ስንክሳር (ገድላት) ዘዕለታት
前往频道在 Telegram
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርሥትያን ስንክሣር ውስጥ የተጻፉ የቅዱሳን አባቶቻችንና የቅዱሳት እናቶቻችን ገድላቸውና አስገራሚ ታሪካቸው ዓመቱን ሙሉ ምንም ሳይቋረጥ በየቀኑ ይነገርበታል! ለአሥትያየትዎ @abitago
显示更多1 208
订阅者
-224 小时
-27 天
-530 天
数据加载中...
吸引订阅者
九月 '269月 '26
九月 '26
+14
在0个频道中
八月 '26
+18
在0个频道中
Get PRO
七月 '26
+26
在0个频道中
Get PRO
六月 '26
+25
在0个频道中
Get PRO
五月 '26
+27
在0个频道中
Get PRO
四月 '26
+11
在0个频道中
Get PRO
三月 '26
+15
在0个频道中
Get PRO
二月 '26
+23
在0个频道中
Get PRO
一月 '26
+38
在0个频道中
Get PRO
十二月 '25
+39
在0个频道中
Get PRO
十一月 '25
+36
在0个频道中
Get PRO
十月 '25
+21
在0个频道中
Get PRO
九月 '25
+20
在0个频道中
Get PRO
八月 '25
+10
在0个频道中
Get PRO
七月 '25
+32
在0个频道中
Get PRO
六月 '25
+21
在0个频道中
Get PRO
五月 '25
+21
在0个频道中
Get PRO
四月 '25
+26
在0个频道中
Get PRO
三月 '25
+54
在0个频道中
Get PRO
二月 '25
+34
在0个频道中
Get PRO
一月 '25
+67
在0个频道中
Get PRO
十二月 '24
+90
在0个频道中
Get PRO
十一月 '24
+82
在1个频道中
Get PRO
十月 '24
+46
在0个频道中
Get PRO
九月 '24
+61
在0个频道中
Get PRO
八月 '24
+67
在0个频道中
Get PRO
七月 '24
+57
在0个频道中
Get PRO
六月 '24
+65
在0个频道中
Get PRO
五月 '24
+66
在0个频道中
Get PRO
四月 '24
+85
在1个频道中
Get PRO
三月 '24
+68
在0个频道中
Get PRO
二月 '24
+118
在0个频道中
Get PRO
一月 '24
+99
在0个频道中
Get PRO
十二月 '23
+98
在0个频道中
Get PRO
十一月 '23
+25
在0个频道中
Get PRO
十月 '23
+13
在1个频道中
Get PRO
九月 '23
+7
在0个频道中
Get PRO
八月 '23
+17
在0个频道中
Get PRO
七月 '23
+16
在0个频道中
Get PRO
六月 '23
+9
在0个频道中
Get PRO
五月 '23
+3
在0个频道中
Get PRO
四月 '23
+4
在0个频道中
Get PRO
三月 '23
+3
在0个频道中
Get PRO
二月 '23
+5
在0个频道中
Get PRO
一月 '23
+14
在0个频道中
Get PRO
十二月 '22
+10
在0个频道中
Get PRO
十一月 '22
+10
在0个频道中
Get PRO
十月 '22
+8
在0个频道中
Get PRO
九月 '22
+11
在0个频道中
Get PRO
八月 '22
+4
在0个频道中
Get PRO
七月 '22
+11
在0个频道中
Get PRO
六月 '22
+11
在0个频道中
Get PRO
五月 '22
+5
在0个频道中
Get PRO
四月 '22
+4
在0个频道中
Get PRO
三月 '22
+6
在0个频道中
Get PRO
二月 '22
+10
在0个频道中
Get PRO
一月 '22
+7
在0个频道中
Get PRO
十二月 '21
+7
在0个频道中
Get PRO
十一月 '21
+8
在0个频道中
Get PRO
十月 '21
+3
在0个频道中
Get PRO
九月 '21
+11
在0个频道中
Get PRO
八月 '21
+9
在0个频道中
Get PRO
七月 '21
+13
在0个频道中
Get PRO
六月 '21
+6
在0个频道中
Get PRO
五月 '21
+8
在0个频道中
Get PRO
四月 '21
+26
在0个频道中
Get PRO
三月 '21
+500
在0个频道中
| 日期 | 订阅者增长 | 提及 | 频道 | |
| 28 九月 | 0 | |||
| 27 九月 | 0 | |||
| 26 九月 | +1 | |||
| 25 九月 | +2 | |||
| 24 九月 | 0 | |||
| 23 九月 | 0 | |||
| 22 九月 | 0 | |||
| 21 九月 | +1 | |||
| 20 九月 | 0 | |||
| 19 九月 | 0 | |||
| 18 九月 | 0 | |||
| 17 九月 | 0 | |||
| 16 九月 | 0 | |||
| 15 九月 | 0 | |||
| 14 九月 | +1 | |||
| 13 九月 | +1 | |||
| 12 九月 | 0 | |||
| 11 九月 | +1 | |||
| 10 九月 | +1 | |||
| 09 九月 | +2 | |||
| 08 九月 | +1 | |||
| 07 九月 | +1 | |||
| 06 九月 | +1 | |||
| 05 九月 | 0 | |||
| 04 九月 | 0 | |||
| 03 九月 | +1 | |||
| 02 九月 | 0 | |||
| 01 九月 | 0 |
频道帖子
| 2 | 没有文字... | 95 |
| 3 | 没有文字... | 94 |
| 4 | 没有文字... | 87 |
| 5 | 没有文字... | 64 |
| 6 | 没有文字... | 50 |
| 7 | ቅድስት ድንግል ታኦግንስጣም ተጋድሎዋን ከፈጸመች በኋላ እግዚአብሔርንም አገልግላ ደስ አሰኝታ በዚያ ገዳም በደናግሉ መካከል በሰላም በፍቅር አረፈች።
ረድኤት በረከቷ ትደርብን በጸሎቷ ይማረን!
+ + + + +
ዳግመኛም በዚችም ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ዐሥራ አራተኛ የሆነ የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ዲዮናስዮስ ዕረፍቱ ነው ።
አቡነ ዲዮናስዮስ:- ይህንንም ቅዱስ ንጉሥ ዳኬዎስ ሊገድለው ፈልጎት ነበር ግን እግዚአብሔር ሠወረው ይህም አባት ብልህ አዋቂ ስለነበረ ብዙዎች የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትን ተረጎመ።
በዘመኑም በሮም ንጉሥ በከሀዲ ዳኬዎስ እጅ ቅዱስ መርቆሬዎስ በሰማዕትነት አረፈ። ሁለተኛም ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው ነቁ እሊህም ለጣዖታት ሊአሰግዳቸው በፈለጋቸው ጊዜ ከዳኬዎስ ፊት የሸሹ ከኤፌሶን አገር ከታላላቆች ተወላጆች ወገን የሆኑ ናቸው።
ዳግመኛም በዘመኑ የመነኰሳት አለቃ ገዳማትን የሠራ ግብጻዊው ታላቁ እንጦንዮስ ለመጀመሪያ ጊዜ መነኰስን ሆነ። ይህም ቅዱስ ዲዮናስዮስ በሊቀ ጵጵስናው ሹመት ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ። መንጋዎቹንም በትክክል በፍቅር አንድነት ጠበቃቸው እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
ረድኤት በረከቱ ትደርብን በጸሎቱ ይማረን! | 40 |
| 8 | ዓሥሩን ታላላቅ ቅዱሳን ይዘው ሄደው መስቀሉን መስከረም 10 ቀን አምጥተውታል፡፡ ቅዱስ መስቀሉን ያመጡት ዓሥሩ ቅዱሳንም የደብረ ቢዘኑ አቡነ ፊሊጶስ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ ኂሩተ አምላክ፣ የጣና ደሴቱ አቡነ እንድርያስ፣ አቡነ በትረ ማርያም፣ አቡነ ዮሐንስ፣ አቡነ ታዴዎስ፣ አቡነ ያፍቅረነ እግዚእ፣ አቡነ ዘካርያስ፣ አቡነ ያሳይ ዘማንዳባና አቡነ ቶማስ ናቸው፡፡
ወደ ቅዱስ መስቀሉ አመጣጥ እንመለስና እስክንድርያ ያሉ ምዕመናንም የዐፄ ዳዊትን "በሀገሬ ኢትዮጵያ ረሀብና ቸነፈር ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀልና የቅዱሳን አጽም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር እንድትልኩልኝ" የሚለው መልዕክት እንደደረሳቸው ከሊቃነ ጳጳሳትና ከኤጲስ ቆጶሳቱ ጋር ውይይት በማድረግ "ይህ ንጉሥ ታላቅ ክርስቲያን ነው፡፡ ስለዚህ ልቡን ደስ እንዲለው የፈለገውን የጌታችንን ግማደ መስቀል ከቅዱሳን ዐፅምና ንዋየ ቅዱሳት ጋር አሁን በመለሰው ወቄት ወርቅ የብርና የነሐስ የመዳብና የወርቅ ሣጥን አዘጋጅተን እንላክለት" ብለው ተስማምተው በክብር በሥነ ሥርዓት በሠረገላና በግመል አስጭነው ስናር ድረስ አምጥተው ለኢትዮጵያውያን ባስረከቧቸው ጊዜ በእጃቸው እያጨበጨቡ በእግራቸው እያሸበሸቡ በግንባራቸው እየሰገዱ በክብር በደስታ ተቀበሏቸው፡፡
ግማደ መስቀሉ ወደ መካከለኛው ኢትዮጵያ ሳይደርስ በድንገት ዐፄ ዳዊት ስናር በሚባል በረሃ ላይ አረፉ፡፡ ግማደ መስቀሉም የግድ በዚያው በስናር መቆየት አስፈለገው፡፡ ከዚህ በኋላ የሟቹ የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ እንደነገሡ ወደ ስናር ሔደው ግማደ መስቀሉን ከሌሎቹ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር አምጥተው በመናገሻ ከተማቸው በደብረ ብርሃን ላይ ቤተ መቅደስ ሠርተው ለማስቀመጥ ሲደክሙ በሕልማችው አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል "ወዳጄ ዘርዐ ያዕቆብ ሆይ መስቀሌን በመስቀለኛ ቦታ ላይ አስቀምጥ" የሚል ራእይ አዩ፡፡ ከእስክንድርያ ሀገር ከቅዱስ መስቀሉ ጋር በልዩ ልዩ ሣጥን ተቆልፈው የመጡትም ዝርዝር ስማቸው ጌታችን በዕለተ ዓርብ ለብሶት የነበረው ቀይ ልብስ፣ ከሮም የመጣው ከለሜዳው፣ ሐሞት የጠጣበት ሰፍነግ /ጽዋ/፣ ዮሐንስ የሳለው ኩርዓተ ርዕሱ ስዕል እንዲሁም የተለያዩ የቅዱሳን አጽም፣ ከግብጽ ታላላቅ ገዳማት የተቆነጠረ አፈር፣ የዮርዳኖስ ውሃ ይገኛል፡፡
ንጉሡም መስቀለኛ ቦታ እየፈለጉ በኢትዮጵያ አውራጃዎች ሁሉ በመፈለግ ከብዙ ቦታ አስቀምጠውት ነበር፡፡ ለምሳሌ በሸዋ በደብር ቅዱስ ደብረ ጽጌ ማርያም ገዳም፣ በማናገሻ ማርያም፣ በወጨጫ መስቀሉን አሳርፈውት ነበር፡፡ ነገር ግን የመጨረሻውን ቦታ ባለማግኘታቸው በራዕይ እየደጋገመ አንብር መስቅልየ በዲበ መስቅል-መስቀሌን በመስቀለኛ ሥፍራ አስቀምጥ እያለ ይነግራቸው ነበር፡፡ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብም ለሰባት ቀን ሱባዔ ገቡ፡፡ በዚያም የተገለጸላቸው "መስቀለኛውን ቦታ የሚመራህ ዓምደ ብርሃን ይመጣል" አላቸው፡፡ እርሳቸውም ከዚያ እንደወጡ መስቀለኛውን ቦታ የሚመራ የብርሃን ዓምድ ከፊታቸው መጥቶ ቆመ፡፡ በዚያ መሪነት ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር አምባሰል አውራጃ ውስጥ ግሸን ከምትባል አምባ መርቶ መስከረም 21ቀን1440 ዓ.ም አደረሳቸው፡፡ በእውነትም ይህች ግሸን የተባለችው አምባ ጥበበኛ ሰው እንደቀረጻት የተዋበች መስቀለኛ ቦታ ሆና ስላገኟት የልባቸው ስለደረሰ ደስ አላቸው፡፡ እግዚአብሔር ገና ዓለምን ሲፈጥር የግሸንን ዓምባ ለዚህ ክብር የተዘጋጀች አድርጎ ፈጥሯታልና፡፡ ንጉሡም በዚያም አምባ ታላቅ ቤተ መቅደስ ሠርተው መስቀሉንና ሌሎች ንዋየ ቅዱሳቱን በየመዓረጋቸው የክብር ቦታ መድበው አስቀመጡዋቸው፡፡
ለልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን! እኛንም የተዋሕዶ ልጆች የሆንን ሁላችንን ዛሬ በዓመታዊ ክብረ በዓሉ አስበነውና በታላቅ ድምቀት አክብረነው የምንውለውን የቅዱስ መስቀሉን ረድኤት በረከቱን ያሳድርብን!!!
ውድ የተዋሕዶ ልጆች ሁላችንንም እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን!!!
