ch
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

前往频道在 Telegram

EEP Communication

显示更多

📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览

频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 572 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 384,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 165

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 572 名订阅者。

根据 23 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 0,过去 24 小时变化为 -2,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 25.89%。内容发布后 24 小时内通常能获得 15.48% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 026 次浏览,首日通常累积 2 408 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 9

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
EEP Communication

凭借高频更新(最新数据采集于 24 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

15 572
订阅者
-224 小时
-37
无数据30
帖子存档
የህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ እንደጠናቀቅ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለፁ ….///…. የኢትዮጵያ የአንድነት ተምሳሌት የሆነውና ብዙ ውጣ ውረድ የታየበት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት በቅርቡ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በቅርቡ አገልግሎት እንደሚጀመር የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) አስታወቁ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ በሚቀጥሉት 6 ወራት የግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በማጠናቀቅ የፕሮጀክቱን ፍፃሜ ለኢትዮጵያ ህዝብ እናበስራለን ብለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአፍሪካ ኩራት ከመሆኑም ባሻገር መቻልን ያሳየንበት፣ በውስጣችን ያለውን ውድቀት ያረምንበት እና 74 ቢሊዮን ሜትር ኩዩብ ውሃ ይዘን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል የምናመርትበት ሀብት ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገለፃ የህዳሴ ግድብ አፍሪካውያን የፋይናንስና ዲፕሎማሲያዊ ጫና ቢደረግባቸው እንኳ የራሳቸውን ሀብት በገዛ ዜጎቻቸው አልምተው መቀየር እንደሚችሉ በተግባር የሚያሳይ ነው፡፡ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ ከታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ጋር ስላለው ዲፕሎማሲ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ማምረት እንጂ ማንኛውንም ሀገር የመጉዳት ፍላጎት የላትም ብለዋል፡፡ ስለሆነም ግድቡ ግብፅን ጨምሮ በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት ምንም ዓይነት ጉዳት እንደማያመጣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ ከግብፅ ጋር በተደረጉ ተደጋጋሚ ውይይቶች የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት በአስዋን ግድብ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ እንደሌለው ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር ለውይይት፣ ለድርድር እና  በትብብር አብሮ ለመስራት ሁል ጊዜም በሯ ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

በአዋሽ 7 ኪሎ አካባቢ የተፈፀመው ስርቆት ለምስራቅ ከተሞች ኃይል መቋረጥ ምክንያት ሆኗል .......///...... በአፋር ክልል አዋሽ 7 ኪሎ ከተማ አቅራቢያ በ3 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ  የብረት ምሰሶዎች ላይ ሥርቆት መፈፀሙን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 2 ሪጅን አስታወቀ። የሪጅኑ ዳይሬክተር አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት ከለሊቱ 6:05 አካባቢ ከቆቃ ወደ ሁርሶ በተዘረጋው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ በተፈፀመው ሥርቆት ድሬዳዋ፣ ሐረር እና ጅግጅጋን ጨምሮ በምስራቅ ኢትዮጵያ በሚገኙ ከተሞች ኃይል ተቋርጧል። የምስራቅ ረጅን 1 ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ በበኩላቸው ኃይል ለተቋረጠባቸው አካባቢዎች በሌላ አማራጭ ኃይል እንዲያገኙ ለማድረግ እየተሰራ ነው። በተቋሙ የትራንስሚሽን ቢዝነስ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አንዱዓለም ሲዓ ሥርቆቱ በከተማ አቅራቢያ መፈፀሙ የችግሩን አሳሳቢነት የሚያሳይ በመሆኑ የፀጥታና የመስተዳድር አካላት ድርጊቱን ለመከላከል ትኩረት እንዲሰጡት ጠይቀዋል። ኃይል የተቋረጠባቸው አካባቢዎች በተቻለ ፍጥነት በሌላ አማራጭ ኃይል እንዲያገኙ እየተደረገ ቢሆንም በጊዜያዊነት በቂ ኃይል ላይኖር ስለሚችል ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚዎች አጠቃቀማቸውን እንዲያስተካክሉ አሳስበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 11 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

