ch
Feedback
Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/

前往频道在 Telegram

Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

显示更多

📈 Telegram 频道 Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ 的分析概览

频道 Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ (@ethpress) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 24 900 名订阅者,在 新闻与媒体 类别中位列第 9 634,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 1 339

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 24 900 名订阅者。

根据 27 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -105,过去 24 小时变化为 -7,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 已认证(Telegram 官方确认)
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 10.23%。内容发布后 24 小时内通常能获得 4.73% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 2 547 次浏览,首日通常累积 1 179 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 7

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
Ethiopian Press Agency, established in 1940 , is a public printing media enterprise operating in Ethiopia.

凭借高频更新(最新数据采集于 28 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 新闻与媒体 类别中的关键影响点。

24 900
订阅者
-724 小时
无数据7
-10530
帖子存档
56ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብስባ ውሳኔዎች +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ - የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 56ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ✍️ የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና ፊስካል ማዕቀፍ ላይ ነው፡፡ የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ ተግባራዊ ከተደረገ ወዲህ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ካሉበት ተግዳሮቶች እየተላቀቀና የኢኮኖሚው መሰረቶችም እየተጠናከሩ መጥተዋል፡፡ ማዕቀፉ በኢኮኖሚ ሪፎርሙ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል እንዲያስችልና በዋና ዋና የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ታሳቢዎች ላይ በመመስረት የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት በጀት ዝግጅት መነሻ ሆኖ እንዲያገለግል ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱ በማዕቀፉ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ ✍️ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት ረቂቅ አዋጅ የ2019 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግስት የበጀት ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ የ2019 የፌዴራል መንግስት በጀት የአስር አመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል የሆነው የ2019-2021 የልማትና ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችንና የመካከለኛ ዘመን (2019-2023) የማክሮ ኢኮኖሚና የፊሲካል ማዕቀፍን መሰረት በማድረግ፣ የ2018 በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም መነሻ ፣ በቀጣይ ሊኖር የሚችለውን የማህበራዊና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎችና አላማዎች እንዲሁም በመንግስት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት የመንግስትን የፋይናንስ አቅምና አስፈጻሚ መስሪያ ቤቶች ከተሰጣቸው ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የሚያስፈልገውን ወጪ በመገምገም ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡ በዚሁ መሰረትም ለመደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልል መንግስታት ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ የሚውል 2,339,268,126,738 (ሁለት ትሪሊዮን፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ቢሊዮን፣ ሁለት መቶ ስድሳ ስምንት ሚሊዮን፣ አንድ መቶ ሀያ ስድስት ሺ፣ ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት ብር) በጀት ለምክር ቤቱ ቀርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው የፌዴራል መንግስት የ2019 ረቂቅ በጀት አዋጅ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

በብስክሌት “ሜትር ታክሲ” +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የታክሲ ሰልፉ ረዥም ነው። ስንት ሰዓት ነው ወረፋ የሚደርሰኝ? ታክሲ ባገኝ ደግሞ መንገዱ ይዘጋጋል። በሰዓቴ ሥራ ቦታ መገኘት ይኖርብኛል
በብስክሌት “ሜትር ታክሲ” +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ- የታክሲ ሰልፉ ረዥም ነው። ስንት ሰዓት ነው ወረፋ የሚደርሰኝ? ታክሲ ባገኝ ደግሞ መንገዱ ይዘጋጋል። በሰዓቴ ሥራ ቦታ መገኘት ይኖርብኛል። ታዲያ ምን ይሻለኛል? ብሎ ለሚጨነቅ ሰው ጭንቀቱን የሚጋራና የሚያቃልል ችግር ፈቺ ስታርትአፕ ተፈጥሯል። ከወጪ አንፃር ገንዘብ ቆጣቢ ጤናም ለመጠበቅ የሚያስችል፤ እንግልትን የሚቀንስ ብስክሌትን በመጠቀም አዲስ ሥራ ይዘን መጥተናል ያሉ ወጣቶች ዘመን ኢኮኖሚ አነጋግራቸዋለች። ወጣቶቹ ስለ ፈጠራ ሥራቸው ያብራራሉ ። እንደ ሜትር ታክሲ አገልግሎት ብስክሌትን በማጋራት ትራንስፖርትን ማቀላጠፍ ይቻላል ብለው የተነሱ ወጣቶች ዳይናሚክ የተሰኘ አክሲዮን ማኅበር መሠረቱ። ድርጅታቸው መሥራት ካሰባቸው ሥራዎች አንዱ የትራንስፖርት ዘርፍ ነውና አንድ ለውጥ የሚያመጣ ሥራ መሥራት አለብን በሚል ሐሳብ “ፔዳል ፍላይ” የሚል ስያሜ አውጥተው ወደ ትራንስፖርት ዘርፍ ተቀላቀሉ።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ ትናንት የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ወይ
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት ተጠናቋል +++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ ትናንት የተካሄደው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ። የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለብዙኃን መገናኛ በሰጡት መግለጫ፣ የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ በስኬት ተጠናቅቋል ። በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫ ወቅት እና የድኅረ ምርጫ ሥራዎች በአግባቡ ተከናውነዋል። የመራጮች ምዝገባ፣ የእጩዎች ምዝገባ፣ ምርጫ ለሚታዘቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የመመዝገብ እንዲሁም ለሌሎችም አካላት ፈቃድ የመስጠት የቅድመ ምርጫ ሥራዎች በተያዘላቸው ጊዜ የተጠናቀቁ ሲሆን፤ በትናንትናው ዕለት በተካሄደው የድምጽ አሰጣጥ ሒደት በተሳካ ሁኔታ መከናወኑን አስረድተዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ማለዳ 12:00 ክፍት ተደርገው ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል። የሲቪክ ማኅበራትም በየምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ታዝበዋል። የአፍሪካ ኅብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለስልጣን (IGAD) ታዛቢዎች ከማለዳው 12:00 ጀምሮ ሲታዘቡ ውለዋል። በብዙ አካባቢዎች የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ከተጠናቀቀበት ሰዓት ጀምሮ ድምጾች የተቆጠሩ ሲሆን፤ የድምጽ አሰጣጡ ዘግይቶ በተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ቆጠራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል። ቆጠራው እንደተጠናቀቀ አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ በሚቀጥሉት ቀናት ይፋ ይደረጋል። ከድምጽ አሰጣጥና ከቆጠራ ጋር በተገናኘ የሚመጡ ጥቆማዎችን በማጣራት ቦርዱ በሕግ አግባብ እርምጃ እንደሚወስድም ገልጸዋል። በአብዱረዛቅ መሐመድ #Ethiopianelection2026 #GeneralElection #EthiopiaVotes #NEBE #AfricanUnion #IGAD

