ch
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

前往频道在 Telegram

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

显示更多

📈 Telegram 频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት 的分析概览

频道 Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) 阿姆哈拉语 语言赛道中的 是活跃参与者。目前社区聚集了 15 369 名订阅者,在 宗教与灵性 类别中位列第 5 619,并在 埃塞俄比亚 地区排名第 2 193

📊 受众指标与增长动态

невідомо 创建以来,项目保持高速增长,吸引了 15 369 名订阅者。

根据 24 六月, 2026 的最新数据,频道保持稳定运转。过去 30 天订阅人数变化为 -18,过去 24 小时变化为 1,整体触达仍然可观。

  • 认证状态: 未认证
  • 互动率 (ER): 平均受众互动率为 23.10%。内容发布后 24 小时内通常能获得 8.16% 的反应,占订阅者总量。
  • 帖子覆盖: 每篇帖子平均可获得 3 551 次浏览,首日通常累积 1 254 次浏览。
  • 互动与反馈: 受众积极参与,单帖平均反应数为 22

📝 描述与内容策略

作者将该频道定位为表达主观观点的平台:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

凭借高频更新(最新数据采集于 25 六月, 2026),频道始终保持新鲜度与高覆盖。分析显示受众积极互动,使其成为 宗教与灵性 类别中的关键影响点。

15 369
订阅者
+124 小时
+477
-1830
帖子存档
ጥር 30 2015 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣው መመርያ መሠረት ሥርዓተ ጸሎቱ (ምሕላው) በደብራችን ተዠምሯል። #ኢንፈርህ_ሞተ #ሞትን_አንፈራውም

በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣው መመርያ መሠረት ሥርዓተ ጸሎቱ (ምሕላው) በደብራችን ተዠምሯል። #ኢንፈርህ_ሞተ ሞትን አንፈራውም
በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣው መመርያ መሠረት ሥርዓተ ጸሎቱ (ምሕላው) በደብራችን ተዠምሯል። #ኢንፈርህ_ሞተ ሞትን አንፈራውም

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጠ! የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዛሬው ዕለት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የተከሰተው ክስተት አየተባባሰና እየተካረረ መሄዱ በእጅጉ እንዳሳሰበው ተቋሙ በመግለጫው አሳውቋል። የስድስቱ አባል የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች ስለጉዳዩ በመጨነቅ አብዝተው ከመጸለይ ባለፈ ከቤተክርስቲያኒቱ አባቶች ጋር ችግሩ በሰላማዊ ሁኔታ ስለሚፈታበት ሁኔታ መወያየታቸውም ተገልጿል። በተያያዘም በዚህ ሂደት ተቋሙ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አሳውቋል። ቤተክርስቲያኒቱ ለዘመናት የኖረ ሕገ ቤተክርስቲያን፣ ቀኖና እና ሥርዓት ያላት አንጋፋ ተቋም ከመሆኗ አንጻር ያጋጠማትን ውስጣዊ ችግር በቤተክርስቲያኒቱ ሕግና ሥርዓት ሊፈታ እንደሚችል እንጠብቃለን በማለት ገልጿል። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የሰላም ጉዳይ የሁሉም ጉዳይ መሆኑን ጠቅሶ ባለ አምስት ነጥብ መግለጫም አውጥቷል። ከኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አማኞች በተጨማሪ የሌላ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሁሉ ፊቱን ወደ ፈጣሪ በመመለስ ጸሎት ወይም ዱዓ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል። የቤተክርስቲያኒቱ አባቶችም ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ከማክበር ጎን ለጎን የችግሩን ስፋትና ጥልቀት ተገንዝበው ውይይትን፣ ይቅርታንና እርምትን እንዲያስቀድሙ በፈጣሪ ስም በማሳሰብ ይህም ሊደርስ የሚችለውን አደጋ አስቀድማችሁ እንድትከላከሉ ሲል ገልጿል። የፌዴራልና የክልሎች መንግሥታት በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረው ችግር በራሷ በቤተክርስቲያኒቱ ሕግ፣ ቀኖና እና ሥርዓት ብቻ ተመሥርቶ እንዲፈታ ኃላፊነታቻውን በአግባቡ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 11 እና አንቀጽ 27 መሠረት እንዲወጡ ተቋሙ አሳስቧል። ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ አመራሮችና አባላት፤ የማኅበረሰብ አንቂዎች ወቅታዊ የቤተክርስቲያኒቱን ውስጣዊ ችግር ከማባባስ እንዲጠበቁ ተቋሙ አደራ ብሏል። የመገናኛ ብዙኋን ባለሙያዎች፣ ዘጋቢዎችና ተንታኞች የሚያስተላልፏቸው መልእክቶችና ንግግሮች ችግርን የሚያባብሱና ሌላ ግጭትና ሁከት የሚቀሰቅሱ እንዳይሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስቧል።

