ch
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

前往频道在 Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览

频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 365 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 754,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 531

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 365 名订阅者。

根据 19 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 119,过去 24 小时变化为 19,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 40.59%。内容发布后 24 小时内通常能获得 15.42% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 5 423 次浏览,首日通常累积 2 060 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 11

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

凭借高频更新(最新数据采集于 20 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。

13 361
订阅者
+1924 小时
+677
+11930
帖子存档
የሁምቦ - ፋርቾ - አባያ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በጥሩ አፈጸጸም ላይ ይገኛል ፡፡ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሶዶ አካባቢ ኮንስትራክሽን ጽ / ቤት ከሚቆጣጠራቸው 11 የመንገድ ስራ ፕሮጀክቶች አንዱ ሲሆን በመስክ የስራ ቅኘት ተጎብኝቷል ። የ 25 . 3 ኪ .ሜ ርዝመት ያለው ፕሮጀክቱ በአሁኑ ወቅት የ 45 ከመቶ አፈጻጸም ላይ ደርሷል። በዚህም የዲዛይን የአፈር ቆረጣ ፣ ሰብ ቤዝ እንዲሁም የ7 ስላብ ካለቨርት ስራዎች ተከናውነዋል ፡፡ በቀጣይም የሁለት ድልድዮች የግንባታ ስራን ለማከናወን እየተሰራ ነው። የቤዝ ኮርስና አስፋልት ንጣፍ ስራዎችን ለመፈጸም የዝግጅት ስራዎች ተጀምረዋል። የግንባታ ፕሮጀክቱን ይበልጥ ለማፋጠን ከወሰን ማስከበር ጋር ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትኩረት እየተሰራ ነው ፡፡ ፕሮጀክቱ ከትራንስፖርት ማሳለጥ ባሻገር የብላቴ ወንዝንና የአባያ ሐይቅን ተፈጥሯዊ ስጦታን በመጠቀም ሰፊ የልማት እርሻ ችሮታዎችን ይበልጥ እውን ለማድረግ ሀገራዊ ፍይዳው የጎላ ነው። ግንባታውን ሀገር በቀሉ ክሮስላንድ ኮንስተራክሽን የስራ ተቋራጭ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው ፡፡ መንገድ ፕሮጀክትን በአማካሪነት የያዘው ደግሞ አርትስ ቴክ ኮንሰልታንት ነው ፡፡ ከወላይታ አርባምንጭ የሚወስደውን ዋና መንገድ የሚገናኘው ይህ ፕሮጀክት ለግንባታው ስድስት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሚሊዮን ( 699 000 000 ) ብር ከኢትዮጵያ መንግስት ተመድቦለታል ፡፡

የደብረ ብርሃን አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በትኩረት እየተሰራ ነው:: ደብረ ብርሃን ፣ መስከረም 27 ቀን2015 ዓ.ም (ኢመአ)፡- በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው የደብረ ብርሃን አንኮበር አስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኘው ይህ መንገድ በጠጠር ደረጃ ተገንብቶ ላለፉት በርካታ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን ከአገልግሎት ብዛት አኳያ በመጎዳቱ እና የቦታው ተፈጥሮአዊ አቀማመጥ በጠጠር ደረጃ ለነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት አመቺ ባለመሆኑ ምክንያት በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲገነባ በመንግስት ተወስኖ ጥቅምት 13 ቀን 2011 ዓ.ም ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት ግንባታው በይፋ ሊጀመር ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት 42 ኪሎ ሜትር ከሚረዝመው አጠቃላይ የመንገድ ግንባታ ውስጥ 30 ኪሎ ሜትር አስፋልት የማንጠፍ ስራ ወይም ከአጠቃለይ ስራው ውስጥ የፕሮጀክቱ 72 በመቶው ስራ ተጠናቋል፡፡ ፕሮጀክቱን ለማካሄድ አገልግሎት ላይ የሚውለው 1,623,194,217.85(አንድ ቢልዮን ስድስት መቶ ሃያ ሶስት ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና አራት ሺህ ሁለት መቶ አስራ ሰባት ብር ከሰማንያ አምስት ሳንቲም) በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው። ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ሀገር በቀሉ ሰንሻይን ኮንስትራክሽን ሲሆን ፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራው ደግሞ በኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጅነርስ አማካኝነት በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ መንገዱ ትከሻን ጨምሮ በቀበሌ 10 ሜትር ፣ በወረዳ ከተማ 17 ሜትር እንዲሁም በዞን ከተማ ደግሞ 30 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡ ከዚህ ቀደም በአካባቢው የነበረው የፀጥታ ችግር ፣ የመሬት ናዳ እና በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት የተካሄደው የዲዛይን ለውጥ በግንባታ ሂደቱ ላይ በተወሰነ ደረጃ መዘግየትን ፈጥሯል፡፡ ከዚህም ባሻገር ያለፈው የክረምት ወራት በግንባታ ሂደቱ ላይ ተጨማሪ ተፅዕኖ ፈጥሮ የነበረ ሲሆን ፣ አስተዳደር መስሪያ ቤቱ በቀጣይ የበጋ ወራቶች በፕሮጀክቱ ላይ የነበሩ ክፍተቶችን በአፋጣኝ በመቅረፍ ፕሮጀክቱን በተገቢው የጥራት ደረጃ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ጥብቅ ክትትል እና ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ አንኮበር በ17ኛው መቶ ክፍለዘመን በሸዋው ነጋሲ በመርድ አዝማች አብዬ የተመሠረተችና በአልጋ ወራሹ መርድ አዝማች አምኀኢየሱስ የተስፋፋች የሸዋ ከተማ ስትሆን ከደብረብርሃን 42 ኪ.ሜ በምስራቃዊ አቅጣጫ የስምጥ ሸለቆ አፋፍ ላይ ትገኛለች። በአንኮበር ከተማ ውስጥ የተለያዩ ታሪካዊ ቅርሶችን በውስጡ የያዘው የአጼ ምኒሊክ ቤተመንግስት የሚገኝ በመሆኑ የመንገዱ መገንባት የአካባቢው የቱሪስት መስህብነት እንዲጨምር ከማድረግ አንፃር የሚኖረው ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው የነበረውን የትራንስፖርት ችግር በማቃለል አርሶአደሮች ምርታቸውን በቀላሉ ወደ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ከዚህም ሌላ ከአንኮበር-ዱለቻ-አዋሽ መንገድ ጋር የሚያስተሳስር በመሆኑ ከዚህ ቀድም ወደ አፋር ለመሄድ ይወስድ የነበረውን ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ ለማስቀረት እንደ አማራጭ ሆኖ ያገለግላል፡፡

የሞርካ - ጊርቻ - ጬንቻ መንገድ ፕሮጀክት የመስክ ምልከታ ተደረገ አርባምንጭ፣ መስከረም 26/ 2015 ዓ.ም(ኢመአ)፡ በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በሶዶ አካባቢ የመንገድ ፕሮከክቶች ማስተባበሪያ ጽ / ቤት ስር ቁጥጥርና ክትትል ከሚደረግላቸው የመንገድ ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የሞርካ - ጊርቻ - ጬንቻ መንገድ ፕሮጀክት የመስክ ምልከታ ተደረገ፡፡ በጎብኝቱ ወቅት ከአፈፃፀም አኳያ የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር የተነሱ ሲሆን የተቋራጭ አቅም ውስንነት ፣ የግብአት አቅርቦት እና የመንገድ ወሰን ማስከበር ችግሮች ይገኙበታል ። ከጉብኝቱ በኋላ በተካሄደ ውይይት የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር እንጂነር ሃብታሙ ተገኝ የወሰን ማስከበር ክፍያን ተንተርሶ ለተነሳው ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጸው በቀጣይም የስራ ተቋራጩ Bei n Urban Construction Group Co. ( BUCG ) ግንባታውን በግዜ ለማጠናቀቅ የሚያስችሉ እና ሊሰመርባቸው የሚገባቸውን አቅጣጫዎች አስቀምጠዋል ። የኢፌዲሪ ህዝብ ተወካዮች ም / ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ መንገድ ለአገር እድገት ያለውን ጠቀሜታ ለውይይት መድረኩ ገልፀው፣ ሥራው በከፍተኛ ትኩረት እንዲጠናቀቅ አሳስበዋል ። የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ በበኩላቸው በዞኑ ውስጥ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ ከሚባሉ መንገዶች አንዱ በሆነው በዚህ መስመር ላይ የነበራቸውን ድጋፍና ክትትል አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ። በተያያዘም የጋሞ ህዝብን በመወከል የአካባቢው ሽማግሌዎችም የውይይቱ አካል የነበሩ ሲሆን ይህ እጅግ ጠቃሚ የሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ ማህበረሰቡን በማስተባበር ረገድ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልፀዋል ። የስራ ተቋራጩ የአፈር ቆረጣ ፣ ሰብ ቤዝ ፣ ሰብ ኮርስና የአስፋልት ንጣፍ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ። ፕሮጀክቱ በታለመለት ጊዜ እንዲጠናቅቅ ተጨማሪ የሰው ሃይልና ግብአት መሟላት አስፈላጊ እንደሆነም አቅጣጫ ተቀምጧል ። የሶዶ አካባቢ ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ጽ / ቤት በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአዲሱ መዋቅር መሠረት ከተቋቋሙ የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች አንዱ ነው፡፡

