ch
Feedback
ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

ፍኖተ ብርሃን ዘ ቅድስት አርሴማ

前往频道在 Telegram

ይህ በግራር ደ/አባይ ቅድስት አርሴማ ቤ/ክ ፍኖተ ብርሀን ሰንበት ት/ቤት የተዘጋጀ :- ለምዕመናን : ትምህርትን , ዝማሬዎችን , ኪናዊ ዝግጅቶችን, የቤተ ክርስቲያንን ወቅታዊ ዜናዎችንና በአላትን(ንግስ, ልዮ ልዮ የሰርክ ጉባኤያት ..ወዘተ) በምን መልኩ እንደተከበሩ ለምዕመናን ተዘጋጅቶ የሚተላለፍበት ገፅ ነው።

显示更多
611
订阅者
-124 小时
-17 天
-1030 天
帖子存档
❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ #የተባረከ_የመጋቢት_ወር_ቀኑ_ዐሥራ_ሁለት ሲሆን ከሌሊቱ ሰዓት ጋር ትክክል ነው። ከዚህም በኋላ ይጨምራል።             ❤ #መጋቢት ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን #ላሜህንም_ለወለደው ለኄኖክ ልጅ #ለማቱሳላ_ለዕረፍቱ መታሰቢ በዓል፣ ለኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ #ለአባ_በርኪሶስ_ለዕረፍቱ በዓልና #ለሰማዕቱ_ቅዱስ_እለእስክድሮስ_ለመታሰቢያ_በዓሉ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከመታሰበው፦ #ከቅዱስ_መርቆሬዎስ ከመታሰቢያ በዓሉ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                     ✝ ✝ ✝ ❤ #የኄኖክ_ልጅ_ማቱሳላ፦ ዕድሜውም ዘጠኝ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ዓመት ሆነ። በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ አባ በርኪሶስ፦ ይህም አባት ክርስቲያኖችን በሚወዳቸው በቄሣር እለእስክድሮስ ዘመን መንግሥት ተሹሞ ሳለ ሐዋርያት ሲጠብቋቸው እንደነበር በበጎ አጠባበቅ ሕዝቡን ጠበቃቸው። ከጥቂት ቀን በኋላ እለእስክድሮስ ሞተ ከእርሱም በኋላ ቄሣር መክስምያኖስ ነገሠ። ክርስቲያኖችንም በጽኑ መከራ አሠቃያቸው ከእርሳቸውም ብዙዎችን ገዳላቸው። አገሮቻቸውን ትተው የተሰደዱም አሉ። ይህም አባት ሸሽቶ ወደ ገዳም ገባ ሕዝቡም ፈልገው አጡት። ከዚህም በኋላ ስሙ ዲዮስ የተባለ ሌላ ኤጲስቆጶስ በላያቸው ሾሙ። እርሱም በጥቂት ቀን ዐረፈ። ከዚያህ በኋላ ስሙ አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሾሙ። የስደቱም ወራት በአለፈ ጊዜ ይህ አባት በርኪሶስ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ ተመለሰ። አግርንዲኖስ የሚባል ሌላ ኤጲስቆጶስ ሹመው አገኛቸው። ወደርሳቸውም በደረሰ ጊዜ ሕዝቡ በመምጣቱ ደስ አላቸው አግርንዲኖስም ተልመሶ በመንበረ ጵጵስናው ላይ እንዲቀመጥ ለመነው በታላቅ ድካምም በወንበሩ ላይ አስቀመጡት። አግርንዲኖስም ዐረፈ። ❤ አባ በርኪሶስም እጅግ እስኪያረጅና እስኪደክም ድረስ ኖረ ወገኖቹንም ሌላ ኤጲስቆጶስ በላያቸው እንዲሾሙ ለመናቸው እነርሱም አይሆንም አሉ። በዚያም ወራት የቀጰዶቅያ ኤጲስቆጶስ ስሙ እለእስክድሮስ የሚባል አንድ ሰው ነበር። እርሱም በውስጥዋ ሊጸልይና ወዳገሩ ሊመለስ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። ሥራውንም በጨረሰ ጊዜ የበዓሉም ቀኖች በተፈጸሙ ጊዜ ወዳገሩ ሊመለስ ወደደ። በመድኃኒታችን ትንሣኤ በዓል በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ወደ ኢየሩሳሌም ከተማ መግቢያ ወደ ዕገሌ ደጃፍ ውጡ ወደ ደጃፋ መጀመሪያ የሚገባውን ያዙት፤ በጵጵስና ሥራም ይረዳው ዘንድ ከበርኪሶስ ጋር አድርጉት የሚል ቃል እንሆ ተሰማ። ወጥተውም ወደ ደጃፋ በደረሱ ጊዜ እለእስክድሮስን አገኙት ይረዳውም ዘንድ ያለ ፈቃዱ ከአባት በርኪሶስ ጋራ አደረጉት። እስከሚአርፍበትም ጊዜ አብሮት ኖረ። መላ የሕይወቱ ዘመን አንድ መቶ ዐሥራ ሰባት ዓመት ሆነ ኤጲስቆጶስነት ሳይሾም ሰማንያ አንድ ዓመት ኖረ በሹመቱም ላይ ሠላሳ ስድስት ዓመታትን ኖረ። እግዚአብሔር አገልግሎ መጋቢት1 በሰላም አረፈ። ጸሎቱና በረከቱ ከእኛ ጋር ለዘላለሙ ይኑር አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_እለእስክድሮስ፦ ይህም ቅዱስ ሰማዕት የሮሜ አገር ሰው ነው ለእርሱ ባለመታዙና ለረከሱ ጣዖቶቹ ባለመሠዋቱ ከሀዲው መክስምያኖስ ጽኑዕ ሥቃይን አሠቃየው። እጅግ ከባድና ታላቅ የሆነ ደንጊያ በእጆቹና በእግሮቹ ላይ አሥሮ ሰቀለው። ብዙ ግርፋትንም ገረፈው ጐኖቹንም ቀደደ በፊቱም ላይ እሳት መብራት ጨመሩ። ሥቃዩንም ባልፈራ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕቲትን አክሊል ተቀዳጀ። የፈጣሪው በረከት ከእኛ ጋራ ለዘላለሙ ትኑር አሜን። ምንጭ፦ የመጋቢት1 ስንክሳር።                          ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "አንተ ውእቱ ዘታገብእ ሊተ ርስትየ። አሕባለ ወረዉ ሊተ የአኀዙኒ። ወርስትየሰ እኁዝ ውእቱ ሊተ"። መዝ 15፥5-6። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ጢሞ 2፥1-17፣ ያዕ 1፥5፥15 እና የሐዋ ሥራ 15፥1-13። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥17-26። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም  የጾም ወራትና በዓል። ለሁላችንም ይሁንልን።                  

