ch
Feedback
HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ

前往频道在 Telegram

❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️ 👇👇👇 http://www.youtube.com/@haileG2239

显示更多
2 288
订阅者
+724 小时
+107
+2930
帖子存档
ጸሎታችን ምን ዓይነት ይዘት ይኑረው? 4ቱ ኦርቶዶክሳዊ ጸሎት ልያካትተው የሚገቡ ነገሮች!! መዝሙረ ዳዊትና ውዳሴ ማሪያምን መጸለይ ያለው በረከት!! https://youtu.be/VkrMjB6Dalc?si=0gUlFmYgxQxQOJGs

የእምነት ኃይል ስኖራችሁ እግዚአብሔር ይኼንን ያደርግላችኋል!! መተት በትዳር ሕይወታችን የሚያስከትለው መዘዝና መፍትሔው!! የምቀኛ ሰው ባሕሪይና መገለጫው!! https://youtu.be/dmdlltm3dDI

የልብሷን ጨርቅ እንደ መቁጠሪያ የተጠቀመች ብርቱዋና ጠንካራዋ ሴት!! #ethiopia https://youtu.be/7K9IyGn5hOM

🛑 ጸበል ለመጠመቅ ከመኼዳችን በፍት ይሄንን ማድረጋችንን እንወቅ!! Haile Gebriel Reacts19 Estifanos Tube #ethiopia https://youtu.be/o_miE5xIe2g

«የዕለቱን ወንጌል እናንብብ!» «የማቴዎስ ወንጌል 11፡25-30» «በዚያን ጊዜ ኢየሱስ መልሶ እንዲህ አለ። አባት ሆይ፥ የሰማይና የምድር ጌታ፥ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ፤ አዎን፥ አባት ሆይ፥ ፈቃድህ በፊትህ እንዲህ ሆኖአልና። ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፥ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም። እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና።» #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

