Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
前往频道在 Telegram
📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览
频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 16 040 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 277,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 233 位。
📊 受众指标与增长动态
自 невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 16 040 名订阅者。
根据 24 十月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 493,过去 24 小时变化为 95,整体触达仍然可观。
- 认证状态: 未认证
- 互动率 (ER): 平均受众互动率为 24.10%。内容发布后 24 小时内通常能获得 9.99% 的反应,占订阅者总量。
- 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 864 次浏览,首日通常累积 1 601 次浏览。
- 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 26。
📝 描述与内容策略
作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
“የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።”
凭借高频更新(最新数据采集于 25 十月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。
16 040
订阅者
+9524 小时
+1537 天
+49330 天
帖子存档
#ሕንጸተ_ቤታ_ለማርያም
#ወሥርዓተ_ማኅሌት
ሰኔ 21 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ #ህንጸተ_ቤተክርስቲያን ይባላል።
በሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን በአምላክ እናት ስም የታነጸችው ሰኔ 20 ነው። አናጺውም ደግሞ እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን ቦታው #ፊልጵስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ #በእመቤታችን_ስም ነው። ጥንተ ነገሩስ (ታሪኩ) እንደምን ነው ቢሉ:-
...
ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱን ‹‹ሑሩ ወመሐሩ ኩሎ አሕዛበ፤ አሕዛብን ሁሉ ሒዱና አስተምሩ፡፡›› /ማቴ. 28:19/ ባላቸው ቃል መሠረት ዓለምን በወንጌል ያርሷት ዘንድ በዕጣ ተካፍለዋታል::
የሰው ልጅ ድኅነቱ የሚፈጸመው ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ሲቀበል ነውና (ዮሐ. 6:56) አበው ሐዋርያት ቁርባንን በተመረጡ ሰዎች ቤት እያዘጋጁ ቀድሰው ያቆርቡ ነበር:: በመጀመሪያ በጽርሐ ጽዮን ፣ ቀጥሎም በተለያዩ ሰዎች ቤት እንዲህ ይከናወን ነበር:: ለጸሎት ሥራ ደግሞ አንዳንዴ ምኩራበ አይሁድን ይጠቀሙ ነበር:: እየቆየ ሲሔድ ግን ከአሕዛብ ያመኑ ሰዎች ቁጥር እጅጉን በዛ:: በተለይ ቅዱስ ጳውሎስ ያሳመናቸው ለጸሎት እያሉ ወደ ጣዖት ቤት መግባት አመጡ:: በዚህ ምክንያት መምሕራን ሕዝቡን ‹‹ካመናችሁ በኋላ እንዴት ወደ ጣዖት ቤት ትገባላችሁ?›› ቢሏቸው ‹‹እኛ ምን እናድርግ! የምንጸልይበት እንደው የለን›› ሲሉ መለሱላቸው::
...
ነገሩ ሲያያዝ ከደጋጉ ሐዋርያት #ጳውሎስና_በርናባስ ደረሰ:: ወዲያውኑ አንዳንድ ወንድሞች ‹‹ለምን አናንጽም?›› ብለው ነበር:: ቅዱስ ጳውሎስ ግን ‹‹ሊቀ ሐዋርያቱ ሳይፈቅድ አይሆንም›› አለ:: (ለዚህ ነው ዛሬም ሊቀ ጳጳስ ካልፈቀደ ቤተክርስቲያን የማይታነጸው፡፡) ከዚያ ቅዱሳን ጳውሎስና በርናባስ ሐዋርያቱ ወዳሉበት ሔደው ነገሩን #ለቅዱስ_ጴጥሮስ አስረዱ:: ሊቀ ሐዋርያቱ ቅዱስ ጴጥሮስም ‹‹የጌታችን ፈቃዱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ ተያይዘን ሱባዔ እንግባ›› ብሎ አዋጅ ነገረ::
...
በዓለም ያሉ ክርስቲያኖች ሁሉ በአንድ ልብ ሱባዔ ገቡ:: በሱባዔያቸው መጨረሻም ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ በግርማ ወደ እነርሱ ወረደ፤ እመቤታችን በቀኙ ነበረች፡፡
ሁሉንም ሐዋርያት በሩቅም በቅርብም ያሉትን ደቀ መዛሙርቱን በደመና ጠቅሶ ፊልጵስዩስ ሰበሰባቸው፡፡ ከዚያም በስተምሥራቅ ከከተማ ወጣ ወዳለ ሥፍራ ወሰዳቸው፡፡ በዚያም ተራርቀው የነበሩ 3 ደንጊያዎች ነበሩ፡፡ 3ቱንም ድንጋዮችን በተአምራት አቀራርቦ አንሥቶ ጎተታቸው፡፡ ድንጋዮቹም እንደሰም ተለጠጡ፣ እንደ ግድግዳም ሆኑ፡፡
ቁመቱን ወርዱን መጥኖ ለሐዋርያቱ ሠጣቸው፡፡ እነርሱም እሣት እንዳየው ሰም ከእጃቸው እየለመለሙ (እየተሳቡ) ቁመቱን 24 ወርዱን 12 ክንድ አድርገው ግርምት የምትሆን 3 ክፍል ያላትን #የመጀመሪያዋን_ቤተክርስቲያን #በ52_ዓ.ም #ሰኔ_20 ቀን አነጹ፡፡ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ፤ ጌታችንም በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም አምሳያ አድርጎ አነጻት፤ ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፡፡ ከዚህም በኋላ ጌታችን ለሐዋርያቱ ‹‹እንግዲህ እናንተም እንዲህ አድርጋችሁ ሥሩ፡፡›› ብሏቸው ዐረገ፡፡
...
በማግስቱ ሰኔ 21 ዕለት ደግሞ ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አእላፍ መላዕክትን፣ ሰማያውያን ቅዱሳንን እና እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን ይዟት ወረደ:: ሐዋርያቱ አብዛኞቹ እዛው ሲጸልዩ አድረው ነበርና ጌታችን ከቅዳሴው በፊት 2 ነገሮችን አሳየ፤ አስቀድሞ ቤተክርስቲያኗን በድንግል እናቱ ስም አክብሮ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አሳየ::
...
ቀጥሎ ደግሞ ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስን ከመካከል አቁሞ ‹‹አርሳይሮስ›› ሲል ሾመው:: ይኼውም የዓለም ሁሉ ሊቀ ዻዻሳት (ፓትርያርክ) ማለት ነው:: በዚህ ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ‹‹አክዮስ›› እያሉ 3 ጊዜ አሰምተው ጮሁ:: #አክዮስ ማለት በግዕዙ #ይደልዎ በአማርኛው ደግሞ #ይገባዋል_ያሥምርለት እንደ ማለት ነው::
...
ጌታችን ይህን ከከወነ በኋላ ይቀድስ ዘንድ ጀመረ:: አማናዊት ማኅደሩን ድንግል ማርያምን መንበር አድርጎ፣ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደ ተራዳኢ ካህን ቆሞ፣ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሠራኢ ዲያቆን ሆኖ፣ ሐዋርያት ድንግልን ከበው፣ መላእክተ ብርሃን በክብራቸው ቆመው ጌታችን ቀድሶ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለወዳጆቹ አቀበለ::
...
በዚያች ዕለት በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የማይችል ደስታ ተደረገ:: ከቅዳሴ በኋላ ጌታችን ሐዋርያትን አዘዛቸው:: ‹‹ከዚህ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም በእናቴ በማርያም ስም አብያተ ክርስቲያናትን አንጹ፤ ይህችን ዕለት የሚያከብራትን አከብረዋለሁ::›› ብሏቸው ከድንግል እናቱ ከመላዕክቱ ጋር ዐረገ::
...
