ch
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 366 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 631,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 191

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 366 名订阅者。

根据 20 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -39,过去 24 小时变化为 -5,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 22.39%。内容发布后 24 小时内通常能获得 7.98% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 441 次浏览,首日通常累积 1 226 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

凭借高频更新(最新数据采集于 21 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 366
订阅者
-524 小时
+297
-3930
帖子存档
ፍቅረ ድንግል በየነ ዓሊ 1928 - 2016 ፣ዓ.ም ሥርዓተ ቀብራቸው በቀጨኔ መድኀኔ ዓለም ከ5-6 ይፈጸማል ። ፍቅረ ድንግል በየነ ዓሊ ከንቡረ ዕድ በየነ ዓሊ እና ከወይዘሮ ሰላመ ድንግል ተክለጊዮ
ፍቅረ ድንግል በየነ ዓሊ 1928 - 2016  ፣ዓ.ም ሥርዓተ ቀብራቸው በቀጨኔ መድኀኔ ዓለም ከ5-6 ይፈጸማል ። ፍቅረ ድንግል በየነ ዓሊ ከንቡረ ዕድ በየነ ዓሊ እና ከወይዘሮ ሰላመ ድንግል ተክለጊዮርጊስ በ 1928 ተወለዱ ። አቅማቸውም እስከደከመ ድረስ ፥  ከአባታቸው  ከንቡረ ዕድ ጋር በመሆን  በተለይ በዘመነ ጽጌ ላይ እንዲኁም  በዐቢይ ፆም  እሑድ ፥ መወድስ  በመቀኘት  ለረጅም ጊዜ አገልግለዋል ። በልዩ የቅኔ አዋቂነታቸው  ይታወቁ ነበር ። የፍቅረ ድንግልን ነፍስ ከአብርሃም ከይስሐቅ  ጋር ይደምርልን ።

#ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_በሥዕሉ_ላይ_አድሮ_ቅዱሳን_የሆኑ_ባስልዮስንና_ጎርጎርዮስን_በመርዳት_ከሃዲውን_ንጉሥ_ዑልያኖስን_የገደለበት_ዕለት_ነው፡፡ #ራሱን_የሸጠው_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ከበሬ_ጋር_ተጠምደው_በማረስ_ሰማዕትነትን_የተቀበሉት_አቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ልደታቸው_ነው፡፡ **ዳግመኛም በዚህ ዕለት፤ #ስብስትያኖስ_ሰባስትያኖስ_ሰማዕት_ጥር_25 ፠ በሕመም፥ በጭንቅ፥ በመከራ፥ በስቃይ፥ #በደዌ_ዳኛ፥ #በአልጋ_ቁራኛ_ላይ_ያላችሁ_ሁሉ በእምነት የሰማዕቱ የቅዱስ ስብስትያኖስን ስሙን ጥሩት፥ ገድሉን አድምጡ ተሻሹ፥ እምነቱን ተቀቡ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለሙ #ፈዋሽ_ሰማዕት_ነው፡፡ #ፈትለ_ሥላሴ በመባል በሚጠራው ቤ.