ch
Feedback
ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር

前往频道在 Telegram

Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

显示更多

📈 Telegram 频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 的分析概览

频道 ERA ኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር (@ethioroads) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 13 464 名订阅者,在 交通 类别中位列第 1 734,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 494

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 13 464 名订阅者。

根据 27 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 198,过去 24 小时变化为 15,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 35.35%。内容发布后 24 小时内通常能获得 N/A% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 756 次浏览,首日通常累积 0 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 11

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
Official ERA Telegram Channal በዚህ የቴሌግራም ቻናል የመንገድ ዜናዎችን የስራና የመንገድ ጨረታ ማስታወቂያዎችን የመንገድ ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮችን ያገኛሉ።

凭借高频更新(最新数据采集于 28 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 交通 类别中的关键影响点。

13 464
订阅者
+1524 小时
+847
+19830
帖子存档
የሰቀላ-አዴት የመንገድ ግንባታ ሂደትን ለማቀላጠፍ በትኩረት እየተሰራ ነው አዲስ አበባ፣ የካቲት 4፣ 2018 (ኢመአ) :- የደምበጫ ፈረስ ቤት አዴት ኮንትራት ሁለት ሰቀላ-አዴት 61.76 ኪሎሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ሂደትን ለማቀላጠፍ በትኩረት እየተሰራ ነው ፡፡ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ ባለው በዚህ የመንገድ ግንባታ ሂደት አሁን ላይ የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ የውሃ ማፋሰሻ፣ የድልድይ እና የድንጋይ ድጋፍ እንዲሁም የጠጠር መፍጨት ሥራዎች እየተሰሩ ናቸው። ግንባታውን ዲ. ኤም.ሲ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፤ ኢንጅነር ዘውዴ እስክንድር ኃ/የተ/የግ/ማህበር ደግሞ የማማከሩንና የቁጥጥሩን ሥራ እየሰራው ይገኛል። ለግንባታው የሚውለው 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በኢትዮጵያ መንግስት የተሸፈነ ነው። በእስካሁኑ የግንባታው ሂደት በአካባቢውአልፎ አልፎ የሚስተዋለው የፀጥታ ፣ የወሰን ማስከበር እና የግብዓት እጥረት ችግሮች ፕሮጀክቱ በሚፈለገው ፍጥነት እንዳይሄድ እንቅፋት ሆኖው ቆይተዋል። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ባደረገው ከፍተኛ ጥረት አሁን ላይ ፕሮጀክቱን ለማፍጠን በትኩረት እየተሰራ ይገኛል። የመንገድ ፕሮጀክቱ የይልማና ዴንሳ ፣ ደጋ ዳሞት እና ቋሪት ወረዳዎች እና የሰቀላ ፣ የሀሙስ ገበያ ፣ አይባር ፣ ጎሽየ ፣ አዴት ዙሪያ እና ብር አዳማ ያሉ ቀበሌዎች በማገናኘት ሁለንተናዊ ትስስርን በዘላቂነት ይፈጥራል። በተጨማሪም በአካባቢው በስፋት የሚመረቱትን እንደ ጤፍ ፣ በቆሎ ፣ ሽንኩርት ፣ ገብስ ፣ ስንዴና ድንች ያሉ ሰብሎችን እንዲሁም የማርና የእንስሳት ተዋፅኦዎችን ያለምንም እንግልት ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማውጣት ሰፊ እድል በመፍጠር የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ያረጋግጣል። ግንባታው ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት በሚሆንበት ጊዜ ቀድሞ ለጉዞ ይባክን የነበረውን ሰዓትና ድካም በግማሽ በመቀነስ የአካባቢውን የንግድ ልውውጥና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሳልጠው ይጠበቃል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የአዲስ  - ሰበታ  - ሆለታ  የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ለማፋጠን እየተሰራ ነው አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2018 (ኢመአ) :- አዲስ  አበባን ከተለያዩ  የክልል  ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና መግቢያ እና መውጫ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች  መካከል አንዱ  የሆነው  የአዲስ  - ሰበታ -ሆለታ  50 ነጥብ 2  ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን ለማፋጠን እየተሰራ  ይገኛል። በኢትዮጵያ  መንግስት  በ 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር  እየተከናወነ የሚገኘው  ይህ የመንገድ ግንባታ፤ በብሪጅ ኮንስትራክሽን፣ በመሳይ ኦሊ  እና  በፋል  ጠቅላላ የሥራ ተቋራጮች ጥምረት በመከናወን ላይ ነዉ። የፕሮጀክቱን  የማማከርና  የቁጥጥር  ሥራ ኮር ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ እና  ፎርትረስ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ በጋራ  እየሰሩት ይገኛሉ። የተሸከርካሪዎችን ፍሰት  በዘላቂነት  የሚያቀላጠፈው ይህ መንገድ፤ የአዲስ-ሰበታ፣ የሰበታ-ሆለታ እና የሱባ መናፈሻ ፓርክን የሚያገናኙ ሦስት ክፍሎች ያሉት ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅትም ከፍተኛ የትራንስፖርት ጫና የሚስተዋልበትን የመጀመሪያ ምዕራፍ  የአዲስ- ሰበታ 11 ነጥብ  9 ኪሎ ሜትር  ግንባታ  በተያዘው  ዓመት አጠናቆ ለአገልግሎት ለአገልግሎት ለማብቃት  እየተሠራ ነው። ቀደም ሲል መንገዱ የነበረው 10 ሜትር የጎን ስፋት የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን አስቸጋሪ አድርጎት ቆይቷል። ይኸው የመንገድ ክፍል፤ አሁን ላይ በግራና በቀኝ አራት የመኪና  መተላለፊያዎችን፣ የእግረኛና የሳይክል መንገዶችን እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በማካተት በ 50 ሜትር የጎን ስፋት እየተገነባ ነው። ይህንኑ የግንባታ ሂደት ለማፋጠን በአሁኑ ወቅት የአፈር ቆረጣና ሙሌት፣ የቁፋሮ፣ የውሃ ማፋሰሻ ቱቦ ቀበራ እንዲሁም የድጋፍ ግንብ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ። በሦስት ዓመት ውስጥ የሚጠናቀቀው የአዲስ -ሰበታ  -ሆለታ የመንገድ ፕሮጀክት በተለይም ከአዲስ አበባ ወደ ወልቂጤ፣ ጅማ እና ጋምቤላ የሚደረገውን የትራንስፖርት ፍሰት የሚያቀላጥፍ ሲሆን፤ ከዚህም ጎን ለጎን የደቡብ ሸዋና ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞኖችን፣ የሸገርና የሆለታ ከተማ አስተዳደሮችን እንዲሁም የሰበታ ሀዋስና የወልመራ ወረዳዎችን በቅርበት  ያስተሳስራል። ግንባታው ሲጠናቀቅ የአካባቢውን ነዋሪዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ከመሆኑም ባለፈ የጉዞ ጊዜን፣ ወጪንና እንግልትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። በተጨማሪም የግብርና ምርቶች በፍጥነት ለገበያ እንዲቀርቡና እንደ ሱባ ፓርክ ያሉ የቱሪዝም መዳረሻዎች በቀላሉ እንዲጎበኙ በማስቻል ለአካባቢው ዕድገት የላቀ ፋይዳ ይኖረዋል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የጅማ - አጋሮ - ዴዴሳ ወንዝ የመንገድ ግንባታ 85 በመቶ ደረሰ አዲስ አበባ፣ ጥር 26፣ 2018 (ኢመአ):- የጅማ - አጋሮ - ዴዴሳ ወንዝ የአስፋልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት 85 በመቶ ደርሷል፡፡ 79.74 ኪሎ ሜትር ርዝመት ባለው በዚህ የመንገድ ፕሮጀክት እስካሁን ድረስ 53.28 ኪሎ ሜትር የሚሆነው የአስፋልት ንጣፍ ሥራ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል። በአሁኑ ወቅት የ71.20 ኪሎ ሜትር የአፈር ጠረጋና ሙሌት እንዲሁም የ61.66 ኪሎ ሜትር የሰብቤዝ ሥራ ተጠናቋል። ከዚህም በተጨማሪ የውኃ መፋሰሻ ቱቦ ቀበራ 87.36 በመቶ፣ የተለያዩ የስትራክቸር ሥራዎች ደግሞ 77.56 በመቶ አፈጻጸም ላይ ደርሰዋል፡፡ በፌደራል መንግሥት ከ 2.29 ቢሊዮን ብር እየተገነባ የሚገኘው የጅማ - አጋሮ ዴዴሳ ወንዝ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በቻይና ሬልዌይ 21 ግሩፕ የሥራ ተቋራጭ አማካኝነት በመከናወን ላይ ሲሆን የፕሮጀክቱን የመቆጣጠር እና የማማከር ሥራ ኦሜጋ ኢንጂነሪንግ አማካሪ ከፕሮም አማካሪ ጋር በመተባበር እየሰሩት ይገኛሉ። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በግንባታ ሂደቱ የታዩ ችግሮችን በመፍታትና ለትራፊክ ደህንነት ምቹ የሆኑ የዲዛይን ማሻሻያዎችን በማካተት፤ የፕሮጀክቱን ጥራትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው። የአዲስ አበባ – ወሊሶ – ጅማ – አጋሮ – ዴዴሳ ወንዝ ድልድይ - በደሌ – መቱ – ጋምቤላ ዋና የመንገድ አካል የሆነው ይህ ፕሮጀክት ከጅማ ከተማ ተነስቶ ዴዴሳ ወንዝ ድልድይ ድረስ የሚዘልቅ ሲሆን፤ በገጠር 10 ሜትር፣ በቀበሌ 12 ሜትር ፣ በወረዳ 19 ሜትር እንዲሁም በዞን 22 .5 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው በመገንባት ላይ የሚገኘው፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ የጉዞ ጊዜን በእጅጉ በማሳጠር ለማህበረሰቡ ምቹ፣ ቀልጣፋና አስተማማኝ የትራንስፖርት ትስስር ይፈጥራል። ይህም ጊዜን ለመቆጠብና የጉዞ ደህንነትን ከማረጋገጡም በላይ የአካባቢውን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ይበልጥ እንዲቀላጠፍ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ከዚህ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው ባሻገር የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሆኑትን የቡና እና ልዩ ልዩ የጥራጥሬ፣ የቅመማ ቅመም እንዲሁም ሌሎች የግብርና ውጤቶችን በፍጥነት ወደ ገበያ እንዲደርሱ በማድረግ የሀገሪቱን ብሎም የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ይጨምራል። በተጨማሪም ወደ አባ ጅፋር ቤተ-መንግሥት በቀላሉ ለመጓዝ ከማስቻሉ ጎን ለጎን የጅማና የአጋሮ ከተሞችን የኑሮ ደረጃ የሚያሻሽሉ የኮሪደር ልማት ሥራዎችን በማካተቱ ፤ የአካባቢውን የቱሪዝም እንቅስቃሴና ሁለንተናዊ ዕድገት በከፍተኛ ደረጃ ያፋጥናል፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የለሚ - ጀማ ወንዝ መንገድ ወደ ግንባታ ሊሸጋገር ነው አዲስ አበባ፣ ጥር 25/2018 ዓ.ም (ኢመአ)፦ የለሚ - ጀማ ወንዝ የ20 ኪሎ ሜትር መንገድን የሚያከናውነው የሥራ ተቋራጭ በመለየት ወደ ግንባታ ምዕራፍ ሊሸጋገር ነው፡፡ በ 5.1 ቢሊየን ብር በጀት የሚገነባው ይህ መንገድ ለአካባቢው ህብረተሰብና ለመንገዱ ተጠቃሚዎች ምቹ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ ከማስቻሉ ባሻገር የተለያዩ የግብርና ውጤቶችን ለማውጣት ብሎም የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ምርቶችን ወደ ተለያዩ የገበያ ማእከላት ለማድረስ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡፡ በህብር ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን አማካኝነት የሚገነባው ይህ መንገድ በአሁኑ ወቅት ወደ ሥራ ለመግባት የሚያስችለውን የዝግጅት ምዕራፍ በማጠናቀቅ ላይ ይገኛል። መንገዱ በሲሚንቶ ኮንክሪት ደረጃ የሚገነባ ሆኖ በገጠር ከ 8-10 ሜትር እንዲሁም በከተማ ደግሞ 15 ሜትር ስፋት ይኖረዋል። ግንባታው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡ በተመሳሳይ ከጀማ ወንዝ - ዓለም ከተማ የሚዘልቀው የመንገድ ግንባታ በአካባቢው በነበረው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር ምክንያት ተቋርጦ መቆየቱ ይታወሳል። በዚህም ረገድ ዋና የግንባታ ሥራው እስከሚጀመር ድረስ ኅብረተሰቡ የተሻለ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንዲችል በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በራስ ኃይል የጥገና ሥራውን ለማከናወን የሚያስችሉ የዝግጅት ሥራዎች በመጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ የጥገና ሥራ በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ የሚጀመር ሲሆን በሚጠናቀቅበት ወቅት ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት እንዲሰጥ የሚያስችል ይሆናል፡፡ የዚሁ መንገድ የመጀመሪያው ክፍል የሆነው የሙከጡሪ - ኮከብ መስክ 59 ኪሎሜትር የሚሸፍነው የመንገድ ግንባታ ቀደም ብሎ ተጠናቅቆ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የደባርቅ - ጃናሞራ መንገድ ግንባታ ለማፋጠን እየተሰራ ነው አዲስ አበባ፣ ጥር 22/2018 (ኢመአ):- በሰሜን ጎንደር ዞን 63 ኪሎሜትር የሚሸፍነው የደባርቅ - ጃናሞራ መንገድ ግንባታ ለማፋጠን እየተሰራ ነው። በመንገድ ፕሮጀክቱ አሁን ላይ አስፋልት የማንጠፍ ሥራ በመከናወን ላይ ነው። ቀደም ሲል በተለያዩ የሥራ ተቋራጮች ሲከናወን የቆየው ይኸው መንገድ በደካማ አፈጻጸም፣ ከዲዛይን ለውጦች እና ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ግንባታው ዘግይቶ እንደነበር ይታወሳል። አሁን ላይ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ ፕሮጀክቱን ተረክቦ በግንባታ ሂደት ላይ ነው። አይዲኮን ኢንፍራስትራክቸር ዴቨሎፕመንት ኮንሰልታንስ የማማከር እና የቁጥጥር ሥራውን በመሥራት ላይ ይገኛል። ለመንገድ ግንባታው 4.174 ቢሊዮን (አራት ቢሊዮን አንድ መቶ ሰባ አራት ሚሊዮን) ብር በጀት ተይዞለታል። ወጪው በፌደራል መንግሥት ይሸፈናል። አሁን ላይ ከአስፋልት ሥራው ጎን ለጎን የአፈርና የአለት ቆረጣ፣ ሙሌት እንዲሁም የሰብቤዝ እና ቤዝኮርስ ሥራዎች በመከናወን ላይ ናቸው። የተጀመረው የአስፋልት ንጣፍ ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል አስፈላጊ የቅድመ-ዝግጅት ሥራዎች ተጠናቅቀዋል። መንገዱ ሲጀመር በድርብ-አስፋልት (DBST) ደረጃ ሊገነባ ታቅዶ የነበረ ቢኾንም፥ ሥፍራው ካለው ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎች እና ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት አንጻር ወደ አስፋልት ኮንክሪት እንዲያድግ ተደርጓል። የመንገድ ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ በፊት ከደባርቅ - ጃናሞራ ለመጓዝ ይወስድ ይነበረውን የጉዞ ጊዜ ከ4 ሰዓት ወደ 1 ሰዓት ተኩል ያሳጥረዋል። በሥፍራው የሚገኙ ከተሞችን ከበለስ እና ወይና ቀበሌ እንዲሁም ከመካነ-ብርሃን ከተማ ጋር በማስተሳሰር የንግድ እንቅስቃሴውን ያቀላጥፋል። የሰሜን ብሔራዊ ፓርክን ለውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ምቹ እንዲሆን ያስችላል። ኢንቨስትመንትን በመሳብ ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