#ሰኔ_ጎልጎታ፦
በሌላ በኩል ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም በዚህ ቀን (ሰኔ 21) ልጇን ወዳጇን ጐልጐታ ላይ ለኃጥአን ምሕረትን ለምናዋለች:: ጌታችንም ‹‹ስምሽን የጠራውን፤ በቃል ኪዳንሽ ያመነውን ሁሉ እምርልሻለሁ፡፡›› ብሏታል::
የፊታችን እሁድ በሁሉም አቢያተ ክርስቲያናት የሚቆመውን የእናታችንን ሙሉ #የማኅሌቱ_ሥርዓት አቅርበንላችኋል፡፡
መልካም የምስጋና ሌሊት ይሁንላችሁ!!!
የድንግል እመቤታችን ልመናዋ ክብሯ፣ ጣዕመ ፍቅሯና በረከቷ በሁላችን ላይ ይደርብን::
...
፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/
፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem
፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ Https://m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
#የሰንበት_ትምህርት_ቤቱ_ጥያቄ አሁንም አጭርና ግልጽ ነው፡፡
#ሕንጻ_ማስገንባት_የሚችል_ቋሚ_የመማርያና_ማስተማርያ_ቦታ_ቅጽረ_ቤተክርስቲያን_ውስጥ_ማግኘት_ብቻ፡፡
#ሕጻናቱ ብርድና ዝናብ በሚፈራረቅባቸው፣ የህጻናትን አዕምሮ መሰብሰብ በማይችሉ ቦታዎች እየተማሩ መሆናቸውን ልብ ይለዋል፡፡
በዚህ ምክንያት ብዙ ወላጆች ልጆቻቸውን ለመላክ ፈቃደኞች አይደሉም፡፡
ታዲያ ቤተክርስቲያን ልጀቿን የምታስተምርባቸው #የመማርያ_ክፍሎች አያስፈልጓትም?
ካልጠፋ ቦታ #አፀዶች_ተቆርጠው የሚሰጠንንስ ቦታ እንዴት በፀጋ እንቀበለዋለን? አፀዶች እንዲቆረጡ የሚያደርገው ውሳኔስ እንዴት ተቀባይነት ይኖረዋል?
#ጥንታዊ_አፀዶች_እንዲቆረጡ_እና_የሴቶች_መጠለያ_እንዲፈርስ_የሚያደርገው_ውሳኔ
ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለደብራችን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት የተጻፈው የውሳኔ ደብዳቤ እና ደብሩ ለሰ/ት/ቤቱ ሰጥቻለሁ ያለው ቦታ (#የሴቶች_መጠለያ) የሚከተሉትን #ሁለት_መሠረታዊ_ነጥቦች ያላገናዘበ ነው፡፡
…
#1ኛ_የደብሩን_አፀድ
የዚህ ታላቅ ደብር አፀድ በተለያዩ ሀገር በቀል ዛፎች የተከበበ ሲሆን አብዛኛውን ቦታ የሚይዙት ግን የጥድ ዕጽዋቶች ናቸው፡፡ በሌሎች አድባራትና ገዳማት ባልተለመደ መልኩ እንደ መቀነት #በሰባ_ሁለቱ_አርድዕት_ምሳሌ የተተከሉት ጥዶች ለሁለቱም አቢያተ ክርስቲያናት ግርማ ሞገስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ (ፎቶ ይመልከቱ)
እነዚህ ዕጽዋት በአዲስ አበባ መኖርዎትን እስከሚረሱ ድረስ መንፈስን የመግዛት፣ አእምሮን የመሰብሰብ፣ ኅሊናን የመመሰጥ አቅም ለደብሩ አላብሰውታል፡፡
ከአዲስ አበባና ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚመጡ ምእመናን በመጀመሪያ ከሚደነቁባቸው ነገሮች አንዱና ዋነኛው እስከ አሁንም ድረስ አፀዱ ተጠብቆ የመቆየቱ ጉዳይ ነው፡፡
#ፓትርያርክ_ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማቲያስ ለንግሥ በዓላት ወደ ደብሩ ሲመጡ ዓይናቸው የሚያርፈው የካህናቱ ሽብሸባ እና #የደብሩ_አፀዶች ላይ ነው፡፡ በመጡ ቁጥር የደብሩን አፀድ እንደ አዲስ እያዩ አድንቀው፤ ጠብቀው የቆዩትን አባቶች አመስግነው ይሄዳሉ፡፡
የአፀዱ ማማር ከተለያዩ የሀገራችን ገዳማትና አድባራት ብዙ መነኮሳትና ሊቃውንት ሲመጡ እንዲያርፉበትና የጸሎት ቦታቸው እንዲሆን አስችሏል፡፡
…
ይህ ከሀገረ ስብከቱ የተላከው የውሳኔ ደብዳቤ በቅዱስ ገብርኤል መጠለያ ውስጥ እና ከአካባቢው ያሉ አጸዶች እንዲቆረጡ ያደርጋል፡፡ እጅግ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህንን ውሳኔ ማደራጃ መምሪያው እንዳይወስን አስቀድመን በአካባቢው አጸዶች እንዳሉ ማሳሰባችን እና ይሄ ጉዳይ እየታወቀ መወሰኑ ነው፡፡
…
በአንድ ወቅት ከማደራጃ መምሪያው ኃላፊ #መምህር_እንቁባህርይ ጋር ባደረግነው ውይይት ስለሚቆረጡት የደብሩ አፀዶች ጉዳይ ሲነሳ ‘‘ደሞ ስለ አፀድ ምን አገባችሁ!? እሱ የምዕመናን ጉዳይ ነው፤ ለምን የተሰጣችሁን ቦታ አሜን ብላችሁ አትቀበሉም?’’ የሚል ምላሽ ነበር ያገኘነው፡፡ በውኑ እነዚህ ታሪካዊ የደብሩ አፀዶች የምዕመናን ጉዳይ ብቻ ናቸው? ካልጠፋ ቦታ አፀዶች ተቆርጠው የሚሰጠንንስ ቦታ እንዴት በፀጋ እንቀበለዋለን? አፀዶች እንዲቆረጡ የሚያደርገው ውሳኔስ እንዴት ተቀባይነት ይኖረዋል?
…
#2ኛ_የሴቶች_መጠለያ
የጸሎት ቤት የሆነቸው ቅድስት ቤተክርስቲያን ለምእመናን ካዘጋጀቻቸው የጸሎት ሥፍራዎች አንዱ የቤተክርስቲያንን አጥሮች ተጠግተው የሚሰሩ መጠለያዎች(ገረገራዎች) ናቸው፡፡ በእነዚህ መጠለያዎች ምእመናን ያስቀድሱባቸዋል፤ በግልና በማኅበር ሆነው ጸሎት ያደርሱባቸዋል፤ ከንስሐ አባቶቻቸው ጋር ሆነው ይመካከሩባቸዋል፤ ሱባኤ ይይዙባቸዋል፤ የተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮቻቸውን በመወያት ይፈቱባቸዋል፤ በማኅበር ጽዋ ይጠጡባቸዋል፡፡
…
በደብራችን ለወንዶች እና ለሴቶች የተሰሩ ሁለት መጠለያዎች አሉ፡፡ እነዚህ መጠለያዎች ለምእመናን ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ ቅዳሜ እና እሁድ ለሰ/ት/ቤቱ ሕጻናት ተማሪዎች መማርያ በመሆን የሰ/ት/ቤቱን የቦታ እጥረት ይቀርፋሉ፡፡ (ፎቶዎችን ይመልከቱ)
…
ይህ የደብሩን ደብዳቤ መሠረት አድርጎ የተወሰነው የሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ከቅዱስ ገብርኤል በስተ ቀኝ የሚገኘውን የሴቶች መጠለያ #ሙሉ_በሙሉ እንዲፈርስ ያደርጋል፡፡
ቢቻል ይህንን ገረገራ ከሚሰጠው ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች አንጻር በአዲስ መልክ እድሳት አድርጎና አስፋፍቶ መስራት ሲገባ እንዲፈርስ ውሳኔ መስጠት ግን እጅጉን አሳዛኝ ነው፡፡ መጠለያው መፍረሱ ከምንም በላይ ጸሎተኛ እና ሱባኤተኛ ምዕመናንን ይጎዳል፡፡ ካልጠፋ ቦታ መጠለያ ፈርሶ የሚሰጠንንስ ቦታ እንዴት በፀጋ እንቀበለዋለን? ገረገራ እንዲፈርስ የሚያደርገው የሀገረ ስብከቱስ ውሳኔ እንዴት ተቀባይነት ይኖረዋል?