‹‹#መሐረነ_አብ (#የምሕላ_ጸሎት)፤ #በግእዝና_በአማርኛ፡፡ በግእዝና በአማርኛ፡ ፠ ‹‹ሳታቋርጡ ጸልዩ›› እንዳለ ቅዱስ ጳውሎስ በ፩ኛ ተሰ. ፭፥፲፯ ጌታችንም ‹‹ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ›› ማቴ ፳፬፥፬ ብሎ አርአያ ሆኖ እንዳስተማረን፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ከምንገለገልባቸው ጸሎቶች አንዱና ዋነኛው ‹‹መሐረነ አብ›› ጸሎት ነው፡፡ ፠ መሐረነ አብ የሚወለውን ስያሜውን ያገኘው ጸሎቱ ሲጀምር ‹‹መሐረነ አብ ፥ መሐረነ ወልድ፥ መንፈስ ቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ፡፡›› (አብ ሆይ ማረን፥ ወልድ ሆይ ይቅር በለን፥ ይቅር ባይ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በይቅርታህ አስበን) ብሎ ስለሚጀምር ነው፡፡ ፠ የመሐረነ አብ ጸሎትን ያዘጋጀው ከ40 መጻሕፍት በላይን የደረሰውና ካልዓይ ቅዱስ ያሬድ ፥ ካልዓይ ቄርሎስ የተባለው ቅዱሱ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ ነው፡፡ ሲያዘጋጀውም ከተለያዩ ቅዱሳት መጻሕፍትና እንደ ቅዱስ ያሬድ ካሉ ሊቃውንት ድርሰቶች ኀይለ ቃላት ያላቸውንና ለጸሎት ተስማሚ የሆኑ ቃላትን እንደ ንብ ቀስሞ ነው ያዘጋጀው፡፡ ፠ ቅዱሱ ያዘጋጀውም በመጽሐፈ ሰዐታት ድርሰቱ ላይ በስተመጨረሻ ከኪዳን በፊት እንዲደረስ አድርጎ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከዓመት እስከ ዓመት በየዕለቱ ኪዳን በሚደርስባቸው ማንኛውም የኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክንና ገዳማት ‹‹የመሐረነ አብ ጸሎት››ም ከኪዳን በፊት ይደርሳል፡፡ ፠ የመሐረነ አብ ጸሎት ከኪዳን በፊት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከመጀመሩ በፊት በዋይዜማው የሚደርስ፣ ለግል ጸሎት፣ ረሃብ ጦርነት፥ አባር ቸነፈር፥ ተስሕቦና ወረረሽኝ በሽታ እና የተለያዩ ችግሮች በመጡ ወቅት የሚደረስ ሲሆን ከእግዚኦታ ጋር አብሮ ስለሚባልም ‹‹የምሕላ ጸሎት›› በመባልም ይጠራል፡፡ ፠ ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ በ14ኛው ክፍለ ዘመን ‹‹መሐረነ አብ››ን ከደረሰው በኋላ የተነሡ ቅዱሳንንና አባ ጊዮርጊስ ያላካተታቸውን በየጊዜው የተነሡ ሊቃውንት አካትተውታል፤ (ነገር ግን ሊቃውንቱ አሻሽለው ያዘጋጁት‹‹የመሐረነ አብ›› ጸሎት የሚደርሰው በታላላቅ ገዳማትና አድባራት ነው፡፡ ፠ የጸሎቱ አደራረስም በመሪና በተመሪ (በቀኝና በግራ) በተራ ስለሆነ በጋራ የሚጸለይና ዜማው የሚመስጥ፤ የቃሉ አሰዳደርም የሚያስደንቅ፤ የያዘው ኀይለ ቃል እንባን የሚያስነባ ነው፡፡ በተለይም በገዳም ያሉ አባቶች በጋራ(በማኅበር)ና በግል ጸሎት ዕለት ዕለት ያደርሱታል፡፡ ፠ በቤተክርስቲያናችን በተከሰተው ምክንያት የነነዌን ጾም እስመልክቶ በቅዱስ ሲኖዶስ(ከጥር 29 - የካቲት 1 ) ድረስ ጸሎት እንዲደረግ ባስተላለፈው ጥሪ መሠረት፤ ቤተ ክርስቲያናችንም ዘወትር ጠዋት እና ማታ የመሐረነ አብ ጸሎት ከዛቴ ጀመሮ እያደረሰች ትገኛለች፡፡ ፠እኛም በመደበኛ የሚጸለየውን ‹‹የመሐረነ አብ›› ጸሎት በግእዝና በአማርኛ አዘጋጅተንላችኋል፡፡ እንዲኁም በኦሮሚፋ ይዘንላችኁ ቀርበናል ፡፡ #share .Facebook... https://www.facebook.com/FinoteHiwotSundaySchool .YouTube... https://www.youtube.com/channel/UCWVKGH0mSJl47u44uopEb2w .Telegram... https://t.me/medihanaelem http://tiktok.com/@finotehiwot www.finotehiwotsundayschool.com

በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣው መመርያ መሠረት ሥርዓተ ጸሎቱ (ምሕላው) በደብራችን ተዠምሯል። #ኢንፈርህ_ሞተ ሞትን አንፈራውም