ch
Feedback
Akaki Kale Heywet Church School📖 አቃቂ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ ት/ቤት

Akaki Kale Heywet Church School📖 አቃቂ ቃለ ሕይወት ቤ/ክ ት/ቤት

前往频道在 Telegram
1 553
订阅者
+324 小时
+37 天
+2230 天
帖子存档
የ2019 ትምህርት ዘመን የማላቅ ስትራቴጂ ከመስከረም 9 ጀምሮ ተግባራዊ መደረግ እንደሚጀምር ተገለፀ:: (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) የ2019 ትምህርት ዘመን የማላቅ ስትራቴጂ በሁሉም ክላስተር ማዕከላት ቅዳሜ መስከረም 9/2019 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጻል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ጥላዬ ዘውዴ የስትራቴጂውን ቀጣይ አፈፃፀም አስመልክቶ ውይይት መነሻ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት የማላቅ ስትራቴጂ በ2018 ትምህርት ዘመን በበጋና በክረምት ሥራ ያስገኘው ውጤት ተገምግሞ ውጤታማ መሆኑ መረጋገጡን ገልፀው፤ በስትራቴጂው የተመዘገበውን ውጤት በተሻል መንገድ ለመድገምና ውጤታማ የትምህርት ስርዓትን ለማረጋገጥ ቢሮው በትኩረት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል:: ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም የAB ስትራቴጂ በተያዘው እቅድ መሰረት ሰኞ መስከረም 11/2019 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑን ገልፀዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ሳምሶን መለሰ ስትራቴጂውን በአግባቡ ለመተግበር ወላጆች የትምህርት ማህበረሰቡ እንዲሁም ተማሪዎችና መምህራን በአቋም መስራት እንዳለባቸው አሳስበው ቢሮው የትምህርት አጀማመሩን አስመልክቶ ተከታታይ ድጋፍና ክትትል የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል:: የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ተስፋዩ አበራ በበኩላቸው በ2019 የትምህርት ዘመን ስኬታማ የትምህርት ስራን ለማከናወን ሁሉም የትምህርት ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡ ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aacaebc

ትምህርት ሚኒስቴር በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የምደባ ምርጫቸውን መሙላት እንደሚችሉ ገልፃል። (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) በ2
ትምህርት ሚኒስቴር በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የምደባ ምርጫቸውን መሙላት እንደሚችሉ ገልፃል። (መስከረም 7/2019 ዓ.ም) በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ-ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫቸውን ከመስከረም 7/2019 ዓ.ም እስከ መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ትምህርት ቤት መሄድ ሳይጠበቅባቸው ባሉበት ቦታ ሆነው ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም እራሳችሁ መሙላት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጻል። የማስፈንጠሪያ ሊንክ (Link): https://student.ethernet.edu.et/preferences ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https://linktr.ee/aebc

የ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ። መስከረም 4/2019 ዓም ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረ
የ2019 ዓ.ም የሬሜዲያል መርሐ ግብር የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ይፋ ሆነ። መስከረም 4/2019 ዓም ለ2019 ዓ/ም የሪሚዲያል መርሃ ግብር ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚያስችላቸው የመቁረጫ ነጥብ በተማሪዎች ውጤት፣ በዩኒቨርሲቲዎች የቅበላ አቅም፣ እና በሀገራዊ የትምህርት ፍትሃዊነት መርህ ላይ ተመስርቶ መወሰኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም መሰረት ከታችን የተገለጸውን ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ለሪሚዲያል መርሃ ግብር የዩኒቨርሲቲ ቅበላ ብቁ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል። 1. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ወንድ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 240 እና ከዚያ በላይ (40%) 2. የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 228 እና ከዚያ በላይ (38%) በልዩ ድጋፍ የሚታይ የተማሪ ምድብ 1. ከአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉሙዝ እና ጋምቤላ ክልሎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 2. ከአርብቶ አደርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የተፈጥሮ ወይም ማህበራዊ ሳይንስ ለተፈተኑ ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) 3. በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ ዓይነ ስውር ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ500 ውስጥ 185 እና ከዚያ በላይ (37%) 4. በተፈጥሮ ወይም በማህበራዊ ሳይንስ የተፈተኑ መስማት የተሳናቸው ወንድና ሴት ተማሪዎች 👉 ከ600 ውስጥ 222 እና ከዚያ በላይ (37%) https://t.me/kolfekeranioeducationbureau

ለአቃቂ ቃለ-ሕይወት ትምህርት ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ መምህራንና የትምህርት ቤት ማህበረሰብ በሙሉ! እንኳን ለ2019 ዓ.ም በስላምና በጤና  አደረሳችሁ! አደረሰን! እያልን የ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን   የመስከረም ወር የድርጊት መርሐ- ግብርና ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ ከተማሪዎች የሚጠበቀውን መላካችንን በፍቅር እናሳውቃለን።

#MoE የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተናን ወስደው በመደበኛ የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋምና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን ከነሐሴ 28 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ድረስ እንዲያስገቡ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ተማሪዎች ምርጫቸውን ትምህርት ቤት መሄድ ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው በኦንላይን ማስገባት ይችላሉ። የምርጫ ማስገቢያ ድረ-ገጹ፦ student.ethernet.edu.et ነው። - በሕክምና ምክንያት ልዩ ሁኔታ ያላቸው፣ - የአካል ጉዳተኛ የሆኑ፣ - ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች - ከ6 ወር በታች ሕፃን የሚያጠቡ እናቶች ተገቢውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ እንደሚጠበቅባቸውም ሚኒስቴሩ ገልጿል። https://t.me/kolfekeranioeducationbureau ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia

የአቃቂ ቃለ ሕይወት የክረምት ማላቂያ የማነ- ብርሐን ክላስተር ማዕከል ተማሪዎች በሙሉ! ነገ አርብ የክላስተር ማዕከል ትምህርት የሚጠናቀቅበትና እንዲሁም የፈተናና የሰርተፍኬት ቀን ስለሆነ ማንም ተማሪ እንዳይቀር ብሏል። የማነ- ብርሐን ክላስተር ማዕከል

7/12/2018ዓ.ም   ለማታ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ!   አቃቂ ቃለ ሕይወት በማታ ትምህርት መርሐ- ግብር ለ2019ዓ.ም ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ ይገኛል። በመሆኑም 11/12/2018ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት በአካል በመገኘት ምዝገባ እንድታከናውኑ ይሁን። ት/ቤቱ

ለውድ የተማሪ ወላጆችና አሳዳጊዎች በሙሉ ከትምህርት ቢሮ በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ከ6ኛ- 8ኛ ክፍል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት መማር ግዴታ መሆኑን አሳውቀን ከ ሰኞ 20/11/18ዓ.ም ጀምሮ ትምህርቱ መሰጠት የተጀመረ መሆኑን በድጋሚ እያሳወቅን እስካሁን ተመዝግባችሁ ላልጀመራችሁ ተማሪዎች ለሚፈጠረው ክፍተት ትምህርት ቤቱ ሀላፊነቱን የማይወስድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን። ት/ቤቱ

ለውድ የተማሪ ወላጆች በሙሉ ! የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ 1 ቀን ብቻ ቀርተውታል። ስለዚህ ቶሎ እንድትመዘገቡ ይሁን። ት/ቤቱ
ለውድ የተማሪ ወላጆች በሙሉ ! የነባር ተማሪዎች ምዝገባ ሊጠናቀቅ 1 ቀን ብቻ ቀርተውታል። ስለዚህ ቶሎ እንድትመዘገቡ ይሁን። ት/ቤቱ