#የቤተ_መቅደሱንስ_ግርማ_የሚጋፋ ሕንጻ እንዲተከል መፍቀድ እንዴት ልክ ይሆናል?
ግልጽና አጭር የሆነው የሰ/ት/ቤቱ ጥያቄ የሚፈልገው ግልጽና አጭርና መልስ ብቻ ነው፡፡ ጉዳዩን በዚህ መጠን ማወሳሰብ ተገቢ አይደለም፡፡
…
#ሰንበት_ትምህርት_ቤቱ_እንደሁል_ጊዜው_አባቶቹን_አክባሪ_ነው፡፡
ሰንበት ትምህርት ቤቱ ደብሩ በገቢ ሩሱን ለመቻል ለሚያደርገው ጥረት ሁሉ ደጋፊ ነው፡፡
ሰንበት ትምህርት ቤቱ ልማቱን በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት፣ በሀሳብ ለመርዳት ዝግጁ ነው፡፡
….
#የሰንበት_ትምህርት_ቤቱ_ጥያቄ አሁንም አጭርና ግልጽ ነው፡፡
#ሕንጻ_ማስገንባት_የሚችል_ቋሚ_የመማርያና_ማስተማርያ_ቦታ_ቅጽረ_ቤተክርስቲያን_ውስጥ_ማግኘት_ብቻ፡፡
#ሕጻናትና_ወጣቶች_ላይ_ትኩረት_አድርጋ_የማትሠራ_ቤተ_ክርስቲያን_ራዕይ_የሌላት_ናት_ብጹዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
...
፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/
፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem
፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ Https://m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
#ገሪማ_ገረምከኒ
ከዕለታት አንድ ቀን #አቡነ_ገሪማ መቁነን(ለገዳማውያን የሚሰጥ ምግብ) ተቀብለው ከሌሎች መነኮሳት ወንድሞቻቸው ጋር ወደ መንገድ ሲሄዱ ቤተ ክርስቲያን ያገኛሉ። ለመሳለም እጅ ሲነሱ የደብሩ ካህናት እየተቻኮሉ መጥተው “ቅዳሴ ሊታጎልብን ነውና ከእናንተ የሚቻለው አንድ ሰው ይርዳን እባካችሁ” አሏቸው።
የቀሩት መቁነናቸውን ቀምሰውት ነበር። #አቡነ_ገሪማ ግን ቋጥረው ይዘዋት ስለ ነበር ከቅጥሩ ውጭ አስቀምጠዋት ገብተው ቀድሰው ወጡ። እነዚያ አብረዋቸው የነበሩ መነኮሳትም አቡነ_ገሪማ በልተው የቀደሱ መስሏቸው ለታላቁ አባት አባ ጰንጠሌዎን ሄደው ነገሯቸው፤ አባ ጰንጠሌዎንም አዘኑ።
#አቡነ_ገሪማን አስጠርተው መነኮሳቱን “አድርጎት እንደሆነ እንዳያፍር፤ ለብቻው እንዳወራው ጥቂተ እልፍ በሉ!” አሏቸው። #አቡነ_ገሪማ ይህንን አውቆ “ሰዎች ብቻ አይደሉም፤ ዛፉም እንጨቱም ገለል ይበል” ቢሉ የቤተ ክርስቲያኑ አጸድ፣ እንጨቶችና ድንጋዮችም አንድ ምዕራፍ (800 ሜትር) ተጠራርገው ሸሹ።
አባ ጰንጠሌዎን ያዩትና የሰሙት ሁሉ ደንቋቸው “ወልድየ ይስሐቅ #ገረምከኒ (ልጄ ይስሐቅ ገረምከኝ)” አሏቸው። ከዚህ በኋላ ይስሐቅ የሚለው የቀድሞ ስማቸው ቀርቶ #ገሪማ ተባሉ።
አቡነ ገሪማ ወደ ገዳማቸው መደራ ሲሔዱ እነዚያ የሸሹ ዛፍና ድንጋዮች “ገሪማ ለእኛም ግሩም ነህ” እያሉ በዝማሬ ተከትለዋቸዋል።
ይህንን መሠረት በማድረግ ቅዱስ ያሬድ በመዝሙሩ “#ገሪማ_ገረምከኒ፤ አስኬማከኒ አልባቲ ሙስና። አባ ገሪማ አስገረምኸኝ፤ ለምንኵስናህም እንከን የለባትም።” በማለት አመስግኗቸዋል፡፡
#ዛሬ ሰኔ ፲፯ #በዓለ_ዕረፍታቸው ነው።
በረከታቸው ከእኛ ልጆቻቸው ጋር ትሁን!
፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክ
Watch "ባንተ ተሻገርን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መዝሙር" on YouTube
https://youtu.be/kxGTJYqELCE
የደብራችን አገልጋይ የሆነው #ዲያቆን_አብርሃም_ጸጋዬ #ቤተ_ክርስቲያናዊ በሆነ ዜማ ላሕይ የተዘጋጁ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙራትን አቅርቦልናል። ያድምጧቸው!
YOU TUBE 🔔 SUBSCRIBE 🔔
#ቤተ_አብርሃም_ዘቀጨኔ
ወንድማችንን ለበለጠ አገልግሎት ያትጋልን!
“...እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ፤
ቦኑ ለከንቱ #ኪዳንኪ ኮነ።
...ያለ በጎ ሥራ የምጸድቅ ካልሆነ፤ እመቤቴ ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ #ቃል_ኪዳንሽ በከንቱ ነበርን?”
(መልክአ ኪዳነ ምሕረት)
✥ ✥ ✥ በቃል ኪዳኗ ትጠብቀን ✥ ✥ ✥
‹‹ከ600 ካሬ ውጪ 599 ካሬ እንኳን ቢሆን ተቀባይነት የለውም፤ ከ600 ካሜ ያነሰ ስፋት ያለው ቦታ በማቅረብ ወደፊት እንደ አስፈላጊነቱ እንሰጣለን የሚለውን ሀሳብ አንቀበልም›› የሚሉትን ውሳኔዎች #ሙሉ_በሙሉ በመቀልበስ ከጋራ ውሳኔው ትንሽ እንኳን የማይቀራረብ 295 ካሜ እንዲሰጥ በመወሰኑ እና በጋራ ጉባኤው እንዲያጣራ የተሰየመው ኮሚቴ ‹‹በቀን 07/06/2012 በተወያየነው መሠረት የተዘጋጀ አለመሆኑን እንገልጻለን›› ብሎ ያቀረበውን የመስክ ሪፖርት #በዜሮ_ያባዛ_በመሆኑ ነው፡፡
…
ይህ የማደራጃው እና የሀገረ ስብከቱ ውሳኔ ወቅቱን የጠበቀ አለመሆኑም ሌላኛው አሳዛኝ ነገር ነው፡፡ በዓለማችን ላይ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ቤተክርስቲያን ለረጅም ጊዜ በመዘጋቷ፤ ሰ/ት/ቤቱ ምዕመናን የህክምና ባለሙያዎችን ምክር እየሰሙ ዳግመኛ የቅድስት ቤተክርስቲያን ደጆች እንዳይዘጉ ርብርብ በሚያደርግበት እና ለውሳኔው ይግባኝ መጠየቅ በማይቻልበት ሰዓት መምጣቱ ሌላው የውሳኔው አሳዛኝ ገጽታ ነው፡፡
…
#ይወቁት
ይህ ውሳኔ ከደብሩ እኩል የተተከሉት እድሜ ጠገብ ዛፎች #እንዲቆረጡ_ያደርጋል፡፡
ይህ ውሳኔ የሴቶች መጠለያ #ሙሉ_በሙሉ_እንዲፈርስ_ያደርጋል፡፡
ይህ ውሳኔ 100 ዓመታትን ያስቆጠረው የደብሩ ቅርስ የሆነውን_አጥር_ያፈርሳል፡፡
ይህ ውሳኔ #የቤተ_መቅደሱንም_ግርማ_የሚጋፋ_ሕንጻ_እንዲተከል ይፈቅዳል፡፡
ይህ ውሳኔ በቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ የንግሥ በዓላት ወቅት #ከፍተኛ_መጨናነቅ_እንዲኖር ያደርጋል፡፡
…
የሰ/ትቤቱ_ጥያቄ እሁንም አጭርና ግልጽ ነው፡፡
#ሕንጻ_ማስገንባት_የሚችል_ቋሚ_የመማርያና_ማስተማርያ_ቦታ_ቅጽረ_ቤተክርስቲያን_ውስጥ_ማግኘት_ብቻ፡፡
…
#ሰንበት_ትምህርት_ቤቱ_እንደሁል_ጊዜው_አባቶቹን_አክባሪ_ነው፡፡
ሰ/ት/ቤቱ ደብሩ በገቢ ራሱን ለመቻል ለሚያደርገው ጥረት ሁሉ ደጋፊ ነው፡፡
ሰ/ት/ቤቱ ልማቱን በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት፣ በሀሳብ ለመርዳት ዝግጁ ነው፡፡
…
#የሰንበት_ትቤቱን_የቋሚ_ቦታ_ጥያቄ_አወናብዶና_አጭበርብሮ_በማለፍ_ያሰብኩትን_አሳካለሁ_ማለት_ግን_ተገቢ_አይደለም፡፡
…
ስለ ነገዋ ቤተክርስቲያን የምትጨነቁ ከሆነ የሰንበት ትምህርት ቤትን አገልግሎት በልባችሁ አኑሩ፡፡›› ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስካልዕ
...