ክ. (ከአዲስ አበባ በሞጣ/በደብረ ድማኅ/ በኩል ወደ ባሕር ዳር ሲሄዱ አዴት ከተማ ከመድረስዎ በፊት ዠማ ወንዝ ለመድረስ ሲቃረቡ ያገኙታል)፡፡ ጥር 25 ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ እንዲሁም በጥንታውያን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የብራና ገድሉ ስላለ አስነብቡ፥ ተሻሹ፤ ፍጹም ፈውስን ታገኛላችሁ፡፡ ፠ ሰባ(ስብ)ስትያኖስ ሰማዕት፤ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው በጽኑ ሕማምና ስቃይ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው፡፡ በተለይም በሕመም፤ በጭንቅ መከራ፤ በስቃይ ውስጥ ኾኖ ያለ ሰው አምላከ ሰብስትያኖስ ብሎ ለጠራኝ እደርስለታለሁ ብሎ በማይታበል ቃሉ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የሰጠው ሰማዕት ሲኾን ለጠሩትም ፈጥኖ የሚደርስ ሰማዕት ነው፡፡ ፠ የስብስትያኖስ አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይፈውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን እያሳረደ አብያተ ክርስቲያናትንም ማቃጠል ጀመረ፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች(ቀስቶች) ሰውነቱን አስነደፈው፤ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡ ፠ ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስደበድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በጥር 25 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም፥ የሕመም ስቃይና መከራ እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡ /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/    #share  .Telegram... https://t.me/medihanaelem      www.finotehiwotsundayschool.com .Facebook...  https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w http://tiktok.com/@finotehiwot #ቅዱሳን  #Saints  #ክብረ_በዓላት #Feasts

#ስብስትያኖስ_ሰባስትያኖስ_ሰማዕት_ጥር_25 ፠ በሕመም፥ በጭንቅ፥ በመከራ፥ በስቃይ፥ #በደዌ_ዳኛ፥ #በአልጋ_ቁራኛ_ላይ_ያላችሁ_ሁሉ በእምነት የሰማዕቱ የቅዱስ ስብስትያኖስን ስሙን ጥሩት፥ ገድሉን አድምጡ ተሻሹ፥ እምነቱን ተቀቡ፥ ቤተ ክርስቲያኑን ተሳለሙ #ፈዋሽ_ሰማዕት_ነው፡፡ #ፈትለ_ሥላሴ በመባል በሚጠራው ቤ.ክ. (ከአዲስ አበባ በሞጣ/በደብረ ድማኅ/ በኩል ወደ ባሕር ዳር ሲሄዱ አዴት ከተማ ከመድረስዎ በፊት ዠማ ወንዝ ለመድረስ ሲቃረቡ ያገኙታል)፡፡ ጥር 25 ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ይከበራል፡፡ እንዲሁም በጥንታውያን ታላላቅ ገዳማትና አድባራት የብራና ገድሉ ስላለ አስነብቡ፥ ተሻሹ፤ ፍጹም ፈውስን ታገኛላችሁ፡፡ ፠ ሰባ(ስብ)ስትያኖስ ሰማዕት፤ በስዕሉ ላይ እንደምንመለከተው በጽኑ ሕማምና ስቃይ ሰማዕትነትን የተቀበለ ነው፡፡ በተለይም በሕመም፤ በጭንቅ መከራ፤ በስቃይ ውስጥ ኾኖ ያለ ሰው አምላከ ሰብስትያኖስ ብሎ ለጠራኝ እደርስለታለሁ ብሎ በማይታበል ቃሉ እግዚአብሔር አምላካችን ቃል ኪዳን የሰጠው ሰማዕት ሲኾን ለጠሩትም ፈጥኖ የሚደርስ ሰማዕት ነው፡፡ ፠ የስብስትያኖስ አባቱ የሮሙ ንጉሥ ሲሆን ሃይማኖቱ የቀናና እግዚአብሔርንም የሚወድ ስለነበር ልጁን የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እያስተማረ ፈሪሃ እግዚአብሔርን እያስተማረ አሳደገው፡፡ አባቱም ከሞተ በኋላ ከሃዲያኑ ዲዮቅልጥያኖስና መክስምያኖስ ነገሡ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስንም አገረ ገዥ አድርገው ሾሙትና እንደ አባቱ እጅግ አድርገው አከበሩት፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ በጥበብና በማስተዋል የሚጓዝ ነው፡፡ በተጋድሎ ሕይወቱ የተመሰገነ ሆነ፡፡ እግዚአብሔርም በእጆቹ የተለያዩ ተአምራትን ገለጠ፡፡ ድውያንን ይፈውሳል፤ በጸሎቱም የዕውራንን ዐይኖች ያበራል፡፡ በእንዲህም ዓይነት በተጋደሎ ሲኖር ዲዮቅልጥያኖስ እግዚአብሔርን ክዶ በዓለም ላይ ያሉ ክርስቲያኖችን እያሳረደ አብያተ ክርስቲያናትንም ማቃጠል ጀመረ፡፡ ይኸውም ከሃዲ አገረ ገዥ አድርጎ ሾሞትና በእጅጉ አክብሮት የነበረውን ቅዱስ ስብስትያኖስን አሁን ለጣዖት እንዲሰግድ ግድ አለው፡፡ ፠ ቅዱስ ስብስትያኖስ ግን የከሃዲውን ንጉሥ ትእዛዝ ቸል በማለት በፊቱ ቆሞ የጌታችንን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፤ ጣዖታቶቹንም ረገመበት፡፡ ንጉሡም በዚህ ጊዜ በታላቅ ቁጣ ሆኖ ቅዱስ ስብስትያኖስን ብዙ አሠቃየው፡፡ ከግንድ ጋር አሥሮ በብዙ ፍላጻዎች(ቀስቶች) ሰውነቱን አስነደፈው፤ በዚህም ጊዜ እንደሞተ አስበው ትተውት ሄዱ፡፡ ምእመናንም ሥጋውን ለመውሰድ በሌሊት ቢመጡ በሕይወት አገኙትና ወስደው በደሴት መካከል አስቀመጡት፡፡ ፠ ዲዮቅልጥያኖስም የቅዱስ ስብስትያኖስን በሕይወት መኖር ሲሰማ ድጋሚ አስመጣውና በብረት ዘንጎች ሲያስደበድበው ዋለ፡፡ ለብዙ ቀናትም እንዲሁ በብረት ዘንግ ሲያስደበድበው ቆየ፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም በጥር 25 ቀን ነፍሱ ከሥጋው ተለየችና የሰማዕትነት ፍጻሜው ሆነ፡፡ ጌታችንም መታሰቢያውን ለሚያደርግና ስሙን ለሚጠራ የቸነፈር ሕመም፥ የሕመም ስቃይና መከራ እንዳይቀርበው ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ቅዱስ ስብስትያኖስም ካረፈ በኋላ ውሉዱስና ለምትባል ለአንዲት ቅድስት ሴት ተገለጠላትና ቅዱስ ሥጋው ያለበትን ነገራት፡፡ እርሷም ወደ ከበሩ ቅዱሳን ጴጥሮስና ጳውሎስ መቃብር ወስዳ ቀበረችው፡፡ #ሰላም_ለዝክረ_ስምከ_ዘይትበደር እምብሩር፤ ወይጥዕም እም ሶከር፡፡ ሰባስትያኖስ ንጹሕ ትሩፈ ምግባር፤ በዝክረ ስምከ ተማኅጸንኩ ኢትኅድገኒ ለገብር፤ አመ ትወፅዕ ነፍስየ እምሥጋ በግብር፡፡ #ሰላም_ዕብል_ለፍጽምከ_መአድም፤ በስመ ሥላሴ ኅቱም፡፡ ሰባስትያኖስ አቡየ ሰላም ሰላም፡፡ በፍጽምከ ተማኅጸንኩ ኢይቅርበኒ ሕማም፤ ማዕተበ ፍጽምከ በፍጽምየ ሢም፡፡ #ሰላም_ለመልክዕከ_ዝብጠታተ ኀጺን ዘተወክፋ፤ ወትዕግስታተ አዝለፋ፡፡ ሰባስትያኖስ ጻማዊ ሱታፌ ሕማሙ ለዘልፋ፤ መልክዐ ገጽከ ኀበ ተጽሕፋ፥ ለመለክዕየ ጸሐፋ፤ ውስተ ምዕራፍከ ረሲ ምዕራፋ፡፡ **ዳግመኛም በዚህ ዕለት፤ #ሰማዕቱ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_በሥዕሉ_ላይ_አድሮ_ቅዱሳን_የሆኑ_ባስልዮስንና_ጎርጎርዮስን_በመርዳት_ከሃዲውን_ንጉሥ_ዑልያኖስን_የገደለበት_ዕለት_ነው፡፡ #ራሱን_የሸጠው_ቅዱስ_ጴጥሮስ_ዕረፍቱ_ነው፡፡ #ከበሬ_ጋር_ተጠምደው_በማረስ_ሰማዕትነትን_የተቀበሉት_አቡነ_ሕፃን_ሞዐ_ልደታቸው_ነው፡፡ Facebook  https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool YouTube    https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w Telegram https://t.me/medihanaelem

