ch
Feedback
EEP Communication

EEP Communication

前往频道在 Telegram

EEP Communication

显示更多

📈 Telegram 频道 EEP Communication 的分析概览

频道 EEP Communication (@eepcommuication) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 560 名订阅者,在 技术与应用 类别中位列第 8 357,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 160

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 560 名订阅者。

根据 25 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 32,过去 24 小时变化为 -5,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 26.03%。内容发布后 24 小时内通常能获得 15.88% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 4 052 次浏览,首日通常累积 2 472 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 8

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
EEP Communication

凭借高频更新(最新数据采集于 26 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 技术与应用 类别中的关键影响点。

15 560
订阅者
-524 小时
+167
+3230
帖子存档
photo content
+9

በዞኑ 507 የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች አካላት ተሰርቀዋል .......///....... በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ባለፉት ሦስት ወራት 507 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ አካላት መሰረቃቸውን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የምስራቅ አንድ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ አስታወቀ። የተቋሙ እና የዞኑ አመራሮች ጋር በመሰረተ ልማት ላይ ስለሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎች በተወያዩበት መድረክ ላይ የሪጅኑ የቴክኒክ ባለሙያ አቶ በሱፈቃድ ባዩ እንደገለፁት በሪጅኑ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ ከ1 ሺህ 3 መቶ በላይ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶ አካላት ላይ የስርቆት ወንጀል ተፈፅሟል። ከዚህ ውስጥ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ቦርደዴ፣ መኤሶ፣ ቡሲን አርቤ እና ኪቶን ካራ ወረዳዎች እና ቀበሌዎች 507 የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ አካላት ተሰርቀዋል። ጉዳት የደረሰባቸውን የምሰሶ አካላት ዳግም ለመጠገን ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ገልፀዋል። ከ2011 እስከ 2016 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች በሚያልፉ 119 የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ምሰሶዎች ላይ 744 ብረቶች ለስርቆት እንደተዳረጉ የጠቀሱት ባለሙያው ስርቆት የተፈፀመባቸውን የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ጠግኖ ወደ ሥራ ለማስገባት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ መደረጉን አስታውሰዋል። እንደ አቶ በሱፈቃድ ገለፃ በዞኑ እና በከተማ አስተዳደሮቹ ባለፉት ሦስት ወራት ብቻ በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የተፈፀመው የስርቆት ወንጀል በአምስት ዓመታት ውስጥ ከተፈፀመው ዝርፊያ ጋር እጅግ ተቀራራቢ ነው። ይህም በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎችና ቀበሌዎች  የሚፈፀመው የስርቆት ወንጀል አሳሳቢነቱ እየጨመረ ለመምጣቱ ማሳያ ነው ብለዋል። በአካባቢው በተደራጀ መልኩ ስርቆት የሚፈፀም መሆኑ፣ የወሰን ማስከበር ጉዳይ፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ቁርጠኝነት ማነስ እና የሥራ ትብብርን ከጥቅም ጋር የማያያዝ እንዲሁም ህብረተሰቡ ለፀጥታ አካላት አፋጣኝ ጥቆማ አለመስጠቱ ለስርቆቱ መባባስ አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው ባለሙያው ያብራሩት። በመሰረተ ልማቶቹ ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ከምንጩ ለማድረቅ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና የጭሮ ከተማ አስተዳደር በቅንጅት ሊሰሩ እንደሚገባም ነው ባለሙያው ያስገነዘቡት። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 28 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+8

ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ማስቆም ይገባል .......///......... በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስ በኤሌክትሪክ መሠረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎችን ማስቆም እንደሚገባ የዞኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ገለፁ። የጽ/ቤት ኃላፊው ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ ከምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና ከተለያዩ ወረዳዎች ከተውጣጡ አመራሮች፣ የፀጥታ እና ደህንነት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከጭሮ ከተማ አስተዳደር ጋር በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ ስለሚፈፀሙ የስርቆት ወንጀሎች ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ላይ በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ስለ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ገፅታና እንደ ተቋም በኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ እየደረሱ ስላሉ ጉዳቶች አብራርተዋል። በተቋሙ የምስራቅ አንድ ሪጅን የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ በበኩላቸው ከ2011 እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ ባሉት ዓመታት በዞኑና በከተማ አስተዳደሩ ስለተፈፀሙ የማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ሞሰሶዎች ስርቆት መጠንና ስርቆቱ በየትኞቹ አካባቢዎች እንደሚፈፀም ለተወያዮቹ ገለፃ አድርገዋል። የጭሮ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ መሀመድ ዑመር የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎቹ በተደራጀ መልኩ ከተሰረቁ በኋላ ፖሊሶች ቁጥጥር የሚያደርጉባቸውን የፍተሻ ጣቢያዎች አቋርጠው ስለሚያልፉ ችግሩም ሆነ መፍትሔ ያለው በእኛው እጅ ነው ብለዋል። በአካባቢው የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎችን የሚቆርጡ፣ የሚደልሉ፣ የሚሸጡና የሚገዙ ግለሰቦችንና ለእነርሱ ሽፋን የሚሰጡ የፀጥታ አካላት የሚፈፅሙትን ወንጀል ለመከላከል ተደጋጋሚ የምክክር መድረኮች በማዘጋጀት ግንዛቤ መፍጠር እንደሚገባ ገልፀዋል። በምዕራብ ሀረርጌ ዞን የጉምቢ ወረዳ ቦርደዴ ፖሊስ አዛዥ ኢንስፔክተር ይርጋ ብሩ እንዳሉት በወረዳው በኃይል መሰረተ ልማቶች ላይ እየተፈፀመ የሚገኘው የስርቆት ወንጀል እጅግ በጣም አስደንጋጭ ነው። የወረዳው ፀጥታ ዘርፍ የተሰረቁ የኃይል ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች መዳረሻቸውን የመለየትና የመፈተሽ ሥራዎችን መስራቱንም ጠቁመዋል። እንደ ኢንስፔክተር ይርጋ ገለፃ በአካባቢው ከማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ዝርፊያ በተጨማሪ በባቡር ሀዲድ ብረቶች ላይም መሰል ችግሮች እያጋጠሙ ይገኛሉ። የጭሮ ከተማ አስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዚያድ አማን በበኩላቸው  ከተማ አስተዳደሩ የመብራት መቋረጥን እንደ ፀጥታ ቾግር አድርጎ ይገነዘባል። የስርቆት ድርጊቱ የአካባቢው መገለጫ እንዳይሆን አበክረን እንሰራለን ብለዋል። እንደ አቶ ዚያድ ገለፃ ዝርፊያ ከሚፈፀምበት አካባቢ እስከ አዲስ አበባ ድረስ የተዘረጋ የስርቆት ሰንሰለት በመኖሩ ችግሩን ለማስቆም በጋራ መስራት ይገባል። በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮች ማስተባበሪያ አንድ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ መንግሥቱ እንደገለፁት የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆትን ለማስቀረት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም እየተሰራ ነው። የምዕራብ ሀረርጌ ዞንና የጭሮ ከተማ አስተዳደርም የስርቆት ወንጀሉን ለመከላከል የቁጥጥር ሥርዓታቸውን እንዲያጠናክሩ ጠይቀዋል። የምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶፊቅ አህመድ በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ኤሌክትሪክ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ አመራሩ በኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች ላይ የሚፈፀሙ ዝርፊያዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ሊሰራ እንደሚገባው ተናግረዋል። የስርቆት ወንጀሉን በሚፈፅሙ ግለሰቦች ላይ ህጋዊና አስተማሪ  ርምጃ በመውሰድ ድርጊቱን ማስቆም እንደሚገባም ነው አቶ ቶፊቅ ያሳሰቡት። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ አመራሮች ህብረተሰቡን በማንቃትና የስርቆት ወንጀሉን በመከላከል ግዴታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+5

