መዝሙር
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 መዝሙር 的分析概览
频道 መዝሙር (@mezmurb) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 11 743 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 7 676,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 966 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 11 743 名订阅者。
根据 06 十一月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 84,过去 24 小时变化为 2,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 32.62%。内容发布后 24 小时内通常能获得 11.59% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 831 次浏览,首日通常累积 1 361 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 0。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“" ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ ተአምራቱንም ሁሉ ተናገሩ።"
(1 ዜና 16: 9)
@biniy27”
凭借高频更新(最新数据采集于 07 十一月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
11 743
订阅者
+224 小时
+17 天
+8430 天
帖子存档
11 743
ተናገር አለኝ ዘምር
ተናገር አለኝ መስክር
ተናገር አለኝ ዘምር
ለቀራንዮ ውለታ አርምሞ የለም ዝምታ
ለመድኃኔዓለም ውለታ አርምም የለም ዝምታ
ሰው አድርጎኝ ሞቶ በደሙ
ኑሮዬን ባርኮት ህመሙ
ሰላም አውጥቶ ካስገባ
ልያዝ ለክብሩ ዘንባባ
ሆሳና ልበል መድኃኒት
ከፍ በልልኝ የኔ አባት
ተጠምተህ እኔ ረካሁኝ
ስራህ ግሩም ነው ደነቀኝ
እጆቹን እዩት በእምነት
ቆሰለ ሊሰጠኝ ህይወት
በዚያ ታትሞ ውበቴ
ኢየሱስ ለኔ ብርታቴ
ከማንም በላይ ከምንም
ለኔ ልዩ ነው ዘላለም
ህይወቴን ለእርሱ አስባርኬ
እኔስ በረታሁ በአምላኬ
የእሾህ አክሊሉ በራሱ
ለእኔ ቤዛነው ሞገሱ
ሞቴን ገድሎታል አባቴ
ሰላሜ እርሱ ነው እረፍቴ
ሰው የመሆኔ ሚስጥሩ
የማይለወጥ ነው ፍቅሩ
የገባኝ እውነት በምድር ላይ
ፍቅር ነው ጌታ ኤልሻዳይ
ክብሩን ለማወጅ ተነሳው
ሲያድነኝ ከሞት እያየው
ገመናን ሸፋኝ ኪዳኔ
ተራበ ውዴ መድኅኔ
ይህ ነው ያቆመኝ በፊቱ
ወሰን የሌለው ምህረቱ
ለዚህ ደግነት ውለታ
ምን ይከፈላል ለጌታ
መዝሙር
👇👇👇👇👇👇👇
👉 @MezmurB 👈
👉 @MezmurB 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
11 743
Repost from መዝሙር
✝ እንባችን ደረቀ ✝
እንባችን ደረቀ ለካስ ያልቃል እንባ
ኃይል አጣን ለኀዘን እረ ወዴት እንግባ
ኤርምያስን እንጥራው ቢያስተምረን ሰቆቃ
መቼ ነው የሚቆመው የምእመናን ሲቃ
አሐዱ አብ ቅዱስ ብሎ የቀደሰው
የካህኑ ደምነው በግፍ የፈሰሰው
ማን ማንን ያጽናና በሁሉም ቤት ለቅሶ
መቼ ነው የምናይ ዕንባችን ታብሶ
ለምን ትተኛለህ ጌታችን ሆይ ንቃ
መገፋት ሥቃዩን አልቻልነውም ይብቃ