እንኳን አደረሳቹሁ #ጥር21_አስተርእዮ_ማርያም_ ( #በዓለ_ዕረፍታ_ለማርያም_(ለሶልያና ) #እመቤታችን_በ64_ዓመቷ_ጥር_21_በ49ዓም_ያረፈችበት_ዕለት_መታሰቢያ_ክብረ_በዓል_ነው፡፡ #ተናገራ_ዕዝራ_ተናገራ_ዳዊት_ዘመራ፤ #ዕዝራ_በመሰንቆ_ዳዊት_በበገና_እያጫወቷት፤ #ሳታውቀው_አለፈች_ያንን_መራራ_ሞት፡፡ ፠ ጌታችን ለእናታችን ለቅድስት ማርያም ብዙ ቃልኪዳንን ከገባላት በኋላ፤ ቅድስት ነፍሷን ከክብርት ሥጋዋ ለይቶ በቃለ አቅርንት፥ በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት ደመና ጠቅሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ በአጎበር አድርገው እናትና  አባቷ  ወደተቀበሩበት  ወደ ጌቴ  ሴማኒ  ሲወስዷት  አይሁድ  አይተው፤  ልጇ ተነሳ፥ አረገ  እያሉ ሲያውኩን ኖሩ አሁን ደግሞ እሷ ተነሳች፥ አረገች እያለ ሉያውኩን አይደለምን? ንዑ ናዓውያ ሥጋሃ ለማርያም /ኑ ሥጋዋን እናቃጥልባቸው/ ብለው ተነሱ፤ ለዚሁም ከመካከላቸውም ታውፊኒያ የተባለውን የጎበዝ አለቃ መረጡ፤ እርሱም የአልጋዋን ሸንኮር ሊያቃጥል ሲይዝ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ሁለት እጁን በሰይፍ ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማፀናት እራሷን ዘምበል አድርጋ ቅዱስ ጴጥሮስን እንደነበረው  አድርግለት ብላ አዘዘችው፤ እርሱም እጁን አድኖለታል፡፡ ከዚህ  በኋላ ጌታችን ከመካከላቸው ነጥቆ ከገነት ከዕፀ ሕይወት ስር አኑሯታል፡፡ ….. ሐዋርያት የቀበሯት ግን ከ6 ወር በኋላ በነሐሴ 14 ነው  ----›እርሱን እዚህ ያንብቡ ----›https://t.me/medihanaelem/6840፤ ‹‹ሞት በጥር ነሐሴ መቃብር እንዲሉ፡፡››ረፍታ ለሶልያና(ለማርያም) ወረደ ወልድ ዲበ እምዲበ ልዕልና ወረደ፡፡ #ሶልያና_የእመቤታችን_የማርያም_ሌላ_ስሟ_ነው፡፡ *የእመቤታችንን ዕረፍት ሊቁ ቅዱስ  ያሬድም  ‹‹ሞትሰ  ለመዊት ይደሉ፥  ሞታ  ለማርያም የአጽብ ለኵሉ፡፡ /ሞት ለሚሞት ሰው ሁለ የተገባ ነው፥ የማርያም ሞት ግን ሁለን ያስደንቃል፡፡›› በማለት አደንቆ ጽፏል፡፡ *እንደየደብራችሁ ይትበሃል ትጠቀሙበት ዘንድ የላይ ቤት (የግምጃ ቤት ማርያም) አብነትና የታች ቤት(የበዓታ) አብነትን ሁለቱንም አዘጋጅተንላችኋል፡፡ መልካም ክብረ በዓል፡፡ **ክብረ በዓሉ በሃገራችንና በዓለማችን ክፍሎች ባሉ የእመቤታችን አብያተ ክርስቲያናት የሚከብሩ ቢሆንም ግን፤ በልዩ ሁኔታ እንደ ጎንደር አዘዞ ሎዛ ማርያም ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ግን እንደ ጥምቀት በዓል፤ ከዋይዜማው ጀምሮ ወደ ጥምቀተ ተወርዶ በማደር ክብረ በዓሉ በልዩ ሁኔታ መከበሩን ልብ ይሏል:: /በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት ሕትመት እና ሚዲያ ንዑስ ክፍል የተዘጋጀ ::/    #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot      www.finotehiwotsundayschool.com #ቅዱሳን  #Saints  #ክብረ_በዓላት #Feasts   #Our_mother_Virgin_mary #እመቤታችን_ቅድስት_ድንግል_ማርያም https://youtu.be/3o4wj7Qqcaw...