photo content
+9

ክሊኒኩ ለጣቢያው ሠራተኞች የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው .....//...... በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የግልገል ጊቤ 2 የውሃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ክሊኒክ የጣቢያው ሠራተኞች ጤንነታቸው ተጠብቆ ሥራቸውን ውጤታማ በሆነ መልኩ እንዲያከናውኑ በቅርበት የህክምና አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ። የክሊኒኩ ነርስ ሲስተር የትናየት አደረግሽ እንደገለጹት ክሊኒኩ የላቦራቶሪ አገልግሎትን ጨምሮ ተኝተው ለሚታከሙና ተመላላሽ ታካሚ ሠራተኞች የተሟላ የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው። የጣቢያው ሠራተኛ በሥራ ላይ ለሚገጥማቸው አደጋም ሆነ ህመም ክሊኒኩ ሙሉ የሕክምና አገልግሎት እና የመድሃኒት አቅርቦት በነጻ እየሰጠ መሆኑን ገልፀዋል። ማመንጫ ጣቢያው የሚገኝበት ቦታ በርሃማ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሚያጋጥውን የወባ በሽታን ጨምሮ ልዩ ልዩ ወረርሽኞችን ለመከላከል በአካባቢው ከሚገኙ የጤና ተቋማት ጋር በመተባበር የአጎበር እደላ እና የመድኃኒት ርጭት እንደሚከናወንም ተናግረዋል። ከህክምና አገልግሎቱ ባለፈ ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችንና ወረርሽኞችን ቀድሞ መከላከል የሚያስችሉ የግንዛቤ ማስጨበጫዎች ለጣቢያው ሠራተኞች እንደሚሰጡም ጠቁመዋል። ከክሊኒኩ አቅም በላይ በሚሆንበት ጊዜ ሠራተኞች ለተጨማሪ ህክምና ተቋሙ አብሮ ለመስራት ስምምነት ወደፈጸመባቸው ሆስፒታሎች ሪፈር እንደሚላኩም ጠቁመዋል። በ2017 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ክሊኒኩ ለ256 የጣቢያው ሠራተኞች የተመላላሽና ተኝተው የማከም ህክምና አገልግሎት መስጠቱን የጠቆሙት ሲስተር የትናየት ይህ የታካሚዎች አሃዝ በድግግሞሽ የህክምና አገልግሎት ያገኙ ሠራተኞችን ቁጥር ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በዋናው መስሪያ ቤት ካለው መካከለኛ ክሊኒክ በተጨማሪ በማመንጫ ጣቢያዎች 12 ክሊኒኮች አሉት። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+7

ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን አሸነፈ ........///....... በ7ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ፋሲል ከነማን ገጥሞ 3 ለ 2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሁለተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዝግቧል። ሁለቱ ቡድኖች በድሬዳዋ ስቴዲየም ዛሬ ባከናወኑት ጨዋታ አቤል ሀብታሙ፣ ናትናኤል ገ/ጊዮርጊስ እና ያሬድ የማነ ለኢትዮ-ኤሌክትሪክ ሶስቱን የማሸነፊያ ጎሎች አስቆጥረዋል። ፋሲል ከነማን ከሽንፈት ያልታደጉትን ሁለት ጎሎች አንጋፋው አጥቂ ጌታነህ ከበደ ከመረብ አሳርፏል። ብርቱ ፉክክር በታየበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመስመር ላይ የተመሰረተ የማጥቃት እንቅስቃሴ ሲከተል ፋሲል ከነማ በአንፃሩ ኳስን በመቆጣጠር የጨዋታ ብልጫ ለመውሰድ ቢሞክርም ሳይሳካለት ቀርቷል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ12 ነጥብ በሊጉ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