#ሐምሌ_19_ቀን ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት ኢየሉጣ ንጉስ ላስቀረጸው ለጣኦት አንሰግድም ብለው ወደ እሳት ብረት ጋኑ የሚጣሉበት ጊዜ በቀረበ ወቅት እናቱ ኢየሉጣ ግን ልቧ ፈራ የልጇን ዐይን እያየች ሆዷ ባባ በፍርሃትም ታወከች ። 🍂 ልጇም « #እናቴ_ሆይ_አትፍሪ ልብሽም አይጠራጠር ዳዊትን ከጎልያድ ሰይፍ ፣ ዳንኤል ከአናብስት አፍ ፣ አናንያን አዛርያንና ሚሳኤልን ከእቶን እሳት ፣ሶስናን ከክፉ ረበናት ያዳነ አምላክ እኛንም ያድነናል ። ከዚህ ከብረት ግርማ የተነሣ አትፍሪ ከሚያልፈው ጭንቀትና መከራ ለመዳን ብለሽ በዘለዓለም እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ? እናቴ ሆይ ! ዛሬ ገድላችንን ፈጽመን ገጸ እግዚአብሔርን እንመልከት ፣ አምላካችንንም ደስ እናሰኘው ፤ ‹‹ ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየን ማነው ? ›› የሚለው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል ትዝ ይበለሽ ፡፡ ( ሮሜ 8 ፥ 35 ) 🍂 #እናቴ ! አይዞሽ አትፍሪ ኋላ በአብርሃም እቅፍ ለመግባት ፤ የሕይወትን አክሊል ለመቀዳጀት ፣ የብርሃን መጎናጸፊያ ለመጎናጸፍ ፤ አሁን በዚህ እሳት ውስጥ ማለፍ ይኖርብናል ፡፡ አንድ ሰዓት ለማትሞላ መከራ ብለሽ ለዘለዓለም መከራ አንዳረግ ፤ ይልቅስ የአንድ ሰዓት መከራ ተቀብለን ለዘለዓለም በመንግሥተ ሰማያት ከብረን ገነን እንኖር ዘንድ ጨክኚ መከራውን አትሰቀቂ መቀነትሽን አጥብቂ ፤ በትውልደ ጻድቃን ስትወደሺ እንድትኖሪ ዛሬ መከራውን ድፈሪ አላት ። ደግሞም በሥጋ ብንሞት በነፍስ ሞት የለብንም ። » ✨ እያለ መረጃ እየጠቀስ አጽናናት ይህም አልበቃ ቢለው ቀሚሷን እየጎተተ « #እናቴ_ነይ_በርቺ ገድላችንን እንፈጽም አላት ። » ሆኖም እናቱ ኢየሉጣ ፍርሃቷ በቀላሉ ሊለቃት አልቻለም ፤ በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ ‹‹ አቤቱ አምላኬ ሆይ ይህቺን ባርያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ አውጣኝ ከሕይወትህ መዝገብ ፋቀኝ ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለህ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይህን እንዳታደርግ ቸርነትህ ትከለክልኻለች ። 🍂 እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለህ ልታዝ መለኮታዊ ባሕርይህ አይደለም ፣ እንደዚሁ ልጅን አጽንተን እናትን መተው ባሕርይህ አይደለም ፤ እንጨቱን ከእነቅጠሉ ትጠብቃለህ እንጂ ። ከጌታ ይልቅ እኔ በረታሁ ፤ ቅዱሳኖቹን ድል ነሣሁ ፤ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማሁ በማለት ጠላት እንዳይደነፋ ለእናቴ ኀይለ መንፈስ ቅዱስን አሳድርባት ›› ብሎ ጸለየ ። ያን ጊዜ ኢየሉጣ የብረት ጋኑ ለምለም ሣር መስሎ ታያት በምንጭ ላይም እንደሚወርድ ጠል መሰላት የልጇን ምዕዳን ሰምታ ቃሉንም አክብራ በፍጹም ልቧ ጨክና እናትና ልጅ ተያይዘው ወደ እሳት ውኃ ገቡ ፡፡ ✨ እስከ ሞት የታመኑለት በዐላውያን ነገሥታት የመሰከሩለት እውነተኛው አምላክ ሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤልን ላከላቸው እግዚአብሔር ዘግይቶም ቢነሣ የሚቀድመው የለምና መልአኩ ገብርኤል እየበረረ መጥቶ የጋለውን የብረት ጋን በበትረ መስቀሉ ቢባርከው ውኃው ቀዘቀዘላቸው ። 🍂 ልብሳቸው ሳይሰበሰብ ሰውነታቸው ሳይሸበሸብ ልክ እንደሚስማማ ሙቅ ውኃ ሆኖላቸው ደስ እያላቸው ታጥበው ወጥተዋል እግዚአብሔርን አመስግነዋል በዚያ የተሰበሰቡም እጅግ አደነቁ ። #ኢየሉጣም በልጇ ገድልና ምክር ተደስታ እንዲህ አለችው « ልጄ በሥጋ ብወልድህም በግብርና በገድል አባቴና መምህሬ ነህ » ብላ መሰከረችለት ። ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ « እናትና ልጅ በሃይማኖት ተባበሩ » ሲል ይገልጣቸዋል ። ✨ ዳግመኛም ‹‹ ልጅ እናቱን መንግሥተ ሰማያትን እንወርስ ዘንድ ከእሳቱ ነበልባል የተነሣ አትፍሪ አላት ምስጋና ለእግዚአብሔር ይግባውና እናትና ልጅ በሃይማኖት ተባበሩ ሰማዕትም ሆኑ ። » ሲል ዘምሯል ። የቅዱስ : ገብርኤል : የቅድስት : ኢየሉጣና : የቅዱስ : ቂርቆስ ምልጃና  : ጸሎታቸው : ይጠብቀን : አሜን ። #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

እኛ ሳናውቀው መንፈስ ቅዱስን ከእኛ የሚያርቁ 5 ባህርያት!! መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ለምን ይርቃል? መንፈስ ቅዱስ ከእኛ እንዳይርቅ ምን እናድርግ? #ጸሎት #ንቁ https://youtu.be/XM5_s3w1T4Q

🙏🙏 አባቶቻችን እግዚአብሔር አምላክ ረጅም ዕድሜና ጤና ያድላችሁ። መቼም ይኼ አንድነት እንዳይመጣና አባቶች በአንድነት እንዳያገለግሉ አድፍጠው ስታገሉ የነበሩና አገልግሎቱ እንድቋረጥ የባጥ የቆጡን
🙏🙏 አባቶቻችን እግዚአብሔር አምላክ ረጅም ዕድሜና ጤና ያድላችሁ። መቼም ይኼ አንድነት እንዳይመጣና አባቶች በአንድነት እንዳያገለግሉ አድፍጠው ስታገሉ የነበሩና አገልግሎቱ እንድቋረጥ የባጥ የቆጡን ሲያወሩ የነበሩ ሁሉም ይፈሩ። ዲያብሎስ አፍሮ እግዚአብሔር የከበረበትና የነገሰበት አገልግሎት ነበር። ገና ከዚህ በላይ ያገለግላሉ ጠላት ይፈር ይዋረድ። 🙏🙏

