptx6.48 MB

በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በሕፃናት ማቆያ ውስጥ ለቆዩ ህፃናት የሽኝት መርሃ ግብር ተካሄደ። በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሕፃናት ማቆያው ውስጥ ሲንከባከ
+9
በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ በሕፃናት ማቆያ ውስጥ ለቆዩ ህፃናት የሽኝት መርሃ ግብር ተካሄደ። በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በሕፃናት ማቆያው ውስጥ ሲንከባከባቸው የቆዩትንና አሁን ላይ ቅድመ-መደበኛ ትምህርትን ለሚቀላቀሉ አራት ዓመት ለሞላቸው ሕፃናት የሽኝት መርሃ ግብር ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተቋማዊ አቅምና ድጋፍ ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ሂካ ባርባ እንኳን ለ2019 አዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞታቸውን የገለፁ ሲሆን የህጻናት ማቆያው በ2018 በጀት ዓመት ለ49 ህፃናት አገልግሎት እየሰጠ መቆየቱን በማንሳትከነዚህ መካከል 8 ህፃናት ቅድመ መደበኛ ትምህርትን ስለሚቀላቀሉ የሽኝት መርሃ ግብሩ መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡ የተቋሙ ሴት ሰራተኞች ስራቸውን ተረጋግተው እንዲሰሩ የህጻናት ማቆያው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው በማንሳት ማቆያው በ2018 በአዲስ አበባ መስተዳደር ከተመረጡት የህፃናት ማቆያዎ ማዕከላት ውስጥ አንደኛ ደረጃ ሞዴል ሆኖ በመመረጡ ለአመራሮችና ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ ለህፃናቱ ሰርቲፍኬት የመስጠትና የተለያዩ ፕሮግራሞች የቀረቡ ሲሆን በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ተወካይና የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ቢሊሱማ ባይሳ ማጠቃለያ መልዕክትና ቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- https://t.me/morwestaa https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322 https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto www.tiktok.com/@morwestaa

አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶች የአንድ ጊዜ ስልጠና ተሰጠ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶ
+2
አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶች የአንድ ጊዜ ስልጠና ተሰጠ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ላወጡ ድርጅቶች በመሠረታዊ የታክስ ህጎች ላይ የግማሽ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ስለታክስ ግንዛቤ ኖሯቸው መብታቸውንና ግዴታቸውን እንዲረዱ ማድረግ፤ ሳያውቁ ወደቅጣት እንዳይገቡ ግንዛቤ መፍጠር የስልጠናው ዓላማ መሆኑን ስልጠናውን የሰጡት የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ አቶ ኃይለሩፋኤል ኑርጊ በመግለፅ አዲስ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ቀጣይ ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባር አስረድተዋል፡፡ በስልጠናው ስለ ታክስ ምንነት፣ የደረሰኝ ህትመትና አጠቃቀም፣ ግብር ቀንሶ ስለማስቀረት (ዊዝሆልዲንግ) ታክስ፣ ስለተጨማሪ እሴት ታክስ፣ ስለሂሳብ መዝገብ አያያዝና ሌሎች አዲስ የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥር ያወጡ ድርጅቶች ማወቅ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከታክስ ህጉ አንፃር ገለፃ አድርገዋል፡፡ ከግብር ከፋዮች ለተነሱ ጥያቄዎችም ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- https://t.me/morwestaa https://www.facebook.com/profile.php?id=100090259834322 https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto www.tiktok.com/@morwestaa

በ2019 በጀት ዓመት የአገልግሎት አሠጣጥን ለማሻሻል እና የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ልዩ ድጋፍ የሚደረግባቸዉ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የመግቢያ ውይይት ተደረገ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አ
+3
በ2019 በጀት ዓመት የአገልግሎት አሠጣጥን ለማሻሻል እና የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ልዩ ድጋፍ የሚደረግባቸዉ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የመግቢያ ውይይት ተደረገ በገቢዎች ሚኒስቴር የምዕራብ አዲስ አበባ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የአገልግሎት አሠጣጥን ለማሻሻል እና የገቢ ዕቅድ ለማሳካት ልዩ ድጋፍ የሚደረግባቸዉ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የመግቢያ ውይይት ከዋናው መስሪያ ቤት ከመጡ የድጋፍና ክትትል ቡድን አባላት ጋር ተደርጓል፡፡ ዋናው መስሪያ ቤት ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን በመደገፍ ውጤታማነቱን ማስቀጠል  የድጋፍና ክትትሉ ዋና ዓላማ መሆኑን በገቢዎች ሚስቴር የታክስ ከፋዮች ምዝገባና አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ደረጄ ፋና ገልፀዋል፡፡ የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፤ የስራ ባህልን ማሳደግ፤ ትብብርና መደጋገፍን ማጠናከር ለውጤታማ አፈጻጸም መሰረቶች መሆናቸውን የጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አቶ መስፍን ጉልላት አንስተዋል፡፡ ወደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለመጡት የድጋፍና ክትትል ቡድን አመራሮች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ተወካይና የታክስ ስርዓት ዘርፍ ም/ስራ አስኪያጅ አቶ ቢሊሱማ ባይሳ የተሰጠንን ተልዕኮ በብቃት ለመፈጸም አመራሩንና ፈጻሚውን ለተልዕኮ ዝግጁ የማድረግና ስምሪት የመስጠት ስራዎች መከናወናቸውን በማንሳት የገቢ ዕቅድን ማሳካት ብቻ ሳይሆን የአገልግሎት አሰጣጥን እና የፊዝካል ስራዎችን በጥራት ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡ በመግቢያ ውይይቱ ላይ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ም/ስራ አስኪያጆች፤ የስራ ሂደት አስተባባሪዎችና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን ቀጣይ ስለሚከናወኑ ተግባራት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ተችሏል፡፡ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት፡- https://www.youtube.com/@morwestaddisababasto

+1
Purchase format.xlsx0.19 KB