ማዕከሉ በጣቢያው ያሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ ኃሳብ ለማቅረብ እየሰራ ነው .......///....... በጊቤ ሦስት የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የተቋቋመው የጥናት፣ ምርምርና ሥልጠና ማዕከል በጣቢያው ያሉ ችግሮችን በመለየት የመፍትሔ ሀሳቦችን ለማቅረብ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። በጣቢያው የኮሙዩኒኬሽን ኢንጅነርና የማዕከሉ አስተባባሪ አቶ ይስሃቅ ወልደየስ እንዳስታወቁት የማመንጫ ጣቢያው የሚያጋጥሙትን ችግሮች በጥናት ላይ ተመስርቶ ለመፍታት ከሦስት ዓመታት በፊት ማዕከሉን አቋቁሟል። ማዕከሉ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ጥናትና ምርምሮችን በመስራት የጣቢያውን የኦፕሬሽንና የጥገና ሥራዎችን ለማቀለጠፍ የሚያግዙ ዘመናዊ አሰራሮችን ለመተግበር ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ማዕከሉ ለጣቢያው የኮሙዩኒኬሽን ሥርዓትና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዘርፎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን  ተናግረዋል። የወረቀት ሥራዎችን በዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት ለመተካት በጣቢያው ኔትወርክ የሚሰራ "ጊቤ ፕላስ" የተሰኘ መተግበሪያ በልጽጎ ወደ ሥራ መግባቱን ገልጸዋል። እንደ አቶ ይስሐቅ ገለፃ መተግበሪያው የእያንዳንዱን የማሽን ታሪክ፣ የንብረት አያያዝ፣ የሰው ኃይሉንና የሚጠቀምባቸውን መሣሪያዎች ኮምፒውተራይዝድ በማድረግ በቀላሉ ታሪካቸውን ለማወቅ የሚያስችል ነው። መተግበሪያው በወረቀት የነበሩ አሰራሮችን በማዘመን ችግሮችን የቀረፈ ቢሆንም አገልግሎቱን ከዚህ የተሻለ ለማድረግ መተግበሪያውን ለማሻሻል ዕቅድ ተይዞ በመስራት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል። ማዕከሉ በተለይም በጣቢያው የኮሙዩኒኬሽንና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ የአሰራር ሥርዓቶች ላይ የሚያስፈልጉ ሥልጠናዎችን በመለየት እንደሚሰጥም ጠቁመዋል። የጥናት፣ ምርምርና ሥልጠና ማዕከላት  በማመንጫ ጣቢያዎች ያሉ ችግሮችን በመቅረፍ በኩል ሚናቸው ከፍተኛ መሆኑን የተናገሩት አቶ ይስሃቅ ይኼን ከግምት በማስገባት በተቋሙ መዋቅር ተፈጥሮለት በሰው ኃይልና በግብዓት የሚደራጅበት መንገድ መታሰብ አለበት ብለዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3

ሪጅኑ የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና እየሰጠ ነው ………//………... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማዕከላዊ ሪጅን 3 ሥር ለሚገኙ የማከፋፈያ ጣቢያ እና ማስተላለፊያ መስመር የጥገና እና ኦፕሬሽን ባለሙያዎች የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ። የሳፕ ትግበራ ኮሚቴ አባልና አሰልጣኝ የሆኑት አቶ ወልዳይ ገ/ትንሳኤ እንደገለጹት ሥልጠናው በሪጅኑ የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮች የአሰራር ሥርዓት ለማዘመን፣ ጠንካራ የሀብት ቁጥጥር ሥርዓት ለመዘርጋት፣ ወጭ ለመቀነስ እና ሥራን ለማቀላጠፍ አስተዋፅኦው ከፍ ያለ ነው። የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የማስተላለፊያና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ንብረቶች የሚመዘግብ ከመሆኑም ባሻገር የጥገና ሥራዎችን በዕቅድ ላይ ተመስርቶ ለማከናወን ፋይዳው የጎላ መሆኑን አስረድተዋል። እንደ አቶ ወልዳይ ገለፃ የሞጁሉ መተግበር የጥገና መረጃዎችን በመሰብሰብና በመተንተን የተሻለ ውሳኔ አሰጣጥ እና ትንበያ እንዲኖር ከማስቻሉም በተጨማሪ  የጥገና ሂደቱን  ሙሉ ለሙሉ በማዘመንና በማቀላጠፍ በኩል ጉልህ ሚና ይጫወታል። ሥልጠናው የማከፋፈያ ጣቢያዎች እና ማስተላለፊያ መስመሮችን ንብረቶች አያያዝና አጠቃቀም ለመከታተልና አስተማማኝነታቸውን ለማረጋገጥ ያስችላል፡፡ በሪጅኑ መደበኛ የፍተሻ እና የጥገና ሥራዎችን  ለመከታተልና የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማዘመን እንዲሁም  የኃይል መቆራረጥን ለመቀነስ እንደሚረዳ አቶ ወልዳይ አብራርተዋል። ሥልጠናው በጥገና አሰራር ሥርዓት፣ በመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፣ አስተዳደር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች የሚያተኩር ሲሆን በሪጀኑ በሚተዳደሩ 20 ማከፋፋያ ጣቢያዎች ውስጥ  ለሚገኙ  ለጥገና  እና ለኦፕሬሽን ባለሙያዎች በአንድ  ወር ቆይታዎች በአራት ዙር እንደሚሰጥ አመልክተዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