ፈረንጆቹ መምህር ግርማን የጠየቁት ጥያቄና የአባታችን አስገራሚ መልሶች!! የእኛ ሀገር መምህራን ይቃወማሉ ፈረንጆቹ ይጠይቃሉ ይማራሉ!! #hailegebriel https://youtu.be/MzrrL0wxKls

የመምህር ግርማ ተከታይ እያሉ እኛን ለማሸማቀቅ ለሚሞክሩ ፈሪሳዊያን ይድረስ!! ብዙዎቻችን ያልተረዳነው የአጋንንቱና የመናፍስቱ ፈተና!! #ዲያቆን #ጸሎት #ንቁ https://youtu.be/lDOp1sY8CCc

መምህር ግርማ ጠንቋይ ናቸው እያልኩ ብዙ ሰዎችን አሳስቻለሁ! አባቶችን የሚያሳዲዱ 5ቱ ውሾችና ሴራቸው ስገለጥ! እንግዳ ስለመቀበል እስካሁን ያልተረዳናቸው ነገሮች! https://youtu.be/yKJBHDHmsXQ?si=fPGwtGUFbtlajwTK

+++ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ አለሁ ይበላችሁ። ከፈተና ከመከራ ይጠብቃችሁ። የተዘጋውን ይክፈትላችሁ በተቸገራችሁበት ነገር ሁሉ ቅዱስ ሩፋኤል አለሁ ይበላችሁ። ፈታኼ ማህጸን ነውና በልጅ እጦት ለምትቸገሩ
+++ ሊቀ መልአኩ ቅዱስ አለሁ ይበላችሁ። ከፈተና ከመከራ ይጠብቃችሁ። የተዘጋውን ይክፈትላችሁ በተቸገራችሁበት ነገር ሁሉ ቅዱስ ሩፋኤል አለሁ ይበላችሁ። ፈታኼ ማህጸን ነውና በልጅ እጦት ለምትቸገሩ የተዘጋውን ከፍቶ በዲያብሎስ የተያዘውን ቦታ አስለቅቆ በልጅ ይባርካችሁ። በዚህ ሰዓት ለመውለድ በሚጥ ላይ ያላችሁ ቅዱስ ሩፋኤል ፈጥኖ ይድረስላችሁ። ለመውለድ በመንገድ ላይ ያላችሁ ቅዱስ ሩፋኤል የተባረከ ልጅ ያስታቅፋችሁ። በኑሮ በገንዘብ የተቸገራችሁ ቅዱስ ሩፋኤል የሰላቢውን መንፈስ ይሰርላችሁ። ሁላችሁም አሜን ቅዱስ ሩፋኤል ያድርግለን በሉ። ለሁሉም ሸር አድርጉ። +++ አስተውሉ ድርሳኑን፣ መልክአውን ማንበባችሁን በጭራሽ እንዳትረሱ። የኼ ካልሆነላችሁ ደግሞ በድምጽም ቢሆን መልክዐውንና ድርሳኑን ማዳመጥ እንዳትረሱ። ለላው ደግሞ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን በአቅራቢያችሁ ደጁን ርገጡ በስሙ ዘክሩ። ሰላም እደሩ 🙏🙏🙏

++ አገልጋይ ማለት ምቾት የሌለውን ስራ የሚሰራ ማለት ነው። አገልጋይ ማለት በሙላት በኩል ሳይሆን በጉድለት በኩል የሚቆም ነው። አገልጋይ ቅጥር የሚያድስ ነው። አገልጋይ ማለት ችግር ጎልጓይ ሳይሆን
+5
++ አገልጋይ ማለት ምቾት የሌለውን ስራ የሚሰራ ማለት ነው። አገልጋይ ማለት በሙላት በኩል ሳይሆን በጉድለት በኩል የሚቆም ነው። አገልጋይ ቅጥር የሚያድስ ነው። አገልጋይ ማለት ችግር ጎልጓይ ሳይሆን ችግር ፈቺ ነው። አገልጋይነት የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ ነው። ++ በሕይወታችን  ውስጥ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሚጎዱን ሰዎች ይኖራሉ መቼም ቢሆን ሥራችን፤ ሀሳባችንና ንግግራችን በሌሎች መጥፎነት ሊገታ አይገባም ለእኛ ቀና ድርጊት መልካም ምላሽ ባናገኝ እንኳን እኛ እንደ ሰው ቀናነታችንና ደግነታችንን ልንቀጥል ይገባል። በልባቸው ውስጥ ክፋት የነገሰ ሰዎች መርዝን በማር እየለወሱ የእኛን ሰላማዊና ቀና ማንነት እንዲያበላሹ ልንፈቅድላቸው አይገባም የሚሰድቧችሁን መርቁ እንደተባለ በመፅሐፍ ቅዱስ መልካምነት ለራስ ነው! ++ በቀጣይም ገዳሙ ተሰርቶ እስኪያልቅ እኔና የመንፈስ ቅዱስ ልጆቼ  ከጎናችሁ መሆናችንን ላሳዉቃችሁ እወዳለሁ! የቀሲስ ኃይለመለኮት መልዕክት ነው። ሰላመ እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን። #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