የጅግጅጋ-ገላልሼ-ደገሕመደው-ሰገግ አስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ። ጅግጅጋ፣ መስከረም 24/2015 ዓም (ኢመአ) ፡ በሶማሌ ክልል የጅግጅጋ-ገላልሼ-ደገሕመደው-ሰገግ ሎት 2እና3 110 ኪ.ሜ አስፋልት መንገድ ግንባታ አስፋልት ማንጠፍ ሥራ ተጀመረ፡፡ በአሁኑ ወቅት 2 ኪሎ ሜትር ያህሉን አስፋልት ማልበስ የተቻለ ሲሆን፥ ከመንገዱ አጠቃላይ ግንባታም 41 በመቶው ተጠናቅቋል፡፡ ይህም በእቅዱ መሠረት እየተካሄደ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ቀሪ ሥራዎችን በማጠናቀቅ፥ የፕሮጀክቱን ሎት ሁለት፥ በሚቀጥሉት አራት ወራት ውስጥ ለትራፊክ ክፍት ለማድረግም በትኩረት እየተሠራ ነው፡፡ በእሰከአሁኑ የግንባታ ሥራ፤ የአፈር ቆረጣ፣ ድልድይ ግንባታ፣ የግንባታ ግብአቶች ማምረትና ዝግጅት የውኃ መፋሰሻ ቱቦዎች ማምረት ሥራ በመከናወን ላይ ይገኛል፡፡ ግንባታውን፥ የፌደራል መንግስት በመደበው 1,828,264,182 (አንድ ቢሊዮን ስምንት መቶ ሃያ ስምንት ሚሊዮን ኹለት መቶ ስልሳ አራት ሺህ) ብር ወጪ፣ ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ሥራ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እያከናወነ ይገኛል፡፡ የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን ሲ-ቴክ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እየሠራ ነው፡፡ በክልሉ የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተፈጠረው የውኃ እጥረት በግንባታው ላይ የሚፈጥረውን ተጽዕኖ ለመቅረፍ በሥራ ተቋራጩ በኩል አስራ አንድ የውኃ ማጠራቀሚያ ኩሬዎች አጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል ፡፡ ኩሬው ከግንባታው አልፎም የአካባቢውን ማኅበረሰብ እየጠቀመ ይገኛል፡፡ መንገዱ ሲጠናቀቅ፥ ቀድሞ ወደ ደገሕመደው ከተማ ለመሄድ፣ በደገሐቡር በኩል ይወስድ የነበረውን የ240 ኪ.ሜ ርቀት ወደ 195 ኪ.ሜ ያሳጥረዋል፡፡ የፋፈን እና ደገሐቡር ዞኖችን በቅርበት በማገናኝት፥ በአካባቢው የሚገኙ አርብቶ-አደሮች እና በእንስሳት ንግድ ላይ የተሰማሩ ባለሀብቶችንም ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡ ፕሮጀክቱ ለአንድ ሺህ ያህል ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ የዚሁ ፕሮጀክት አካል የሆነው ሎት-1 ተጠናቅቆ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ሲሆን፣ ሎት-4 ደግሞ በግንባታ ላይ ይገኛል፡፡

አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ
+6
አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ

በባህርዳር ከተማ እየተገነባ የሚገኘው አዲሱ የዓባይ ወንዝ ድልድይ በቀጣይ 3 ወራት ውስጥ የድልድዩ ዋነኛ አካል የሆነው (Grider) ሙሉ ለሙሉ ለመግጠም በትኩረት እየተሰራ ነው። የድልድዩን ዋና ዋና ስራዎች በእቅዱ መሰረት ለማከናወን አጠቃላይ የግንባታ ሂደቱ በመፍጠን ላይ ይገኛል። አጠቃላይ የግንባታ አፈፃፀሙ 76 በመቶ ደርሷል። በእስካሁኑ የግንባታ እንቅስቃሴ ከ760 ሜትር (Girder) ርዝማኔ ውስጥ (በሁለትም መስመር) 511 ሚትር የድልድይ (Grider) ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። በግንባታው ፕሮጀክት ላይ በዋነኛነት የድልድይ ተሸካሚ ምሰሶዎች (piers and Abutments) እንዲሁም ከመሬት በታች የድልድዩ የቋሚ ተሸካሚ መሰረቶች (Piers piles, Abutment piles and ramp piles) ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል ። ለድልድዩ የሚያስፈልጉ 8 ቋሚ ተሸካሚ መሶሶዎች ( pylons/towers) ሙሉ ለሙሉ ተጠናቋል: ድልዲዩን ወጥሮ ለመያዝ ከሚያግዙ 72 (Stay cables) አምሳው የተጠናቀቀ ሲሆን የተቀሩትን በቅርብ ለመጨረስ እየተሰር ነው። በኢትዮጵያ መንግስት በተመደበ 1.4 ቢሊዮን ብር ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ቻይና ኮሙኒኬሽን ኮንስትራክሽን ካምፓኒ የተባለው ተቋራጭ ነው። የማማከር እና ቁጥጥር ስራውን ደግሞ ቦቴክ ቦስፈረስ ኮንሰልቲንግ ከስታዲያ ኢንጅነሪንግ ጋራ በጣምራ እየሰሩት ይገኛሉ። አዲሱ የአባይ ወንዝ ድልዲይ በባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ነባሩ የአባይ ወንዝ ድልድይ 2 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው እየተገነባ ያለው። ይህ ዘመናዊ ድልድይ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ከሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ጎን ለጎን ምቹ የሆነ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ያደርጋል። በተጨማሪም ባህር-ዳር ከተማ ተጨማሪ ውበት እንድትላበስ ይረዳታል። ድልድዩ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ በግራና በቀኝ በአንድ ጊዜ 6 ተሽከርካሪዎችን ማስተናገድ ይችላል፣ በተጨማሪም 5 ሜትር የእግረኛ መንገድ እንዲሁም የብስክሌት ተጠቃሚዎችን መስመር ባካተተ መልኩ ነው እየተገነባ የሚገኘው ፡፡

Call for Project Managers and Resident Engineers Training
Call for Project Managers and Resident Engineers Training

