ch
Feedback
HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

前往频道在 Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

显示更多
2 280
订阅者
无数据24 小时
+77
+3930
帖子存档
መተተኞች የሚያድሱበት እኛ ደግሞ የምንታደስበት የጳጉሜ ወቅት!! በዘንዶው መንፈስ የተበላና የጨነገፈ ትውልድ ይማረን!! መተተኞች ለምን ጳጉሜን ለማደስ ይጠቀማሉ!! https://youtu.be/COE7-pDRbBE?si=_ejxtq6zkA5QQN9G

የተበደረችውን ገንዘብ ላለመክፈል የገዛ ወንድሟን በመተት አፉን አዘጋችው!! Haile Gebriel Reacts19 https://youtu.be/UHFFm_gu9a4

ሕይወትን የሚቀይሩ 5 መንፈሳዊ ምክሮች ከቅዱሳን እናቶች!! የ5ቱ ቅዱሳን እናቶች ወሳኝና አስተማሪ ምክሮች! #hailegebrielreact #ethiopia https://youtu.be/Rs1EgN-rSXQ

Why I'm Not Protestant – The True Faith of Oriental Orthodoxy #ethiopia #protestant #orthodoxfaith https://youtu.be/6qV3FYewV5U

አስቀድመን ካወራን አስቀድሞ ሰይጣን ያበላሽብናልና ይኼንን ሁላችሁም አዳምጡ!! ሰይጣን መቀለጃ መጫወቻ አደረገን እባካችሁ ንቁ! ከነጠላ ጀርባ ያለው መንፈሳዊነታችን እንዴት ነው? https://youtu.be/HlE7dU9eh8A?si=wuPqYxP6LIZxi4Uu

ለሰይጣን በር የሚከፍቱ 15 የተሳሳቱ ኦርቶዶክሳዊ አለባበሶች! ሥጋችሁ ቤተ መቅደስ እንጂ የማስታወቂያ ሰሌዳ አይደለም https://youtu.be/yVwIb1YWDgk?si=mkAYX1zJt-AZELU-

ይኼንን  የክፋትና የተንኮል ጥግ ተመልከቱ በሯጮቻችንና በስፖርቱ ዓለም!! መፍትሔ ሥራይና አውደነገሥት እየተደገመባቸው ጸበል ይጸበላሉ!! https://youtu.be/QMFwmDPfqR8?si=3z3XqqAqsnSpykSH

አጋንንት የሚፈሯቸው 12ቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ኃይለኛ ጥቅሶችና ቃላቶች!! ሁሉም ክርስቲያን ማወቅ የሚገባው የመናፍስት ውጊያ መረጃ! #አጋንንት #ሰይጣን #ጸሎት https://youtu.be/lNDWIH1Gh2s

ይኼንን ትምህርት ሰምታችሁ አሁኑኑ እራሳችሁንና ቤታችሁን ፈትሹ ታተርፋላችሁ!! ቤተክርስቲያን ጎበዝ ዘማሪ ሰፈራችን ደግሞ አስጨፋሪ! 4ቱ ከባባድ ልምምዶችና መርዝ እህታችን የረጨችው! https://youtu.be/BpwkdyiZ2_Q?si=xpmDp-Ny6BPIXeKp

የመከራና የፈተና ምንጩ አጋንንትና ሰይጣን አይደሉም ነጻ ፍቃዳችን እንጂ!! ማንያዘዋል አስተምሮ ያስመረቃት ያልነቃች አንቂና ስህተቷ! የዲያቆን ሄኖክና መምህር ግርማ ድንቅ ትምህርት! https://youtu.be/Olzy-OD-jcA

ጨነቀኝ ከበደኝ ከጀርባዬ የሆነ ነገር የቆሜ ይመስለኛል ብላችሁ ለምትጨነቁ!! ደጋ ላይ የወደቀው ሰይጣንና አጋንንት! ክፉ መናፍስትና የጥቃት አቅጣጫው ክፍል 4 https://youtu.be/g2rAbYkINP4

የአየር አጋንንት የጥፋት አቅጣጫዎቹና ማወቅ የሚገቡን እውነቶች! ክፉ መናፍስት እና የጥቃት አቅጣጫዎቻቸው ክፍል 3 | 3ቱ የአየር አጋንንት የአያያዝ ስልቶች! https://youtu.be/PG020k9mJsI

ክፉ መናፍስት እና የጥቃት አቅጣጫዎቻቸው #ክፍል_2 መናፍስት ለምን አጋንንትና ሰይጣን ተብለው ይጠራሉ? መናፍስት እኔን አያጠቁኝም የምትሉ አዳምጡ!! https://youtu.be/0OOV8_VrHWw

