💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀
前往频道在 Telegram
« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر» قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ ↓↓↓↓↓↓ @Ass_Selefyaa1bot @Ass_Selefyaa1bot
显示更多📈 Telegram 频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 的分析概览
频道 💎🎀የሰለፍያ ሴቶች ከቀይ ወርቅ የበለጠ ውድ ናቸው 💎🎀 (@https_asselefya1) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 814 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 6 308,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 574 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 814 名订阅者。
根据 29 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -207,过去 24 小时变化为 -14,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.87%。内容发布后 24 小时内通常能获得 6.08% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 575 次浏览,首日通常累积 840 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“« الـنِّـسَـاء الـسَّــلَــفِـيَّـة أَغْـلَى مِـنَ الـذَّهَـبِ الأحْـمَـر»
قال العلامة المحدث:مقبل الوادعي رحمه الله
ማንኛዉም አስተያየት/እርምት መስጫ
↓↓↓↓↓↓
@Ass_Selefyaa1bot
@Ass_Selefyaa1bot”
凭借高频更新(最新数据采集于 30 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
13 814
订阅者
-1424 小时
-457 天
-20730 天
帖子存档
Repost from 💎ሱና የኑህ መርከብ ናት!! السنة سفينة نوح
➲ደሴና አካባቢዋ ኮቦልቻና አካባቢዋ ለሚገኙ ሁሉም_ቦታ ባሉበት ሆነው ቢያዙን ትዛዛቹሁንና ፈላጉታቹሁን አሟልተን እቤትወ ድረስ እናቀረባለን
➛ጅልባብ
➛ኒቃብ
➛ካልሲ
➛ጓንት
➛ቢጃማ
➛የቤት እቃዎች
➛የቤት አስቤዛዎችን በትዕዛዛችሁ መሰረት እናደርሳለን
➭ሱኳር
➭ዘይት
➭ቡና
➭ዱቄት
➭መኮረኒ
➭ፖስታ እና የተለያዩ የቤት አስቤዛዎች ለቤተሰቦቻችሁ ማሟላት የምትፈልጉ በአማና እናደርሳለን
በቴሌ ግራም አካውንተ
👇👇👇👇👇
@Selahudin1444
@Hayuumufa
ቀጥታ መስመር
👇👇👇👇👇👇
➭Umu Faruq
📱0914886171
➭አቡ ኦካሻ
📱+251914500532
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/Zun_NureynOn_line_Shopping
➭ውዷ እህቴ የአቂዳ መስተካከል ብቻ ትዳር አይሆንም! የአቂዳ መስተካከል ከትዳር ማገሮች አንዱ ቢሆንም አቂዳ ላይ ብቻ መጠልጠሉን አልደግፍም! ምክንያቱም ስንት አለ በአቂዳው ጠንከራ ሆኖ ስነ ምግባሩ የሻከረ ፣ ለአቂዳ ቦታ እንደምንሰጠው ሁሉ ስነ ምግባሩ ላይ እናትኩር ስንቶች መሰላችሁ በአቂዳቸው ላይ ጠንካራ ተብለው ስነ ምግባር ላይ ዜሮ የሆኑ እህቶቻቸውን የደም እንባ የሚያስለቅሱ! ስለዚህ ጥንቃቄ አድርጉ ለማለት ነው!!