[Forwarded from Abrham Era] የጎዴ - ቀላፎ - ፌርፌር ሎት1 ጎዴ -ቀላፎ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በመካሄድ ይገኛል፡፡ መስከረም 3 ቀን 2015 (ኢመአ)- በሶማሌ ክልል ሸበሌ ዞን ውስጥ የሚገኘው ይህ መንገድ በጠጠር ደረጃ ተገንብቶ ላለፉት በርካታ ዓመታት አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ሆኖም ግን ከአገልግሎት ብዛት አኳያ በመጎዳቱ እና ለትራንስፖርት አገልግሎት አመቺ ባለመሆኑ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እንዲገነባ በመንግስት ተወስኖ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ.ም ግንባታው በይፋ ሊጀመር ችሏል፡፡ 94.8 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍነውን ፕሮጀክት ለማካሄድ አገልግሎት ላይ የሚውለው 1,530,000,000.00(አንድ ቢልዮን አምስት መቶ ሰላሳ ሚሊዮን ብር)ብር በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው። ግንባታውን በማካሄድ ላይ የሚገኘው ቻይና ሬል ዌይ ሰቨንዝ ግሩፕ(China Railway Seventh Group Co. Ltd) የተባለ የቻይና አለም አቀፍ ድርጅት ሲሆን ፣ የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ ስታድያ የምህንድስና ሥራዎች አማካሪ ኃላ/የተ/ የግል ማህበር ከንዑስ አማካሪ ጂ እና ዋይ ኢንጂነሪንግ ኮንሰልት ኃላ/የተ/ የግል ማህበር ጋር በጋራ በመሆን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ የጠጠር መፍጫ ማሽን በመትከል ለግንባታ ግብዓትነት የሚውል ምርት የማምረት ፣ የአፈር ቆረጣና ሙሌት ፣ የአነስተኛ የውሃ መተላለፊያ ቱቦዎችና የድልድይ ግንባታዎች ስራዎች በመካሔድ ላይ ይገኛሉ፡፡ መንገዱ በቀበሌ 12 ሜትር ፣ በወረዳ ከተማ 19 ሜትር እና በዞን ከተማ 21.5 ሜትር ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡ ፕሮጀክቱን በተቀመጠለት የጥራት ደረጃ እና የጊዜ ገደብ መስከረም 5 ቀን 2016 ዓ.ም ተገንብቶ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በግንባታ ሂደቱ ወቅት የታዩ ውስንነቶችን በመለየት አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረገ ይገኛል፡፡ መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ የጎዴ እና ቀላፎ ከተሞችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መስተጋብር ይበልጥ የሚያስተሳስር ከመሆኑም ባሻገር በአካባቢው ለሚገኙ ትንንሽ ከተሞች እድገትም ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ተብሎ ይታመናል፡፡ ከዚህም ባሻገር በዚህ አካባቢ ፍየል ፣ ግመል ፣ ሽንኩርት እንዲሁም ሌሎች አትክልት እና ፍራፍሬዎች በከፍተኛ ሁኔታ የሚገኙ በመሆናቸው አርሶ እና አርብቶ አደሮች ምርቶቻቸውን እና የቁም እንስሶቻቸውን ካለምንም ውጣ ውረድ በአፋጣኝ ወደ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፡፡ በተጨማሪም የጤና ፣ የትምህርትና ሌሎች ማህበራዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ተደራሽነትን ያሰፋል።