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን #ለታላቁ_ነቢይ፣ ሰማዕት፣ ሐዋርያ ፣ካህን #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ ሕግ አፍራሽ በሆነ በንጉሥ ኄሮድስ እጅ አንገቱን ከተሰየፈ በኋላ አንገቱ ክንፍ አውጥታ በዓለም ላይ በመዞር ዐሥራ አምስት ዓመት አስተምራ ከዐረፈች በኋላ በዓረቢያ ምድር #የከበረች_ራሱ_ለተገኘችበት ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰበው፦ ከእስክድርያ ሊቀ ጳጳሳት #ከአባ_ሚናስ ከመታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የመጥምቁ_ቅዱስ_ዮሐንስ_የከበረች_ራሱ መገኘት፦ ይህም እንዲህ ነው ከሐዲ ኄሮድስ የከበረ ዮሐንስን ራሱን ይቆርጡት ዘንድ በአዘዘ ጊዜ በእሥር ቤት ራሱን ቆርጠው ወደ ኄሮድስ አቀረቧት እርሱም ለወገኖቹ በማሳየት በቅዱስ ዮሐንስ ላይ ስለ አደረገው ሥራ እደሚያዝን ገለጠላቸው የክብር ዮሐንስንም ራስ በቤቱ ውስጥ አስቀራት። ❤ የፊተኛዪቱ ሚስቱ የንጉሥ አርጣ ልጅ ግን በአበረራት ጊዜ ወደ አባቷ መጥታ በፊቱ አለቀሰች ኄሮድስ በእርሷ ላይ ያደረገውን ሁሉ እርሷን አሳዶ የወንድሙን ሚስት ኄሮድያዳን እንዳገባ ነገረችው። በዚያንም ጊዜ ንጉሥ አርጣ ተቆጥቶ ተነሣ ሠራዊቱንም ሰብስቦ ወደ ገሊላ ዘመተ የገሊላንም አገሮች ሁሉ አጠፋ በእሳትም አቃጠለ። ❤ ንጉሥ ጢባርዮስ ቄሣር ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ኄሮድስ በአባረራት በልጁ ምክንያት ንጉሥ አርጣ ይህን እንዳደረገም በአስረዱት ጊዜ ስለዚህ ንጉሥ ጢባርዮስ ቄሣር ተቆጣ ኄሮድስንም ወደ ሮሜ ከተማ ወደርሱ አስቀረበው በእርሱም ምክንያት የአገሮች ጥፋት በመደረጉና ታላቁን ነቢይም ስለ መግደሉ ከሹመቱ ሻረውና እንድልኩ ወደሚባል አገር አጋዘው በዚያም በክፉ አሟሟት ሞተ። ❤ የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ግን በኄሮድስ ቤት ተቀብራ ትኖር ነበር ከዚህም በኋላ ንጉሥ ጢባርዮስ ጭፍሮቹን ልኮ የኄሮድስን ቤት አስፈረሰ ጥሪቱን ሁሉ ወሰደ ለሚያየውም ሁሉ አርአያና ተረት ሆነ ያለ ጣሪያና ያለ ደጃፍ ቀርቷልና ነጋዴዎችም መነሃሪያ አድርገው ያድሩበት ነበር። ❤ በዚያንም ወራት በገንዘብ ድኆች በሃይማኖት ባለጸጎች የሆኑ ሁለት ሰዎች ነበሩ እነርሱም ሊሰግዱ የከበረች የአርባ ቀን ጾምንም ሊጾሙ ወደ ኢየሩሳሌም ተጓዙ ይህም ከብዙ ዘመን በኋላ ነው። ምሽትም በሆነ ጊዜ ምድረ በዳ በሆነ በኄሮድስ ቤት ውስጥ አደሩ ቅዱስ ዮሐንስም ከእርሳቸው ለአንዱ በሕልም ተገለጠለትና የከበረች ራሱ ያለችበትን ቦታ አስረዳው ወደቤቱም ተሸክሞ ይወስዳት ዘንድ አዘዘው በነቃም ጊዜ ራእይን እንዳየ ለባልንጀራው ነገረው። ቅዱስ ዮሐንስም ወደአመለከተው ወደዚያ ቦታ ተነሥተው በአንድነት ሔዱ በቆፈሩም ጊዜ የሸክላ ዕቃ አግኝተው ከፈቷት ያን ጊዜ እጅግ የሚመስጥ በጎ መዓዛ ወጣ የቅዱስ ዮሐንስንም ራስ አገኙዋት ከእርሷም ተባረኩ ወደ ሸክላው ዕቃ መለሱዋትና በፊቱ እንደ ነበረ አፉን ዘጉ ያም ሰው ከእርሱ ጋር ወደ ቤቱ ወሰዳት ታላቅ ክብርንም አከበራት ሁል ጊዜም የሚያበሩ መብራቶችን በፊቷ አኖረ። ❤ የዚያም ሰው ዕረፍቱ በቀረበ ጊዜ ለእኅቱ ነገራት እርሷ ቅድስና ስለአላት እርሱ ሲሠራው እንደነበረ ትሠራ ዘንድ አዘዛት እርሷም የምታከብራትና ሁል ጊዜ መብራትንም የምታበራ ሆነች። የቅዱስ ዮሐንስም ራስ ወደ አርዮሳዊ ሰው እስከ ደረሰች ድረስ ከአንዱ ሰው ወደ አንዱ ሰው የምትፋለስ ሆነች ይህም ሰው በከሀዲው አርዮስ እምነት ውስጥ እያለ የቅዱስ ዮሐንስ ራስ ድንቆች ተአምራቶችን እንደምታደርግ ያስብ ነበር። ❤ የከበረ ዮሐንስም ከእርሱ የሚበልጥ ሰው በላዩ አስነሣበትና በዚያ ቦታ አሳደደው ያም ቦታ አባ ቄርሎስ በኢየሩሳሌም  አገር አባ አንያኖስ በአገረ ኀምዳ ኤጲስ ቆጶስነት እስከ ተሾሙ ድረስ ፈጽሞ ሰው የማይኖርበት ምድረ በዳ ሆነ። ቅዱስ ዮሐንስም ለአባ አንያኖስ በሕልም ተገልጦ የከበረች ራሱ ያለችበትን ቦታ ነግሮ አመለከተው አባ አንያኖስም ሒዶ እንደ ዛሬው ግንቦት ሠላሳ ከዚያ አወጣት ይህም የካቲት ሠላሳ ቀን ከአገኙዋት በኋላ ዳግመኛ ያገኙበት ነው። ❤ እንዲህም የሚል አለ የከበረ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ተናገረ ይህም ኄሮድስ በአዘዘ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ በእሥር ቤት ሳለ ራሱን በሰይፍ ቆርጠው በጻሕል አድርገው ወደ ኄሮድስ አመጡለት እርሱም ለኄሮድያዳ ልጅ ሰጣት እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠቻት። ይቺም የረከሰች አመንዝራ ልትዳስሣት በወደደች ጊዜ በወጭቱ ውስጥ ጠጒሩዋ ተዘርግቶ ወደ አየር በረረች በአየርም ሁና "የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም" እያለች የምትጮኸ ሆነች እንዲህም እያለች ዐሥራ አምስት ዓመተት ኑራ በዓረቢያ ምድር ዐርፋ በዚያ ተቀበረች። ❤ ነጋድያንም በዚያ ቦታ የሚድሩ ሆነ በእግዚአብሔርም ፈቃድ ሁለት አማንያን ነጋዴዎች ወደዚያ ቦታ ደርሰው አደሩ ቅዱስ ዮሐንስም በሕልም ተገለጠላቸውና የከበረች ራሱን ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው እነርሱም አወጡዋት ከእርሳቸውም ጋር ቤታቸው ወስደው ታላቅ ክብር አከበሩዋት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም መለኮትን በአጠመቀ በከበረ ቅዱስ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን ልዩ የሆነች በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የካቲት 30 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_እብል_ለእርስከ_ክቡር። ዘተረክበ ዮም በንዋየ ጽቡር። #ዮሐንስ_ሠራሪ_ንጉሠ አዕዋፍ ንስር። ንሥአኒ በክነፊከ ወአዕድወኒ ለገብር። ከመ ኢያስቆቁ ቀዊምየ በጽንፋ ለባሕር"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_30።                           ✝️ ✝️ ✝️ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ገሥፆሰ ገሠፀኒ እግዚአብሔር። ወለሞትሰ ባሕቱ ኢመጠወኒ። አርኅው ሊተ አናቅጸ ጽድቅ"። መዝ 117፥18። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 4፥7-ፍ.ም፣ 2ኛ ጴጥ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 13፥24-32። የሚነበበው ወንጌል ማር 6፥21-34። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።                   

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ እንኳን #ለዐቢይ_ጾም_አራተኛ_ሳምንት_ለመፃጒዕ እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የመፃጒዕ_መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፭ "#አምላኩሰ_ለአዳም_ለዕረፍት_ሰንበተ_ሠርዐ ወይቤልዎ አይሁድ በዓይ ሥልጣን ትገብር ዘንተ #ወይቤሎሙ_ኢየሱስ አነ እገብር አንትሙኒ እመኑ በግብርየ #አነ_ውእቱ_እግዚኣ_ለሰንበት_ወልድ_ዋሕድ ወይቤሎሙ ብውህ ሊተ ኅድግ በዲበ ምድር እስብክ ግዕዛነ ወእክሥት አዕይንተ ዕውራን አቡየ ፈነወኒ"። ትርጉም፦ #የአዳም_አምላክ_ሰንበትን_ለዕረፍት ሠራ፤ አይሁድ በምን ሥልጣን ይህን ታደርጋለህ አሉት፤ #ኢየሱስም_በራሴ_ሥልጣን_አደርጋለሁ፤ እናንተ ግን በሥራዬ እመኑ፤ #እኔ_የሰንበት_ጌታ_ነኝ፤ እኔ ወልድ ዋሕድ በምድር ላይ ኃጢአትን ይቅር እል ዘንድ፤ ነጻነትን እሰብክ ዘንድ #የዕውራንን_ዐይን_አበራ_ዘንድ የባሕርይ አባቴ ላከኝ አላቸው። #ሊቁ_ቅዱስ_ያሬድ_በድጓው_ላይ።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #መፃጒዕ፦ አራተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት "መጻጒዕ" ይባላል። ፀግ0 ፤መጻጕዕ፦ በቁሙ ጎባጣ በጀርባው ላይ እንደ ሻኛ ያለው ደረቱ ከጉልበቱ የተጠጋ ሕመምተኛ በሽተኛ ማለት ነው። ❤ በዚህ ሣምንተ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድውያንን መፈወሱን ዕውራንን ማብራቱን የሚያነሳ መዝሙር ይዘመርበታል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለጌትነቱ ምልክት በሕዝቡ ያሉ ድውያንን ሁሉ ይፈውስ ነበር። የተአምራቱም ዜና በሶርያ በአራቱ ማዕዘን ደረሰ ተብሎ በተነገረው መሠረት ቅዱስ ማቴዎስ 4፥23-25 አንደጻፈው ቀጥለን እናያለን በማቴ 8 ፥1-4 ከተራራ በወረደ ጊዜ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት ለምጻም ቀርቦ ጌታ ብትወድስ ልታነፃኝ ትችላለህ እያለ ሰገደለት እጁንም ዘርግቶ ዳሰሰውና ንፃ አለው ወዲያውም ለምፁ ነፃ። በማቴ 8፥5-13 የመቶ አለቃውን ልጅ በቃሉ ፈወሰ፣ የጴጥሮስ አማት ከንዳድ ፈወሳት። በማቴ 8 ፥14 አጋንንት አወጣ ማቴ 8፥16ና በማቴ 8፥28 በዚህ ተአምራት የምንረዳው ቁም ነገር በሰዎች ያደሩ አጋንንት ክርስቶስን የእግዚአብሔር ልጅ ብለው ማመናቸውን ነው። የሐዋ 19÷15፤ ያዕ 2÷19። ❤ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፈወሳቸው ሕሙማን ብዙ ሲሆኑ ለምሳሌ ያህል ከላይ በጠቀስነው በማቴዎስ ምዕራፍ 8 ያሉትን እንዳዳነ ሁሉ በሌሎች ወንጌላውያን ምዕራፍና ቁጥርም በርካታ በሽተኞችን እንደፈወሰ ተገልጿል ከተፈወሱት ሰዎች መካከል የኻያ ሦስቱ ታሪክ ተገልጦአል ከእነርሱ ሌላ ኢየሱስ ሦስት ሙታንን አስነስቶአል አንደኛ የኢያኢሮስን ሴት ልጅ (ማቴ 9፥18-26) ሁለተኛ የመበለቲቱን ልጅ ፈወሳት (ሉቃ 7÷11-17) ሦስተኛውም ደግሞ አልዓዛር (ዮሐ 11፥43-44)፡፡ ❤ ክርስቶስ በአምስት አይነት መንገድ ሕሙማን ፈወሰ። 1) በቃሉ (ማቴ8፥16፡፡ ዮሐ 4÷50) 2) በመዳሰስ (ማቴ 8፥} ፣ ሉቃ 5÷13) 3) እጅ በመጫን(ማር 6፥5፣ 8፦22) 4) ጭቃን በመቀባት (ዮሐ 9÷6-7) 5) በልብሱ ጫፍ (ማቴ9፥20፡፡ 14፥36) ❤ እግዚአብሔር ፈዋሽ ነው (ዘጸ 15፥26) ፈዋሽነቱ ለሁሉ ቢሆንም በሰፊው የሚነገረው ግን በዮሐ 5÷5-15 ያለ በሽተኛ ነው። ይኸውም ኋላ ጌታችን ኢየሱስን በጥፊ የመታው ነው ብለው ሊቃውንት ይተረጉማሉ (ዮሐ 18፥22)። ምንጭ፦ ከመምህረሰ አምኃ ሥላሴ (መኩርያ ተስፍዬ) ፌስቡክ ገጽ የተወሰደ።                                                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔር ይረድኦ ውስተ ዐራተ ሕማሙ። ወይመይጥ ሎቱ ኵሎ ምስካቢሁ እምደዌሁ። አንሰ እቤ እግዚኦ ተሣሃለኒ"። መዝ 40፥3-4። የሚነበቡት መልዕክታት ገላ 5፥1-ፍ.ም፣ ያዕ 5፥14-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥1-12። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 5፥1-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም ዕለተ ሰንበት (መፃጕዕ)ና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።                  