photo content

የሁለቱ ተቋማት አመራሮች የደዴሳ ማከፋፈያ ጣቢያን ጎበኙ ........///.......... የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች የደዴሳ ባለ 500 ኪሎ ቮልት የማከፋፈያ ጣቢያን ዛሬ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት የፌዴራል  ፖሊስ የምዕራብ ኦሮሚያ አዛዥ ኮማንደር ማሙዬ አባተ እንዳሉት የተቋሙ አመራሮች በግዳጅ ላይ ያሉትን የሠራዊት አባላት መጎብኘታቸው ለሠራዊቱ አባላት የሞራል ጥንካሬ ይሰጣል። ማከፋፈያ ጣቢያው በረሃማ ቦታ ላይ የሚገኝ በመሆኑ የውሃ አቅርቦት እንዲስተካከል እና የወባ መከላከያ አጎበር እንዲሰጣቸው እንዲሁም የጥበቃ ማማ እንዲገነባላቸው ጠይቀዋል። በተቋሙ የዋና ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት የመሠረተ ልማት ደህንነትና ቁጥጥር ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደተናገሩት ተቋሙ ከፌደራል ፖሊስና ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የመሠረተ ልማት ስርቆትን ለመከላከል በትኩረት እየሰራ ይገኛል። በሠራዊቱ አመራሮች ለቀረቡት ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር እንደሚነጋገሩም ገልፀዋል። በተቋሙ የንብረት አስተዳደር መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ በበኩላቸው  ለጥበቃ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር የንብረት ማስቀመጫ መጋዘን ለመገንባት መታቀዱንና ያልተሟሉ ፋሲሊቲዎችን ከሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች ጋር በመነጋገር ለመመለስ ጥረት እንደሚደረግ አረጋግጠዋል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+6

የኃይል ማከፋፊያ ጣቢያው የማስፋፊያ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ……...///…….... የቦሌ ለሚ ባለ 230/33/15 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ሥራ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ ሁለት ሪጅን የማከፋፈያ  ጣቢያዎች ኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የማከፋፈያ ጣቢያዎች ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮሐንስ ተስፋዬ እንዳስታወቁት በማከፋፈያ ጣቢያው የማስፋፊያ ግንባታ የተከናወነው ጣቢያው ኃይል የመጫን አቅሙ በመቀነሱ ሳይሆን በ15 ኪሎ ቮልት ተጨማሪ ኤሌክትሪክ ለማቅረብ በመታሰቡ ነው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአካባቢው የ15 ኪሎ ቮልት የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር መጨመር ለማስፋፊያ ግንባታው ዋና ምክንያት እንደሆነ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል። እንደ አቶ ዮሐንስ ገለፃ የማስፋፊያ ሥራው የተለያዩ የሲቪልና የኤሌክትሮ ሜካኒካል ግንባታዎችን ጨምሮ አንድ ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያለው ትራንፎርመር የማስቀመጥ፣ የኃይል መቆጣጠሪያ ቤት ግንባታ፣ የጂ.አይ.ኤስ ስዊችጊር ገጠማና በ230 ኪሎ ቮልት በኩል የቤይ ዕቃዎችን የመትከል እንዲሁም የፍተሻና የሙከራ ሥራዎችን ያጠቃልላል። የቦሌ ለሚ የማከፋፈያ ጣቢያ በተደረገለት የማስፋፊያ ግንባታ በአሁኑ ወቅት ስድስት ባለ 15 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች እንደተገነቡለት የገለፁት ሥራ አስኪያጁ ይህም ለቦሌ አራብሳ፣ በሻሌና አካባቢው አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ እንደሚያስችል ተናግረዋል። ዝግጁ የተደረጉት አዳዲሶቹ ወጪ መስመሮች ኃይል መስጠት የሚጀምሩት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኩል የማሰራጫ መስመሮች ከተዘረጉ በኋላ በመሆኑ ለአዲስ አበባ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እና ለዲስትሪክቱ የማሳወቅ ሥራ መሰራቱን አስታውቀዋል፡፡ የማስፋፊያ ግንባታው በሪጅኑ አቅም መከናወኑን የጠቆሙት ሥራ አስኪያጁ ይህም አዳዲስ መሐንዲሶች እና የቴክኒክ ባለሙያዎች የልምድና የዕውቀት ሽግግር እንዲያገኙ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን አብራርተዋል። የማስፋፊያ ግንባታው በሪጅኑ አቅም በመከናወኑ ተቋሙን ከተጨማሪ ወጪ ማዳን እንዳስቻለም ነው አቶ ዮሐንስ የገለፁት። የማስፋፊያ ሥራው በሪጅኑ አቅም እንዲከናወን የተቋሙ የሥራ አመራር እና የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ ለሰጡት ዕድልና ኃላፊነት እንዲሁም በሥራው ላይ ለተሳተፉ ባለሙያዎች ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል። የቦሌ ለሚ የማከፋፈያ ጣቢያ ካሉት 14 ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች መካከል ለኢንዱስትሪዎችና ለከፍተኛ የኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች ኤሌክትሪክ እያቀረቡ የሚገኙት ዘጠኙ ብቻ ናቸው። ማከፋፈያ ጣቢያው ከ240 ሜጋ ዋት በላይ ኃይል የመጫን አቅም ያላቸው አንድ ባለ 50 እና  ሁለት ባለ 125 ሜጋ ቮልት አምፒር ትራንስፎርመሮች አሉት። በ15 ሚሊየን ብር በጀት የተከናወነውን የቦሌ ለሚ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ የማስፋፊያ ግንባታ ለማጠናቀቅ ሁለት ዓመት ጊዜ ወስዷል። 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+2