+ + + + +
ዳግመኛም በዚችም ቀን የከበረች ሮማዊት ታኦግንስጣ ዕረፍቷ ነው።
ቅድስት ታኦግንስጣ ይቺም ቅድስት በደጋጎች ነገሥታት በአኖሬዎስና በአርቃዴዎስ ዘመን የነበረች ናት። በዚያም ወራት የህንድ ንጉሥ መልእክተኞች እጅ መንሻ ይዘው ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ መጡ በሚመለሱም ጊዜ ይችን ድንግል ታኦግንስጣን አገኟት የምታነበውም መጽሐፍ በእጅዋ ውስጥ ነበር ወደ አገራቸውም ነጥቀው ወሰዷት ለህንድ ንጉሥም ሚስቶቹንና ቤተሰቦቹን የምትጠብቅ ሆነች።
በአንዲት ዕለትም የንጉሡ ልጅ አስጨናቂ በሆነ ደዌ ታመመ የከበረች ታኦግንስጣም ወስዳ በብብቷ ታቅፋ በመስቀል ምልክት አማተበችበት በዚያንም ጊዜ ዳነ ከእርሷም ስለ ተደረገው ተአምር የዚች የከበረች ድንግል ታኦግንስጣ ዜናዋ በሀገሩ ሁሉ ተሰማ ከዚያችም ቀን ወዲህ በእነርሱ ዘንድ እንደ እመቤት እንጂ እንደ አገልጋይ አልሆነችም።
ከዚህም በኋላ የህንድ ንጉሥ ወደ ጦርነት በሔደ ጊዜ ጉም ጭጋግ ዐውሎ ነፋስና ጨለማ በላዩ መጣ ንጉሡ ግን የከበረች ታኦግንስጣ ስታማትብ ስለአየ በመስቀል ምልክት ማማተብን ያውቅ ነበርና ያን ጊዜ በጭጋጉ በጉሙ በጨለማውና በጥቅሉ ነፋስ ላይ በመስቀል ምልክት አማተበ። ወዲያውኑ ፀሐይ ወጣ ታላቅ ጸጥታም ሆነ ጠላቶቹንም በዚሁ የመስቀል ምልክት ድል አደረጋቸው እጅግም ደስ አለው።
ንጉሡም ከጦርነት በተመለሰ ጊዜ ለከበረች ታኦግንስጣ። ከእግርዋ በታች ሰገደ እርሱንና ቤተሰቦቹን ሁሉ የሀገሩንም ሰዎች የከበረች የክርስትና ጥምቀትን ታጠምቀው ዘንድ ለመናት ቅድስት ታኦግንስጣም እንዲህ አለችው ይህን አደርግ ዘንድ ለእኔ አይገባኝም የሚያጠምቃችሁን ካህን ይልክላችሁ ዘንድ ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ ላኩ።
ያን ጊዜም ከወገኖቹ ጋር የሚያጠምቀውን ካህን እንዲልክለት የህንድ ንጉሥ ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ መልእክተኞችን ላከ ንጉሥ አኖሬዎስም ልመናውን ተቀብሎ የሚያጠምቃቸውን ቄስ ላከ ቄሱም አጠመቃቸው መሥዋዕትንም ቀድሶ ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው እግዚአብሔርንም የምትወድ የከበረች ድንግል ታኦግንስጣ እጅግ ደስ አላት ያንንም ቄስ መንፈሳዊ ሰላምታ ሰጠችውና ከእርሱ ቡራኬ ተቀበለች እርሱም ከእርሷ በረከትን ተቀበለ።
ከዚህም በኋላ ለራስዋ ገዳም ሠራች ብዙዎች ደናግልም ተሰበሰቡ የምንኩስና ልብስንም በመልበስ እንደርሷ መሆንን ወደዱ እርሷም እመ ምኔት ሆነች። ያም ባሕታዊ ቄስ የክርስትና ጥምቀትን ከአጠመቃቸው በኋላ ወደ ንጉሥ አኖሬዎስ ተመልሶ የህንድን ሰዎች እንዳጠመቃቸውና ክብር ይግባውና ወደ ክርስቶስ ሃይማኖት እንደገቡ ነገረው። ንጉሥ አኖሬዎስም እጅግ ደስ አለው የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳትንም ይህን ባሕታዊ ኤጲስቆጶስ አድርጎ እንዲሾምላቸው አዘዘው እርሱም ኤጲስቆጶስነት ሹሞ ከህንድ ሰዎች ላከላቸው እጅግም ደስ አላቸው።
ከዚህም በኋላ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩ ጀመሩ ምሰሶዎችንም በፈለጉ ጊዜ አላገኙም በዚያም አከባቢ ታላቅ የጣዖት ቤት ነበረ በውስጡም ያማሩ ምሰሶዎች አሉ። ድንግሊቱ ታኦግንስጣም ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ብዙ በማልቀስ ለመነች ያን ጊዜም እሊያ ምሰሶዎች ከጣዖት ቤት ፈልሰው ሐናፂዎች ከሚሹት ቦታ በቤተ ክርስቲያን መካከል ተተከሉ አማንያን ሁሉ ክብር ይግባውና ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን አመሰገኑት ጣዖትን ሲያመልኩ የነበሩም ጣዖቶቻቸውን ሰብረው ክብር ይግባውና ወደ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ተመልሰው ገቡ በዚያችም አገር ታላቅ ደስታ ሆነ። | 32 |
| 9 | ዕሌኒ ተራሮቹን ለማስቆፈር ከሦስቱ ተራሮች የቱ እንደሆነ ለመለየት ደመራ አስደምራ ብዙ ዕጣን በመጨመርና በማቃጠል ከኢየሩሳሌም ወጣ ብለው ያሉትን ኮረብቶች አሳያት፡፡ የዕጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ በመውጣት በቀጥታ ተመልሶ መስቀሉ ባለበት ተራራ ላይ በማረፍና በመስገድ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ሥፍራ አመለከታት፡፡ ቅዱስ ያሬድም "ሰገደ ጢስ" ጢሱ ሰገደ ብሎታል፡፡ ከዚያም መስከረም 16 ቀን ቁፋሮው እንዲጀመር አዘዘች፡፡ ሰባት ወር ያህል ከተቆፈረ በኋላ መጋቢት 10 ቀን ሦስት መስቀሎች በአንድነት ተገኙ፡፡ ንግሥት ዕሌኒም የክብር ባለቤት ጌታችን የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ በወደደች ጊዜ "ከራሱ በላይ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ የአይሁድ ንጉሥ ነው" የሚል የተቀረጸበት ጽሑፍ ያለው እንደሆነ የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ ቅዱስ መቃርስ ነገራት፡፡ ከእርሱም ምልለክት ታይ ዘንድ ወደደች፡፡ የሞተ ሰው አምጥታ በሁለቱ መስቀሎች ላይ በተራ ቢታስቀምጠው አልተነሣም፡፡
በመጨረሻ ጽሕፈት ባለው በአንዱ መስቀል ላይ ቢታስቀምጠው ያንጊዜ የሞተው ሰው ተነሣ፡፡ በዚህም የጌታችንን መስቀል ለየችው፡፡ ዕሌኒም ለጌታችን መስቀል ሰገደችለት፡፡ ክርስቲያኖች ሁሉ ሰገዱለት፡፡ በየሀገሩ ያሉ ክርስትያኖች ሁሉ የመስቀሉን መገኘት በሰሙ ጊዜ መብራት አብርተው ደስታቸውን በመግለጥ ለዓለም እንዲታወቅ አደረጉ፡፡ በዚህም ምክንያት ይህ ታላቅ የድኅነት ምልክት የሆነው መስቀል የኢትዮጵያ ቤተክርስትያን ደመራ በመደመር በታላቅ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ታከብረዋለች፡፡
ንግሥት ዕሌኒ መስከረም 16 ቀን 320 ዓ.ም በዕጣን ጢስ ምልክት ቁፋሮ አስጀምራ መጋቢት 10 ቀን አግኝታ በማውጣት ታላቅ ቤተመቅደስ ጎልጎታ ላይ ሠርታ በክብር አስቀመጠችው። ይህ መስቀልም ከዚያ ዕለት ጀምሮ እንደ ፀሐይ እያበራ ድውይ እየፈወሰ አጋንንት እያባረረ ልዩ ልዩ ገቢረ ተአምራት እየሠራ ሙት እያነሳ ዕውር እያበራ ተአምራቱን ቀጠለ፡፡
ይህንንም የሰማው ከኃያላን ነገሥታት መካከል የፋርስ ንጉሥ መስቀሉን ማርኮ ፋርስ ወስዶ አስቀመጠው፡፡ ነገር ግን ንጉሡ ሕርቃል የጌታችንን ቅዱስ መስቀል አስመልሶታል፡፡ በዚህ ጊዜ የኢየሩሳሌም ምእመናን የድሉን ዜና ሰምተው ስለነበር የአንድ ቀን መንገድ ያህል ሄደው በመቀበል ካህናቱ በዝማሬና በቸብቸቦ ወንዱ በሆታ ሴቱ በእልልታ ሆ! እያሉና ችቦ አብርተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ የቤተክርስቲያን አባቶች እንደሚሉት ንጉሡ ሕርቃል ይህንን ታላቅ ድል ለማግኘትና የጌታችንን ቅዱስ መስቀል ከአሕዛብ (ከፋርሶች) እጅ ለማስመለስ የቻለው በዚያን ጊዜ አብያተ ክርስቲያንናት ሁሉ ለአንድ ሳምንት (አንድ ሱባዔ) ባደረጉት ጾም ጸሎት ነው፡፡ ይህንንም ለማስታወስና ጌታችንን ለማመስገን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና የግብጽ ኮፕቲክ ቤተ ክርስቲያን በየዓመቱ የዐቢይ ጾም ከመጀመሩ አስቀድሞ "ጾመ ሕርቃል" ብለው አንድ ሳምንት ይጾማሉ፡፡
የጌታችን መስቀል ለብዙ ጊዜያት ኢየሩሳሌም ከቆየ በኋላ ነገሥታት ይህን መስቀል "እኔ ልውሰድ እኔ ልውሰድ" በማለት ጠብ ፈጠሩ፡፡ በዚህ ጊዜ በወቅቱ ኃያላንና የክርስቲያን መንግሥታት የነበሩ የአንጾኪያ፣የኤፌሶን፣ የአርማንያ፣ የግሪክ፣ የእስክንድርያ፣ የመሳሰሉት የሃይማኖት መሪዎች ጠቡን አበረዱት። ከዚያም አያይዘው በኢየሩሳሌም የሚገኘውን የክርስቶስን መስቀል ከ4ት ከፍለው በዕጣ አድርገው በስምምነት ተካፍለው ከሌሎች ታሪካዊ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር በየሀገራቸው ወስደው በክብር አስቀመጡት። የቀኝ ክንፉ የደረሰው ለአፍሪቃ ስለነበር ከታሪካዊ ንዋየ ቅዱሳት ጋር በግብጽ የሚገኘው የእስክንድርያ ፓትርያርክ ተረክቦ ወስዶ በክብር አስቀመጠው፡፡
ግማደ መስቀሉ ለብዙ ዘመን በእስክንድርያ ሲኖሩ በግብጽ ያሉ እስላሞች እየበዙ ኃይላቸው እየጠነከረ ሲሔድ በእስክንድርያ የሚኖሩ ክርስትያኖች ላይ ሥቃይ ያጸኑባቸው ጀመር፡፡ ክርስቲያኖቹም አንድ ሆነው መክረው ለኢትዮጵያዊው ዐፄ ዳዊት እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ፡- "ንጉሥ ሆይ! በዚህ በግብጽ ያሉ እስላሞች መከራ አጽንተውብናልና ኃይልህን አንሥተህ አስታግስልን" ብለው ጠየቁት። ዳግማዊ ዐፄ ዳዊትም ለመንፈሳዊ ሃይማኖት ቀንተው የክርስቶስ ፍቅር አስገድዷቸው 20,000 ሠራዊት አስከትለው ወደ ግብጽ ዘመቱ በዚህ ጊዜ በግብጽ ያሉ ኃያላን ፈሩ ተሸበሩ። ንጉሡ ዳግማዊ ዳዊትም እንዲህ የሚል መልዕክት ለእስላሞቹ ላከ፡- "በተፈጥሮ ወንድሞቻችሁ ከሆኑት ክርስቲያኖች ካልታረቃችሁ ሀገራችሁን መጥቼ አጠፋለሁ" የሚል ማስጠንቀቂያ ላከ፡፡ የንጉሡ መልዕክትም ለእስላሞቹ እንደደረሳቸው ፈርተው እንደ ጥንቱ በየሃይማታቸው ጸንተው በሰላም እንዲኖሩ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር ታረቁ፡፡ መታረቃቸውን ዐፄ ዳዊት ሰሙ በዚህም ጉዳይ ንጉሡ ደስ አላቸው፡፡ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ።
በግብጽ የሚኖሩ ክርስቲያኖችም ከ12,000 ወቄት ወርቅ ጋር ደስታቸውን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ለዳግማዊ ዳዊት በደብዳቤ አድርገው ላኩላቸው፡፡ ንጉሡም የደስታውን ደብዳቤ ተመልክተው ደስ አላቸው ወርቁን ግን መልሰው በመላክ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ጻፉ፡- "በግብጽ የምትኖሩ የክርስቶስ ተከታዮች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ፣ የላካችሁልኝ 12,000 ወቄት ወርቅ መልሼ ልኬላችኋለሁ፡፡ የእኔ ዓላማ ወርቅ ፍለጋ አይደለም የክርስቶስ ፍቅር አስገድዶኝ በተቻለኝ ችግራችሁን ሁሉ አስወገድኩላችሁ አሁንም የምለምናችሁ በሀገሬ ኢትዮጵያ ረሀብና ቸነፈር ድርቅ ስለወረደብኝ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ቅዱስ መስቀልና የቅዱሳን አጽም ከሌሎች ክቡራን ዕቃዎች ጋር እንድትልኩልኝ ነው" የሚል ነበር፡፡