http://t.me/https_Asselefya1
➭ምናልባት ህመም ላይ ላለች ልብ
እረፍት ትሰጥ ይሆናል‥
﴿نَبِّئْ عِبَادِي أَنِّي أَنَا الْغَفُورُ الرَّحِيم﴾
ባሮቼን እኔ መሓሪው አዛኙ እኔው ብቻ መሆኔን ንገራቸው። [አል-ሂጅር 49]
√ ሒጃብ ከመልበስ ምን ከለከለሽ ⁉️
🔖ክፍል ➅ ማጠቃለያ
🛑👉 አስረኛው ምክንያት፦ በመጨረሻም አስረኛዋ እህት እንዲህ አለች "ሸሪዓዊ ሒጃብ ከለበስኩ የሆነ ቡድን አባል ነሽ እባላለሁ። እኔ ደሞ ቡድንተኛና ጎጠኛ መባል አልፈልግም" የኢስላም እህቴ ሆይ! በኢስላም ውስጥ ሁለት አይነት ህዝቦች ናቸው ያሉት አምላካችን አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል አስፍሮታል። የመጀመሪያው ህዝብ፦ አላህን በመታዘዝና ወንጀልን በመራቅ የአላህን ውዴታ የተጎናፀፈ የአላህ ህዝብ ነው። ሁለተኛው ህዝብ ፦ አላህን የሚያምፅ ብልሽትን የሚያስፋፋ ድንጋጌዎቹን የሚጥስ ወሰን አላፊ የሆነ የሸይጣን ህዝብና መንጋ ነው። እህቴ ሆይ! ሒጃብና መሰል የፈጣሪሽን የእዝነት ድንጋጌዎቹን በተገበርሽ ቁጥር ከቅጣቱ ነፃ ከሚወጡት ውዴታውን ከሚጎናፀፉት ቅን ባሮቹ ውስጥ ትሆኚያለሽ። ከአላህ ህዝቦችም ትሆኚያለሽ። በተገላለጥሽና በተጣበበ ቀሚስ ሰውን መፈተንና እራስሽንም ማዋረድ ካማረሽ በሸይጣንና በወዳጆቹ ከሀዲያንና መናፍቃን መርከብ ላይ ተሳፍረሻል። ምን የከፋ ወዳጅነት ነው!!!
🔖ተመለከትሽ ከአላህ መንገድና ከነፃነት ወደ ሸይጣን እስር ቤት እንዴት እንደገባሽ?
ጥሩውን በመጥፎ ጣፋጩን በመራራ መልካሙን በቆሻሻ እንደለወጥሽ አስተውይ!
እህቴ ሆይ!
ወደ አላህ ሽሺ!! ሸሪዓውንም ተግብሪ! " ወደ አላህም ሽሹ እኔ ለእናንተ ግልጽ አስጠንቃቂ ነኝና " ዛሪያት 50
🛑👉ማጠቃለያ ፦ በጌታሽ የውዴታ መንገድ የእዝነቱ በር የጀነቱ መግቢያ ላይ ትሆኚ ዘንድ የሰውና የጋኔን ሰይጣናትን ጥሪ ከራስሽ አርቀሽ ወርውሪ!!! የአላህን ሸሪዓ አጥብቀሽ ያዢ። በቀደምት ቅዱሳን አማኝ እናቶች መንገድ ላይ ተጓዢ። በሰሀቢያት አስደናቂ ጀብድና የእምነት ፍኖት ላይ ተጓዢ።
🛑👉ማገባደጃ፦ አካልሽ በሸይጣን ገበያ ላይ በርካሽ ቀርቧል፤ የሰዎችን ልቦና ይመርዛል፣ የፀጉርሽ ጫፎች ከግንባርሽ ላይ ተዝረክርኳል፤ ጠባቡ ቀሚስሽ የአካልሽን ቅርፅና መገጣጠሚያ በሚቀፍ መልኩ ቁልጭ አድርጎ አጋልጦታል፤ የተጋጌጠውና በሽቶ የታወደው ልብስሽ ጌታሽን አስቆጥቶ የሸይጣን ጭፍሮችን አስደስቷል። በዚህ ሁኔታ የምታሳልፊው እያንዳንዱ ቀን ከጌታሽ መራቅን ለሸይጣን ቅርበትን እየሸለመሽ ያልፋል። ተውበት አድርገሽ ወደ ጌታሽ እስክትመለሺ ድረስ የእርግማን በር ከሰማይ ተከፍቶብሻል። በየቀኑ ወደ ቀብር እየቀረብሽ ነው። የሞት መልአክም ነፍስሽን ሊረከብ ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ነው። አልዒምራን " ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት። ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በ ትንሳኤ ቀን ብቻ ነው። ከ እሳትም የተራቀና ገንተትን የተገባ ሰው በርግጥ ምኞቱን አገኘ። ቅርቢቱም ህይወት የመታለያ መሳሪያ እንጂ ሌላ አይደለችም" አሊዒምራን 185"
🛑👉እህቴ ሆይ! የተውበት ባቡር ሳያመልጥሽ ፈጥነሽ ተሳፈሪ! እህቴ ሆይ! ከነግ በፊት ዛሬን አስቢና አስተውይ! እህቴ ሆይ! ግዜው ከማለፉ በፊት አሁን ተመለሽ።
ተ
ጠ
ና
ቀ
ቀ
•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈•
https://t.me/https_Asselefya1Repost from ተቀርተው ያለቁ ደርሶች
ጠያቂ፦ ቢክራ ትሁን ሠይብ ማየት ይቻላል?
