ch
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

前往频道在 Telegram

EEP Communication

显示更多

📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览

频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 544 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 357,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 176

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 544 名订阅者。

根据 01 七月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 22,过去 24 小时变化为 4,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.24%。内容发布后 24 小时内通常能获得 16.50% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 921 次浏览,首日通常累积 2 563 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
EEP Communication

凭借高频更新(最新数据采集于 02 七月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

15 544
订阅者
+424 小时
-357
+2230
帖子存档
photo content
+2

ከአቢአዲ - አድዋ በተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የፍተሻ ሥራ ተጀመረ ……....//.......... ከአቢአዲ- አድዋ በተዘረጋው ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የፍተሻ ሥራ መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የጥገና እና ቴክኒካል ድጋፍ ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ መንግስቴ እንደገለፁት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን የፍተሻ ሥራ በፍጥነት በማጠናቀቅ ጥገናውን ለማስጀመር እየተሰራ ነው። የፍተሻ ሥራው እየተከናወነ የሚገኘው የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩን የጉዳት መጠን ለማወቅ እንደሆነ የገለፁት አቶ ተስፋዬ ጥገናውን እስከ ቀጣይ ሳምንት ለማጠናቀቅ ዕቅድ እንደተያዘም ነው የጠቆሙት። የአቢአዲ - አድዋ ባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር የጥገና ሥራ ሲጠናቀቅ ለአክሱም እና አድዋ እንዲሁም በአቅራቢያቸው ለሚገኙ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ለመስጠት እንደሚያስችል ገልፀዋል። ሥራ አስኪያጁ እንደገለፁት የነዳጅና የመለዋወጫ ዕቃዎች እጥረት፣ የፀጥታ ስጋቶች፣ የተሽከርካሪዎች ጥገና በአካባቢዎቹ ያለመኖር፣ የመልክዐ - ምድሩ ተራራማነትና የአየር ሁኔታው ሞቃታማ መሆን በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ለመጠገን ፈታኝ ሆኖ ነበር። ይሁን እንጂ ይላሉ አቶ ተስፋዬ የወልቃይት - ሰቲት ሁመራ አስተዳደርና ማህበረሰብ እንዲሁም የሀገር መከላከያ ሠራዊት የጥገና ሠራተኞች የፀጥታ ስጋት እንዳይገጥማቸው ከማድረግ ጀምሮ ነዳጅ በሚፈለገው መጠን በማቅረብ የጥገና ሥራው በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ በማድረጋቸው ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል። የተቋሙ የጥገና ሠራተኞች የጥገና ሥራውን በዕቅድ ከተያዘው ጊዜ ባነሰ ለማጠናቀቅ ያደረጉት ርብርብ የሚደነቅ መሆኑን የጠቆሙት አቶ ተስፋዬ ለከፈሉት ዋጋ ምስጋና እንደሚቸራቸው ተናግረዋል። እየተካሄደ ባለው የጥገና ሥራ ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተውጣጡ የተቋሙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን እንዲሁም የራስ ኃይል ሠራተኞች እየተሳተፉ ይገኛሉ። “ከካርቦን ልቀት የፀዳ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ታህሳስ 06 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

