HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
前往频道在 Telegram
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239
显示更多2 277
订阅者
+224 小时
+97 天
+3830 天
帖子存档
ቀሲስ የመተተኛ አገልጋዮችን ጉድ ዘረገፉ ጭፈራ ቤት የሚያሯሩጥ አጋንንታዊ ሴራ የስልብና መንፈሶች በዘመናችን #ebs #ethiopia #ebstv 💥🔥😱
https://youtu.be/G3mC8N-zAdw
=> እግዚአብሔር የሌለበት ሃብት ልክ እንዳገጠጠ አውሬ ያስፈራል። እርሱ የሌለበት ትዳር ሆድን ብቻ የሚሞላ እንጂ ሕሊናን አይሞላም። ኑሮም ተበልቶ እንዳለቀ አጥንት ወይም የበቆሎ ቆሮቆንዳ ብናገላብጠው ለጥጋብ የሚሆን አንድም ነገር የለውም። ያለ እግዚአብሔር የተደሰቱ እያረሩ ይስቃሉ። ያለ እግዚአብሔር ያዘኑ መጽናናትን አያገኙም። ያለ እግዚአብሔር የተመራመሩ የተማሩ ባለጌዎች ይሆናሉ። የሰው ልጅ የኑሮ ማትረፊያው የሰላሙ መሠረት የእርካታው ምንጭ እግዚአብሔር ነው። ነብዩ እንደተናገረው => "እርሱም ይከፍታል የሚዘጋም የለም፤ እርሱም ይዘጋል የሚከፍትም የለም።" (ኢሳ.22፡22)
=> ሰው ከእግዚአብሔር ሲሸሽ እንቅልፍና መኝታ ለጊዜው ይመቸዋል፤ የሚያስጨንቅና የሚያሳስብ ችግር ለጊዜው አይታየውም። ይህ ትውልድ ዜግነቱን በመለወጥ አልረካም፤ ማንነቱን በመጥላትና በመርሳት፤ የታከተና የሰለቸ ሕሊና፣ በስውር የቆሰለ ልብ እያለው ወርዶ ተኝቷልና እንንቃ! እንበርታ!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
ምናምንቴዎችን የሚከተሉ ድህነትን ይወርሳሉ || ክፉውን መንፈስ አጋዥና ረዳት ያደረጉ || የመናፍቁ መንፈስ ዘመናዊ ሴራው || የመተት ዕድሳት ምንድነው? 💥🚩🔥 https://youtu.be/ApeO0jpa87A
🌹🍀በዓታ ለማርያም 🍀🌹
ኢያቄም ወሐና ስዕለታቸው ሲደርስ፤
ልጃቸውን ይዘው መጡ ቤተ መቅደስ ፤
የሐናን አበባ የኢያቄምን ፍሬ፤
ካህናት በደስታ ተቀበሏት ዛሬ፤
✨ ስምዒ ወለትየ ወርዕዪ ወአጽምዒ አዝነኪ
ርስዒ ሕዝበኪ ወቤተ አቡኪ
እስመ ፈተወ ንጉሥ ስነኪ
ወውእቱ እግዚእኪ
✨ ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ
ወገንሽም የአባትሽንም ቤት እርሺ
ንጉሥ ደም ግባትሽን ወዷልና
እርሱ ጌታሽ ነውና።
🌹 (መዝ 45፥10-11) 🌹
እንኳን አደረሳችሁ በዓታ ለማሪያም ለ2017
የመጀመሪያው ወርሃዊ መታሰቢያ።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
አጋንንት የሚራገፍበት፣ እኛም የተሳነፍንበት ዓይነ ጥላው እንዲለቀን እንዴት እንጠመቅ? ዓይነ ጥላ ያለበት ሰው ጸበል ሲጠመቅ የሚያየው ምልክቶች 🔥😱😭
https://youtu.be/-pa4_B4Cdfk?si=ANr6-nir-PuJAI_J
ድንቅ ልጆች በዘመናችን 5ቱ በአዲሱ ዓመት ልናደርጋቸው የሚገቡ ነገሮች Donkey Tube || Eshetu Melese #ethiopia #ebstv 🔥🚩
https://youtu.be/mPuN-TWKS18?si=w8i3jrhcQqZx4mpP
ሰባኬ ወንጌል በጥዑም ልሣኑ፤
ርስነ መለኮት ገሠሠት እዱ፤
ጸጉረ ገመል ተከድነ ዘባኑ፤
ለዮሐንስ ሂሩቶ ንዜኑ ንዜኑ።
በጣፋጭ አንደበቱ ወንጌልን የሚሰብክ ፣ ቀኙ የሚያቃጥል መለኮትን የዳሰሰች ፣ ጀርባው በግመል ጠጉር የተሸፈነ ፣ የዮሐንስን ደግነት ፈጽመን እንናገራለን ። / ድጓ ዘዮሐንስ /
"ወብዙኃን ይትፌሥሑ በልደቱ"
( #በመወለዱ_ብዙዎች_ደስ_ይላቸዋል) ሉቃ 1 ፥14