የሰማዕታት ደም እንደ ጎርፍ ፈሰሰ
የሰማነው ሁሉ በእኛ ላይ ደረሰ
ኃጢአት በአንድ በኩል ከውስጥ ይወጋናል
ጠላትም ከወጪ ቀስት ያነሣብናል
ከማዕተባችን ጋር በፍቅርህ እሰረን
ከፈተና አታግባን ቢመጣም አስችለን
እኛን ከሞት ይልቅ መካድ ያስፈራናል
ከፈተናም ይልቅ መውደቅ ያስፈራናል
የሠለስቱ ደቂቅ የአርባዕ ሐራ ጌታ
አሁን ድረስልን በአለም አንረታ
ቅዱሳን ሰማዕታት ኢትዮጵያን ክበቡ
በእምነታችን አጽኑን ሳይሰጥም መርከቡ
ጊዮርጊስ ሆይ ድረስ ዛሬም እንደ ጥንቱ
ያንተን ጸሎት አምነን አንቀርም በከንቱ
ዘማሪ ዲያቆን ቀዳሜጸጋ
መዝሙር
👇👇👇👇
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏 @MezmurB 🙏
🙏 @MezmurB 🙏
🙏 @MezmurB 🙏
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
👉 @biniy27 👉 @biniy27
11 743
Repost from መዝሙር
✞ ርግብና ዋኔን ✞
ርግብና ዋኔን
አብረዉ ዘመቱና ዋኔን
ርግብ ደህና ገባች >> /2/
ዋኔን ገደሉና >> /2/
በዘርና ጎሳ ዋኔን
ሠዉ ሁሉ ተከፍሎ >>
ሰይፍንም ጨበጠ >>
ልቦናዉ ቂም አዝሎ>>
ሰላምን የሚያወርድ >>
እንድ የሚያረገንን >>
እባክህን አምላክ >>
ሙሴን አድለን >>
ሠላምህን አብዛ ምድሪቷን አሳርፍ
የቅዱሳን አምላክ በጭንቃችን ድርስ /2/
/አዝ = = = = =
በወገን ላይ ወገን ዋኔን
ይብቃ መነሳቱ >>
ይስፈን በምድር ላይ >>
የእግዚአብሔር መንግስቱ >>
ጦራችን ይሰቀል >>
እንያዝ በገና >>
ሠላምን እናዚም >>
በፍቅር እንፅና >>
ምድሪቷን አሳርፍ ሰላምህም ይብዛ
በአንድነት አኑረን የአለሙ ቤዛ /2/
/አዝ = = = = =
የመርገም ጨርቅ ሆነ ዋኔን
ፅድቃችን በሙሉ >>
አንተን ያልበደለ >>
ማነዉ በዘመኑ>>
አማነዉ በማታ >>
ቀን ያከበርነዉን >>
የኛ ስራ ሆኗል >>
መክሰስ የበቃው >>
ፍቅር ባትሆን ኖሮ ባያቅትህ መጥላት
አይታይም ነበር የሰዉ ልጅ በህይወት
መዝሙር
👇👇👇👇👇👇👇
👉 @MezmurB 👈
👉 @MezmurB 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
11 743
"ኀበ ማርያም "
ኀበ ማርያም ድንግል
በእንተ ፍልሰተ ዐፅሙ
ጸለየ እነዘ ይብል ጊዮርጊስ ቀዲሙ
ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ
አዝ…..
ከሥጋ ፍቃድ ለመራቅ
ወደርስት ሀገር ለመድረስ (2)
ርግበ ገሊላዋ ማርያም
ዖፈ ከራዲዮን ጊዮርጊስ (2)
አዝ…..
በመከራ ጌጥ ተሸልሞ
የግፍ ጽዋን ለሚቀምስ (2)
እመ ሰማዕታት ማርያም
መክብበ ሰማዕት ጊዮርጊስ (2)
አዝ……
ሰባ ነገሥታት ፊት ቆሞ
ስቃይ መከራን ቢታገስ(2)
ቀጸላ መንግስቱ ማርያም
የጽጌ አክሊል ለጊዮርጊስ(2)
አዝ…..
ከድራጎን አፍ ለመትረፍ
ከድል ነሺዎች ለመድረስ (2)
የመለኮት ዙፋን ማርያም
ባለ ነጭ ፈረስ ጊዮርጊስ(2)
አዝ….
በነፍስ ዝለን እንዳንወድቅ
ከክብራችንም እንዳንረክስ (2)
አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም
ፍጡነ ረድኤት ጊዮርጊስ(2)
አዝ…..
ስዕሏ ከስዕሉ ጋር
ባንድ ተስሎ የሚቀድስ (2)
ሰዋሰው ነፍሰ ማርያም
ተንከተ መድሒን ጊዮርጊስ (2)
አዝ….