photo content
+9

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በኃላፊነት ስሜት እንዲጠበቅ ማድረግ ይገባል ……….///……… ሁሉም የቀበሌ እና የወረዳ አመራሮች በየአካባቢያቸው የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን በኃላፊነት ስሜት እንዲጠብቁ የምስራቅ ወለጋ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አሳሰቡ፡፡ የነቀምቴ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ምስጋኑ ቱሉ በበኩላቸው ያለ ኤሌክትሪክ የትኛውንም ዕቅድ ማሳካት ስለማይቻል በአጥፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮች ትናንት የምስራቅ ወለጋ ዞን እና ከዞኑ 18 ወረዳዎች የተውጣጡ አመራሮች እንዲሁም የነቀምቴ ከተማ አመራሮች በተሳተፉባቸው ሁለት መድረኮች ላይ በመገኘት ተቋሙን እየፈተኑት ስላሉት የመሰረተ ልማት ስርቆት ወንጀሎች ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመድረኩ ላይ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የመሠረተ ልማት ደህንነት ቁጥጥር እና ክትትል ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዋለ ታምሬ እንደገለፁት በዞኑ ሥርቆት በሚበዛባችው ጉቶ ወረዳ - ሶረቃ ቀበሌ፣ ሁኪ ከተማ ዙሪያ፣ ሌቃ ዱለቻ ወረዳ፣ ደዴሳ አካባቢ፣ ጅማ አርጆ ወረዳ፣ ጊዳ አያና ወረዳ -ጉትን ከተማ አመራሩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡ በአዋጅ ቁጥር 464/97 አንቀጽ 3 እንደተደነገገው ሁሉም የመንግስት መዋቅር የኤሌክትሪክና የቴሌኮም መሠረት ልማቶችን የመጠበቅ ግዴታ አለበት፡፡ በአዋጁ የተጣለባቸውን ግዴታ በማይወጡ አመራሮች ላይ ተጠያቂነትን ለማስፈን የሚያችል አሰራር መዘርጋት እንደሚገባም ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር የመሰረተ ልማቶቹ በሚጠበቁበት ሁኔታ የተጀመረው ወይይት በመላው ሀገሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡ በተቋሙ የንብረት እና ጠቅላላ አግልግሎት ዘርፍ የንብረት አስተዳደር መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ከሊል ሽፋ በበኩላቸው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ረጅም ኪሎ ሜትሮችን ስለሚያቆራርጡ የመሰረተ ልማቱን መጠበቅ የሁሉንም ተሳትፎ ይፈልጋል ብለዋል፡፡ በመሆኑም ከማህበረሰቡና በየደረጃው ከሚገኙ የመስተዳድር አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አንስተው አመራሩ በኃላፊነት ስሜት እንዲሰራ ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል፡፡ ምክትል አስተዳዳሪው አቶ ገመዳ ተረፈ በዞኑ በተዘጋጁ መድረኮች ላይ ለተሳተፉ ከ18 ወረዳ ለተውጣጡ አመራሮች እንደገለፁት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን መጠበቅ ለሁሉም የተሰጠ በመሆኑ የቀበሌና የወረዳ አመራሮች በባለቤትነት ስሜት እንዲጠበቅ ማድረግ ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ ቀደም በዞኑ ሁኬ ከተማ በተካሄደ የተቀናጀ ፍተሻ ብዛት ያላችው የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት አካላት በጋሪ ላይ የበየዱ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ በማካሄድ ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ መሰረተ ልማቱን በማስጠበቅ ረገድ የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋት አመራሮቹ የተሻለ ወጤት ለማምጣት እንዲሰሩም አሳስበዋል፡፡ የነቀምቴ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ምስጋኑ ቱሉ በበኩላቸው ያለ ኤሌክትሪክ የትኛውንም ዕቅድ ማሳካት ስለማይቻል በአጥፊዎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል፡፡ የህዝብ እና የመንግሥትን ንብረት የማይጠበቅ አመራር ካለ ተጠያቂነት እንደሚኖርበት ሊያውቅ ይገባል ብለዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 26 ቀን 2017 ዓ.ም