🙏 የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ረድኤት በረከት በመወለዱ ደስ በሚለን በሁላችን ላይ ጸንቶ ይኑር 🙏
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
🌼 “ቀናት እየሮጡ ነው፤ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፤ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፤ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ? እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ! አዲሱ ዓመት የእውነት አዲስ ዓመት እንዲኾንላችሁ ካሻችሁ ነፍሳችሁን ከኃጢአት ቀንበር አላቋት እንጂ ድጋሜ በኃጢአት ሸክም አትጫኗት፤ አሮጌው ዓመት እንዳለቀ ስታዩ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ወደሌላ ዘመን አሸጋግሯቸዋልና እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ልቡናችሁንም ውቀሱት፤ በዕድሜአችሁ ስንት ጊዜ እያለፈ እንደ ኾነ እያሰባችሁም ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁት። “ቀናት እየሮጡ ነው፤ ዓመታቱም እየነጐዱ ነው፤ የዕድሜዬ መንገድም እየተጋመሰ ነው፤ ታዲያ ምን በጐ ምግባር ያዝኩ?
🌼 ከዚህ ምድር የማልፍበት ቀን እየቀረበ ነው፤ ታዲያ ምን የጽድቅ ሥራ ሠራሁ? በዚህ ዕድሜዬ መሥራት የነበረብኝ ምግባር ትሩፋት ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ አልችልም፡፡ ታዲያ ዕድሜዬ ሲገፋ ማድረግ የማልችላቸውም የጽድቅ ሥራዎች (ፆም፣ ጸሎት፣ ስግደት፣ አገልግሎት፣… ዕድሜ ሲገፋ ይከብዳሉና) እንዳቅሜ እያደረግኩ ነውን?” በማለት ልቡናችሁን ጠይቁት፡፡
#ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
🌼 በዓለ ሲመቱ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል 🌼 መስከረም 1 ✨
«ከቅዱሳን መላእክት አንዱ የሆነ ጸላዒ ዲያብሎስን የሚበቀለው ራጉኤል በብርሃናት ላይ የሰለጠነ ነው። » ሲል ስለ እርሱ ተናግሯል። (ድርሳነ ራጉኤል ዘመስከረም ገፅ፮)
=> ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቀው በፍርሐተ እግዚአብሔር አምልኮቱን ለሚፈጽሙ ሁሉ ጠላት ዲያብሎስን የሚያርቅላቸው ወደ እነርሱም ፈጥኖ በመድረስ የሚታደጋቸው ነው። (ሔኖክ 6:4)
=> ሎጥን ሚስቱን እና ልጆቹን ከእሳተ ጎመራ ያዳነ የበለአምን እርግማን ወደ በረከት የለወጠ እርሱ ነው። (ድርሳነ ራጉኤል መግለጫ)
(ዘፍ 19፥ 1/ ዘኁ 21 ፥ 1-25 )
(ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እንደሣሉት)
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
መቁጠሪያን የምትቃወሙ ይሄንን አዳምጡ! እረኛውን መታለሁ መንጋው ይበተናል ገዳማዊያንን በዝሙት የመጣል ሴራ | memihir girma wondimu 😱🔥
https://youtu.be/_9y7SEeVvGE
የቀሲስ ሄኖክ ጥብቅ መልዕክት! || በአዲሱ ዓመት ልናደርጋቸው የሚገቡ || የአልኮል መጠጥ አጋንንታዊ ሴራዎቻቸው || የሴት ጨንገር አጋንንት ክፋቱ!! 😱🔥🚩 https://youtu.be/_ETkGFAs8H4
#ዘመን መለወጫ ምንድ ነው?
#እንቁጣጣሽ ምንድነው?
#አዲስ አመት ለምን ቅዱስ ዮሐንስ ይባላል?