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን #ለአርሞኒ_አገር_ኤጲስቆጶስ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ለደረሰ ለከበረ #ለአባ_ቢላካርዮስ ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከእመቤታችን_ከቅድስት_ድንግል_ማርያም በሥጋ ከመወለዱ ከክብር ባለቤት #ለጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ_ከልደቱ_ከበዓለ_ወልደ በዓል መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_ቢላካርዮስ፦ ይህም አባት ፈጽሞ እስከ አረጀ ድረስ በተሾመበት ወንበር ብዙ ዘመናት ኖረ ብዙ ድርሳናትንና ተግሣጻትንም ደረሰ እሊህም ስለከበረች የልደቱ በዓልና ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ስለ ሞትና ስለ መቃብር፣ በኃጥአንም ላይ ስለ ሚደርስባቸው ሥቃይ፣ ስለ መድኃኒታችንም የረቀቀ ጥበብ ስለ ከበሩ በዓላትም ናቸው። ሕይወት በሆኑ ትምህርቶቹም ብዙ ነፍሳትን መሥዋዕትን አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ። ❤ በክርስቲያንም ወገኖች ላይ የስደትና የመከራ ወራት በሆነ ጊዜ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ ወደደ ሕዝቡንም ሰብስቦ "በቀናች ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ" አዘዛቸው ስለ ጌታችን ኢየሱስ ደሙን ሊያፈስ ይሻልና እነርሱ እንግዲህ "ፊቱን እንደማያዩት" ነገራቸው። ሰምተውም አለቀሱ ስለ መለየታቸውም እጅግ አዘኑ "የሙት ልጆች እንሆን ዘንድ ለምን ትተውናለህ" አሉት። ማስቀረትና ማስተውም ባልተቻላቸው ጊዜ ከእርሳቸው ዘንድ ወጥቶ ወደ መኰንኑ ሔደ በፊቱም ቁሞ በክብር ባለቤት በጌታችን ኢየሱስ ክርሰቶስ ታመነ መኰንኑም ብዙ አሠቃየው። ❤ ሕዝቡም ብዙ ልመናን አብዝተው ለመኑት "ራስህን አድን ከከተማም ውጣ" አሉት እርሱም ልባቸውን ደስ ያሰኝ ዘንድ "በሥውር እወጣለሁ"አላቸው። በዚያች ሌሊት "ሰማዕትን ትሆን ዘንድ የተመኘኸውን በጎ ምክር ለምን ረሳህ" እንደሚለው ሰው ሁኖ ራእይን አየ። ከዚያም በኋላ ተመልሶ ለመኰንኑ ተገለጠለት በዚያንም ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡት ዘንድ መኰንኑ የካቲት29 ቀን አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበለ። ሥጋውንም ምእመናን አንሥተው ወሰዱት ለኢጲስቆጶሳትም እንደሚገባው አክብረው ገንዘው በመቃብር አኖሩት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ቢላካርዮስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት29 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_እብል_ለልደትከ_መድምም። እምድንጋሌ ሥጋ ኅቱም። #ኢየሱስ_ክርስቶስ_መድኃኔዓለም። ልብየ አንቅሕ ለስብሐቲከ አዳም። ለሥጋየሰ አኀዞ ድካም"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_29።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ወኢሰምዑኒ ሕዝብየ ቃልየ። ወእስራኤልኒ ኢያፅምዑኒ። ወፈነውኩ ሎሙ በከመ ምግባሮሙ። መዝ 80፥11-12 ወይም መዝ 2፥7-8። ። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 22፥1-5 ወይም ሉቃ 2፥1-21።                                            

❤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጣላት በልጅዋ ምክንያት ስለ ደረሰባት ሀዘኖች አውርታላታለች፡፡ የፈለገችውንም እንድታደርግበት በእጅዋ ያለውን መስቀል ለቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሰጥታታለች፡፡ በዚህም መስቀል ባሕር ከፍላ ደቀ መዛሙርቶቿን አሻግራለች፡፡ ❤ እናታችን የአባታችን የአባ ኤዎስጣቴዎስን ገድል በማንበብና በመልአኩ ቅዱስ ሚካኤል እርዳታ ባሕሩን በአጽፏ ተሻግራ ወደ አገረ ናግራን ሄዳለች፡፡ እንዲሁም በበትረ መስቀል እንደ ዘርዐ ቡሩክ ከባሕር ውስጥ የሰጠሙ የደቀ መዛሙርቶቿን መጻሕፍት ምንም ሳይሆኑ ማውጣት ችላለች፡፡ በሁሉም አገር እየዞረች ቅዱሳት መካናትን ትሳለም ነበር፡፡ ደብረ ደሞ ሄዳ "ሴቶች መውጣት አይችሉም" ቢሏት በሀዘን ስታለቅስ ቅዱስ ሚካኤል በሥውር ወስዶ አድርሷታል፣ አቡነ አረጋዊም ተገልጸውላት ባርከዋታል በዚያም ሥጋ ወደሙን ተቀብላለች፡፡ ❤ እናታችን ወደ ኢየሩሳሌምም ሄዳ ቅዱሳት መካናትን እየተሳለመች ለ7 ዓመታት ቆይታለች ቅዱስ ሚካኤልም በዓምደ ብርሃን እየመራት ተመልሳ ወደ አገራችን መጥታ በድጋሚ ከሱስንዮስ ጋር ተሟግታለች፡፡ ሙታንንም እያስነሳች እንዲመሰክሩላት ብታደርግም እርሱ ግን ከጥፋቱና ከክህደቱ ሊመለስ አልቻለም ነበር፡፡ የተለያዩ ተአምራትን በማድረግ መልእክቷንም በንስር አሞራ አድርጋ እየላከች ትመክረው ነበር ፡፡ ❤ በአንድ ወቅትም በአገራችን እህል መታጣት ሆነና ቅድስት እናታችን ዝክር የምታደርግበት እህል አጣች፡፡ደናግል ልጆቿንም ጠርታ ትንሽ ዱቄት እንዲያመጡላት ነግራቸው በእርሱ ጸሎት አድርጋበት "ወደ ቦታው መልሱት" አለቻቸው፡፡ በማግስቱም እንሥራው ጋኑ ሁሉ በዱቄት ተሞልቶ አግኝተውታል፡፡ የካቲት ኪዳነ ምሕረትንም በዓል በደስታ አክብረዋል፡፡ ❤ መልአኩም ከቅድስት አገር ኢየሩሳሌም መልሶ ወደ ኢትዮጵያ ካመጣት በኋላ ዛሬ ገዳሟ ካለበት ቦታ ስትደርስ ከቦታዋ ላይ ዓምደ ብርሃን ተተክሎ በቀስተ ደመና ተከቦ አይታ "ይህች ቦታ ምንታምር" ብላ ጠራቻት፡፡ በቦታውም ላይ በመድኃኔዓለም ትእዛዝ የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን ቤተ ክርስቲያን በአንዲት ቀን ታህሣሥ14 ቀን በዕለተ ዓርብ ጧት በሰንሰል (በስሚዛ) እንጨት ጀምራ ማታ እንደተፈጸመ በ3ኛው ቀን እሁድ ታህሣሥ16 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር በድርገት (በቁርባን) ጊዜ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከእልፍ አእላፋት መላእክት ጋር ወርዶ መቅደሱን ሲባርክ መቅደሱ በ4ቱ ማዕዘን ለጌታ ሰገደ። ለጌታ እንደ ሰገደ ዛሬም ድረስ ይታያ፡፡ ❤ ጌታችንም "ይህ መቅደስሽ ሳይፈርስ እስከ ዕለተ ምጽአት ድረስ ይቆይልሻል፡፡ በዚህ ቦታ ሥጋዬን የበላ ደሜን የጠጣ ኃጢአቱ ይሰረይለታል፡፡ በምድርም ስምሽን የጠራ፣ መታሰቢያሽን ያደረገ፣ የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ያነበበ፣ የተረጐመ ሁሉ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልቡና ያልታሰበውን ለነዚህ ሁሉ ዋጋቸውን እሰጣቸዋለሁ፡፡ ከሩቅም ከቅርብም ከቀኝም ከግራም መጥቶ መቅደስሽን ለተሳለመ ሁሉ እስከ 12ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ፡፡ላልምረው ቦታችን አላስረግጠውም፡፡ በረከቴም በእሱ ላይ በልጆቹም በንብረቱ ላይ ለዘለዓለሙ ይኖራል፡፡ ስለጾምሽ፣ ስለጸሎትሽ፣ ስለተጋድሎሽ፣ ስለ ስግደትሽ ሰባት አክሊል ሰጠሁሽ" አላት፡፡ ❤ ፃድቋ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ብዙ ገድል በሠራችበት ብዙ መነኰሳይያትን በአቋቋመችበት ገዳሟ በእመ ምዑዝ ኪዳነ ምሕረት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድነት ገዳም የካቲት29 ቀን ዐረፈች። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከቅዱሳን መላእክት ከጻድቃን ከሰማዕታት ጋር መጥቶ ነፍሷን ተቀብሎ ወደ ገነት ወስዶ አኖራት፡፡ ባረፈች ጊዜ በሥጋዋ ላይ ታላቅ የብርሃን ዓምድ ተተክሎ የታየ ሲሆን እንደ ፀሓይም ከጠዋት እስከ ማታ ያበራ ነበር፡፡ በመካነ መቃብሩዋም ላይ እስከ አርባ ቀን ድረስ ብርሃን ተተክሉ ታይቷል፡፡ ምንጭ፦ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ። ከእናታችን ከቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከት ያሳትፈን። በጸሎቷም ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ።                 