photo content
+1

photo content
+9

10 ሰዓታት የፈጀው የጥገና ሥራ በስኬት ተጠናቋል ……..///……… ከትናንት በስቲያ በእሳት አደጋ ምክንያት በጊዜያዊነት አገልግሎት መስጠት ያቋረጠውን የድሬዳዋ ቁጥር 3 ማከፋፈያ ጣቢያ መስመር የማዛወር ሥራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታወቀ። በዘርፉ የምስራቅ አንድ ሪጅን የኦፕሬሽንና ጥገና መምሪያ ዳይሬክተር አቶ ወርዲ መሀመድ እንደገለፁት ትናንት ምሽት ከ1:00 ሰዓት እስከ ሌሊት 11፡00 ከሁርሶ ወደ ድሬዳዋ አንድ፣ ወደ ሀረር እና ጅግጅጋ የሚሄዱ መስመሮችን የማዛወር ሥራ ተሰርቷል፡፡ ዛሬ ረፋድ መስመሩን የመፈተሽ ሥራ ተከናውኖ ወደሁሉም አካባቢዎች ኃይል እንደደረሰ መረጋገጡን ገልፀዋል። የሁርሶ ማከፋፈያ ጣቢያ ጉዳት እንዳጋጠመው ተደርጎ የተሰራጨው ዘገባ የሀሰት መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ ከሁርሶ ማከፋፈያ ጣቢያ ተጨማሪ ወጪ መስመር በማዘጋጀት ችግሩ መፈታቱን አስታውቀዋል፡፡ ፈታኝ የሆነው የመስመር ማዛወር ሥራ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የኃይል መቋረጥ አጋጥሟቸው በነበሩ አካባቢዎች የሚገኙ ደንበኞች በትዕግስት ስለጠበቁ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ 💡 "ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!” የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric ; ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com:/@ethiopowermedia ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power ድረ - ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et ጥቅምት 25 ቀን 2017 ዓ.ም