=> ኢትዮጵያ የወራት ሁሉ መጀመሪያ መስከረም ነው፤ ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ እየተባለ ይጠራል፡፡ ስለ አዲስ ዓመት በተለያየ ስም የመጠራቱ ታሪካዊ አመጣጥና ስያሜ መነሻ አሳቡ ምን እንደሆነ እንደሚከተለው እንመለከታለን፡፡
#ዘመን_መለወጫ
=> ዘመን መለወጫ መስከረም ወር የሆነበት ምክንያት “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው፡፡ ሌሊቱ ከቀኑ ጋር ይተካከላል፤ ዓመቱን ጠንቅቀው ቢቆጥሩ 366 ቀናት ይሆናል፡፡ “ሌሊቱም ከቀኑ ጋራ ይተካከላል፤ ዓመቱም ጠንቅቆ ቢቆጥሩት ሦስት መቶ ስልሳ አራት ቀን ይሆናል፡፡ (ሄኖክ 26፥44) “ዘመናችንን እንደ ቀድሞ አድሱ” (ሰ.ኤር 5፥21 በዘመነ ኖኅ ዓለምን ንፍር ውኃ አጥለቅልቆት በኋላ ዳግመኛ ውኃው የጎደለበት በመሆኑ “በመጀመሪያው ወር መባቻም ምድር ታየች” እንዲል፡፡ (ኩፋሌ 7፥1)
#ዕንቁጣጣሽ
=> ዕንቁጣጣሽ የተባለበት ምክንያት አንደኛ “ዕንቁ - ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባውን አህጉራትን መፈንዳት ያመለክታል፡፡ ሁለተኛ ኖኅ ለሦስቱ ልጆቹ በእጣ ሲያካፍላቸው አፍሪካ ለካም ደረሰችው፤ በአፍሪካ ምድርም ሲገባ በመጀመሪያ ያረፈው በኢትዮጵያ ነበር፡፡ ሀገሪቱም በአደይ አበባ አሸብርቃ ነበር፤ ወሩ ወርኀ መስከረም በመሆኑ ደስ ብሎት ዕንቁ ዕጣ ወጣሽልኝ ይህችን ወቅት እንቁጣጣሽ ብሏታል፡፡
=> ሦስተኛው /1ነገ.10፥1-10/ ኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ሣባ /መነሻ አዜብ የንጉሡን ጥበብ ከመስማት ማየትን መርጣ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን ከብዙ ሠራዊቶቿ ጋር የእጅ በመያዝ ሄደች፡፡ ንጉሡም በደስታ ተቀብሎ እርሱም “እንቁ ለጣትሽወርኀ ጌጥ ይሁንሽ” በማለት አራት አይነት ቀለም የሚታይበት በቀንና በሌሊት የምታበራ ቀለበት ሰጥቷታል፡፡ ወሩም መስከረም ነበር፡፡ ከዚህ በመነሣት እንቁጣጣሽ የሚለው ስያሜ ወጥቷል፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ
=> ሦስተኛው የአዲስ ዘመን ስያሜ ቅዱስ ዮሐንስ ነው፤ የመጥምቁ ዮሐንስ ተግባር ለዘመነ ወንጌል በር ወይም መነሻ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ዐውደ ዓመት መስከረም አንድ ቀን እንዲከበር አባቶች ወስነዋል፡፡ (ድርሳነ ዮሐንስ አፈወርቅ ገጽ 1-3) መጽሐፈ ስንክሳር “የመስከረም ወር የተባረከ ነው፤ እርሱም የግብጽና የኢትዮጵያ ዓመቶች መጀመሪያ ነው፤ የዚህ ወር ቀኑና ሌሊቱ እኩል 12 ሰዓት ነው፤ ከዚህ በኋላ ቀኑ እየጎደለ ይሄዳል” እንዲል፡፡
=> በአጠቃላይ ዘመን መለወጫ ከላይ ባየናቸው የተለያየ ስያሜ ይጠራ እንጂ ዘመኑ አዲስ እየተባለ ቢጠራም አዲስ መሆን ያለበት ወርና ወቅቱ ብቻ ሳይሆን የእኛ የክርስቲያኖች ሥርዓት ነው፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውነታችሁን አታርክሱ የእግዚአብሔር ማደሪያ ነውና እያለ በመዋዕለ ሥጋዌው ያስተምር ነበር፡፡ አዲስ ዓመት ሲመጣ በኃጢአት፣ በተንኮል፣ በክፋት የቆሸሸው ሰውነታችን በንስሓ፣ በቅዱስ ቊርባን፣ በመልካም ተግባር አዲስ ልናደርገው ይገባናል፡፡
መልካም አዲስ አመት!