የተቋሙ ሴት ሠራተኞች ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አከበሩ …………///……….. የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ሴት ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች በዓለም ለ114ኛ በሀገር አቀፍ ደግሞ ለ49ኛ ጊዜ « ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ» በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አክብረዋል፡፡ በመርሀግብሩ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙላት ገዛኸኝ እንደተናገሩት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ሲከበር ሴቶች በሁሉም ዘርፍ አቅማቸውን በማጎልበት ውጤታማ እንዲሆኑ የተጀመረውን ጥረት በማስቀጠል ሊሆን ይገባል፡፡ የሥራ ቦታዎችን  ከጾታ መድልዖ የጸዱ፣ አካታች እና አሳታፊ እንዲሆኑ በሚደረገው ጥረትም የተቋሙ ሴት ሠራተኞችና የሥራ መሪዎች ሚናቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። በተቋሙ  የሴቶች እና ማህበራዊ መመሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ በበኩላቸው ሴቶች  የሚያገኙትን ዕድል ሳያባክኑ አሟጠው  በአግባቡ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ ተቋሙ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በርካታ የድጋፍ እርምጃዎችን ያመቻቻ ቢሆንም ዕድሉን ከመጠቀም አንጻር ውስንነቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ስለሆነም ተቋሙ ለሴት ሠራተኞች ያስቀመጣቸውን የድጋፍ እርምጃዎች በአግባቡ በመጠቀም የሚጠበቅባቸውን ተቋማዊና ሀገራዊ አስተዋጽኦ ማበርከት አንዳለባቸውም ገልፀዋል፡፡ በበዓሉ ላይ በጡት እና በማህጸን በር ጫፍ ካንሰር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና  እና  ሥነ ግጥም ቀርቧል፡፡ በተመሳሳይ በዓሉ በተቋሙ በአዳማ 1 እና 2፣ በቆቃ፣ በአዋሽ 2 እና 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እንዲሁም በደሴና በማዕከላዊ ሪጅን 2 በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+9

photo content

በምዕራብ ሪጅን ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎች ኃይል አግኝተዋል ....///... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ምዕራብ ሪጅን ኃይል ተቋርጦባቸው የነበሩ አካባቢዎች ኃይል ማግኘታቸውን የሪጅኑ የኦፕሬሽንና ጥገና ኃላፊ ገለጹ። ኃላፊው አቶ ታሪኩ ደጉ እንደገለጹት የጊዳ አያና ባለ132 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያን ከነቀምቴ ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር በሚያገናኝው ትራንስፎርመር ላይ በደረሰ ችግር የተነሳ ከየካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ወረዳዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር ኃይል ተቋርጦ ቆይቷል። ኃይል የተቋረጠባቸው ጊዳ፣ ገሊላ፣ ኤበቱ፣ ሀሮ ሊሙ፣ ኪረሙና ሀምሩ ወረዳዎች እንዲሁም ጉትን ከተማ አስተዳደር ናቸው። ችግሩ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ የተጎዳውን የትራንስፎርመር ክፍል በመቀየር ወደ ሥራ ለማስገባት ጥረት ሲደረግ መቆየቱን የገለጹት አቶ ታሪኩ በዛሬው ዕለት የአራት ወረዳዎችንና አንድ አተማ አስተዳደር ኃይል እንዲያገኙ መደረጋቸውን ተናግረዋል። ቀሪ ኃይል ያላገኙ አካባቢዎች በአጭር ጊዜ ኃይል እንዲያገኙ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በአደጋው በተከሰተው የኃይል መቋረጥ በትዕግስት ለጠበቁ ነዋሪዎችም ምስጋና አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 8 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+4