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊቷ_ጻድቅ በአጤ (ዐፄ) #ሱሱንዮስ አንገቷን ተሰይፈ ሰማዕት ከሆነች በኋላ #ቅዱስ_ሚካኤል ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ 14ቀን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከተቀመጠች በኋላ እንደገና እንደተኛ ወይም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ከሞት ተነስታ ብዙ ገዳማትን (ታላቁን ገዳም ራማ ኪዳነ ምሕረትን) ላቀናች #ለታላቋ_ለጻድቅ_ወሰማዕት_ለቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ለዕረፍቷ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #ጻድቅ_ወሰማዕት_ቅድስት-ፍቅርተ_ክርስቶስ (እመ ምዑዝ)፦ በጎንደር ክፍለ አገር ደራ ፎገራ አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ አቡነ ሐራ ገዳም አጠገብ ኮክታ ማርያም ተብሎ በሚጠራው ቦታ ውስጥ ተወለደች፡፡ዛሬም ይህ አካባቢ እመ ምዑዝ መንደር ይባላል፡፡የአባቷ ስም ቅዱስ ላባ የእናትዋ ስም ቅድስት ወንጌላዊት ይባላል፡፡ እነዚህም ወላጆቿ እጅግ ደጋግ ሰዎች እግዚአብሔርን የሚፈሩ ለተራበ፣ ለተጠማ የሚያዝኑና የሚራሩ እንደ አብርሃምና እንደ ሣራ በጎ ምግባር ያላቸው ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን በረከት ሁሉ በሥራ ላይ የሚያውሉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልጅ ስላልወለዱ ወደፈጣሪያቸው ወደ እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣቸው ይለምኑ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አምላክም የለመኑትን የማይነሳ የነገሩትን የማይረሳ ቸር አምላክ ስለሆነ እንደ ቅድስት ሐና እመ ሳሙኤል ጸሎታቸውን ሰምቶ የተመረጠች ደግ ሴት ልጅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በሚያዚያ 4 ቀን ተፀንሳ ታኀሣሥ29 ቀን ከእነሱ ተወለደች፡፡ ስመ ጥምቀቷ ማርያም ጸዳላ የዓለም ስሟ ሙዑዚት ሲሆን ሙዑዚት ማለት ጣፋጭ ማለት ነው፡፡ (ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ደግሞ የቆብ ስሟ ነው።) ❤ በተወለደችም ጊዜ በእግርዋ ቆማ "በማኀየዊ ቸርነትህ ከጨለማ ወደ ብርሃን ላወጣኸኝ ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል" ብላ አመሰገነች ከእግዚአብሔር የተላከ መነኵሴም ወደ እርሷ በመሄድ የዳዊትን መዝሙር፣ መጻሕፍትንና የቤተክርስቲያንን ትምህርት በሚገባ አስተምሯአታል፡፡ ❤ ቅድስት እናታችን አምላኳን አስከ መጨረሻው በድንግልና ማገልገል ብትፈልግም ዕድሜዋ ከፍ ሲል ቤተሰቦቿ ዘርዐ ክርስቶስ ከሚባል አገረ ገዥ ጋር በቤተክርስቲያን ሥርዓት በተክሊል አጋቧት ፡፡ እርሷ ግን በጫጉላ ቤት ሳሉ በእኩለ ሌሊት ባሏን "ወንድሜ ሆይ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ድንግልናችንን እንጠብቅ" አለችው፡፡ እርሱም "እሺ" ብሏት ይህንን ተመካክረው በጸሎት ሲተጉ አደሩ፡፡ ለእግዚአብሔር እየተገዙ በጾም በጸሎት በንጽሕናና በድንግልና ኖሩ በሌሊትም ወደ፡ባሕር ውስጥ እየገቡ ጸሎት ያደርጉ ጀመር፡፡ በመጨረሻም እርሷ በጳጳሱ በአባ ማርቆስ እጅ ስትመለኵስ ባሏም ድንግልናውን እንደጠበቀ በሰማዕትነት አንገቱን ተሰይፎ አርፏል፡፡ እርሷ በነበረችበት ዘመን ንጉሥ ሱስንዮስ "ሁለት ባሕርይ" የሚለውን የረከሰ የሮማውያንን ሃይማኖት ሕዝቡ ሁሉ እንዲያምን በማወጁ ምክንያት በአገራችን ከፍተኛ የሆነ የሃይማኖት ግጭት ስለተነሣና ከ8ሺህ በላይ ክርስቲያኖች በግፍ ተጨፍጭፈው ሲያልቁ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከእነ አቡነ ስምዖንና ከሌሎችም ቅዱሳንና ቅዱሳት ጋር ተሰልፋ ሰማዕትነትን ተቀብላ ለሃይማኖትዋ ምስክር ሆናለች፡፡ ባለቤቷ ዘርዐ ክርስቶስም በሰማዕትነት ዐርፎ ሰባት አክሊላት ወርደውለታል፡፡ ❤ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሱስንዮስ በአደባባይ ሲያስገርፋቸው ሥጋቸው እየተቆራረጠ መሬት ላይ የወደቀውን የሰማዕታቱን ሥጋቸውን ሰብስባ "ይህን ለንጉሡ እጅ መንሻ ስጡልኝ" ብላ ላከችለት፡፡ "ይህ የሃይማኖ ፍሬ ነው፡፡ እኛስ አስከአሁን በሃይማኖታችን አለን፣ አንተ ብትገለን መከራም ብታደርስብን ሃይማኖታችንን አልካድንም፡፡ ነገር ግን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቸርነቱ ከሞት አስነሣን ይህን የሥጋዬን ቁራጭና የእህቶቼን የደናግላንን ሥጋ ብላው ፣ ደማችንን ጠጣ ሃይማኖትህ የከፋ፣ ሰነፍ፣ የረከስህ ነህ" ብላ ልካለታለች፡፡ መልእክተኞቹም ለንጉሡ ወስደው ሰጥተውታል፡፡ ሱስንዮስ አዋጁን እንዳወጀ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖንም ካህናትንና ክርስቲያን ልጆቻቸውን አነሳስተው እያስተማሩና እያጠነከሩ እያለ በጦር ተወግተው በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ❤ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ስምዖን በሰማዕትነት ከማረፋቸው በፊት ግን እነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ፣ ቅድስት ወለተ ጴጥሮስን፣ ቅድስት አካለ ክርስቶስን፣ ቅድስት እመ፡ወተትን ... ወዘተ አነሳስተው ንጉሡን መክረውታል፣ ገሥጸውታል፣ ንጉሡ ግን ሊመለስ አልቻለም፡፡ ይልቁንም ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን የሃይማኖቷን ጽናት ስላየ ሥጋዋ እየተቆረሰ መሬት ላይ እስኪወድቅ ድረስ በብረት በትር አጥብቆ ያስገርፋት ጀመር፡፡ በመጨረሻም ምድር እየሰወረቻት ለመግረፍ የማይመቻቸው ቢሆን ከሌሉቹ ሰማዕታት ጋር አንገቷን በሰይፍ አስቆርጦታል፡፡ በዚህም ጊዜ ፍጹም ጨለማ ሆኖ ምድርም ተነዋወጠች፡፡ ስምንት ሺህ ዐሥር ቅዱሳንም በሰማዕትነት ዐረፉ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን አንገቷን በሰይፍ ቢቆርጧትም ነገር ግን ቅዱስ ሚካኤል ገነትንና ሲኦልን አሳይቶ 14ቀን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ከተቀመጠች በኋላ እንደገና እንደተኛ ወይም ከእንቅልፉ እንደሚነቃ ሰው ከሞት አስነሥቶ ወደ ቦታዋ መለሳት፡፡ ❤ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ቅዱስ ሚካኤልም ከሞት ካስነሣት በኋላ መናኝ ሆና በየገዳሙና በየአድባራቱ እየሄደች ዓለምን ስትዞር ያቀናቻቸው ብዙ ገዳማት አሉ፡፡ ለምሳሌ ከተሰዓቱ ቅዱሳን አንዱ በሆኑት በአባ ጉባ ተመሥርታ በግራኝ ወረራ ጠፍታ የነበረችውን ራማ ኪዳነ ምሕረት አንድነት ገዳምን አቅንታ የወንድና ሴቶች መነኰሳት በጋራ አብረው ይኖሩ የነበረ ቢሆንም የበጎ ሥራ ጠላት የሆነው ሰይጣን በማኀበረ መነኰሳቱ መካከል ሊፈጥር ያለውን ክፉ ፈተና ለእናታችን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተገልጾላት በገዳሟ ውስጥ የወንዶችና የሴቶች መነኰሳት መኖሪያ የተለያየ እንዲሆን አድርጋለች፡፡ ❤ ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌምም በመሄድ ላይ ሳለች በመንገድ ሰውን የሚበሉ ፍጡሮች ወደሚኖሩበት አካባቢ ስትደርስ 60 የሚሆኑ አገልጋዮቿን ለመብላት ይዘው ሳር ቅጠል እንዲበሉ በማድረግ ዓይናቸውን በጉጠት በማውጣት ለወራት በጨለማ ቤት ውስጥ ዘጉባቸው ሰይጣንንም ያመልኩ ነበርና ከ4 ወራት በኋላም በዓል አድርገው ለመብላት ከእሳት ውስጥ ጨመሩአቸው፡፡ እነርሱ ግን ምንም አልሆኑም፡፡ ያን ጊዜም "እናንተ ሰዎች ምንድን ናችሁ?" ብለው ጠየቋቸው፡፡ ቅድስት እናታችን ፍቅርተ ክርስቶስም ክርስቲያን መሆናቸውንና እነርሱ የሥላሴ ሕንጻ የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው ብትመክራቸው "ምን እንበላለን?" አሏት፡፡ እርሷም ከራማ ኪዳነ ምሕረት ስትነሳ የእህል ዘርን ለአገልጋዮቿ አስይዛ ስለነበር ከዚያ ስንዴ ወስዳ ዘራችው፡፡ስንዴውም በአንድ ቀን ተዘርቶ በቅሎ፣ ታጭዶ፣ ደርቆ፣ ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡ ቅድስት እናታችንም ቀምሳ ስታቀምሳቸው እንደማር እንደ ወተት የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም እንደዚህ እያደረጉ እየሠሩ እንዲበሉ አስተምራ አስጠምቃቸው ስድስት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርታላቸዋለች፡፡ወንጌልን፣ ስንክሳርን፣ ሃይማኖተ አበውን፣ ግንዘትን፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ አርጋኖንን ሁሉ በእጅዋ ጽፋ አስቀመጠችላቸው፡፡