ፍልሰተ ህሊና እንድናገኝ
የሀገር አንድነት እንዳንፈርስ (2)
የአስራት ርስት ለማርያም
ገበዘ ኢትዮጵያ ጊዮርጊስ (2)
መዝሙር
👇👇👇👇👇👇👇
👉 @MezmurB 👈
👉 @MezmurB 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
11 743
✝✝✝ ያዳነኝን አውቀዋለሁ ✝✝✝
ያዳነኝን አውቀዋለሁ የሞተልኝ ኢየሱስ ነው
ስለሌኝለኝ የምከፍለው ስጦታዬም ምስጋና ነው
ጨለማዬን አስወግዶ ያበራልኝን አውቃለሁ
ሙሉ ሰው ነኝ ከእንግዲስ ስከተለው እኖራለው
የብርሀኔን ልዩ ውበት ፊት ለፊቴ ቆሞ አየሁት
ፍቅሩ ማርኮኝ በመቅደሱ ሰገድኩለት አመለኩት
ላመስግነው (3) ፍቅሩ ማያልቅ ነው
አሳደረኝ በእቅፉ መጠውለጌን አለምልሞ
በመስቀል ላይ ተሰቀለ ደንኩኝ እኔ እርሱ ታሞ
በማይዝለው ክንዶቹ ላይ እኔን በክብር አያኖረ
እንዲመቸኝ ዝቅ ብሎ በበረት ውስጥ እርሱ አደረ
ላመስግነው (3) ፍቅሩ ማያልቅ ነው
ቅኔ ባፈስ ምን ይደንቃል ደሙን በመስቀል አፍስሶ
ስለ ልጁ መዳን ብሎ ነፍሱን ሳይቀር ለኔ ክሶ
ፍቅር ይዞት ከፀባኦት በትህትና ወቶ ወርዶ
ተቀደስኩኝ በነጩ በግ ቀራንዮ ጌታ ታርዶ
ላመስግነው (3) ፍቅሩ ማያልቅ ነው
አክሊለ እሾህ አጠለቀ ግርማ ክብሩን ሁሉን ትቶ
አሻገረኝ ወደ ክብሬ በቅዱስ ደም እኔን ዋጅቶ
አጎንብሶ ቀና አረገኝ ፌቴን በፅድቅ እያበራ
እኖራለሁ ለዘላለም ካከበረኝ ጌታ ጋራ
ላመስግነው (3) ፍቅሩ ማያልቅ ነው
መዝሙር
👇👇👇👇
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🙏 @MezmurB 🙏
🙏 @MezmurB 🙏
🙏 @MezmurB 🙏
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
👉 @biniy27 👉 @biniy27
11 743
እኔ ሆንን
አለውቅህም ብዬ በሰው ፊት የምክድህ
ለጠላት አንስቼ አሳልፌ ምሰጥህ
እኔ ሆንን ጌታ ሆይ እኔ ሆንን
እኔ ሆንን አምላክ ሆይ እኔ ሆንን
ይሁዳ ነኝ ወይስ ጴጥሮስ ሐሙስ ማታ እኔ ማነኝ
የዛሬን መቆሜን እንጂ አለውቅም መጨረሻዬን
እወድሃለሁ ብዬ የዛሬን እናገራለሁ
አላውቅህም አንዳልልህ ስለነገ ግን እፈራለሁ
ስንት ያጥቢያ ኮከቦች ለአንተ ዘምረውልህ ወደቁ
በሰማይ መቅደስህ አጥነው በትዕቢት ረግፈው አለቁ
እፈራለሁ እኔም ለራሴ መንገዴን ንገረኝ ጌታ
ጠዋት በዘመርኩበት አፍ እንዳልሳደብ በማታ
ሳጥናኤል መልአክ ነበረ ይሁዳም ሐዋርያ
ንስጥሮስም ጳጳስ ነበር አርዮስም ባለሞያ
እነዚህ ሁሉ ከወጡ ከአምላካቸው ጉያ
ደካማ ለሆንኩትማ የት ይሆን የኔ መገኛ
ታናሹን ጅማሪዬን አንተው ታላቅም አድርግልኝ
ነበረች ከሚባል ፈተና አንተው በፍቅርህ አድነኝ
ያስጀመርከኝ አምላክ ሆይ እንግዲህ መንገዴን አደራ
በፊትህ ቆሜ ለማመስገን አብቃኝ ከቅዱሳን ጋራ
መዝሙር
👇👇👇👇👇👇👇
👉 @MezmurB 👈
👉 @MezmurB 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
11 743
መድኃኔዓለም
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አማኑኤል የለም የሚሳነው
እርሱ ቃል ሲናገር ተራራው ሜዳ ነው