የተጠመቁ አረማዊያንና ከመናፍስት ጋር ጋብቻ የፈጸሙ ደብተራዎች!! ኃጢአትን የመተው ኃይል ለማግኘት ይኼንን እናድርግ!! የቆንጆ ሴቶች የመናፍስት ጉዳት!! https://youtu.be/VBg-BlJ_Uyg?si=xKLyML5ATxe6jXBJ

🙏 የምንወዳቸው የምናከብራቸው ሁለቱ አባቶቻችን በካናዳ ካልጋሪ በአንድ መድረክ በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን። በእውነት እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን ያድልልን። በሰላም
+1
🙏 የምንወዳቸው የምናከብራቸው ሁለቱ አባቶቻችን በካናዳ ካልጋሪ በአንድ መድረክ በአገልግሎት ላይ ይገኛሉ እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን። በእውነት እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን ያድልልን። በሰላም ወደ ሀገር ቤት ይመልሳችሁ የአባቶቻችን አምላክ። #ሸር ይደረግ!

አቶ ቢኒያም በኮሜንት እያጨናነቀን ነው ወዳጆች ለዚህ ወንድማችን ልንጸልይለት ይገባል። እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለው።
+1
አቶ ቢኒያም በኮሜንት እያጨናነቀን ነው ወዳጆች ለዚህ ወንድማችን ልንጸልይለት ይገባል። እግዚአብሔር ማስተዋሉን ያድለው።

አይናፋር ብቸኛ ፈሪና በላብ እንድንዘፈቅ የሚያደርጉ አጋንንቶችና ሴራቸው!! የቡዳ ዛር መንፈስ የሕይወት ፈተናቸው!! ያልተረዳናቸው የመናፍስት ጉዳቶች! #ጸሎት https://youtu.be/Hmvcnh1skHg

«የዕለቱን ወንጌል እናንብብ» «የሉቃስ ወንጌል 6፡20-27» «እርሱም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ዓይኑን አነሣ እንዲህም አላቸው። እናንተ ድሆች ብፁዓን ናችሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት የእናንተ ነውና። እናንተ አሁን የምትራቡ ብፁዓን ናችሁ፥ ትጠግባላችሁና። እናንተ አሁን የምታለቅሱ ብፁዓን ናችሁ፥ ትስቃላችሁና። ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ሲጠሉአችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፉአችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ፥ ብፁዓን ናችሁ። እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። ነገር ግን እናንተ ባለ ጠጎች ወዮላችሁ፥ መጽናናታችሁን ተቀብላችኋልና። እናንተ አሁን የጠገባችሁ ወዮላችሁ፥ ትራባላችሁና። እናንተ አሁን የምትስቁ ወዮላችሁ፥ ታዝናላችሁና ታለቅሱማላችሁ። ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ፥ ወዮላችሁ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና። ነገር ግን ለእናንተ ለምትሰሙ እላችኋለሁ፥ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ ለሚጠሉአችሁ መልካም አድርጉ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ።» #Subscribe #Like #Share    👇👇👇👇 www.youtube.com/@haileG2239 www.youtube.com/@Estifanos2239

ፓስተር ቢኒያም ሽታዬና አረማዊ ወዳጆቹ ይቅርታ ልጠይቁ ይገባል!! የማሕበረ በኩራት የአቋም መግለጣ! አባ ዮሐንስ ተስፋማርያም https://youtu.be/GKo4plYC7yY?si=T-i0UqB5Z0HYNPap