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤           ❤ #የካቲት ፳፰ (28) ቀን። ❤ እንኳን #ለአርእስተ_አበው_ለቅዱሳን #ለአብርሃም_ለይስሐቅና_ለያዕቆብ ለበዓላቸው መታሰቢያና #ለሮማዊ_ቅዱስ_ቴዎድሮስ በነገሥታት መክሲሞስና መክስምያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱስ_ቴዎድሮስ_ማኅበር ከሆኑ #ስድስት_ሺህ_ሦስት_መቶ_አራት ሰዎች በሰማዕትነት ከዐረፉ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                                                          ✝ ✝ ✝ ❤ #ሮማዊው_ሰማዕቱ_ቅዱስ_ቴዎድሮስ፦ እርሱም ከእስያ አውራጃ አስጢር ከሚባል አገር ነው። ይህንንም ቅዱስ በነገሥታት ዘንድ አማልክትን በማምለክ እርሱ እንደማይስማማ ወነጀሉት በዚያንም ጊዜ አስጠርተው "ለአማልክት ለምን አትሰግድም" አሉት፡እርሱም "እኔ ክርስቲያን ነኝ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታዬ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አላመልክም" ብሎ መለሰላቸው። የበርብዮስጦስ፡ ልጅን ጉሥም "ለአማልክቶቼ ብትገዛ በጭፍራዎቼና በመኳንቶቼ ሁሉ ላይ አለቃ አድርጌ እሾምሃለሁ ብዙ ወርቅና ብር የከበሩ ልብሶችንም እሰጥሃለሁ" አለው ቅዱስ ቴዎድሮስም "ወርቅህና ብርህ ለጥፋት ይሁንህ እኔስ በንጉሤ በሕያው እግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ባለጸጋና አለቃ ነኝ" አለው። ❤ ንጉሥም "ለአምላክህ ልጅ አለውን?" አለው የከበረ ቴዎድሮስም "አዎን ከመለኮቱ ባሕርይ የተገኘ ከእርሱ ጋር ዓለምን የፈጠረ በእውነት ልጅ አለው" ብሎ መለሰለት ንጉሡም "አምላክህን ብናውቀው ልናገኘው እንችላለን" አለው ቅዱስ ቴዎድሮስም "ወደርሱ ከተመለስክ እንደ እኔ ጭፍራ ትሆናለህ የተወደደ መሥዋትም ያደርግሃ" አለው። ንጉሡም "ነገር አታብዛ ብዙ ገንዘብ እሰጥ ዘንድ ለአማልክቶቼ መሥዋዕትን አቅርብ እንጂ" አለው የከበረ ቴዎድሮስም ንጉሡን ረገመው ጣዖታቱንም ሰደበ በዚያንም ጊዜ ንጉሡ ተቆጣ። ልብሱንም እንዲገፉት በትምህርቱም ከአመኑ አሕዛብ ጋር በጨለማ ቤት ያሥሩት ዘንድ አዘዘ። የከበረ ቴዎድሮስም ጸለየ በሌሊትም ወጣ ዕንጨቶችንም ሰብስቦ ጣዖቶችን ሁሉ አመድ እስኪሆኑ ድረስ አቃጠላቸው እንዳይሰሙ በአገልጋዮቻቸው ላይ እግዚአብሔር ከባድ እንቅልፍ አሳድሮባቸዋልና። ❤ ለንጉሡም በነገሩት ጊዜ አጽንቶ አሠረውና ልዩ ልዩ በሆነ በጽኑ ሥቃይ አብዝቶ ያሠቃየው ዘንድ ለመኰንኑ ሰጠው መኰንኑም እንዲህ አለው "ለንጉሥ ለምን አትሠዋም" የከበረ ቴዎድሮስም "እኔስ ለረከሱ አማልክት አልሠዋም ለከሀዲ ንጉሥም አልታዘዝም" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከወንበሩ ላይ ተነሥቶ እንደ ነብር ተወርውሮ አንገቱን አነቀውና የከበረ ቴዎድሮስን በምድር ላይ ጥሎ ፊቱን ጸፋው በእግሮቹም ረገጠው እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ላከለት መኰንኑንም ገድሎ ከምድር ዐዘቅት አሠጠመው ለከበረ ቴዎድሮስም በእስያ አገር ውስጥ እየተዘዋወረ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስን ሃይማኖት እንዲአስተምር መንፈሳዊ ፀዓዳ ፈረስ ሰጠው። ንጉሡም ይህ በሰማ ጊዜ የከበረ ቴዎድሮስን ከነፈረሱ እንዲይዙት በትምህርቱም የአመኑትን ሁሉ እንዲገድሉ መቶ ፈረሰኞች ወታደሮቹን ላከ። ከሴቶችና ከልጆች በቀር ስድስት ሺህ አርባ ስምንት ሰውን ገደሉ። ሊይዙትም ወደ ቅዱስ ቴዎድሮስ በደረሱ ጊዜ ፈረሱ በላያቸው ተወረወረ ከአፉም እሳትን አውጥቶ አመድ እስኪሆኑ አቃጠላቸው ነገር ግን ሌሎች አግኝተው ያዙትና ወደ ንጉሥ ወሰዱት እርሱም ወደ እሥር ቤት እንዲአስገቡት እንዳይበላና እንዳይጠጣም ደጃፎችን እንዲዘጉበት አዘዘ። ❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጸለትና ቃል ኪዳን ሰጠው በዚያንም ጊዜ ከእሥር ቤት አውጥተው ዘቅዝቀው ሰቀሉት ደሙ እንደ ውኃ እስቲፈስ ከላም ቆዳ በተሰራ ጅራፍ ገረፉት ደሙ የነካቸውም ብዙ በሽቶኞች ዳኑ ተዓምራቱንም ያዩና የሰሙ በጌታችን አመኑ በዚያችም ቀን መቶ አርባ ስምንት ሰዎች ተገደሉ። እሊህን የተገደሉትንም ሰማዕታት ወደ እሳት ማደጃ ውስጥ ከእርሱ ጋር ጨመራቸው በዚያንም ጊዜ ነፋስ ነፈሰ መብረቅና ነጐድጎድም ሆነ እሳቱንም አቀዝቅዞት የከበረ ቴዎድሮስ ምን ሳይነካው ከእሳት ውስጥ ወጣ። ❤ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የሚያደርግበትን በአጣ ጊዜ ኃምሳ አራት ልጥር የሚመዝን ልጓም አምጥተው አፉን እንዲለጒሙት እግሮቹንና እጆቹንም በችንካር ቸንክረው ለአንበሳ እንዲጥሉት አዘዘ። አንበሳውም እንባውን እያንጠባጠበ እንደ ሰው አለቀሰለት እንጂ ምን አልነካውም ጌታችንም ተገለጠለትና ስሙን ለሚጠራ፣ መታሰቢያውን ለሚያደርግ፣ ገድሉንም ለሚጽፍ እድል ፈንታውም ከእርሱ ጋር በመንግሥተ ሰማያት ያደርግ ዘንድ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ የሁለት መቶ ሰው ሸክም እንጨት፣ መቶ ልጥር ባሩድ፣ መቶ ልጥር የዶሮ ማር፣ መቶ ልጥር ነሐስ አመጡ ከማንደጃውም ጨምረው እጅግ እስከሚግል አነደዱት ጸሎቱንም ከፈጸመ በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስን ወደ ነደደው እሳት ወረወሩት ምስክርነቱንም የካቲት28 ፈጸመ። ❤ የመላእክት አለቆች ቅዱስ ሚካኤልና ቅዱስ ገብርኤል ነፍሱን ተቀበሉት በሦስት አክሊላትም አቀዳጁት ሥጋውንም አውሳብያ የተባለች የመኰንኑ ሚስት ወሰደች ዋጋው ብዙ በሆነ ሽቱም ገነዘችውና ወደ ገላትያ ወሰደችው በዕብነ በረድ ሣጥንም አድርጋ በዚያ ቀበለችው ቤተ ክርስቲያንም ሠራችለት ከሥጋውም ታላላቆች ድንቆች ተዓምራቶች ተገለጹ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቴዎድሮስ በጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላላሙ አሜን። ምንጭ፦ የካቲት 28 ስንክሳር።                                                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለክሙ_አምዓት_ስሳ። ወበበዐሠርቱ ሠላሳ #ማኅበራነ_ቴዎድሮስ_ማር_መኵሴ_ቴዎድሮስ ዕጓለ አንበሳ። እምኂሩትክሙ ብየ ኃሠሣ። ታናሕስዩ ሊተ ክቡደ አበሳ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_28።                               ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ዘሠርዓ ለአብርሃም። ወመሐለ ለይስሐቅ። ወአቀመ ስምዐ ለያዕቆብ"። መዝ 104፥9። የሚነበቡት መልዕክታት ዕብ 11፥8-22፣ ያዕ 3፥1-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 7፥1-17። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 20፥37-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።                   