ተቋማዊ አሰራሮች ሕግን የተከተሉ እንዲሆን መስራት ይገባል ….....///…….. በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ እየተተገበሩ ያሉ አሰራሮች ሕጋዊ ሂደትን ተከትለው መከናወናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ በተቋሙ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ኮምፕሊያንስ ሥራ አስፈጻሚ አሳሰቡ። ሥራ አስፈጻሚው አቶ ዱጉማ ነዳ ከተቋሙ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ውይይቱ ዓላማ በተቋሙ እየተከናወኑ ያሉ ተቋማዊ የለውጥ ሥራዎች ከመደገፍ ባለፈ የተቋሙን የፋይናንስ አቅም በእጅጉ እየተፈታተኑ ባሉት የታወር ስርቆትና የካሳ ክፍያ ጉዳዮች ዙሪያ መምሪያው በምን አግባብ እየሰራ ነው የሚለውን አይቶ ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ያለመ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡ ለውይይት መነሻ እንዲሆን አምስት አባላት ያሉት የጥናት ኮሚቴ በማቋቋም በመምሪያው እና በስሩ ባሉ ክፍሎች እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችና የመፍትሔ ሀሳቦች ለማመላከት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት መሰራቱን ተናግረዋል። መምሪያው ቅንጅታዊ አሰራርንና ሙያዊ ብቃትን በማሳደግና አሰራሮች ሕግን የተከተሉ መሆናቸውን በመቆጣጠር ተቋሙን በመጠበቅና በመከላከል በኩል ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ ተቋሙ በሀገር ደረጃ የሚሰራቸውን ትልልቅ ፕሮጀክቶች ከብክነት በፀዳ መልኩ በውጤታማነት ለመፈፀም የመምሪያው ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ በሕግ አገልግሎት መምሪያና በሥሩ በሚገኙ የሥራ ክፍሎችን የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመለየት እና የመፍትሔ ሀሳቦችን  ለማመላከት የተሰራው የዳሰሳ ጥናትም ለውይይቱ ተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡ በመምሪያው ውስጥ ከሠራተኛ አቅም ግንባታ፣ ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ ከመፈጸም አቅምና ከግብዓት አቅርቦት ጋር ያሉ ችግሮች እንዲሁም ከሌሎች የተቋሙ የሥራ ክፍሎች ጋር ያለውን ግንኙነት በተመለከተ በጥናቱ ተዳሷል። የውይይቱ ተሳታፊዎችም ጥናቱ ራሳቸውን እንዲያዩና በሥራ ክፍሎች መካከል እርስ በእርስ የመማማር ዕድልን እንደሚፈጥር ተናግረዋል። መምሪያው ተቋሙን የሚመጥን ሥራ ለመስራት ያስችለው ዘንድ ሊፈቱና ሊታዩ ይገባሉ ያሏቸውን ሀሳቦችና አስተያየቶች አንስተው መሰል ጥናቶችና ወይይቶች በየጊዜው የሚደረጉበት አሠራር እንዲዘረጋም ጠይቀዋል፡፡ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ዳይሬክተር ወ/ሮ መስከረም በቀለ በበኩላቸው ከተሳታፊዎች የተነሱ እንዲሁም በጥናቱ የተለዩ ችግሮችን እንደ ግብዓት በመውሰድ በተቋማዊ ለውጡ የሕግ ክፍል ሊኖረው የሚችለውን ሚና እንዲወጣ ይደረጋል ብለዋል፡፡ ከታወር ስርቆትና ከካሳ ክፍያ ጋር ያሉ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች፣ ከፍትህና አስተዳደር አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራም አብራርተዋል፡፡ የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ በፍርድ ቤት ባሉ ጉዳዮች ዙሪያም መረጃና ማስረጃ በማጠናከር የተቋሙን ጥቅም ለማስጠበቅና ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጠቆሙት ዳይሬክተሯ ተቋማዊ አሰራሮችን በመፈተሸ በሕግ እንዲደገፉ ብሎም ግልፅነትና ተጠያቂነት እንዲሰፍን መምሪያው በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 6 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9