ቅዱስ መስቀሉ ወደ ሀገራችን ስለመግባቱ ስናነሣ የእነ አቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን ታሪክም የግድ አብሮ መነሣት አለበት፡፡ የአቡነ ፊሊጶስ ዘደብረ ቢዘን እጅግ አስደናቂ ገዳማቸው በኤርትራ ክፍለ ሀገር በሐማሴን አውራጃ ከአሥመራ ከተማ በስተምሥራቅ 25 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፡፡ ጻድቁ የሐይቅ እስጢፋኖስን ባሕር በተአምራት ያቃጠሉት አባት ናቸው፡፡ በንጉሡ በዐፄ ዳዊት ዘመን ሰንበትን አንድ ብቻ ናት እያሉ በአንደኛዋ ሰንበት ሥራ ሲሠሩ ጻድቁ አቡነ ፊሊጶስ ይህን ሰምተው አንዲት ሰንበት የሚሉትን ሁሉ ተቃወሟቸው፡፡ ከግብፅ የመጡት ጳጳስም ቀደም ብሎ ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አሁንም ከአቡነ ፊሊጶስ ጋር ንጉሡ ዐፄ ዳዊት አከራክረዋቸው ጳጳሱ ተረቱ፡፡ ነገር ግን ክፉዎችም በአቡነ ፊሊጶስ ላይ በክፋት ተነሱባቸው፡፡ በአቁማዳ ጠቅልለው ሐይቅ ባሕር ውስጥ ጣሏቸው፡፡ በዚህም ጊዜ እሳቸው የተጣሉበት ባሕር በእሳት ተቃጥሎ ጽድቃቸውን መስክሮላቸዋል፡፡ ዛሬም ድረስ በሐይቅ እስጢፋኖስ ባሕር ዳርቻ ላይ የተቃጠለው ድንጋይ ምልክቱ በግልጽ ይታያል፡፡
በወቅቱ የንጉሡ የዐፄ ዳዊት ሚስት በዋናተኛ አስፈልጋ ከሐይቁ ውስጥ አስወጣቻቸው፡፡ እግራቸውንም አጥባቸው ስትጨርስ የእግራቸውን እጣቢ ጠጣችው፡፡ ወዲያውም አቡነ ፊሊጶስ ‹‹ከማኅፀንሽ ፍሬ ታላቅ ጻድቅ ልጅ ይወጣል›› ብለው ትንቢት ነገሯት፡፡ በትንቢታቸውም መሠረት ታላቁ ጻድቅ ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ተወልዱ፡፡ በወቅቱ በተፈጠረው አለመግባባትና ክፉዎችም በባሕር ውስጥ ስለጣሏቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም አቡነ ፊሊጶስን ከልብ ይቅርታ ጠይቀው ወዲያው ታርቀዋል፡፡ በዘመናቸውም ርኃብ ስለነተሳ ዐፄ ዳዊት ጻድቁን ከገዳማቸው አስጠርተው ‹‹ምን ባደርግ ይሻለኛል?›› ብለው አማክረዋቸዋል፡፡ አቡነ ፊሊጶስም ‹‹የጌታችንን መስቀል ያስመጡ›› ብለው መከሯቸው፡፡ ንጉሡ ዐፄ ዳዊትም ከኢየሩሳሌም፣ ከቍስጥንጥንያና ከእስክንድርያ መንግሥታት ጋር ተጻጽፈው | 23 |
| 10 | ከዚያም መርከቡ ወደብ ከመድረሱ በፊት ነጋዴው ወደ ዕሌኒ ቤት ደረሰና በሩን አንኳኩቶ ሠራተኛይቱን "ዕሌኒን ማነጋገር እፈልጋለሁና ንገሪልኝ" ብሎ ጠየቃት፡፡ እርሷም እያፈረች የተላከችውን ለዕሌኒ ነገረቻት፡፡ ዕሌኒም ተቆጥታ "ከመች ወዲህ ነው እንግዳ የማነጋግረው?" ብላ አሳፈረቻት፡፡ ሠራተኛይቱም ለነጋዴው መልሱን ስትነግረው ነጋዴው እንደማይሆንለት ከተረዳ በኋላ ሌላ ተንኮል አቀደና ለሠራተኛይቱ "ባልና ሚስቱ ብቻ የሚያውቁትን አንድ ነገር ብቻ ብትሰጪኝ ብዙ ገንዘብና ወርቅ እሰጥሻለሁ" ብሎ ወርቅ ሰጣት፡፡ ሠራተኛይቱም "ሁለቱ ብቻ የሚያውቁት የእመቤቴ ሀብል አለ ያንን እመጣልሀለሁ መጀመርያ አንተ በከተማው ውስጥ እየዞርህ ነጋዴዎችን መጡ የብስ ረገጡ እያልክ አስወራ ከዚያም ተመልሰህ እንድትመጣ" ብላ ሰደደችው፡፡ ነጋዴውም እንደተመከረው የነጋዴዎቹን መምጣት በከተማይቱ እንዳወራ የነጋዴዎቹ ቤተሰቦች ነጋዴዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረግ ጀመሩ፡፡ የዕሌኒም ሠራተኛ "እመቤቴ ነጋዴዎች መጡ ተብሎ ይወራልና፡፡ ባለቤትዎ በሰላም ስለመጡ ይዘገጃጁ ገላዎን ይታጠቡ" ብላ መከረቻት፡፡
ዕሌኒም ገላዋን ስትታጠብ ያንገቷን ሐብል ቁጭ ካደረገችበት ቦታ ሠራተኛይቱ አንስታ ለነጋዴው በተቃጠሩበት ዕለት ሰጠችው፡፡ ነጋዴውም ለሠራተኛይቱ የውለታዋን ብዙ ገንዘብና ወርቅ ሰጥቶአት ደስ እያለው ወደ ጓደኞቹ ሄደና ለተርቢኖስ "ሚስትህን ለምጃት ወድጃት መጣሁ" አለው፡፡ ተርቢኖስም "ውሸት ነው ለዚህ ምን ምልክት አለህ?" ብሎ ጠየቀው፡፡ ተንኮለኛውም ነጋዴ ያንን ሐብል አውጥቶ ››ይህ ሀብል የሚስትህ አይደለምን?›› ብሎ ሰጠው፡፡ ተርቢኖስም ደነገጠ የሚናገረውን አጣ፡፡ በውርርዱም መሠረት ሀብቱን ሁሉ አስረከበና ባዶ እጁን ወደቤቱ እያዘነ እየተቆጨ ሔደ፡፡
ባለቤቷን በናፍቆትና በታማኝነት ስትጠብቅ የከረመችው ዕሌኒ በተርቢኖስ ያልተለመደ ሀዘንና ብስጭት ግራ ተጋብታ "ወንድሜ ምን ሆነሀል? ለወትሮው እንኳን ይህን ያህል ዘመን ተለያይተን ቀርቶ ለጥቂት ቀናት ተለያይተን እንኳ ለጥቂት ቀናት ተለያይተን ስንገናኝ እንነፋፈቃለን፡፡ አሁን ግን ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ አዝነህ አይሃለሁ" ብላ ጠየቀችው፡፡ ተርቢኖስም "ብዙ የደከምኩበትና የለፋሁበት ሀብት ንብረቴ እንዳለ ማዕበል አጠፋብኝ እኔ ያላዘንኩ ማን ይዘን?" አላት፡፡ ዕሌኒም ጽኑ አማኝና የተማረች ናትና "እግዚአብሔር ሰጠ እግዚአብሔር ነሣ የእግዚአብሔር ስም የተመሰገነ ይሁን እንዳለ ኢዮብን አስበው፡፡ አንተ እንኳን በሰላም መጣህ እንጂ ሀብቱ ውሎ አድሮ ይመጣል..." እያለች አጽናናችው፡፡ ተርቢኖስም "እንግዲህ በተከበርኩበት ሀገር ተዋርጄ፣ በሰጠሁበት ሀገር ለምኜ ለመኖር አልችልምና ወደሌላ ወደማያውቁኝ ሀገር እሔዳለሁ አንቺ ግን ሁሉ ይወድሻል ያከብርሻል ከወደድሸው ጋር ኑሪ" አላት፡፡ ዕሌኒም "በደስታ ጊዜ አብሬህ እንደሆንኩ በችግርም ጊዜ ልለይህም የእኔንና ያንተን አንድነት ችግር አይፈታውም ከአንተ ተለይቼ ወዴት እቀራለሁ ወደምትሄድበት አብሬህ እሄዳለሁ" ብላ ተነሳች፡፡
ሁለቱም ቤታቸውን ጥለው ሲሄዱ በመንገድ ላይ ተርቢኖስ በልቡናው ይዞት የነበረውን ምሥጢር አወጣው "ዕሌኒ ስወድሽ የጠላሽኝ ሳምንሽ የከዳሽኝ ምን አድርጌሽ ነው?" ብሎ ጠየቃት፡፡ ዕሌኒም "እኔ አንተን አልጠላሁም አልከዳሁምም ይህንን ሐሳብ እንዴት አሰብህ?" ብትለው ከኪሱ አውጥቶ ሀብሉን አሳያትና የሆነውን ሁሉ ነገራት፡፡ ዕሌኒም ያልጠበቀችው ነገር ስለተፈጸመ አዝና የሆነውን እውነተኛ ታሪክ በሙሉ ነገረችው፡፡ ተርቢኖስ ግን አላመናትም፡፡ ከባህር ዳር በደረሱ ጊዜ በቁመቷ ልክ ሣጥን አሠርቶ ዕሌኒን በውስጡ አስገባትና "ብታደርጊውም ባታደርጊውም እንደሥራሽ፣ ሥራሽ ያውጣሽ" ብሎ ወደ ባሕሩ ወረወራት፡፡
ዕሌኒም ያለችበት ሣጥን በፈቃደ እግዚአብሔር እየተንሳፈፈ ከወደብ ደረሰ፡፡ በዚያ ወደብ አካባቢ ምዕራብ ሮምን ያስተዳደር የነበረው ኮስታንዲዮስ (ቁንስጣ) የተባለው ንጉሥ ነበርና ሣጥኑን አይቶ አውጥቶ እንዲከፍቱት ወታደሮችን አዘዘ፡፡ ሣጥኑን አውጥተውም ሲከፍቱት እጅግ የተዋበች ሴት ሆና አገኟት፡፡ ንጉሡም ዕሌኒን ወስዶ ሚስቱ አደረጋት፡፡ ኮስታንዲዮስ (ቁንስጣ) የመክስምያኖስ ቄሳር ሆኖ ምዕራብ ሮምን ያስተዳደር ነበር፡፡ ንግስት ዕሌኒም በ272 ዓ.ም ታላቁ ቆስጠንጢኖስን ወለደችለት። ቆስጠንጢኖስም ገና በወጣትነቱ የአባቱ እንደራሴ ሆኖ እንደሠራ አባቱ ሞተ፡፡ የአባቱ ባለሟሎችና ሕዝቡ ተስማምተው የ18 ዓመቱን ቆስጠንጢኖስን በአባቱ ቦታ ሐምሌ 25 ቀን 316 ዓ.ም በሮም ምዕራብ ክፍል በገላትያ አነገሡት፡፡ በጦር ሜዳዎች ብዙ የጀግንነት ሥራዎች ስለሠራ በሠራዊቱ ዘንድ ይወደድ ነበር፡፡
ሊቀ ነቢያት ሙሴን ወላጅ እናቱ ተራ ሠራተኛ መስላ ገብታ በፈርዖን ቤት ሃይማኖቱን ባሕሉን ታሪኩን በሚገባ እያስተማረች እንዳሳደገችው ሁሉ ንግሥት ዕሌኒም ልጇን ቆስጠንጢኖስን ከልጅነቱ ጀምሮ ስለክርስትና ሃይማኖትና ስለክርስቲያኖች መከራ ታስተምረው ስለነበር በክርስቲያኖች ላይ የነበረው አመለካከት በሮም ከነገሡት ቄሣሮች ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ በተለይም በ312 ዓ.ም ከጠላቱ ከመክስምያኖስ ጋር ለመዋጋት "ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት" ብሎ ለዘመቻ እንደተሰለፈ በራእይ በሰማይ ላይ "በዚህ መስቀል (ምልክት) ጠላትህን ድል ታደርጋለህ" የሚል የመስቀል ቅርጽና የተጻፈ ጽሑፍ ስላየ ለሠራዊቱ የመስቀል ምልክት በመሳሪያቸውና በሰንደቅ ዓላማው ላይ እንዲያደርጉ አዘዘ፡፡ ወዲያው ጦርነት ቢገጥም ጠላቱን ድል ነሥቶ በጠቅላላው የሮም መንግሥት ግዛቶች ሁሉ ገዥ ሆነ፡፡
ታላቁ ቆስጠንጢኖስ የሮም ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ በ300 ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነጻነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ተባለች፡፡ ንግሥት እሌኒም በተፈጠረላት አመች ሁኔታ በመጠቀም የጌታችን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ327 ዓ.ም ወደኢየሩሳሌም ሔደች፡፡ ዕሌኒ ልጅዋ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳነጽ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ337 ዓ.ም ተጠመቀ፡፡ ቅድስት ዕሌኒም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡ ከእርሷም ጋር ብዙ ሠራዊት ነበር፡፡ እንደደረሰችም ስለ ቅዱስ መስቀል መረመረች፡፡ ነገር ግን ቦታውን የሚያስረዳት አላገኘችም፡፡ የአይሁድ ወገን እንቢ ቢሉም በኋላ ግን ባደረገችው ጥረት አረጋዊው ኪራኮስ የጎልጎታን ኮረብታ አመለከታትና "አስቆፍሪው" ብሎ ነገራት።
ኪራኮስም ዘመኑ ከመርዘሙ ጋር ተያይዞ እውነተኛው ተራራ ይህ ነው ብሎ ማሳየት ባለመቻሉ "ከሦስቱ ተራሮች አንዱ ነው" ስላላት አይሁድን ተራሮቹን ይቆፍሩ ዘንድ አዘዘቻቸው፡፡ የጌታችን ቅዱስ መስቀል በሚያደርጋቸው አስደናቂ ተአምራት የተነሣ ሕዝቡ እያመነ በተቸገሩ ጊዜ ክፉዎች አይሁድ ማንም እንዳያገኘው የኢየሩሳሌም ነዋሪ ሁሉ የቤቱን ቆሻሻ የከበረ መስቀል ባለበት ቦታ እንዲጥል አዘው ስለነበር ከሁለት መቶ ሃምሳ ዓመት በላይ ጥራጊ ስለጣሉበት ታላቅ ተራራ ሆነ፡፡ | 24 |