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን #በታላቁ_በቈስጠንጢኖስ_ዘመን ለነበረ ለከበረ አባት ለአንጾኪያ አገር ሊቀ ጳጳሳት ትምህርቱ በዓለም ለመላ ቁጥሩ #ከሠለስቱ_ምዕት ለሆነ #ለታላቁ_አባት_ለአባ_አንስጣስዮስ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ #ከቸሩ_መድኃኔዓለም_ከስቅለቱ መታሰቢያ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                                                         ✝ ✝ ✝ ❤#አባ_አንስጣስዮስ፦ ይህንንም ቅዱስ የከበሩ አባቶቻችም በኒቅያ ከተማ የአንድነት ስብሰባ በአደረጉ ጊዜ በዚህ ጉባኤ ከተሰበሰቡ ሊቃውንት አንዱ እርሱ ነው፡፡ በዚህም ጉባኤ ተስማምተው አርዮስን ከባልንጀሮቹም የቂሣርያ አውሳብዮስ የኒቆምድያ አውሳብዮስና አርናሲስ ናቸው። እሊህም፡ በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ ታውቀዋል እሊህም የከበሩ አባቶችም ሥርዓትን ሠርተው ወደ የአገራቸው በተመለሱ ጊዜ እሊህ ከኤጲስቆጶስነት ሹመት የተሻሩት ከሃድያኑ ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄዱ መስለው ወጡ ወደ አንጾኪያም ከተማ በአንዲት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሰበሰቡ፡፡ ብዙ ገንዘብም ሊሰጧት ቃል ገቡላት ወደ ቤተ ክርስቲያን እንድትገባ ይህ አባት ከእርሷ ጋር እንዳመነዘረ የወለደችውም ልጅ የእርሱ እንደሆነ በዚህ ቅዱስ አባት አንስጣስዮስ ላይ ለካህናቱና ለሕዝቡ እንድትናገር አስተማሩዋት። ሕዝቡም እንዲህ አሏት "አንቺ ሐሰተኛ ነሽ በዚህ ቅዱስ አባት ላይም ሐሰት ተናግረሻል፣ በከበረ ወንጌል ካልማልሽ በቀር ቃልሽን አንቀበልም" አሏት፡፡ እርሷም ስለገንዘብ ፍቅር በሐሰት ማለች፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ከሀድያኑ ለንጉሥ ነግረው ከመንበረ ሢመቱ ወደ አጥራክያ ደሴት አሳደዱት በስደትም ሳለ በርሷ የካቲት27፡ ዐረፈ፡፡ ነገር ግን ለእሊህ ከሃድያን ወዮላቸው የእግዚአብሔርን ልጅ ከመለኮቱ ባሕርይ ለይተው "ፍጡር ነው" ብለውታልና ይህንንም ንጹሕ አባት ሰይጣን አባታቸው እንዳስተማራቸው ከአመንዝራ ጋር አንድ ሁነው በተንኰል ከመንበረ ሢመቱ አውጥተውታልና። እግዚአብሔር ግን ቸለል አላለም ይህን አባት ከአሳደዱት በኋላ ያች አመንዝራ ሴት ጭንቅ በሆነ ደዌ ተይዛ ብዙ ተሠቃየች ለሞትም ተቃረበች ያን ጊዜም ይህ ሁሉ መከራ የደረሰባት በከበረ ወንጌል በሐሰት ስለማለች እንደሆነ ተገነዘበች፡፡ በአንጾኪያም ሰዎች ሁሉ ፊት በደሏን አመነች፡፡ እንዲህም አለቻቸው "ይህ ቅዱስ አንስጣስዮስ ከዝሙት ንጹሕ ነው፣ እነዚያ ከሀድያን ብዙ ገንዘብ ሰጥተውኝ በእርሱ ላይ ሐሰት እንድድናገር በከበረ ወንጌልም በሐሰት እንድምል አደረጉኝ እንጂ"፡፡ ❤ የአንጾኪያ አገር ሰዎችም ኃጢአቷን ማመኗን በሰሙ ጊዜ እጅግ አዘኑ፡፡ ካህናቱም በጸሎትና በቅዳሴ ጊዜ ስሙን የሚያነሱ ሆኑ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም አመሰገነው በመታሰቢያውም ቀን ስለእርሱ ብዙ ቃላትን ደረሰ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አንስጣስዮስ ጸሎት ይማረን በረከትም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፥ የካቲት 27 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_እብል_አንስጣስዮስሃ_ፍጹመ። ትምህርታቲሁ፡ ዘመልዐ ኲሎ ዓለም። እኩያን ዕደው እለ ተዓጽፋ መርገመ። ነገረ ሐሰት ላዕሌሁ እንዘ ይነቡ ሕሱመ። ኀበ ሰደድዎ አዕረፈ ወኖመ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_27።                                ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የማኅሌት_ምስባክ፦ "ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን። ወአኃዙኒ ማኅበሮሙ ለእኩያን። ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ"። መዝ 21፥16-17። የሚነበበው ወንጌል ማር 15፥22-28።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_የቅዳሴ_ምስባክ፦ "እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም። ወገብረ መድኃኒት በማእከለ ምድር። አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ"። መዝ 73፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 6፥5-12፣ 1ኛ ጴጥ 2፥21-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 10፥36-44። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ19፥16-25። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የአቡነ ዓምደ ሥላሴ የዕረፍት በዓልና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።                 

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤            ❤ #የካቲት ፳፯ (27) ቀን። ❤ እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ታላቁን ገዳም #ማኅበረ_ሥላሴ_ለመሰረቱና እንደ መሶበ ወርቅ ከፍ አድርገው ላስባረኩ፤ #ንጉሥ_ሱሱንዮስ የካቶሊክን እምነት በተቀበለ ጊዜ ምላሱ ተጎልጉሎ የነበርው በመስቀላቸው ባርከው ለፈወሱት ለታላቁ አባት #ለአቡነ_ዓምደ_ሥላሴ ለዕረፍት በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #አቡነ_ዓምደ_ሥላሴ (ጎጃም)፦ የትውልድ አገራቸው ጎጃም ሲሆን በአጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ዘመን የነበሩ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደርጉ የነበሩ ገዳማዊ መነኵሴ ናቸው፡፡ ጻድቁ ማኅበረ ሥላሴን ያቀኑ ታላቅ አባት ሲሆኑ በተለይም አንድ የሚታወቁበት ትልቅ ታሪክ አላቸው፡፡ እርሱም አጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ካቶሊካውያን ደግፈው 8ሺህ የአገራችንን ሊቃውንት በአንድ ቀን ባሳረዱ ጊዜ ንጉሡ ወዲያው "ኦርቶዶክስ ይርከስ ካቶሊክ ይንገስ" ብሎ ያወጀበት ምላሱ ተጎልጉሎ ወጣ፡፡ እንደ አርዮስም ሆዱ አብጦ አንጀቱ ተልቶ ሊሞት ባለ ሰዓት አቡነ ዓምደ ሥላሴ አዘዞ ድረስ ሄደው "ፋሲል ይንገሥ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት ትመለስ የሱስንዮስም ምላስ ይመለስ" በማለት ተጎልጉሎ የወጣውን ምላሱን በመስቀላቸው ቢባርኩት ምላሱ ተመልሶለታል፡፡ ❤ አጤ (ዐፄ) ሱስንዮስ ግን ለካደበት ክህደት ቅጣቱ ነውና በመቅሰፍቱ ሳይድን በዚያው ታሞ ማቆ ማቆ ክፉ አሟሟት ሞቷል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ዓምደ ሥላሴ የአጤ (ዐፄ) ፋሲልን ሹመትና ሃይማኖትን በአዋጅ፡አጽንተው ተመልሰው ወደ ገዳማቸው ማኅበረ ሥላሴ ገዳም ገብተዋል፡፡ አጤ (ዐፄ) ፋሲልንም የማኅበረ ሥላሴን ገዳም ግዛቱን ከሱዳን እስከ ጣቁሳ ድረስ እንዲሆን በአዋጅ ወስነው ሰጥተውት ነበር ነገር ግን ላይጠቀምበትና ላይጸና ነገር የደርግ መንግሥት የገዳሙን ሥርዓት ከማፍረሱም በላይ ርስት ጉልቱን ነጥቆ ወሰደበት፡፡ ❤ በደርቡሾች ወረራ ጊዜ እንግሊዞች አጋጣሚውን ተጠቅመው የአቡነ ዓምደ ሥላሴን ቅዱስ ገድል ዘርፈው ወስደውታል፡፡ ዛሬ፡ በእንግሊዝ አገር ገድለ አቡነ ዓምደ ሥላሴ ይገኛል፡፡ ጻድቁ የካቲት27 ቀን ያረፉ ሲሆን ዐፅማቸው በዚያው በመሠረቱት በማኅበረ ሥላሴ ገዳም በክብር ተቀምጧል፡፡ ከአቡነ ዓምደ ሥላሴ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን።                 