(LIKE, SHAREEE በማድረግ መልዕክቱን አስተላልፉ!!)፤
...
፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://
www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-16
20932764891482/
፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/
medihanaelem
፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ Https://m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
#ስለ_ነገዋ_ቤተክርስቲያን_የምትጨነቁ_ከሆነ_የሰንበት_ትምህርት_ቤትን_አገልግሎት_በልባችሁ_አኑሩ_ብጹዕ_አቡነ_ጎርጎርዮስ
✞ ✞ ✞
ጥቂት ለማይባል ጊዜ በሰ/ት/ቤታችን እና በደብሩ አስተዳደር መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ‘‘ይፈታል’’ የተባለውን ውሳኔ የያዘ ደብዳቤ ከሀገረ ስብከቱ ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት የመድረሱን ዜና ሰማን፡፡ እኛም የአለመግባባቱን መንስኤ ላልተረዱት ምዕመናንና አባላቶቻችን ጉዳዩን ግልጽ ለማድረግ እና የውሳኔውን #ኢ_ፍትሐዊነት ለማስረዳት ይህንን ጻፍን፡፡
…
የሰ/ት/ቤቱ የ55 ዓመታት ጉዞ አልጋ በአልጋ አልነበረም፤ ይልቁንም በበርካታ ተግዳሮችትና ፈተናዎች የታጀበ ነበር፡፡ ከእነዚህ ችግሮች ውስጥ ግን እንደ #ማስተማርያ_ቦታ_እጥረት ሰ/ት/ቤቱን በብርቱ የፈተነው የለም፡፡
ይህንን ችግር ለመቅረፍ እና ሰ/ት/ቤቱ በቂ የማስተማርያ ቦታ እንዲሰጠው በየዘመኑ ለተቀያየሩት የደብሩ አስተዳደር አካላት በተደጋጋሚ ጥያቄውን ቢያቀርብም ምላሽ ሳይሰጠው ቀረ፡፡ ይህ የቦታ ጥያቄ 2008ዓ.ም ላይ በተደራጀና በተጠና መልኩ የሰ/ት/ቤቱን የሕንጻ ዲዛይን እና የደብሩን ማስተር ፕላን አካትቶ ሰ/ት/ቤቱ የ50ኛ ዓመት በዓሉን ባከበረበት ወቅት ለደብሩ ቀረበ፡፡
ከብዙ ዓመታት ጥረት እና ትዕግስት በኋላ አጥጋቢ የሆነ ምላሽ ከደብሩ ተገኘ፡፡ ሰ/ት/ቤቱ ቀድሞ የነበረበት ቦታ ላይ (ያሁኑ #መዋዕለ_ሕጻናት ላይ) ለመንፈሳዊ ትምህርትና አገልግሎት የሚውል ሕንጻ የመዋዕለ ሕጻናቱ ውል ሲጠናቀቅ እንዲሠራ ፈቃድ ተሰጠው፡፡
…
ባሳለፍነው ዓመት የመዋዕለ ሕጻናቱ ውል ተጠናቆ ሰ/ት/ቤቱ የተሰጠውን ቦታ ሊረከብ ሲል አዲሱ የደብሩ አስተዳደርና ሰበካ ጉባኤ የቀድሞውን ሰበካ ጉባኤ ውሳኔ ሻረ፡፡ ወሉን ዳግመኛ ለ5ዓመታት አራዘመ፤ ከመንፈሳዊው ትምህርት ይልቅ በኪራይ ለሚገኘው ጥቂት ብር የሰ/ት/ቤቱ የዘመናት ጥያቄ በብር ተለወጠ።
…
ይሄ ዳግመኛ የተነሳው የማስተማርያ ቦታ ጥያቄ ሳይመለስና መቋጫ ሳያገኝ ደብሩ ሌላ ዕቅድ ይዞ ብቅ አለ፡፡ ‹‹የደብሩን ገቢ ለማሳደግ ለንግድ የሚውል ባለ 5 ወለል (G+5) ሕንጻ ለመገንባት›› ሰፊ እንቅስቃሴ ጀመረ፡፡ ይህንንም ህንጻ ለመገንባት አሁን ሰ/ት/ቤቱ ለትምህርት እና አገልግሎት የሚጠቀምበትን ቦታ መረጠ፡፡ (የሰ/ት/ቤቱ የቦታ ጥያቄ ሳይመለስ መሆኑን ልብ ይለዋል) ሰ/ትቤቱም በምትኩ በደብሩ ማስተር ፕላን ላይ ወደ ጸደቀለትና በቀድሞ ሰበካ ጉባኤ ወደ ተሰጠው (አሁን መዋዕለ ሕጻናት ወደ ሆነው) ቦታ እንዲዘዋወርና ደብሩም ያሰበውን ዕቅድ እንዲያስፈጽም ይሁንታውን ሰጠ፡፡
…
የደብሩ አስተዳደር በማስተር ፕላኑ ላይ ለሰ/ት/ቤቱ የተሰጠውን #ቋሚ_ቦታ ከመስጠት ይልቅ ለትምህርት ምቹ ያልሆኑ፣ ሌላ ተደራራቢ አገልግሎት ያለባቸው፣ ሰንበት ትምህርት ቤቱን የጽዋ ማኅበራት ላይ ጥገኛ የሚያደርጉ እንዲሁም አንዳንዶቹም ከቅጽረ ቤተክርስቲያን ውጭ የሆኑ ጊዜያዊ ቦታዎችን አቅረበ፡፡ ችግሩን በቋሚነት ከመፍታት ይልቅ ጊዜያዊና አጫጭር መፍሔዎች ላይ አተኮረ፡፡
…
የደብሩ አስተዳደር ለሕንጻው ግንባታ ያሳየውን ቁርጠኝነት ለሰ/ት/ቤቱ ጥያቄ መድገም አልቻለም፡፡ የሰ/ት/ቤቱን #የቋሚ_የቦታ_ጥያቄ ወደ ጎን በመተው ሕንጻውን ለመገንባት እንቅስቃሴውን አጠናከረ፡፡
…
ቀናት ቀናትን እየተኩ ሲሄዱ ልዩነቶች ሰፉ፡፡ የሰ/ት/ቤቱ አጭርና ግልጽ ሆነው የመብት ጥያቄ እንደ አለመታዘዝና አመጽ ከፍ ሲልም እንደ ሥርዓት አልበኝነትም ተቆጠረ፡፡ አጀንዳውን ቀይሮ ጉዳዩን የካህናት እና የሰ/ት/ቤት ጸብ ለማድረግ ተሞከረ፡፡ ጉዳዩን ለመፍታት ለቁጥር የሚታክቱ ስብሰባዎች ተደረጉ፤ መፍትሔ ጠቋሚ ጥናቶች ቀረቡ፤ በሽምግልና ተሞከረ፤ በርካታ የደብዳቤ ልውውጡች ተደረጉ፤ ከአካባቢው የጸጥታ አካላትም ጋር ሳይቀር ውይይቶች ተደረጉ፡፡ #መፍትሔ_ግን_ጠፋ፡፡