| 11 | አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 17-ጌታችን የተሰቀለበት የከበረ ቅዱስ መስቀል በዓሉ ነው፡- "መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው... ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን፡፡"
"...መልአኩ ቅዱስ ራጉኤል አንዱን ሰው በመብረቅ ቀሰፈውና ቅዱስ ሚካኤል ሄዶ ቅዱስ ራጉኤልን ሲከራከረው አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም ተመለከቱ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል ‹‹የእኔ አገልጋይ ነውና ለምን ገደልከው?›› ሲለው ቅዱስ ራጉኤልም ‹‹ሰንበት ሳይለይ ዝሙትን መሥራት የለመደ ሥራውም ዝሙት ስለሆነ በፈጣሪዬ ታዝዤ ነው የገደልኩት፡፡ ኃጥአንን ሊያጠፋ እንጂ ጻድቃንን ለመቅጣት መብረቅ እንዳይታዘዝ አንተስ ታውቅ የለም እንዴ?›› አለው፡፡ ይህንንም ተባብለው ከሥላሴ ፊት ሰግደው ቅዱስ ሚካኤል የተገባለትን ቃልኪዳን በማሳሰብ ምልጃውን አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም በጎና ክፉ ሥራዋን ባስመዘነ ጊዜ በጎ ሥራዋ ስለበለጠ ቅዱስ ሚካኤል ያችን ነፍስ ታቅፎ ወስዶ ለቅዱስ ገብርኤል ሰጠው፡፡ ሰባቱም ሊቃነ መላእክት እየተቀባበሉ ወስደው ከመስቀል ዘንድ አደረሷት፡፡ ለቅዱስ መስቀልም ካሰገዷት በኋላ አሳልመዋት በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት ወደ ገነት አስገቧት፡፡ አቡነ ሀብተ ማርያምም ይህን በተመለከቱ ጊዜ ቅዱስ ሚካኤልን ‹‹መስቀል ታሳልሟት ዘንድ ያችን ነፍስ ወደ መስቀል ለምን ወሰዳችኋት?›› ብለው ጠየቁት፡፡ መልአኩም ‹‹በትልቅም በትንሽም ነገር ክርስቲያናዊትን ነፍስ የሚቃወም ቢመጣባት ድል የምትነሳበትን በመስቀል ፍርድ ይታይላታልና ስለዚህ ነው፡፡ የሚከራከራት ቢኖር ግን እንዳየኸው ወደ መስቀል ባደረሷት ጊዜ የሚቃወማት ሰይጣን ፈጥኖ ይርቅላታል ዳግመኛም ሊከራከራት አይችልም›› አላቸው፡፡" ገድለ አቡነ ሀብተ ማርያም፡፡
በመጽሐፈ አክሲማሮስ ላይ በዝርዝር እንደተቀመጠው ይኸው ክቡር መልአክ አስቀድሞም ቢሆን ገና ከጥንት ከመነሻው ዲያብሎስ "ፈጣሪ መሆንን" በተመኘ ጊዜ ድል ነስቶት ወደ ጥልቁ የጣለው ጌታችን በሰጠው በቅዱስ መስቀል ኃይል ነው፡፡ በመጀመሪያማ የዲያብሎስ ኃይሉ በርትቶባቸው ሁሉንም ሊቃነ መላእክት ከነሠዊታቸው ከአንድም ሁለት ጊዜ ድል አድርጓቸው ነበር፡፡ በ3ኛው ግን ጌታችን ዲያብሎስንና ሠራተኞቹን ድል የሚያደርጉበትን የብርሃን ቅዱስ መስቀሉን ለእነ ቅዱስ ሚካኤል ሰጣቸውና እነርሱም በመስቀሉ ኃይል ዲያብሎስን ድል አድርገውት ወደ ጥልቁ ጣሉት፡፡ ራእይ 12-7።
እንግዲህ ምን እንላለን! ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል "ክርስቲያናዊትን ነፍስ የሚቃወም ቢመጣባት ድል የምትነሳበትን በመስቀል ፍርድ ይታይላታል የሚከራከራት ቢኖር ግን ወደ መስቀል ባደረሷት ጊዜ የሚቃወማት ሰይጣን ፈጥኖ ይርቅላታል ዳግመኛም ሊከራከራት አይችልም" ብሎ ምስክርነቱን ሰጠን፡፡
እነሆ ራሱ መድኃኔዓለም ክርስቶስም በቃሉ "በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ" አይደል ያለው! ማር 8፡34-36፣ ማቴ 10፡39፡፡ እናም የክርስቶስ ተከታዮችና የመንግሥቱ ወራሾች የመሆናችን ማረጋገጫው መከራ መስቀሉን መሸከማችን አይደለምን!? ዳግመኛም የከበሩ ሐዋርያትን እንስማቸው-እንዲህ ብለው ነግረውናልና፡-
በመስቀሉ ድነናል (ኤፌሶን 1፡7፤ 1ኛ ጴጥ 1፡19)፤ በመስቀሉ ክርስቶስ ወደ ራሱ አቅርቦናል በሰማያት ወደ አባቱ አቅርቦናል (ዮሐ 12፡32፣ ኤፌሶን 2፡13፣ መጽሐፈ ኪዳን)፤ በመስቀሉ ከእግዚአብሔር ጋር ታርቀናል ሰላምን አግኝተናል (ሮሜ. 5፡2፣ 1ቆሮ. 1፡31፣ ዕብ 10፡10)፤ በመስቀሉ ለዘለዓለም ፍጹማን ሆነናል (ዕብ 10፡14)፤ በመስቀሉ የዕዳ ደብዳቤያችን ተደምስሰዋል (ቈላይ 2፡14)፤ በመስቀሉ ላይ በፈሰሰው በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ደም ከበደላችን ሁሉ ታጥበናል (ራዕ 12፡11)፤ በመስቀሉ ቤዛነት እንመካለን (ገላ 6፡14)። ስለዚህም የከበሩ ቅዱሳን አባቶቻችን በጸሎተ ሃይማኖታችን እንደደነገጉልን "መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው... ያመነውም እኛ በመስቀሉ እንድናለን፡፡"
ዳግመኛም ጌታችን ለቅድስት ንግስት ዕሌኒ ቃልኪዳን ሲገባላት እንዲህ ነው አላት፡- "በደሜ የከበረ የመስቀሌን ስም የሚጠራውን እርሱን እምረዋለሁ፡፡ በዕፀ መስቀሌ ቤተክርስቲያን ውስጥ የለመነውን የጸለየውን ሰው መላእክት እንኳን ተድላ ደስታውን ወደማያውቁት ወደ መንግሥተ ሰማያት አዳራሽ ያለወቀሳ ይገባል፡፡ ለከበረ መስቀሌ ከቅርብም ከሩቅም ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ተጉዞ የመጣውን ወደ መቃብሬ ኢየሩሳሌም እንደጓዘ እኔ አደርግለታለሁ፡፡ ይህንንም መጽሐፍ የጻፈ ያጻፈ ወይም ያነበበውን የተረጎመውን ቃሉን በዕዝነ ልቡና የሰማውን የመጽሐፉንም ገበታዎቹን የሳመውን በተጸለየበት ውኃም የተጠመቀውን እኔ በሕይወት መጽሐፍ በዓምደ ወርቅ ላይ በወርቅ ቀለም ስሙን እጽፈዋለሁ›› (ድርሳነ መስቀል-ገጽ 186-188)
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ሙት እያስነሳ ድውይ እየፈወሰ አጋንንት እያወጣ የተለያዩ ገቢረ ተአምራት ሲሰራ ክፉዎች አይሁዶች አይተው ሕዝቡ ክርስቲያን እንዳይሆኑ በመፍራት በ34 ዓ.ም ከኢየሩሳሌም ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ቆፍረው ቀበሩት፡፡ ከዚያም የከተማውን ቆሻሻ ሁሉ ከዚያ መስቀሉ በተቀበረበት ቦታ ላይ እየደፉ ከዘመን ብዛት ቦታው በቆሻሻ ክምር የተነሣ ተራራ ሆነ፡፡ እስራኤልን ከሮም ቅኝ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ከ66-70 ዓ.ም ባደረጉት እንቅስቃሴ ጥጦስ የተባለው የሮም ንጉሠ ነገሥት ዘምቶ ኢየሩሳሌምን በ70 ዓ.ም ደመሰሳት፡፡ ትልቁን የአይሁድ ቤተመቅደስንም አቃጠለው፡፡ እስራኤላውያንም በመላው ዓለም ተበተኑ፡፡
ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በተከታታይ በሮም የነገሡ ነገሥታት /ቄሳሮች/ በክርስቲያኖች ላይ የማያባራ መከራ አድርሰዋል፡፡ ክርስቲያኖች የተቀበረውን መስቀል አስፈልገው ለማውጣት ቀርቶ ሃይማኖታቸውን የማመን ነጻነት ስላልነበራቸው የጌታችን ቅዱስ መስቀል ለ300 ዓመታት ያህል ተቀብሮ የጉድፍ መጣያ ሆኖ ቆየ፡፡ የመስቀሉ የመገኘት ታሪክ የቤተክርስቲያን የመከራ ዘመን አልፎ የዕረፍትና የሰላም ዘመን ሲመጣ ለብዙ ዘመን ተቀብሮ የተረሳውን መስቀል ባለቤቱ መድኃኔዓለም አልረሳምና እርሱ የፈቀዳት ዕለት ስትደርስ በዕሌኒ ንግሥት አማካኝነት ከተቀበረበት እንዲወጣ አደረገ፡፡
ዕሌኒና ተርቢኖስ የሚባሉ ሁለት ደጋግ ክርስቲያኖች ተጋብተው ይኖሩ ነበር፡፡ ተርቢኖስና ዕሌኒ ኑሮአቸው ፍቅርና ሰላም የሰፈነበት በመሆኑ ለብዙ ሰዎች እንደ ምሳሌ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ ተርቢኖስ ነጋዴ ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን ራቅ ወዳለ ሀገር በመርከብ ለንግድ ሄደ፡፡ ዕሌኒም ባለቤቷ ተርቢኖስ ለንግድ ወጥቶ እስኪመለስ ስለባሏ ከመጸለይና ከማሰብ በቀር ከግቢዋ አትወጣም ነበር፡፡
አንድ ጊዜ ተርቢኖስ ለንግድ ሄዶ ብዙ ዓመታትን ቆይቶ ከጓደኞቹ ጋር ወደሀገሩ ሲመለስ ከነጋዴዎች አንዱ "በእግዚአብሔር ፈቃድ ከሽፍታና ከማዕበል ከልዩ ልዩ አደጋ ተርፈን በሰላም ተመልሰን ሚስቶቻችን ሌላ ሳይወዱ ሳይለምዱ እናገኛቸው ይሆን?" ብሎ ጠየቀ፡፡ ተርቢኖስ ግን "እንኳን በሰላም አደረሰን እንጂ ሚስቴን በዚህ አልጠረጥራትም" ብሎ ሲመልስ ሌላው ጓደኛው "ያንተ ሚስት ከማን ትበልጣለችና ነው አሁን ሄጄ ከሚስትህ ጋር ለምዳኝ ወዳኝ ወድጃት ብመጣስ ምን ትቀጣለህ?" አለው፡፡ ተርቢኖስም በሚስቱ ዕሌኒ ተማምኖ "ይህንን ብታደርግ ይህን ያህል ዓመት የለፋሁበት ሀብት ከነትርፉ ውሰድ አንተም ብታደርግ እንዲሁ ሀብትህ ከነትርፉ ለእኔ ይሁን" ተባብለው ተወራረዱ፡፡ | 25 |
| 12 | 没有文字... | 26 |
| 13 | አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 16-ከጌታችን መቃብር ላይ ቤተ ክርስቲያን የታነፀችበትና የተቀደሰችበት ዕለት ነው፡፡ ደግሞም በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ የተሠሩበትና የከበሩበት ሆነ፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ተራ ነገርን እንዳይናገር ድንጋይ ጎርሶ የኖረ አባ አጋቶን ዕረፍቱ መሆኑን ስንክሳሩ በስም ይጠቅሰዋል፡፡
+ በፋርስ ንጉሥ አሜኔሶር እጅ ተማርኮ ወደ ነነዌ አገር የተወሰደ ከንፍታሌም ነገድ የገባኤል ልጅ ጦቢት ዐረፈ፡፡
በጌታችን መቃብር ላይ ቤተ ክርስቲያን ስለመታነፁዋና በኢየሩሳሌም ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ እንደከበሩ፡- ይህም እንዲህ ነው፡- ልጇ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ በ20 ዓመት ቅዱሳን የሆኑ 318 ቅዱሳን ሊቃውንት አባቶችን በኒቅያ ከሰበሰበ በኋላ ቅድስት እናቱ ዕሌኒ እንዲህ አለችው፡- ‹‹ልጄ ሆይ እኔ ወደ ቅድስት አገር ኢየሩሳሌም በመሄድ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ዕፀ መስቀል ፈልጌ አወጣ ዘንድ ለእግዚአብሔር ስዕለት ተስያለሁ፡፡›› ቆስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ደስ አለውና ከብዙ ሠራዊት ጋር ብዙ ገንዘብ ሰጥቶ ላካት፡፡