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ  አሜን"። ❤             ❤ #የካቲት ፳፮ (26) ቀን። ❤ እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቀ_ነቢያት ለአንዱ ዖዝያ ይባል ለነበረው ለዕውነተኛ #ለቅዱስ_ሆሴዕ ለዕረፍቱ በዓልና ለከበሩ #ለቅዱሳን_ሳዶቅና ከእርሱ ጋር ሰማዕትነት ለተቀበሉ #ሁለት_ሺህ_ስምንት ሰዎች ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።                               ✝ ✝ ✝ ❤ ነቢዩ ቅዱስ ሆሴዕ፦ ዳግመኛም ይህ ነቢይ በአራቱ የይሁዳ ነገሥታት ዘመን ትንቢት ተናገረ። እሊህም ዖዝያን፣ ኢዮአታም፣ አካዝና ሕዝቅያስ ናቸው። በትንቢቱም ድንቆች ሥራዎችን ተናገረ የእስራኤል ልጆች ገሠጻቸው "የአመንዝራ ልጆች" ብሎም ጠራቸው እግዚአብሔርም ቊጣውን ከእርሳቸው እንደማይመለስ አሰረዳቸው። እንዲህም አለ "የእስራኤል ልጆች ቊጥራቸው እንደማይሠፈርና እንደማይቆጠር የባሕር አሸዋ ቢሆን ከጥቂት በቀር አይተርፍም" አለ። ❤ ስለ አሕዛብም በእግዚአብሔር ማመን ተናገረ እንዲህም አለ "እኔ ወገኖቼ ያልሆኑትን እጠራቸዋለሁ እነርሱም ይሰሙኛል። ዳግመኛም ስለ መድኃኒታችን መከራ መቀበልና በደሙ ስለ መዳናችን ስለ ትንሣኤውም እንዲህ ብሎ ተናገረ "እሱ በመከራ ገርፎ ያድነናል እርሱም በመከራ አቊስሎ ይቅር ይለናል ሲያድነንም በሁለተኛው ቀን ነው በሦስተኛውም ቀን ድነን በእሱ ፊት እንነሣለን" እግዚአብሔርንም አውቀን እንከተለው ዘንድ ስለ ሞት ሥልጣን መሻር ስለ መቃብርም መሸነፍ እንዲህ ብሎ ትንቢት ተናገረ "ሞት ይዘህ ማስቀረትህ መቃብርስ ድል መንሳትህ ወዴት ነ" ትንቢትን እየተናገረ ሰባ ዓመት ያህል ኑሮ በበጎ ሽምግልና የካቲት26 ቀን ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሆሴዕ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ ቅዱስ ሳዶቅ፦ ይህንንም የከበረ ሳዶቅን ለፀሓይ ይሰግድ ዘንድ የፋርስ ንጉሥ ብርህም ፈለገው ቅዱሱም "ለፈጣሪዋ እንጂ ለዚች ለምትታይ ፀሓይ ልሰግድ ከእናቴ ማኅፀን አልወጣሁም" ብሎ መለሰለት። ብርህም ንጉሥም መልሶ "ለዚች ፀሓይ አምላክ አላትን" አለው ቅዱስ ሳዶቅም "ዓለሙን ሁሉ የፈጠረ ክርስቶስ አምላክ ነው" አለው። ንጉሡም የቅዱስ ሳዶቅን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የከበረ ሳዶቅም ቁሞ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፡፡ ❤ ከዚህም በኋላ ራሱን ዘንበል አድርጎ ቆረጡት። ያን ጊዜ ከሰማይ ብርሃን በላዩ ወረደ ከዚያ ያሉትም ሁሉ አይተው "እኛ ሁላችንም በቅዱስ ሳዶቅ አምላክ የምናምን ክርስቲያን ነን" ብለው ጮኹ ንጉሡም ሁሉንም ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ ቊጥራቸውም ሁሉት ሺህ ስምንት ነፍስ ናቸው። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት26 ስንክሳር።                            ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለሆሴዕ_ምጽአተ_ክርስቶስ እንዘ ይስብክ። በቃለ ትንቢት ቡሩክ። የኀሥሥዋ ይቤ #ለእግዚአብሔር_አምላክ። እንበለ ንጉሥ ወኢ #መልአክ። እምድኅረ ነበሩ እስራኤል በበክ"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_26።                            ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ወይርአዩ አሕዛብ በቅድመ አዕይንቲነ። በቀለ ደሞሙ ለአግብርቲከ ዘተክዕወ። ይባእ ቅድሜከ ገዓሮሙ ለሙቁሓን"። መዝ 78፥10-11። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 9፥24-30፣ 2ኛ ጴጥ 1፥19-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 3፥17-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥36-ፍ.ም። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።                   

❤ በዋሻው ደጃፍ የውኃ ምንጭ ነበረ ምሳርንም ወረወረበት ምሳሩም ነቢይ ኤልሳዕ እንዳደረው በውኃ ላይ ተንሳፈፈ። የከበረች አርባ ቀንን ጾም ከሦስት ቀኖች፡በቀር ሳይበላ ፈጸመ። ሲባልም ሲያንቀላፋም ግድግዳ ተጠግቶ ነው እግሮቹም እንደ ዝሆን እግር እስከሚሆን እንዲህ ተጋደለ። ❤ በአንዲትም ዕለት ለደቀ መዛሙርቱ "እንሆ ዓለም አለፈ" አላቸው በጠየቁትም ጊዜ "ንጉሥ ቴዎዶዮስ ሞተ" አለ። በአንዲትም ዕለት ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር የያዘ እንግዳ በአንድ ቄስ ቤት አደረ በተኛ ጊዜ ስለ ገንዘቡ ቄሱ ገደለውና ወስዶ ከአንድ መነኵሴ ደጅ ጣለው ለቅዱስ አቡፋናም በነገሩት ጊዜ ከሟቹ ላይ እንዲጥሉት ቆቡን ሰጣቸው ሲጥሉትም ሟቹ ተነሣ ስለ ገንዘቡ ቄሱ እንደ ገደለው ነገራቸው እጅግም አደነቁ። ❤ በአንዲትም ዕለት አንድ ሰው ቡራኬ ሊቀበል ወደርሱ ሲመጣ ልጁ በጒዞ ላይ ሞተ ልጁንም ተሸክሞ ወደ ቅዱስ አቡፋና ሔደ በፊቱም ሰግዶ ተባርኮ ተመለሰ ያን ጊዜ የሞተው ብላቴና ተነሥቶ አባቱን ተከተለው። ከቆመ ጀምሮ ዐሥራ ስምንቱ ዓመት በተፈጸመ ጊዜ ዕረፍቱን አውቆ ቅዱስ ቊርባንን ተቀበለ ወደ መኖሪያውም ሒዶ ራሱን ዘንበል አድርጎ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ የካቲት25 ሰጠ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ አቡናፋር በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የየካቲት 25 ስንክሳር።                             ✝ ✝ ✝ ❤ "#ሰላም_ለክሙ_ቶና_ዲያቆን። #ወሚናስ_ብፁዕ ሠናየ አሚን። #ወይልማድዮስ ነሣኢ አክሊለ ግዕዛን። ሀቡኒ አጋእዝትየ ለብእሲ ምስኪን። ዕሴተክሙ ዘኢርእየ ዐይን"። #ሊቁ_አርከ_ሥሉስ (አርኬ) #የየካቲት_25።                             ✝ ✝ ✝ ❤ #የዕለቱ_ምስባክ፦ "ጸገብነ እግዚኦ እምበረከተ ቤትከ። ቅዱስ ጽርሕከ ወመንክር በጽድቅ። ስምዐነ አምላክነ ወመድኃኒነ"። መዝ 64፥4-5። የሚነበቡት መልዕክታት  ፊሊ 1፥1-13፣ 2ኛ ጴጥ 1፥10-15 እና የሐዋ ሥራ 9፥1-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 9፥12-17። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም በዓልና የጾም ወራት። ለሁላችንም ይሁንልን።                  