…
ይህ አለመግባባት ለዳኝነት ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሄደ፡፡ ችግሩን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመፍታት #የካቲት_7_2012ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት አስተዳደር መሰብሰቢያ አዳራሽ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ #በመምህር_እንቁባህርይ_ተከስተ ሰብሳቢነት፣ በመምሪያው ፀሐፊ በመምህር ሰሎሞን ኃይለማርያም ቃለ ጉባኤ ያዥነት፣ የደብሩ አስተዳዳሪና ጸሐፊ፣ የደብሩ የሰበካ ጉባኤና የልማት ኮሚቴ አባላት፣ የሰ/ት/ቤቱ ሥራ አመራሮች፣ የሰ/ት/ቤቶች አንድነት ኃላፊ #ቀሲስ_ሔኖክ፣ የአራዳና ጉለሌ ክፍላተ ከተማ ሰንበት ት/ት ቤቶች አንድነት ኃላፊ ዲያቆን ኢንጂነር አርአያ እንዲሁም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተወካዮች በተገኙበት ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኋላ የሚከተሉት #የጋራ_ውሳኔዎች ላይ ተደረሰ፡፡
…
1ኛ) ደብሩ ለሰ/ት/ቤቱ አገልግሎት የሚሆን፣ የወደፊት የሰ/ት/ቤቱን ሕንጻ ማስገንባት የሚችል #600_ካሜ_ቦታ #በቋሚነት_ቅጽረ_ቤተክርስቲያን ውስጥ እንዲሰጥ፤ ከ#600_ካ.ሜ ያነሰ 599 ካ.ሜ እንኳን ቢሆን ተቀባይነት እንደማይኖረው፣
2ኛ) ደብሩ የተባለውን #600_ካሜ ቦታ መስጠት ካልቻለ ሰ/ት/ቤቱ ከ40ዓመታት በላይ ሲገለገልበት የነበረውን አሁን #መዋዕለ_ሕጻናት የሆነውን ቦታ እንዲሰጥ
3ኛ) የደብሩ ሰበካ ገባኤ 600 ካሜ ቦታ በቋሚነት ለሰ/ት/ቤቱ መስጠቱን የሚያረጋግጥ ቃለጉባኤ እንዲልክ፣ ይህንንም በቦታው ላይ ተገኝተው ትክክለኛነቱን እንዲያረጋግጡ ቀሲስ_ሔኖክን፣ መምህር_ሰሎሞንን፣ ዲ/ን ኢንጂነር አርአያን፣ ኢንጂነር ሕሊናን ጉባኤው መርጦ በጸሎት ተጠናቀቀ፡፡ (ውሳኔዎቹ በቂ የድምጽ ማስረጃ የተያዘባቸው ናቸው፡፡)
…
ደብሩ እሰጣለሁ ያለው የሴቶች መጠለያ ቦታ (ከቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በስተ ግራ የሚገኘው) በደብሩ የልማት ቴክኒክ ኮሚቴ መሀንዲሶች ተለካ፤ ነገር ግን ግማሹ እንኳን አልተገኘም፤ 265 ካ.ሜ ብቻ ሆነ፡፡ በምህንድስና የግንባታ ሕግ መሠረትም ከአጥሩ መራቅ ያለበት (off set) 1.5ሜትር እና በመንገድ ሥራ ምከንያት የሚቀነሰው 1.5ሜትር ግምት ውስጥ ገብቶ ሲሰራ የተጣራ #108_ካሜ ብቻ እንደሆነ በደብሩ መሀንዲሶች ተረጋገጠ፡፡
…
ደብሩ ግን ለካሬ ማሟሟያ ብቻ እንዲሆን የሰንበት ትምህርት ቤቱን ሕንጻ ማስገንባት የማይችሉ እና እጅግ በጣም የተራራቁትን የሰ/ት/ቤቱን የንዋያተ ቅድሳት መሸጫ ሱቅ፣ ጽ/ቤት፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የአብነት ት/ቤቶች፣ የጽጌ ማኅበርተኞች አዳራሽ እና ካልጠፋ ቦታ #ታላቅ_ምሥጢር_የሚፈጸምበትን ክርስትና ቤት፤ ቤተልሔሙ ብቻ ሲቀር #ከደብሩ_መሐንዲሶች_ዕውቅና_ውጪ ሙያው የሌላቸውን ሰዎች በማስለካት እና ሆን ተብሎ የሰ/ትቤቱ የሰበካ ጉባኤ ተወካይ እንዳይገኝ በማድረግ 626 ካ.ሜ ሰጥቻለሁ አለ፡፡
…
የመስክ ምልከታ እንዲያደርግ እና አጣርቶ ሪፖርት እንዲያቀርብ የተሰየመው ልዑክ ደግሞ የሚከተለውን ሪፖርት አቀረበ፡-
‹‹ከ295ካ.ሜ ውጪ የተዘጋጀ ቦታ ካለመኖሩም ባሻገር ቀሪዎቹ ጊዜያዊ እንጂ ቋሚ ቦታዎች ከመሆናቸውም ባሻገር በቀን 7/06/2012ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት #በተወያየነውና_በደረስነው_መሠረት_የተዘጋጀ_አለመሆኑን_እንገላጻለን፡፡›› የሚል ነበር፡፡
…
በቀርቡ ግን ከሀገረ ሰብከቱ ለደብሩ ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት የተጻፈው እና የመምሪያውን ውሳኔው የያዘው ደብዳቤ ግን በቀን 7/06/2012ዓ.ም በጠቅላይ ቤተክህነት ከተደረሰበት ስምምነት #ፍፁም_ተቃራኒ የሆነና በተለመደው የቤተክህነቱ ብልሹ አሠራር የተተበተበ ነው፡፡
…
ይሄ ኢ-ፍትሐዊነት የተንጸባረቀበት ውሳኔ በሰንበት ትምህርት ቤቱ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡ ይኸውም ቃል በቃል..