(ከተለያዩ መጽሐፍት)
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
"ችግር ለራሳችን እንድንጸልይ ያነቃቃናል፤ ፍቅር ደግሞ ለሌሎች ሰዎች እንድንጸልይ ያስገድደናል።" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
አፍዝ አደንግዝ አጋንንትና ከባድ ሴራዎቹ || አፍዝ አደንግዝ እንዳለብን እንዴት እናውቃለን? | ሰው አራት ዓይነት መንፈስ ይኖርበታል | መምህር ግርማ 🌼💥🚩 https://youtu.be/uMt_esV20P0
«2017 ዓ.ም ለሁላችን የደግነት፣ የበረከት፣ የጠንካራነት፣ የተግባራዊ መንፈሳዊነት፣ የመልካሚነት እንዲሆን እመኛለሁ። እንዲሁም ደግሞ በጸሎት፣ በስግደት፣ በንስሐ ጉዟችን ጠንካራ ሆነን በሥጋውና ደሙ ታትመን የሚንቆይ እንዲንሆን የጌታ የአምላክ ፍቃድ እንዲሆን እመኛለሁ። ከሁሉም በላይ ክፋትን፣ ተንኮልን፣ ንፉግነትን፣ ችኩልነትን፣ ዘረኝነትን አስወግደን በመልካሙ መንገድ እንድንጓዝ እግዚአብሔር እንዲያከናውንልን የእርሱ ቅዱስ ፍቃድ እንዲሆን ምኞቴ ነው። ለተራቡት የምናበሉ፣ ለተጠሙት የምናጠጣ፣ ለታረዘው የምናለብስ፣ ለተቸገረው ካለን የምናካፍልን እንዲንሆን እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ይርዳን። በዚህ በ2017 ዓመት ከመጥፎ አመሎቻችን ርቀን ወደ ቤተክርስቲያን የምንቀርብ እንዲንሆን ኢየሱስ ክርስቶስ ንጽሕ ልብን ያድለን። ሁሉም መልካም የሆኑ መሻቶቻችን የሚከናወኑበት ዘመን ይሁንልን። ይሄን ምኞታችንን እግዚአብሔር አምላካችን ያከናውንልን፣ ያድርግልን። አሜን! እንበርታ፣ እንጠንክር!»
እንኳን ለ2017 ዓ.ም አደረሳችሁ እላለሁ። #ሸር_ሸር!
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@Estifanos2239
ሰይጣንን አስርቡት || አእምሮ የሰይጣን የጦር ሜዳ | ትልልቅ ህልሞች ትናንሽ ሰዎች | ተንኮለኛው ጠላታችን እባብን ላስተዋውቃችሁ | አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ 😱💥
https://youtu.be/3tmLWLp-U3M
ጸሎትና ስግደትን ስናቆም የሚከተለው ሆነብን በውሻና በእንስሳት የሚደግሙ ደብተራዎች የጳጉሜ ሦስት በረከቶች || መምህር ተስፋዬ አበራ 2024 🚩🔥😱💥
https://youtu.be/aytoF4XwFRU?si=Wsn0sQe45t-6lhib
=> ሰላም ለከ ሩፋኤል ዐቃቤ ኆኀቱ ለአምላክ፣
ሰላም ለከ መገሥፀ ዐንበሪ ድሩክ፣
ሰላም ለከ ምዑዝ ቅዳሴ ሰሊክ፣
ሰላም ለከ አምላከ አማልክት ዘትባርክ፣
ሰላም ለከ እምሁከተ ልሳን መሪር ወእመልዐክ ሞት ድሩክ፤ ሰላም ለከ ሩፋኤል ዕቀበኒ ወአድኀነኒ በጽባሕ ወሠርክ ሊተ ለሀይለ ገብርኤል፣ ለሕሩተ ሥላሴ፣ ለሀብተ ማሪያም፣ ለወለተ ሥላሴ ......
እንኳን አደረሳችሁ። ሁላችሁም "ቅዱስ ሩፋኤል ወደ እኔ ና ና" እያላችሁ በኮሜን ላይ ጻፉ።
#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