ክፉ መናፍስት እና የጥቃት አቅጣጫዎቻቸው ክፍል 1 | የሁሉም መናፍስት 5ቱ ዋና ዋና ባሕሪያቶች ሰይጣን  ለምንድነው  እንዲህ  አጥብቆ  የሚፈትነን? https://youtu.be/v8reiuQE26w?si=ggD0tOLKxJKiRrrQ

የቀሲስ ሄኖክን #መጽሐፍ የጻፈው #የዓይነጥላ #መንፈስና የሆነውን ጉድ ተመልከቱ!! በጸሎታችን ዘወትር ልናካትተው የሚገባ ወሳኝ ነገር!! #አጋንንት #መናፍስት https://youtu.be/3m255yVqX0M?si=eqTpKrRxNs9HJm0W

«የዕለቱን ወንጌል እናንብብ» ነሐሰ 24 (የማቴዎስ ወንጌል 10፡1-42) «ሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ እርሱ ጠርቶ፥ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ሁሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው። የአሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ስም ይህ ነው፤ መጀመሪያው ጴጥሮስ የተባለው ስምዖን ወንድሙ እንድርያስም፥ የዘብዴዎስ ልጅ ያዕቆብም ወንድሙ ዮሐንስም፥ ፊልጶስም በርተሎሜዎስም፥ ቶማስም ቀራጩ ማቴዎስም፥ የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም ታዴዎስም የተባለው ልብድዮስ፥ ቀነናዊውም ስምዖን ደግሞም አሳልፎ የሰጠው የአስቆሮቱ ይሁዳ። እነዚህን አሥራ ሁለቱን ኢየሱስ ላካቸው፥ አዘዛቸውም፥ እንዲህም አለ። በአሕዛብ መንገድ አትሂዱ፥ ወደ ሳምራውያንም ከተማ አትግቡ፤ ይልቅስ የእስራኤል ቤት ወደሚሆኑ ወደ ጠፉት በጎች ሂዱ እንጂ። ሄዳችሁም። መንግሥተ ሰማያት ቀርባለች ብላችሁ ስበኩ። ድውዮችን ፈውሱ፤ ሙታንን አስነሡ፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ። ወርቅ ወይም ብር ወይም ናስ በመቀነታችሁ፥ ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። በምትገቡባትም በማናቸይቱም ከተማ ወይም መንደር፥ በዚያ የሚገባው ማን እንደ ሆነ በጥንቃቄ መርምሩ፤ እስክትወጡም ድረስ በዚያ ተቀመጡ። ወደ ቤትም ስትገቡ ሰላምታ ስጡ፤ ቤቱም የሚገባው ቢሆን ሰላማችሁ ይድረስለት፤ ባይገባው ግን ሰላማችሁ ይመለስላችሁ። ከማይቀበላችሁም ቃላችሁንም ከማይሰሙ ሁሉ፥ ከዚያ ቤት ወይም ከዚያች ከተማ ስትወጡ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። እውነት እላችኋለሁ፥ በፍርድ ቀን ከዚያች ከተማ ይልቅ ለሰዶምና ለገሞራ አገር ይቀልላቸዋል። እነሆ፥ እኔ እንደ በጎች በተኵላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ። ነገር ግን ወደ ሸንጎ አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ በምኩራቦቻቸውም ይገርፉአችኋልና ከሰዎች ተጠበቁ፤ ለእነርሱና ለአሕዛብም ምስክር እንዲሆን፥ ስለ እኔ ወደ ገዥዎች ወደ ነገሥታትም ትወሰዳላችሁ። አሳልፈውም ሲሰጡአችሁ፥ የምትናገሩት በዚያች ሰዓት ይሰጣችኋልና እንዴት ወይስ ምን እንድትናገሩ አትጨነቁ፤ በእናንተ የሚናገር የአባታችሁ መንፈስ ነው እንጂ፥ የምትናገሩ እናንተ አይደላችሁምና። ወንድምም ወንድሙን፥ አባትም ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፥ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ ይነሣሉ ይገድሉአቸውማል። በሁሉም ስለ ስሜ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል። በአንዲቱ ከተማም መከራ ቢያሳዩአችሁ ወደ ሌላይቱ ሽሹ፤ እውነት እላችኋለሁና፥ የሰው ልጅ እስኪመጣ ድረስ የእስራኤልን ከተማዎች አትዘልቁም። ደቀ መዝሙር ከመምህሩ፥ ባሪያም ከጌታው አይበልጥም። ደቀ መዝሙር እንደ መምህሩ፥ ባሪያም እንደ ጌታው መሆኑ ይበቃዋል። ባለቤቱን ብዔል ዜቡል ካሉት፥ ቤተሰዎቹንማ እንዴት አብዝተው አይሉአቸው! እንግዲህ አትፍሩአቸው፤ የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለምና። በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ፤ በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ። ሥጋንም የሚገድሉትን ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ፤ ይልቅስ ነፍስንም ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ። ሁለት ድንቢጦች በአምስት ሳንቲም ይሸጡ የለምን? ከእነርሱም አንዲቱ ያለ አባታችሁ ፈቃድ በምድር ላይ አትወድቅም። የእናንተስ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ ተቈጥሮአል። እንግዲህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች እናንተ ትበልጣላችሁ። ስለዚህ በሰው ፊት ለሚመሰክርልኝ ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እመሰክርለታለሁ፤ በሰው ፊትም የሚክደኝን ሁሉ እኔ ደግሞ በሰማያት ባለው በአባቴ ፊት እክደዋለሁ። በምድር ላይ ሰላምን ለማምጣት የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ሰይፍን እንጂ ሰላምን ለማምጣት አልመጣሁም። ሰውን ከአባቱ፥ ሴት ልጅንም ከእናትዋ፥ ምራትንም ከአማትዋ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና፤ ለሰውም ቤተ ሰዎቹ ጠላቶች ይሆኑበታል። ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ መስቀሉንም የማይዝ በኋላዬም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን አይገባውም። ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል፥ ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛታል። እናንተን የሚቀበል እኔን ይቀበላል፥ እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል። ነቢይን በነቢይ ስም የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ይወስዳል፥ ጻድቅንም በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ ይወስዳል። ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋው አይጠፋበትም።» #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 https://www.youtube.com/@estifo2239