ባሕራንም መልእክቱን ለማድረስ ዘጠኝ ቀን ተጉዞ የአንድ ቀን ጎዳና ሲቀረው እነሆ ክቡር የሚሆን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በንጉሥ ጭፍራ አምሳል በፈረስ ተቀምጦ ወደሱ ደረሰና ወዴት እንደሚሄድ ጠየቀው፡፡ ባሕራንም ‹‹ከአንድ ባለጸጋ ሰው የተጻፈ ደብዳቤ ይዤ እርሱን ለማድረስ ዕገሊት ወደምትባል አገር እሄዳለሁ›› አለው። ንዑድ ክቡር የሚሆን ቅዱስ ሚካኤልም "እስኪ የመልእክቱን ደብዳቤ አሳየኝ?" አለው፡፡ ባሕራንም ‹‹ጌታዬ ለማንም አታሳይ ብሎኛል›› አለው፡፡ መልአኩም ‹‹እሺ ያም ባይሆን እንደተጠቀለለ አሳየኝ›› አለው፡፡ ባሕራንም አሳየው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በሞቱ ደብዳቤ ላይ እፍ ቢልበት የሞቱን ትእዛዝ አጥፍቶ የሕይወት ትዕዛዝ ጽፎበታል፡፡ በደብዳቤው ላይ የተጻፈውን የሞት መልእክት ደምስሶ ‹‹ከእኔ ከባለጸጋ ዕገሌ የተጻፈ›› ይልና ‹‹ይህን መልእክት ይዞ ለመጣሰው ዕገሊት የምትባለዋን ልጄን አጋቡት (ዳሩለት) በዱር የተሰማራውን ከብቴን ፥ በቤት ያለውን ሀብቴን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረቴን በሙሉ አውርሼዋለሁና እኔ እስክመጣ ድረስ አትጠብቁ በሄድኩበት ሀገር የምቆይበት ጉዳይ አለኝና፤ በቤቴና በንብረቴ ላይ ሙሉ ሥልጣን ሰጥቼዋለሁና የወደደውን ያደርግ ዘንድ አትከልክሉት ስለዚህም በእኔና በአንተ መካከል የምንተዋወቅበትን ምልክት አድርጌበታለሁ›› የሚል ጽሑፍ ጻፈበት "እንግዲህ ወደ ባለጸጋው ቤት ሂድና ይህን መልእክት አድርስ አለው፤ ባሕራንም ‹‹እሺ ጌታዬ እንዳዘዝከኝ አደርጋለሁ›› ብሎ ጉዞውን ቀጠለና የዚያን የባለፀጋ ቤት እየጠየቀ ከደረሰበት በኋላ ደብዳቤውን ለሹሙ ሰጠው።
ያም ሹም ደብዳቤውን ተቀብሎ ሲያነብ የታተመበት ማኅተም ዕውነተኛ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ደንብ የባለጸጋውን ልጅ አጋባው፣ የሠርጉንም በዓል እስከ ፵ ቀን ድረስ በታላቅ ደስታ አከበሩ። ከሠርጉም በዓል ፍጻሜ በኋላ ያ ባለጸጋ ሰው ከሄደበት አገር ወደ ሀገሩ ተመልሶ ገባና በቤቱ አካባቢ ሲደርስ የደስታና የዘፈን ድምፅ ስለሰማ "ይህ የምሰማው ድምፅ ምንድነው?" ሲል ጠየቀ፡፡
ሰዎቹም ‹‹ባሕራን የተባለ ጐበዝ ካንተ ዘንድ ልጄን ዳሩለት የሚል ትእዛዝ አምጥቶ ልጅህን አግብቶ በሠርጉ ምክንያት ይዘፍናሉ ይደሰታ፤ እነሆ እየበሉና እየጠጡ በቀንና በሌሊት እየዘፈኑ ሲደሰቱ ፵ ቀን ሆኗቸዋል በመልእክትህም እንዳዘዝከው ገንዘብህን የወንድና የሴት ባሮችህን በጠቅላላው የሚንቀሳቀስና የማይንቀሳቀስ ንብረትህን ሁሉ በሙሉ አስረክበውታል›› አሉት። ያም ባለጸጋ ያህን ቃል በሰማ ጊዜ ከድንጋጤው የተነሳ በታላቅ ቃል በመጮኽ ከመሬት ላይ ተከስክሶ ሞተና ነፍሱን አጋንንት ተረክበው ወደ ሲኦል አወረዷት። ከዚህም በኋላ ባሕራን የተባለ ያ ጐልማሳ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ እያከበረ ዝክሩን እየዘከረ ይኖር ጀመር። በዚያን ጊዜ በጉዞ ላይ ሳለ ተገልጾለት የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት የለወጠለት ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነም አወቀ ተረዳ። ንዑድ ክቡር የሚሆን የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ያደረገው ተአምር ሊቈጥሩት የማይቻል ብዙ ስለሆነ በኛም ላይ ኃይለ ረድኤቱ አድሮብን ይኑር እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን፡፡
#፬. አፎምያን ያዳነበት
ቅድስት አፎምያ ሀገሯ ኪልቅያ ነው፡፡ ባለቤቷ አስተራኒቆስ መስፍነ ኪልቅያ ነበረ፡፡ በየወሩ በ29 ቀን የጌታችንን የልደቱን፣ ወር በገባ በ21 የእመቤታችንንና ወር በገባ በ12 የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያደረጉ ነዳያንን ይጎበኙ ነበር፡፡
ባለቤቷ አስተራኒቆስ ከዚህ ዓለም የሚያርፍበት ጊዜ እንደደረሰ ባወቀ ጊዜ ይሰጡት የነበረውን ምጽዋት እና የሦስቱን በዓላት መታሰቢያ ማድረግ እንዳታስታጕል ከአደራ ጋር አዘዛት፡፡ እርሷም የመልአኩን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ያሥልላት ዘንድ ባለቤቷን ጠይቃ አሠርቶ ሰጣት፡፡ በከበረ ቦታም አኖረችው፡፡ ባሏ ካረፈ በኋላ ያዘዛትን መንፈሳዊ ሥራ ከወትሮው አስበልጣ መሥራት ቀጠለች፤ ከሀብቷ ከንብረቷ እየሰጠች እየመጸወተች በጾም ፥ በጸሎት ተወስና ትኖር ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያርፍምና ደግ መነኵሴ መስሎ አጋንንትን መነኰሳይያት አስመስሎ መጥቶ ከደጅ ሆኖ አስጠራት፡፡
እርሷም ‹‹ከቤት ገብታችሁ በቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ፊት ጸልዩልኝ›› አለቻቸው፡፡ ሰይጣናቱም ‹‹እኛማ በነግህ ጸልየናል?›› አሏት፡፡ ቀጥሎም ሰይጣን ‹‹...እንደው አንቺ ግን ይህ ሁሉ ጾም ጸሎት ምን ያደርገልሻል? ሀብትሽን ሰጥተሸ መጨረስሽስ ስለምንድን ነው? በዚያ ላይ አንቺ ስትደክሚ የሚደግፍሽ ፥ ስታረጂ የሚጦርሽ ልጅ የለሽም ሁለተኛ ማግባት ኃጢአት መስሎሻልን? እነ አብርሃም እነ ዳዊት ከብዙ ሴቶች ብዙ ልጆች ወልደው የለምን? አሁንም ቤት ሰሪ፥ ጎመን ዘሪ ልጅ ያስፈልግሻልና ባል አግቢ፣ እሺ በይኝ›› አላት፡፡ ቅድስት አፎምያም ‹‹አባ ቆብህ መልካም ነበር ንግግርህ ግን ክፉ ነው፣ አትጹሚ፥ አትጸልዩ ያልከኝ፤ ጌታ ምጽዋትን መጽውቱ ብሎ የለምን? ሁለተኛ ባል አግቢ ማለትንስ ከምን አገኘኸው? ርግቦች እንኳን ባሎቻቸው ከሞቱባቸው ከሌላ ወንድ አይቀርቡም፤ ታዲያ ጥንት በንጽሕና ሊኖር የተፈጠረ ሰው ሁለተኛ አላገባም ቢል ዕዳ ፍዳ ሊሆንበት ነውን?›› ብላ ሞገተችው፡፡ የሰው ልጆች ጠላት የሆነው ሰይጣንም በመልካም አገልግሎት ስትበረታ አይቷታልና ዝም ብሎ ሊተዋት አልወደደም፡፡ ከላይ እንዳየነው በመጀመሪያ ባል ሳታገባ ማገልገሏን ትታ ሌላ ባል አግብታ ልጅ ወልዳ እንድትኖር በብዙ ማባበል ጠየቃት፡፡ ባሏ መንግሥተ ሰማያትን ስለወረሰ ምንም ምጽዋት እንደማይሻ አስመስሎ ነገራት፡፡ ቅድስት አፎምያ ግን ዳግመኛ ትዳር ላለመመሥረት ቃል ኪዳን እንደገባች ርግብንና ዖፈ መንጢጥን አብነት አድርጋ እነርሱ እንኳ በሕይወት ዘመናቸው ከአንድ ባል ውጪ ሌላ ባል እንደማያውቁ በመጥቀስ አሳቡን እንደማትቀበለው ገለጸችለት፡፡ ሰይጣንም አስመሳይ መሆኑ አላዋጣ ሲለው ማንነቱን ቀይሮ ሊያንቃት ቢሞክር የእግዚአብሔርንና የቅዱስ ሚካኤልን ስም ጠርታ አባረረችው፡፡ እርሱም ተመልሶ መጥቶ እንደሚያጠፋት ዝቶባት እንደአቧራ በኖ እንደ ጢስም ተኖ ጠፋ፡፡