ጣቢያው የጥገና ሥራዎቹን ቢያሳካም ኃይል የማምረት አፈፃፀሙ ከዕቅዱ ያነሰ ነበር …….///……. የአዳማ 2 የንፋስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ በ2017 ግማሽ በጀት ዓመት በቅድመ መከላከል፣ በትንበያ እና የገጠሙ ችግሮችን በማስተካከል ከዕቅዱ በላይ ቢያከናውንም ኃይል በማምረት ረገድ የያዘውን ዕቅድ ማሳካት እንዳልቻለ አስታወቀ፡፡ የጣቢያ ኃላፊው አቶ መለሰ ሲሎ እንደገለፁት ጣቢያው በግማሽ ዓመቱ በቅድመ መከላከል፣ በትንበያ እና የገጠሙ ችግሮችን በማስተካከል 141 ጥገናዎች ለማከናወን አቅዶ 150 ጥገናዎችን በማከናወን የ106 ነጥብ 21 በመቶ አፈፃፀም አስመዝግቧል፡፡ በንፋስ ተርባይኖችና በስዊችያርድ 152 የፍተሻ ሥራዎችን ለማከናወን የያዘውን ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ማሳካቱን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ ይሁንና በመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ለማምረት ካቀደው 249 ጊጋ ዋት ሰዓት ኢነርጂ ውስጥ ማምረት የቻለው 184 ነጥብ 26 ጊጋ ዋት ሠዓት ብቻ መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡ እንደ ኃላፊው ገለጻ የኃይል ማምረት አፈፃፀሙ ከዕቅዱ አንፃር ዝቅ ያለ ቢሆንም የንፋስ ተርባይኖች የሚቆሙበትን ጊዜ በመቀነስ እና አስተማማኝ የጥገና ሥራዎችን በመስራት በተለዋዋጭ የንፋስ ሁኔታዎች ውስጥ ያልተቋረጠ ኃይል ማምረት ተችሏል፡፡ የጣቢያው የጥገና ባለሙያዎች ቴክኖሎጂን በቀላሉ መላመዳቸውና የሥራ ተነሳሽነታቸው ከፍ ያለ መሆኑ ለበጥገና ሥራ ለተመዘገበው ውጤት አስተዋጽኦ አበርክቷል ብለዋል፡፡ የተቋም ሀብት ዕቅድ ሶፍትዌር ወይም ERP፣ የሳፕ ጥገና ሞጁልና የኃይል አስተዳደር ሥርዓቶች እና ሌሎች የለውጥ መሳሪያዎች በጣቢያው መተግበራቸው ለጣቢያው የኦፕሬሽን ሥራዎች ጉልህ ድርሻ እንደነበራቸው ገልፀዋል፡፡ ኃላፊው እንደተናገሩት የጥገና ሥራዎች በዕቅድ መተግበራቸው የሥራ ጊዜን ውጤታማ በማድረግ እና የመሳሪያዎችን የህይወት ዘመን በማራዘም በጣቢያው የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖር አስችሏል፡፡   💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 5 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+9

ማከፋፈያ ጣቢያው ለአግልግሎት ዝግጁ ተደርጓል .......///…..... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የበቆጂ ባለ 230/33 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን የፕሮጀክቱ ሳይት ሥራ አስኪያጅ ገለጹ፡፡ ሥራ አሰኪያጁ አቶ እንዳልካቸው ጃምቦ እንደገለጹት በማከፋፈፈያ ጣቢው የፍተሻ እና የሙከራ ሥራዎች ላለፉት ሦስት ወራት ሲከናወኑ ቆይተዋል። የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያውን ከመልካ ዋከና ወደ ቆቃ ከሚሄደው ባለ 230 ኪሎ ቮልት የማስተላለፊያ መስመር ጋር በማገናኘት የፍተሻና የሙከራ ሥራዎች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡ የፍተሻና የሙከራ ሥራው መጠናቀቁን ተከትሎ አስር ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ለደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መደረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያው ለበቆጂና እና በ120 ኪሎ ሜትር ዙሪያ መለስ ውስጥ ለሚገኙ ከተሞች እና ወረዳዎች አስተማማኝ የኃይል ለማቅረብና የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማፋጠን እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡ የማከፋፈያ ጣቢያው ግንባታ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በተቋሙ የራስ ኃይል ግንባታ መምሪያ ላለፉት አስራ ዘጠኝ ወራት ሲከናወን ቆይቷል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et መጋቢት 4 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+3