ch
Feedback

不要被骗子欺骗!Telemetrio 会找到并标记这些频道 👉 如果想查看标记,请订阅

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

Ethio-Italy Polytechnic College (Dire Dawa)

前往频道在 Telegram
2 394
订阅者
+424 小时
+677 天
+35730 天
帖子存档
#ፅዱና_ውብ_የስራ_አካባቢን_መፍጠር          የኢትዮ- ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሰራተኞች ኮሌጁን ፅዱና ውብ ለማድረግ ባለመውና በየወቅቱ በሚደረገውን የፅዳት ፕሮግራም ላይ የተሳተፉ ሲሆን በቀጣይም የፅዳት ዘመቻው በየወቅቱ  የሚቀጥል ይሆናል። ህዳር 27/2015 የኢትዮ-ጣሊያን ፓሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ኮምንኬሽን

#እንኳን_ደስ_አለን🏆 የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የድሬዳዋ አስተዳደርን በመወከል የተሳተፈበትን የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውድድር አንደኛ በመውጣት በአሸናፊነት አጠናቋል። ……………………………………………………………… ለአንድ ሳምንት በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች ሲካሄድ የቆየው #9ኛው_አለም_አቀፍ_የኢንተርፕረነርሺፕ_ሳምንት_በኢትዮጵያ በዛሬው እለት ፍፃሜውን ያገኘ ሲሆን በሳምንቱ የተለያየ የፈጠራ ሀሳብ ባላቸውና ከተለያዩ አካባቢዎች በተገኙ ቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች መካከል በተደረገ ውድድር የድሬዳዋ አስተዳደርን በመወከል የተሳተፈውና በስራ ክህሎትና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ስር የሚገኘው #የኢትዮ_ጣሊያን_ፖሊ_ቴክኒክ_ኮሌጅ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተደረገውን ውድድር አንደኛ በመውጣት ውድድሩን በአሸናፊነት አጠናቆ በድል ተመልሷል። በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑትና ቴክኖሎጂ ላይ ለተሳተፉ መምህራን 2መቶ ስልሳ ሺህ ብር ሽልማት የተበረከተላቸው ሲሆን እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን እያልን… በዚህ ስራ ውጤት ላስመዘገቡ የኮሌጁ አሰልጣኝ መምህር ዘሪሁን ነጋሽ፣ሲሳይ ምንዳ፣አበበ ተረፈ፣ስንታየው ቀጭኔ፣ጎሳዬ አዳነ ፣ ብሩክ አንለይ እና ለአስተባበራችሁ ድጋፍ ላረጋችሁ ሁሉ ኮሌጁን ለዚህ ውጤት ስላበቃችሁ በኮሌጁ ስም እናመሰግናለን።

የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ  ት/ቤት ተማሪዎች ጉብኝት። …………………………………………………………             በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ቀደም ሲል ከተለያዩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በተደረገው ውይይትና በተደረሰው የጋራ መገባባትና በተዘጋጀው ዕቅድ መሰረት በዛሬው እለት የአፈቴሳ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ ማለትም(STEM) ግንዛቤ ለማስጨበጥ በኢትዮ ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ  ጉብኝት አድርገዋል፡፡        በዚህም ተማሪዎቹ በኮሌጁ የተግባር ስልጠና የሚሰጥባችውን ዲፓርትመንቶች የጎበኙ ሲሆን  በዚህም የማኑፋክቸሪግ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል እና የአውቶሞቲቭ ትምህርትና ሰልጠና ክፍል  አሰልጣኝ መምህራን ለጉብኝት ለመጡት ተማሪዎቹ የተግባር ስልጠና የሚስጥበትን ክፍሎች(workshops) በማስጎብኘት ስለቴክኒክና ሙያና በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና እና በሂሳብ (STEM) ተማሪዎቹ ግንዛቤ እንዲጨብጡ አድርጓል፡፡     በተጨማሪም ሌሎችም በድሬዳዋ አስተዳደር ስር የሚገኙ የአንደኛ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተዘጋጀው ዕቅድና በተዘረጋው መርሃግብር መሰረት በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ በመገኘት መሰል ጉብኝቶችን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡   ድሬዳዋ ህዳር 9/2015 የኢትዮ ጣሊያን ኮምንኬሽን

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ላለፉት አራት ተከታታይ ቀናት ለተቋሙ ማኔጅመንት አባላትና ፑል አመራሮች ሲሰጥ የነበረው ስልጠና አጠናቀቀ።      በ Public Enterpreneurship and Innovation Ecosystem Building(PEIEB) ላይ በተቋሙ አመራሮች አቶ ታደለ አሰፋ እና አቶ ተሾመ ሸዋዬ ላለፉት ቀናት ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በዛሬው እለት ፍፃሜውን ማግኘቱን ተከትሎ ስልጠናውን ወስደው ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች የእውቅና ሰርተፊኬናየመፅሀፍ ስጦታ የቴክኒክና ሙያ ትምርትና ስልጠና ኤንጀንሲ ሀላፊ ከሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ  እጅ ተረክበዋል።       በተጨማሪም የኤጀንሲ ሀላፊዋ በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ከተሳታፊዎች ጋር የመከሩና  አቅጣጫዎችን ያስቀመጡ ሲሆን ስልጠናውም በዚህ መልኩ ተጠናቋል። የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ህዳር 2/2015 ዓ.ም ድሬዳዋ

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተቋሙ ለሚገኙ የማኔጅመንት አባላትና የፑል አመራሮች Mind Set ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀመረ።           ስልጠናው በንግግር የመክፈቻ ንግግር ያስጀመሩትት በስራና ክህሎት ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለፁት ይህን ስልጠና ከሚወስዱ ሰልጣኞች ብዙ እንደሚጠበቅ ገልፀው  ሰልጣኞች ስልጠናውን በጥብቅ ዲሲፒሊን ወስደው በቀጣይ በስራቸው የሚገኙ ሰራተኞችንና ሌሎችንም የማሰልጠን ተግባር ላይ እንዲሳተፉ አፅኖት ሰተው ተነናግረዋል።           በዛሬው እለት የተጀመረው ይህ ስልጠና  በኮሌጁ ዲኖች መሰጠት የጀመረ ሲሆን ስልጠናውም ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚቀጥል ይሆናል። የኢትዮ ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ኮምኒኬሽን ጥቅምት 29/2015 ዓ.ም ድሬዳዋ