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ድምፃቸውን ሰጡ ++++++++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ ⵏ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕርዳር ምርጫ ክልል ህዳሴ ምርጫ ጣቢያ(
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ድምፃቸውን ሰጡ ++++++++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ ⵏ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በባሕርዳር ምርጫ ክልል ህዳሴ ምርጫ ጣቢያ(02-1) በመገኘት ድምፃቸውን ሰጥተዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎችም በ164 የምርጫ ጣቢያዎች ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ። በአማን ረሺድ

የኢዜማ ፓርቲ መሪ አቶ ኢዮብ መሳፍንት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጡ።
የኢዜማ ፓርቲ መሪ አቶ ኢዮብ መሳፍንት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጽ ሰጡ።

"ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን" -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ++++++++++++++++ #ጋዜጣ-ፕላስ | ያከበረንን አክብረን
"ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን" -ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ++++++++++++++++ #ጋዜጣ-ፕላስ | ያከበረንን አክብረን የመረጠንን ሰርተንለት የምናልፍ ከሆነ ሁላችንም አሸናፊ እንሆናለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በበሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ለመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ከማለዳ ጀምሮ በመውጣት በሰልፍ ምርጫ እያካሄደ ይገኛል። ይህም የሚሻውን ለመምረጥ መካሪ እንደማያስፈልገው ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል። እኔ ዛሬ የሚያሳስበኝ ከመራጩ በላይ ተመራጩ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህ ህዝብ በቁርጠኝነት የሚሻውን ወስኖ በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከመረጠ በኋላ የተመረጡት ሰዎች በዚያ ልክ ታምነው እጃቸውና ልባቸው ንጹህ ሆኖ ደከመን ታከተን ሳይሉ ሰርተው የሀገር ታሪክ ለመቀየርና የህዝቡን ውለታ ለመክፈል ዝግጁነታቸው ምን ያክል ነው የሚለው ነው ሲሉ ተናግረዋል" በምርጫው ሂደት ያሸነፉ በታማኝነት ማገልገል የተሸነፉ ደግሞ ውጤቱን በጸጋ ሊቀበሉ እንደሚገባ አሳስበዋል። ++++++++++++++ @የኢትዮጵያ_ፕሬስ_ድርጅት@ጋዜጣ-ፕላስ#በምርጫብቻ#ዲሞክራሲ#ምርጫ2018#ኢትዮጵያ#አርባምንጭ #EthiopianElection 2026#ዐቢይ አሕመድ

በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድ መደበኛ ስራ እንደማይኖር ምርጫ ቦርድ አስታወቀ +++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም የ7ተኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ እንዲከናወን መወሠኑ ይታወቃል። በዚህም መሠረት በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ በዕለቱ ድምፃቸውን ለመስጠት ይችሉ ዘንድና የደምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር ይከናወን ዘንድ ቦርዱ የሚከተሉት ተግባራዊ እንዲሆኑ የምርጫ የፓለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/ 2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ለመንግሥታዊና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ያሳውቃል። በዚህም መሠረት፤ ✍️ ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የፌዴራል እና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ፣ ✍️ ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ በፌዴራል እና በክልሎች የሚገኙ ማንኛውም መንግሥታዊ ያልሆኑና የግል ተቋማት በተመሳሳይ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ዝግ እንዲያደርጉ እያሳወቀ፤ ✍️ የአስቸኳይ ጊዜ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት፣ ሆስፒታሎች፣ የዕለት ተዕለት አገልግሎት ሰጪዎችም (ሆቴሎች፣ ሬስቶራንቶች፣ የትራንስፓርት አገልግሎት) በዝግ ቀናት የሚያደርጉትን አገልግሎት በተመሳሳይ የሚያከናውኑ ሲሆን፤ የመተባበር ግዴታው እነዚህን ተቋማት እንቅስቃሴ መዘጋት አያስገድድም። ✍️ የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችንና ዕቅዶችን እንዳይይዙና እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ ያበረታታል። #ምርጫ #ኢትዮጵያ Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/ #gazette_plus

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለዒድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ +++++++++++++++++ #ጋዜጣ_ፕላስ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ! ስለዒድ አል-አድሐ “ዐረፋ” በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፤ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፤ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡበት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ” በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው። እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹክታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፥ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ፤ ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ። ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት። የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፤ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፤ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው። የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለግዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት-ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን አናመንታ። የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል። የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው። ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፤ ታላላቆችና ታናናሾች፤ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የግላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል። ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞክራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞክራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው። የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነክርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፤ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ። በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ! ዒድ ሙባረክ!! ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ! ግንቦት 18፣ 2018 ዓ.ም

መላው የአፍሪካ ወንድም እህቶቻችን እንኳን ለአፍሪካ ቀን አደረሳችሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ++++++++++++ HAPPY AFRICA DAY TO ALL OUR AFRICAN BROTH
+1
መላው የአፍሪካ ወንድም እህቶቻችን እንኳን ለአፍሪካ ቀን አደረሳችሁ - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ++++++++++++ HAPPY AFRICA DAY TO ALL OUR AFRICAN BROTHERS AND SISTERS! 63 years ago, our forefathers gathered right here in Addis Ababa and dared to dream of a free, united Africa, and that dream still burns bright. Today, as the proud home of the African Union, Ethiopia stands shoulder to shoulder with every African nation in that same spirit of unity.The work is far from over. Let us move from words to action, from promises to progress. Africa's greatest resource has always been her people, and together, WE RISE! #AfricaDay #Africa #Ethiopia #Afrique #AfricanUnion #dayinthelife

ከ80 በመቶ በላይ የሀገር ውስጥ ግብዓትን የሚጠቀመው የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተመረቀ +++++++++++++++ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካልና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትል
+6
ከ80 በመቶ በላይ የሀገር ውስጥ ግብዓትን የሚጠቀመው የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ ተመረቀ +++++++++++++++ የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ጉዟችን አካልና የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ እመርታ ትልቅ ማሳያ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞጆ የተገነባውን የግራንዴር ሴራሚክ ፋብሪካ መርቀው አገልግሎት አስጀምረዋል። በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ቁልፍ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውን መሰል ፋብሪካዎች ግንባታ፣ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን በመሳብ በመላ ሀገሪቱ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በተግባር ያረጋገጠ ነው ብለዋል። ‎ ‎​ፋብሪካው የዓለም ዓቀፍ ጥራትና ተወዳዳሪነት መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሴራሚክ ምርቶችን የሚያቀርብ ሲሆን፣ ለምርቱ የሚያስፈልጉትን ጥሬ ዕቃዎች ከ80 በመቶ በላይ ከሀገር ውስጥ ዐቅም ያገኛል። ይህ ስኬት ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሀብትና እምቅ ጸጋ የመጠቀም ብቃቷን ከመገንባቱ ባሻገር፣ ከውጭ ገቢ ምርቶች ላይ ያለንን ጥገኝነት በከፍተኛ ደረጃ ይቀንሰዋል ሲሉም ገልጸዋል። #ሴራሚክስ #ግራንዴርሴራሚክፋብሪካ #ተኪምርት #ceramics #የኢትዮጵያአየርመንገድ #MadeInEthiopia #EthiopiaDelivers

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ኢትዮጵያን በመረጃ ላይ የተመሠረተ የልማት መጻኢ ዕድል የሚያሳየው ''በመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት'' ብሔራዊ ጉባኤ ላይ
+9
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ከፍተኛ የመንግሥት አመራሮች ኢትዮጵያን በመረጃ ላይ የተመሠረተ የልማት መጻኢ ዕድል የሚያሳየው ''በመረጃ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት'' ብሔራዊ ጉባኤ ላይ የቀረቡ የብሔራዊ ዕቅድና ስታቲስቲክስ ዳሽቦርዶች (የመረጃ መከታተያ ሰሌዳዎች) እና ኤግዚቢሽን ያደረጉት ጉብኝት። #PMOEthiopia

#አዲስ_ዘመን_ጋዜጣ https://press.et/e-paper
#አዲስ_ዘመን_ጋዜጣ https://press.et/e-paper