አኩይላ-አቻኛ ዲማ/ራድ መንገድ ግንባታ በታቀደለት የግንባታ ጊዜ እየተከወነ ይገኛል ----------------------------------------------------------------------------------- ጋምቤላ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኢመአ) በጋምቤላ ክልል ግንባታው እየተከናወነ ያለውና የጋምቤላ ክልልን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ከኦሮሚያ ክልሎች ጋር በአቋራጭ የሚያስተሳስረው (የጋምቤላ አቦቦ-ጎግ ዲማ) አኩይላ-አቻኛ ዲማ/ራድ መንገድ ግንባታ በታቀደለት የግንባታ ጊዜ እየተከወነ ይገኛል ፡፡ ሰማኒያ ሁለት ኪሜ ( 82ኪሜ) የሚረዝመው ይህ መንገድ በአሁኑ ወቅት የዲዛይን ስራን ጨምሮ የምንጣሮ ስራ፣የአፈር ጠረጋ፣ ድልዳሎ እና ሙሌት፣ ተጨማሪ የጠጠር መፍጫ ማሽነሪ ተከላ ስራዎች እየተከናወኑለት ይገኛል። ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው አገር በቀሉ NKH Construction Plc ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ በለስ ኮንሰልት Plc እየከወነ ይገኛል:: አጠቃላይ የግንባታ መዋለንዋይ ብር 1,574,746,965.24 ሲሆን የግንባታ ውጪውም የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው። ነባሩ መንገድ በጠጠር መንገድ ደረጃ የነበረና ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በመሆኑ ሕብረተሰቡን ለከፍተኛ እንግልት፣ አሽከርካሪዎችን ለጊዜ ወጪ እና ብክነት የዳረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ካለው ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ አንፃር መንገዱ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ይገኛል። መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ወደ ደቡብ ሱዳን ከሚወስደው ዋና አውራ ጎዳና (Trunk Road) ጋራ ያገናኘዋል፡፡ በተጨማሪም ዲማ ወረዳን ከጎግ ወረዳ ጋራ በማገናኘት ወደ ጋምቤላ የሚደረገውን ጉዞ የግዜና ገንዘብ ብክነት በእጥፍ ይቀንሰዋል። የመንገዱ መግንባት የኢሉአባቦር እና የሸካ ዞኖችን ከአኙዎክ ዞን ጋራ በቅርበት ያስተሳስራል። አካባቢው በርካታ ማዕድናት (ወርቅ) እና ሰፋፊ የእርሻ መሬት የሚገኝበት በመሆኑ የመንገዱ መገንባት ፋይዳው የጎላ ነው። በመንገዱ ኮሪደርና በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን የማር፥ ቡና፥ ቅመማቅመም እንዲሁም የሻይ ተክል ምርቶች በተገቢው ፍጥነት ወደ መሃል ገበያ ለማድረስ ያስችላል። የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን ከማሳለጡም ባሻገር፣ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች ማሕበራዊ አገልግሎት ተቋማት ተደራሽነትን ያሰፋል። ነባሩ መንገድ የጎን ስፋት ከ (3) ሶስት ሜትር የማይበልጥ ሲሆን አሁን እየተገነባ የሚገኘው በከተማ 17 ሜትር፣ በገጠር 10 ሜትር ተጨማሪ የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው እየተገነባ ያለው።

አኩይላ-አቻኛ ዲማ/ራድ መንገድ ግንባታ በታቀደለት የግንባታ ጊዜ እየተከወነ ይገኛል ----------------------------------------------------------------------------------- ጋምቤላ፣ ነሐሴ 30፣ 2014 (ኢመአ) በጋምቤላ ክልል ግንባታው እየተከናወነ ያለውና የጋምቤላ ክልልን ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ከኦሮሚያ ክልሎች ጋር በአቋራጭ የሚያስተሳስረው (የጋምቤላ አቦቦ-ጎግ ዲማ) አኩይላ-አቻኛ ዲማ/ራድ መንገድ ግንባታ በታቀደለት የግንባታ ጊዜ እየተከወነ ይገኛል ፡፡ ሰማኒያ ሁለት ኪሜ ( 82ኪሜ) የሚረዝመው ይህ መንገድ በአሁኑ ወቅት የዲዛይን ስራን ጨምሮ የምንጣሮ ስራ፣የአፈር ጠረጋ፣ ድልዳሎ እና ሙሌት፣ ተጨማሪ የጠጠር መፍጫ ማሽነሪ ተከላ ስራዎች እየተከናወኑለት ይገኛል። ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው አገር በቀሉ NKH Construction Plc ሲሆን የማማከርና የቁጥጥር ሥራውን ደግሞ በለስ ኮንሰልት Plc እየከወነ ይገኛል:: አጠቃላይ የግንባታ መዋለንዋይ ብር 1,574,746,965.24 ሲሆን የግንባታ ውጪውም የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው። ነባሩ መንገድ በጠጠር መንገድ ደረጃ የነበረና ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በመሆኑ ሕብረተሰቡን ለከፍተኛ እንግልት፣ አሽከርካሪዎችን ለጊዜ ወጪ እና ብክነት የዳረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ካለው ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ አንፃር መንገዱ በአስፋልት ኮንክሪት ደረጃ እየተገነባ ይገኛል። መንገዱ ተገንብቶ ሲጠናቀቅ ወደ ደቡብ ሱዳን ከሚወስደው ዋና አውራ ጎዳና (Trunk Road) ጋራ ያገናኘዋል፡፡ በተጨማሪም ዲማ ወረዳን ከጎግ ወረዳ ጋራ በማገናኘት ወደ ጋምቤላ የሚደረገውን ጉዞ የግዜና ገንዘብ ብክነት በእጥፍ ይቀንሰዋል። የመንገዱ መግንባት የኢሉአባቦር እና የሸካ ዞኖችን ከአኙዎክ ዞን ጋራ በቅርበት ያስተሳስራል። አካባቢው በርካታ ማዕድናት (ወርቅ) እና ሰፋፊ የእርሻ መሬት የሚገኝበት በመሆኑ የመንገዱ መገንባት ፋይዳው የጎላ ነው። በመንገዱ ኮሪደርና በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን የማር፥ ቡና፥ ቅመማቅመም እንዲሁም የሻይ ተክል ምርቶች በተገቢው ፍጥነት ወደ መሃል ገበያ ለማድረስ ያስችላል። የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን ከማሳለጡም ባሻገር፣ የጤና፣ የትምህርትና ሌሎች ማሕበራዊ አገልግሎት ተቋማት ተደራሽነትን ያሰፋል። ነባሩ መንገድ የጎን ስፋት ከ (3) ሶስት ሜትር የማይበልጥ ሲሆን አሁን እየተገነባ የሚገኘው በከተማ 17 ሜትር፣ በገጠር 10 ሜትር ተጨማሪ የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው እየተገነባ ያለው።