መድኃኔዓለም የለም የሚሳነው
አዝ
አላስብም አልፈዋለሁ ብዬ
ጉንጭ አልፎ ትራሴን እያጠበ እንባዬን
እየተፈጸመ ኃይሉ በድካሜ
ማእበሉን አለፍኩኝ ቀለለልኝ ሸክሜ
አዝ
የቤቴ እራስ ነው የእቅዴ መሪ
በክፉም በደጉም ነፍሴን አስተማሪ
ፈጥሮ የማይረሳኝ ቤዛዬ ደረሰ
ቤቴን ደስታ ሞላው እንባዬ ታበሰ
አዝ
ትናንት ባዶ ነበር የለኝ የሚሰፈር
አንዳች አልነበረኝ የሚታይ የሚቆጠር
ከርሱ የተነሳ ዛሬ ግን ሙሉ ነኝ
ክብር ለእርሱ ይሁን አለ የማያተወኝ
አዝ
እየከለከለ ለእኔ ማይጠቅመኝን
በጊዜ እየሰጠ ደግሞ የሚረባኝን
ሁሉ በእርሱ ሆኗል አልሆነም ያለ እርሱ
ውዳሴ ምስጋና ይድረስ ለንጉሱ
መዝሙር
👇👇👇👇👇👇👇
👉 @MezmurB 👈
👉 @MezmurB 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
11 743
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
አለምና መላው ያንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ ያንተው አይደለም ወይ
አዝ
ኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ሥሉስ ያሉህ
መላዕክት በራማ የሚያመሰኑህ
ድንቅ መካር ኃያል ኤልሻዳይ ነህና
ትንቢያ ነኝ ምን ልስጥህ ምንስ አለኝና/2/
አዝ
ቅዱሱን መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ
ምን ይዤ ልምጣና በአምላኬ ፊት ልስገድ
ወደ ላይ በሰማይ ወደ ታች በጥልቀት
አምላኬ የት አለ የማትገኝበት
ጌታ ሆይ የት አለ የማትገኝበት
አዝ
በኪዳን በፀሎት ቅዳሴ ሰዓታት
አንተ የሰጠኸኝ የመንፈስ ቅዱስ ሀብት
መልሰን ወደ አንተ ብንሰጥ ምን አለ
ተወው ጉዳችንን ስስታችን ይኸው(2)
አዝ
ሀብትና ንብረቴስ ጉልበቴስ ምንድነው
ጤናዬ የሰጠኝ ከአንተ በቀር ማነው
በሰጠኸኝ እድሜ በሕይወት ዘመኔ
ከገላዬስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ
ከአካላቴስ ቢሆን የትኛው ነው የኔ
መዝሙር
👇👇👇👇👇👇👇
👉 @MezmurB 👈
👉 @MezmurB 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
11 743
ሰረገላዎችህ
ሰረገላዎችህ የእሳት ናቸው
የሌጌዎን ጭፍሮች ማይችሏቸው
የገሀነም ደጆች ማይችሏቸው
አንተ ብቻ ቅዱስ ሀያል ጌታ
ሳመልክህ እኖራለሁ ጠዋት ማታ/2/
በእሳት ሰረገላ ታጥሮአል መንደራችን
ጊያዝ ሆይ አትፍራ አለ ፈጣሪያችን
የጠላትን ምሽግ በቃሉ ይቆርጣል
ከእኛ ጋራ ያለው ከነሱ ይበልጣል
ከቴማን ተራራ ከፋራን ሲወርድ
ጠላት ይጨነቃል በድምጹ ሞገድ
ጦረኛ አያበዛም ሞአብን ሲመታ
በአህያ መንጋጋ ሺውን ጥሏል ጌታ
የጥልቁን መሰረት በንፋስ አስሮታል
ከሰማያት በላይ ዙፋኑን ዘርግቷል
ዘንባባ ይዛችሁ ግቡ ከመቅደሱ
በምስጋናው ስርአት እንድትቀደሱ
ወደረኞቻችን ከቁጥር ቢበዙም
እንደ ቃየል ልጆች ሾተል አንመዝም
እንጀራን መግበን እንሰዳቸዋለን
በቀል እና ፍርድን ለአምላካችን ትተን
መዝሙር
👇👇👇👇👇👇👇
👉 @MezmurB 👈
👉 @MezmurB 👈
👆👆👆👆👆👆👆
👉 @biniy27