ሸይኽ አወል፦ በምን ያያል!?? ሊሞክር ነው?? መጠየቅ ነው እንጂ በምንም ማየት አይችልም!!
=
[ሸይኽ አወል አሕመድ፣ ቡሉጉል መራም (49)]
➩ፈገግ በሉ ፈገግታ ሱና ነው ....
አንድ ወጣት ለሌላ ወጣት ደውሎ እንዲህ ይለዋል
➭ወጣቱ :- ዛሬ ቁርአን እየቀራሁ አስታወስኩህ እኮ
➭ሌላኛው ወጣት :- ማሻአሏህ እንዴት ደስ ይላል! ግን በየትኛው ሱራ ላይ አስታወስከኝ?!
.
.
.
.
.
.
➭ወጣቱ :- ሱረቱል ሙናፊቁን
👉እና ምን ልላችሁ ነው ሰዎች የሚያስታውሱን በምን ሁኔታ ነው?! ራሳችንን እንፈትሽ የሀፉ ቤተሰቦች
መንቁል
http://t.me/https_Asselefya1
➭የምትወደዉ ሰዉ ሲናፍቅህ የሆነች የዝምታ ግዜ ትመጣለች!! ያኔ ወይ ደስተኛ ትሆናለህ ወይ ደግሞ እንባህን መቆጣጠር ያቅትሀል!!
“ልብ የልብን ጠረን ያሸታል” ይላሉ ኢብነል ቀይዪም።
አንዳንዴ መውደድ የልብ ትውውቅ ነው። ብዙ ያላወራኸውን፣ ብዙም የማታውቀውንና ምንም ያላደረገልህን ሰው እንዲሁ ትወደዋለህ። "ለምን ወደድከኝ?” ብለህ ምክንያት ብትጠይቅ ምክንያት የማይነግርህ ብዙ ወዳጅ አለ።
=
t.me/abdu_rheman_aman🛑👉ፆታዊ ፈተናን መከላከል
🎙ኡስታዝ አቡል ዓባስ ናሲር ሙሐመድ
6ኪሎ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ
🗓19/04/2017:
=
ወድቷ እህታችን መልካም ጉዞ
የርሱ ፍቃድ ሁኖ የአላህ ጌታችን
እንገናኛለን በዉዷ ሀገራችን
ልባችን ተነሳሳ ሊጓዝነዉ ካንችጋ
ታድ ምን ዋጋለዉ እግራችንመች ተነሳ
አትሂጂ አንልም ከሰዉ ቤት አትዉጪ
መልካሙን ይግጠምሽ ሀገርሽ ስትመጪ
አላህ ይወፍቅሽ ትእዛዙን አድምጪ
ሀገርሽ ላይ እርጊ ስደትም አትዉጪ
አመልሽ ወርቅነዉ ፀባይሽምሸጋ
ስጦታ የለንም ላንች የሚበቃ!!
መልካም ጉዞ ብለን ዛሬ ብንሸኚሽም
መዲ እንወድሻለን መቼም አንረሳሺም !
«ዉዷ እህታችን መድዬ ኡሙ ፋሩቅ መልካም ጉዞ እንመኝልሻለን «የኢብኑ ተይሚያ» ጀመአ እሕቶችሽ!»النَّاس في العقل ثلاثة أصنافٍ: راجح العقل، وناقصه، وفاقده، وأنت في واحدٍ منها، فاختر لنفسك مقامها، بما تنمي به عقلك، وتجعله فيه، والنَّاس شهودٌ عليك.