photo content

photo content
+3

የወልዲያ ዶሮ ግብር ማከፋፋያ ጣቢያ ግንባታ ሥራ 65 በመቶ ተጠናቀቀ ……///…… የወልዲያ ዶሮ ግብር ባለ 230/33/15 የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ አጠቃላይ ሥራ 65 በመቶ መጠናቀቁን በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኮንስትራክሽን የራስ ኃይል መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የግንባታው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሥራ አስኪያጅ አብርሃም አባተ እንዳስታወቁት የዶሮ ግብር 230/33/15 ኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፋያ ጣቢያ አንድ ባለ 230 ኪሎ ቮልት ገቢ መስመር ሲኖረው፤ አምስት ባለ 33 ኪሎ ቮልት እና አምስት ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመር አለው፡፡ ጣቢያው አንድ 63 ሜጋ ቮልት አምፒር የሆነ 230/33/15 ትራንስፎርመር ያለው መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡ የኤሌክትሮ መካኒካል አጠቃላይ ሥራው 34 በመቶ መድረሱን፣ የመቆጣጠሪያ ክፍሉ እና የስዊችያርድ ሥራዎች በአብዛኛው መጠናቀቃቸውንም ገልፀዋል፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያው የሲቪል ሥራዎች ሥራ አስኪያጅ ቴዎድሮስ ከፈለኝ በበኩላቸው የሲቪል ሥራው 94 በመቶ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ የዲዛይን ለውጥ ተደርጎበት ለላሊበላ 66 ኪሊ ቮልት እንዲሰጥ ታስቦ የነበረው የዶር ግብር ማከፋፈያ ጣቢያ አሁን የአላማጣ ማከፋፈያ ጣቢያ ሥራ በመጀመሩ ምክንያት ወደነበረበት እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል፡፡ እንደ ሥራ አስኪያጆቹ ገለፃ ከነባሩ የወልዲያ 66 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል እያገኙ የነበሩት ሃራ፣ ጭፍራ፣ ሮቢት፣ ጎብዬ እና አካባቢው ከዶሮ ግብር የማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ማግኘት እንዲችሉ እየተሰራ ነው፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያው ከተንቀሳቃሽነት ጣቢያነት ወደ ቋሚነት በመቀየሩ በአካባቢው በተደጋጋሚ የሚነሳውን የኃይል ጥያቄ መልስ መስጠት እንደሚያስችል ጠቁመዋል፡፡ የዶሮ ግብር ማከፋፈያ ጣቢያ ከተጀመረ ስምንት ወራት የሆነው ሲሆን በቀጣዮቹ ሁለት ወራት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ኢንጅነር አብርሃም ገልፀዋል፡፡ የግንባታው አፈፃፀም 65 በመቶ የደረሰ ሲሆን 80 ለሚሆኑ የአካባቢው ወጣቶች ጊዜያዊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል፡፡ “ከካርቦን ልቀት የፀዳ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ታህሳስ 04 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+2

በተጀመረውን የፀረ - ሙስና ንቅናቄ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች ሊሳተፉ ይገባል ..........///……..... በሀገር አቀፍ ደረጃ በተጀመረውን የፀረ - ሙስና ንቅናቄ ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች ሊሳተፉ እንደሚገባ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የፀረ-ሙስና እና ሥነ-ምግባር ጽ/ቤት ሥራ አስፈፃሚ አቶ መርጋ ተረፈ አሳሰቡ፡፡ ዓለም አቀፍ የፀረ- ሙስና ቀንን የጊቤ 1ኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እና የምስራቅ ሪጅን የኃይል ማስተላለፊያ እና ማከፋፈያ ጣቢያ ኦፕሬሽን ሠራተኞችሲያከብሩ ሥራ አስፈፃሚው ባቀረቡት ጽሑፍ እንደገለፁት ሙስና በሀገሪቱ እያሳደረ ያለውን ሁሉንአቀፍ ኪሳራ አጥብቆ መታገል ይገባል። ሥራ አስፈፃሚው በጽሑፋቸው ስለሙስና ትርጉምና መገለጫዎቹ፣ የሙስና እና ብልሹ አሰራር መንስኤዎች፣ የሙስና ዓለም አቀፍዊ ሁኔታና በኢትዮጵያ ላይ ስላሳደረው ተፅዕኖ፣ ስለስነ-ምግባርና የፀረ-ሙስና ትግሉ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መረጃ አቅርበዋል፡፡ የሙስና ወንጀል ድንጋጌዎች፣ በሥልጣን ያለ አግባብ ስለመገልገል፣ የማይገባ ጥቅም ሰለመቀበል፣ የመንግሥት ሥራን በማያመች አኳኋን ስለመምራት፣ በሥልጣን ስለመነገድ፣ ያለአግባብ ጉዳይን ስለማጓተት፣ ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ስለማግኘት፣ በሌለው ሥልጣን ስለመጠቀም በሚሉ ጉዳዮች ላይ የሥራ ክፍሉ ባለሙያዎች ለመርሀግብሩ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የፀረ-ሙስና ቀን ሲከበር አሁን የተጀመረውን ንቅናቄ ወደ ህብረተሰቡ በትክክል ማውረድ በሚያስችል አግባብ መሆን እንዳለበትም አመልክተዋል። ሠራተኛው ለተጀመረው የፀረ-ሙስና ትግል የበኩሉን አስተዋጽኦ እንዲያበረክትም ነው መልዕክት ያስተላለፉት። የዘንድሮው የፀረ-ሙስና ቀን በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ እንዲሁም በኢትዮጵያ ለ18ኛ ጊዜ "ሙስናን መታገል በተግባር" በሚል መሪ ቃል ይከበራል። “ከካርቦን ልቀት የፀዳ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ታህሳስ 03 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+3

በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተፈጸመ ስርቆት ተቋሙ የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ አጋጥሞታል ………///……… በ2014 ዓ.ም ብቻ ከኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ላይ በተሰረቀ 756 ቶን ብረት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ እንዳጋጠመው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ፡፡ በዘርፉ የምስራቅ ሪጅን ዳይሬክተር አቶ ጋሻው እንድሪያስ እንደገለጹት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሚያስተዳድራቸው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ ተደጋጋሚ ስርቆት እየተፈፀመ ነው፡፡ በ2014 ዓ.ም ብቻ 24 የሚደርሱ ከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊ የብረት ማማዎች ሙሉ ለሙሉ ተቆርጠው የወደቁ ሲሆን የብረትና የኮንዳክተር ዘረፋ እንደተፈጸመባቸው እና በቁጥር 30 ሺ 257 የሚሆኑ የተለያዩ የታወር ብረቶች ደግሞ በቁማቸው ካሉ ማማዎች ተፈታተው መወሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡ ከወደቁትና በቁማቸው ከተዘረፉት ማማዎች 756 ቶን ብረት መሰረቁን የተናገሩት ዳይሬክተሩ ይህም በገንዘብ ሲሰላ 72 ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ብር የሚገመት ኪሳራ መድረሱንና የተሰረቀውን ብረት መልሶ ለመተካት ተቋሙ 23 ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ብር ማወጣቱን አስታውቀዋል፡፡ በ2014 ዓ.ም በስርቆት፣ በመልሶ ግንባታና ከአገልግሎት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የባከነውን 2 ሺ 396 ሜጋ ዋት ሰዓት ኃይል ጨምሮ ተቋሙ ከመቶ ሚሊዮን ብር ያላነሰ ኪሳራ እንዳጋጠመው ተናግረዋል፡፡ የተቋሙ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በበኩላቸው ስርቆትን ለመከላከል ከህብረተሰብ ተወካዮች፣ ከጸጥታ እና ከፍትህ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶች መካሄዳቸውንና ውጤት እያስገኘ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች በህብረተሰቡና በባለድርሻ አካላት ትብብር ወንጀሉን ለመከላከል ቢሞከርም በሌሎች አካባቢዎች አሁንም ችግሩ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡ ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ተከሰው በሚቀርቡ ወንጀለኞች ላይ የፍትህ አካላት የሚጥሉት ቅጣት አስተማሪ አለመሆኑና ግብዓት ለማግኘት ሲሉ ስርቆቱን የሚደግፉና የሚረከቡ የብረታብረት ፋብሪካዎችና ባለሀብቶች እንቅስቃሴ ሊፈተሸ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ታህሳስ 03 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+6

ሁመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ከሁለት ዓመት በኋላ ኤሌክትሪክ አግኝቷል ……….////……… ከሁለት ዓመት በላይ ኤሌክትሪክ ተቋርጦበት የቆየው ሁመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝቷል፡፡ አካባቢው ከሽሬ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ያገኝ የነበረ በመሆኑ አስቸጋሪ መልክዐምድርና የአየር ሁኔታ ያለው የሁመራ - ሽሬ 230 ኪሎ ሜትር ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ሲጠገን ቆይቷል። ይሁንና ጥገናው ተጠናቆ ከሽሬ ማከፋፈያ ጣቢያ ለማገናኘት ሲሞከር ከተከዜ ወደ ሽሬ የሚመጣው መስመር ላይ ችግሮች በማጋጠሙ ኃይል ሽሬ ከተማ ለማድረስ አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጥሮ እንደነበር መግለፃችን ይታወሳል። አስቸጋሪ የነበረው የተከዜ መስመር ጥገና ከተጠናቀቀ በኋላ ሁመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ማድረስ ተችሏል። በመሆኑም ከሁመራ ማከፋፈያ ጣቢያ ኃይል ያገኙ የነበሩ ከተሞች በሙሉ ኃይል የሚያገኙበት ሁኔታ ተፈጥሯል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ እና የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን በተከናወነው ሥራ የተገኘው ውጤት እንዳስደሰታቸው ገልፀዋል። በቀጣይም ኃይል ያላገኙ አካባቢዎችን መልሶ ለማገናኘት በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ታህሳስ 02 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content