በሰኔ 12 ቀን የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ እያዘጋጀች ሳለች ሰይጣን ብርሃናዊ መልአክ መስሎ መጣ፡፡ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ገልጾ የመጀመሪያውን የመሰለ ከንቱ ምክሩን አሰማምሮ አቀረበላት፡፡ አሳቡንም የእግዚአብሔር ፈቃድና አሳብ እንደሆነ አድርጎ ለማሳመን ቅድስት አፎምያም በእግዚአብሔር ኃይል ጸንታ በቅዱስ ሚካኤልም ተራዳኢነት ታምና ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ ከሆንክ መንፈሳዊ ማረጋገጫህ የሆነው የመስቀል ምልክት የታለ?›› በማለት በምድራዊ ንጉሥና በጭፍራው መካከል የሚኖርን የጋራ መግባቢያ መንገድ ዋቢ አድርጋ ጠየቀችው፡፡ ለጊዜው ‹‹በእኛ በመላእክት ዘንድ እንዲህ አይደለም›› ብሎ ሊሸነግላትና አቋሟን ሊያስቀይራት ሞከረ። ከቤቷ ያለ የቅዱስ ሚካኤል ሥዕል ላይ ያለውን ምልክት አብራርታ የእርሱ ግን ከዛ ጋር አንድነት እንደሌለው አረጋገጠችበት፡፡ በመቀጠልም ከቤቷ ላለው ለቅዱስ ሚካኤል ሥዕል እጅ እንዲነሣ ጠየቀችው፡፡ በዚህ ጊዜ መልኩ ወደ ትክክለኛ ሰይጣናዊ ማንነቱ ተለወጠና ጨለማ ለብሶ እየዛተ አነቃት፡፡ ቅድስት አፎምያም የከበረ መልአክ ቅዱስ ሚካኤልን "ድረስልኝ" እያለች በጠራችው ጊዜ መልአኩም ፈጥኖ በመድረስ ከሰይጣን እጅ አዳናት፡፡
የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለሰይጣኑ ተገቢውን ቅጣት ሰጥቶ ቅድስት አፎምያን ባረካት፡፡ የዕረፍት ቀኗ በዚህ ቀን መሆኑን ነግሮ ቤቷን እንድታዘጋጅ አዘዛት፡፡ የበዓሉን ዝግጅት አከናውና ሥጋ ወደሙን ተቀብላ ኤጲስ ቆጶሱንና ካህናቱን እንደየመዓርጋቸው ጠርታ በቤቷ አክብራ ተቀበለቻቸው፡፡ ለነዳያንና ለጾም አዳሪዎች በኤጲስ ቆጶሱና በካህናቱ እጅ ገንዘቧን መጽውታ መንገዷን አሳመረች፡፡ ስለ ኃጢአቷ እንዲጸልዩላት ተማፅና በፊታቸው ተንበርክካ ጸለየች፡፡ ባሏ ያሠራላትን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አቅፋ ስማ ከተማጸነች በኋላ ሰኔ 12 ቀን በሰላም ዐረፈች፡፡
#፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ማሳረጉን፤ ወደፊት ውቅር አብያተ ክርስቲያናትን እንደሚያንጽ ጌታችን የነገረውና የሕንጻዎቹን አሠራር ዝርዝር የነገረው በዚሁ እለት ነው፡፡
፠ በፌስቡክ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://www.facebook.com/የቀጨኔ-ደብረ-ሰላም-መድኀኔዓለምና-ደብረ-ትጉሃን-ቅዱስ-ገብርኤል-ቤተ-ክርስቲያን-ፍኖተ-ሕይወት-ሰንበት-ትምህርት-ቤት-1620932764891482/
፠ በቴሌግራም ሊያገኙን ከፈለጉ፤ https://t.me/medihanaelem
፠ በዩቲዩብ ሊያገኙን ከፈለጉ፤ Https://m.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w
እንኳን አደረሰን፡፡
ሰኔ ቅዱስ ሚካኤልና ሥርዐተ ማኅሌት፡፡
#ሰኔ_፲፪ #መከበሩ_ስለምንድን_ነው_ቢሉ_፤
ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር፤ ንሥረ አርያም የሚባል፥ ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ፥ ንዑድ ክቡር የሆነ ፥ የመላእክት ሁሉ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ፭ት ነገሮችን የፈጸመበት እለት ስለኾነና የሌሎችም ቅዱሳን መታሰቢያ ቀናቸው ስለኾነ ነው፡፡ እነርሱም፤
፠፩. በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል፤
፠፪. ባሕራንን ያዳነበት፤
፠፫. የአስተራኒቆስ ሚስት ቅድስት አፎምያን ያዳነበት፤ በዓለ እረፍቷም በዚሁ እለት ነው፤
፠፬. በግብፅ ሃገር ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ ቅዳሴ ቤቱን ያከበረበት፤
፠፭. ቅዱስ ላሊበላን ወደ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ያሳየበት፤
፠ ሐናፄ መቅደስና በሰማያት ያለ ምሥጢርን የተመለከተ ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ በዓለ ዕረፍቱ ነው፤
፠67ኛ ሊቀ ጳጳስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት ዘእስክንድርያ እረፍቱ ነው፤
፠የእስክንድርያ 6ኛ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ዮስጦስ (ወንጌላዊና ሐዋርያው ቅዱስ ማርቆስ የክርስትና ጥምቀትን ያጠመቀው፥ ዲቁናና ቅስናን የሾመው) እረፍቱ ነው፡፡
/ከቀጨኔ ደ/ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደ/ት/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ/ት/ቤት ሰሌዳ መጽሔት/
ማብራሪያ፤
#፩. ቅዱስ ሚካኤል በፈቃደ እግዚአብሔር ከዲያብሎስ ጋር ተዋግቶ ያሸነፈበት፤ አምላክነትን ሽቶ በወደቀው በዲያብሎስ ምትክ ሊቀ መላእክት ሆኖ የተሾመበት እለት በመሆኑ ነው፡፡ ቀድሞ ከ100 ነገደ መላእክት ኃይላት የሚባሉ የ10 ነገደ መላእክት አለቃ ነበር፤ በዚህች ቀን ግን የኃይላት አለቅነቱን እንደያዘ አጋእዝት የተባሉትንና ሳጥናኤል(ሰማልያል) ይመራቸው ለነበሩት 10 ነገዶች በተጨማሪ አለቃ ኾኗል፤ እንዲሁም በአጠቃላይ ለሌሎችም 100 (99ኝ) ነገደ መላአክት አለቃ ሁኗል፡፡ ልዑል ውእቱ ልዑለ መንበር ያሰኘውም ይኸው ነው፡፡