የጅግጅጋ ከተማ ባይፓስ(Bypass) መንገድ ግንባታ በትኩረት እየተከናወነ ነው። ጅግጅጋ ፣ ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም. ፦ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ የሚያስቀረው የጅግጅጋ ባይፓስ (Bypass) መ
+4
የጅግጅጋ ከተማ ባይፓስ(Bypass) መንገድ ግንባታ በትኩረት እየተከናወነ ነው። ጅግጅጋ ፣ ነሐሴ 23/2014 ዓ.ም. ፦ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅ የሚያስቀረው የጅግጅጋ ባይፓስ (Bypass) መንገድ ግንባታ ሥራ እየተካሄደ ነው። ሰባት (7) ኪ.ሜ የሚረዝመው የመንገድ ፕሮጀክቱ የፌደራል መንግስት በመደበው 672 ሚሊዮን ብር ወጪ ነው ግንባታው እየተከናወነ የሚገኘው። 'ባይፓስ' መንገድ አንድ ዋና ማሳለጫ ባላቸው ከተሞች በውጭ የሚገነባና ተሽከርካሪዎች ከተማ ውስጥ መግባት ሳያስፈልጋቸው አልፈው እንዲሄዱ የሚያገለግል ነው። መንገዱ የከተማዋን የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ ለመቅረፍ ታልሞ ነው የሚገነባው። ግንባታውን እያከናወነ የሚገኘው ይርጋለም ኮንስትራክሽን ሲሆን በእስካሁኑ የግንባታ ሂደት የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ የሰብቤዝ፣ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራና የ94 ሜትር ድልድይ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። አስፋልት ለማንጠፍ የሚረዱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችም እየተሠሩ ነው። የመንገድ ግንባታው ዋነኛ ግብዓት የሆነው የሲሚንቶ ዕጥረት ለስራው ፈተና እንደሆነበትም ታውቋል። ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ። የማማከሩን ስራ እያከናወነ የሚገኘው ደግሞ ኤልዳ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልታንትሲ ሲሆን የድጋፍና ክትትል ሥራውን እያከናወነ ይገኛል። የመንገድ ግንባታው በትላልቅ ከተሞች የመንገድ ደረጃ በኮንክሪት አስፋልት እየተገነባ የሚገኝ ሲሆን፥ የእግረኛ እና የብስክሌት መተላለፊያ እንዲሁም የአረንጓዴ ሥፍራ በፕሮጅክቱ ተካትተውበታል። የጅግጅጋ ባይባስ ግንባታ ሲጠናቀቅ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በማሳለጥ፤ ለከተማዋ ዕድገት ምቹ ዕድል ይፈጥራል። በክልሉ ለሚደረጉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም የጎላ ሚና አለው። መንገዱ 30 ሜትር የጎን ስፋት አለው።