ቅድስት ዕሌኒም ኢየሩሳሌም በደረሰች ጊዜ ከከበሩ ቦታዎች ተባረከችና አዳኝ ስለሆነ ቅዱስ መስቀል መረመረች፡፡ እርሷም በታላቅ ድካምና ችግር አገኘችው፡፡ ታላቅ ክብርንም አከበረችው፡፡ ከዚህም በኋላ በጎልጎታ፣ በቤተልሔም፣ ጌታችን በተወለደበት ዋሻ፣ በጽርሐ ጽዮን፣ የእመቤታችን ቅዱስ ሥጋዋ በተቀበረበት በጌቴሴማኒ፣ በደብረ ዘይትም በከበሩ ቦታዎች ሁሉ የቤተ መቅደስ መሠዊያ እንዲሠሩ አዘዘች፡፡ ዳግመኛም በዕንቁ፣ በወርቅና በብር እንዲያስጌጧቸው አዘዘች፡፡ በኢየሩሳሌምም ስሙ መቃርስ የሚባል ኤጲስቆጶስ አለ፡፡ እርሱም ንግሥት ዕሌኒን ‹‹እንዲህ አትሥሪ፣ ከጥቂት ዘመናት በኋላ በዚህ አገር ሊነግሡ አሕዛብ ይመጣሉ፡፡ ሁሉን ይማርካሉ፣ ቦታዎችን ሁሉ ያፈርሳሉ፡፡ ዕንቁውን ወርቁን ብሩንም ሁሉ ይወስዳሉና ነገር ግን ጠንካራ የሆነ የማይናወጽና የማይፈርስ ጥሩ ሕንፃ ልታሠሪ ይገባል፣ ከዚህ የሚተርፈውንም ለድኆችና ለችግረኞች ስጪ›› ብሎ መከራት፡፡
ቅድስት ዕሌኒም የአባ መቃርስን ምክር ተቀብላ በከበሩ ቦታዎች ሁሉ አብያተ ክርስቲያናትን እንዲያንጹ አዘዘች፡፡ ከዚህም በኋላ ንግሥት ዕሌኒ ወደ ልጇ በተመለሰች ጊዜ በኢየሩሳሌም ያደረገችን በነገረችው ጊዜ እጅግ ደስ አለው፡፡ እንደገና ሌላ ብዙ ገንዘብና ሕንፀውን ተቆጣጥረው የሚያሠሩ ሹሞችን ላከ፡፡ የሠራተኞችንም ደመወዝ በየቀኑ ማታ ማታ እንዲከፍሉ አዘዘ፡፡
ጻድቅ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ በነገሠ በ30 ዓመቱ የከበሩ ቦታዎች ሕንፃቸው በተፈጸመ ጊዜ ንዋየ ቅዱሳትን፣ ዋጋቸው እጅግ ውድ የሆኑ የከበሩ የግምጃ ልብሶችንም ላከ፡፡ ቀጥሎም ለቁስጥንጥንያ፣ ለአንጾኪያ፣ ለእስክንድርያ ሊቃነ ጳጳሳት ኤጲስቆጶሳትን ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው የታነጹትን አብያተ ክርስቲያናት እንዲያከብሩ መልእክት ላከባቸው፡፡ ሁሉም በኢየሩሳሌም ተሰብስበው እስከ መስከረም 16 ቀን ኖረው በዚህች ቀን ሁሉንም አብያተ ክርስቲያናት መሠዊያቸውንም አከበሯቸው፡፡ የቁርባን ቅዱሴንም ቀድሰው ለምእመናን ሥጋ ወደሙን አቀበሉ፡፡ በዚህችም ዕለት ከቶ እንደ እርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ፡፡ የከበረ ቅዱስ መስቀልንም ተሸክመው በነዚያ በከበሩ ቦታዎች ዞሩ፡፡ በውስጣቸውም ለእግዚአብሔር ሰገዱ፡፡ ቅዱስ መስቀሉንም አከበሩት፡፡ ወደ ሀገሮቻቸውም በሰላም በፍቅር ተመልሰው ገቡ፡፡ ከበዓሉ ረድኤት በረከት ይክፈለን!
+ + + + + + + + + + + + + + +
ጻድቁ ጦቢት፡- ይኽም ጻድቅ ጦቢት በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ዕውነትና ቅን በሆነ ሕግ ጸንቶ የሚኖር ነው፡፡ ከወገኖቹ ጋራ ከመማረኩ በፊት ለችግረኞች ብዙ ምጽዋትን ይሰጥ ነበር፣ ብዙ ጊዜም የበጎቹን ጠጉርና ከእህሉም ዓሥራት በኩራቱን ይዞ ወደ ኢየሩሳሌም ይወጣ ነበር፡፡ ከገንዘቡም ከሦስት አንዱን ለድኆች ይሰጣል፡፡ በዚያን ጊዜም ሕዝቡ ሁሉም ክደው በዓልና ደማሊ ለሚባሉ ጣዖታት ይሰው ነበር፡፡
የቅዱስ ጦቢት ወገኖቹ ነነዌ በተማረኩ ጊዜ ሁሉም የአሕዛብን እህል በሉ እርሱ ግን ሰውነቱን ይጠብቅ ነበር፡፡ የአሕዛብንም መብል እንዳይበላ እግዚአብሔርን ያስበው ነበርና፡፡ በአንዲት ዕለትም በአደባባይ የወደቀ በድን አግኝተው ነገሩት፡፡ እርሱም እህል ሳይቀምስ ተነሥቶ ሔደ፡፡ ፀሐይም እስከሚገባ ወደ አንድ ቤት ውስጥ አስገብቶ አኖረውና ፀሐይ ሲገባ ቆፍሮ ቀበረው፡፡ በዚያችም ሌሊት እንደኃጢአተኛ ሆኖ በእድሞ ሥር ተኝቶ አደረ፡፡ በእድሞውም ላይ ወፎች መኖራቸውን ስላላወቀ ፊቱን ገልጦ ሳለ ወፎች እርኩሳቸውን ዐይኖቹ ላይ ጣሉበትና ዐይኖቹ ተቃጠሉ፡፡ ከዐይኖቹም ጢስ ወጣ፡፡ ታወሩም፡፡ ባለ መድኃኒትም ሊያድነው አልቻለም፡፡ መልአኩን ልኮ ነፍሱን እንዲወስዳት ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ በዚያችም ዕለት የራጉኤል ልጅ የሣራ እና የጦቢት ጸሎታቸው ተሰማላቸው፡ ይህችም ሣራ አስማንድድዮስ የሚባል የሚባል ጋኔን በጭኗ አድሮ ሰባት ባሎቿን በየተራ የገደለባት ናት፡፡
ጦቢትም በገባኤል ዘንድ በአደራ ያስቀመጠውን ገንዘብ ያስመጣለት ዘንድ ልጁን ጦቢያን አሽከር እንዲፈልግ ነገረው፡፡ ጦቢያም ለአባቱ ታዥ ሆኖ አሽከር ሲፈልግም መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል ስሙን አዛርያ ነኝ ብሎ በሰው አምሳል ተገለጠለትና ጦቢት አንድ ላይ ላካቸው፡፡ ጤግሮስ ወንዝ በደረሱ ጊዜ ጦብያ ሊታጠብ ባለ ጊዜ ታላቅ ዓሣ ሊውጠው ሲል መልአኩ ‹‹አትራው ያዘውና ጉበቱንና ልቡን አውጣ›› አለው፡፡ እንዳዘዘውም አደረገ፡፡ ጦቢያም ‹‹አንተ ወንድሜ አዛርያ ሆይ! ይህ የዓሣ ሐሞት፣ ጉበትና ልቡ ምን ይሠራል?›› አለው፡፡ አዛርያ ጠባለው ቅዱሱ ምአክም ‹‹ጉበቱና ልቡ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሱት ጋኔን ያደረበትን ጢሱ ያድነዋል፤ ሐሞቱም ዐይኖቹ የታወሩበትን ሰው ቢኩሉት የታወረ ዐይኖቹ ይበራሉ›› አለው፡፡
ዳግመኛም አዛርያ የራጉኤልን ልጅ ሣራን እንዲያገባት ነገረው፡፡ እንዳይፈራም አጽናናው፡፡ ወደ ራጉኤል ቤት በደረሱም ጊዜ ሣራ ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው፡፡ ጦቢያም ሣራን ወደዳትና እርሷን ይሰጠው ዘንድ አባቷን ጠየቀው፡፡ አበቷም ካሁን በፊት ለሰባት ባሎች ሰጥቷት ሰባቱም እንደሞቱ ቢነግረው ጦቢያም ‹‹የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን›› አለው፡፡ አባቷም ሣራን ሰጠውና ወደ ጫጉላ ቤት ባገቧቸው ጊዜ ጦቢያ አዛርያ የነገረውን አስታወሰ፡፡ የዓሣውን ጉበትና ልብ ከደቀቀ ዕጣን ጋራ ቢያጤሰው ጋኔኑ አስማንድድዮስ ሸሸ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ይዞ ለዘለዓለም አሠረው፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢያ ሚስቱን ሣራን ወስዶ ወደ አባቱ ቤት ተመለሰ፡፡ የአባቱንም ዐይኖች በኳለ ጊዜ እንደ ጭጋግ ሆኖ ከዐይኖቹ ተገፈፈ፡፡እርሱም ዳነና ማየት ቻለ፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤልም ራሱን ገለጠላቸውና ብዙ ምሥጢርን ከነገራቸው በኋላ ዐረገ፡፡
ከዚህም በኋላ ጦቢት ከወገኖቹ ጋራ ታላቅ የደስታ በዓል አደረገ፡፡ ስለ ጌታችንም መከራ ትንቢት ሲናገር ‹‹እርሱ በኋጢአታችን ይገርፈናል፣ ደግሞ እርሱ ይቅር ይለናል፣ ይፈውናልም፡፡ ሁለተኛም መከራህን የሚያስቡ የተመሰገኑ ናቸው፣ እነርሱ ክብርህን ባዩ ጊዜ በአንተ ደስ ይላቸዋልና›› አለ፡፡ ከዚህም በኋላ ጦቢት ብዙ ትንቢቶችን ተናገረ፡፡ ስለ ኢየሩሳሌም መታነጽና የእስራኤል ምርኮኞች ከባቢሎን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሚመለሱ ትንቢትን ተናገረ፡፡ ልጁን ጦቢያንም ‹‹ልጄ ሆይ! ምጽዋት እንደምታድንና እንደምታጸድቅ ተመልከት›› አለው፡፡ ይህንንም ተናገሮ በአልጋው ላይ ሳለ በ158 ዘመኑ በሰላም ዐረፈ፡፡ | 57 |
| 14 | 没有文字... | 93 |
| 15 | 没有文字... | 90 |
| 16 | ያንጊዜም አፈፍ ብላ ከሞት ተነሣች፡፡ አባታችን ከሞት ያስነሷቸው ሰዎች እንዲሁ በጣም ብዙ ናቸው፡፡
27 ዓመት ሙሉ ሆዱን የታመመ አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱም ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ አቡነ ገብረ ማርያም በመምጣት ጉዳዩን ሳይነግራቸው አንድ ቀን ቆየ፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን የመጣበትን ጉዳዩን በጠየቁት ጊዜ ‹‹አባት ሆይ ሃያ ሰባት ዓመት ሙሉ ታመምኩ፣ እህል አልበላም ውኃም አልጠጣም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ሆዱን ይዘው በእጃቸው አሻሹትና ምራቃቸውን ቀቡት፡፡ በዚህም ጊዜ በሆዱ ውስጥ ልዩ ልዩ ዓይነት ድምፆች ተሰሙ፡፡ በውሻ ድምፅ አምሳል፣ በድመት ድምፅ አምሳል፣ በዝንጀሮ ድምፅ አምሳልና በቁራዎቸ ድምፅ አምሳል ጮኸ፡፡ አባታችንም ልጁን ‹‹ልጄ ሆይ እግዚብሔር አድኖሃልና ወደ ቤትህ ተመለስ›› አሉት፡፡ ልጁም ‹‹አባቴ ሆይ ተመልሼ ወደቤቴ አንገባም እስከ ዕለቴ ሞቴ ድረስ አልመለስም ከአንተም አልለይም›› አላቸው፡፡ አባታችንም ‹‹በዚህ መኖር ክፍልህ አይደለምና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለፈወሰህ ወደ ቤትህ ተመለስ›› አሉት፡፡ በደስታም ወደ ቤቱ ሄደና በሌላ ጊዜ ከብዙ ሰዎች ጋር መጥቶ አባታችን ያደረጉለትን ተአምር ለሕዝቡ ሁሉ መሰከረ፡፡
አቡነ ገብረ ማርያም በእንዲህ ዓይነት አገልግሎት በተአምራታቸው ድውያንን እየፈወሱ ሙታንን እያስነሡ በወንጌል ቃል የነፍስን ቁስል እየፈወሱ የጌታችንንም መከራውን እያሰቡ ራሳቸውን ከመከራው ተሳታፊ በመሆን ብዙ ከደከሙ በኋላ በሥጋ ሞት ከማረፋቸው በፊት ቅዱሳን መላእክት ነጥቀው ገነትንና ሲኦልን አሳይተዋቸዋል፡፡ ጌታችንም በመጨረሻ ተገልጦላቸው ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ከፍጹም ድካምና መታከት ከኃዘንም ታርፍ ዘንድ ወደ ፍጹም ደስታና ወደ ዘላለማዊ ዕረፍት ወደ እኔ ና›› አላቸው፡፡ እርሳቸውም ‹‹ጌታዬ ሆይ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ?›› ቢሉት ጌታችም ብዙ አስደናቂ ቃልኪዳኖችን ሰጣቸው፡፡ ‹‹…እንደፈጠርኩህ አግኝቼሃለሁና ክብርህ እንደ መጥምቀ መለኮት ዮሐንስ ይሁንልህ›› አላቸውና በቅዱሳን እጆቹ ዳስሷቸው ቢስማቸው ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለይታለች፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞ | 86 |