#፪. ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት፤ ፓትርያርክ እለ እስክንድሮስ /312 - 326/ በግብፅ ሃገር ንግሥት ክሌዎፓትራ ‹‹ሳተርን›› ለሚባለው ያሠራችውንና ጣዖት ይመለክበት የነበረውን ቤተ ጣዖትን አፍርሶ በቦታው ላይ ቤተ ክርስቲያን ሠርቶ ታቦተ ሚካኤልን አግብቶ በዓሉን በታላቅ ክብር ያከበረበት እለት ነው፡፡
#፫. ባሕራንን ያዳነበት
ሊቀ ጳጳሳት እለ እስክንድሮስ የተሠራውን የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ከሚያከብሩ ምእመናንን አንዱ የባሕራን አባት ነበር፡፡ እርሱም እግዚአብሔርን የሚፈራ ወር በገባ በየዐሥራ ሁለቱ ቀን የቅዱስ ሚካኤልን ዝክሩን የሚዘክርና ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን በታላቅ ክብር የሚያከብር አንድ ሰው ነበር፤ በዚህ ሰው ላይ ላይ ጥላቻ ያደረበትና ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለጸጋ ጐረቤት ነበረው፡፡ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በሚያከብርበት ጊዜ ሁሉ ይዘብትበት ይሳለቅበት ነበር፡፡
ይህ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰውም በዚህ ዓይነት በጐ ሥራ ብዙ ጊዜ ከኖረ በኋላ ከዚህ ዓለም ድካም ያርፍ ዘንድ የሞቱ ጊዜ ቀረበ። ሚስቱንም ጠርቶ ‹‹በጐ ስራ ከመሥራት ለድኃ ከመመጽወት ቸል አትበይ! የቅዱስ ሚካኤልንም በዓል በየወሩ ከማክበር አትቦዝኝ፤ ይልቁንም በኅዳር ፲፪ትና በሰኔ ፲፪ት ቀን ከፍ ባለ ሥነ ሥርዓት እንድታከብሪ አደራ እልሻለው›› አላት፡፡ በሚሞትበትም ጊዜ ሚስቱ ፀንሳ ነበር። ይህም ደገኛ ሰው በሰላም ዐረፈና ፍጹም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰ። ሚስቱም የመውለጃዋ ሰዓት በደረሰ ጊዜ ታላቅ ጭንቅ ላይ ኾነች እርሷም መልአኩን ቅዱስ ሚካኤል እንዲደርስላት ተማጸነችው በሰላምም ተገላገለች፡፡ መልኩ በጣም ያማረ ልጅ ወለደች። የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤልም ከሰማይ ወርዶ ያን ሕፃን ባረከውና ‹‹ቸርነት ርኅራኄ የሌለውን የዚህን ባለጸጋ ገንዘብና ሀብት እርሻውንም ሁሉ ይህ ሕፃን እንዲወርስ እግዚአብሔር አዟል›› አለ። ያን ጊዜ ያ ባለጸጋ በሴትዮዋ ቤት መስኮት አጠገብ ሆኖ ሁኔታውን ሁሉ ይመለከት ነበርና ይህን ነገር በሰማ ጊዜ ልቡ በታላቅ ሐዘን ተነካ፤ ሕፃኑንም የሚገድልበትን ምክንያት ይፈልግ ጀመር፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ብላቴናውን ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀው ነበር።
ብላቴናውም ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ እናቱ በጣም ችግር ፀናባት፡፡ ባለጸጋው እኔ ጋር ተንከባክቤ ላሳድገው ብሎ ከእናቱ ከተቀበለ በኋላ፤ በልጅ ቁመት ልክ ሳጥን አሠርቶ ሕፃኑን በሣጥኑ ውስጥ አግብቶ በላዩ ላይ ቆለፈበትና ሣጥኑን ወስዶ ከባሕር ጨመረው፤ እንዲሁም የሣጥኑን ቁልፍ መክፈቻ አብሮ ወረወረው። ነገር ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ያ ሣጥን ሳይሰጥም በባሕሩ ላይ እየተንሳፈፈ ከዚያች አገር ርቃ ወደምትገኝ የባሕር ወደብ ደረሰ።
በባሕሩ አካባቢ በጎቹን አሰማርቶ የሚጠብቅ አንድ ሰው ነበርና ያንን ሣጥን ባየው ጊዜ ከባሕሩ አወጣውና ወደ ቤቱ ወስዶ ሣጥኑን ቢከፍተው ያ ባለ ፀጋ ሊገድለው ያሰበውን ሕፃን በሣጥኑ ውስጥ አገኘው። ባየውም ጊዜ እጅግ ተደስቶ በባሕር ውስጥ ስላገኘው ስሙን "ባሕራን" ብሎ ሰየመውና እንደ ልጁ አድርጐ ይንከባከበው ዘንድ ወሰነ፡፡
ከባሕራን ሀገር የበግ ጠባቂው አገር የዐሥር ቀን ጐዳና የሚያስኬድ ርቀት ነበረው። ከብዙ ዓመታት በኋላ ያ ባለ ጸጋ ሰው ለንግድ ከሀገሩ ወጣ፡፡ በጉዞውም ላይ ሳለ ፀሐይ ስትገባ ከዚያ የበግ ጠባቂው ዘንድ ደረሰ። በግ ጠባቂውንም ‹‹ወንድሜ ሆይ ባንተ ዘንድ የማድርበት ቢኖር ታሳድረኝ ዘንድ እለምንሃለው፣ ኪራዩንም እከፍልሃለው›› ብሎ ጠየቀውና ያ በግ ጠባቂ ወደ ቤቱ አስገባው። ባለጸጋውም ገብቶ ጥቂት ካረፈ በኋላ በግ ጠባቂው ያን ብላቴና ባሕራን ብሎ ሲጠራው በሰማ ጊዜ ‹‹ልጅህ ነውን?›› ብሎ ጠየቀው። በግ ጠባቂውም ‹‹አዎን ይህ አሁን ጐልማሳ ሆኖ የምታየው ወጣት ገና ሕፃን ሆኖ ሳለ በሣጥን ተከቶ ከባሕር ውስጥ ተጥሎ አግኝቼው ወስጄ አሳድጌዋለሁና ልጄ ነው›› አለው። ባለጸጋውም በባሕር ውስጥ የጣለው ሕፃን መሆኑንም ስላወቀ ይህንን ነገር በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደነገጠ፤ ይገድለውም ዘንድ ፈለገ፡፡ በበነጋውም መንገዱን ለመሄድ ሲዘጋጅ ልዩ ልዩ ምክንያት (ሰይጣናዊ ሐሳብ) በመፍጠር በግ ጠባቂውን ‹‹ወንድሜ ሆይ አንድ የማስቸግርህ ጉዳይ አለኝ ይኸውም በቤቴ የረሳሁት ነገር ስላለ ሄዶ መልእክት ያደርስልኝ ዘንድ ይህን ብላቴና እንድትሰጠኝ ነው የድካሙንም ዋጋ ሃያ ወቄት ወርቅ እከፍላለሁ›› አለው።
ያም በግ ጠባቂ ስለ ወርቁ ስጦታ ደስ በመሰኘት ያን ጐልማሳ ጠርቶ ‹‹ልጄ ባሕራን ሆይ ይህ ክቡር ሰው ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤቱ ሊልክህ ይፈልጋልና መልእክቱን አድርስለት እግዚአብሔር በሰላም ያግባህ›› ሲል ጠየቀው፡፡ ልጁም ‹‹እሺ መልካም ነው አባቴ ሆይ ያዘዝከኝን ሁሉ ለመፈጸም ዝግጁ ነኝ›› አለው። ከዚህም በኋላ ያ ባለጸጋ ‹‹ይህችን የመልእክት ደብዳቤ ይዞ ወደ አንተ የመጣውን ስሙ ባሕራን የተባለውን መልእክቷ በደረሰችህ ጊዜ ፈጥነህ ግደለው፤ ገድለህም ሬሣውን ከጉድጓድ ጣለው እኔ በሰላም ተመልሼ እስክመጣ ድረስ ማንም ማን ይህን ምሥጢር አይወቅ›› የሚል ጽሑፍ ለሹሙ ጽፎ አዘጋጀ፤ በአገልጋዩ (በሹሙ)ና በእርሱ መካከል የሚተዋወቁበትን ማኅተም በደብዳቤው ላይ አትሞ ለባሕራን ሰጠው፡፡ ለመንገዱም የሚሆነው ስንቅ ሰጥቶ ላከው።