#تغريد_العصيمي
እጂህ ይባረክ ወንድማችን አብዱረሕማን ልብ ብላችሁ አንብቡ!! ሀቂቃ ብዙ ሴቶች ባል እህቱ እናቱ እንድሁም ከሌላ ዘመዱ እንድጋጭ እንድርቅ እንድቆራረጥ የምታፈነፍኑ ለጊዜዉ ቢመስልሽም ዞሮ ዞሮ ራስሽ ዳር እንደምትቀሪ እሰቢበት ! አንች እሕትሽ እንደምትወጅ ባልሺም ይወዳታል እሕቱ እናትሽንም እንደምትወጅ እሱም እናቱን ይወዳል ! መላ ቤተሰብሽ እንደምትወጅ እሱም ይወዳል! ስለዚህ የራስሽ ቤተሰብ እንድደረግባቸዉ የማትፈልጊዉን የባልሽ ቤተሰቦች ላይ እንድደረግ ሰበብ አትሁኚ ! ጥግሽ ያዢ የሚስትነት ቦታሽ ብቻ ተብቃቂ ! የባል ቤተሰብ ማለት የራስ ቤተሰብ ናቸዉ። ሊከበሩ ሊወደዱ ይገባቸዋል።
=
ወንድም ከእህቱ ጋር በብዛት ሀያ አመታትን አብሮ ያሳልፋል። ይሄን ሁሉ አመታት ይወዳታል። ያዝንላታል። ማንም አዛ እንዳያደርጋት ይታገልላታል፣ ይጋደልላታል። እሷም ወንድማለም፣ ወንድም ጋሻዬ፣ መከታዬ፣ ኩራቴ እያለችው፣ ሲያመሽ እየተጨነቀችለት፣ ጩኸት ስትሰማ ወንድሜ ምን ሆኖ ይሆን እያለች እየሰጋችለት፣ እያከበረቺው፣ እያሰበችለት ይሄን ሁሉ አመታት ከሱ ጋር ታሳልፋለች።
ይህ በሥስት አይን የምታየው ወንድሟ አሏህ ብሎለት በሀያዎቹ የእድሜው አጋማሽ ላይ የሆነችን ልጅ ያገባል። ሚስት ተብዬዋ ደግሞ ገና በመጣች በወሯ ወይም ጥሩ ከሆነች ባመቷ ያችን የእድሜ ልክ ወዳጁን፣ ሚስጥረኛውን እና አክባሪውን እህቱን ማጣጣልና ክፋቷን መጠቃቀስ ትጀማምራለች። በአንድ ማህጸን ላይ የኖሩን አጣጥላ፣ ከማዶ መጥታ የእህትን ቦታ ላትተካ ነገር ከእህቱ ጋር ልታቀያይመው ብዙ አይነት ምክንያቶችን ትደረድራለች። በዚህም በእህቱ ላይ የአጭር ጊዜ ቂም ይይዝ ይሆናል። ሚስት ግን ባሏ ለቀናት እህቱን ተወት ሲያደርጋት ጊዜ የምርም እኔ የምለውን ይሰማል በሚል ትቀጥልበታለች። ወይም ከመነሻውም የሚስትን ወቀሳ ከቁብ ካልቆጠረው ደግሞ ለኔ አታስብ፣ የኔ ነገር ግድ አይሰጥህ እያለች ትነዘንዘዋለች። ይህን ተከትሎ እህቱን ከመውቀስ ይልቅ ይች ጨቅጫቃና ነገረኛ ሚስት ማለት ይጀምራል። የሆነ ጊዜ ሚስቱን ያርቅና ስለእህቱ መልካምነትና ስለሚስቱ ክፋት በአደባባይ ሲያወራ ይሰማል።
እቴ እህቱ እህቱ ነች። የተጋሩት ደምና ስጋ አላቸው። 9 ወራትን አንድ ማህጸንን ተጋርተዋል። የእድሜያቸውን ግማሽ ወይም ሲሶ ያክል በአንድት ጣሪያ ስር በፍቅር ኖረዋል። እህቱ ነገሩ ሁሉ ነች።ቭምናልባት ትኩስ ፍቅር ላይ ማሚዬ፣ ማማዬ፣ እህቴ እያለ ቢያንቆለጳጵስሽ አንቺ የእህትም ይሁን የእናት ምትክ የሆንሽ ያክል አይሰማሽ። ውሸት ነው!ዉሸት ነው። የእህቱን ልክ ካላወቅሺ ያንችን ክብር ታጫለሽ። የትዳር አጋርን ቤተሰብ (በተለይም የባልን ብዬ ብጽፍ ባል ምን ስለሆነ ትላላችሁ አይደል) አይደለም በቋሚነት መጥላትና በአጋጣሚ ማነወር የሚያስከትለው ጦስ ከሚገመተው በላይ ከባድ ነው። ዘመድ ከዘመዱ አህያ ከአመዱ የሚባለውም አባባል ትክክል ነው።
እወቁበት።
t.me/abdu_rheman_aman