| 17 | እመቤታችን ልጇን ይዛ ወደ ግብጽ ከዚያም ወደ አገራችን ኢትዮጵያ ስትሰደድ በእግሯ እየሄደች በሞረት ዋሻ በአቡነ ዜና ማርቆስ ቦታ ግራርያ ከሚባል ቦታ ተቀምጣ እንደነበር የሐምሌው ድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ይናገራል፡፡ በኋላም ተጭነው ከእነ ልጇ በዚህ በአቡነ ገብረ ማርያም ገዳም በሆነ ቦታ ስታልፍ ጌታችን ለቅድስት እናቱ ‹‹ይህች ቦታ ሐንታ ትባላለች፣ በኋለኛው ዘመን በስምሽ የሚጠራ የእኔ ወዳጅና ታዛዥ የሆነ የታላቅ ጻድቅ ቦታ ትሆናለች›› ብሎ ስለነገራት በኋላም ትንቢቱ ደርሶ ጻድቁ ገዳማቸውን በዚሁ ቦታ ስለገደሙት ገዳሙ ‹‹አማን ደብረ ሐንታ›› ይባላል፡፡ ጻድቁ በመንዝና በመርሐ ቤቴ ከ1245-1268 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከ19 በላይ የተላያዩ አብያተ ክርስቲያናትን ተክለዋል፡፡ ጾም ጸሎተኛ ባሕታዊ ከመሆናቸው በተጨማሪ የወንጌል ገበሬ፣ ጻድቅና ደራሲም ናቸው፡፡
አቡነ ገብረ ማርያም በጣም ከሚታወቁበት ድርሰታቸው አንዱ የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት ከታላቁ ሊቅ ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥቶ ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግሎ ይመለሳል፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው ‹‹ማኅሌተ ጽጌ›› ድርሰት የእመቤታችንንና የልጇን የጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በጨማሪም ስደት የማይገባው አምላካችን ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የእመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
አቡነ ገብረ ማርያም አዲስ አፍልሰው በሠሯት ቤተ ክርስያን ውስጥ ልጆቻቸው ተሰበሰቡና ‹‹አባታችን ሆይ የት እናድራለን? ማረፊያን ያዘጋጅልን ዘንድ እግዚብሔርን ለምነው›› አሉት፡፡ አባታችንም ‹‹ይህ ሥራ ለእኔ አይቻለኝምና እናንተ ለምኑት›› አላቸው፡፡ እነርሱም ‹‹አባታችን ሆይ አትበትነን›› ብለው ግድ አሉት፡፡ ልጆቹም ግድ ባሉት ጊዜ አባታችን ተነሥቶ ጸለየ፡፡ ስለዚህም ነገር ሲናገር አባታችን እንዲህ አለ፡- ‹‹ከዚህ ነገር አስቀድሞ በቁርባን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይመጣና ይባርከኝ ነበር፣ እናቱ ድንግል ማርያምም ትባርከኝ ነበር፡፡ ስለዚህ ነገር ግን ጌታችን ተቆጣ፣ እምቢ አለኝ፡፡ ከእኔም ፊቱን መለሰ፡፡ እኔም ብዙ አለቀስኹ የእጁን ቡራኬ አጥቻለሁና፡፡ እናቱ ድንግል ማርያምም ፈጽሜ ሳለቅስ ባየችኝ ጊዜ ‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ታለቅሳለህ?› አለችኝ፡፡ እኔም እመቤቴ ሆይ ጌታዬና አምላኬ ፊቱን ከእኔ መልሷልና ስለዚህ አለቅሳለሁ አልኳት፡፡ እመቤታችን ማርያምም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን በምን ሥራ አሳዘነህ?› አለችው፡፡ ጌታችንም ለድንግል እናቱ ‹እርሱ አሳዝኖኛል፣ የዮሴፍ ልጅ ያዕቆብ ‹ይህን ዓለም የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት ይሆናል› (ያዕ 4፡4) እንዳለ ከእኔ ፍቅር ይልቅ የዓለምን ፍቅር ወዷልና› አላት፡፡› እናቱ እመቤታችንም የተወደደ ልጇን ‹ልጄ ሆይ ወዳጅህ ገብረ ማርያምን አታሳዝነው ይቅር በለው ባጠባሁህ ጡቶቼ አምልሃለሁ› አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ጊዜ ቅድስት እናቱን ‹የላይኛውን ወይም የታችኛውን ይወድ እንደሆነ ጠይቂው› አላት፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤልም ከዚያ ቆሞ ነበርና ለእኔ ‹የላይኛው ያለህ መንግሥተ ሰማያትን ነው፣ የታችኛው ያለህ ይህች ዓለም ናት› አለኝ፡፡ እኔም ያንጊዜ ይህችን ዓለም አልፈልጋትም ነገር ግን ማረፊያ እንዲሰጠን በጸሎቴ የጠየቁት ልጆቼ ከሞቴ በኋላ ተስፋ እንዳይቆርጡ እንዳይበተኑም ብዬ ነው አልኩት፡፡ ጌታችንም ‹‹ገብረ ማርያም ሆይ ለምን ይህንን ታስባለህ? ለልጆችህ እኔ አስብላቸዋለሁና፡፡ ወዳጄ ዳዊት ‹የጻድቃን ልጆች ይባረካሉ፣ ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፣ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል› (መዝ 111፡33) ብሎ እንደተናገረ እኔ ለፍጥረት ወገን ሁሉ አስባለሁ› አለኝ፡፡ ይህንንም ብሎኝ ሰላሙን ሰጥቶኝ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡››
አቡነ ገብረ ማርያም ያደረጓቸው ተአምራት ተነግረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ በብቸኝነት ሳለ በአንዲት አገር የሚኖር ልጁ የሞተበት ሰው የልጁን አስክሬን ወደ አባታችን አምጥቶ በፊታቸው አስቀመጠውና ‹‹አባታችን ሆይ ልጄ እንደሞተ ተስፋዬ ሁሉ ጠፍቷልና አሁን ብትወድ ከሞት አንሣው ባትወድ ግን እዚሁ ቅበረው›› እያለ አለቀሰባቸው፡፡ አባታችንም የሰውየውን ሁኔታውን አይተው ፈጽመው አለቀሱ፡፡ ልቡናቸውም ታወከባቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ይጸልዩ ዘንድ ተነሡና ‹‹…በተቀበረ በ4ኛው ቀን አልዓዘርን ያስነሣኸው አሁንም ይህን ሕፃን አስነሣው…›› ብለው ከጸለዩ በኋላ የልጁን እጅ ይዘው ‹‹በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሥ›› ብለው እፍ አሉበት፡፡ ያንጊዜም ሕፃኑ ከእንቅልፉ እንደሚነቃ አፈፍ ብሎ ተነሣ፡፡ ለአባቱም ‹‹ልጅህን ውሰድ ፈጣሪዬ አስነሣልህ›› ብለው ሰጡት፡፡ ሰውዬውም ከአግራቸው ሥር ሰግዶ የእግራቸውን ትቢያና ሰውነታቸውን ሁሉ ሳመው፡፡ ልጁንም ይዞ ፈጽሞ ደስ እያለው ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
በአንዲት ሀገርም አንድ ልጅ ብቻ ያላት አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ልጁም ወደ አባታችን እየመጣ ‹‹አመንኩሱኝ›› እያለ ሁልጊዜ ይጠይቃቸው ነበር፡፡ አንድ ቀንም እንዲሁ መጣና ‹‹አባት ሆይ ካላመነኮሱኝ ወደሌላ ሰው ዘንድ ሄጄ እመነኩሳለሁ›› አላቸው፡፡ በዚህም ጊዜ አባታችን ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቀው የፍላጎቱን ፈጸሙለትና አመነኮሱት፡፡ ወላጅ እናቱም መጥታ ልጇ የምንኩስናን ልብስ እንደለበሰ ባየች ጊዜ እያለቀሰች ሄደችና ራሷን ወደ ገደል ውስጥ ጨመረች፣ ሞተችም፡፡ ሰዎችም ተሰብስበው አለቀሱላትና አስክሬኗን ተሸክመው ይቀብሯት ዘንድ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወሰዷት፡፡ ሰዎችም ወደ አባታችን መጥተው ‹‹ሴትዮዋ ከመቀበሯ በፊት መጥተው ይዩዋት›› አሏቸው፡፡ አባታችንም ወደ አስክሬኗ አልመለከትም›› አሉ፡፡ እነርሱም በእግዚአብሔር ስም ባማሏቸው ጊዜ አባታችን አስክሬኗ ወዳለበት መጡና አዩዋት፡፡ በማግሥቱም ከገነዟት በኋላ አባታችን ከመዝገበ ጸበላቸው በአፏና በጆሮዎቿ ጸበልን ጨመሩባት፡፡ በፊቷም ‹‹እፍ›› አሉባትና ‹‹በጌታዬ በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ኃይል ተነሺ›› አሏት፡፡ | 48 |
| 18 | ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ፡- በኢየሩሳሌም የሚኖር የቁስጥንጥንያ ተወላጅ የሆነ ስሙ እለእስክንድሮስ የሚባል ሰው ነበር፡፡ እርሱም ለቅዱስ እስጢፋኖስ ውብ የሆነች ቤተ ክርስቲያን ሠርቶለት ሥጋውን አፍልሰው በዚያ በክብር አኖሩት፡፡ ከ5 ዓመት በኋላም እለእስክንድሮስ ዐረፈና ሚስቱ በቅዱስ እስጢፋኖስ አስክሬን ጎን ቀበረችው፡፡ ከሌሎች ከ5 ዓመቶችም በኋላ ሚስቱ የባሏን አስክሬን ወደ ቁስጥንጥንያ አገር ይዛ ልትሄድ አስባ ወደ መቃብሩ ስትሄድ የባሏን አስክሬን የወሰደች መስሏት በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሣጥን ወስዳ እስከ አስቃላን ከተማ ድረስ ተሸከመችውና በመርከብ ተሳፍራ ወደ ቁስጥንጥንያ ሄደች፡፡
የእለእስክንድሮስም ሚስት በመርከብ ስትጓዝ ጣዕም ያለው የመላእክትን ዝማሬ ሰማች፡፡ ልታየውም በተነሣች ጊዜ ሣጥኑ የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋ ያለበት መሆኑን ዐወቀቸ፡፡ ወደ ኢየሩሳሌምም ለመመለስ አልተቻላትም ይልቁንም ይህ እንዲሆን የእግዚአብሔር ፈቃድ መሆኑን ዐውቃ ለዚህ ክብር ስላበቃት አመሰገነች፡፡ ቁስጥንጥንያም እንደደረሰች ለሊቀ ጳጳሱ በእግዚአብሔር ፈቃድ የቅዱስ እስጢፋኖስብ ሥጋ ይዛ እንደመጣች ላከችበት፡፡ ካህናቱና ሕዝቡም ሁሉ በታላቅ ደስታ ወጥተው በክብር ተቀበሏት፡፡ ከሥጋውም ብዙ ተአምራት ተገልጠው ታዩ፡፡ ከዚህም በኋላ ሥጋውን በበቅሎ ጭነው ሲጎትቱ ቁስጣንጢኖስ ከሚባል ቦታ ሲደርሱ የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የያዘችው በቅሎ አልንቀሳቀስ አለች፡፡ እግዚአብሔር የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው በዚህ ቦታ እንዲኖር የፈቀደ መሆኑን ዐወቁ፡፡ ሥጋውን የተጫነው በቅሎም በሰው አንደበት ‹‹የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በዚህ ሊያኖሩ ይገባል›› ብሎ ተናገረ፡፡ ይህንንም ያዩና የሰሙ ሁሉ እጅግ አደነቁ፡፡ የበለዓምን አህያ ያናገረ አምላክ አሁንም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ የተሸከመችውን በቅሎ እንዳናገራት ዐውቀው ደስ አላቸው፡፡ የሀገሪቱም ንጉሥ በቦታው ላይ ውብ ቤተ ክርስቲያን ሠርተውለት ሥጋውን በውስጧ በክብር አኖሩ፡፡ ከሥጋውም ብዙ አስገራሚ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን!
