School of Indiana (Kality branch)
前往频道在 Telegram
Dear parents, Click on the grade level of your child to get all the necessary materials.
显示更多4 484
订阅者
-124 小时
-57 天
+1030 天
帖子存档
በ2018 ዓ.ም በት/ቤታችን የኬጂ 3 የነበራችሁና በ2019 ዓ.ም የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች የክፍያ የተቀየረ ስለሆነ ከጥቅምት 2019 ዓ.ም የተማሪዎችን የትምህርት ክፍያ ከዚህ በታች በተማሪዎች ስም ትይዩ በተቀመጠው ኮድ ብቻ እንድትፈፅሙ በአክብሮት እናሳውቃለን::
ማሳሰቢያ:-
የትምህርት ኮድ = SC006 ተጠቀሙ
የት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል
ለሁሉም ወላጆች
የአዲስ ተማሪዎች የመክፍያ ኮድ ስለማሳወቅ
በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመዘገባችሁ ሁሉም ኬጂ 1 እና ከ1ኛ - 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ወርሃዊ የትምህርት አገልግሎት የሚከፈለው በአዋሽ ባንክ E-School ከዚህ በታች በተማሪዎች ስም ትይዩ በተሰጠው ኮድ ብቻ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን::
ማሳሰቢያ:-
የተማሪዎች ወርሃዊ የትምህርት አገልግሎት ክፍያ የሚከፈለው ወር በገባ ከ25 - 05 ቀን መሆኑን እያሳወቅን ከቀን 6 ጀምሮ ክፍያው እስከሚፈፀም በየቀኑ የ10ብር ቅጣት የሚኖረው መሆኑን ከወዲሁ ለማሳሰብ እንወዳለን::
የት/ቤቱ ፋይናንስ
ዉድ ወላጆች
ቅዳሜ መስከረም 23፣ 2019ዓ.ም በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ምክንያት መንገድ ሰለሚዘጋጋ ነገ አርብ መስከረም 22፣ 2019ዓ.ም ትምህርት ቤት ዝግ መሆኑን እናሳውቃለን።
ት/ቤቱ!
ለሁሉም ወላጆች/ ህጋዊ አሳዳጊዎች በሙሉ፡-
ከነገ ሐሙስ 07/01/2019 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት የሚሰጠው ለሙሉ ቀን ሲሆን ተማሪዎች የሚለቀቁት 9:20 ላይ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን::
ት/ቤቱ
ቀን:- 02/01/2019 ዓ.ም
የት/ቤቱ ሰርቪሶች ተጠቃሚ ተማሪ ወላጆች በሙሉ:-
የ2019 ዓ.ም የት/ቤቱ ሰርቪስ አገልግሎትን ይመለከታል።
በ2019 ትምህርት ዘመን ገላን ኮንዶሚኒየም አከባቢ (ሰላም ህንፃ ማህበር ቤትና ሳሎ ማህበር ቤት ፣ ገላን ኮንዶሚኒየም አሮጌና አዲሱ ሳይት) የሆናችሁ ፤ በ2018 ዓ.ም የት/ቤቱን ሰርቪስ ስትጠቀሙ የነበሩ ሁሉም ተማሪዎች እና አዲስ የኬጂ ተማሪዎች በሙሉ የሰርቪስ መታወቂያ ስለተዘጋጀ ነገ ሰኞ ከ2:30 - 11:00 ድረስ የት/ቤቱን ፋይናንስ ክፍል በአካል በመገኘት እንድታስመዘግቡና የሰርቪስ መታወቂያ እንድትወስዱ በአክብሮት እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:-
ከላይ የተጠቀሰው አከባቢ የሆኑ ሁሉም የኬጂ ተማሪዎች የሚጠቀሙት የት/ቤቱን ሰርቪስ ብቻ መሆኑን አውቃችሁ ከወዲሁ እንዲታስመዘግቡ እናሳስባለን።
ት/ቤቱ