Do Orthodox Christians Believe Saint Mary Can Save Us? Ethiopian Faith Explained! #orthodox #faith https://youtu.be/nZB0fVC4kH0

«የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ነሐሴ 24» ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማሕሌት፣ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለተክለሃይማኖት፤ አቡነ ተክለ ሃይማ
«የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት የዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል ነሐሴ 24» ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማሕሌት፣ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለተክለሃይማኖት፤ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ መቃረቡን ባወቁ ጊዜ የመንፈስ ልጆቻቸውን ጠርተው ጌታችን የነገራቸውን ዅሉ አስረድተው አባታዊ ምክርና ተግሣፅ ከሰጧቸው በኋላ ነሐሴ ፳፬ ቀን ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል፡፡ የመንፈስ ልጆቻቸውም ለአንድ ቅዱስ አባትና ካህን በሚገባ ሥርዓት በማኅሌት፣ በዝማሬና በምስጋና ቀብረዋቸዋል፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችንና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾላቸዋል፤ ነፍሳቸውንም ‹‹የጠራሽ፣ ንጽሕት ነፍስ ሆይ ወደ እኔ ነዪ›› ብሎ በክብር ተቀብሏታል፡፡ በመጽሐፈ ገድላቸው እንደ ተጠቀሰው አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህ ዓለም የኖሩበት ዕድሜ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ከዐሥር ወር ከዐሥር ቀን ነው። በእናት አባታቸው ቤት ፳፪ ዓመት፤ በከተታ ፫ ዓመት፤ በይፋት ፱ ወር፤ በዳሞት ፲፪ ዓመት፤ በአማራ ፲ ዓመት፤ በሐይቅ ፲ ዓመት፤ በደብረ ዳሞ ፲፪ ዓመት፤ በትግራይና በኢየሩሳሌም ገዳማት ፩ ዓመት፤ ዳዳ በሚባል አገር ፩ ወር፤ በደብረ አስቦ ገዳም ፳፱ ዓመት ከ፲ ቀን መቆየታቸውን መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል (ገ.ተ.ሃ ፶፱፥፲፬-፲፭)፡፡ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማሕሌት፣ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለተክለሃይማኖት፤ አባ አባ ጸሎትከ ትባርከኒ ወትረ፣ ንበር ምስሌየ በኩሉ መዋዕልየ። 🙏🏾 የጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሐይማኖት ረድኤት በረከታቸው አይለየን 🙏🏾 #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 https://www.youtube.com/@estifo2239

ተጠንቀቁ!! ትዳር ወንጌል በሕይወት የሚሰበክበት ቅዱስ መንገድ ነው!! መማርና ማወቅ ወደ ቅዱስ ቁርባን ማደግ እንዲህ ነው!! ለሰይዶ ማርሻል የተሰጠ መልስ!! https://youtu.be/27r6Fx_6r-Y