+ + + + + + + + + + + + + + +
አቡነ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታ፡- ጻድቁ አቡነ ገብረ ማርያም ምግባር ሃይማኖታቸው ከቀና፣ ትሩፋት ተጋድሎአቸው ከሰመረ ደጋግ ወላጆቻቸው ከአባታቸው ኒቆዲሞስ እናታቸው አመተ ማርያም በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት ኅዳር 24 ቀን ተወለዱ፡፡ ዕደሜአቸው ለትምህርት ሲደር እነዚህ ደጋግ ወላጆቻቸው ፈሪሃ እግዚአብሔርንና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እያስተማሩ አሳደጓቸው፡፡
አባታችን በልጅነታቸው የወላጆቻቸውን ላሞች እየጠበቁ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ጌታችን በወጣት አምሳል ተገለጠላቸውና ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ለምን እንስሳትን ትጠብቃለህ ደቀ መዝሙሬ ጴጥሮስን ዓሣ ማጥመድን ትተህ ተከተለኝ እንዳልኹት በእንስሳት ፈንታ ሰውን ትጠብቅ ዘንድ …››› አላቸው፡፡ አባታችንም ይህንን በልቡናቸው ሲያወጡ ሲያወርዱ ለ2ኛ ጊዜ ጌታችን በሚያስፈራ ግርማ በእርሻ መካከል ተገለጠላቸው፡፡ ስለዚህም ነገር አባታችን ሲናገሩ ‹‹ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወጣት አምሳል ሁለት ሰዎች ከእኔ ጋር ሳሉ በእርሻ መካከል ወደ እኔ መጣ፤ እነዚያም ከእኔ ጋር የነበሩት ሁለት ሰዎች ባዩት ጊዜ እጅግ ደንግጠው ከግርማው የተነሣ ወዲያና ወዲህ ወደቁ፡፡ በኋላም ተነሥተው ያዩትን መሰከሩ፡፡ ዳግመኛም በሦስተኛ መምጣት ጌታችን እንዲህ አለኝ፡- ‹ለምን ዘገየህ አብርሃምን ለአባቱ ርስት ለይቼ ያወጣሁት እኔ እንደሆንኹ ዐላወቅህምን?› አለኝ፡፡››
ከዚህም በኋላ አባታችን ‹‹እናት አባቱን ያልተወ ሊያገለግለኝ አይችልም›› (ማቴ 10፡37) የሚለውን የጌታችንን አምላካዊ ቃል ሰምተው ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው ወጥተው በመሄድ ቀበት በምትባል ቦታ በዓት ሠርተው በጾም በጸሎት እየታደሉ መኖር ጀመሩ፡፡ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔር ያገለግላቸው ዘንድ አንዱን ነብር አዘዘላቸው፡፡ ሰዎችም ከአባታችን በረከትን ለመቀበል ወደ እርሳቸው ይመጡ ነበርና ከዕለታትም በአንደኛው ቀን አንድ ምእመን ወደ አባታችን በመጣ ጊዜ አባታችንን የሚያገለግላቸው ነብር ሰውየውን ዘሎ ያዘው፡፡ ሰውየውም ‹‹አባታችን አድኑኝ›› እያለ ሲጮኽ አቡነ ገብረ ማርያም ከበዓታቸው ወጥተው ነብሩን በመስቀላቸው ቢባርኩት ኃይሉ ደክሞና ለቃላቸው ታዝዞ ሰውየውን ለቀቀው፡፡ አባታችንም ያንን ወጣት ያየውን ነገር ለማንም እንዳይነግር አዘዙት፡፡ አቡነ ገብረ ማርያም እንደ ሊቀ ነቢያት 40 ቀንና 40 ሌሊት እህል ሳይበሉ ውኃ ሳይጠጡ እየጾሙ ወንጌላትን ያነቡ ነበር፡፡ ከመጾማቸውም ብዛት ሰውነታቸው ፍጹም በደከመና አንደበታቸውም መናገር በተሳናቸው ሰዓት የብርሃን እናቱ እመቤታችን ተገልጻላቸው ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ይህን ያህል ገድል የምትጋደል ሰውነትህንስ የምታስጨንቃት ለምንድነው?›› በማለት አጸናቻቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ረሀብና ጥሙ ጠፋላቸው፡፡
በአንደኛውም ቀን ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል ወደ አባታችን መጣ፡- ‹‹ገብረ ማርያም ሆይ በተክለ ሃይማኖት ወንበር ከተሾመ ከመርሐ ክርስቶስ እጅ የመላእክትን አስኬማ ትቀበል ዘንድ ወደ እርሱ ሂድ›› አላቸው፡፡ አባታችንም ወደ ደብረ ሊባኖስ ከመሄዳቸው በፊት አቡነ መርሐ ክርስቶስ በደብረ ሊባኖስ ሆኖ ይህን በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ዐውቆ ለደቀ መዛሙርቱ ‹‹እነሆ ከፀሐይ ይበልጥ የሚያበሩ ሦስት ከዋክብት ቅዱሳን ይመጣሉ›› አላቸው፡፡ አቡነ መርሐ ክርስቶስም እንደተናገረው እነ አቡነ ገብረ ማርያም ደብረ ሊባኖስ ደረሱ፡፡ አቡነ መርሐ ክርስቶስም የምንኩስናን ልብስ አለበሳቸው፡፡
አቡነ ገብረ ማርያም ከመነኮሱ በኋላ ወደ በዓታቸው ተመልሰው ከበፊቱ ይልቅ በጾም በጸሎት ሲተጉ ጌታቸን አሁንም ተገለጠላቸውና ‹‹በጾም በጸሎት ብቻ ተወስነህ አትቀመጥ ሂድና ወንጌልን አስተምር፣ ድውያንን ፈውስ፣ ሙታንን አንሣ…›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ዳግመኛም በከበረ እስትንፋሱ እፍ አለባቸውና ‹‹መንፈስ ቅዱስን ተቀበል፤ ይቅር ያልካቸው ኃጢአታቸው ይቀርላቸዋል፣ ይቅር ያላልካቸው ኃጢአታቸው አይቀርላቸውም፡፡ የመንግሥተ ሰማያትን መክፈቻዎች እሰጥሃለሁ በምድር ያሰርከው በሰማያት የታሰረ ነው፤ በምድርም የፈታኸው በሰማያት የተፈታ ይሁን›› አላቸው፡፡ ጌታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ‹‹ካህናት በሊቃነ ጳጳሳት አፍ ይሾማሉ አንተ ግን በመንፈስ ቅዱስ አፍ ተሾምህ›› እንዳላቸውና እንደሾማቸው ሁሉ አሁንም አባታችን አቡነ ገብረ ማርያምን እንዲሁ ብሎ ራሱ ሾማቸው፡፡ አባታችንም እንደታዘዙት ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረጉ ድውያንን እየፈወሱ ሙታንን እያስነሡ ወንጌልን ዞረው አስተማሩ፡፡ ቂሐ ወደምትባል ምድር ገብተው ጎሽ ወደምትባለው ሀገርም ደርሰው ጣዖታትን የሚያመልኩትን የሀገሪቱን ሰዎች አገኟቸው፡፡ ሰዎቹም የሚያመልኩትን ትልቅ ዘንዶ በመስቀሉ ባርኮ ከገደለው በኋላ በውስጧ ወንጌልን እያስተማረ ድውያንን እየፈወሰ ሲቆይ ሰዎቹም አባታችንን ‹‹ቅዳሴ ቀድስልን›› አሉት፡፡ አባታችንም ስለዚህ ነገር ጌታችንን በጸሎት በጠየቁት ሰዓት ‹‹ሳትናዘዛቸውና ሳታጠምቃቸው አትቀድስላቸው›› የሚል ቃል ከሰማይ ወደ አባታችን መጣ፡፡ ያንጊዜም ሰዎቹን ሁሉ ሰብስቦ በአብ በወልደ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃቸውና ቅዳሴ ቀድሶ አቆረባቸው፡፡ | 36 |
| 19 | የነበሩ ሁሉ ዳግም ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመልሰዋል፡፡
የሰማዕታት መጀመሪያ የሆነው ቅዱስ እስጢፋኖስ በትምህርቱና በተአምራቱ ብዙዎችን ወደቀናች ሃይማኖት ስለመለሰ ክፉዎች አይሁድ ቀኑበትና የሐሰት ምስክር አዘጋጁበት፡፡ ‹‹በእግዚአብሔርና በሙሴ ላይ የስድብን ቃል ሲናገር ሰምተነዋል›› ብለው በሐሰት ከሰሱትና በሸንጎአቸው አቆሙት፡፡ ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስም ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ጌታችን ያለውን ሁሉንም እየጠቀሰ የሃይማኖትን ነገር አስተማራቸው፡፡ ነቢያትን ስለማሳደዳቸውና ስለመግደላቸው እየወቀሰ ሲናገራቸው በትምህርቱ ተናደው ጆሮአቸውን ይዘው በመጮህ በድንጋይ ወግረው ይገድሉት ዘንድ እየጎተቱ ከከተማው ውጭ አወጡት፡፡ ቅዱሱም በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ከጌታችን የተማረውን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይህን ኃጢአት አትቁጠርባቸው›› እያለ ስለገዳዮቹ ምሕረትን ይለምን ነበር፡፡ ሰማይም ተከፍቶ የእግዚአብሔርን ክብር ተመለከተ፡፡
ቅዱስ ጳውሎስ ይኸውም የቀድሞው ሳውል ቅዱስ እስጢፋኖስን በድንጋይ ሲወግሩት የገዳዮቹን ልብስ ይጠብቅና ድንጋይ ያቀብል ነበር፡፡ ‹‹የሰማዕትህንም የእስጢፋኖስን ደም ባፈሰሱ ጊዜ፥ ራሴ ደግሞ በአጠገባቸው ስቆም ተስማምቼ የገዳዮችን ልብስ እጠብቅ ነበር አልሁ›› ብሎ ራሱ ቅዱስ ጳውሎስ መስክሯል፡፡ ሐዋ 22፡20፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ መምህር የነበረው ምሑረ ኦሪቱ ገማልያልና ልጁ አቢብ በእስጢፋኖስ ትምህርትና የሞቱ ሰዎች የሰጡትን ምስክርነት አይተው ከይሁዲነት ተመልሰው በክርስቶስ አምነው ተጠምቀዋል፡፡ ስለ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡- ‹‹እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር፡፡ የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም፡፡ በዚያን ጊዜ በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ፡፡ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና ‹ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና› የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ፡፡ በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት፡፡›› 6:8-15፡፡
የአይሁድ በቅዱስ እስጢፋኖስ ላይ ያቀረቡት የክሳቸው ምክንያት ጌታችንን ከከሰሱት ክስ ጋር በሁለት ነጥቦች ይመሳሰላል፡፡ የመጀመሪያው ክሳቸው ‹‹የሙሴን ሕግ ሽሯል›› የሚል ነው፡፡ ‹‹የሙሴን ሕግ በመሻር ኦሪት አትጠቅምም አትመግብም አታድንም፤ ሐዲስ ኪዳን (ወንጌል) ግን ትመግባለች ታድናለች›› ብሏል ብለው ከሰሱት፡፡ ሐዋ 6፡13፡፡ ሁለተኛው ክሳቸው ‹‹እግዚአብሔርንም ይሰድባል›› የሚል ነው፡፡ ሐዋ 7፡50፡፡ አይሁድም የቅዱስ እስጢፋኖስን የወንጌል ቃል ንግግሮች በእግዚአብሔር ላይ እንደተሰነዘሩ ስድቦች በመቁጠር ነበር የወነጀሉት፡፡ የኦሪት የካህናት አለቃውም ቅዱስ እስጢፋኖስ ለተከሰሰበት መልስ ይሰጥ ዘንድ ሲጠይቀው እርሱ ግን ለተከሰሰበት መልስ ከመስጠት ይልቅ ከአብርሃም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጽሑፍ በዝርዝር በሚገባ ተረከላቸው፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስም እንዲህ አላቸው፡- ‹‹ከነቢያትስ አባቶቻችሁ ያላሳደዱት ማን ነው? የጻድቁንም መምጣት አስቀድሞ የተናገሩትን ገደሉአቸው፤ በመላእክት ሥርዓት ሕግን ተቀብላችሁ ያልጠበቃችሁት እናንተም አሁን እርሱን አሳልፋችሁ ሰጣችሁት ገደላችሁትም፡፡ ይህንም በሰሙ ጊዜ በልባቸው በጣም ተቈጡ ጥርሳቸውንም አፋጩበት፡፡ መንፈስ ቅዱስንም ተሞልቶ ወደ ሰማይ ትኵር ብሎ ሲመለከት የእግዚአብሔርን ክብር ኢየሱስንም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አየና፡፡ እነሆ ሰማያት ተከፍተው የሰው ልጅም በእግዚአብሔር ቀኝ ቆሞ አያለሁ አለ፡፡ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፣ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤ ከከተማም ወደ ውጭ አውጥተው ወገሩት፡፡ ምስክሮችም ልብሳቸውን ሳውል በሚሉት በአንድ ጎበዝ እግር አጠገብ አኖሩ፡፡ እስጢፋኖስም ‹ጌታ ኢየሱስ ሆይ ነፍሴን ተቀበል› ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር፡፡ ተንበርክኮም ‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው› ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ፡፡ ይህንም ብሎ አንቀላፋ፡፡ ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር፡፡ 7:52-60፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ስለንጽሕናው ስለድንግልናው፣ ስለሰማዕትነቱ ስለተጋድሎው እና ስለስብከቱ ስለተአምራቱ ሦስቱ አክሊላት ተቀዳጅቷል፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስ አምላኩን ክርስቶስን በብዙ ነገር መስሏል፡፡ በመጨረሻዋ የመሞቻው ሰዓት ላይ እንኳን ሆኖ አምላኩን አብነት አድርጎ ተገኝቷል፡፡ ጌታችን ‹‹ነፍሴን ተቀበላት›› እንዳለ ሁሉ ቅዱስ እስጢፋኖስም ‹‹አቤቱ ጌታ ሆይ ነፍሴን ተቀበላት›› ብሏል፡፡ ጌታችን ‹‹አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው›› እንዳለ እስጢፋኖስም ‹‹ጌታ ሆይ ይህን ኃጥአት አትቁጠርባቸው የሚያደርጉትን አያውቁምና›› በማለት ለገዳዩቹ ምሕረትን ለምኗል፡፡ በጌታችን ጸሎት እነ ፊያታዊ ዘየማንን ጨምሮ እልፍ ነፍሳት ወደ ንስሐ ተመልሰው ገነት መንግስተ ሰማያትን እንደወረሱ ሁሉ በቅዱስ እስጢፋኖስም ጸሎት ብዙ ነፍሳት ድነው ገነት መንግስተ ሰማያትን ወርሰዋል፡፡ የጌታችን ቅዱስ መስቀል እልፍ ሙታንን ያስነሣ ድውያንን ይፈውስ እንደነበር ሁሉ የቅዱስ እስጢፋኖስም ዐፅም ሙታንን ያስነሣ ድውያንን ይፈውስ ነበር፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተወገረበት ድንጋይ ሰባት አብያተ ክርስቲያናት ታንጸውበታል፡፡
የቅዱስ እስጢፋኖስ ልደቱና ዕረፍቱ ጥር 1 ቀን ነው፡፡ መእመናንም ሥጋውን ወስደው በክብር ቀበሩት፡፡ ጥቅምት 17 የተሾመበት ነው፡፡ መስከረም 15 ቀን ፍልሰተ ሥጋው ነው፡፡ የቅዱስ እስጢፋኖስ ቅዱስ ዐፅሙ ሙትን ያስነሣ ድውይን ይፈውስ ነበርና አይሁድ በቅናት ተነሥተው እንደ ጌታችን ቅዱስ መስቀል የቅዱስ እስጢፋኖስን ዐፅም አርቀው በመቆፈር ቀብረው በላዩም ቆሻሻ በመጣል ለ300 ዓመት ያህል ተቀብሮ ኖሮ በመጨረሻ በፈቃደ እግዚአብሔር እንደ ቅዱስ መስቀሉ ተቆፍሮ በመውጣት መስከረም 15 ቀን ቅዱስ ዐፅሙ ወጥቶ በክብር በስሙ በታነጸው ቤተ ክርስቲያን በክብር ተቀምጧል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡- ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ ካረፈ ከ300 ዓመት በላይ በሆነ ጊዜ ጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሲነገሥና ሃይማኖትን በመላው ዓለም አቀና፡፡ ተዘግተው የነበሩ ገዳማትና አብያተ ክርስያናት ተከፈቱ፡፡ በዚህም ወቅት የቅዱስ እስጢፋኖስ ሥጋው በሚገኝበት በኢየሩሳሌም አካባቢ ሉክያኖስ ለሚባል ሰው ቅዱስ እስጢፋኖስ በራእይ ተገለጠለትና ‹‹እኔ እስጢፋኖስ ነኝ፣ ሥጋዬ በዚህ ቦታ ተቀብሯል›› በማለት ሥጋውን ያወጡ ዘንድ አዘዘው፡፡ ሉክያኖስም ለኢየሩሳሌሙ ኤጰስ ቆጶስ ሄዶ ነገረውና ወደ ቦታው ሄደው ሲቆፍሩ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነና ሳጥኑ ተገኘ፡፡ ከሳጥኑ እጅግ ደስ የሚል በዓዛ ወጣ፡፡ በዚያ ቦታም ቅዱሳን መላእክት ሲያመሰግኑ ተሰሙ፡፡ ኤጲስ ቆጶሳቱና ካህናቱም የቅዱስ እስጢፋኖስን ሥጋ በክብር በታላቅ ዝማሬ ወስደው አስቀመጡት፡፡ | 36 |
| 20 | አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን!