❤ "በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤             ❤ #የካቲት ፳፭ (25) ቀን። ❤ እንኳን ለከበሩ #በቅዱስ_ጳውሎስ ትምህርት ላመኑ #ለቅዱሳን_አውሳንዮስ_ፊልሞ፣ ለድንግል #ቅድስት_ሉቅያ ሰማዕትነት ለተቀበሉበት ለዕረፍታቸው በዓል፣ ለከበረ #ሐዲስ_አባ_እንጦኒ ይህም ረውሕ ለሚባለው ሰማዕትነት ለተቀበለበት ለዕረፍቱ በዓልና ከግብጽ አገር ከእስሙናይን አውራጃ ለሆነ ዐሥራ ስምንቱ ዓመት ቆሞ ሳይቀመጥ ለጸለየ #ለአባ_አቡፋ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከሮሜ አገር #ከዲያቆን_ቶና ከአገረ ቊስ #ሚናስ_ከጋዛ_ይልማድዮስ በሰማዕትነት ከዐረፉ፣ #ከደማይልናልና_ከርጊኖስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ  ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።                              ✝ ✝ ✝ ❤ #የከበሩ_ቅዱሳን_አውሳንዮስ_ፊልሞና_ሉቅያ፦ እሊህ ቅዱሳንም በአፍራቅያ አገር ሳለ በከበረ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ትምህርት ያመኑ ናቸው ከሀድያንም ዝሑራ በሚባል ኮከብ ስም ለሚጠሩት ለአርታዳሚ ጣዖት በዓልን በአደረጉ ጊዜ አይተው በስሕተታቸው ሊዘብቱ እሊህ ቅዱሳን ተስብስበው ወደ ጣዖቱ ቤት ገቡ ሰዎችም ለጣዖቱ ሲሠዉና ከፍ ከፍ ሲያደርጉት በአዩአቸው ጊዜ በክብር ባለቤት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር እሳትነት ልባቸው ነደደ ከጣዖቱም ቤት ወጥተው ወደ ክርስቶሳዊት ቤተ ክርስቲያን ሔደው የክብር ባለቤት የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብሩንና ልዕልናውን አብዝተው አመሰገኑ። ከዚያ ካሉት አንድ ሰው በሰማቸው ጊዜ በጣዖታቸው ላይ እንደ ዘበቱ የተናገሩትን ልብ ብሎ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀላቸው መኰንኑም በፈረስ ተቀምጦ ሔደ ከወታደሮቹም ጋር ቤተ ክርስቲያኒቱን ከበባት ከምእመናንም ሰዎች የሸሹ አሉ። ❤ እሊህም ሦስቱን ቅዱሳን ያዛቸው የብረት ዘንጎችን በእሳት አግለው ቅዱሳኑ ጐኖች ውስጥ አደረጉት ከዚህም በኋላ የከበረ አውሳንዮስን ወደ ጒድጓድ ወረወሩትና ነፍሱን እስከ ሰጠ ድረስ በድንጊያ ወገሩት። የከበረ ፊልሞናንና የከበረች ሉቅያን ግን ብዙ ጊዜ በጸና ሥቃይ ያሠቃዩአቸው ጀመር ነፍሳቸውንም ይወስድ ዘንድ እግዚአብሔርን ለመኑት እርሱም ልመናቸውን ተቀብሎ ነፍሳቸውን የካቲት25 ወሰደ። በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ እንሆ የምስክርነታቸውና የሃይማኖቻቸው መታሰቢያ ተጽፎአል። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን።                                  ✝ ✝ ✝ ❤ #ሐዲስ_አባ_እንጦኒ (ረውሕ)፦ ይህም ከከበሩ ዐረቦች ወገን የቆሮስ ሰው የሆነ ብዙ ገንዘብ ያለው ነው በሰማዕታት አለቃ በቅዱስ ቴዎድሮስ ገዳም አጠገብ በወንዝ ዳርቻ የሚኖር ነው። ይህም ጐልማሳ አብያተ ክርስቲያናትን የሚቃወም ሁኖ ቅዱስ ቊርባንን በመስረቅ ኅብስቱን ይበላዋል የከበረ ደሙንም ከጽዋው ውስጥ ይጠጣል የመሠዊያውንም ልብስ ገፎ በእሳት ያቃጥለዋል በክርስቲያን ሃይማኖትም ላይ ይዘብታል። መኖሪያው ቤቱ በከፍታ ቦታ ላይ ስለ ሆነ ካህናት ሲያገለግሉ ይታዩት ነበር። ❤ በአንዲትም ዕለት በቅዳሴ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን ተከፍቶ አየ በፈረስም ተቀምጦ መጣ የቅዱስ ቴዎድሮስንም ሥዕል ተመልክቶ በፍላፃዎች ወጋው። አንዲቱም ፍላፃ ተመልሳ መሐል እጁን ነደፈችው በጭንቅም ከእጁ ላይ መዘዛት ይህንንም ለማንም አልነገረም። በሌላዪቱም ዕለት በወንበሩ ላይ ተቀምጦ ሳለ መሥዋዕትን ተሸክመው ወደ መቅደስ ሲገቡ ካህናትን አያቸው በጻሕሉም ውስጥ ነጭ በግ ተኝቶ ከበላዩ ነጭ ርግብ ሲጋርደው በቅዳሴውም ፍጻሜ ያ በግ በየመለያያው የተከፋፈለ ሆኖ ካህናቱም ከተከፋፈለው ሥጋውን ሲቀበሉ ደሙንም ከጽዋው ውስጥ ሲቀበሉ አየ እጅግም አደነቀ። በልቡም የክርስቲያን ሃይማኖት እጅግ ድንቅ ነው በእውነትም የከበረ ክቡር ነው አለ። ዳግመኛም ያ በግ ተመልሶ እንደ ቀድሞው ኑሮው ሕያው ሁኖ አየ ከዚያም በኋላ ከመቀመጫው ወርዶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ሔዶ ያየውን ሁሉ ለካህናቱ ነገራቸው እርሱም ሰምተው ስለዚህ ድንቅ ሥራ ደስ አላቸው። ❤ በዚችም ሌሊት ተግቶ ሲጸልይ ሊቅ ቅዱስ ቴዎድሮስ ተገለጠለት እርሱም በፈረሱ ላይ ተቀምጦ ነበር እንዲህም አለው "እንሆ በእኔ ላይ ሥዕሌን እስከ ወጋህ ድርስ ክፉ ሠራህ በክብር ባለቤት ክርስቶስ ሥጋ ላይም ዘበትክ አሁንም ከክህደትህ ተመልሰህ በክብር ባለቤት በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን" አለው ይህንም ብሎ ከእርሱ ተሠወረ። በማግሥቱም በፈረሱ ላይ ሁኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ወደ ሊቀ ጳጳሳቱም ገብቶ ከእርሱ የሆነውን ሁሉ ነገረው ሊቀ ጳጳሳቱም ሰምቶ እግዚአብሔርን አመሰገነው እርሱንም "በሕዝብ፡ፊት እዳላጠምቅህ እፈራለሁ ነገር ግን ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ሒድ ጌታችን ክርስቶስ የሚያጠምቅህን ይሰጥሃል" አለው። እርሱም ሰምቶ ወደ ዮርዳኖስ ሔደ ወደ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገባ የሌሊቱም እኩሌታ ሲሆን የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ነጭ ሐር ግምጃ ለብሳ ተገለጠችለት ከእርሷም ጋር በንጹሕ ልብስ የተሸለመች ሴት ነበረች በእጅዋም ይዛ አነሣችውና "አትዘን እኔ ካንተ ጋር እኖራለሁና" አለችው። ሲነጋም ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ በሔደ ጊዜ ሁለት ገዳማውያን መነኰሳትን አገኛቸው እነርሱም በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቁት። ስሙንም እንጦንስ ብለው ሰየሙት የምንኵስና ልብስ አስኬማንም አልብሰው በሰላም አሰናበቱት ወደ ደማስቆም ሔደ ወደ ቤቱ ገባ። ❤ ባልንጀሮቹና ወገኖቹም በአዩት ጊዜ "የለበስከው ምንድን ነው አሉት" እርሱም "እኔ ክርስቲያን ነኝ" አላቸው በዚያንም ጊዜ ይዘው በሜዳ ውስጥ እየጐተቱ ወደ መኰንኑ እስኪያደርሱት ይደበድቡት ነበር። መኰንኑም ወደ እስር ቤት እንዲጨምሩት አዘዘ በታላቅ ሥቃይም ዐሥራ ሰባት ሌሊት በዚያ ኖረ እንሆ በላዩ ብርሃን ወረደ እንዲህም የሚል ቃል ሰማ "እንጦንዮስ ሆይ አክሊል ተዘጋጅቶልሃልና አትፍራ" ብርሃንን የለበሱ ሁለት አረጋውያንም መጥተው በራሱ ላይ የብርሃን አክሊል አኖሩ በነጋ ጊዜም ወደ አደባባይ ወስደው ራሱን በሰይፍ ቆረጡትና በዕንጨት ላይ ሰቀሉት። በሌሊትም በላዩ ብርሃን ወረደ ጠባቆችም አይተው ከዕንጨት ላይ አውረዱት በጤግሮስ አቅራብያ ቀበሩት ከመቃብሩም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሐዲስ በአባ እንጦንስ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                                 ✝ ✝ ✝ ❤ #አባ_አቡፋና፦ ይህም አባት ከቶ ብርሃን በሌለበት ዋሻ ውስጥ የሚኖር ሁኖ በየሁለት ቀን ይጾማል የሚበላውም የሚጠጣውም በመለኪያ ተለክቶ ነው በሌሊትም በመዓልትም አምስት መቶ ጊዜ ይጸልያል። በአንደዲትም ዕለት ወንድሞች ሊጐበኙት ወደርሱ መጡ እንጀራንም አጣ ሦስት እንጀራንም በአገኘ ጊዜ ለሃያ ሰዎች አቀረበላቸው እነርሱም በልተው ጠገቡ ተአምራትም እያደረገ በሽተኞችንም እየፈወሰ ኖረ። ❤ ከዚያም በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ "አቡፋና ሆይ ዐሥራ ስምንት ቀረህ" የከበረ አቡፋናም" ዐሥራ ስምንት ዕለታት እንደሆኑ አስቦ እሊህ ዕለቶች እስቲፈጸሙ ቆመ ከዚያም በኋላ ሱባዔዎች ናቸው ብሎ ይህንንም በመቆም ፈጸመ እንደ፡ገና ወሮች ይሆናሉ ቢሆኑስ ብሎ ይህንም በመቆም ሳያጓድል አደረሰ። ዳግመኛም እንዲህ የሚል ቃል ወደርሱ መጣ "አቡፋና ሆይ ዐሥራ ስምንት ዓመት ናትና ጽና በርታ" አለው በዚያንም ጊዜ ፈጽሞ ጸና።