የጨረቲ - ጎሮቦከክሳ - ጎርዳሞሌ: ሎት 3 ቁንዲ - ጎሮዳሞሌ - ጅብሪል የአስፋልት መንገድ ግንባታን ፕሮጀክት በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው አዲስ አበባ፣ ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ መ አ)፦ የሶማሌ እና ኦሮሚያ ክልሎችን በአስፋልት መንገድ የሚያስተሳስረው ሎት 3 ቁንዲ - ጎሮዳሞሌ - ጅብሪል የአስፋልት መንገድ ግንባታ ፕሮጀክትን በአጠረ ጊዜ ለማጠናቀቅ እየተሰራ ይገኛል። ይህ የመንገድ ፕሮጀክት 77.8 ኪሎ ሜትር ርዝመትን የሚሸፍን ሲሆን በእስካሁኑ የመንገድ ግንባታ ስራ የተለዋዋጭ መንገድ ፣የጠረጋ ፣የማፋሰሻ ቱቦ እና የፋካ ስራዎች፣አፈር ቆረጣ እና ሙሌት፣የካፒንግ ፣እንዲሁም በርካታ የስትራክቸው ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛል። ይህም እንቅስቃሴውን 44.7 % በመቶ እንዲደርስ አስችሎታል። የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቱ መነሻውን ቁንዲ ከተማ (192+000) አድርጎ እስከ ጅብሪል ከተማ (269+800) ድረስ የሚዘልቅ ነው። ለግንባታ ማስፈጸሚያ የሚውለውን ገንዘብ 3,811,899,916.93 (ሶስት ቢሊዮን ስምንት መቶ አስራ አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ሺህ ዘጠኝ መቶ አስራ ስድስት ከዘጠና ሶስት ሳንቲም) ብር የሚሸፈነው በኢትዮጵያ መንግስት ነው ። የግንባታ ፕሮጀክቱን እያካሄደ የሚገኘው ኤምሲጂ ኮንስትራክሽን ኃ/የ/ማ ሲሆን የማማከር እና የቁጥጥር ስራውን ደግሞ ኮር አማካሪ መሀንዲሶች አ.ማ እያከናወኑት ይገኛሉ። ፕሮጀክቱ ደረጃውን በጠበቀ አስፋልት መገንባቱ ለአካባቢው ማህበረሰብም ሆነ ለመስመሩ ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት ላይ ከፍተኛ ለውጥን ያመጣል። ይህ የመንገድ ፕሮጀክት ተገንብቶ ሲጠናቀቅ አቋርጧቸው የሚሄዱ ከተሞች፣ ወረዳዎች እና ቀበሌዎችን በአስፋልት መንገድ ከማገናኘቱም ባለፈ የትራንስፖርት ተደራሽነት እና ተጠቃሚነትን ከፍ ያደርገዋል፤ በተጨማሪም ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ከቁንዲ ከተማ እስከ ጅብሪል ከተማ በተሽከርካሪ ለማጓዝ ይወስድ የነበረውን የ8፡00 ሰዓት ጉዞ ወደ 1:30 ከማሳጠሩም ባለፈ ለትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል። የመንገድ ግንባታው በከተማ 19 ሜትር የጎን ስፋት ሲኖረው በገጠር 8 ሜትር የጎን ስፋት እንዲኖረው ተደርጎ ነው እየተገነባ ነው የሚገኘው ። የዚህ መንገድ አካል የሆኑት የጨረቲ - ሀገረመቆር ክፍል -1 እና የሀገረመቆር - ቁንዲ ክፍል ሁለት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ቀደም ብሎ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑ ይታወሳል ፡፡ በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads

ባለፉት 6 ወራት የ237 ኪሎሜትር የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ፣ 133 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶች ማጠናከርና ደረጃ ማሻሻል እና 6 ሺህ 577 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ የጥገና ሥራዎች ተከናወኑ አዲስ አበባ፣ ጥር 19/2018 (ኢ መ አ):- በበጀት ዓመቱ ባለፉት 6 ወራት 237 ኪሎሜትር የሚሸፍኑ የአዳዲስ መንገዶች ግንባታ፣ 133 ኪሎ ሜትር ነባር መንገዶች ማጠናከርና ደረጃ ማሻሻል እና 6 ሺህ 577 ኪሎሜትር ልዩ ልዩ የጥገና ሥራዎች ተከናውነዋል። ተቋማችን የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ ወራት ዕቅድ አስመልክቶ በዓለምገና ኢንጅነሪንግ እና ማኔጅመንት ማሠልጠኛ ማዕከል አጠቃላይ ውይይት አካሂዷል። በዚሁ ወቅት በቀረበው ሪፖርት መሰረት የመንገዶች ግንባታ፣ ማጠናከርና ማሻሻል የእቅዱን 81 በመቶ፤ የመንገዶች ከባድ ጥገና የእቅዱን 80 በመቶ፤ ወቅታዊ የመንገዶች ጥገና የእቅዱን 71 በመቶ እንዲሁም መደበኛ ጥገና የእቅዱን 86 በመቶ አፈጻጸም ተመዝግቧል፡፡ በሌላ በኩል በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራት በምህንድስና ግዥ፣ በዲዛይን ፕሮጀክቶች፣ በግንባታ እና በልዩ ልዩ የጥገና ሥራዎች እንዲሁም በተቋም አቅም ግንባታ ስራዎች በተሰጣቸው ክብደት መሰረት በተቋም ደረጃ ሲጠቃለል የዕቅዱን 81 በመቶ ማሳካቱ ተገልጿል። ተቋማችን በተያዘው በጀት ዓመት 314 የግንባታ፣ 50 የከባድ ጥገና ፣ 73 ወቅታዊ ጥገና፣ 56 መደበኛ ጥገና ፣ 184 የምህንድስና ግዥ እና 35 የዲዛይን ጥናት ፕሮጀክቶች ጨምሮ በአጠቃላይ 712 ፕሮጀክቶችን እያከናወነ እንደሚገኝ ሪፖርቱ አመላክቷል። የኢተያ - አርሲ ሮቤ፣ እስቴ - ስማዳ ፣ የድሬዳዋ ሽንሌ እና የድሬዳዋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ፣ የጅግጅጋ ከተማ ተለዋጭ መንገድ እንዲሁም ሳውላ - ቃቆ መንገድ ፕሮጀክቶች በዚህ በጀት ዓመት የተጠናቀቁ መሆኑም ተገልጿል። በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻም የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ከ16 ሺህ 976 ኪሎሜትር በላይ የሚሸፍኑ የመንገድ ግንባታ እና ልዩ ልዩ የጥገና ሥራዎችን ለማከናወን ግብ ተቀምጦ እየተሠራ ይገኛል። ከዚሁ ጎን ለጎን ተቋማችን የመንገድ ግንባታውን የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ውጤቶች ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ የምርምር ሥራዎችን የሚያከናውን ሲሆን፣ የዚሁ ጥረት ውጤት የሆነውን ያገለገሉ የተሽከርካሪ ጎማዎችን ከአስፋልት ጋር በማዋሀድ ለመንገድ ንጣፍ በመጠቀም የአገልግሎት ጊዜን አራዝሞ ለጥገና የሚወጣውን ወጪ ለመቀነስ የሚያስችል የቴክኖሎጂ ውጤት በተሞክሮነት አቅርቧል። በተጨማሪ › አጭር መልዕክት 8561 › ፖስታ ሳጥን ቁጥር 1770 › ድህረገጽ www.era.gov.et › ፊስቡክ https://www.facebook.com/www.era.gov.et › ቴሌግራም https://t.me/ethioroads › ትዊተር https://twitter.com/EthiopiaRoadsAd › ኢንስታግራም https://www.instagram.com/ethioroads › ኢሜል communication@era.gov.et › ዩቲዮብ www.youtube.com/@ethioroads