መስከረም 15-የማኅሌተ ጽጌን ድርሰት ከአባ ጽጌ ድንግል ጋር በአንድነት እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው የደረሱት የአቡነ ገብረ ማርያም ዕረፍታቸው ነው፡፡ እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ይህንን ድርሰታቸውን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰውታል፡፡ ስለ ጽኑ የተጋድሎ ሕይወታቸውም 40 ቀንና 40 ሌሊት ጾመው እጅግ ቢደክሙ የብርሃን እናቱ እመቤታችን ተገልጻላቸው ‹‹ወዳጄ ገብረ ማርያም ሆይ ይህን ያህል ገድል የምትጋደል ሰውነትህንስ የምትታስጨንቃት ለምንድነው?›› በማለት አጽንታ የደከመ ሰውነታቸውን አድሳላቸዋለች፡፡
+ ዳግመኛም በዚኽች ዕለት ዐፅሙን የተሸከመችው በቅሎ በሰው አንደበት በመናገር ቤተክርስያኑ የሚሠራበትን ቦታ ያመለከተችለት ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ፍልሰተ ዐፅሙ ነው፡፡
+ እግራቸው በውኃው ሳይርስ በእግራቸው በባሕር ላይ ሲራመዱ የነበሩት አቡነ ጴጥሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡
አቡነ ጴጥሮስ፡- ጠራው ከሚባል አገር የተኙት እኚህ ጻድቅ ከእናታቸው ማኅፀን ጀምሮ ለእግዚአብሔር በስዕለት የተሰጡ ነበሩ፡፡ ባደጉም ጊዜ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ ጾም ጸሎትን ከማብዛታቸው የተነሣ ሥጋቸው አልቆ ከቆዳቸው ጋር እስከመጣበቅ ደረሰ፡፡ ጻድቁ በዱር ያገኙትን ጥቂት ሣር ይመገባሉ እንጂ እንደ ሰው ምግብ አይበሉም ነበር፡፡ ምግባቸው እግዚአብሔርን ማመስገን ነውና፡፡ አቡነ ጴጥሮስ ልብሳቸው የብረት ልብስ ነበር፡፡ ጻድቁ በምድር ሳሉ የመላእክትን ኑሮ ነበር የሚኖሩት፡፡ አሎን በሚባል ባሕር ላይ በእግራቸው ሲራመዱ እንኳን እግራቸው በውኃው አይርስም ነበር፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ተጋድሎ እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ኖረው በሰላም ዐርፈዋል፡፡ የጻድቁ ረድኤት በረታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + + + + + + + + + + + + + +
ዳግመኛም በዚህች ዕለት ዐፅሙን የተሸከመችው በቅሎ በሰው አንደበት በመናገር ቤተክርስያኑ የሚሠራበትን ቦታ ያመለከተችለት ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ፍልሰተ ዐፅሙ ነው፡፡ (ዝርዝር ታሪኩ ከዕረፍቱ ዕለት ከጥር አንድ ላይ ተካቷል፡፡)
ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ፡- እስጢፋኖስ ማለት ‹‹መደብ›› ማለት ሲሆን በግሪክ ቋንቋ ‹‹አክሊል›› ማለት ነው፡፡ በግብሩ የቀን ሃሩር የሌሊት ቁር የማይለውጠው፣ መብራት ማለት ነው፡፡ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ስምዖን እናቱ ሐና ይባላሉ፡፡ እነርሱም እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከነቢያትና ከጻድቃን ወገን ናቸው፡፡ በመጀመሪያ ሁለት ወንድ ልጆችን ወለዱ፡፡ አንዱ ይሁዳ ሲባል ሁለተኛውም ቅዱስ እስጢፋኖስ (አስተፓኖስ) ነው፡፡ እስጢፋኖስ የተወለደው ጥር 1 ቀን በእስራኤል ሃገር ውስጥ ልዩ ስሟ ሐኖስ በተባለች ቦት ነው፡፡ የተወለደውም በስለት ነው፡፡ እርሱም ከመጥምቁ ዮሐንስ እግር ሥር በመሆን ተምሯል፡፡ በኋላም ወደ ቅዱሳን ሐዋርያት በመሄድ ይላላካቸውና ያገለግላቸው ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያን ከተሾሙት ከ7ቱ ዲያቆናት አንዱ ሲሆን የዲያቆናት አለቃ እርሱ ነው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ ወንጌልን በማስተማሩና ብዙዎችን ክርስቶስን ወደማመን ስለመለሳቸው ክፉዎች አይሁድ በጠላልትነት ተነስተውበት ጥር 1 ቀን በ34 ዓ.ም ከጌታችን ቀጥሎ ከምእመናን ወገን የመከራውን ገፈት ስለተቀበለ (በድንጋይ ተወግሮ በሰማዕትነት ስላረፈ) ‹‹ቀዳሜ ሰማዕት›› ተሰኘ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ‹‹ሊቀ ዲያቆናት ቅዱስ እስጢፋኖስ›› እየተባለ ይጠራል፡፡ ይኸውም የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያት በሰባቱ ዲያቆናት ላይ አለቃ አድርገው በሾሙት ጊዜ የተሰጠው ስያሜ ነው፡፡
የመጀመሪያ ክርስቲያኖች የአማኞች ቊጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በሄደ ጊዜ የማኅበራዊው ኑሮ አስተዳደር ማለትም የምግብንና የመሳሰሉትን ቁሳቁሶች (ገንዘብም ጭምሮ) በትክክልና በእኩልነት የማከፋፈሉ ሥራ በሐዋርያት ዘንድ አስቸጋሪ ሆኖ ተገኘ፡፡ እነርሱም ደግሞ ዋና ተግባር አድርገው በትጋት ለመያዝ የፈለጉት ማስተማርን ነበር፡፡ ስለዚህም አማኞችን ሁሉ ሰብስበው ከመካከላቸው በመልካም ጠባያቸው የተመሰገኑ በመንፈስ ቅዱስና በጥበብ የተሞሉ ሰባት ሰዎችን እንዲመርጡ አሳስቧቸው፡፡ አማኞችንም ነገሩ አስደስቷቸው ሰባት ሰዎችን መረጡ፡፡ እነርሱም፡- ቅዱስ እስጢፋኖስ (ዕረፍቱ ጥር 1)፣ ቅዱስ ጵሮኮሮስ (ሰኔ 8)፣ ቅዱስ ጢሞና (ሚያዝያ 16)፣ ቅዱስ ፊልጶስ (ጥቅምት 14)፣ ቅዱስ ጰርሜና (መስከረም 1)፣ ቅዱስ ኒቃሮና (3 ጊዜ ሞቶ የተነሣ)፣ ቅዱስ ኒቆላዎስ (ሚያዝያ 15) ናቸው፡፡ ሐዋ 6፡5፡፡
እነዚህንም ቅዱሳን በከበሩ ሐዋርያት ፊት ባቆሟአቸው ጊዜ ጸልየው እጃቸውን በራሳቸው ላይ ጭነው ሾሟቸው፡፡ በከበሩ ሐዋርያት ጫንቃ ላይ ተጭኖ የነበረው ከባድ ሸክም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶችና ወላጆቻቸው የሞቱባቸውን ደሀ አደጎች በመርዳት ችግሮቻቸውን አቃለሉላቸው፡፡ በከበሩ ሐዋርያት ከተመረጡት ሰባቱ ዲያቆናት መካከል ሊቀ ዲያቆናት ተደረጎ የተመረጠው ቅዱስ እስጢፋኖስ ሲሆን ሌሎቹም ዲያቆናት እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ወንጌልን በማስተማርና የመጀመሪያ ክርስቲያኖች በማስተዳደር በጽናት ተጋድለዋል፡፡
እነዚህም ሰባቱ ዲያቆናት ከአባቶቻቸው ከከበሩ ሐዋርያት አይተው የእነርሱንም መንፈስ ተቀብለው ያልተማሩ አህዛብን ልቡናቸውን ለመስበርና የእግዚአብሔርን ኃይልነት ተረድተው እንዲገነዘቡ በማሰብ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በዋነኛነት ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ ፊት ያደረጋቸው ተአምራት እጅግ ድንቅ ናቸው፡፡ ቅዱስ እስጢፋኖስ በአህዛብ መካከል ቆሞ ሲያስተምር ከቆየ በኋላ አንድ አንደበቱ ዲዳ የሆነ ሰው አጠገቡ ቢመጣ በጆሮው የሕይወት እስትንፋስ እፍ ቢልበት መስማት የማይችለው መስማት ቻለ፡፡ በዚህም ጣኦት አምላኪው ናኦስ እና ተከታዮቹ ሁሉ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ተመለሱ፡፡ ጣኦት አምላኪው ናኦስ በድርጊቱ በጣም ከመናደዱ የተነሣ በአጠገቡ የቆመውን በሬ ጠንቋዩ ናኦስ በጆሮው እፍ ብሎ ቢተነፍስበት በሬው በምትሃት ለሁለት ተሰንጥቆ በመሞቱ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተመለሱት በናኦስ ምትሃታዊ ድርጊት በመሳባቸው እንደገና ወደ ናኦስ ተመለሱ፡፡
ቅዱስ እስጢፋኖስም በዚህ ጊዜ የአህዛብ ልቡና ወላዋይ እንዳይሆንና እንዳይጠፉም በማሰብ ናኦስ እፍ ብሎ ለሁለት ሰንጥቆ የገደለውን በሬ መልሶ በሕይወት እንዲያስነሣው ናኦስን ጠየቀው፡፡ ነገር ግን ናኦስ ያንን ማድረግ አልቻለም፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ እስጢፋኖስ ‹‹ናኦስ ዳግመኛ ሕይወት ዘርቶ ማስነሣት ካልቻለ እኔ ነገሩ ሀሰተኛ ነው ማለት ነው፣ እኔ ግን በእግዚአብሔር ኃይልና ድንቅ ሥራ ይህን ለሁለት ተሰንጥቆ የሞተውን በሬ ዳግመኛ ሕይወት ዘርቶ እንዲነሣ አደርገዋለሁ›› በማለት ወደ እግዚአብሔር ከጸለየ በኋላ በሬውን አስነሣው፡፡ ይህንንም ተአምር አድርጎ በማስተማር ልቦናቸው ወላውሎ ወደ ናኦስ የተመለሱትን አህዛብ ገንዘቡ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ኃይልነት እንዲያምኑ አድርጓል፡፡ ናኦስ በአልሸነፍ ባይነትና በአጋንንት ረዳትነት ራሱን ወደ ላይ እንዲንሣፈፍ አድርጎ በአየር ላይ ቢወጣ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ተአምር በማሳየት በትዕግስት ጠብቆ በአጋንንት ረዳትነት ወደ ላይ የተነሳውን ናኦስ በትምዕርተ መስቀል ቢያማትብበት ይዘውት የነበሩት አጋንንት ሁሉ ለቀውት ሲበተኑ ናኦስም ምድር ደርሶ ተንኮታኩቶ በመውደቁ በጣኦት አምላኪነት | 67 |