photo content
+8

ተቋሙ የዓለም የኤችአይቪ/ኤድስ እና የፀረ-ፆታዊ ጥቃት ቀንን አከበረ …….//…….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሠራተኞችና ሥራ አመራሮች ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ/ኤዲስ እና   የፀረ- ፆታዊ ጥቃት  ቀንን በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አክብረዋል፡፡ በመርሃ-ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት በተቋሙ የሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ እንደገለፁት በሴቶችና ህፃናት ላይ እየተፈፀሙ ያሉ ጥቃቶችንና ትንኮሳዎችን ያለወንዶች ተሳትፎ መቀነስም ሆነ መቆጣጠር አይቻልም፡፡ ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል እንዲቻል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የድርሻውን እንዲወጣም ነው ዳይሬክተሯ  የጠየቁት፡፡ የተቋሙን  ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ በበኩላቸው ተቋሙ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡ ሴቶች ለሀገር ብልፅግና እና ዕድገት የማይተካ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉትን ኋላቀር አመለካከቶች መቅረፍ እንደሚገባም አሳስበዋል። በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ፆታዊ ጥቃቶችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ዓለም አቀፋዊ ቀውሶች መሆናቸውን ያነሱት አቶ ሙላት ሁሉም የተቋሙ ሠራተኞች እና የሥራ መሪዎች ለሴቶች ተገቢውን ክብር በመስጠትና ከጥቃት በመከላከል የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። የኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ የተቋሙ ሠራተኞች ተገቢውን ድጋፍና አገልግሎት እንዲያገኙ የተቋሙ ሥራ አመራር ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ነው ያረጋገጡት፡፡ የተቋሙ የህግ መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መርክነህ ይገዙ ስለ ሴቶች መብትና ፆታዊ ጥቃት፣ ስለ ሰብዓዊ መብት ምንነት፣ ስለሚያስከትለው ውጤት፣ ስለ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳትና መንስኤዎቹ እንዲሁም ስለ ህግ ማዕቀፎቹ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ጽሁፍ አቅርበዋል። በተያያዘ ዜና የተቋሙ የኤችአይቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ቢሮ አስተባባሪ አቶ ዓለምሰገድ ባሲሊዮስ የኤች.አይ. ቪ/ ኤድስ ሥርጭትና የመቆጣጠር ሒደቱን አስመልክቶ ለመርሃ ግብሩ ተሳታፊዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በተቋሙ የኃይል ማመንጫ፣ ማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎች እንዲሁም ፕሮጀክቶች ላይ ለሚገኙ ሠራተኞች በኤችአይቪ/ ኤድስ እና አባላዘር በሽታዎች ላይ ያተኮሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዓለም አቀፍ የኤችአይቪ/ኤድስ ቀን በሀገራችን "ፍትሐዊና ተደራሽ የኤችአይቪ/ኤድስ አገልግሎት" በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት አስተባባሪው መሪ ቃሉ አገልግሎቱን ተደራሽ የማያደርጉ አለመመጣጠኖች መወገድ እንዳለባቸው የሚያሳይ ነው ብለዋል። የፀረ-ፆታዊ ቀን በዓለም ለ31ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ለ17ኛ ጊዜ"ሴትን አከብራለሁ፤ ጥቃቷንም እከላከላለሁ" በሚል መሪ ቃል ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ እየተከበረ ይገኛል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+3

የከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይልን በመጠቀም ሀገርን መለወጥ ይቻላል ………///………. የከርሰ ምድር እንፋሎት ኃይልን በመጠቀም ሀገርን መለወጥ እንደሚቻል የከርሰምድር እንፋሎት የቁፋሮ ኢንጂነር ሰለሞን ከበደ ገለፁ፡፡ ኢንጂነር ሰለሞን እንደገለፁት የከርሰምድር እንፋሎትን ከኤሌክትሪክ ኃይል ባለፈ ለጨርቃጨርቅ፣ ለኮንስትራክሽን፣ ለለስላሳና ለአልኮል መጠጥ ኢንዲስትሪዎች፣ ለመዝናኛ፣ ለፈውስና ለሌሎችም ዘርፎች መጠቀም ይቻላል፡፡ አብዛኛው ኢንዱስትሪ የእንፋሎት ኃይልን የሚፈልግ ቢሆንም እንደሀገር ያለውን እምቅ ሀብት ለማልማት ብዙ ሥራ መስራት እንደሚፈልግ ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በከርሰምድር እንፋሎት ሀብት በተፈጥሮ የታደለች ብትሆንም ከሀብቷ የተጠቀመችው ግን እጅግ ጥቂቱን ብቻ ነው ብለዋል፡፡ ዘርፉ ከፍተኛ ፋይናንስ፣ የሰለጠነ የሰው ኃይልና ቴክኖሎጂ የሚጠይቅ በመሆኑ ኢትዮጵያ እንደሀገር ያላትን ሀብት በማልማት የዜጎቿን ህይወት ለማሻሻል የጀመረቻቸው ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንደ ኢንጂነር ሰሎሞን ገለፃ በአሉቶ ላንጋኖ ፕሮጀክት የሀገር ውስጥ ባለሙያዎች ከውጭ ሀገራት ባለሙያዎች ጋር በመሆን ልምድ እንዲቀስሙ የተጀመረው ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ የትምህርትና ምርምር ተቋማትም የዘርፉን ዕድሎች በአግባቡ በማሳየት የመሪነት ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ባለሙያው ጠይቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም

ሽረ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አገኘች ……….////……… በትግራይ ክልል የምትገኘው ሽረ ከተማ ከረጅም ጊዜ በኋላ ዳግም የኤሌክትሪክ ኃይል አግኝታለች፡፡ ከሁመራ እስከ ሽሬ ያለው 230 ኪሎ ሜትር ባለ 230 ኪሎ ቮልት መስመር ላይ በሶስቱም ጥምር መስመሮች ያጋጠሙት 92 ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ቢጠገኑም ከተከዜ የሚመጣው መስመር ላይ ችግሮች በማጋጠማቸው ኃይል ሽሬ ከተማ ማድረስ አልተቻለም ነበር፡፡ ይሁንና አስቸጋሪ የነበረውን ከተከዜ እስከ ሽሬ ያለው የ160 ኪሎ ሜትር የጥገና ሥራ በስኬት በመጠናቀቁ ሽሬ ማከፋፈያ ጣቢያ ማምሻውን የተሳካ የኤሌክትሪክ ኃይል ሙከራ ተደርጓል፡፡ ይህም ከሁለት ዓመት በላይ ኃይል ተቋርጦባቸው ለቆዩት ወልቃይት፣ ሁመራና አካባቢያቸው ኃይል ለማድረስ የተጀመረውን ጥረት እንደሚያፋጥነው ይታመናል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ጥገና ባጠናቀቀቻቸውና ኃይል ዝግጁ ባደረገባቸው አካባቢዎች የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥርጭት መስመሮች እንደተጠናቀቁ ህብረተሰቡ ኤሌክትሪክ እንደሚያገኝ ይጠበቃል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ ባስተላለፉት መልዕክት በጥገና ሥራው ላይ የተቋሙ ሰራተኞች ያሳዩትን ጽናትና ቁርጠኝነት አድንቀው የኤሌክትሪክ መሰረተልማቶችን ለመጠገን የተከናወነው ሥራ መንግስት ለሰላም ስምምነቱ መተግበር ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ህዳር 29 ቀን 2015 ዓ.ም

photo content
+5